በባህር ዳር ጨርቃጨርቅ አ/ማህበር እና በባ/ዳር ጨ/ጨ/አ/ማህበር መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር መካከል ለ19ኛ ጊዜ የተደረገ የህብረት ስምምነት

Untitled Document

አንቀጽ 1

የስምምነት ዓላማ፡-

የዚህ ህብረት ስምምነት ዋና ዓላማ በአ/ማህበሩና በሠራተኛው መካከል የኢንዱስትሪ ሠላምን ለማስፈን እንዲቻል የሥራ ሁኔታዎችንና የሥራ ግንኙነቶችን በመወሰን የአክሲዮን ማህበሩንና የሠራተኛውን መብት እንዲከበር በማድረግ ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ነው፡፡

አንቀጽ 2

ትርጉም

2.1 በዚህ ስምምነት ውስጥ አዋጅ ፡- ማለት የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና ወደፊት ከላይ የተጠቀሱትን ተክቶ የሚወጣ አዋጅ ወይም ደንብ ማለት ነው፡፡

2.2 ሕጐች ወይም መመሪያዎች ፡- ማለት መንግስት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ላይ ያወጣቸውንና ወደፊት የሚያወጣቸውን ሕጐችና የማስፈፀሚያ ደንቦች ማለት ነው፡፡

2.3 ቦርድ ፡- ማለት የጥረት ኮርፖሬት ሥራ አመራር ቦርድ ማለት ነው፡፡

2.4 የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ፡- ማለት በክልሉ የተቋቋመው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳዮችን የማየትና የመወሰን ስልጣን የተሠጠው አካል ነው፡፡

2.5 አ/ማህበር ፡-
ማለት የባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ነው፡፡

2.6 የሠራተኛ ማህበር ፡-
ማለት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት የተደራጀው የባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ማለት ነው፡፡

2.7 ሠራተኛ ፡- ማለት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በተመለከተው መሠረት ከአሠሪው ጋር በቅጥር ላይ የተመሠረተ የሥራ ግንኙነት ያለው ግለሠብ ነው፡፡

2.8 አዲስ የሥራ መደብ ፡- ማለት ለአክሲዮን ማህበሩ እድገት፣ መስፋፋት፣ እንዲሁም የሥራ መቃናት አስፈላጊ ሆኖ በጥናት የሚከፈትና በዚህ ኀ/ስምምነት ውስጥ የሚመዘገብ አዲስ የሥራ መደብ ማለት ነው፡፡

2.9 የእድገት መስጫ ማወዳደሪያ ሚዛን ፡- ማለት በአ/ማህበሩ ውስጥ በሚፈጠር የክፍት የሥራ መደብ ላይ ሠራተኞችን በእድገት ለመመደብ ችሎታቸው የሚመዘንበት ነው፡፡

2.10 የሥራ መደብ ለውጥ ፡- ማለት አንድ ሠራተኛ የነበረበት የሥራ መደብ ለጤንነቱ የማይስማማ መሆኑ በሐኪም ቦርድ ሲረጋገጥለት ወይም የሥራ መደብ ለውጥ የጠየቀው ሠራተኛ ያቀረበው ሃሳብ በአክሲዮን ማህበሩ ተቀባይነት ካገኘ ወይም በዲስፕሊን ጉድለት ሠራተኛውን ከነበረበት የሥራ መደብ አንስቶ ወደ ሌላ ቦታ መመደብን ያጠቃልላል፡፡ በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ሠራተኛው የሚመደብበት የሥራ መደብ ነው፡፡

2.11 ዝውውር ፡- ማለት ለሥራው ወይም ለሠራተኛው ደህንነት ሲባል ሠራተኛው ከነበረበት የሥራ መደብ ወይም ተመሳሳይ ደረጃ ወደ አለው ሌላ የሥራ ክፍል የሚዛወርበት ነው፡፡

2.12 መነሻ ደመወዝ ፡- ማለት ለአንድ የሥራ መደብ በፀደቀው መዋቅር መሠረት ለስራ መደቡ የተሰጠው መነሻ ደመወዝ ነው፡፡

2.13 ቀድሞ ያልታዩ ጉዳዮች ፡- ማለት አስቀድሞ ተጠንቶ በዚህ ህብረት ስምምነት በግልጽ ያልተብራራ ድንገተኛ ጉዳይ ማለት ነው፡፡

2.14 የወል የሥራ ክርክር ፡- ማለት በአዋጅ 1156/2011 በአንቀጽ 143 ከፊደል ሀ-ሸ የተዘረዘሩትን ያጠቃለለ ነው፡፡

2.15 የግል የሥራ ክርክር ፡- ማለት በአዋጅ 1156/2011 በአንቀጽ 139 በክልል የመጀመሪየ ደረጃ ፍ/ቤት የሥራ ክርክር ችሎት የሚቀርቡትን ከተራ ቁጥር 1 ከሀ - ረ በተጠቀሱት ምክንያት የሚነሱ ክርክሮችን ማለት ነው፡፡

2.16 ቋሚ ሠራተኛ ፡- ማለት ላልተወሰነ ጊዜ በአ/ማህበሩ የተቀጠረ ሠራተኛ ማለት ነው፡፡

2.17 የኰንትራት ሠራተኛ ፡- ማለት የተወሰነ ሥራን በተወሰነ ጊዜ ለማከናወን የተቀጠረ ሠራተኛ ማለት ነው፡፡ ይህ ውል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሥራውም ካልተተጠናቀቀ በሁለቱ ተዋዋዮች ስምምነት ሊራዘም የሚችል ነው፡፡

2.18 ጊዜያዊ ሠራተኛ ፡- ማለት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 1ዐ በቁጥር 1 በፊደል “ ሸ “ እና “ቀ“ ላይ የተጠቀሱትን ሥራዎች ለመሸፈን ከ45 ቀናት ላልበለጠ የተቀጠረ ሠራተኛ ማለት ነው፡፡

2.19 መዋቅር ፡- ማለት በባለሙያ ተጠንቶ የፀደቀው የአክሲዮን ማህበሩ የሰው ኃይል ብዛት፣ ደመወዝ፣ የሥራ መደብ ፣ ደረጃና የመስፈርቶችን የሥራ መመሪያ የያዘ ማለት ነው፡፡

2.20 የደመወዝ ስኬል ማለት ፡- አ/ማህበሩ ወደ ጎን እድገት የሚሰጥበት ወይም ቦነስና የደመወዝ ጭማሪ የሚደርግበት ለየሥራ መደቡ የተፈቀደ የገንዘብ መጠን ማለት ነው

2.21 አሠሪ ፡- ማለት የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 2 ንዑስ ቁጥር 1 ላይ የተሰጠውን ትርጉም ይይዛል፡፡

አ ን ቀ ጽ 3

የስምምነቱ ተፈፃሚነት ወሰን፡-

ይህ ስምምነት በአ/ማህበሩ ውስጥ ላልተወሰነ ጊዜ ተቀጥረው በሚሠሩት ሠራተኞች ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለማንኛውም አገልግሎት ለተወሰነ ሥራ በተቀጠረና በትርፍ ጊዜው ወይም ለተወሰነ ቀናት ራሱን ችሎ የተወሰነ ሥራ በተለየ ስምምነት ለመሥራት በተቀጠረ ሰው ላይ ተፈፃሚነት የለውም፡፡

አ ን ቀ ጽ 4

የአሠሪው መብትና ግዴታ

ሀ/ የአሠሪው መብት

4.1.1 በዚህ ህብረት ስምምነት ላይ ከተጠቀሱት ጉዳዮች በተጨማሪ ማንኛውም የአ/ማህበሩን ሥራ የማቀድ፣ የመምራት፣ የመቆጣጠር፣ ሠራተኛን በየሥራ መደቡ የመመደብና በበቂ ምክንያት ከቦታ ወደ ቦታ የማዘዋወር መብቱ የአክሲዮን ማሕበሩ ነው፡፡

4.1.2 በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 የተጠቀሱትን ሁሉ ተግባራዊ የማድረግና በህብረት ስምምነቱ በተቀመጠው መሠረት እርምጃ የመውሰድ የአ/ማህበሩ መብት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በየክፍሉ ያሉ የሆርሻ ተጠሪዎች በቅጣት ፎርሙ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ፣ አክሲዮን ማህበሩም የወሰደውን እርምጃ ለመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ በግልባጭ ያሳውቃል።

4.1.3 አዲስ መደብ የመክፈት፤ አስፈላጊነቱን የመወሰን፣ በየሥራው አስፈላጊውን የሠራተኛ ኃይል ብዛት የመወሰን፣ በየሥራው የሚፈለገውን የት/ደረጃና የሥራ ልምድ የመወሰን፣ አዲስ ሠራተኛ በሕጉ መሠረት የመቅጠር፣ በዚህ የህብረት ስምምነት መሠረት ተወዳድሮ ላለፈ ሠራተኛ የደረጃ እድገት የመስጠት፣ ለሚወሰዱ የስነ ስርዓት እርምጃዎች ይቅርታ የማድረግ ወይም የማሻሻል መብቱ የአክሲዮን ማህበሩ ነው፡፡

4.1.4 ስለ አ/ማህበሩ ንብረትና ሀብት እንዲሁም ስለ አክሲዮን ማሕበሩ የሥራ ሁኔታዎች ጉዳይ ከሌላ ወገን ጋር የመነጋገር፣ ስለ ዕቃ ግዥና ሽያጭ የመዋዋል፣ ኢንሹራንስ የመግባት፣ ሌላም አስፈላጊ የሆነ ውል የመግባት፤ በአክሲዮን ማሕበሩ ስም የመከሰስና የመክሰስ መብትና ግዴታ የአክሲዮን ማሕበሩ ነው፡፡

4.1.5 ውክልና የመስጠት መብት የአክሲዮን ማህበሩ ነው፡፡ የውክልና አሰጣጡ ሂደት መወከል የሚያስፈልገው መምሪያ/አገልግሎት ክፍት ቦታውንና ለቦታው ተቀራራቢ ሙያና ልምድ ያለውን ሠራተኛ በመግለጽ ለዋና ስራ አስኪያጅ ወይም ለም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ያቀርባል ሥራ አስኪያጅ ከሰው/ሃ/ል/አስ/መምሪያ ጋር በመነጋገር ውክልና ይፈቅዳል፡፡

4.1.6 በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር የአክሲዮን ማሕበሩን ሥራና ሠራተኛን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ሁሉ መግለጫ፣ ማስታወቅያና የትምህርት ኘሮግራም የሚያወጣ አክሲዮን ማሕበሩ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ሠራተኛ ማህበሩ እና በማሕበሩ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች መግለጫ ለመስጠትም ሆነ ማስታወቂያ ለማውጣት ከፈለጉ ጥያቄው ለማሕበሩ ቀርቦ ማሕበሩም ጥያቄውን ለማኔጅመንቱ አቅርቦ ሲፈቀድ በሕግ የተደገፈ መግለጫና ማስታወቂያ ማውጣት ይችላሉ፡፡

4.1.7 አንድ ሠራተኛ ከፍተኛ የዲሲኘሊን ስህተት ከፈጠረና እስኪጣራ ድረስ የግለሰቡ በሥራ ላይ መቆየት ጉዳት ያለው ሆኖ አ/ማህበሩ ከአገኘው ለአንድ ወር ሠራተኛውን ያለ ደመወዝ ከሥራው ሊያግደው ይችላል፡፡ በመጨረሻም በሚደረገው ማጣራት ግለሰቡ ጥፋተኛ ሳይሆን ወይም ጥፋቱ ለመታገድ የማያበቃው ሆኖ ከተገኘ የታገደበት የወር ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ግን ደመወዙ አይከፈለውም ይህም እንደ ቅጣት አይቆጠርለትም ።

4.1.8 አክሲዮን ማሕበሩ ለሠራተኛው የመታወቂያ ደብተር ለመጀመሪያ ጊዜ በነፃ ይሠጣል፡፡ ሆኖም ጠፋብን ብለው በድጋሚ ለሚጠይቁ ያሳተመበትን ሂሳብ ከሠራተኛው ላይ የመጠየቅ መብት አለው፡፡

