ዝቅተኛ ክፍያ – ኢትዮጵያ

  • በ መጋቢት 2024 ገቢር

የስራ ሰዓት

  • በአዋጅ ቁጥር 515/2007 አንቀፅ 32 መሰረት የመንግስት ሰራተኞች (ሲቪል ስረቫንቶች) መደበኛ የስራ ሰዓት እንደየስራው ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ በሳምንት ክ39 ሰዓት መብለጥ የለበትም፡፡ ይህ ለሁሉም በመንግስት ስራ (በሲቪል ስርቪስ) ውስጥ ላሉ ደምወዝ ተከፋዮች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በአዋጅ ቁጥር 515/2007 አንቀፅ 34 መሰረት ማንኛውም ትርፍ ሰዓት የሰራ የመንግስት ሰራተኛ (ሲቪል ስረቫንት) እንደ ምርጫው የማካካሻ ፍቃድ ወይም የትርፍ ሰዓት ክፍያ የማግኝት መብት አለው፡፡

ትርጓሜዎች:

የደረጃ እርከን፡ የደረጃ እርከን ረድፍ እያንዳንዱ የአገልግሎት አይነት የሚጀምርበትን የደረጃ እርከን ያሳያል፡፡ የአገልግሎት አይነት፡ የአገልግሎት አይነት ጥበቃን፣ የቀን (የጉልበት) ሰራተኞችን፣ ፅዳት ሰራተኞችን፣ ፀሀፊዎችን፣ መካከለኛ ባለሙያዎችን፣ የአስተዳድር ሰራተኞችን እና ባለሙያዎች የሚያካትት ሆኖ በትምህርት ደረጃ ይከፋፈላል፡፡ ለምሳሌ፡- ጥበቃ እና የቀን (የጉልበት) ሰራተኞች ማንበብና መፃፍ አለባቸው (ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል) ፡፡ የፅዳት ሰራተኞች 5ኛ ክፍልና ክዛ በላይ መሆን አለባቸው፡፡ ፀሀፊዎች 10+2 ወይም 10+3 መሆን እና በሰክረተሪያት ሳይንስ እና በሌሎችም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ መካከለኛ ደረጃ ባለሙያዎች ዲፕሎማና ከዛ በላይ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የአስተዳድር ሰራተኞች በስራ አመራር፣ በአስተዳድር፣ በሰው ሀይል እና በሌሎችም መስኮች በመጀመሪያ ድግሪ (BA) የተመረቁ መሆን አለባቸው፡፡ ባለሙያዎች የመጀመሪያ ድግሪ (BA) እና ከዛ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸውን መሆን አለባቸው፡፡ በአገልግሎት ዓመት ላይ ተመስርቶ በ 1፣2፣3፣4፣5 የተሰየሙ የተለያዩ ደረጃዎች ይወጣሉ/ይወሰናሉ፡፡ ስለሆነም ዜሮ የስራ ልምድ ያለው የስራ መደቡ ጥበቃ እና የቀን (የጉልበት) ሰራተኛ የሆነ አንድ ተቀጣሪ ደረጃው ጥበቃ እና የቀን (የጉልበት) ሰራተኛ ደረጃ 1 ይሆናል ማለት ነው ፡፡ የሰራተኛው የአገልግሎት አመት ሲጨምር ደረጃውም ይጨምራል፡፡

ተጨማሪ መረጃ በ ይገኛል

loading...
Loading...