አንቀጽ 1 /አንድ/

የስምምነት ዓላማ

አንቀጽ 2 /ሁለት/

ትርጓሜ 

አንቀጽ 3 /ሶስት/

የሰራተኛ ማህበር ስለማሳወቅ

አንቀጽ 4 /አራት/

የሰራተኛ ግዴታ 

አንቀጽ 5 /አምስት/

የድርጅቱ ወይም የአሰሪው ግዴታ

አንቀጽ 6 /ስድስት/

የድርጅቱ መብት ጥበቃ

አንቀጽ 7 /ሰባት/

የሠራተኛ ማህበር መብትና ጥበቃ

አንቀጽ 8 /ስምንት/

8. የህብረተሰብ ስምምነት የሚመለከታቸው ሰራተኞች

አንቀጽ 9 /ዘጠኝ/

9. ስለ ሙከራ ጊዜ

አንቀጽ 10 /አስር/

10. ህጋዊ ግዴታዎች   

አንቀጽ 11 /አስራ አንድ/

11. ልዩ ልዩ ፍቃድ

አንቀጽ 12 /አስራ ሁለት/

12. የወሊድ ፍቃድ 

አንቀጽ 13 /አስራ ሶስት/

13. የጋብቻ ፍቃድ 

አንቀጽ 14 /አስራ አራት/

14. የሐዘን ፍቃድ 

አንቀጽ 15 /አስራ አምስት/

15. የትምህርት ፍቃድ  

አቀንቀጽ 16 /አስራ ስድስት/

16. የሙያ ማሻሻያና ሥልጠና 

አንቀጽ 17 /አስራ ሰባት/

17. ለማህበር ሥራ የሚሰጥ ፍቃድ 

አንቀጽ 18 /አስራ ስምንት/   

18. የሕመም ፍቃድ 

አንቀጽ 19 /አስራ ዘጠኝ/ 

19. ነፃ ፍቃድ 

አንቀጽ 20 /ሃያ/

20. በሥራ ምክንያት ስለሚመጡ ጉዳቶች የህመም ፍቃድ ክፍያ 

አንቀጽ 21 /ሃያ አንድ/

21. በሥራ ላይ የሚደርስ አደጋ 

አንቀጽ 22 /ሃያ ሁለት/

22. ከሥራ ጋር ግንኙነት የሌለው በሽታ ወይም አደጋ 

አንቀጽ 23 /ሃያ ሶስት/

23. ለሥራ ጉዳይ ስለሚሄድ ሠራተኞች የውሎ አበል 

አንቀጽ 24 /ሃያ አራት/

24. የሕዝብ በዓላት 

አንቀጽ 25 /ሃያ አምስት/

25. የአካል ጉዳት የአደጋ ዋስትና 

አንቀጽ 26 /ሃያ ስድስት/

26. የደመወዝ መክፈያ ቀን  

አንቀጽ 27 /ሃያ ሰባት/

27. የቀብር ሥነ-ሥርዓት 

አንቀጽ 28 /ሃያ ስምንት/

28. ስለ መልዕክት 

አንቀጽ 29 /ሃያ ዘጠኝ/

29. ተተኪ ሠራተኛ ስለመመደብ 

አንቀጽ 30 /ሰላሳ/

30. የስልክና የፖስታ አገልግሎት 

አንቀጽ 31 /ሰላሳ አንድ/

31. ዕድገት

31.1. ድርጅቱ ክፍት የሥራ ቦታ ሲኖረው ቦታውን ሊሸፍኑ ለሚችሉ ለውስጥ ሰራተኞች ቅድሚያ በመስጠት አወዳድሮ ማለፊያ ነጥብና ከዚያ በላይ ካመጡት ተወዳዳሪዎች መካከል የተሻለ ብልጫ ላመጣው ተወዳዳሪ ዕድገት ይሰጣል፡፡ 

አንቀጽ 32 /ሰላሳ ሁለት/ 

32. የአደጋ መከላከያዎችና የሥራ ልብስ 

አንቀጽ 33 /ሰላሳ ሶስት/

33. የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ

አንቀጽ 34 /ሰላሳ አራት/

34. ኢንሹራንስ 

አንቀጽ 35 /ሰላሳ አምስት/

35. የምስክር ወረቀት 

አንቀጽ 36 /ሰላሳ ስድስት/

36. ልዩ ልዩ ክፍያዎች 

አንቀጽ 37 /ሰላሳ ሰባት/

37. የማህበርተኝነት መዋጮ 

አንቀጽ 38 /ሰላሳ ስምንት/

38. ስለ ይርጋ ጊዜ  

አንቀጽ 39 /ሰላሳ ዘጠኝ/

39. ስለ አዲስ ህጎች መብት

አንቀጽ 40 /አርባ/

40. ስፖርት 

አንቀጽ 41 /አርባ አንድ/

41. በፍርድ ለሚታሰሩ ሠራተኞች 

አንቀጽ 42 /አርባ ሁለት/

42. የጋራ ውይይት 

አንቀጽ 43 /አርባ ሶስት/

43. የትርፍ ሰዓት ክፍያ  

አንቀጽ 44 /አርባ አራት/

44. የስራ ሰዓት 

አንቀጽ 45 /አርባ አምስት/

45. የህክምና ክፍያ 
በናዝሬት ልብስ ስፌት አክስዮን ማህበር

እና

በናዝሬት ልብስ ስፌት ሠራተኛ

ማህበር መካከልለአምስተኛ ጊዜ የተደረገ ሕብረት ስምምነት

ጳጉሜ 4 2005ዓ.ም 

 
ናዝሬት 


 1. ድርጅቱና ሰራተኛ ማህበሩ በተቻላቸው መጠን የድርጅቱ ውጤት አምሮና ዳብሮ የታለመውን ግብ እንዲመታ ከተቻለ ግቡን እንዲያልፍ በቅን ልቦና እየተወያዩ ይሰራሉ፡፡ 
 2. የዲሲፕሊን ቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓትን የሚመለከቱ መመሪዎችን በማውጣት ድርጅቱና ማህበሩ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ 
 3. ድርጅቱና ሰራተኛ ማህበሩ የሰራተኛው ደህንነትና የስራውም ውጤት ደንብ ተጠብቆ ሰራተኛው መብትና ግዴታውን አውቆ የዕለት ተግባራን እንዲያከናውንና መብቱንም እንዲጠይቅ ይጥራሉ፡፡ 
 4. በድርጅቱና በሰራተኛ ማህበሩ መካከል አስፈላጊ የሆነ መግባባትና መረዳዳት እንዲኖር ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ 
 5. የሰራተኛው የኑሮ ሁኔታ በሚሻሻልበትና ድርጅቱ ምርታማና ትርፋማ የሚሆንበት መንገድ ሁለቱም ወገኖች በጋራ ይሰራሉ፡፡ 
 6. ከመንግስት የሚሰጡ ተለዋጭ ህጋዊ መመሪያዎችን በስራ ላይ ያውላሉ፡፡ 
 7. የሚቋቋመው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በድርጅቱና በሠራተኛው ማህበሩ መካከል በተፈጠረው ቅሬታ የሚያስማማ ኮሚቴ ነው፡፡ አጀንዳዎች ከአሉ በወር አንድ ግዜ ለሁለት ሰዓት ስብሰባ ያደርጋል፡፡ ሠራተኛው ቅሬታ ለማህበሩ ሲያቀርብ ማህበሩ በሕጉ መሠረት ከማኔጅመንቱ ጋር መፍትሄ ይሰጣል፡፡ 
 8. የኮሚቴው ብዛት ከድርጅቱ ሁለት ከሠራተኛ ሁለት ይሆንና በተጨማሪም ሁለት ወገኖች የመረጡት አንድ ገለልተኛ ሰው በኮሚቴው ይካተታል፡፡ 

በዚህ ስምምነት አላማ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ቃላት እንደሚከተለው ትርጉም ተሰጥቷቸዋል፡፡  

 1. ድርጅቱ /ፋብሪካው/ ሲባል የናዝሬት ልብስ ሰፌት አክስዬን ማህበር ማለት ነው፡፡ 
 2. ማህበር /ሰራተኛ ማህበር/ ሲባል የናዝሬት ልብስ ስፌት አክስዬን ማህበር /የድርጅቱ/ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ማለት ነው፡፡
 3. ሰራተኛ ማለት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት ካሰሪው ጋር በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት ያለው ግለሰብ ማለት ነው፡፡ 
 4. ሁለቱም ወገኖች ሲባል ድርጅቱና ማህበሩ ማለት ነው፡፡ 
 5. የስራ መሪ ማለት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3/2/ሐ የሚሰጠውን ትርጉም የያዘ ነው፡፡ 
 6. የስራ ልብስ ማለት የተመደበበትን ስራ ላይ በሚሰራበት ጊዜ የሚሰጠው የስራ ልብስና የአደጋ መከላከያ ሲሆን ለጤናና ለደህንነት የሚሰጠው ማለት ነው፡፡ 
 7. ደመወዝ ማለት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 53 መሰረት ተራ ቁጥር 1 መሰረት ያለውን ትርጉም ያካትታል፡፡ 
 8. የህዝብ በዓላት ማለት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 73 መሰረት አግባብ ባለው ህግ መሰረት የሚከበሩና ወደፊት እንዲከበሩ የሚወሰኑ ደመወዝ የሚከፈልበት ቀን ማለት ነው፡፡ 
 9. ውሎ አበል ማለት አንድ ሰራተኛ ከተመደበበት የስራ ቦታ ለስራ ታዞ ሲሄድ የሚደረግ ክፍያ ማለት ነው፡፡ /ከአዳማ ከተማ ውጭ/
 10. አዋጅ ማለት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ቁጥር 377/96 ማለት ነው፡፡ 
 11. የመንግስት መመሪያ እና ደንብ ማለት መንግስት ወይም በመንግስት አዋጅ የተቋቋመ የበላይ አካል የሚያወጣው መመሪያ /ደንብ/ ማለት ነው፡፡ 