4.1.9 ያለ አግባብ የደመወዝ ብልጫ ጭማሪ የተሠጠው ሠራተኛ ሲያጋጥመው ደመወዙ ከተጨመረበት እስከተስተካከለበት ቀን ድረስ የተሰጠውን ብልጫ ጭማሪ በየወሩ ከደመወዙ 1/3 እየቀነሰ ገቢ የማድረግ የአክሲዮን ማህበሩ መብት አለው፡፡

4.1.10 አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ አ/ማህበሩ የመዋቅር ለውጥ፣ ደረጃ እና ደመወዝ ማስተካከያ ከባለቤቱ ፈቃድ ሲያገኝ ሊያስተካክል ይችላል፡፡

4.1.11 በሐኪም ቦርድ የቦታ ለውጥ የታዘዘለት ሠራተኛ ሊሠራ ወደ ሚችልበት ሌላ ቦታ ወስዶ በዝቅተኛም ሆነ በተመሳሳይ የሥራ መደብ የሚያገኘውን ደመወዝ ሳይነካ አሠማርቶ ማሠራት የአ/ማህበሩ መብት ነው፡፡ ይህ የማይቻል ከሆነ አ/ማህበሩ በህጉ መሰረት ማሰናበት ይችላል።

4.1.12 በተከታታይ ቀሪነት ከስራ የሚሰናበቱ ሰራተኞችን በተመለከተ አሳማኝ ምክንያት ካለው ማኔጅመንቱ ጉዳዩን ሊያይ ይችላል፡፡

4.2 ለ/ የአሠሪው ግዴታዎች፡

4.2.1 ለሠራተኛው በስራ ውሉ መሠረት ሥራ የመስጠት፤

4.2.2 በሥራ ውሉ ወይም በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር ለሥራ የሚየስፈልገውን መሣሪያና ጥሬ ዕቃ ለሠራተኛው የማቅረብ፤

4.2.3 ሠራተኛውን የሚመለከቱ የመንግስት አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም በህብረት ስምምነቱ ውስጥ የተመለከቱትን ሁሉ በሚገባ የማክበር፡

4.2.4 ሠራተኞች በሙያም ሆነ በዕውቀት እንዲሻሻሉ ከሚያደርጉ የመንግስትም ሆነ ከግል ድርጅቶች ጋር የመተባበር፤

4.2.5 ለሠራተኛው ደመወዙንና ሌሎች ክፍያዎችን በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 1156/2011 እና በህብረት ስምምነቱ መሠረት የመክፈል፤

4.2.6 ለሠራተኛው የሚገባውን ሰብዓዊ ክብር የመጠበቅ፤

4.2.7 የሠራተኛውን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅና ከአደጋ ለመከላከል የሚያስፈልጉትን በሕግ አግባብነት ካላቸው መ/ቤቶች በሚሠጡ መመሪያዎች መሠረት የማሟላት።

4.2.8 ሠራተኛው መብትና ግዴታውን በቅድሚያ እንዲያውቅ አክሲዮን ማሕበሩ ከመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ ጋር ያደረገውን የJብረት ስምምነት ቅጅ አባዝቶ የመስጠት።

4.2.9 የሠራተኛው ጤንነት እንዲመረመር በሕግ ወይም አግባብ ባለው ባለስልጣን ትዕዛዝ በሚሰጥበት ጊዜ ለምርመራ የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን፡

4.2.10 በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 የተመለከቱትን አግባብ ያላቸውን ዝርዝሮች ያካተቱ የሠራተኛውን የጤንነት ሁኔታ በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት እና ሌሎችም በሚኒስትሩ /በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር/ እንዲያዙ የተወሰኑ መረጃዎችን የሚያሳዩ መዝገብ የመያዝ፤

4.2.11 የሥራ ውል በሚቋረጥበት ጊዜ ሠራተኛው ሲሰራ የነበረውን የሥራ ዓይነት፤ የአገልግሎት ዘመንና ሲከፈለው የነበረውን ደመወዙን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ለሠራተኛው የመስጠት እንዲሁም ሠራተኛው በሥራ ላይ እያለ በጠየቀ ጊዜ የስራ ልምድ የመስጠት፤

4.2.12 አዲስ ተቀጣሪ ሠራተኛ ሲቀጠር እድገትና ዝውውር ሲፈፀም ለማሕበሩ የማሳወቅ፤

4.2.13 በሠራተኛው ላይ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ሲወስድ በግልባጭ ለማህበሩ የማሳወቅ፤

4.2.14 በየበጀት ዓመቱ መጨረሻ የአ/ማህበሩን ትርፍና ኪሳራ ለመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ የማሳወቅ፤

4.2.15 መሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበሩንና አባላቱን የሚመለከት የቃልም ሆነ የጽሑፍ መልዕክቶች ሲመጡ መልእክቱ እንዲደርስ የማድረግ፤

4.2.16 አጠቃላይ የአ/ማበሩን ሠራተኞች የሚመለከት አዳዲስ የአሠራር ሲስተሞችና አደረጃጀቶች ሲኖሩት ለሠራተኛ ማሕበሩ የማሳወቅ፡፡ ለውጡም ከዚህ ኀብረት ስምምነት ጋር የሚቃረን መሆን የለበትም ሆኖም የፈረቃ ሥራ ለውጥ እንደ ከባድ የሥራ ለውጥ ሆኖ አይታይም፤

4.2.17 የሠራተኛ ማሕበር መሪ፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመሆኑ ሕጋዊ መብቱን ሲያስከብር በማንኛውም አኳኋን አይደናቀፍም፣ ወይም ሕጋዊ መብቱን በማስከበሩ በሠራተኛው ላይ እርምጃ አይወስድም እንዲሁም በሠራተኛው ማህበር መሪ እና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ላይ የተሞላው የሥራ አፈፃፀም ነጥብ ላይ በማሕበር ውስጥ ከመመደቡ በፊት ካለው የሥራ አፈፃፀም ቀንሶ ቢገኝ አክሲዮን ማሕበሩ ከሠራተኛ ማሕበሩ ጋር ጉዳዩን መርምሮ መፍትሔ የመስጠት፤

4.2.18 ይህን የሕብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም ስለ አዲስ የሥራ ሁኔታዎች ወይም የሠራተኞች መብት ለማስከበር ለውይይት መሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበሩ ሲጠይቅ አሠሪው የመቀበል፤

4.2.19 አ/ማህበሩ ለሠራተኛው የሰርቪስ አገልግሎት ይሠጣል፡፡ ሆኖም ግን ከዚህ በፊት የሰርቪስ አገልግሎት ሲሰጥበት ከነበረው የፋይናንስ ወይም የኢኮኖሚ አቅም ዝቅ ካለ የነበረው ሰርቪስ አገልግሎት ሊቋረጥ ይችላል። አክሲዮን ማህበሩ ሰርቪስ የማይሰጥ ከሆነ አስቀድሞ ለሰራተኛው ያሳውቃል፤
የአዲስ አበባ ማ/ጽ/ቤት ሠራተኞች የትራንስፖርት አበልን በተመለከተ አ/ማህበሩ ባፀደቀው መምሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

4.2.20 የመሠረታዊ የሠራተኛ ማሕበሩ፤ ሠራተኞች የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ አባል ለመሆን የፈቀዱበትን ቅጽና የሠራተኛውን ፊርማ የያዘ ሠነድ /ማስረጃ/ ለአክሲዮን ማህበሩ ሲያቀርብ የማህበርተኝነት መዋጮን ከወር ደመወዙ 1% እየቆረጠ በመሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበሩ ስም በተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገቢ በማድረግ ያሳውቃል፡፡ ከማህበሩ አባልነት የሚወጡ ሠራተኞች ሲያጋጥም ለመሠረታዊ ማሕበሩ ሠራተኛው አመልክቶ ለመፈቀዱ መሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበሩ ለአ/ማህበሩ ሲያሳውቅ ተቆራጭ አይቀነስበትም፡፡

4.2.21 የመሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበር አባላት ልዩ ልዩ የህብረት ሥራዎች ለማቋቋም በሚፈልጉበት ጊዜ እያንዳንዳቸው በፈቃደኝነት የፈረሙበትን ስም ዝርዝር፤ የገንዘብ ልክ በማሕበሩ ደብዳቤ አማካኝነት ሲደርስ አክ/ማሕበሩ የተባለውን ገንዘብ ከደመወዛቸው ላይ ቀንሶ በዚሁ አንቀጽ ተራ ቁጥር 4.2.20/ በተገለፀው መሠረት ይፈፀማል፡፡

4.2.22 በዚህ አንቀጽ ተ.ቁ 4.2.20 እና 4.2.21 መሠረት በአክ/ማሕበሩ አማካኝነት ከሠራተኞች ደመወዝ እየተቀነሰ በማሕበሩ የባንክ ሂሣብ ቁጥር ገቢ የሆነውን ገንዘብ ትክክለኛነቱን ማሕበሩ እንዲቆጣጠር አክ/ማህበሩ ይፈቅዳል፡፡

4.2.23 እያንዳንዱ ሠራተኛ ስለተመደበበት የሥራ መደብ የሥራ ዝርዝር /Job Description/ በጽሁፍ አክሲዮን ማሕበሩ አዘጋጅቶ ይሠጣል፡፡

4.2.24 አክሲዮን ማህበሩ ለሠራተኞች የጡረታ ቁጥራቸውን ያሳውቃል፡፡ የጡረታ ጊዜያቸው ሲደርስ የጡረታ አበል በጊዜው እንዲያገኙ የማድረግ እና ከ6 ወር በፊት የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

4.2.25 የሠራተኛው የሥራ አፈፃፀም በየአመቱ በታህሳስ መጨረሻና ሰኔ መጨረሻ ላይ ሁለት ጊዜ ይሞላል። በወቅቱም ሠራተኛው በክፍሉ ውጤቱን እንዲያውቅ ይደረጋል። ቅሬታ ካለ በመምሪያ/አገልግሎት ሃላፊው ታይቶ የሚፀድቅ ወይም የሚሻሻል ሆኖ ወደፊት ዝርዝር አፈፃፀምና መለኪያዎች የሥራ ደንብ ያዘጋጃል።

4.2.26 አክሲዮን ማሕበሩ በሕግ ከታወቀው ሠራተኛ ማሕበር ሌላ በውስጥም ሆነ በውጭ የማሕበሩን ሕልውና የሚቃረኑ ግለሰቦችን ወይም ሰዎችን አይደግፍም፡፡

4.2.27 አክሱዮን ማሕበሩን የሚጐዳ ነገር መከሰቱን በሠራተኛው ወይም በሌላ አካል ሲጠቆም አክሲዮን ማሕበሩ አጣርቶ አስቸኳይ እርምጃ ይወስዳል፡፡

4.2.28 አክ/ማሕበሩ ከሠራተኛ ማሕበር አባላት የመሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበሩን በሚመለከት የሚቀርብለትን ጥያቄ አያስተናግድም፡፡

4.2.29 አክ/ማህበሩ ከሠራተኛው ደመወዝ ላይ ያለ አግባብ ቀንሶበት ቢገኝ የተቀነሰበትን ገንዘብ በአንዴ ይከፍላል፡፡

4.2.30 አሠሪው ሠራተኞችን የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር አባል እንዲሆኑ አይቀሰቅስም ጣልቃ በመግባትም ሆነ በማባበል ከመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር እንዲወጡ አያደርግም፡፡

4.2.31 አክሲዮን ማህበሩ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር አባል በመሆንና ባለመሆን በሠራተኛው ላይ ልዩነት አይፈጥርም በመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩም ህጋዊ እንቅስቃሴ በማድረጉ ምክንያት ተፅዕኖ አያደርግም።

4.2.32 ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት ያለመፈጸም፤እንዳይፈጸም የመከላከል፤ተፈፅሞም ሲገኝ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ግዴታ አለበት፤

4.2.33 የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ስራ አስፈፃሚ ለልምድ ልውውጥ ለማድረግ በሚሄዱበት ጊዜ ነዳጅ እና መኪና ያመቻቻል፡፡ የሹፌሩን አበል ሰራተኛ ማህበሩ ይሸፍናል፡፡

