ወሊድ እና ሥራ

This page was last updated on: 2025-06-22

የወሊድ ፈቃድ

በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት እና በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት ሴት ሰራተኞች በህክምና ዶክተር ምክር የ120 ቀናት (ከመውለዷ በፊት 30 ቀናት እንዲሁም ከወሊድ በኋላ 90 ቀናት) የወሊድ ፈቃድ ከሙሉ ክፍያ ጋር የማግኘት መብት አላቸው:: እርጉዝ በ30ቀናት የቅድመ ወሊድ ፍቃዷ ጊዜ ውስጥ ያልወለደች እንደሆነ እስክትወልድ ድረስ ተጨማሪ ፍቃድ የማግኘት መብት አላት፡፡ እርጉዝ ሴት 30 ቀን ፍቃዷ ከመጠናቀቁ በፊት ከወለደች የድህረ ወሊድ ፍቃዷ ከወለደች በኋላ ይጀምራል፡፡ ከወሊድ ፈቃድ በተጨማሪ ሠራተኞች ከእርግዝና ጋር ለተያያዙ የሕክምና ምርመራዎች ከክፍያ ጋር ፈቃድ የማግኘት፣ በሕክምና ዶክተር ሲታዘዝም የእርግዝና እረፍት ከክፍያ ጋር የማግኘት መብት አላቸው፡፡ በ2011ዓ.ም በተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ የወሊድ ፈቃድ ከ90 የስራ ቀናት ወደ 120 የስራ ቀናት ከፍ ብሏል፡፡

ምንጭ፡-በ1987 የፀደቀው የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀፅ 35(5)፤ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 88

ገቢ

የወሊድ ፈቃድ ሙሉ ደምወዝ የሚከፈልበት ፍቃድ ነው፡፡ የተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ በቅድመ-ወሊድ (30 ቀናት) እንዲሁም በድህረ-ወሊድ (90 ቀናት) ወቅት ሙሉ ደምወዟ እንዲከፈላት ያዛል፡፡ አጠቃላይ የወሊድ ፈቃድ ከ90 የስራ ቀናት ወደ 120 የስራ ቀናት ከፍ ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ህገ-መንግሰት ሴት ሰራተኞች የወሊድ ፈቃድ ከሙሉ ደምወዝ ጋር የማግኘት መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡

ምንጭ፡ በ 1994 በወጣው የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀጽ 35(5)፣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 88; ምንጭ ISSA የሀገር ፕሮፋይል

ነፃ የህክምና አገልግሎት

በወሊድ ህክምናን በተመለከተ ምንም አይነት ድንጋጌ የለም፡፡ እኤአ በ2010 አዲስ የማህበራዊ ጤና ደንብ አዋጅ ወጥቷል፡፡ ይህም ሁሉም ሠራተኞች የማህበራዊ ጤና መድን ዕቅድ አባላት እንዲሆኑ ይጠይቃል፡፡ ቢሆንም ይህ ህግ ወሊድን የተመለከቱ የጤንነት ጥቅሞችን በቀጥታ አይመለከትም፡፡ 2022 የወጣው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አዋጅ ቁጥር 1273 ለአለም አቀፍ የጤና ሽፋን ይሰጣል።

ወሊድ እና ሥራን የተመለከቱ ድንጋጌዎች

  • የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት 1994 / Constitution of Ethiopia 1994
  • የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 1156/2011 / Labour Proclamation No. 1156/2019
loading...
Loading...