የስራ ዋስትና

በፅሁፍ የተቀመጡ የቅጥር ጉዳዮች

የግለሰብ የቅጥር ስምምነት በቃል ወይም በፅሁፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ከተወሰነ ጊዜ ወይም ስራ የተደረገ ውል ካልሆነ በስተቀር የስራ ቅጥር ውል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡ የስራ ቅጥር ውል በገጽ መቀመጥ ያለበት ሲሆን በህገወጥ ስራ ወይም ሞራልን የሚነኩ ተግባራትን ለመፈጸም ሊደረግ አይገባም፡፡  ውሉም በህጉ፣ በህብረት ስምምነቱ እና በስራ ደንብ ውስጥ ከተቀመጡት በተሻለ ለሰራተኛው አመቺ የሆኑ ድንጋጌዎችን ማካተት ይኖርበታል፡፡ በጽሑፍ የተደረገ የስራ ቅጥር ውል (የስራ ውል ከሌለ ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚገልጽ መግለጫ) የሚከተሉትን መግለጽ ይጠበቅበታል፡ የቀጣሪው ስምና አድራሻ፣ የሠራተኛው ስም፣ አድራሻ እና የሥራ ካርድ ቁጥር፣ የቅጥሩ ዓይነት፣ የሥራ ቦታ፣ የደሞዝ መጠንና ስሌት፣ የክፍያው ጊዜ እና የኮንትራት ጊዜ፡፡ በሁለቱ ወገኖች መፈረም ይኖርበታል፡፡ አሰሪው የነዚህን ድንጋጌዎች መስፈርቶች የሚያሟላ ከሆነ ሰራተኛው በዚህ አዋጅ መሰረት የተሰጡትን መብቶችን ሊገፈፍ አይገባም፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 4-8

የተወሰነ ጊዜ ውል

የኢትዮጵያ አሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የቋሚነት ባህርይ ላላቸው ስራዎች የውስን ጊዜ ሰራተኞች መቅጠርን ይከለክላል፡፡ለተወሰነ ወይም ለተቆረጠ ጊዜ የሚሰራ የቅጥር ውል በሚከተሉት ሁኔታዎች ወቅት ሊፈፀም ይችላል፡፡ ተቀጣሪው ይሰራው ዘንድ ለተቀጠረበት የተወሰነ ስራ ፣ በእረፍት ወይም በሕመም ወይም በሌላ ምክንያት ለጊዜው በስራው ላይ ያልተገኘን ሰው ለመተካት፣ ከተለመደው የተለየ የስራ ጫና በሚኖርበት ወቅት፣ በሕይወት ወይም በንብረት ላይ አደጋ ወይም ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል የሚሰራ አስቸኳይ ስራ ሲኖር፣ በስራ ቦታ የሚገኙ የካምፓኒው ስራዎች፣ ማቴሪያሎች፣ ህንፃዎችንና ማሽኖችን እንከኖችንና ብልሽቶችን ለመጠገን፣ የዋናው ስራ አካል የሆነ ነገር ግን መደበኛ ባልሆነ ጊዜያት የሚሰራ መደበኛ ያልሆነ ስራ፣የቀጣሪው ዋና ስራ አካል የሆነና በዓመት ለተወሰነ ጊዜ የሚሰራ ነገር ግን በየተወሰነ ዓመት የሚደጋገሚ ወቅታዊ ስራ፣ የቀጣሪው ዋና ተግባር ወይም ስራ አካል ያልሆነ ነገር ግን አልፎ አልፎ የሚሰራ ስራ፣ የረዥም ጊዜ የስራ ውል እያለው በድንገትና ጠቅላላውን ከስራ የለቀቀን ሰራተኛ በጊዜያዊነት ለመተካት፣በአደረጃጀት መዋቅር ጥናትና በትግበራ መካከል ባለው ጊዜ በክፍት ቦታ በጊዜያዊነት ሰው ለመመደብ፡፡ የሰራተኛ አዋጁ ውሉ ከ45 ተከታታይ ቀናት መብለጥ የለበትም እንደዚሁም መከናወን ያለበት አንድ ጊዜ ነው ብሎ ለመጨረሻዎቹ ሁለት አይነቶች ካስቀመጠው በስተቀር የውስን ጊዜ ውል የጊዜ መጠንን (እድሳቶችን ጨምሮ) አይወስንም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ/ሥራ የተደረገ የሥራ ውል ከፍተኛው የቆይታ ጊዜ 5 ዓመት መሆኑ በፍትሐ ብሔር ህጉ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ከ5 ዓመት በኋላ ሥራውን ከቀጠለ ወይም ውሉ ከታደሰ ነባሩ ውል ላልተወሰነ ጊዜ/ሥራ ውል እንደተደረገ ይሆናል፡፡

 

አዲሱ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ አንድ ሰራተኛ በራሱ ቤት ሆኖ አሠሪው በቀጥታ ሳይቆጣጠረው ወይም ሳይመራው ለተሰራው ሥራ ደመወዝ የሚከፈልበትን በቤት የሚሰራን ስራ አካቷል፡፡ በራሱ ቤት በሚሠራ ሠራተኛና በአንድ አሠሪ መካከል የሚደረግ ውል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ እንደተደረገ የሥራ ውል ይቆጠራል፡፡

ምንጭ፡- የተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 9-10 እና 46፤የ1952 የፍታብሄር ህግ አዋጅ ቁጥር 165 አንቀፅ 2568 

የሙከራ ጊዜ

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሠረት የሙከራ ጊዜ አንድ ሰው በስራ ውሉ መሠረት ሊመደብበት ለታቀደው ቦታ ተስማሚ መሆኑን ለመመዘን የሚደረግ ነው፡፡ የሙከራ ጊዜው ስምምነት በፅሁፍ መደረግ ሲኖርበት ከ60 ተከታታይ ቀናት ሊበልጥ አይችልም፡፡ - በተመሳሳይ ቀጣሪ ለተመሳሳይ ሥራ የተቀጠረ ሠራተኛ ከአመክሮ ነፃ ነው፡፡ የአመክሮ ተቀጣሪዎች ከሌሎች ተቀጣሪዎች ጋር ተመሳሳይ መብቶች እና ግዴታዎች አሏቸው፡፡ አንድ ሠራተኛ በአመክሮው ወቅት ለሥራው ተስማሚ ሳይሆን ከቀረ አሠሪው ያለምንም ማስጠንቀቂያና ምንም ዓይነት የጥቅማ ጥቅም ወይም የካሣ ክፍያ ኮንትራቱን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ ሠራተኛውም ያለምንም ማስጠንቀቂያ ኮንትራቱን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 11

የስራ ሁኔታዎችን የተመለከቱ ደንቦች

  • የአሰሪና ሰራተኛ ዓዋጅ ቁ. 377/2003 / Labour Proclamation No.377/2003
loading...
Loading...