የሰራተኛማህበራት መብት

የማህበር አባል የመሆን ነፃነት

የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት እና የአሠሪና ሠሪተኛ ጉዳይ አዋጅ ሠራተኞችና አሠሪዎች በማህበር የመደራጀት እንዲሁም ማህበሮቻቸውን የማቋቋም መብት እንዳላቸው ተደንግጓል፡፡ ይህ መብት አሠሪዎችም የአሠሪ ማህበር፣ ሠራተኞች የሠራተኛ ማህበር ለማቋቋምና ለመደራጀት መብት እንዳላቸው ተደንግጓል፡፡

የሰራተኛ ማህበር የሰራተኞችን መብት እና ጥቅም የሚያስከብር የሰራተኞች ድርጅቱን በህብረት ስምምነት እና በስራ ግጭት ላይ ሰራተኞችን ይወክላል፡፡ የሰራተኛ ማህበሩ ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች፣ ትእዛዞች በአባላቱ መታወቃቸውን፣ መከበራቸውን እና መፈጸማቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ የሰራተኛ ማህበር አባላት ህጎች እና መመሪያዎች በሚወጡበት እና በሚሻሻሉበት ጊዜ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የሰራተኛ ማህበራት የራሳቸውን የሚከተሉትን የሚያካትት ህገ-ደንብ ሊያወጡ ይችላሉ፡- የድርጅቱ ስም፣ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፣ የድርጅቱ አላማ፣ ድርጅቱ የተቋቋመበት ቀን፣ የድርጅቱ አርማ፣ የአመራር ብቃት፣ የአባላት መዋጮ፣ የድርጅቱ የፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር፣ የስብሰባ እና የምርጫ ስነ-ስርዓት፣ የዲሲፕሊን እርምጃዎች፣ ድርጅቱን ለማፍረስ የሚያስችሉ ሁኔታዎች፣ ድርጅቱ ከፈረሰ የንብረት ሁኔታ፡፡ የሰራተኛ ማህበራት ህጎቻቸውን፣ የአመራሩን ስም፣ አድራሻ እና ፊርማ አጠቃላይ ማህበር ከሆነ ደግሞ አባላቱ የሚሰሩበት ድርጅት ስሞች እና የድርጅቱ ስምና አርማ የያዘ ሰነድ በማቅረብ በሚኒስቴሩ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰራተኛ ማህበር የሚያቀርቡትን የምዝገባ ማመልከቻ ከተቀበለ በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ መልስ ካልሰጠ የሰራተኛ ማህበሩ እንደተመዘገበ ይቆጠራል፡፡

ማንም ሰው በዛቻ፣ በኃይል ድርጊት፣ በማታለል ወይም በሌላ በህገ-ወጥ መንገድ ሊላውን ሰው በማስገደድ የማህበር አባል እንዲሆን ወይም እንዳይሆን ያደረገ ከሆነ በእሥር ወይም በመቀጮ ይቀጣል፡፡ ሠራተኛው ከደመወዙ የተወሰነ መቶኛ እየተቀነሰ ለሠራተኛ ማኅበር መዋጮ ገቢ እንዲደረግለት በጽሁፍ ሲያመለክት አሰሪው ይህንኑ መጠን በየወቅቱ ተቀናሽ በማድረግ ወደ ሠራተኛ ማኅበሩ የባንክ ሂሳብ በየወቅቱ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

የሠራተኞች ማኅበር መሪዎች የሥራ ክርክር ለማቅረብ፣ የኅብረት ስምምነት ለመደራደር፣ በማኅበር ስብሰባ ለመገኘት፣ በሴሚናሮችና በሥልጠና ለመካፈል እንዲችሉ ከክፍያ ጋር ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ ፈቃዱም የሚሰጥበት ሁኔታ በኅብረት ስምምነት ሊወሰን ይችላል፡፡

ምንጭ፡  በ1995 የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 603 እና 42(1ሀ) እና የወንጀለኛ መቅጫ አዋጅ ቁጥር 414(2004፡- የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 12(4), 82 እና 113

በህብረት የመደራደር ነፃነት

የስራ ህጉ በህብረት መደራደርን ዕውቅና ሰጥቶታል፡፡

የህብረት ስምምነት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የሰራተኛ ማህበር ተወካዮች እና አንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ አሰሪዎች ወይም ወኪሎች ወይም የአሰሪ ድርጅቶች ተወካዮች መካከል በጽሑፍ የሚደረግ ስምምነት ነው፡፡ የህብረት ድርድር በአሰሪዎች እና በሰራተኛ ማህበራት ወይም በተወካዮቻቸው መካከል ስለ ስራ ሁኔታ ወይም የህብረት ድርድር ወይም ስለ ህብረት ስምምነት እድሳት እና ማሻሻያ ለመደራደር የሚደረግ ስምምነት ነው፡፡ በህብረት የመደራደር ስምምነት በህጉ ከተሰጡት የተሻለ ለሰራተኛው ጥቅም የሚሰጥ ነው፡፡ የህብረት ድርድር ስምምነት በህጉ ከተሰጠው ባነሰ ለሰራተኛው ጥቅም የሚሰጡ ድንጋጌዎች ካሉበት ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

