This page was last updated on:
2025-06-22
የጡረታ መብቶች
ህጉ ሙሉ እና ከፊል ጡረታን ይደነግጋል፡፡ ለሙሉ ጡረታ ሰራተኛው 60 ዓመት የሞላው /ለሴቶችም ተመሳሳይ ነው/ እና የ120 ወራት / 10 ዓመታት/ አልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡ አስቀድሞ ጡረታ መውጣትም የሚቻል ሲሆን ለዚህም ሰራተኛው 55 ዓመት የሞላውና ቢያንስ የ300 ወራት /25 አገልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡
የዕርጅና ጡረታ መጠን ሰራተኛው ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ያገኘው የነበረው አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ 30% ሆኖ በዚህ ላይም ዋስትና ያለው ሰራተኛ ከ10 ዓመት በላይ ለፈፀመው ለእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ 1.25% በመደመር ይታሰባል፡፡ ሲሆን ከፍተኛው ወርሃዊ የጡረታ አበል መጠን መድን የገባ ሰራተኛ ወርሃዊ መነሻ ደመወዝ 70% ነው፡፡ የመጀመሪያ ጡረታ አበል እንደ እርጅና ጡረታ አበል በተመሳሳይ ሊሰለፍ አንድ ሰራተኛ በ60 አመት እድሜው ለእርጅና ጡረታ ብቁ የሚያደርጉትን ሁኔታዎች የማያሟላ ከሆነ የሰራተኛው መነሻ ወርሃዊ ደመወዝ ጡረታ ከመውጣቱ አንድ ወር በፊት የነበረው ደመወዙ በአገልግሎት ዘመኑ እና መዋጮው ይከፈለዋል፡፡
ምንጭ፡- የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2022 አንቀጽ 18-21; ISSA የሀገር ፕሮፋይል
የጥገኞች ተተኪዎች ጥቅም
ከላይ የተጠቀሱት ህጐች በህይወት ላሉ ጥገኞች ባል/ሚስት ህፃናት እና ወላጆች በህይወት ያለ የትዳር ጓደኛ ወይም 18 አመት በታች የሆኑ ህጻናት (አካል ጉዳተኛ ከሆነ 21 አመት) እና ወላጆች (በህይወት ያለ የትዳር ጓደኛ ከሌለ) ጥቅሞችን እንደሚያገኙ ይደነግጋሉ፡፡
ይህም የሟቹ ጡረታ 50% ለባል/ሚስት ይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 20% ለእያንዳንዱ ወላጅ የሞተበት ህፃን ይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 30% ለእያንዳንዱ ሁለቱም ወላጅ ለሞተበት ህፃን ይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 15% ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወላጅ ይከፈላል፤ ሌሎች አግባብነት ያላቸው በህይወት ያሉ ተትኪዎች ከሌሉ ጥቅሙ የሟቹ ጡረታ 20% ይሆናል፡፡ ሚስት/ባል ሌላ ትዳር በሚመሰርቱበት ጊዜ ሴት ከሆነች ዕድሜዋ ክ45 አመት በታች ፤ ወንድ ከሆነ ደግሞ 50 ዓመት በታች ከሆነ ክፍያው ይቋረጣል። ጠገኛው የአካል ጉዳተኛ ከሆነ ማግባቷ/ማግባቱ ክፍያውን አያስቆመውም። ሆኖም ለሁሉም ተተኪዎች የሚከፈላቸው ክፍያ ከሟች አጠቃላይ ወርሃዊ የጡረታ ክፍያ ሊበልጥ አይችልም።
ሟች ከ10ዓመት በታች የሆነ አገልግሎት እና መዋጮ ካለው እና ለጡረታ ብቁ ካልሆነ በህይወት ላለ የትዳር ጓደኛ የሚከፈል ክፍያ ብቃት ላላቸው በህይወት ያሉ የትዳር ጓደኞች ለሌላው በህይወት ያለ የትዳር ጓደኛ ጥቅም በተመሳሳይ ምጣኔ ይሰላል፡፡
ምንጭ፡- የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2022 አንቀጽ 39-44; ISSA የሀገር ፕሮፋይል
የመስራት አለመቻል / ጥቅሞች
ከላይ የተጠቀሱት ህጐች በዘለቄታነት መስራት የማያስችሉ ከስራ ጋር ግንኙነት የሌላቸው አደጋዎች /ጉዳዮች/ በሽታዎችን የተመለከቱ ድንጋጌዎች አሏቸው፡፡ ሰራተኛው መደበኛ ጥቅም የሚያስገኝ ስራ መስራት የማያስችል የተገመገመ ችግር ያጋጠመውና የ10 ዓመት አገልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡ መስራት ያለመቻል ጥቅሞችም የሚሰራው ከእርጅና ጡረታ ጋር በተመሣሣይ ነው፡፡ መስራት ያለመቻል ጡረታ ሰራተኛው ከጉዳቱ በፊት ባሉት ሶስት አመታት የነበረው ወርሃዊ ገቢ 30% በዚህ ላይም ዋስትና ያለው ሰራተኛ ከ10 ዓመታት በላይ ላበረከተው አገልግሎት የአማካይ ወርሃዊ ገቢ 1.25% (ወታደር ላልሆነ) እና 1.65%(ወታደር) በመደመር ይሆናል፡፡ መድን የገባ ሰራተኛ ከፍተኛ ወርሃዊ የጡረታ አበል የወረሃዊ መነሻ ደመወዙ አማካይ 70% ነው፡፡
የአካል ጉዳተኝነት ከመቆሙ በፊት በነበረው ወር ውስጥ 1.25 (ሲቪል) ወይም 1.65 (ወታደራዊና ፖሊስ) በሚባሉት ወርሃዊ ደመወዝ በአንድ ጊዜ አጠቃላይ የሆነ የደመወዝ ክፍያ መጠን ከ 10 አመታት ድጐማ ይከፈላል።
ምንጭ፡- የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2022 አንቀጽ 22-26; ISSA የሀገር ፕሮፋይል
ማህበራዊ የተመለከቱ ደንቦች
-
የማህበራዊ ጤና ዋስትና አዋጅ ቁጥ 690/2010 / Social Health Insurance Proclamation No.690/2010
-
የግል ድርጅቶች የሰራትኞች ማህበራዊ ዋስትና አዋጅ ቁጥር 1268/2022 / Private Organization Employees Pension Proclamation No. 1268/2022