 1. በዚህ የህብረት ስምምነት ውስጥ ሰራተኛ ማህበሩን የሚመለከቱ የሥራ ሁኔታዎች ወይም ከድርጅቱ ጋር የህብረት ድርድር ለማድረግ ሰራተኛን በማንኛውም ጊዜና ቦታ መወከል የሚችል የሰራተኛ ማህበር ብቻ መሆኑን ድርጅቱ ያውቃል፡፡ 
 1. የመንግስት ህጎች ደንቦች አዋጆችና እንዲሁም ድርጅቱ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ የተመለከቱትን ሁሉ አክብሮ መገኘት አለበት፡፡ 
 2. የሰራተኞች አዋጅ ድንጋጌዎን የዚህ ህብረት ስምምነት፣ በስራ ደንብና ህግ የሚተላለፍ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን ያከብራል፡፡ 
 3. ለሰራተኛ በተሰጠው የስራ መደብና መመሪያ መሰረት ስራውን ይሰራል የድርጅቱን የስራ ሰዓትም ማክበር ግዴታ አለበት፡፡ 
 4. በተመሳሳይ የሥራ መደብ ሰራተኛው ሲመደብ የድርጅቱን የስራ ትዕዛዝ የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ 
 5. ፍቃድ ለመጠየቅ በሚያስችል ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሰራተኛው ሳያስፈቅድ ከስራው አይቀርም፣ ሆኖም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከቀረ ግን ከቀረበት ጊዜ በ5 ቀናት ውስጥ በቂ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 
 6. ማንኛውም ለስራ የሚገለገልባቸው የድርጅቱን የስራ መሳሪያዎች በአግባቡ መያዝና መንከባከብ ግዴታ አለበት፡፡ 
 7. አደጋ አስከታይ ሁኔታዎች ከሚፈጥሩ ነገሮች ራሱንና የስራ ጓዶቹን እንዲቆጠቡ ማድረግ አለበት፡፡ ለአደጋ አሳሳቢ የሆኑትን ወዲያውኑ ለሚመለከተው ክፍል የማመልከት ግዴታ አለበት፡፡ 
 8. በመጠጥ ወይም አእምሮን በሚያደነዝዙ ሌሎች ነገሮች ተመርዞ በስራ ላይ መገኘት የለበትም፡፡ 
 9. ማንኛውም የድርጅቱ ሰራተኛ የተሰጠውን የስራ ልብስ እና ሌሎች ለሙያ ደህንነት የሚሰጡ ቁሳቁሶን በስራ ላይ ለብሶ መገኘትና በጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡ 
 10. ማንኛውም የድርጅቱ ንብረት፣ ሰነድ ለሁለተኛ ሰው አሳልፎ አለመስጠት ወይም ለግል ጥቅሙ አለማዋል ወይም ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ አለማድረግ፡፡ 
 11. ማንኛውም ሰራተኛ ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ሁሉ ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት የድርጅቱን ጥቅም የሚቀንሱ ስራዎችን መስራት የለበትም፡፡ በተጨማሪም የመሳሪያውን ብልሽት ወዲያው ለቅርብ አለቃው ማሳወቅ አለበት፡፡ 
 12. ለራሱና ለድርጅቱ እንዲሁም ለስራ ጓዶቹ ጥሩ ሰላም በሚያስገኝ መንገድ/ መጥፎ ሽታ ከሚያስከትሉና ሁከትን ከሚያመጡ ነገሮች/ ሁልጊዜ ራሱን መምራትና መጠበቅ አለበት፡፡ 
 13. በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 158፣ 159 እና 160 ውጪ ስራ ማቆም አይፈቀድም፡፡ 
 14. ማንኛውም የድርጅቱ ሰራተኛ ወደ ስራ ሲገባም ሆነ ከስራ ሲወጣ ለመፈተሽ ግዴታው መሆኑን አውቆ መፈተሽ አለበት፡፡ 
 15. እያንዳንዱ ሰራተኛ የቅርብ አለቃው ሳያስፈቅድ የስራ ቦታውን ለቆ መሄድ የለበትም፡፡ 
 16. ማንኛውም ሰራተኛ የመስራት የሥራ የሥራ ኃይሉን አይቀንስም፡፡ 
 17. ድርጅቱ ሠራተኛውን ማሠልጠን ሲፈልግ ደረጃውን ጠብቆ የመሰልጠን ግዴታ አለበት፡፡ 
 1. ስልጠናውን በተመለከተ ድርጅቱና ሰልጣኙ በሚገቡት ውል መሰረት ይሆናል፡፡ 
 1. ማንኛውም ሠራተኛ ባልተስተካከለ መሣሪያ ሰርቶ ምርት /ሥራ/ ቢያበላሽ ለደረሰው ብልሽት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 
 1. የመንግስት ህጎችንና ደንቦችን እንዲሁም በዚህ የህብረት ስምምነት ውስጥ የሰፈሩትን አንቀጾች የመፈፀም ግዴታ አለበት፡፡ 
 2. ድጅቱ በህብረት ስምምነት ላይ በተወሰነው ጊዜ ደመወዝ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ 
 3. የሰራተኛው ህጋዊ መብት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ አያጎድልም ወይም አይቀንስም፡፡ 
 4. ድርጅቱ ሰራተኛው ሳያውቅና በጽሁፍ ግልባጭ ሳይደርሰው ማስጠንቀቂያም ሆነ ሌላ ቅጣት በግል ማህደር ውስጥ ማስቀመጥ አይችልም፡፡ 
 5. ለስራው አስፈላጊ የሆኑትን መሳሪያዎችንና መመሪያዎችን ጥሬ ዕቃዎች አሟልቶ ለሰራተኛው ያቀርባል፡፡ 
 6. ከሰራተኛው ቁጥጥር ውጭ በመሳሪያው አለመስተካከል ወይም አለመሟላት ምክንያት ለሚፈጠረው ችግር ሠራተኛው ተጠያቂ አይሆንም፡፡ 
 7. ከአዋጅና ከዚህ የህብረት ስምምነት ውጪ ድርጅቱ በሙሉም ሆነ በከፊል ወይም በተናጥል ሰራተኞችን አያግድም አይቀንስም፡፡ 
 8. ስራ እያለ ድርጅቱ ለሰራተኛው ስራ ሳይሰጠው ከቀረ በጥፋት ምክንያት ሰራተኛው በደብዳቤ ከስራ ካልታገደና ከድርጅቱ ቁጥጥር ውጪ ባልሆነ ምክንያት ሰራተኛው ስራ ቢፈታ ድርጅቱ ለሰራተኛው መደበኛ ደመወዙን ይከፍላል፡፡ 
 9. ድርጅቱ በስራ ላይ ከተሰማሩት ወይም ከታሰቡት ሰራተኞች ተግባርና ኃላፊነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ወይም አግባብነት ባላቸው ልዩ ልዩ ሞያዎች ለማሰልጠንና ለማሻሻል በውጪ ሀገርና በሀገር ውስጥ መንግስታዊ ሆነ የግል ድርጅቶች በሚያዘጋጁት ፕሮግራም ዕቅድ እያወጣ ከሙያው አንፃር ሰራተኛው እንዲሳተፍ የሚቻለውን ጥረት ያደርጋል፣ ለእድገትና ለአዲስ ቴክኖሎጂ ትውውቅ ለሚደረጉ ስልጠናዎች በውድድር ይሆናል፡፡ 
 10. የሰራተኛውን ደህንነት በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 92 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 
 11. ድርጅቱ የተሟላ መጸዳጃ ያዘጋጃል፡፡ 
 12. ድርጅቱ ወይም አሠሪው በማናቸውም የስራ ሰዓት በሰራተኛው ላይ ለሚደርሰው ድንገተኛ ህመምና አደጋ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 
 13. ሠራተኛው የሙያና ሌላም ዕውቀት ለማሻሻል በሀገር ውስጥም ሆነ ወደ ውጭ አገር በድርጅቱ ሲላክ ደመወዙን በአዋጁ መሰረት ለህጋዊ ወኪል ይከፈላል፡፡ 
 14. ማንኛውም የድርጅቱ ሹፌር ለድርጅቱ ስራ ጉዳይ የድርጅቱን መኪና በሚያንቀሳቅስበት ጊዜ ምንም ዓይነት አደጋ ቢደርስ ድርጅቱ ከኢንሹራንስ ጋር ባለው ስምምነት ከትራፊክ ፖሊስ በሚሰጠው ሪፖርት መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ሆኖም በአሽከርካሪው ቸልተኝነት በሚፈጠረው አደጋ አሽከርካሪው ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 
 15. ማንኛውም የድርጅቱ ሰራተኛ የእውቀት ደረጃውን በማሻሻል የሚያገኘውን ዲግሪ፣ ዲፕሎማ ወይም ሰርተፊኬት ከድርጅቱ ወይም ለአሰሪው ሲያቀርብ ከግል ማህደሩ ጋር ተያይዞ ይቀመጣል፡፡
 16. ድርጅቱ በሚኖረው ክፍት የስራ ቦታ በቅድሚያ ብቁ ለሆኑና ቦታውን ለሚያሟሉ ለውስጥ ሰራተኛ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ 
 17. ማህበሩ በዕድገት፣ በሰራተኛ ቅነሳ፣ በትርፍ ላይ በተመሰረተ በደመወዝ ጭማሪ በህብረት ስምምነት መሠረት ይሳተፋል እንዲሁም መዋቅር ጥናት ከተጠና በኃላ ድርጅቱ ለማህበሩ ያሳውቃል፡፡ 
 18. ማንኛውም የሠራተኛ የሥራ መመዘኛ ከግል ማህደሩ ከመቀመጡ በፊት ሠራተኛው ስለምዘናው ያለው አስተያየት ሰጥቶ ይፈርምበታል፡፡ 
 19. ህጉ ለፈቀደላቸው ሠራተኞች የሥራ ልብስ በየስድስት ወሩ ሆኖ የጨርቁ ዓይነትና የስፌት ስታይል ለስራ ተስማሚ በሆነ መልኩ ይሆናል፡፡ 
 20. ድርጅቱ የጠቅላላውን ሠራተኛ ጥቅም በተመለከተ ከማህበሩ ጋር ተወያይቶ መፍትሔ ሊሰጥ ይችላል፡፡ 
 21. ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ዝውውር በሚደረግበት ጊዜ ሰራተኛውና ድርጅቱን በሚጠቅም ሁኔታ ይፈፀማል፡፡ 
 22. ተላላፊ በሽታ በሰራተኛው መካከል ቢከሰት ድርጅቱ በፍጥነት ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ በሽታው እንዲወገድ ጥረት ያደርጋል፡፡ 
 23. ድርጅቱ ለሠራተኛው የመጠጥ ውሃ በጤና ጥበቃ መመሪያና ደንብ መሰረት በየጊዜው ለጤና ተስማሚ መሆኑን ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የውሃ ማጠራቀሚያ ንጽህና እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡ 
 24. ድርጅቱ የሚቀጥረው ሰራተኛ የጤና ምርመራ ውጤት እንዲያቀርብ ያደርጋል፡፡ 
 25. ሠራተኛው የተቀጠረበትን ቀን፣ ደመወዝ ልክ፣ በየጊዜው የሚወስዳቸውን ፍቃዶች፣ የጤንነት ሁኔታ፣ የመሳሰሉትን በግልጽ የሚያሳይ የግል ማህደር ይይዛል፡፡ 
 26. የሠራተኛው ጤንነት እንዲመረመር በህግ ወይም አግባብ ባለው ባለስልጣን ግዴታ በሚገባበት ጊዜ ለምርመራው የሚያስፈልገውን ወጪ ይችላል፡፡ 
 27. የሥራ ውል በሚቋረጥበት ወይም ሠራተኛውን በሚጠየቅበት ማናቸውም ጊዜ ሠራተኛው ሲሰራ የነበረውን የደመወዝ፣ የሥራ ልምድ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ለሰራተኛው በነፃ ይሰጣል፡፡ 
 28. ሠራተኛ መብትና ግዴታውን በቅድሚያ እንዲያውቅ ከማህበሩ በሚደረግ ስምምነት የህብረት ስምምነቱን ቅጂ 25 ኮፒ ተባዝቶ ለሠራተኛው ይሰጣል፡፡ 
 29. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኞች ከድርጅቱ ሲለቅ የሠራተኛ ማህበራትን ከማንኛውም ዕዳ ነፃ መሆኑን ድርጅቱ ማረጋገጫ ይጠይቃል፡፡ 
 30. የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎችን የህብረት ስምምነት የስነ-ስርዓት ደንብና በህግ መሠረት የሚተላለፍ መመሪያዎችን፣ ትዕዛዞችን ያከብራል፡፡ 
 1. በህግ በአዋጅና በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት የድርጅቱን ስራ ለመምራት የሠራተኞችን የአስተዳደር ሥራ ለመፈፀምና ለማስፈፀም ድርጅቱ ጥረት ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የድርጅቱ ሥራ ለመምራትና ለመቆጣጠር የድርጅቱ ሥራና የሠራተኞች ስራ ውጤት እንዲሻሻል ፕላን ያወጣል፡፡ 
 2. የድርጅቱ ሥራ ለመምራትና ለመቆጣጠር የድርጅቱ ሥራና የሠራተኞች ስራ ውጤት እንዲሻሻል ፕላን ያወጣል፡፡ 
 1. ድርጅቱ ሠራተኞችን የማህበር አባል እንዳይሆኑ ሊከለክል ወይም ከማህበር እንዲወጡ በመገፋፋት ጣልቃ መግባት አይችልም፡፡  
 2. ድርጅቱ ማንኛውንም የሠራተኛ ማህበሩ አባል በመሆኑና በማህበር ስራ አመራር ተካፋይ በመሆኑ የሞራልም ሆነ የማንኛውንም ተፅዕኖ አያደርግበትም፡፡ 
 3. ድርጅቱ ማንኛውም የሠራተኛ ማህበር መሪዎች የማህበር ሥራ ለማከናውን ከደመወዝ ጋር ፍቃድ ይሰጣል፡፡ 
 4. ማህበሩ የድርጅቱን ሠራተኞች ጉዳይ ከሚመለከተው ጋር መነጋገር ይችላል፡፡ 
 5. ድርጅቱ የድርጅቱን ትርፍና ኪሳራ ለማህበሩ በበጀት መዝጊያ እስከ አዲስ ሩብ ዓመት መጨረሻ እንያውቀው ያደርጋል /ያሳውቃል/፡፡  
 6. በማህበሩ ስራ የሚዋቀሩ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ለመሰባሰብና ለስብሰባ እንዲቻል ድርጅቱ በቅድሚያ ሲጠየቅ ሥራን በማይበደልበት ሁኔታ ፍቃድ ይሰጣል፡፡ 
 7. የመሠረታዊ ሰራተኛ ማህበር ስራ አስፈፃሚ ዘወትር በሳምት ማክሰኞ 2 (ሁለት) ሰዓት /ከ9-11/ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋለ፡፡ እንዲሁም አስኳይ ስብሰባ ሲኖርድርጅቱ ፈቅዳል፡፡