አ ን ቀ ጽ 5

5.1 የመሠረታዊ የሠራተኛ ማሕበሩ መብትና ግዴታ፡-

ሀ/ የማሕበሩ መብት፡

5.1.1 በዚህ ስምምነት ውስጥ ስለተካተቱት እና ሌሎች ጉዳዮች ሠራተኛውን ወክሎ ከአሠሪው ጋር ሊነጋገር የሚችለው የመሠረታዊ የሠራተኛ ማሕበር ብቻ ነው፡፡

5.1.2 የአ/ማሕበሩን የምርት እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ ማሕበሩ ማወቅ ሲፈልግ የመጠየቅና የማወቅ መብት አለው፡፡

5.1.3 አ/ማህበሩ የመዋቅር ለውጥ ሲያደርግ በዝግጅትም ሆነ በአፈፃፀም ላይ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩን እንዲተባበር ሲጠየቅ ሙሉ ተሳትፎ ማሕበሩ ያደርጋል፡፡

5.1.4 በየክፍሉ ሠራተኞችን የሚያስተባብሩ የሚመሩ አንድ አንድ የሆርሻ ተጠሪዎች ተመርጠው ይሠራሉ፡፡ ሠራተኛውንም በምርት ሥራ ተግተው እንዲሠሩ ይቀሰቅሳሉ የሠራተኛውን ቅሬታ እዚያው ሥራ ቦታ መፍትሔ እንዲያገኙ ያደረጋሉ፡፡

5.1.5 በአ/ማህበሩ ውስጥ ያለው ህጋዊ የመሠረታዊ የሠራተኛ ማሕበር ጽ/ቤት ሠራተኛውን በሚመለከት ጉዳይ ላይ ሕጋዊ መግለጫ የመስጠት መብት አለው፡፡

ለ/ የማሕበሩ ግዴታ፡

5.2.1 ሠራተኛው የህብረት ስምምነቱን አንቀፆች ትርጉምና አፈፃፀም በሚገባ እንዲረዳ የበኩሉን ሁሉ ያደርጋል፤ አ/ማህበሩም ፍቃድ ይሰጣል፡፡

5.2.2 ይህን ህብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም ስለ አዲሱ የስራ ሁኔታዎች ለውይይት አሠሪው ሲጠይቅ ይቀበላል፡፡

5.2.3 የሕብረት ስምምነት ሕጐችና መንግስታዊ መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ አሠሪው የሚያወጣውን አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችን እና ዕቅዶችን ለማስፈፀም ማኔጅመንቱ በሚያደርገው ጥረት ሁሉ ማሕበሩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

5.2.4 በአክሲዮን ማሕበሩና በሠራተኛው መካከል አንዳንድ ቅሬታዎች ሲፈጠሩ ጉዳዩን በውይይት ለመፍታትና በመግባባት ለመፈፀም ማሕበሩ ሙሉ ትብብር ያደርጋል፡፡

5.2.5 የአ/ማህበሩ ምርት የበለጠ እድገት እንዲኖረውና ትርፋማ እንዲሆን ሠራተኛውን ማበረታታትና መቀስቀስ አለበት፡፡

5.2.6 ለሠራተኛው የሚሸጡትን ምርቶች አክሲዮን ማሕበሩ በሚያወጣው ኘሮግራም መሠረት በቅደም ተከተል እንዲፈፀም ክትትል ያደርጋል፡፡

5.2.7 ሠራተኛው በአ/ማህበሩ ላይ ቅሬታ ኑሮት ይህንንም ለመወጣት ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ በዚህ ሕብረት ስምምነት ላይ የተመለከቱትን የቅሬታ አቀራረብ ስርዓቶች እንዲከተል ያደርጋል፡፡

5.2.8 ማህበሩ ማንኛውም ሠራተኛውን የሚመለከት ህብረት ስምምነት የተጠቀሱትን ጉዳዮች በግሉ ለማሻሻል ለመሠረዝ ወይም ለመለወጥ አይችልም፡

5.2.9 ማሕበሩ በአዋጅና በኀ/ስምምነት የተደነገገውን የሠራተኛ መብቶችና ግዴታዎች በአክሲዮን ማሕበሩ ሠራተኞች ዘንድ እንዲከበሩ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ወይም ስለ አ/ማሕበሩ እድገት እንዲሁም ስለሚያጋጥሙ ችግሮች የአሠራር ለውጥ ወይም ከነበረው አደረጃጀት የተለየ ሌላ አደረጃጀት ሲያደርግ ሠራተኛ ማሕበሩ ጉዳዩን በጥልቀት አውቆና ተረድቶ ለአሠሪው ድጋፍ ያደርጋል፡፡

አ ን ቀ ጽ 6

6.1 የሠራተኛው መብትና ግዴታ፡

ሀ/ የሠራተኛው መብት

6.1.1 ለሠራበት የሚከፈለው ደመወዝ ወይም አበል በወቅቱ የማግኘት መብት አለው፡

6.1.2 ደመወዝ የሚከፈለው ለሠራበት ወይም በሕግ እንዲሠራ የተቀጠረበትን ሥራና ጊዜ ቢሆንም ተቀናናሽ ሂሳቦችን በግልጽ በሚያሳይ በተዘጋጀ የደመወዝ የመክፈያው ሰነድ ጉልህ በሆነ እና የሚታይ መሆን አለበት ፡፡ ከመደበኛ ተቆራጮች ውጭ የሚቆረጥ ክፍያዎችን የሚገልጽ መረጃ መኖር አለበት ፡፡

6.1.3 ሠራተኛው ሳያውቅ ማስጠንቀቂያም ሆነ ቅጣት በግል ማሕደሩ ውስጥ አይቀመጥም፣ እንዲሁም ሠራተኛው በግል ማሕደሩ ላይ ጥርጣሪ ሲኖረው እና ሲጠይቅ የአ/ማህበሩን አሠራር ጠብቆ የግል ማሕደሩን ማየት ይችላል፡፡

6.1.4 ማንኛውም ሠራተኛ ጡረታ የሚሞላበትን የሕይወት ታሪክ ቅጽ የትምህርት ማስረጃ ወይም ሌላ መረጃ በጽሁፍ ሲጠይቅ ከማሕደሩ ከሚገኘው ቀሪ በራሱ ወጭ ፎቶ ኮፒ አድርጎ የመውሰድ መብት አለው፡፡

6.1.5 በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 158 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በሀገሪቱ ህጐች መሠረት የሠራተኛው ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች የተጠበቁ ናቸው፡፡

6.1.6 በዲሲኘሊን ችግር ምክንያት ካልተወሰነበት በስተቀር ሠራተኛውን በሥራ ውሉ መሠረት ከሚሠራበት ሥራ ደረጃና ደመወዝ ዝቅ አድርጉ ማሠራት የተከለከለ ነው፡፡ ይሁን እንጅ በጤና ምክንያት መሥራት ያልቻሉ ሠራተኞች ዝቅ ባለ መደብ ደመወዛቸውን ሳይነካ የታዘዙትን እየሠሩ እንዲያገግሙ ይደረጋል፡፡ ይሁን እንጂ ነገሩ ዘላቂ ሆኖ ለአክሲዮን ማሕበሩ ጉዳት ካመጣ ግን በሐኪሞች ቦርድ ውሳኔ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

6.1.7 አ/ማህበሩ አዲስ አደረጃጀት በሚፈጥርበት ጊዜ ለሠራተኞች ተፈላጊውን መስፈርት መሠረት አድርጐ ምደባ ያደርግላቸዋል፡፡ በዚህ ወቅት ሠራተኛው የነበረበትን የሥራ መደብ በተፈላጊው የትምህርትና የሥራ ልምድ መስፈርት ማደግ ምክንያት ሳያሟላ ቢገኝ አክ/ማህበሩ ሠራተኛውን ዝቅ ወዳለ መደብ ባሟላበት ደረጃ ሊመድበው ይችላል፤ ሆኖም ቀድሞ የያዘውን ደመወዝ አይቀነስበትም፡፡

6.1.8 ሴቶች የቅድመ ካንሰር ምርመራ በአ/ማህበሩ ወጪ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ/ የሠራተኛው ግዴታዎች፡-

6.1.10 ስለ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የወጣ አዋጅ ፣ ተጓዳኝ ደንቦች ፣ ይህን የህብረት ስምምነት እንዲሁም በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ወደፊት የሚወጡትን ማሻሻያዎችና መመሪያዎች ተቀብሎ በሥራ ላይ የማዋል፡፡

6.1.11 ሠራተኛው ለተቀጠረበት ሥራ መላ ጉልበቱንና ችሎታውን በማዋል የአክ/ማሕበሩን የሥራ ውጤት እንዲዳብር በትጋትና በጥንቃቄ የመሥራት ፡፡

6.1.12 ሠራተኛው ሥራውን ለማከናወን በሥራ ላይ የሚገለገልባቸውን የአደጋ መከላከያ ወይም ማንኛውም መሣሪያ ወይም ዕቃ በጥንቃቄ ጠብቆ የመያዝ እና የመገልገል፡፡

6.1.13 ለሥራ ብቁ በሆነ አእምሮና የአካል ሁኔታ በሥራ ላይ መገኘት፡

6.1.14 በሥራ ቦታ በሕይወትና ንብረት ላይ አደጋ ሲደርስ ተገቢውን ዕርዳታ መስጠት፡

6.1.15 ራሱም ሆነ ጓደኞቹን አደጋ ላይ የሚጥል ወይም የአ/ማህበሩን አጠቃላይ ጥቅም የሚነካ ማናቸውም ሁኔታ ሲያጋጥም በወቅቱ ለአሠሪው ማሳወቅ፡፡

6.1.16 በአ/ማህበሩ ግቢ ውስጥ “ሲጋራ ማጨስ ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ማጨስ” ክልክል ነው፡፡

6.1.17 ለአ/ማህበሩ ሥራ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሠራተኛውን ሰብዓዊ ወይም መሠረታዊ የሥራ ሁኔታዎችን የሚለውጥ ሆኖ እስካልተገኘ ድረስ በተመሣሣይ ደረጃና ተዛማጅ ሥራ እንዲሠራ የሚወጣውን መመሪያ የመቀበል፡፡

6.1.18 በአዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 67 ከ “ሀ” እስከ “መ” በተጠቀሱት መሠረት የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ ሲታዘዝ የመሥራት

6.1.19 የአክሲዮን ማሕበሩን የኢንዱስትሪ ሰላም የሚያናጋ የሀሰት ወሬና ውዥንብር ከመንዛትና ጠብ አጫሪነት ራስን ማጽዳት ፡፡

6.1.20 ሁልጊዜ የራሱንና የአክሲዮን ማሕበሩን ስም በመጠበቅ መልካም ፀባይ መያዝ፤

6.1.21 አክሲዮን ማሕበሩ ካልፈቀደ በስተቀር በሥራ ቦታና በሥራ ጊዜ ልዩ ልዩ ሕትመቶችን፣ መጽሐፎችንና ማስፈረሚያ ሊስቶችን የመሳሰሉትን ማደል፣ መለጠፍ ፣ ማዞር ፈጽሞ የተከለከለ ስለሆነ ይህንን አለመፈፀም፡፡

6.1.22 አክሲዮን ማሕበሩ ሳይፈቅድና ሠራተኛ ማሕበሩ ሳያውቅ በሥራ ሰዓትም ሆነ በእረፍት ጊዜው በአክሲዮን ማሕበሩ ግቢ ውስጥ ስብሰባ ማድረግ የተከለከለና ሕገ ወጥ ስለሆነ ይህን መፈፀም የለበትም፡፡

6.1.23 በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከአክሲዮን ማህበሩ ደንበኞች፣ ወኪሎቻቸው ወይም ከማናቸውም ተገልጋይ ኮሚሽን፣ ማማለጃ ወይም ጉቦ አለመቀበል፡፡

6.1.24 ሰክሮ እና አእምሮ በሚያደነዝዙ ዕፆች ተመርዞ በሥራ ቦታ መገኘት የሚያስቀጣ መሆኑን መረዳት፤ ማንኛውም ሠራተኛ ከአቅም በላይ መሆኑ ሲታመንበት ካልሆነ በስተቀር አስቀድሞ ፈቃድ ሳይሰጠው ከመደበኛ ሥራው ላይ መቅረት አይገባውም።