በስምምነቱ ውስጥ በተለየ ካልተገለጸ በስተቀር የህብረት ድርድር ስምምነት በህጉ ተፈጻሚ የሚሆነው ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ እስከ 3 አመት ይሆናል፡፡ በዚያ ውስጥ በታቀፉት ወገኖች ሁሉ ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡ የህብረት ድርድር ስምምነት የህብረት ስምምነት አካል የሆነው የሰራተኞች ማህበር ቢፈርስ እንኳን በአሰሪና ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

የተካተቱ ወገኖች እንዲመዘገብላቸው የህብረት ስምምነት በቂ ኮፒዎችን ለሚኒስቴሩ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡ የተፈረመበት እና የተመዘገበ ስምምነት በሌሎች ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ለማናቸውም የአሠሪ ወይም የሠራተኛ ማኅበር ከቅን ልቦና ተቃራኒ በሆነ ማንኛውም መንገድ የኅብረት ድርድር ጊዜ እንዲራዘም ማድረግ ህገወጥ ድርጊት ነው፡፡

ምንጭ፡-የተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 125-135

ስራ የማቆም መብት

ስራ የማቆም መብት በህገ መንግስቱ ተደንግጓል በስራ ህጉም የህግ አግባብ ተበጅቶለታል ቢሆንም ግን በስራ የማቆም መብት ላይ የሚደረጉ ምክንያታዊ ያልሆኑ እገዳዎች /ረጅም የአስፈላጊ አገልግሎቶች ዝርዝር፣ ባልተፈቀዱ የስራ ማቆም እርምጃዎች ላይ በተሳተፉ ሰዎች ላይ የሚጣሉ ተመጣጣኝ ያልሆኑ የወንጀልና የፍትሀብሔር እገዳዎች እና የተንዛዙ ሂደቶች/ ይህንን መብት ያኮላሹታል፡፡

ሰላማዊ የስራ ማቆም አድማ ሁሉም የግጭት አፈታት ጥረቶች ሳይሳኩ ከቀሩ መብታቸውን ለማስጠበቅ ብቻ ይፈቀዳል፡፡ ከዚያ በፊት የሚደረግ የረጅም ጊዜ ድርድር እና የእርቅ እና ድርድር ሂደቶች በአጠቃላይ የስራ ማቆም መብትን ይገድባሉ፡፡ ህጋዊ የሆነ የስራ ማቆም አድማ ከመፈቀዱ በፊት አስገዳጅ የ30 ቀናት የድርድር ጊዜ ይሰጣል፡፡

ቢያንስ 2/3ኛ የሚሆኑ የሰራተኛ ማህበር አባላት በተገኙበት አብላጫ ድምጽ ስራ ማቆምን መደገፍ ይኖርባቸዋል፡፡ የስራ ማቆም አድማ የሚያደርጉ ሰራተኞች በክልሉ ለሚገኝ የሚኒስቴሩ ተወካይ ወይም የሚመለከተውን የመንግስት መስሪያ ቤት ቢያንስ የስራ ማቆሙ ሊደረግ ከታሰበበት ቀን 10 ቀን አስቀድሞ ማሳወቅ እና ይህንን እርምጃ የሚወስዱበትን ምክንያት መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ የስራ ማቆም አድማ ሰላማዊ ካልሆነ እና ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ጋር የሚጣረስ ከሆነ ህገ-ወጥ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በዚህም ሁከት፣ ማስፈራራት ፣ ኃይል መጠቀም ወይም በማንኛውም መልኩ በግልጽ እና በህጉ መሰረት ህገ-ወጥ የሆነ ተግባር የተከለከለ ነው፡፡ አሰሪዎች እና ሰራተኞች በድርጅቱ ውስጥ የደህንነት መመሪያዎች እና የአደጋ መከላከያ ደንቦች መከተል አለባቸው፡፡ አሠሪዎች በህጋዊ የሥራ ማቆም አድማ የተሣተፉ ሠራተኞችን ከሥራ ማባረር አይችሉም፡፡ በህጉ የተከለከለ ነው፡፡ ሠራተኞች በህጋዊ የሥራ ማቆም አድማ በመሣተፋቸው የተነሣ የሥራ ውላቸውን አሠሪዎች ለማቋረጥ ህጋዊ ምክንያት ሊሆናቸው አይችልም፡፡ ፡፡

ምንጭ፡  በ1994 የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 42(1ለ) እና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 157-160; ምንጭ አንቀጽ 2581 የፍትሐ ብሔር ህግ አዋጅ ቁጥር 165/1960 ዓ.ም.

የሰራተኛ ማህበራትን የተመለከቱ ደንቦች

  • የአሰሪና ሰራተኛ ዓዋጅ ቁ. 377/2003 / Labour Proclamation No.377/2003
loading...
Loading...