8.1 ይህ ህብረት ስምምነትማናቸውም በድርጅቱ የተቀጠሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ስምምነቱ የማይመለከታቸው የስራ መሪዎች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3  ተራ ቁጥር 2 #; መሰረት ይፈጸማል፡፡ 

9.1 በለማንኛዉም አዲስ ለሚቀጠር ሰራተኛ የመጀመሪያ 45 /አርባ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የሙከራ ጊዜ ናቸው፡፡

9.2 ራተኛ በሙከራ ላይ ባለበት ጊዜ ለስራዉ ተስማሚ አለመሆኑ ቢረጋገጥ ድርጅቱ ያለ አንዳች ማስጠንቀቂያ ወይም የስራ ካሳ መክፈል ሳይገደድ የስራ ዉሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ 

9.3. ማንኛውም በሙከራ ጊዜ የተቀጠረ ሠራተኛ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 11 መሠረት ይፈፀማል፡፡ 

9.4. ሠራተኛው በሙከራ ጊዜ ባለበት ጊዜ ከአገልግሎት ካሳ በስተቀር በዚህ የህብረት ስምምነት መሰረትና አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 11 የተጠቀሱትን ጥቅሞችንና መብቶችን ሁሉ ያገኛሉ፡፡ በስምምነቱ የተመለከቱትን ግዴታዎች ሁሉ ያከብራል፡፡ 

9.5. ሠራተኛው በሙከራ ላይ ባለበት ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 11 መሰረት አርባ አምስት ቀን ሙከራ ጨርሶ ደብዳቤ ሳይሰጠው ከቀረ እንደ ቋሚ ሠራተኛ ይቆጠራል፡፡ 

10.1. አንድ ሠራተኛ ህጋዊ ከሆ ክፍል ድርጅቱ መጥሪያ ሲደርሰው በራሱ ጉዳይ ከሶ ወይም ተከሶ ወይም ለምስክርነት ሲጠራ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 83 በተራ ቁጥር 1 እና 2 መሰረት ድርጅ ከደመወዝ ጋር ፍቃድ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 

11. የዓመት እረፍት ፍቃድ 

11.1. የዓመት እረፍት ፍቃድ ማለት ሰራተኛው በመደበኛ የስራ በዓት ከምድብ ስራ ቀሪ ለመሆን የሚያስችለው ከደመወዝ ጋር የሚሰጥ ፍቃድ ማለት ነው፡፡ 

11.2. አሰጣጡም በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 77 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

11.3. ሠራተኛው የዓመት ፍቃድ ለመውሰድ በሚፈልግበት ጊዜ ቅጽ በመሙላት የክፍል አለቃውን አስፈቅዶ ያለው የዓመት ፍቃድ በሠራተኛ አስተዳደር ሲረጋገጥ ይሰጠዋል፡፡ 

11.4. ማንኛውም ከአቅም በላይ የሆነ ድንገተኛ ችግር አጋጥሞት ችግሩ በስራ ክፍሉ ከታመነበት ከ10 ቀናት ባልበለጠ ነፃ ፍቃድ ይሰጠዋል፡፡ 

11.5. ሠራተኛው የዓመት ፍቃድ እንዲሰጠው ከጠየቀ ወይም ከሰሪው ጥያቄውን በስራ ላይ ችግር የማያስከትል ከሆነ ፍቃዱን ይሰጣል፡፡ ሆኖም በስራ ላይ ችግር የሚያስከትል ከሆነ ፍቃዱ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ የተላለፈው ዓመት ፍቃድ ከሁለት ዓመት በላይ ሊራዘም አይችልም፡፡ 

11.6. ሠራተኛው የዓመት እረፍቱን በሚወስድበት ጊዜ እረፍቱን ከመጀመሩ በፊት የሰራበትን ደመወዝና የእረፍት ጊዜ ክፍያ ሂሳቡን በቅድሚያ ያገኛል፡፡ 

11.7. የዓመት ፍቃድ በሚወስድበት ጊዜ የሳምንቱ የእረፍት ቀንና ሌሎች የህዝብ በዓላት አይቆጠሩም፡፡ 

11.8. ሠራተኛው የዓመት ፍቃድ ወስዶ ቢታመም 

ሀ. ሆስፒታል የሚያስገባ ሆኖ ከተገኘ ከማንኛውም ከመንግስት ሆስፒታልና ጤና ጣቢያ በሚያቀርብ የህመም ፍቃድ ልክ የዓመት ፍቃድ ይራዘምለታል፡፡ 

ለ. ሆኖም ግን ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር ህመምተኛው ናዝሬት ከተማ ውስጥ ከሆነ ድርጅቱ ክሊኒክ መጥቶ መታከም ይኖርበታል፡፡ 

ሐ. ስራ በሌለበት ቀና ከሆነ ከመንግስት ሆስፒታል ወይም ጤና ጣቢያ/ የህክምና አገልግሎት ሰጪ ታክሞ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ በአካባቢው የመንግስት ጤና ጣቢያና ሆስፒታል ያለመኖሩን ከህጋዊ አካል ማቅረብ አለበት፡፡ 

11.9. ድርጅቱ ለሠራተኛው የዓመት ፍቃድ ለመስጠት ካወጣው ፕሮግራም ውጪ እረፍት ማስወጣት ቢፈልግ ከ30 ቀን በፊት ለሰራተኛው ማሳወቅ አለበት፡፡ 

11.10. አንድ ሰራተኛ የዓመት ፍቃዱ ወስዶ በየጊዜው ባጋጠመው ችግር ምክንያት በወቅቱ ወደ ስራ ባይመለስ እና ላልተመለሰበትም ጊዜ በቂ ማስረጃ ካቀረበና የዓመት እረፍት ፍቃድ ካለው የዓመት እረፍት ፍቃድ ከሌለው በቆየበት ጊዜ ደመወዝ የማይከፈልበት ፍቃድ ይሰጠዋል፡፡ 

11.11. ከአንድ ዓመት በታች ላገለገለ ሠራተኛ ከድርጅቱ ሲሰናበት ላገለገለበት ጊዜ ተመጣጣኝ የሆነ የእረፍት ክፍያ በህጉ መሠረት በገንዘብ ተሰልቶ ይሰጠዋል፡፡ 

11.12. ለዓመት ፍቃድ ብቁ የሚያደርገው የአገልግሎት ጊዜ ለመወሰን ሲባል በድርጅቱ ለ26 ቀናት የሰራ ሰራተኛ በአንድ ወር እንደሰራ ይቆጠራል፡፡ 

11.13. በፍቃድ ላይ ያለ ሠራተኛን ድርጅቱ ለሥራ ከፈለገው ጠርቶ ማሠራት ይችላል፡፡ 

ሀ. ከፍቃድ ሲጠራ በጉዞ ያጠፋውን ጊዜ ተደምሮ የቀረውን የዓመት ፍቃድ በገንዘብ ተሰልቶ ይከፈለዋል፡፡ 

ለ. ከፍቃድ በመጠራቱ ምክንያት የደረሰበትን የመጓጓዣና የውል አበል ወጪ አሰሪው ይችላል፡፡ 

12.1. ነፍሰ ጡር ሴት የሆነች ሠራተኛ ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ከክሊኒኩ ኃላፊ ከተፈቀደ አሰሪው ከደመወዝ ጋር ፍቃድ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ከምርመራው በኃላ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 

12.2. ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ ከመውለዷ በፊት ሐኪም ካዘዘ ከክፍያ ጋር እረፍት ይሰጣታል፡፡ 

12.3. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት መውለጃዋ ሲደርስ የ30 ተከታታይ ቀን የወሊድ ፍቃድ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ለ60 ተከታታይ ቀናት ፍቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል፡፡ 

12.4. ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ30 ቀን ፍቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከምትወልድበት ቀን ድረስ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት የምትወልደው የሐኪም ፍቃድ እረፍት ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ 

12.5. ነፍሰጡር የሆነች የድርጅቱ ሠራተኛ ከመውለዷ በፊት ወይም በወሊድ ፍቃድ ላይ እያለች ብትታከም ሐኪሟም ለመታመሟ ካረጋገጠ ይኸው ሕመም ከሥራ ግንኙነት እንደሌለው በሽታ ተቆጥሮ ከሥራ ግንኙነት ለሌለው በሽታ የሚከፈለውን የሕክምና ወጪ ይከፈላታል፡፡ 

12.6. ነፍሰጡር የሆነች ሴት ሠራተኛን ከስራ በኃላ ከተመለከተው የሥራ ቦታዋ ውጪ ማሰራት አይቻልም፡፡ ሆኖ ነፍሰጡሯ የምትሰራው ሥራ ለራሷ ጤንነትም ሆነ ለጽንስ አደገኛ መሆኑ በሐኪም ሲረጋገጥ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ተመድባ መስራት አለባት፡፡ 

12.7. ማንኛውም ነፍሰጡር ሰራተኛ በምትወልድበት ጊዜ ደመወዟ በቅድሚያ ይሰጣታል፡፡ 

12.8. ነፍሰጡር ለመሆናቸው ከድርጅቱ ወይም ከአሰሪው ክሊኒክ ለቅርብ አለቃቸው መረጃ ያቀረቡ የድርጅቱ ሠራተኛ ከ4 ወር እርግዝና በኋላ የሥራ ሰዓት ከመፈፀሙ በፊት የአምስት ደቂቃ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ 

12.9. በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ ንዑስ ቁጥር 3 መሠረት ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ትርፍ ሰዓት ሥራ እንድትሰራ አትገደድም፡፡ 

12.10. ከሙከራ ጊዜ አንዲት ሠራተኛ ያረገዘች እንደሆነ ማርገዟ እንደነውር ተቆጥሮባት ምንም ዓይነት ቅጣት ወይም ከሥራ መውጣት አይደርስባትም፡፡ 

12.11. የድርጅቱ ሠራተኛ ያረገዘችው ጽንስ ከሥራ ጋር ግንኙነት ባለው አደጋ ምክንያት የተጠናወታት /ያስወረዳት/ መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ ለሌሎች አደጋ የደረሰባቸው ሰራተኞች እንደሚደረገው ሁሉ ሙሉ ደመወዝ ከህክምና ፍቃድ ጋር ይሰጣታል፡፡ በአደጋም ይመዘገብላታል፡፡ 

12.12. የድርጅቱ ነፍሰ ጡር ሰራተኛ በጤንነት ጉድለትና በአንዳንድ አክል ምክንያት ያስወረዳት /የተጠናወታት/ እንደሆነ እንደማንኛውም በሽታ ድርጅቱ የሐኪም ፍቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣታል፡፡ ሆኖም ህገ ወጥ ውርጃ መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ ተቀባይነት አይኖረውም በሌላ በኩል ከ7ወር ያላነሰ ሕጋዊ ውርጃ ለመሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ የወሊድ ፍቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል፡፡ 

12.13. ማንኛውም ነፍሰጡር ሰራተኛ ስለመሆኗ ለቅርብ ኃላፊዋ ማስረጃ በማቅረብ በማሳወቅ ከዚሁ ጋር የተያያዘ መብትና ጥቅሞችን ማግኘት ትችላለች፡፡ 