6.1.25 በስራ ሰዓት ያለፈቃድ ሥራውን ትቶ ከክፍል ወደ ክፍል ከሥራ ቦታ ውጭ አለመዘዋወር፡፡

6.1.26 ስለ ጤና አጠባበቅ እና አደጋ መከላከል በአክሲዮን ማሕበሩ የሚመጡትን መመሪያዎች አክብሮ በጥንቃቄ ሥራ ላይ ማዋል፡፡

6.1.27 ድምጽ ያለውም ሆነ ድምጽ የሌለው የጦር መሣሪያ ወደ አክ/ማሕበሩ ይዞ መግባት የለበትም፡፡ ሕጋዊ ፈቃድ ቢኖረውም እንኳ ለጥበቃ አስረክቦ መግባት አለበት፡፡

6.1.28 የተቀጠረበትን ሥራ በተወሰነው የሥራ ሰዓት ተገኝቶ የመስራት ፡፡

6.1.29 በሥራው ላይ የቅርብ አለቃውን ትዕዘዝ የመፈፀም፡

6.1.30 ያለ በቂ ምክንያት ወይም ከአለቃው ፈቃድ ሳይቀበል ከሥራ አለመቅረት፡

6.1.31 በአ/ማህበሩ በቋሚነት ከተቀጠረ በኋላ የሥራ ውል ሣያቁርጥ በሌላ መ/ቤት በቋሚነት ተቀጥሮ አለማገልገል፡፡

6.1.32 በሥራ ሰዓት በተገቢው ኃላፊ ሳይታዘዝ ለውጭ ሰው ወይም ድርጅት ሥራ አለመሥራት፡

6.1.33 ማሕበሩ ሳያውቀው ሠራተኞችን አስተባብሮ በሥራ ቦታና ጊዜ ማስፈረምና ተፈራርሞ ለአ/ማህበሩም ሆነ ለማሕበሩ ማቅረብ ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡

6.1.34 ሠራተኛው የሚሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎችን መጠቀም ግዴታው ነው፡፡

6.1.35 ሠራተኛው የሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓቶችን የማክበርና ያለፈቃድ መደበኛ ሥራውን ትቶ መቅረት የተከለከለ ነው፡፡

6.1.36 ሠራተኛው ሥራውን ትቶ መተኛት፣ በግቢው ውስጥና በሌሎች ቦታዎች መዘዋወር እንዲሁም የሚሠሩ ሠራተኞችን ሥራ ማስፈታት የተከለከለ ነው፡፡

6.1.37 ሠራተኛው በተዋረድ በአ/ማህበሩ የሥራ ኃላፊዎች ዘንድ የሚሰጠውን መመሪያ ተቀብሎ የመስራት ግዴታ አለበት፡

6.1.38 በማንኛውም ሁኔታ በአ/ማህበሩ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ያለ ፈቃደ መገልገል ወይም ሕጋዊ ማስታወቂያ መቅደድ ወይም መሰረዝ እርምጃ ያስወስዳል፡፡

6.1.39 ሠራተኛው ከሥራው ጋር በተያያዘ ምክንያት አክ/ማህበሩ የምስክርነት ቃል እንዲሰጥ ሲጠይቀው የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

6.1.40 አክ/ማህበሩ ወደፊት ምርታማነትን ለማሳደግና ጥራትን ለማሻሻል የሚጠቀምባቸውን አዳዲስ የአሠራር ስርዓቶች ሲኖሩ ተቀብሎ የመፈፀም ግዴታ ይኖርበታል፡፡

6.1.41 ማንኛውም ሠራተኛ ከተፈቀደው የሻይና የምሣ ኘሮግራም ውጭ ሻይ ቤትና ምግብ ቤት ቁጭ ብሎ መገኘት በሕግ ያስቀጣል፡፡

6.1.42 አንድ ሠራተኛ ቋሚ ዝውውር ሲፈፀምለት ጥቅማ ጥቅምን በተመለከተ የደንብ ልብስ ወይም የአደጋ መከላከያ በነበረበት ክፍል ያላገኘ ሠራተኛ ሆኖ ወደ ሌላ የሥራ መደብ ከተዘዋወረ በአዲሱ የሥራ መደብ የሚገባውን ያገኛል እንጅ የነበረበትንና አዲስ የተመደበበትን ሁለቱን የማግኘት መብት የለውም፡፡

6.1.43 ከዚህ በላይ የተመለከተዉን ግዴታ የማያከብር ሠራተኛ በሕጉ ወይም በዚህ ህብረት ስምምነት የተመለከቱት የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች ይወሰዱበታል፡፡

6.1.44 በአ/ማህበሩ በተዘጋጀው የሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ እና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የመፈፀም ግዴታ አለበት፡፡

6.1.45 ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት ያለመፈጸም፤

አ ን ቀ ጽ 7

7.1 በድርጅቱ ውስጥ ስለሚደረግ የሰራተኛ ዝውውር፡

7.1.1 ሠራተኛው ለአክሲዮን ማሕበሩ ሊሠጠው የሚችለው ጠቀሜታ ሲታመንበትና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አክሲዮን ማሕበሩ የሠራተኛውን ደረጃ ሳያጓድል አዛዋውሮ ማሠራት ይችላል፡፡ ጥቅማ ጥቅምን በተመለከተ ግን የደንብ ልብስ ወይም የአደጋ መከላከያ በነበረበት ክፍል ያላገኘ ሠራተኛ ሆኖ ወደ ሌላ የሥራ መደብ ከተዘዋወረ በአዲሱ የሥራ መደብ የሚገባውን ያገኛል እንጅ የነበረበትንና አዲስ የተመደበበትን ሁለቱን የማግኘት መብት የለውም፡፡

7.1.2 ሠራተኛው በሥራ ላይ የሚፈጽመው ጥፋት በህ/ስምምነቱ መሠረት ከሥራ የሚያስወጣ ሆኖ ሲገኝ አክሲዮን ማሕበሩ እንደአስፈላጊነቱ ለማሻሻል ከፈለገ ከፍተኛውን ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በተገኘው የሥራ ቦታ አዛውሮ ማሠራት ይችላል፡፡

7.1.3 በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ በተመሳሳይ ደረጃና የሚሠሩት ሥራ ተዛማጅ ሆኖ ሲገኝ በሥራ መደቡ ላይ የተመደቡትን ሠራተኞች የያዙትን የሥራ መደብ እንዲለዋወጡ ሲስማሙና አክ/ማህበሩ ሲፈቅድ ሊዘዋወሩ ይችላሉ፡፡

7.1.4 አክ/ማህበሩ በአንድ መምሪያ/አገልግሎት ውስጥ ትርፍ የሰው ኃይል ሲኖረው በዚህ ስምምነት ተ.ቁ 7.1.1 ላይ የተጠሰቀውን ሳያጓድል ወደ ሌላ ቦታ ሊያዘዋውረው ይችላል፡፡

7.1.5 ሥራው የማይበደል መሆኑ ከታመነበተና ቦታ ከተገኘ በሠራተኛው ጥያቄ አክ/ማህበሩ ሲፈቅድ ሠራተኛውን ከፈረቃ ወደ ፈረቃ ከክፍል ወደ ክፍል ከመምሪያ ወደ መምሪያ በዚህ ስምምነት ተ.ቁ 7.1.1 ላይ የተጠቀሱትን ሳያጓድል ሊያዘዋውረው ይችላል፡፡

7.1.6 በአ/ማኀበሩ ውስጥ አንድ የሥራ መደብ ሲለቀቅ ወይም ሲከፈት በቅድሚያ መስፈርቱን ያሟላና ለዚሁ ብቁ ነው ተብሎ በውድድር የተለየ ሠራተኛ ወይም በሐኪሞች ቦርድ የሥራ አካባቢ ለውጥ የታዘዘለት ሠራተኛ በድርጅቱ ክፍት ቦታ ካለ ተዛውሮ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡

7.1.7 ሠራተኛው ከባ/ዳር ውጭ አዲስ አበባ ማ/ጽ/ቤት እና ወደፊት አ/ማህበሩ በሚከፍታቸው የሽያጭ ጣቢያዎች ሠራተኞችን ማሠራት ሲፈልግ በዚህ አንቀጽ ተ.ቁ 7.1.1 እና 7.1.6 ላይ የተጠቀሱትን ሳያጓድል አዛውሮ ማሠራት ይችላል፡፡ ዝውውሩ በአክሲዮን ማሕበሩ አነሳሽነት የተፈፀመ ከሆነ የአንድ ወር ደመወዝ ክፍያ ይፈጽማል፡፡

አ ን ቀ ጽ 8

8.1 የደረጃ ዕድገት፡

8.1.1 በአክሲዮን ማህበሩ ክፍት የሥራ መደብ ሲፈጠር ከውጭ ከመቀጠሩ በፊት ለውስጥ ሰራተኞች የሥራ መደቡ የሚጠይቀውን መመዘኛዎች የሚያሟሉ መኖራቸውን ለማጣራት ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀን ያህል የሚቆይ ማስታወቂያ ይወጣል፡፡ በአንድ ማስታወቂያ በወጡ ክፍት የሥራ መደቦች አንድ ሰራተኛ በ3 ክፍት ቦታዎች ማመልከት ይችላል፡፡ የማስታወቂያው ግልባጭ ለሠራተኛ ማህበሩ ይሰጣል፡፡ የመወዳደርያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ሌላ ምዝገባ አይፈቀድም።

ሀ/ ለአ/ማህበሩ ሥራ ከአክሲዮን ማህበሩ አካባቢ ውጭ የሄደ ሠራተኛ ለክፍት ቦታው የሚመጥን ከሆነ አ/ማህበሩ በውድድሩ እንዲገባ ይደረጋል፡፡

ለ/ በሕጋዊ ፈቃድ በሥራ ላይ ያልተገኘ ሠራተኛ ከሆነ ግን ለክፍት ቦታው የሚመጥን ሆኖ ከተገኘ በወኪሉ /በሚመለከተው/ ሰው አማካኝነት ሊመዘገብ ይችላል፡፡

8.1.2 ሀ/ ለክፍት የሥራ መደቡ ብቁ ሊሆኑ የሚችሉ ሠራተኞች መኖራቸው ከተረጋገጠ የማህበሩ ተወካይ በአባልነት በሚገኝበት ኮሚቴ በማወዳደር ብልጫ ያለው ሠራተኛ በዕድገት እንዲመደብ ይደረጋል፡፡

ለ/ በአ/ማሕበሩ መስፈርት መሠረት ለውስጥ ሠራተኞች ማስታወቂያ አውጥቶ የሚያሟሉ ሲጠፋ ለውጭ አመልካቾች /ቅጥር/ እድሉ ይሰጣል፡፡ ይህ ሁሉ ተሞክሮ ከጠፋ የውስጥ ሠራተኛ ባሟላው መጠን በታሳቢ እየተከፈለው እንዲሰራ ይደረጋል፡፡

ሐ/ ለአንድ ክፍት የሥራ መደብ የዕድገት ማስታወቅያ ወጥቶ ምዝገባ ከተካሄደ በኋላ ዕድገቱ በ45 ቀን ውስጥ ተጠናቅቆ መቅረብ አለበት፡፡ ይህን የማይፈጽም የአስተዳደር አካል ተጠያቂ ይሆናል ፡፡

መ/ የአ/ማህበሩ ሠራተኞች ዕድገት ከታየ በኋላ የተወዳዳሪዎች ውጤት በድርጅቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጠፋል፡፡

ሠ/ አግባብ ያለው የሥራ ልምድ ማለት ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ የወጣበት የሥራ መደብ ወይም በተመሣሣይ የሥራ መደብ /ደረጃ/ ዝቅ ብሎ ያለና መስመሩ ጠብቆ /ተከትሎ/ የሚገኝ ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጅ የዚህን አፈፃፀም በተመለከተ አክ/ማህበሩ ሊከተለው የሚገባ አግባብ ያለው የሥራ ልምድ መመሪያ ተቀርጾ እንዲፀድቅ ያደርጋል፡፡

