በስራ ቦታ ፍትሀዊ አያያዝ

እኩል ክፍያ

ለዕኩል ስራ እኩል ክፍያ የሚለው መርህ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን ሴቶች በጾታቸዉ ምክንያት የክፍያ ልዩነት ማድረግ ህገ ወጥ ድርጊት ነው  ህገ መንግስቱም ሴት ሰራተኞች ለተመሣሣይ ስራ ተመሣሣይ ክፍያ የማግኘት መብታቸውን ይደግፋል ፡፡

 

ምንጭ፡  በ1994 የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 42(1)መ እና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ቁጥር 1156/2019

ዕኩልነት

በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መሠረት ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው፡፡ በመካከላቸውም ማንኛውም ልዩነት ሣይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡

በዚህ ረገድ በዘር፣ በብሔር ብሔረሰብ፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች እኩልና ተጨባጭ የህግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው፡፡(አንቀጽ 25)

የአካል ጉዳተኞች አዋጅ ውስጥ በአንቀጽ 4 እንደተደነገገው ሁሉ በአካል ጉዳተኛነት ምክንያት በሥራ ቅጥር አድሎ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

በህጉ መሠረት ሠራተኛው በሠራተኞች ማህበር አባል በመሆኑ ወይም በማህበሩ ህጋዊ ተግባሮች ተካፋይ በመሆኑ ወይም የሠራተኛ ተጠሪ በመሆኑ ምክንያት አሠሪው የሥራ ውልን ለማቋረጥ አይችልም፡፡ ይህም በማህበር ላይ የሚደረግ አድሎን ይከላከላል፡፡ በዚሁ አንቀጽ መሠረት አሠሪው የሠራተኛውን ብሔረሰብ፣ ፆታ፣ ሃይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ የዘር፣ የቀለም፣ የቤተሰብ ኃላፊነት፣ የዘር ሐረግ፣ እርግዝና ወይም ማህበራዊ አቋም ምክንያት በማድረግ የሥራ ውሉን ማቋረጥ አይችልም፡፡

ምንጭ፡  በ1994 የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 25 እና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 14 እና 26

የመስራት መብት

ሴቶች ከወንዶች ጋር በተመሣሣይ በተለይም ለጤናቸው ጎጂ በሆኑ ስራዎች ላይ አይሰማሩም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ‹‹እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መተዳደሪያውን፣ ስራውን እና ሙያውን የመምረጥ መብት ይኖረዋል›› ይላል፡፡

ምንጭ፡  በ1994 የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 41 እና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 87(2)

loading...
Loading...