12.14. የሥነ ፆታዊ መብት ሴቶች መብታቸው መከበርና መጠበቅ ይገባዋል፡፡ 

13.1. የድርጅቱ ሠራተኛ ሕጋዊ ጋብቻ ለመፈጸምና ለድርጅቱ ከ8 ቀናት በፊት አስቀድሞ ሲያሳውቅ ሶስት /3/ የሥራ ቀናት ከደመወዝ ጋር ፍቃድ ይሰጠዋል፡፡ 

14.1. የድርጅቱ ሠራተኛ እናት፣ ልጅ የትዳር ጓደኛ በሞት ሲለዩባቸው በናዝሬት ከተማ ውስጥ ከሆነ 3 /ሶስት/ የሥራ ቀናት የሐዘን ፍቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣል፡፡ ሌሎች ዘመዶች በሞት ሲለዩባቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

14.2. ሠራተኛ በሀዘን ላይ እያለ ልዩና አሳሳቢ ሁኔታ ሲያጋጥመው በሥራ ላይ ችግር የማያስከትል መሆኑ በድርጅቱ ከታመነበት የዓመት ፍቃድ ወይም አምስት የሥራ ቀናት ደመወዝ የማይከፍልበት ፍቃድ ይሰጠዋል፡፡ 

15.3. በመንግስትና መንግስት እውቅና በሰጣቸው 8ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ሙሉ ቀን በሚያቀርቡት መረጃ መሠረት ፍቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ 

16.1. ድርጅቱ ወይም አሠሪው በውጭ ሀገር ለከፍተኛ ትምህርት ዕድል ሲገኝና በድርጅቱ ሲታመን ከድርጅቱ ሰራተኞች መካከል አወዳድሮ ይልካል፡፡ 

16.2. በሀገር ውስጥ በፋብሪካም ሆነ ከፋብሪካ ውጭ በሚደረግ ስልጠና ለሚያስፈልጋቸው የድርጅቱ ሠራተኛ መካከል በፕሮግራም እንዲሰለጥኑ ያደርጋል፡፡ 

16.3. በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኛ በሙያውና በዕውቀቱ ስልጠና እንዲያገኝ በድርጅቱ ውስጥ ማሰልጠኛ ይቋቋማል፡፡ ሠራተኛው ስልጠና እንዲያገኝ ከመደረጉ በፊት በቅድሚያ አስፈላጊውን ውል ከድርጅቱ ጋር መዋዋል አለበት፡፡ 

17.1. በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 82 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

18.1. ማንኛውም ሠራተኛ ከሥራ ጋር ግንኙነት በሌለው ምክንያት ለሚደርስበት ሕመም ከመንግስት ሆስፒታል ወይም ጤና ጣቢያ የሕክምና ማስረጃ ሲያቀርብ ፍቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣል፡፡ 

18.2. የሕመም ፍቃድ በተከታታይ ወይም በተለያዩ ጊዜያት ቢወስድም በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 85 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት በ12 ወር ውስጥ ከ6 ወር አይበልጥም፡፡ 

18.3. ማንኛውም ሠራተኛ የሚሰጠውን የህመም ፍቃድ በዕለቱ ለማስታወቅ በቂ ምክንያት ካላጋጠመው በስተቀር ፍቃድ በተሰጠው ዕለት ወይም በማግስቱ ለፋብሪካው ማቅረብ አለበት፡፡ 

18.4. አንቀጽ 18.2 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በተከታታይ ለሶስት ወራት የህመም ፍቃድ የተሰጠው ሠራተኛ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

18.5. የሕመም ፍቃድን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 85 ተራ ቁጥር 4 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

19.1. ማንኛውም ሠራተኛ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 81 ተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡   

20.1. ከሥራ ግንኙነት ያለው በሽታ ወይም አደጋ 

20.2. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ሥራው በሚያከናውንበት ጊዜ አደጋ ቢደርስበት ወይም በሚያከናውነው ሥራ ምክንያት በሽታ ላይ ቢወድቅ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ የማሳከም ግዴታ አለበት፡፡ 

20.3. አንድ ሠራተኛ በስራው ላይ እያለ አደጋ ቢደርስበት በክፍሉ ተቆጣጣሪ አማካኝነት ለመጀመሪያ እርዳታ ወደ ድርጅቱ ክሊኒክ በአስቸኳይ ሄዶ የመጀመሪያ እርዳታ ከተደረገለት በኃላ የድርጅቱ ክሊኒክ አስፈላጊ ከሆነ ወዲያውኑ በድርጅቱ ትራንስፖርት ወደ ሆስፒታል ይላካል፡፡ 

20.4. የደረሰበት አደጋ ሆስፒታል የሚያስተኛ ሆኖ ከተገኘ ድርጅቱ በተዋዋልነው ኢንሹራንስ ስምምነት መሰረት ሆስፒታል ተኝቶ አስፈላጊው ሕክምና ይደረግለታል፡፡ 

20.5. ሠራተኛው የደረሰበት አደጋ በቅርብ በሚገኝ ሐኪም የማይድን ከሆነ የሀኪሞች ቦርድ በሚወስነው መሰረት/ እንዲታከም ይደረጋል፡፡ 

20.6. ሠራተኛ በስራ ላይ እያለ በሚደርስበት አደጋ ወይም ምክንያት የአካል ጉድለት ከደረሰበት ድርጅቱ ከኢንሹራንስ ጋር ባደረገው ስምምነት የአካል ጉድለት ካሳውን ያገኛል፡፡ 

20.7. ከሥራ ጋር ግንኙነት ባለው በሽታ አንድ ሠራተኛ ለደረሰበት ሕመም አደጋ አስፈላጊው ሕክምና አድርጎ እስኪጨርስና ይኸውም በሐኪም እስከተረጋገጠ ድርጅቱ ደመወዝ ይከፍለዋል፡፡ 

20.8. አንድ ሠራተኛ በሥራ ቦታ ላይ በደረሰበት አደጋ ምክንያት ስራውን ለመቀጠል የማይችል መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ ድርጅቱ ከኢንሹራንስ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት የኢንሹራንስ ካሳውን አግኝቶ የሞራል መጠበቂያ ድርጅቱ የሶስት ወር ደመወዝ ይከፍላል፡፡ 

20.9. አንድ ሠራተኛ ከስራ ግንኙነት ባለው ምክንያት የዓይን ህመም ደርሶበት መነፅር እንደሚያስፈልገው በሐኪም ከተረጋገጠ ድርጅቱ ለሰራተኛው ይገዛለታል፡፡ በተጨማሪም የታዘዘለትን መነፅር በስራ ላይ እንዳለ በራሱ ጥንቃቄ ጉድለት ማነስ ምክንያት የተሰበረበት አለመሆኑ ሲረጋገጥ ተመሳሳይ መነፅር በሐኪም ትዕዛዝ መሰረት ድርጅቱ ይተካለታል፡፡ 

20.10. ከሥራ ግንኙነት ባለው ምክንያት ሠራተኛው የጥርስ መውለቅ ወይም ስብራት መድረሱ ከተረጋገጠ ድርጅቱ ለሠራተኛው ጥርስ ያስተክልለታል፡፡ በተጨማሪም የተተከለውን ጥርስ በስራ ላይ እንዳለ ከራሱ ጥንቃቄ ጉድለት ማነስ ምክንያት ያልወለቀ ስለመሆኑ ሲረጋገጥ ጥርሱን ድርጅቱ ያስተክልለታል፡፡ 

20.11. ስለ ሕክምና አገልግሎት በተመለከተ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 105 መሠረት ድርጅቱ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ 

20.12. አንድ በሽታ ከስራው ጋር በተያያዘ ሁኔታ የመነጨ መሆኑን ሊረጋገጥ የሚችለው በሐኪም ብቻ ነው፡፡ 

21.1. በዚህ ህብረት ስምምነት በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ማለት ማንኛውንም ሠራተኛ ስራውን በማከናወን ላይ ሳለ ወይም ከስራ ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ ከራሱ ውጪ በሆነ ምክንያት ወይም ስራውን ለማከናወን ባደረገው ጥረት ምክንያት በአካል ወይም በማንኛውም ክፍል ላይ ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት የደረሰበት ጉዳት ሲሆን የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡ 

ሀ. ሠራተኛው ከሥራ ቦታው ወይም የሥራ ሰዓት ውጪም ቢሆን የአሰሪውን ትዕዛዝ ሥራ ላይ ያውል በነበረበት ጊዜ የደረሰበት ጉዳት፣ 

ለ. ሠራጠኛ በሥራ ቦታው ወይም ከሥራ ቦታው ድርጅቱ /አሰሪው/ ለሠራተኞቹ አገልግሎት እንዲሰጥ በመደበው የመጓጓዣ አገልግሎት ወይም ድርጅቱ ለዚሁ ተግባር በተከራየውና በግልጽነት በመደበው የመጓጓዣ አገልግሎት በመጓዝ ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰበት ማንኛውም ጉዳት በአንቀጽ 25 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

ሐ. ሠራተኛው ሥራውን በማከናወን ላይ ባለበት ጊዜ በአሰሪው ወይም በሶስተኛው ወገን ድርጊት ምክንያት የደረሰበት ጉዳት፣ 

መ. ስለጥገኞች ክፍያ በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

22.1. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ከሥራ ጋር ግንኙነት የሌለው በሽታ ወይም አደጋ ቢደርስበት በድርጅቱ ክሊኒክ ተገኝቶ የመጀመሪያ ዕርዳታ ማግኘት ይችላል፡፡ 

22.2. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ በጠና ታሞ ከክሊኒክ ወደ ሆስፒታል በድርጅቱ ተሽከርካሪ ወይም ድርጅቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ይሆናል፡፡

22.3. ሠራተኛው በሥራ ላይ እያለ ሕመም ከደረሰበት በማንኛውም የሥራ ሰዓት በድርጅቱ ክሊኒክ ተገኝቶ አስፈላጊው ሕክምና ይደረግለታል፡፡ 

22.4. ድርጅቱ በሽታውን የሚያስመረምርበትና የሚያሳክምበት ሆስፒታል በሥራ ክልል ከሆነ በስምምነቱ መሰረት ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሕክምና ቦታ ከክልሉ ውጪ ከሆ የትራንስፖርትና እንዲሁም የአንድ ቀን የውሎ አበል ይከፍላል፡፡ 

22.5. ሠራተኛው በደረሰበት ሕመም ምክንያት ሆስፒታል ተኝቶ የሚታከም ከሆነ በሆፒታሉ ሁለተኛ ደረጃ ተኝቶ እንዲታከም ያደርጋል፡፡ ሆኖም በሆስፒታሉ ሁለተኛ ማዕረግ አልጋ ቢጠፋ እስኪገኝ ድረስ በተገኘው ደረጃ ተኝቶ እንዲታከም ይደረጋል፡፡ 

22.6. አንቀጽ 20.12 እንደተጠበቀ ሆኖ ድንገተኛ ሕመም በሐኪም ካልተረጋገጠ በስተቀር ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ወደ ሆስፒታል የሚሄደው በክሊኒክ ወይም በአስተዳደር ፍቃድ ነው፡፡ 

23.1. አበል 

23.1.1. የውሎ አበል ተግባራዊ የሚሆነው ከናዝሬት ከተማ ውጭ ወይንም አበል ተከፋይ ካለበት ከተማ ውጭ ሲሆን፡፡ የአበል አከፋፈል ቁርስ 15%፣ ለምሣ 25%፣ ለእራት 25% እና ለመኝታ 35% ይሆናል፡፡ 