ረ/ በአጠቃላይ የደረጃ ዕድገት ውጤታቸዉ እኩል የሚወጡ ሠራተኞችን ለመለየት ኮሚቴው ፈተና እንዲሠጥ ለማድረግ ይችላል፡፡

ሰ/ የደረጃ ዕድገት የሚያገኙ ሠራተኞች የደመወዝ ለውጥ የሚያገኙት አጽዳቂው ካፀደቀበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡

ሸ/ ለሁሉም ደረጃ እድገቶች ከ3ዐ% የሚታረም የሚወዳደሩበትን ሥራ በሚመለከት ፈተና ይሠጣል፣ ከዚህ ውስጥ 15 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ብቻ ተመርጠው ውጤታቸው ከሌላው መስፈርት /7ዐ%/ ጋር ተደምሮ በተገኘው ነጥብ አሸናፊው ይለያል፡፡ ይሁን እንጅ በፈተናው ከ15 በታች ያገኘ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

ቀ/ ሴት ሠራተኞች የሥራ መሪነት ክፍት ቦታ በሚወጣበት ጊዜ ከወንዶች ጋር ሲወዳደሩ 5 ነጥብ ይጨመርላቸዋል።

በ/ በተቋሙ ውስጥ እየሰራ በግሉ ጥረትም ሆነ በተቋሙ ፍላጎት የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሮት በዚህ ሙያ ስራ ላይ ካልሆነ በተማረውና በሰለጠነው ሙያ መስክ ደረጃ እድገት ሲወጣ ከዚህ ተቋም ያገለገለው አገልግሎት ቀጥታ የማይያዝ ከሆነ 20% አገልግሎቱ እንደ ቀጥታ ልምድ ሆኖ ይያዝለታል። ይህም ከስራ መሪ መደቦች እና ልዩ ሙያ ከሚጠይቁ የስራ መደቦች ውጭ ተግባራዊ ይሆናል።

8.1.3 የደረጃ እድገትና የሚያስከትለው የደመወዝ ጭማሪ በአ/ማህበሩ ክፍት የሥራ መደብ ሲፈጠር ከውጭ ከመቀጠሩ በፊት ካሉት ሠራተኞች መካከል የሥራ መደቡ የሚጠይቀውን መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ሠራተኞች በደረጃ ዕድገት በማወዳደር ይመደባል፡፡ ውድድሩና አፈፃፀሙ በህብረት ስምምነቱ መሠረት ሆኖ የደመወዝ አከፋፈሉ ሥርዓት የሚከተለውን መምሰል ይገባዋል፡፡

ሀ/ ቀድሞ የሚያገኘው ደመወዝ ካደገበት ቦታ መነሻ ደመወዝ እኩል ወይም በልጦ ከተገኘ የደመወዝ እስኬል ታይቶ የሚቀጥለውን እርከን ያገኛል፡፡

ለ/ ቀድሞ የሚያገኘው ደመወዝ ከደረጃው መነሻ በታች ከሆነ መነሻውን ያገኛል፡

8.1.4 ሠራተኛውን በዕድገት ለመመደብ የሚኖሩት የማወዳደሪያ ሚዛን የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ/ ለትምህርት ---------------------------- 30%
ለ/ አግባብ ላለው የሥራ ልምድ ------- 30%
ሐ/ የሥራ አፈፃፀም ---------------------- 2ዐ%
መ/ ለአገልግሎት -------------------------- 15%
ሠ/ ለማህደር ጥራት ---------------------- 5%
ጠቅላላ ድምር -------------------------------100%

ቢሆንም ይህ ወደ 60% ይለወጣል። የጽሁፍ ወይም የተግባር ፈተና ከ 3ዐ% ይወሰዳል አፈፃፀሙ ከላይ በተራ ቁጥር 8.1.2 “ሸ” መሠረት ይፈፀማል፡፡

ማሳሰቢያ፡

  1. ለትምህርት የተሠጠውን ነጥብ ለተጠየቀው የሥራ መደብ ዝቅተኛ መስፈርቱን አሟልቶ ከተገኘ እኩል ነጥብ ይሰጣል፡፡
  2. አግባብ ያለው የሥራ ልምድ አያስፈልግም ተብሎ ለወጣ የሥራ መደብ በውድድሩ ወቅት ከተወዳዳሪዎች የሥራ ልምድ ቢቀርብ የማወዳደሪያ ነጥብ አያሰጥም፡፡ (ለሁሉም ሰራተኛ እኩል ነጥብ ያሰጣል)
  3. ሠራተኛው ላደገበት የሥራ መደብ በድርጅቱ መዋቅር የደመወዝ እስኬል ሠንጠረዥ መሠረት ይፈፀማል፡፡

8.2 የሥራ ችሎታ፡

ሀ/ ለሥራ ችሎታው የተመደበው ነጥብ የሚሰጠው በዚህ ህብረት ስምምነት አንቀጽ 8 ተራ ቁጥር 8.1.4 መሠረት ይሆናል፡፡

ለ/ በዚህ ህብረት ስምምነት አንቀጽ 14 ከተጠቀሰው ውጭ በዕድገት ውድድርም ሆነ በሌላ ጊዜ ተሞልቶ የሚቀርብ የሥራ አፈፃፀም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም

ሐ/ በአንድ ዓመት ሁለት ጊዜ /ታህሣስ ወር መጨረሻና ሰኔ ወር መጨረሻ/ የሠራተኛው የሥራ አፈፃፀም መመዘኛ በአግባቡ ተሞልቶ በአ/ማህበሩ ውስጥ መቀመጡን የአክሲዮን ማሕበሩ የሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ ያረጋግጣል፡፡

መ/ የሠራተኛው የሥራ አፈፃፀም መመዘኛ በሠራተኛው የግል ማሕደር ውስጥ ተሞልቶ ባይገኝ በአጥፊው ላይ በዚህ ህብረት ስምምነት የተጠቀሰው የሥነ ሥርዓት እርምጃ ይወሰዳል፡፡ የሠራተኛው ያልተሟላ የሥራ አፈፃፀም መመዘኛ በዚህ ሕብረት ስምምነት አንቀጽ 14-2 መሠረት የሠራተኛ ተወካይ ባለበት ተሞልቶ እንዲቀርብ የአክሲዮን ማህበሩ የሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ ያደርጋል፡፡

8.3 ለትምህርት ደረጃ፡

የተመደበውን ነጥብ የሚሠጡት የዕድገት ኮሚቴ አባላት ናቸው፡፡ ይኸውም ከተወዳዳሪዎች የግል ማህደር የሚገኘውን የትምህርት ማስረጃ መሠረት በማድረግ ሲሆን የነጥብ አሠጣጡም ቀጥሉ በተመለከተው ሁኔታ ይሆናል፡፡

ሀ/ አሁን በሥራ ላይ በዋለው የመዋቅር የተፈላጊ ችሎታ መስፈርት አሠራር ተግባራዊ ይሆናል ፡፡

ለ/ ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መካከል ለቦታው የተጠየቀው ዝቅተኛ የትምህርት መስፈርት ያሟላ ተወዳዳሪ ሙሉውን 3ዐ ነጥብ ያሠጠዋል፡፡

ሐ/ የክፍሉን ትምህርት ሙሉውን ዓመት ተከታትለው ላልጨረሱ ተወዳዳሪዎች ያላጠናቀቁበት ክፍል 6 ወር ከቀረው ማስረጃ ከት/ቤት ካመጣ/ች ከውድድሩ አይታገዱም፣ የብሔራዊ ፈተና ተፈትነው የወደቁ ሠራተኞች እንዳጠናቀቁ ተቆጥሮ ይያዝላቸዋል፡፡

ይሁን እንጅ ለአንድ ዓይነት የት/ደረጃ ሁለት የምስክር ወረቀት የሚያያቀርቡ ተወዳዳሪዎች ድርብ ነጥብ አያሳጥም ትምህርታቸውን ሳያጠናቅቁ በተሰጠው እድል አሸናፊ ቢሆኑም ማስረጃቸውን እስኪያቀርቡ ድረስ በተጠባባቂነት ይመደባሉ፡፡ ሆኖም መረጃቸውን ካቀረቡበበት ቀን ጀምሮ ያለተጨማሪ ውድድር ለሥራ መደቡ የተፈቀደውን የደመወዝ ስኬል /እርከን/ ያገኛሉ፡፡ ነገር ግን በ 6ወር ውስጥ የትምህርት መረጃውን ካላመጣ በተጠባባቂ ከተመደበበት ይነሳል።

መ/ ሠራተኛው ከእድገት በፊት ያለውን የትምህርት ማስረጃ በግል ማሕደሩ ምዝገባው እስከሚጠናቀቅበት ድረስ ካላያያዘው ተቀባይነት የለውም፡፡

ሠ/ ሠራተኛው በውጭ አገር በተልዕኮ ትምህርት ተምሮ የትምህርት ማስረጃውን አቻ ግምት በትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጦ በግል ማህደሩ ማያያዝ አለበት። ይህን ካላደረገ ተቀባይነት የለውም፡፡

ረ/ በአጠቃላይ የደረጃ ዕድገት ውጤታቸው በማንኛውም በኩል ታይቶ የሚበላለጡበት ሁኔታ ከሌለ ኮሚቴው ድጋሚ ፈተና ሰጥቶ ሊለያቸው ይችላል፡፡

8.4 ለአገልግሎት ዘመን፡

ለአገልግሎት ዘመን ነጥብ የሚሰጡት የዕድገት ኮሚቴ አባላት ናቸው። ዝርዝር አሠራሩም ከተወዳዳሪዎች የግል ማሕደር በሚገኘው ማስረጃ ሲሆን አገር ውስጥ በሚገኙ በሌላ መንግስታዊ ያልሆኑ መ/ቤቶች እና የግል ድርጅት የተሠጠ ሕጋዊና ብቁ ለሆኑ አገልግሎት በዚሁ መሠረት ነጥብ ይሠጠዋል፡፡ ይኸውም፡-

ሀ/ ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ አገልግሎት ላለው ተወዳዳሪ ሙሉውን ነጥብ ይሰጠዋል የቀሩት ተወዳዳሬዎች ከዚሁ በመነሳት ድርሻቸው እየተሰላ ይሠጣቸዋል፡፡

ለ/ የቀረቡት ተወዳዳሪዎች ሁሉ ተመሳሳይ አገልግሎት ካላቸው ለእያንዳንዳቸው ሙሉው ነጥብ ይሠጣቸዋል፡፡

ሐ/ በመንግስት ድርጅት ተቀጥረው የነበሩ ተወዳዳሪዎች የሥራ ግብር የማይጠይቅ ሲሆን ከግል ድርጅቶች የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ብቻ የሥራ ግብር ለመክፈላቸው ይጠየቃሉ፡፡

8.5 አግባብ ያለው የሥራ ልምድ

የሥራ ልምድ ነጥብ የሚሠጡት የዕድገት ኮሚቴ አባላት ናቸው ዝርዝር አሠራሩ በተወዳዳሪዎች የግል ማህደር በሚገኘው ማስረጃ ሲሆን አገር ውስጥ በሚገኙ ከሌሎች መ/ቤቶችና ድርጅቶች ለተገኘ የሥራ ልምድ ሕጋዊ ብቁ መሆኑ ሲረጋገጥ በዚሁ መሠረት ይሠጠዋል፡፡ በተጨማሪም ለተመሳሳይ ሙያ በውጭ አገር ለተገኘ ልምድ ሕጋዊነት እየተረጋገጠ ይሠጠዋል፡፡

ሀ/ ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መካከል በወጣው የደረጃ ዕድገት ማስታወቂያ መሰረት ዝቅተኛውን አግባብ ያለው የስራ ልምድ መስፈርት ያሟላ ተወዳዳሪ ሙሉውን ነጥብ ይሰጠዋል፡፡

ለ/ የቀረቡት ተወዳዳሪዎች ሁሉም ተመሳሳይ እኩል ዓመት አግባብ ያለው የሥራ ልምድ ካላቸው ለእያንዳንዳቸው ሙሉ ነጥብ ይሠጣቸዋል፡፡

