የቤተሰብ ሀላፊነቶች

የአባትነት ፈቃድ

የ2003ቱ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ የትዳር ጓደኛ ስትወልድ ሰለሚሰጥ ፍቃድ የሚደነግግ አንቀፅ አልነበረውም፡፡

በ2011ዓ.ም በተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ አንድ ወንድ ሠራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 3 ተከታታይ ቀናት ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጠዋል፡፡

ምንጭ፡- የተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 81

እና ስራ የወላጅነት ፈቃድ

የወሊድ ፈቃድ ከወጡ በኋላ ለአዲሶቹ ወላጆች የወላጅ ፈቃድን በሚደግፍ ሕግ ውስጥ የሉም ፡፡

ህፃናት ልጆችና ሌሎች የቤተሰብ ሀላፊነት ላሉባቸውሠራተኞች የሚበጁ አማራጭ

በህጉ ውስጥ የወላጆች እና የቤተሰብ ሀላፊነት ያለባቸው ሰራተኞች የስራና ህይወት ሚዛን ይጠብቁ ዘንድ አጋዥ የሆኑ ድንጋጌዎች የሉም፡፡

loading...
Loading...