23.1.2. በአዳማ ከተማ በሚደረገው በባዛር ሽያጭ ስራ ለተሰማሩ ሠራተኞች የምሳ አበል ይከፈላቸዋል፡፡ 

ሀ. ከ310 እስከ 1010 ብር ደመወዝ ለሚያገኙ 120ብር የውሎ አበል፣ 

ለ. ከ1011 እስከ 1711 ብር ደመወዝ ለሚያገኙ 130ብር የውሎ አበል፣ 

ሐ. ከ1712 እስከ 2412 ብር ደመወዝ ለሚያገኙ 140ብር የውሎ አበል፣ 

መ. ከ2413 እስከ 3113 ብር ደመወዝ ለሚያገኙ 150ብር የውሎ አበል፣ 

ሠ. ከ3114 እስከ 3814 ብር ደመወዝ ለሚያገኙ 160 ብር የውሎ አበል፣ 

ረ. ከ3815 በላይ 170 - 190  


24.1. መስከረም 1 ቀን 

24.2. ኢድ አልፈጥር 

24.3. መስቀል 

24.4. ኢድ አል አድሀ /አረፋ/

24.5. ጥምቀት 

24.6. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 

24.7. የአድዋ ድል መታሰቢያ 

24.8. መውሊድ /የነቢዩ መሐመድ ልደት/

24.9. ሚያዝያ 27 /የአርበኞች በዓል/

24.10. ስቅለት 

24.11. ትንሣኤ 

24.12. ግንቦት 20 

24.13. ሜይ ዴይ /የወዛደሮች ቀን/ 


ይሁን እንጂ የሕዝብ በዓላት በሳምንት በሥራ ቀን ላይ የዋለ እንደሆነ ለቋሚና ለኮንትራት ሠራተኞች ሳይሰሩ ደመወዝ ይከፈላቸዋል፡፡ 

25.1. የአካል ጉዳት ማለት የመስራት ችሎታ መቀነስ ወይም ማጣትን የሚያስከትል ሁኔታ በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው፡፡ 

ሀ. ጊዚያዊ የአካል ጉዳት፣ 

ለ. ዘላቂ የአካል ጉዳት፣ 

ሐ. ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት እና 

መ. ሞት 

25.2. ድርጅቱ ወይም አሰሪው ጉዳት ለደረሰበት ሰራተኛ የሚከተሉትን የመፈፀም ግዴታ አለበት፡፡ 

ሀ. ጉዳት ለደረሰበት ሰራተኛ የመጀመሪያ ሕክምና ዕርዳታ በጊዜው መስጠት፣ 

ለ. ጉዳት የደረሰበት ሰራተኛ በድርጅቱ ተሽከርካሪ በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው ህጋዊ የህክምና ድርጅት አድርሶ ይመልሳል፡፡ 

25.3. የአካል ጉዳት ለደረሰበት ሰራተኛ ድርጅቱ ወይም አሰሪው ለህክምና አገልግሎት የሚያስፈልገውን ወጪ ይከፍላል፡፡ እነዚህም፡- 

ሀ. የጠቅላላና የልዩ ህክምና እንዲሁም የቀዶ ህክምና ወጭዎች 

ለ. የሆስፒታል የመድኀኒት ወጭዎች 

ሐ. የማንኛውም አስፈላጊ ሰው ተጨማሪ አካላትን የአጥንት ጥገና ወጪዎች 

መ. ሠራተኛው ለደረሰበት ጉዳት የሚደረግለት የሕክምና አገልግሎ ቦርድ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት ይሆናል፡፡  

25.4. ዘላቂ የአካል ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የጡረታ ወይም ዳረጎት ወይም ካሳ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ 

25.5. የሞተ እንደሆነ ለጥገኞቹ የጡረታ አበል ወይም ዳረጎት ወይም ካሣ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ 

25.6. ዘላቂ የአካል ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የአካል ጉድለት ካሳ ክፍያው ፋብሪካው ከኢንሹራንስ ጋር ባለው ውል መሰረት ይፈፀማል፡፡ ሠራተኛው በሞት የተለየ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 107/02 ሀ-ሐ በተጠቀሰው መሰረት ይሆናል፡፡ በዚሁ ሳቢያ ለተደረገ ሕክምና ዓይነቶች ወጭዎችን ድርጅቱ ይከፍላል፡፡ 

25.7. አንድ ሠራተኛ በሞት ቢለይ ለሠራተኛው የሚገባው ማንኛውም ልዩ ልዩ ክፍያዎች ለሕጋዊ ጥገኞች አሰሪው ይከፍላል፡፡ 

25.8. ስለ ሠራተኛው ጉዳት ካሳ በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109 ቁጥር 1 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 

25.9. ድርጅቱ ወይም አሰሪው የኢንሹራንስ ውል አንድ ኮፒ ወይም ፎቶ ኮፒ ለማህበሩ መስጠት አለበት፡፡ 

26.1. የወር ደመወዝተኛ ደመወዙን እ.ኤ.አ ከ28ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 31 ቀን የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ 

26.2. በንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው የደመወዝ መክፈያ በበዓል ቀን ከዋለ ቀደም ባለው የስራ ቀን ይከፈላል፡፡  

26.3. ከዚህ በላይ የተገለጸው የደመወዝ መክፈያ ቀን ከተወሰነው ቀን በላይ ሊያልፍ እነና ሊራዘም አይችልም፡፡ 

26.4. በበዓል ወይም በሌላ አስፈላጊ ምክንያት ሠራተኛው በቅድሚያ እንዲከፈለው ቢፈልግ ፋብሪካውና ማህበሩ በተስማሙበት መሰረት ይፈፀማል፡፡ 

26.5. አንድ ሠራተኛ በእክል ምክንያት ደመወዙን መጥቶ ሊወስድ ካልቻለ በጽሁፍ ለሚወክለው ሰው ሊሰጥ ይችላል፡፡ የሚወክለው ሰው የፋብሪካውን ሠራተኛ ሲሆን ውክልናውም በአስተዳደሩ ሲፀድቅ ለተወከለው ሰው ሊከፍለው ይችላል፡፡ 

27.1. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ በአደጋ ወይም በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ ከዚህ በታች የተገለጹት ሁኔታዎች ይመቻቹለታል፡- 

27.1.1. ድርጅቱ የሠራተኛ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ለማስፈፀም ከድርጅቱ ሠራተኞች 4 በመቶ ድረስ ሙሉ ቀን እንዲያስተዛዝኑ ከደመወዝ ጋር ፍቃድ ይሰጣል፡፡ ነገር ግን ከናዝሬት ውጭ ከሆነ ስለሚሄዱት ሰራተኞች አስቸኳይ ውይይት ተደርጎ ወዲያውኑ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ 

27.1.2. አንድ ሠራተኛ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ ለቀብር ሥነ ሥርዓት ማስፈፀሚያ ድርጅቱ ወይንም አሰሪው 1500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለህጋዊ ጥገኞቹ ይከፍላል፡፡ 

27.1.3. ማንኛውም ሠራተኛ ወይም ለማጅ ሠራተኛ በሥራ ምክንያት በደረሰበት ጉዳት የተነሳ የሞተ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110 በተ.ቁ ‹‹ለ›› መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

27.1.4. አንድ የድርጅቱ ሠራተኛ ለድርጅቱ ወይም ለአሰሪው ሥራ ጉዳይ ታዞ ቢሄድና የሞት አደጋ ቢደርስበት አስክሬኑ ከሞተበት ቦታ ወደ ቤቱ ለማድረስ ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን ወጪ ድርጅቱ ወይም አሰሪው ይከፍላል፡፡ 

27.1.5. አንድ የድርጅቱ ሠራተኛ ለሙያ ስልጠና ወይም ለድርጅቱ ስራ ውጭ አገር ሄዶ ቢሞት አስክሬን ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ ድርጅቱ ወይም አሰሪው ይከፍላል፡፡ 

28.1. ማንኛውም የድርጅቱ ሰራተኛ ከአቅሙ በላይ በሆነ አሳማኝ ምክንያት ከሥራው ቢቀር በአንድ ቀን ወይም በ24 ሰዓት ውስጥ በደብዳቤ፣ በሰው ወይም በስልክ መልዕክት በመላክ ድርጅቱ ካመነበት ሊፈቀድለት ይችላል፡፡ 

28.2. ሠራተኛው የገጠመውን ድንገተኛ ችግር ድርጅቱ ሲያምንበት መቅረቱን በመልዕክት ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ወደ ፋብሪካው በመምጣት ተጨማሪ ፍቃድ የሚያስፈልገው ሆኖ ቢገኝ በግንባር ቀርቦ ማስፈቀድ አለበት፡፡ 

28.3. በአንቀጽ 28.2 በግንባር ቀርቦ ማስፈቀድ ካልቻለ ፍቃዱን ጨርሶ ሲመለስ ለቀረበለት ቀናት ማስፈቀድ ያልቻለበት ምክንያት የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 

29.1. አንድ ሠራተኛ ለተወሰነ ጊዜ በሥራ ጉዳይ፣ በህመም፣ በዓመት ዕረፍትና በወሊድና በመሳሰሉት ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው ላይ ቢለዩ የሥራ መደቡን ለመሸፈን ተተኪ ሰራተኛ እንደ አስፈላጊነቱ ይመደባል፡፡ 

29.2. አዲስ ክፍት ቦታ ሲኖር በዕድገት ወይም በቅጥር እስኪያሟላ ድረስ በቦታው እንደ አስፈላጊነቱ ተከቶ ማሰራት ይቻላል፡፡ የተተኪው ምደባ የሚፈፀመው በክፍል ኃላፊው ተጠይቆ በዋና ሥራ አስኪያጅ ሲጸድቅ ነው፡፡ 

29.3. የተተኪ አበል አከፋፈል የተተኪው ሠራተኛ ደመወዝ 25% ይሆናል፡፡ ሆኖም ለምትክነት የሚከፈለው ተጨማሪ ክፍያ ከሁለት መቶ ብር መብለጥ የለበትም፡፡ 

29.4. ይኸውም አበል ሥራውን ከጀመረበት ጊዜ እስከ ተቋረጠበት ጊዜ የሰራበት ይከፈለዋል፡፡ 

29.5. ሀ. ይኸውም 29.1 ለተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ከ6 ወር መብለጥ የለበትም፡፡ ሆኖም አስገዳጅ ሁኔታ ካጋጠመው ለተጨማሪ ሶስት ወራት ውክልናው ማራዘም ይቻላል፡፡ 

29.6. የተተኪ አበል የሚከፈለው ተተኪው ሠራተኛ ሥራው ላይ ለ1 ወርና ከአንድ ወር በላይ ሲሰራ ነው፡፡ 

30.1. ለድርጅቱ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ከፖስታ ቤት ጋር በመነጋገር አንድ ደብዳቤ ማጠራቀሚያ ሳጥን እንዲዘጋጅ ድርጅቱና ሠራተኛ ማህበሩ በጋራ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ 

30.2. በድርጅቱ አድራሻ ለሠራተኞች የሚመጣን ደብዳቤ ለሠራተኞች ያከፋፍላል፡፡ 

30.3. በማህበር ስም የሚመጡ ደብዳቤዎችና ፖስታዎች ድርጅቱ ወይም አሰሪው ለማህበሩ ይሰጣል፡፡ 


31.2. ድርጅቱ ወይም አሰሪው ባለው የሥራ መዋቅር መሰረት በመዋቅሩ ወይም ለሥራ መደቡ ደመወዝ ይመድባል፡፡ 

31.3. ድርጅቱ ለአዲስ የዕድገት ቦታ ሠራተኛ ሲመድብ ለቦታው በተመደበው እስኬል መነሻ መሰረት ይሆናል፡፡ ሆኖም የተወዳደረው ደመወዝ ዕድገቱ ከሚሰጥበት የሥራ መደብ በላይ ከሆነ በሚያገኘው ደመወዝ ላይ ከ2 እርከን ያላነነሰ ተጨማሪ ያገኛል፡፡ 

31.4. አንድ ሠራተኛ ለእድገት ውድድር ቀርቦ በዕድገት ኮሚቴ ሲመረጥና በዋና ሥራ አስኪያጅ ሲፀድቅ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ 

31.5. የተገኘውን የዕድገት ቦታ ከድርጅቱ ሠራተኛ ውስጥ ተወዳድሮ አሸናፊ ሆኖ ከተገኘና ድርጅቱ ወይም አሰሪው ሠራተኛውን በወቅቱ ወደ አዲስ ዕድገት ቦታ ሳያዘዋውረው ቢቀር ድርጅቱ በአዲሱ የዕድገት ቦታ ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ 