ሐ/ በማስታወቂያው ለወጣው ክፍት የሥራ መደብ መስፈርት መስመሩን የተከተለ /አግባብ ያለው/ ከትምህርት ዝግጅት መሻሻል በፊት የሚፈለገውን ዝቅተኛ የትምህርት ይዘት የሠሩበት የሥራ ልምድ በቀጥታ ሊያወዳድራቸው ይችላል፡፡ በደረጃ ዕድገት ወቅት ከአጠቃላይ ውጤት ላይ ለሴቶች 3 ነጥብ ተጨምሮላቸው ከወንዶች ጋር እኩል ከሆኑ ቅድሚያ ከፍተኛ የላቀ የት/ደረጃ ላለው፣ ተመሳሳይ ሆነው ከተገኙ ከፍተኛ አገልግሎት ላለው ይሠጣል፡፡ ይህ ሁሉ ተከናውኖ እኩል ሆነው ከተገኙ የዕድገት ኮሚቴው ፈተና በመስጠት ይለያቸዋል፡፡

መ/ ለአንድ የሥራ ደረጃ ለመወዳደር ብቁ የሚሆነው የሶስት ጊዜ የሥራ አፈፃፀም አማካኝ 50% እና ከዚያ በላይ ሲሆን ነው ፡፡ የሶስት ጊዜ የሥራ አፈፃፀም ከሌለው ምክንያቱ ተጣርቶ አሳማኝ ከሆነ የሁለቱ አልያም የአንድ ጊዜ የአፈፃፀም ውጤት ብቻ ይያዝለታል፡፡ ሆኖም ግን ለእያንዳንዱ ውድድር አግባብ ያለዉ የሥራ ልምድ በሥራ ደንቡ ላይ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡ ሠራተኛውም ቀድሞ እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡

8.6 ለግል ማሕደር ጥራት፡

ለግል ማህደር ጥራት የተመደበውን ነጥብ የሚሰጡ የደረጃ እድገት ኮሚቴው አባላት ናቸው ይኸውም፡-

ሀ/ ማስጠንቀቂያና የገንዘብ(የደረጃ) ቅጣት ያለበት ------- 5 ነጥብ ያስቀንሳል

ለ/ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ---------------------------2 ነጥብ ያስቀንሳል

ሐ/ የገንዘብ ቅጣት የተቀጣ -------------------------- 3 ነጥብ ያስቀንሳል

መ/ ማስጠንቀቂያና የገንዘብ(የደረጃ) ቅጣት የለለበት ------- 5 ነጥብ ያሰጠዋል

በዚህ ላይ ጥፋት የምንላቸው ከላይ በፊደል “ሀ” ለተጠቀሰው 9 ወር በፊደል “ለ” እና “ሐ” ለተዘረዘሩት ደግሞ 6 ወር እስኪሞላው ድረስ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ሆኖም ውድድሩ ከመካሄዱ በፊት እልባት ያላገኙ የዲስኘሊን ክስ ከውድድር አያሳግድም፡፡

8.7 የዕድገት ተፈፃሚነት፡

በዕድገት የተመደበ ሠራተኛ በዕድገት የሚያገኘውን ደመወዝ ማግኘት የሚችለው ማጽደቅ ለሚገባው ኃላፊ ቀርቦ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡

በዕድገት የተመደበ ሠራተኛ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በዕድገት ላገኘው ሥራው ብቁ ሆኖ ካልተገኘና በቅርብ አለቃው ተገምግሞ ማረጋገጫ /ማስረጃ/ ከቀረበ ወደ ቀድሞ ቦታው ወይም በተመሳሳይ ቦታ ቀድሞ በነበረበት ደረጃና ደመወዝ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡

8.7.1 አ/ማህበሩ ባወጣው የደረጃ ዕድገት ማስታወቂያ መሠረት ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መካከል ተፈላጊውን የት/ደረጃና የሥራ ልምድ ሌላም የሥራ መደቡ የሚጠይቀዉን ልዩ ልዩ ሙያ አሟልተው የተገኙትን ሠራተኞች መርጦ አስፈላጊ ከሆኑ ማስረጃዎች ጋር የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍል አስተባባሪው ለዕድገት ኮሚቴ ያቀርባል፡፡

8.7.2 የዕድገት ኮሚቴ ዕድገቱን መርምሮ የውሳኔ አስተያየቱን የመወሰን ሥልጣን ላለው አካል ከአቀረበ በኋላ ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር በ 7 ቀናት ውስጥ መልስ መስጠት አለበት፡፡

8.8 የደረጃ ዕድገት ለመወዳደር ስለሚቀርቡ ሠራተኞች፡

ሀ/ ከፍተኛ ወይም ተመሳሳይ የሥራ ደረጃ ያለው ሠራተኛ በዝቅተኛ ወይም በተመሳሳይ የሥራ ደረጃ ሊወዳደር አይችልም፡፡ ዝቅተኛ የሥራ ደረጃ ያለው ሠራተኛ ዕድገት የሚካሄድበት ቦታ ከሚያስከፍለው መነሻ ደመወዝ በላይ ቢያገኝም መወዳደር ይችላል፡፡

ለ/ ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜውን ካልጨረሰ ለዕድገት መወዳደር አይችልም፡፡

ሐ/ ለዕድገት የወጣውን ክፍት የሥራ መደብ መመዘኛ የሚያሟላ ማንኛውም ሠራተኛ ለውድድር መቅረብ ይችለል፡፡

መ/ አንድ ሠራተኛ የደረጃ ዕድገት ካገኘ በኋላ ቢያንስ 9 ወራት ሳያገለግል ሌላ አዲስ ዕድገት ሊወዳደር አይችልም፡፡ ሆኖም ተወዳዳሪ ከሌለ ግን ዕድገቱን ካገኘ ከ6 ወር በኋላ ሊወዳደር ይችላል፡፡

8.9 የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ ስለማቋቋም፡-

8.9.1 በሥራ መሪነት የታቀፉት ፈረቃ መሪዎች፣ ክፍል ሃላፊዎች እና ተጠሪነታቸው ለዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑ አገልግሎቶችና መምሪያዎች የደረጃ ዕድገት የሚታየው በሥራ መሪዎች ደንብ ሆኖ በዋና ሥራ አስኪያጅ በሚቋቋም ኮሚቴ የውሣኔ ሀሣብ የሚቀርብባቸው ሲሆን ሌሎች መደቦች ግን፡-

ሀ/ የሰው ኃይል ል/አስተዳደር መምሪያ --------- ሰብሳቢ

ለ/ ዋ/ስ/ አስኪያጅ የሚወክለው ኃላፊ -------------------- አባል

ሐ/ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበር ተወካይ --------------- አባል

መ/ የስርዓተ ፆታ አገልግሎት ኃላፊ…………………… አባል

ሠ/ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋ/ክፍል እና ኦፊሰሮች - አባል ሆነው የውሣኔ ሃሣብ ያቀርባሉ፡፡

8.10 የዕድገት ኮሚቴ አሠራር ሥነ ሥርዓት፡

ሀ/ የኮሚቴው ሰብሳቢ ዕድገት በሚካሄድበት ጊዜና ቦታ በመወሰን የዕድገት ኮሚቴ አባላት ይሰበሰባል፡፡ እንደአስፈላጊነቱም አስቸኳይ ጥሪ ያደርጋል፡፡

ለ/ ኮሚቴው የዕድገት ዕጩውን የት/ደረጃ፣ የሥራ ልምድ፣ የአገልግሎት ዘመን የማሕደሩ ጥራት፣ የሥራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት ወዘተ ይመረምራል፡፡

ሐ/ ማስረጃዎችን ከመረመረና ትክክለኛነታቸውን ከአጣራ በኋላ ተወዳዳሪው ለሥራው ያለው ፍላጐት፣ ዝንባሌ፣ የማሰብና የማመዛዘን ችሎታ ለሚወዳደርበት ቦታ ብቁ መሆኑን ይበልጥ ለማረጋገጥ ከሥራው ባሕሪ የተነሳ ከ30% የሚያዝ የጽሑፍ ወይም የተግባር ፈተና ይሰጣል፡፡

መ/ ኮሚቴው የቀረበለትን ማስረጃዎች መርምሮና ከዕጩዎች መካከል በአጠቃላይ ውጤት ብልጫ ያለውን መርጦ የራሱን አስተያየት በማከል ለማፀደቅ ኃላፊነት ለተሰጠው ኃላፊ ከማስረጃዎች ጋር ያቀርባል፡፡

ሠ/ የአ/ማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ወይም ውክልና ያለው ኃላፊ በዕድገት ኮሚቴ ተመርምሮና አስተያየት ታክሎበት ከአስፈላጊ መረጃዎች ጋር የሚተላለፍለትን የዕድገት ጥያቄዎች መርምሮ ይወስናል፡፡

ረ/ ማንኛውም የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ አባል ለአንድ ክፍት የሥራ መደብ በዕጩ ተወዳዳሪነት ሲቀርብ ከኮሚቴ አባልነት ተነስቶ ዕድገቱ በቀሩት አባላት ይታያል፡፡ የሠራተኛ ማህበሩ ተወካይ እራሱ ተወዳዳሪ ሆኖ ከቀረበ ለዚያ ጊዜ ብቻ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ ሌላ ሰው ይተካል፡፡

ሰ/ የዕድገት ኮሚቴ ሰብሳቢና የሠራተኛ ማህበር ተወካይ፣ የሥራ አስኪያጅ ተወካይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔው ተሟላ ይባላል፡፡

ረ/ ለማሽን ኦፕሬተርነት የስራ መደብ ለሚቀጠሩም ሆነ በደረጃ እድገት ለሚወዳደሩ አመልካቾች ሳይኮቴክኒክ ፈና እንደ ቅደመ መመልመያ መስፈረት የሚወሰድ ሲሆን በውጤቱም ከ60% እና በላይ ያመጣ ተወዳዳሪ ወደ ቀጣይ ሂደት እንዲሸጋገር ይደረጋል።

አ ን ቀ ጽ 9፣

ቅ ጥ ር፣

ሀ/ በአክሲዮን ማህበሩ ክፍት የሥራ መደብ በሚፈጠርበት ጊዜ የሠራተኛ አቀጣጠር፡

  1. አክ/ማህበሩ ካሉት ሠራተኞች በደረጃ ዕድገት ለመመደብ ሙከራ ተደርጐ ተፈላጊውን መመዘኛ የሚያሟላ ሲታጣ ድርጅቱ በሚያወጣው የራሱ የውጪ ማስታወቂያ መሠረት ከሚቀርቡት ተወዳዳሪዎች መካከል አወዳድሮ ይቀጥራል፡፡
  2. ሥራውን ለቆ የቆየ ሠራተኛ ቀድሞ ሲሠራው በነበረው የሥራ መደብ ላይ እንደገና በአሠሪው ሲቀጠር ለሙከራ ሊቀጠር አይችልም፡፡
  3. በሠራተኛው የሙከራ ጊዜ መጨረሻ በመምሪያ/አገልግሎት ኃላፊ አስተያየት ሥራው አጥጋቢ ከሆነ በውሉ መሠረት የተቀጠረ መሆኑ በጽሑፍ ይረጋገጥለታል፡፡ ለሠራተኛው ይህ ማረጋገጫ ሳይሠጠው የ60 ቀን የሙከራ ጊዜው ሲያልፍ ለሙከራ ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ በቋሚነት እንደተቀጠረ ይቆጠራል፡፡
  4. በሙከራ ጊዜ ውስጥ ከሁለቱም ወገኖች አንዱ ያለ ማስጠንቀቂያ የሥራ ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል
  5. አዲስ ለሚቀጠር ሠራተኛ ለጤንነትና ለአሸራ ምርመራ የሚላከው ሠራተኛ ተቀጥሮ ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ወጭውን አክ/ማህበሩ ይሸፍናል፡፡
  6. አዲስ የተቀጠረ ሠራተኛ የመጀመሪያው የሥራ አፈፃፀም ከተሞላለት ለዕድገት መወዳደር ይችላል፡፡

ለ/ ክፍት የሥራ መደቦች ማስታወቂያ ይዘት፣

  1. የሥራ መደቡ መጠሪያ
  2. ለሥራ መደቡ የተወሰነው ደረጃና ደመወዝ
  3. ከተወዳዳሪዎች የሚፈለግ የት/ደረጃና የሥራ ልምድ
  4. የዕድሜ ወሰንና ፆታ
  5. ማመልከቻ የሚቀርብበት የተወሰነ የጊዜ ገደብ
  6. ተወዳዳሪዎች ማቅረብ ያለባቸው ሌሎች ማስረጃዎችና ሠነዶች የወጭ ማስታወቂያ የጊዜ ገደብ አ/ማህበሩ በሚወስነው ይሆናል
  7. ፈተና የሚሰጥበት ጊዜና ቦታ
  8. የምዝገባ ሰዓትና ቢሮ

