የግዳጅ ስራ
የግዳጅ ስራ በህገ መንግስቱ የተከለከለ ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላውን በማስፈራራት፣ በጉልበት፣ በማጭበርበር ወይም ሌላ ሕገ-ወጥ መንገድ በመጠቀም አንድን ሥራ ወይም የተለዩ የቅጥር ሁኔታዎችን እንዲቀበል ቢያደርግ፣ ወይም አሠሪው የቅጥር ሁኔታን እንዲቀበል ወይም እንዲቀይር ለማስገደድ አለመስራት ወይም መለገም (refuse labor or withhold labor) ቅሬታ በሚቀርብበት ወቅት ቢያንስ በሶስት ወራት ቀላል እስር ወይም ለገንዘብ ቅጣት ይዳርጋል፡፡
ፀረ ህገ-ወጥ የሰው ማዘዋወር ህግ ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ለቤት ውስጥ ሥራ ቅጥር ወይም በውጭ ሀገር ለማስቀጠር በሚል ስበብ ማዘዋወርን ይከላከላል፡፡ ለብዝበዛ የሰጠው ትርጉም የጉልበት ብዝበዛን፣ የግዳጅ ሥራን ወይም ያለውዴታ አገልጋይነትን ያካትታል፡፡ ይህ የወንጀል ድርጊት ከ7 እስከ 15 ዓመት ጽኑ እሥራትና ከብር 20,000 እስከ 100,000 ቅጣት ያስቀጣል፡፡
ምንጭ፡- በ1994 የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 42(2 እና 3) ፤ የወንጀለኛ መቅጫ አዋጅ ቁጥር 414/2004 አንቀፅ 603 ፤ ህገወጥ የሰው ማዘዋወር መከላከልና ማቆም በማጭበርበር/በማዘዋወር አዋጅ ቁጥር 909/2015 አንቀጽ 2 እና 3።
ስራን የመቀየር ነፃነት እና ስራን የመተው መብት
ሰራተኞች ለአሰሪያቸው ማስታወቂያ ከሰጡ በኋላ ስራቸውን የመቀየር መብት አላቸው:: ይህንን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎን የቅጥር ዋስትና የሚለውን ክፍል ይመልከቱ፡፡
ምንጭ፡- የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 26-35
ኢ-ሰብአዊ የስራ ሁኔታ
የስራ ሰዓት ከመደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን ከ8 ሰዓት ወይም በሣምንት ከ48 ሰዓት በላይ ሊሄድ ይችላል፡፡ ሆኖም የትርፍ ሰዓት ሥራ በቀን ከ4 ሰዓት ወይም በሳምንት ከ12 ሰዓት ሊበልጥ አይችልም፡፡ ከፍተኛው የስራ ሰዓት ትርፍ ሰዓትን ጨምሮ (48 ሰዓት + 12 ሰዓት) በሣምንት 60 ሰዓት ነው፡፡ ማንኛውም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ አይገደድም አደጋ ሲደርስ ወይም የሚደርስ መሆኑ ሲያሰጋ፤ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም፣ በአስቸኳይ መሰራት ያለበት ሥራ ሲያጋጥም ወይም በማያቋርጥና ተከታታይ ሥራ ላይ ከሥራ የቀሩ ሠራተኞችን ለመተካት ካልሆነ በቀር፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በዚህ ጽሁፍ ካሳ በሚለው እርስ ስር ያለውን ክፍል ይመልከቱ።
ምንጭ፡-የተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀፅ 61-67