31.6. የዕድገት መወዳደሪያ መመዘኛዎች መቶኛ /%/ ነጥቦች ይይዛሉ፡፡ 

ሀ. የሥራ አፈፃፀም ምዘና 20% 

ለ. የተግባር፣ የጽሁፍ፣ የቃል ፈተና 30% 

ሐ. የግል ማሕደር ጥራት 25% 

መ. የስራ ቅርበት 25% ሲሆን የትምህርት ደረጃው የአገልግሎት ጊዜ አስፈላጊ የማጣሪያ አፈጻጸም መወዋል ያለባቸው ናቸው፡፡ 

31.7. እስከ ዲፕሎማ የትምህርት ደረጃ የሚጠይቅ ቦታ 12ኛ ክፍል ለጨረሰ ተወዳዳሪ የሶስት ዓመት የሥራ ልምድ እንደ አንድ የትምህርት ዓመት ይቆጠርለታል፡፡ 

31.8. እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት ደረጃ ለሚጠይቅ ክፍት የሥራ ቦታ ተወዳዳሪው የ8ኛ ክፍል የፈፀመ ከሆነ የአራት ዓመት የሥራ ልምድ አንድ ዓመት የትምህርት ዓመት ይቆጠርለታል፡፡ 

31.9. ማንኛውም አዲስ ቅጥር በድርጅቱ ለስድስት ወር ግልጋሎት ሳይሰጥ ለዕድገት ውድድር መቅረብ የማይችል ሲሆን እንደዚህም አንድ ሰራተኛ ለሌላ ዕድገት መወዳደር የሚችለው ባደገበት ቦታ ለስድስት ወር ግልጋሎት ከሰጠ በኃላ ነው፡፡ 

31.10. በፋብሪካው ውስጥ በዋና ክፍልና ከዚያ በላይ ያሉት የሥራ መደቦች በአሰሪው ወገን ይመደባል፡፡ 

ተ.ቁ

የሥራ ክፍል

የአደጋ መከላከያ ዝርዝር

የእደላ ጊዜ

በ1 ዓመት

በ3 ዓመት


የቆረጣ ሠራተኛ 

ጫማ 

1የቆረጣ ሠራተኛ 

የስራ ልብስ ጃኬትና ሱሪ 

2

-


የስፌትና ማጠናቀቂያ ሠራተኞች 

የስራ ልብስ 

2የማጠናቀቂያ ካውያ ሠራተኞች 

የስራ ልብስ ጃኬትና ሱሪ 

2

-


የማጠናቀቂያ ካውያ ሠራተኞች 

ጫማ 

1

-


ለጥገና ሠራተኞች 

የስራ ልብስ ጋዋን 

2ለጥገና ሠራተኞች 

ጫማ 

1የኤሌክትሪሻን ሠራተኞች 

የስራ ልብስ ጋዋንና ሜዞ ቱታ 

2የኤሌክትሪሻን ሠራተኞች 

ጫማ 

1ለመጋዘን፣ ለግዥና ሽያጭ ሠራተኞች 

የስራ ልብስ ጋዋን 

1ለምርት ክፍል ኃላፊና ተቆጣጣሪ 

የስራ ልብስ ጋዋን 

1ለጥራት ተቆጣጣሪዎች 

የስራ ልብስ ጋዋን 

1ለስልጠና ክፍል ኃላፊዎችና አሰልጣኞች 

የስራ ልብስ ጋዋን 

1ለሰዓት ተቆጣጣሪዎች 

የስራ ልብስ ገዋገን 

1ለዲዛይን ክፍል 

የስራ ልብስ ገዋን 

1ለሴት ፈታሽ 

የስራ ልብስ ገዋን 

1ለሕክምና ሰራተኞች 

የስራ ልብስ ገዋን 

2ለጥበቃ ሰራተኞች 

የስራ ልብስ ኮት ሱሪ፣ ሸሚዝ፣ ከነከረባቱና ኮፍያ 

2ለጥበቃ ሠራተኞች 

ጫማ ከነካልሲው 

2ለጥበቃ ሠራተኞች 

ካፖርት 

-

1


ለጥበቃ ሠራተኞች 

የዝናብ ልብስ 

-

1


ለጥበቃ ሠራተኞች 

የእጅ ባትሪ 

-

-


የጽዳት ሠራተኞች 

የስራ ልብስ ገዋንና ሽርጥ 

1+1የጽዳት ሠራተኞች 

አፍንጫ መሸፈኛ 

2የጽዳት ሠራተኞች 

ላስቲክ ጫማ፣ ከቆዳ የተሰራ ጫማ 

1+1የጽዳት ሠራተኞች 

ጓንት 

2አትክልተኛ 

ቱታ 

1አትክልተኛ 

ጫማ 

1አትክልተኛ 

ቦቲ ጫማ 

1መለስተኛ መኪና ሹፌር 

ቱታ 

1መለስተኛ መኪና ሹፌር 

ጃኬት፣ ሱሪ፣ ሸሚዝ ከነከረባቱ 

1መለስተኛ መኪና ሹፌር 

ቆዳ ጫማ 

1+1ለከባድ መኪና ሹፌር 

ቱታ፣ ጃኬትና ሱሪ

-ለከባድ መኪና ሹፌር 

ብርድ ልብስ፣ ጥንድ አንሶላ ከነትራሱ 

-

1


ለከባድ መኪና ረዳት ሹፌር 

ቱታ 

2

-


ለከባድ መኪና ረዳት ሹፌር 

ጫማ 

2

-


ለከባድ መኪና ረዳት ሹፌር 

ትልቅ የእጅ ባትሪ ከነድንጋዩ 

-

-


32.2. በተመለከተ ባለሙያ የስራውን ፀባይ የሚያስፈልገው ጥናት ከተጠና በኃላ ብዛቱ በሚወሰነው መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ ቀለል ካለ /Light Material/ እንደ ቲ. ሸርት፣ ካናቴራ የመሳሰሉት ሆኖ ከስር የሚለበስ ለሴቶች ቀሚስ ለወንዶች ሱሪ ይሰጣል፡፡ 

33.1. ድርጅቱ ባለው ክሊኒክ አስፈላጊውን የሕክምና መሣሪያዎችና መድሃኒቶች እንዲሟላ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል፡፡ 

33.2. የድርጅቱ ድንገተኛ ህሙማኖች የተሻለ ሕክምና እንዲያገኙ ከግቢ ውጪ በናዝሬት ከተማ ውስጥ ባሉ ድርጅቱ በተስማማባቸው ሆስፒታሎች ሲላኩ ድርጅቱ ውስጥ ባሉ ተሽከርካሪዎ ቅድሚያ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡  

33.3. ለህክምና ወይም ለምርመራ ሠራተኛ ቀርቦ አገልግሎት የሚያገኝበት ዕለትና ሰዓት የፋብሪካው ክሊኒክ ፕሮግራም ያወጣል፡፡ የሕክምና ክፍሉ በመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍት ሆኖ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 

33.4. ወደ ክሊኒክ ለሕክምና የሚላኩ ሠራተኞች ለዚህ ጉዳይ በተዘጋጀው ቅጽ በቅርብ አለቃቸው እየተሞላ ይላካሉ፡፡ 

33.5. በክሊኒኩ ኃላፊ ሠራተኛ የህመም ፍቃድ ሲሰጠው በፍቃድ መስጫ ቅጽ መሠረት ስርጭት ይፈፀማል፡፡ በተጨማሪም ሠራተኛው ወደ ሆስፒታል ሲላክ ክሊኒክ ለሠራተኛ አስተዳደር ያሳውቃል፡፡ ህሙማኑ ወደ ሆስፒታል ስለመላኩ የሥራ ክፍሉም እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡ 

33.6. ድርጅቱ ሆነ ሠራተኛ ማህበሩ በህክምና ባለሙያዎች ሥራ ላይ ጣልቃ በመግባት በሙያቸው ላይ ተፅዕኖ አያደርግም፡፡ 

33.7. በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክሊኒኩ ሁሉንም ሠራተኞች በእኩል ዓይን በመመልከት ያለአድሎ በተሰለፈበት ሙያ በቂ አገልግሎት ሠራተኛው ሁሉ እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡ 

33.8. በበዓላት፣ በሰንበት ዕለትና ፈረቃ በሚሰራበት ጊዜ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሚሰሩት የትርፍ ሰዓታት ከ30 ሠራተኛ በላይ ሲመደብ ክሊኒኩ ክፍት ሆኖ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 

33.9. ድርጅቱም ሠራተኛው በዱቤ እንዲታከም በመንግስት በታወቁ የህክምና ተቋማት ጋር ስምምነት ይዋዋላል፡፡ ይህም ሲልከው ህክምና ይፈፀማል፡፡ 

34.1. በሥራ ሰዓት መውጫና መግቢያ ላይ አደጋ ለደረሰበት ሠራተኛ ድርጅቱ የአንድ ሰዓት ኢንሹራንስ ዋስትና ይገባል፡፡ 

35.1. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ከሥራ ከሚሰናበትበት ወቅት በቅድሚያ በእጅ ያሉትን የድርጅቱን ንብረቶች በሙሉ ለሚመለከተው ክፍል አስረክቦ የነፃ ወረቀት /ክሊራንስ/ ማቅረብ አለበት፡፡ 

35.2. የነፃ ወረቀት ወይም ክሊራንስ ተፈርሞ እንዲቀርብ ለሚሰናበተው ወይም ለሚዛወረው ሠራተኛ ተገቢ የሆነ ክፍያና የምስክር ወረቀት ወዲያውኑ ይሰጣል፡፡ በሚሰጠው የምስክር ወረቀት የሠራተኛው ጉርድ ፎቶግራፍ የተለጠፈ ሆኖ፣ 

ሀ. ይሰራው የነበረው የሥራ መደብና ዓይነት በዝርዝር 

ለ. የአገልግሎት ዘመን 

ሐ. ይከፈለው የነበረው ደመወዝና ሌላም ጥቅም ካለ መጠኑን 

መ. በድርጅቱ ውስጥ ባገለገለበት ጊዜ ከወር ገቢ ላይ የከፈላቸው የታክስ ክፍያዎች ተገልፀው በሚመለከተው ባለሥልጣን ተፈርሞ ይሰጠዋል ወይም ይሰጣታል፡፡ 

36.1. ለዋና ገንዘብ ያዥ የሳጥን መጠባበቂያ ድርጅቱ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በየወሩ ይከፍላል፡፡ 

36.2. ከላይ ከአንቀጽ 36.1 የተዘረዘረው ክፍያ ተፈፃሚ የሚሆነው በማያዣነት አንድ ዓመት ከተጠራቀመ በኃላ ነው፡፡ 

37.1. ሠራተኛው የማህበር አባል ለመሆን የጠየቀበትን የጽሑፍ ማረጋገጫ ማህበር በሸኚ ደብዳቤ ለአስተዳደር ሲያቀርብ የማህበሩ የአባልነት መዋጮ ድርጅቱ ከሠራተኛው ደመወዝ ላይ በየወሩ እየሰበሰበ ደመወዝ በተከፈለ 15 ቀን ባልበለጠ ለማህበሩ በቼክ /በጥሬ ገንዘብ/ ይከፍላል፡፡ 

37.2. አሰሪው ለሰራተኛው ማህበሩ በኩል ለሚቋቋመው ለገንዘብ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ዕድርና ለመሳሰሉት ከሰራተኛው የወር ደመወዝ ለሚቀነሱ ተቀናናሾች በአንቀጽ 37.1 መሠረት ለየማህበራቱ ገቢ ያደርጋል፡፡ 

37.3. ማንኛውም ሠራተኛ የማህበሩን መዋጮ ላለመክፈል ሲፈልግ ለድርጅቱና ለማህበሩ በጽሁፍ ያሳውቃል፡፡ 

37.4. በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 59.1 እና 2 የደመወዝ መጠን ቅነሳን ተግባራዊ ይሆናል፡፡ 

38.1. የመብት ጥያቄ በተመለከተ ስለሚቀርቡ የጊዜ ገደብና ጥያቄዎች በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

39.1. በድርጅቱና ሠራተኛ ማህበሩ በህብረት ስምምነት የሚያወጧቸውን የሠራተኞች ደንቦች በዚህ ስምምነት ውስጥ ከተወሰኑት በላይ ለሠራተኛው የበለጠ ጥቅም የሚሰጠው ሆኖ ከተገኘ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