ሐ/ የቅጥር ኮሚቴ፡

1. በአ/ማህበሩ ውስጥ የቅጥር ኮሚቴ የሚከተሉትን አባላት የያዙ ይሆናል፡፡

ሀ/ የሰው ኃይል ል/አስተዳደር መምሪያ --------- ሰብሳቢ

ለ/ ዋ/ስ/ አስኪያጅ የሚወክለው ኃላፊ -------------------- አባል

ሐ/ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበር ተወካይ --------------- አባል

መ/ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍል ሃላፊ ------------- አባል

ሠ/ የሠው ሃይል ኦፊሰር ----------------------------------- ፀሐፊ

2. የቅጥር ኮሚቴ ተወዳዳሪዎችን በሚመረጥበት ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ በመስኩ ሙያ ዕውቅና ያለው ሰው አስተያየቱን እንዲሰጥበት የቅጥር ኮሚቴው ሊጋብዝ ይችላል፡፡

3. የቅጥር ኮሚቴ ተወዳዳሪዎችን በሚመርጥበት ጊዜ ውሳኔውን በድምጽ ብልጫ ይሠጣል፡፡ የአባሎች ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ ሰብሳቢው የሚገኝበት ወገን ወሳኝ ይሆናል፡፡

መ/ የቅጥር ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት፡

የአ/ማህበሩ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍል የቅጥር ማመልከቻዎች መሟላታቸውን ከአረጋገጠ በኋላ ለቅጥር ኮሚቴው ሲያቀርብ ኮሚቴው፡-

1. የአመልካቾችን ማስረጃዎች በመመርመር ፈተና በመስጠት ያወዳድራል፡፡

2. ኮሚቴው የተግባርና የቃል ፈተና ይሰጣል፣ በተለይ የተግባር ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል የመሣሪያ እጥረት አ/ማህበሩ ካለበት ከሌላ መ/ቤት ወስዶ ሊፈትን ይችላል፡፡

3. ብቁ የሆነውን አመልካች ይመርጣል፣ ብቁ የሆነው አመልካች ውጤት ብልጫ የሚለካው፡-

3.1. ቅጥሩ የሚፈፀመው በፈተና በመሆኑ የተግባርና የቃል ፈተና 5ዐ% እያንዳንዱ ይይዛል፡፡

3.2. የተግባር ፈተናው ከ25/5ዐ እና በላይ ያመጣ ብቻ ለቃል ፈተና ሊቀርብ ይችላል፡፡ በተግባር ፈተናው 25/5ዐ ያላመጣ ለቀጣይ የቃል ፈተና አይቀርብም

3.3. የሥራ መስኩ 1ዐኛ ወይም ከዚያ በላይ የሚጠይቅ ከሆነ እና በዚህ ፈተና እኩል ነጥብ ካገኙ በተፈላጊው የትምህርት ደረጃ ያላቸው የትምህርት ውጤት (ጅፒኤ) ታይቶ ሊበላለጡበት ይችላል፡፡

3.4. የሥራ መደቡ የተግባር ፈተና የማይጠይቅ ከሆነ የቃል ፈተና ተሰጥቶ በተገኘው ውጤት አሸናፊው ይለያል፡፡

ሠ/ የቅጥር ኮሚቴ የውሣኔ አሠጣጥ፡

1. የአ/ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይም ውክልና የተሰጠው ኃላፊ የቅጥር ኮሚቶ በሚያቀርብለት ሀሳብ ሲስማማ የተመረጠውን ተወዳዳሪ በፎርማሊቲው መሠረት እንዲቀጠር ይወስናል፡፡ በኮሚቴው ሀሳብ ካልተስማማ ግን ምክንያቱን በመግለጽ እርማትና አስተያየቱን በማከል ወደ ኮሚቴው ይልካል፡፡ ይህ ሁሉ ተፈጽሞ በቅጥር ኮሚቴው እና በአጽዳቂው የበላይ አካል መግባባት ካልተፈጠረ አጽዳቂው የበላይ አካል ልዩነቱን በጽሁፍ በማስቀመጥ ይወስናል፡፡ ውሣኔውም ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

2. በውሳኔው መሠረት የሚቀጠረው ተወዳዳሪ /አመልካች/ ስም በአ/ማህበሩ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጠፋል፤ ወይም አመልካች በሚሠጠው አድራሻ መሠረት እንዲያውቀው ያደርጋል፡፡

ረ/ ለተወሰነ ሥራ ሠራተኛ የሚቀጠርበት ሁኔታ፡

1. ሥራው ዘላቂነት የሌለው ከሆነና በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚያልቅ መሆኑ ከተረጋገጠ አ/ማህበሩ ለተወሰነ ሥራ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ሠራተኞችን አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ለተወሰነ ጊዜ መቅጠር ይችላል፡፡

2. ለተወሰነ ጊዜ የሚቀጠር ሠራተኛ በሚቀጠርበት የሥራ ውል ቅጽ ላይ የሠራተኛው ደመወዝ ሌሎች ጥቅሞችና ውሉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በመግለጽ ይሠጠዋል፡፡

አ ን ቀ ጽ 1ዐ

የሥራ ውል አመሠራረት

ማንኛውም ሰው ደመወዝ እየተከፈለው በአሠሪው መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለተወሰነ ወይም ለአልተወሰነ ወይም የተወሠነ ሥራ ለአሠሪው ለመሥራት በአሠሪው ሲቀጠር በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ምዕራፍ አንድ በአንቀጽ 4 እና 6 መሠረት የሥራ ውል በጽሁፍ ይሠጠዋል፡፡

አ ን ቀ ጽ 11

11.1 ደመወዝ

11.1.1 አክ/ማህበሩ ሠራተኛው ለሠራበት የሚከፍለው ደመወዝ ጥቅልና ተቀናናሽ ሂሳቦችን ሊያውቅ በሚችልበት ግልጽ የክፍያ ሠነድ አዘጋጅቶ ክፍያውን ይፈጽማል፡፡

11.1.2 ሠራተኛው ሥራው ላይ ተገኝቶ ለሥራው የሚያስፈልገው መሣሪያና ጥሬ ዕቃ ሳይቀርብለት በመቅረቱ ወይም በሠራተኛው ጉድለት ባልሆነ ምክንያት ሳይሠራ ቢውል መደበኛ ደመወዝ አይቆረጥበትም። ሆኖም ከአሠሪው አቅምና ቁጥጥር ውጭ በሚሆኑ ተፈጥሮአዊና አገራዊ ችግሮች ምክንያት አክ/ማህበሩ መሥራት ባይችል በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

11.1.3 አ/ማህበሩ ባወቀውና በተስማማበት ምክንያት ሠራተኛው በደመወዝ መክፈያ ጊዜ ቀርቦ መቀበል ካልቻለ ለወከለው ሰው አ/ማህበሩ ይሰጥለታል፡፡

11.1.4 የወሩን ወደ ቀን ለማዛወር ማባዣው ወይም ማካፈያው 26 ቀን ነው፡፡

11.1.5 የደመወዝ መክፈያ ቀን በባዕል ቀን የሚውል ከሆነ ከበአሉ በፊት በአለው ቀን ይከፈላል፡፡ ሆኖም ከዚህ የተለየ ሁኔታ ሲያጋጥም በማሕበሩ አሳሳቢነት አ/ማህበሩ ይተባበራል፡፡ የደመወዝ መክፈያ ጊዜ እ.ኤ.አ. ወሩ በገባ በ28 ቀን ይሆናል፡፡

11.1.6 በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልሆነ ወይም ሠራተኛው በጽሁፍ ካልተስማማ ወይም በልዩ ልዩ ጉዳይ በሰነድ ፈርሞ የተረከበውን ገንዘብ በወቅቱ አወራርዶ ያልከፈለውን ገንዘብ ካልሆነ በስተቀር አሠሪው ከሠራተኛው ደመወዝ ሊቀንስና ደመወዙን በዕዳ ሊይዝ፣ ሊያቻችል አይችልም፡፡ ሆኖም አ/ማህበሩ ከሠራተኛው ጋር ያለው የሥራ ግንኙነት ውል ካልተቋረጠ በስተቀር ከሠራተኛው ደመወዝ ከ1/3ኛ በላይ መቁረጥ አይቻልም፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው በፁኁፍ ከተስማማ ከ1/3ኛ በላይ ሊቆርጥ ይችላል፡፡

11.1.7 አ/ማህበሩ ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ ለመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ የአባልነት መዋጮን በደመወዝ መክፈያ ሊስት ላይ እራሱን ችሎ በሚያሳይ ኮሎመን ላይ አስፍሮ በመቀነስ ለሠራተኛ ማሕበሩ በየወሩ ገቢ ያደርጋል፡፡

አ ን ቀ ጽ 12

12.1 የውሎ አበልና የመጓጓዣ ወጭ፡

12.1.1 ለመተማ፣ ለሁማራ፣ ለዱፍቲና ሌሎች በአገሪቱ ተመሳሳይ የበረሃ ፀባይ አላቸው ተብሎ የተወሰነባቸው አካባቢዎች ለሥራ ጉዳይ ለሚሄድ ሠራተኛ የውሎ አበል አከፋፈል ከመደበኛ ውሎ አበል ልዩ ተጨማሪ፡-

  • ለአነስተኛ በረሃማ በሆነ ቦታ ---------- 2ዐ%
  • መካከለኛ በረሃማ በሆነ ቦታ ---------- 3ዐ%
  • ከፍተኛ በረሃማ በሆነ ቦታ ------------ 4ዐ%

ይሁን እንጅ የበረሃ አበልና የውጭ ሀገር አበልን በተመለከተ መንግስት እየተጠቀመበት ባለው መመሪያ መሠረት ይወሰናል፡፡

12.1.2 በሥራ ጉዳይ ከተመደቡበት ሥራ ውጭ ለተጨማሪ ስራ አ/ማህበሩ አውቆት ለሚሄድ ሠራተኛ አ/ማህበሩ የመጓጓዣ ወጭ በሕዝብ ማመላለሻ ታሪፍ በተወሰነው መሠረት ይፈጽማል፡፡

12.1.3 ሠራተኛው የመስክ ሥራውን አከናውኖ እንደተመለሰ የውሎ አበል ሂሳቡን በ 7 ቀናት ውስጥ ካላወራረደ ከደመወዙ ይወራረዳል፡፡

12.1.4 የውሎ አበል ለአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች ለስራ ጉዳይ ከባህር ዳር ውጭ በሚጓዙበት ጊዜ በቀን 700.00 /ሰባት መቶ/ ብር ይከፈላቸዋል። ይኸውም፡-

  • የምግብ 400 ብር
  • ለአልጋ 300 ብር ሁኖ በሚያቀርበው ህጋዊ ደረሰኝ መሰረት ይወራረዳል።

አ ን ቀ ጽ 13

13.1 ሥራን በውክልና ማሠራትና ስለሚከፈለው ክፍያ፤

13.1.1 ተወካይ የሚመደብበት አንድ የኃላፊነት የሥራ መደብ ክፍት ሲሆንና ቋሚ ሠራተኛ እስኪመደብ ወይም ጊዜያዊ ሠራተኛ በቦታው መመደብ የማይቻልበት ወይም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ፣ አንድ የሥራ ኃላፊ ለተወሰነ ጊዜ በሥራ ጉዳይ፣ በህመም፣ በዓመት እረፍትና በመሳሰሉት ምክንያት ከሥራ ገበታው ሲለይ የሥራ መደቡን ለመሸፈን ነው፡፡

