መካካሻ

የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ

የመደበኛ የስራ ሰዓት በቀን 8 ሰዓት እና በሳምንት 48 ሰዓት ነው፡፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ‹‹መደበኛ የስራ ሰዓት›› ማለት ሰራተኛው በትክክል ስራውን የሚሰራበት ወይም እራሱን ለስራ ዝግጁ አድርጎ በህጉ፣ በህብረት ስምምነት ወይም በስራ ደንቦች መሰረት በስራ ቦታ የሚገኝበት ሰዓት ማለት እንደሆነ ይገልጻል፡፡ በሚኒስቴሩ መመሪያ መሰረት ለኢኮኖሚ ዘርፎች፣ ለኢንዱስትሪዎች ወይም ልዩ የስራ ሁኔታዎች ባሉባቸው ስራዎች የሰራተኛው ደመወዝ ሳይቀነስ በሰራተኛው የስራ ሰዓት ሊቀነስ ይችላል፡፡ የስራ ሰዓቶች ለሳምንቱ የስራ ቀናት እኩል ይደለደላሉ፡፡ ነገር ግን የስራው ባህሪይ ቢያስገድድ በማናቸውም የሣምንቱ የስራ ቀኖች ሰአቶችን ማሣጠርና ልዩነቱን ለተቀሩት ቀኖች ማደላደል ይቻላል፡፡ የስራ ሰዓታት በቀን እስከ 10 ሰዓታት ማራዘም ይቻላል::

ከመደበኛ የሥራ ሰዓት በላይ የሚሠራ ሥራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ነው፡፡ በአደጋ ጊዜ (አደጋ ሲደርስ ወይም የሚደርስ መሆኑ ሲያሰጋ) ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም፤ በአስቸኳይ መሰራት ያለበት ሥራ ሲያጋጥም እና በማያቋርጥና ተከታታይ ሥራ ላይ ከሥራ የቀሩ ሠራተኞችን ለመተካት ካልሆነ በስተቀር አንድ ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ አይገደድም፡፡ የትርፍ ሰዓት ሥራ በቀን ከ4 ሰዓት ወይም በሣምንት ከ12 ሰዓት ላይበልጥ ይችላል፡፡ አንድ ሰራተኛ በስራ ቀናት እነዲሰራ ከተወሰነው መደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ቢሰራ ማለትም በቀን 8 ሰዓት እና በሣምንት 48 ሰዓት ቢሰራ ከመደበኛ ደመወዙ በተጨማሪ ቀጥሎ በተመለከተው አኳኋን ይከፈለዋል፡፡

-      ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በ150 % ተባዝቶ ይከፈላል

-      ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በ175 % ተባዝቶ ይከፈላል

-      ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍያ ተመን 2ዐዐ% በሳምንቱ የዕረፍት ቀን ስራ እና 

-      ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍያ ተመን 25ዐ% በህዝባዊ በዓላት ቀን  ስራ

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 61-68

የምሽት ስራ ክፍያ

በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ  መሠረት የምሽት ስራ ከምሽት 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት የሚሠራ ሥራ ማለት ነው፡፡ በሥራ ህጉ ላይ አሰሪዎቹ ለምሽት ሠራተኞች ክፍያ እንዲፈፅሙ የሚያደርግ አንቀፅ የለም፡፡ ከፍተኛ ክፍያዎች የሚፈፀሙት የቀን ሠራተኞች ሆነው በምሽት ትርፍ ስራ ለሚሰሩ ማካካሻ ክፍያዎችን ለመክፈል የሚያስገድድ የተለየ ድንጋጌ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ውስጥ የለም፡፡ የምሽት ሰዓታት ትርፍ ሰዓታት ከሆኑ ለሠራተኛው የመደበኛውን ክፍያ 175% ማግኜት አለበት፡፡

 

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 68

በምትክ የሚሰጥ ዕረፍት

ሰራተኞች በአደጋ(አደጋ ሲኖር ወይም ይደርሳል ተብሎ ሲገመት) ምክንያት የተከሰተ ከባድ ችግር ለማስወገድ ወይም ከአቅም በላይ በሆነ አደጋ ወይም አስቸኳይ ስራ ሲኖር በሳምንት የእረፍት ቀን ወይም በህዝባዊ በዓል ቀን ስራ እንዲሰሩ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡

አንድ ሰራተኛ ማካካሻ የሚያገኝበት የበዓል ቀን ከመድረሱ በፊት የስራ ውሉ/ሏ ቢቋረጥ ማካካሻ የሚያገኝ/ታገኝ ይሆናል፡፡ በህዝባዊ በዓላት ቀናት ለሚሰሩ ሰራተኞች የሚሰጥ የምትክ ዕረፍት ጊዜን የተመለከተ ድንጋጌ የለም፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 75

የሳምንት መጨረሻ / የህዝባዊ በዓላት ስራ ክፍያ

ሰራተኞች በሳምንት የእረፍት ቀናት ወይም ህዝባዊ በዓል ቀናት እንዲሰሩ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ሲኖር ሰራተኞቹ በህጋዊ ህዝባዊ በዓል ቀናት እንዲሰሩ ከተፈለገ  መደበኛ የሰዓት ክፍያ ተመን 200% በማካካሻ ክፍያ የመቀበል መብት ይኖራቸዋል፡፡

 

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 75

መካካሻ የተመለከቱ ደንቦች

  • የአሰሪና ሰራተኛ ዓዋጅ ቁ. 377/2003 / Labour Proclamation No.377/2003
loading...
Loading...