39.2. ህብረት ስምምነቱ ተመዝግቦ ወጪ ሆኖ ስራ ላይ በሚውለው ወይም ስራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የመንግስት መመሪያና ፖሊሲ የሚጥስ ሕገ ወጥም ህግ የሚቃረን ቃል ሐረግ ወይም ዐረፍተ ነገር ሲገኝበት ይኸው ቃል ሐረግ ወይም ዐረፍተ ነገር ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ 

39.3. ድርጅቱና ሠራተኛ ማህበር ተባብረው የህብረት ስምምነት ህጋዊ ሆኖ እንዲፀድቅና ከፀደቀ በኃላ በትክክል በተግባር እንዲተረጎም ያደርጋል፡፡ 

39.4. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ሁሉ የዚህ ህብረት ስምምነት መንፈስ ተረድቶ የመፈፀምና የማስፈፀም ግዴታ አለበት፡፡ 

39.5. የህብረት ስምምነት ተፈጻሚነት በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 134 ቁጥር 1 እና 2 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

40.1. ድርጅቱም ወይም አሰሪው ስፖርትን ለማጠናከር የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ያደርጋል፡፡ 

40.2. ድርጅቱ ለስፖርተኞች የውድድር ጊዜ ፍቃድ ይሰጣል፡፡ 

40.3. በሠራተኛ ማህበር አማካኝነት ለሚቋቋመው የስፖርት ኮሚቴ ድርጅቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ 

40.4. ስፖርትን ለማጠናከርና ለማዳበር ሲባል 

1. ድርጅቱ 

2. ማህበሩ 

3. ጠቅላላ የድርጅቱ ሠራተኞች በኮሚቴው ለሚጠየቁ እርዳታ እንደአስፈላጊነቱ ይተባበራል፣  

40.5. ድርጅቱ ወይም አስሪው በውድድር ጊዜ ለስፖርተኞች መጓጓዣ መኪና ያቀርባል፡፡ 

41.1. በማንኛውም ሁኔታ ከ30 ቀናት የሚበልጥ ጊዜ በፍርድ የእስራት ፍርድ የተወሰነበት ሠራተኛ በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

41.2. ድርጅቱ በግል ከሶ ላሳሰራቸው ሠራተኞች ጥፋተኞች ሆነው ካልተገኙ ነፃ ሆነው ከተመለሱ በፍ/ቤት ውሳኔ መሰረት አስፈላጊው ይፈፀማል፡፡  

42.1. ድርጅቱና ሠራተኛው በሚመለከት የስራ ሁኔታ ወይም ጉዳዮች ላይ ከሁለት ወገን አንደኛውን ሲጠይቅ የሁለቱም ወገን ህጋዊ ተጠሪዎች የጋራ ስብሰባ እያደረጉ የሚፈጠረው ችግር ያስወግዳሉ፡፡   

42.2. አስቸኳይ ጉዳዬች በሚፈጠሩበት ወቅትና በማንኛውም ወገን ጠያቂነት በማንኛውም ጊዜና ሠዓት በማመቻቸት የጋራ ስብሰባ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ 

42.3. ሁለቱም ወገኖች ተወያይተው የተስማሙባቸው ጉዳዬች በጽሑፍ ሰፍረው በሁለቱም ፊርማ ይፀድቃሉ፡፡ 

43.1. የትርፍ ሰዓት ቁጥር 377/96 አንቀጽ 66፣ 67 እና 68 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

43.2. ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በትርፍ ሰዓት እንዲሰሩ ለሚመደቡ ሠራተኞች ድርጅቱ የሰርቪስ አገልግሎት ያቀርባል፡፡ 

 

44.1. የፋብሪካው የስራ ሰዓት በሳምንቱ ውስጥ ባሉት ቀናት ተደልድሎ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

ሀ/ ለፋብሪካ ሰራተኞች 

ተ.ቁ

የሳምንቱ የስራ ቀናት

መግቢያ መውጫ ጠዋት

መግቢያ መውጫ ከሰዓት

በቀን የሥራ ሰዓት

1

ከሰኞ - አርብ 

1፡30 – 6፡00 

6፡30 – 9፡30 

7፡30 

ቅዳሜ ግማሽ ቀን 

1፡30 – 6፡30 


5፡30

 

ለ/ ለቢሮ ሰራተኞች ከሰኞ እስከ አርብ፡- የመግቢያ ሰዓት ጠዋት 1፡30 – 6፡00 

  ከሰዓት 7፡00 – 11፡00 

 • የዕረፍት ሰዓት ጠዋት በ4፡00 15 ደቂቃ 

  ከሰዓት በ9፡00 15 ደቂቃ 

44.2. የሽያጭ ሱቅ ሠራተኞች የስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሆኖ የንግድ መምሪያ በሚያወጣው የስራ መርሀ ግብር መሰረት ይሆናል፡፡ 

44.3. የጽዳት ሠራተኞች የስራ ሰዓት 

- አስተዳደር መምሪያ በሚያወጣው የስራ መርሃ ግብር መሰረት ይሆናል፡፡ 

44.4. የጥበቃ ሠራተኞች የስራ ሰዓት በተመለከተ አስተዳደር መምሪያ በሚያወጣው መምሪያ መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡ 

44.5. በሳምንት የዕረፍት ቀን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 69 ከተራ ቁጥር 1-3 ባሉት መሰረት ይፈፀማል፡፡ 

45.1. ከስራ ሰዓት ውጪ በድንገተኛ ህመም፣ በዓመት ፍቃድ ላይ ወይም ከናዝሬት ከተማ ውጪ ክሊኒክ ለማግኘት በማይችልበት ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሠራተኛ ከስራ ጋር ግንኙነት በሌለው በሽታ በራሱ ወጪ ሕክምናው ፈጽሞ ለሕክምና የከፈለበት ደረሰኝ ሲያቀርብ 

አንቀጽ 46 (አርባ ስድስት)

46. የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ

46.1. በአንድ ዓመት ውስጥ በድርጅቱ የተገኙ የተጣራ ትርፍ ምክንያት ሠራተኛው በነበረው ደመወዝ ላይ የእርከን ጭማሪ እና ቦነስ በሚመለከት ይሆናል፡፡ 

ሀ. ማንኛውም ሠራተኛ ድርጅቱ ከሚያገኘው የተጣራ ትርፍ ጭማሪ ሲደረግ የዓመቱ የሥራ አፈፃፀም መመዘኛ (ኢቫሊዮሽን) ታይቶ የሚጨመር ይሆናል፡፡ 

ለ. ማንኛውም ሠራተኛ ድጋፍ እየተደረገለት ኃላፊነት የማይሰማው የመመዘኛ ነጥቡ ከ2.0 በታች ያገኘ ጭማሪ አያገኝም፡፡ 

ሐ. መመዘኛ ነጥቡ ከ2.0 እስከ 2.49 ያገኘ ሠራተኛ የሚያገኘው የጭማሪው ግማሽ ይሆናል፡፡ 

መ. መመዘኛ ነጥቡ ከ2.5 በላይ ያገኘ ሠራተኛ ሙሉ ጭማሪ ያገኛል፡፡ 

ከላይ የተቀመጠው የመመዘኛ ነጥብ ከግምት ውስጥ ገብቶ ድርጅቱ የተጣራ ትርፍ ከአገኘ ቀጥሎ የተቀመጡትን ማበረታቻዎች ይሰጣል፡፡ 

ተ.ቁ

የተጣራ ትርፍ በገንዘብ

የሚሰጥ የደመወዝ ጭማሪ በእርከን መሰረት

በደመወዝ ልክ የሚሰጥ ቦነስ

1

3 ሚሊዮን ትርፍ ካገኘ 


የአንድ ወር ደመወዝ ያገኛል 

2

4 ሚሊዮን ትርፍ ካገኘ 


የአንድ ወር ከግማሽ ደመወዝ ያገኛል 

3

5 ሚሊዮን ትርፍ ካገኘ 

አንድ እርከን ጭማሪ 

የግማሽ ወር ደመወዝ ያገኛል 

4

7 ሚሊዮን ትርፍ ካገኘ 

አንድ እርከን ጭማሪ 

የአንድ ወር ደመወዝ ያገኛል 

5

9 ሚሊዮን ትርፍ ካገኘ 

አንድ እርከን ጭማሪ 

የሁለት ወር ደመወዝ ያገኛል 

ድርጅቱ 80% ወጪውን ይከፍልለታል፡፡ በተጨማሪም የፋብሪካው ክሊኒክ ውስጥ ለሚሰጥ የመጀመሪያ ዕርዳታ ወጪውን አሰሪው ይሸፍናል፡፡ ሆኖም በክሊኒክ የታዘዘው መድሃኒት ከፋብሪካው ወጪ ከተገዛ ድርጅቱ የመድሃኒቱን ዋጋ 80% ይሸፍናል፡፡ 

አንቀጽ 47 /አርባ ሰባት/

47. የኤች አይ ቪ 

47.1. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ በኤች አይ ቪ /ፖዘቲቭ/ የሆነ የመስራት አቅሙ የደከመ መሆኑ በሐኪም ሲረጋገጥ ቀላል ስራ ወዳለበት ተዘዋውሮ ይሰራል፡፡ 

47.2. የድርጅቱ ሠራተኛ በየወሩ በደመወዝ ጊዜ 0.50 ሣንቲም በማዋጣት በድርጅቱ ውስጥ ለሚገኙ በኤች አይ ቪ ለተጎዱ ወገኖች ይሰጣል፡፡ 

47.3. ድርጅቱ ለኤች አይ ቪ ህሙማን መደገፊያ አጠቃላይ ሠራተኛው በሚያወጣው ልክ ለማዋጣት ተስማምቷል፡፡ 

47.4. የእርዳታው አፈፃፀም በድርጅቱና በሠራተኛው ማህበሩ በሚደረገው ስምምነት ይሆናል፡፡  

አንቀጽ 48 /አርባ ስምንት/

48. ጡረታ 

48.1. አንድ ሰራተኛ ከድርጅቱ በሰላም የጡረታ መብቱ ተከብሮለት ከወጣ የአንድ ወር ደመወዝ ድርጅቱ ይሸልመዋል፡፡ 

48.2. ፋብሪካው ዕድሜአቸው የጡረታ መብት ላላቸው ሠራተኞች የጡረታ መውጫ ጊዜ ከመድረሱ ከሶስት ወር በፊት የጡረታ አበል መቀበያ ቅጽ አዘጋጅቶ ከአስፈላጊ ማስረጃ ጋር ለጡረታና መተዳደሪያ ዋስትና ድርጅት ይልካል፡፡ ሠራተኛው ማቅረብ የሚገባው ማስረጃ ባለመቅረቡ ለሚፈጠረው የመዘግየት ኃላፊነት ፋብሪካው አይጠየቅም፡፡ 

48.3. ሠራተኛው የጡረታ ዕድሜው ደርሶ ማግኘት የሚገባውን ሳያገኝ የድርጅቱ ችግር ከሆነ ሠራተኛው ጉዳዩ እስከሚስተካከል ድረስ ሠራተኛው ያገኝ የነበረው ደመወዝ ያገኛል፡፡ 

48.4. ፋብሪካው ዕድሜአቸው የጡረታ መብት ላላቸው ሠራተኞች የጡረታ መውጫ ጊዜ ከመድረሱ ከሶስት ወር በፊት የጡረታ አበል መቀበያ ቅጽ አዘጋጅቶ ከአስፈላጊ ማስረጃ ጋር ለጡረታና መተዳደሪያ ዋስትና ድርጅት ይልካል፡፡ ሠራተኛው ማቅረብ የሚገባው ማስረጃ ባለመቅረቡ ለሚፈጠረው የመዘግየት ኃላፊነት ፋብሪካው አይጠየቅም፡፡ 

48.5. ሠራተኛው የጡረታ ዕድሜው ደርሶ ማግኘት የሚገባውን ሳያገኝ የድርጅቱ ችግር ከሆነ ሠራተኛው ጉዳዩ እስከሚስተካከል ድረስ ሠራተኛው ያገኝ የነበረው ደመወዝ እየሰራ ያገኛል፡፡ 

አንቀጽ 49 /አርባ ዘጠኝ/

49. የሥነ ሥርዓት እርምጃ 

49.1. ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሚያስወጡ እርምጃዎች፣ 

49.1.1. በሥራ ሰዓት በምድብ ስራው ላይ ሰክሮ የተገኘ ሠራተኛ ይህን በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.2. በሳምንት 5 ቀን በተከታታይ በማንኛውም ጊዜ በወር 10 ቀን በዓመት 30 ቀን ያለበቂ ምክንያት ከስራ የቀረ ሠራተኛ ወይም በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.3. ማንኛውም ሠራተኛ በስራ ቦታና ከድርጅቱ ክልል ውስጥ እንዲሁም ከስራ ጋር ግንኙነት ባለው የፀብ መንስኤ ተደባድቦ ቢገኝና በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.4. የድርጅቱ ገንዘብ ወይም ንብረት ያለአግባብ ለግል ጥቅሙ ያዋለ ወይም ለሌላ ሰው ማስተላለፉ በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.5. ማንኛውም የድርጅቱ ሀብት ይዞ ወይም ደብቆ ሲወጣ ቢገኝ ይህን በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.6. የሀሰት ሰነዶችን የሚያቀርቡ፣ ወይም የምስክር ወረቀቶችን ደልዞ፣ ሰርዞ ማቅረቡ በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.7. በማንኛውም የድርጅቱ ወይም የአሰሪው ንብረት ላይ ሆን ብሎ አደጋ ላይ የጣለ ወይም አደጋ ላይ ለመጣል የሞከረ እና ይኸው በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.8. ልዩ ልዩ የድርጅቱ ወይም የአሰሪው ንብረት ላይ ሆን ብሎ የለአግባብ ብልሽት ማድረሱ በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.9. ሆን ብሎ የድርጅቱ የምርት ውጤት ገበያ እንዳያገኝ ደህናውን ከመጥፎ በማደባለቅና እንዲሁም ጉድለት የሌላቸውን የድርጅቱን ምርቶች ገበያ እንዳያወጡ ማድረግ በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.10. በተከለከለ ቦታ ሲጋራም ሆ እሳት ያነደደ ይህም በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.11. አንድ ሠራተኛ ሌላውን ሠራተኛ ሆን ብሎ ለመጉዳት በሀሰት ቃሉን የሰጠ ወይም የመሰከረ ወይም ውዥንብር የፈጠረ ይህም በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.12. በዘብ ስራ ላይ ተሰማርቶ የድርጅቱን ንብረት ሲወጣ በቸልተኝነት የተመለከተ ይህም በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.13. በዘብ ስራ ላይ ተሰማርቶ እያለ ተኝቶ የተገኝ ዘበኛ በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.14. ሠራተኛውን በተሳሳተ አመለካከት ውዥንብር በመንዛት የድርጅቱ ህልውና አደጋ ላይ ያደረሰና ይህም በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.15. አንድ ሠራተኛ ለተመደበበት ሥራ አልተሠራም ብሎ እንቢተኛ ከሆነና እንቢተኝነቱ በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 

49.1.16. በዚህ ህብረት ስምምነት የተጠቀሱትን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 የተጠቀሱትን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብቱ ምክንያቶች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡  

አንቀጽ

የጥፋት ዓይነቶች

1ኛ ቅጣት

2ኛ ቅጣት

3ኛ ቅጣት

4ኛ ቅጣት

5ኛ ቅጣት

50.9 

በስራ ጊዜ ከስራው ጋር ባልተያያዘ ምክንያት በድርጅቱ ውስጥ ለድርጅቱ ቅጥር ግቢና በስራ ላይ ማንኛውም የድብደባ ተግባር የፈፀመ 

ለ3 ቀን የስራ እገዳና ተጣርቶ ሰንብት 

50.10 

በስራ ላይ ሆኖ ህገ ወጥ ፀባይ የሚያሳይ 

ለ1 ቀን ስራ እገዳ 

ለ3 ቀን ስራ እገዳ 

ለ5 ቀን የስራ እገዳና የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 


50.11 

ቅጣትም ሆነ ማንኛውም ዓይነት ድርጅቱ የሚሰጠውን ደብዳቤ አልቀበልም የሚል ሠራተኛ 

ከስራ ታግዶ እስከ 3 ቀን ደብዳቤ ካልተቀበለ ከስራ ይሰናበታል 

በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ሁኔታ በድጋሚ ደብዳቤ ካልተቀበለ በዕለቱ ይሰናበታል  
50.12

ካርዱን አውጥቶ ወይም ፈርሞ ከቅጥር ግቢ ውጪ ያለበቂ ምክንያት ወይም ያለፍቃድ የወጣና ይህም በማስረጃ ሲረጋገጥ 

የ3 ቀን የስራ እገዳ 

ለ5 ቀን ከስራ እገዳና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 50.13 

መፈተሽ አስፈላጊ ሆኖ በጥበቃዎች እዲፈተሽ ሲጠየቅ ፍቃደኛ ያልሆነ ሠራተኛ በማስረጃ ሲረጋገጥ 

የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 
50.14 

በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ለመፀዳዳት ተብሎ ከተመደበው ውጪ ሲፀዳዳ የተገኘ ሠራተኛ 

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ1 ቀን የስራ እገዳ 

የ2 ቀን የስራ እገዳና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 


50.15. 

የጦር መሳሪያ ወይም ሰው ለመጉዳት ስለት ይዞ የተገኘ ሠራተኛ ይህም በማስረጃ ሲረጋገጥ  

ከኤግዚቢቱ ጋር ለፖሊስ ማስረከብና ስንብት 

50.16

ለምርት አስፈላጊ ሳይሆን በምርት አካባቢ መርዛማ የሆኑ ኬሚካሎ ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሠራተኛ በማስረጃ ሲረጋገጥ 

ከኤግዚቢቱ ጋር ለፖሊስ ማስረከብና ስንብት 

50.17.

ከሳምንት የዕረፍት ጊዜ ውጪ ያለበቂ ምክንያት የትርፍ ሰዓት ስራ ታዞ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ፍቃደኛ ያልሆነ ሠራተኛ   

የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ 

የ1 ቀን የስራ እገዳ 

የ2 ቀን የስራ እገዳ 

የ3 ቀን የስራ እገዳና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 

50.18 

በቅርብ አለቃው በግልጽ የሚሰጠውን ስራና የስራ ትዕዛዝ ተቀብሎ በተገቢ መንገድ የማያከናውን 

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ1 ቀን ከስራ እገዳ 

የ2 ቀን ከስራ እገዳና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 


50.19

አፀያፊ ስድብ የተሳደብና በማስረጃ ሲረጋገጥ 

የ1 ቀን ከስራ እገዳ 

የ2 ቀን ከስራ እገዳና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 50.20

ሳይፈተሸ በእንቢተኝነት የወጣ ሠራተኛ 

እንቢተኝነቱ ተጣርቶ ሲረጋገጥ ስንብት 

50.21

ካርዱን ሳያወጣ ወደ ስራ የገባ ሰራተኛ በትክክል መግባቱ በክፍሉ ከተረጋገጠ 

የቃል ማስጠንቀቂያ 

የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ 

1ቀን ከሥራ እገዳ 

2ቀን ከሥራ እገዳና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት አንቀጽ 51 /ሃምሳ አንድ/

51. የትራንስፖርት 

51.1. ሰርቪስን በተመለከተ ድርጅቱና ሰራተኛው በጋራ ተወያይተው መፍትሔ ይሰጣሉ፡፡ 

አንቀጽ 52 /ሃምሳ ሁለት/

52. የውል ተፈፃሚነት 

52.1. ይህ ህብረት ስምምነት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 134 በተራ ቁጥር 2 መሰረት ተፈፃሚ ይሆና፡፡ 

አንቀጽ 53 /ሃምሳ ሶስት/ 

53. ይህ ህብረት ስምምነት የሚፀናበት ጊዜ 

53.1. ይህ ህብረት ስምምነነት ተደራዳሪዎች ከተፈራረሙበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ ይውላሉ፡፡ 

53.2. ይህ ህብረት ስምምነት ፀንቶ የሚቆየው የጊዜ ገደብ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 133 ተራ ቁጥር 3 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

ማሳሰቢያ፡- የድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በዚህ ህብረት ስምምነት እና ደንቦች ያልተሸፈኑ ህጎችን የጣሰ ወይም የዲሲፕሊን ግድፈት የፈፀመ ሠራተኛ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

  ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ  የፋብሪካው የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር 


 _____________________ _____________________

    አቶ ደረጀ ጌታሁን  አቶ ንጉሱ ተክሉ 

ተወካይ ተደራዳሪዎች

በድርጅቱ በኩል     በማህበር በኩል 

 1. አቶ ደረጀ ጌታሁን _____________ 1. አቶ ንጉሴ ተክሉ _____________
 2. ኮሎኔል ታከ ሞላ ______________ 2. አቶ አበራ ደንቦባ _____________

3. ደባልቄ ታዬ ________________

ናዝሬት ልብስ ስፌት - 2005

Start date: → 2005-04-01
End date: → Not specified
Name industry: → Manufacturing (no translation found)
Name industry: → አልባሳት ማምረት
Public/private sector: → In the private sector
Concluded by:
Name company: →  ናዝሬት ልብስ ስፌት
Names trade unions: →  የናዝሬት ልብስ ስፌት ሠራተኛ ማህበር

TRAINING

Training programmes: → Yes
Apprenticeships: → No
Employer contributes to training fund for employees: → Yes

SICKNESS AND DISABILITY

Maximum days for paid sickness leave: → 180 days
Provisions regarding return to work after long-term illness, e.g. cancer treatment: → No
Paid menstruation leave: → No
Pay in case of disability due to work accident: → Yes

WORK/FAMILY BALANCE ARRAGEMENTS

Maternity paid leave: → 13 weeks
Maternity paid leave restricted to 100 % of basic wage
Job security after maternity leave: → No
Prohibition of discrimination related to maternity: → Yes
Prohibition to oblige pregnant or breastfeeding workers to perform dangerous or unhealthy work: → 
Workplace risk assessment on the safety and health of pregnant or nursing women: → 
Availability of alternatives to dangerous or unhealthy work for pregnant or breastfeeding workers: → 
Time off for prenatal medical examinations: → 
Prohibition of screening for pregnancy before regularising non-standard workers: → 
Prohibition of screening for pregnancy before promotion: → 
Facilities for nursing mothers: → No
Employer-provided childcare facilities: → No
Employer-subsidized childcare facilities: → No
Monetary tuition/subsidy for children's education: → No
Leave duration in days in case of death of a relative: → 3 days

GENDER EQUALITY ISSUES

Equal pay for work of equal value: → No
Discrimination at work clauses: → No
Equal opportunities for promotion for women: → No
Equal opportunities for training and retraining for women: → No
Gender equality trade union officer at the workplace: → No
Clauses on sexual harassment at work: → No
Clauses on violence at work: → Yes
Special leave for workers subjected to domestic or intimate partner violence: → No
Support for women workers with disabilities: → No
Gender equality monitoring: → No

EMPLOYMENT CONTRACTS

Trial period duration: → 45 days
Part-time workers excluded from any provision: → No
Provisions about temporary workers: → No
Apprentices excluded from any provision: → No
Minijobs/student jobs excluded from any provision: → No

WORKING HOURS, SCHEDULES AND HOLIDAYS

Working hours per day: → 7.5
Working days per week: → 6.0
Paid annual leave: →  days
Paid annual leave: →  weeks
Fixed days for paid annual leave: → 13.0 days
Rest period of at least one day per week agreed: → Yes
Provisions on flexible work arrangements: → No

WAGES

Wages determined by means of pay scales: → No
Adjustment for rising costs of living: → 

Wage increase

Once only extra payment

Once only extra payment due to company performance: → Yes

Premium for overtime work

Allowance for commuting work

Meal vouchers

Meal allowances provided: → No
Free legal assistance: → 
 
Loading...