13.1.2 በውክልና የሚመደብ ሠራተኛ ለክፍት የሥራ መደቡ ቀራቢና የተሻለ ልምድና አፈፃፀም ያለው ይሆናል።

13.1.3 ተወካይ ሠራተኛ የሚመደበው የአ/ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ በማስፈቀድ ሆኖ ተወካይ በደብዳቤ ሲገለጽለት ነው፡፡ ነገር ግን ውክልናው ለአጭር ጊዜ ማለትም ከ1ወር በታች ከሆነ የመምሪያ/የአገልግሎት ሃላፊው በራሱ ሊወክል ይችላል።

13.1.4 ከአንድ ወር በላይ በውክልና ለተመደበ ሠራተኛ የውክልና ክፍያ በሚከተለው አኳኋን ይከፈለዋል፡፡
ሀ/ ከተመደበበት የስራ ደረጃ ከፍ ወዳለ ደረጃ ሲወከል በቋሚ ደመወዝ ተከፋዮ እና በተወካዩ ደመወዝ መካከል ያለው ልዩነት 25% ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ከብር 5ዐዐ.ዐዐ አይበልጥም። ሆኖም አንድ የሥራ ኃላፊ የበታች ሠራተኛውን ሥራ ደርቦ እንዲሠራ ሲደረግ የውክልና አበል አይከፈለውም፡፡ እንዲሁም በተመሳሳይ ደረጃ የሚገኝና አስተራራፊዎች ተመድበው ሲሰሩ የውክልና አበል አይከፈላቸውም፡፡

13.1.5 የውክልና ጊዜ ከ3 ወር መብለጥ የለበትም፡፡ ሆኖም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት መኖሩ ሲረጋገጥ የአ/ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጊዜውን ለማራዘም ይችላል፡፡ በዚህም መሠረት የውክልናው ጊዜው እንዳበቃ ለተወካዩ በደብዳቤ ይገለጽለታል፡፡

አ ን ቀ ጽ 14

14.1 የሥራ አፈፃፀም መመዘኛ ስለመሙላት፤

14.1.1 የእያንዳንዱ ሠራተኛ የሥራ ችሎታ እንቅስቃሴ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ለመመዘን የሚያስችል መግለጫ በዓመት 2 ጊዜ በታህሣስ እና በሰኔ መጨረሻ ይሞላል፡፡

14.1.2 የሥራ አፈፃፀም ለመሙላት የሆርሻ አባላት ከሥራ መሪዎች ጋር አብረው በታዛቢነት ይገኛሉ፣

14.1.3 የግምገማው ውጤት ሠራተኛው እንዲያውቀው ተደርጐ በማሕደሩ ውስጥ ይቀመጣል፡፡

14.1.4 የሥራ አፈፃፀም መመዘኛዎችን ማኔጅመንቱ ያዘጋጃል፡

አ ን ቀ ጽ 15

15.1 ስለግል ማሕደር አያያዝ፣

ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱት መረጃዎች በእያንዳንዱ ሠራተኛ የግል ማህደር ውስጥ በሚገባ ተጠናቅቀው መገኘት አለባቸው፡፡

አዲስ ለተቀጠረ ሠራተኛ ለክፍት የሥራ መደብ የወጣው ማስታወቂያ

15.1.1 የቅጥር ኮሚቴ ቃለ ጉባዔ

15.1.2 ሠራተኛው በቅርብ ቀን የተነሳው 3 ጉርድ ፎቶ ግራፍ

15.1.3 የሠራተኛው የሕይወት ታሪክ ቅጽ ተሞልቶ የትምህርት የምስክር ወረቀት፣ በሌላ ድርጅት ውስጥ አገልግሎት የሰጠ ከሆነ የጽሑፍ ማስረጃው ይያዛል፣

15.1.4 በመጀመሪያ ቅጥር ወቅት ከታወቀ ሆስፒታል የተሠጠው የጤንነት ምርመራ የምስክር ወረቀት፡

15.1.5 የተቀጠሩበት የቅጥር ደብዳቤ

15.1.6 የሙከራ ጊዜውን ጨርሶ ቋሚ ሠራተኛ ለመሆኑ የተሠጠው የማረጋገጫ ደብዳቤ

15.1.7 በህ/ስምምነቱ መሠረት በሠራተኛ ላይ የተወሰዱ የስነ ስርዓት እርምጃ ካለ

15.1.8 የጡረታ ቅጽ ድ/ጡ/1.1 ሠራተኛው የሞላው

15.1.9 በሠራተኛው ላይ አደጋ ደርሶ እንደሆነ የአደጋው ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ ቅጽ

15.1.10 ሠራተኛው በጡረታ የተገለለ ከሆነ ወይም ከሥራ የተሰናበተ ከሆነ የተሰጠው የመልቀቂያ የምስክር ወረቀት ሠራተኛው ከሞተም የሥራ ውል የተቋረጠበት ማስረጃ

15.1.11 ማንኛውም የሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ ይጠቅማል ያለውን ጽሁፍ ሁሉ ያካትታል ሆኖም ሠራተኛው እንዲያውቀው ያልተደረገ ማንኛውም ወቀሳ፣ ቅጣት፣ ማስጠንቀቂያ በግል ማሕደሩ ቢቀመጡ ዋጋ አይኖራቸውም፡፡

15.1.12 በዚህ ህ/ስምምነት አንቀጽ 2ዐ ፊደል “ረ “በተገለፀው መሠረት ለሚሰጥ የሐዘን ፈቃድ ሠራተኛው የቤተሰቡን የዝምድና ደረጃ ለይቶ ሲቀጠር በሕይወት ያሉትን ያስመዘግባል፡፡ በተጨማሪ ከተቀጠረ በኋላ አዲስ ቤተሰብ ካፈራ በሚያመጣው መረጃ መሰረት ይመዘገብለታል።

15.1.13 ሌሎች መሰል መረጃዎችን እንዲሟሉለት ያደርጋል፡፡

አ ን ቀ ጽ 16

16.1 መደበኛ የሥራ ሰዓት

16.1.1 መደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን 8 /ስምንት ሰዓት/ በሳምንት ከ48 /አርባ ስምንት/ ሰዓት አይበልጥም፡፡ ይህም አምራች ሠራተኞችና ፈረቃ እየገቡ የሚሠሩ ማናቸውንም ሠራተኛ ያጠቃልላል፡፡

16.1.2 ሥራው ከምርት ጋር በቀጥታ በመያያዙ የፈረቃ ሠራተኛ ካልሆነ በስተቀር በመደበኛ ሰዓት የሚሠሩ ሠራተኞች፣
ሀ/ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2፡3ዐ - 6፡3ዐ ከሰዓት በኋላ ከ7፡3ዐ-11፡ዐዐ ሰዓት
ለ/ ቅዳሜ ከ2፡3ዐ እስከ 6፡0ዐ ሰዓት ተገቢውን አግልግሎት ይሠጣሉ፡፡
ሐ/ እንደሥራው ባሕሪ እየታዩ የመግቢያና የመውጫ ሰዓት በአ/ማህበሩ ሊሻሻል ይችላል፡፡

16.1.3. ማንኛውም ሠራተኛ በሥራው መካከል ለመመገቢያ፣ ለሻይ መዝናኛ ከመደበኛ የሥራ ስዓት የሚቆጠር 30 ደቂቃ የመዝናኛ ካንቴኑ በሚያዘጋጀው ኘሮግራም መሠረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡

16.1.4. በህፃናት ማቆያ ህፃናት ያላችው እናቶች የጡት ማጥቢያ ጊዜ ከምሳ ስዓታቸው በተጨማሪ 30 ደቂቃ በአጠቃላይ 1፡00 ስዓት ይፈቀድላቸዋል። በመውጫና መግቢያ ሰዓታቸውም ልጆቻቸውን ለመረካከብ 10 ደቂቃ ትብብር ይደረግላቸዋል፡፡

አ ን ቀ ጽ 17

17.1 የትርፍ ሰዓት ሥራ አከፋፈል

17.1.1 ሠራተኛው የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ አይገደድም ሆኖም አሠሪው ሌላ አማራጭ መንገድ ሊኖረው አይችልም ብሎ ሲገመትና አደጋ ሲደርስ ወይም የሚደርስ መሆኑ ሲታመን ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም የማይቋረጥና ተከታታይ ሥራ ላይ የሚሠሩ ሠራተኞች ሲቀሩ ለመተካት አሠሪው ትርፍ ሰዓት እንዲሠራ ሲያዝ የሚከናወን ይሆናል፡፡ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አፈፃፀም እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡

ሀ/ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ለሚሠሩ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራ ሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በአንድ ተኩል /11/2 / ተባዝቶ ይከፈላል፡፡

ለ/ ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት የሚሠሩ ሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራ ሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ አንድ ሶስት አራተኛ /1 3/4/ ተባዝቶ ይከፈላል፡፡

ሐ/ በሕዝብ በዓል ቀን የሚሠራ የትርፍ ስዓት ሥራ ከመደበኛ ሥራ ስዓት የሚከፈለው ደመወዝ በሁለት ተኩል (21/2) ተባዝቶ ይከፈላል፡፡

መ/ በሳምንት የዕረፍት ቀን ለሚሠሩ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራው በሰዓት የሚከፈለው በሁለት /2/ ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡

ሠ/ ኀ/ስምምነቱ የሚመለከተው ሠራተኛ ሁሉ ትርፍ ሰዓት ከሠራ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይከፈለዋል፡፡

17.1.2 ነፍሰ ጡር ሴቶች የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠሩ አይገደዱም፡፡

17.1.3 የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከደመወዝ ጋር ተደምሮ ይከፈላል፡፡

17.1.4 በአዋጁ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 67 ንዑስ ቁጥር 2 መሠረት የትርፍ ሰዓት በቀን ከ4 ሰዓት በሳምንት ከ12 ሰዓት መብለጥ የለበትም፡፡ ሆኖም ግን ስራው አስገዳጅ ሁኖ ከተጠቀሰው ሰዓት በላይ ከተሰራ ለተሰራበት ሰዓት ክፍያ ይፈፀማል፡፡

አ ን ቀ ጽ 18

18.1 የሣምንት የዕረፍት ቀን

በአዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 69 መሠረት ከሰኞ እስከ እሁድ ባሉት ቀናት በኘሮግራም ተወስኖ እረፍት ይሠጣል፡፡

አ ን ቀ ጽ 19

19.1 የሕዝብ በዓላት

ሀ/ በሕዝብ በዓላት ቀን መሥራት የሚያስፈልግ ሆኖ ሲገኝ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 68 (1) (መ) መሠረት በሰዓት የሚገኘው ክፍያ /21/2 / ሁለት ተኩል ተባዝቶ በበአሉ ቀን ለሠራበት ለእያንዳንዱ ሰዓት ይከፈለዋል፡፡

ለ/ አንድ የሕዝብ በዓል ከሌላ በዓል ተደርቦ የሕዝብ በዓል ወይም በአዋጅ 1156/2011 ወይም ከማንኛውም ልዩ ሕግ በተወሰነ የእረፍት ቀን ላይ ቢውልና ሠራተኛው ሥራ እንዲገባ ቢደረግ በዚሁ ቀን ለሠራተኛው ክፍያ የሚደረግለት በአንድ የሕዝብ በዓል ይሆናል፡፡

አ ን ቀ ጽ 2ዐ

20.1 ልዩ ልዩ ፈቃድ

ሀ/ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ

20.1.1 የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ማለት አንድ ሠራተኛ በዓመት ውስጥ ለተወሰኑ ቀኖች ከደመወዝ ጋር ዕረፍት የሚሰጠው ፈቃድ ነው፡፡

20.1.2 የአ/ማህበሩ ሠራተኞች ሁሉ የዓመት ዕረፍት ፈቃዳቸውን በአዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 77 መሠረት ከደመወዛቸው ጋር እንደሚከተለው ያገኛሉ፡፡

ሀ/ አንድ ዓመት ያገለገለ ሠራተኛ 16 የሥራ ቀን ፈቃድ ያገኛል፡፡

ለ/ ከአንድ ዓመት በላይ ያገለገለ ሰራተኛ ከላይ በ “ሀ” በተመለከተው ላይ ለአገለገለበት ለእያንዳንዱ 2 የአገልግሎት ዓመታት ተጨማሪ አንድ የሥራ ቀን እየታከለ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ያገኛል፡፡

ሐ/ ሠራተኛው የዓመት እረፍት በወሰደበት ጊዜ በመካከሉ የሕዝብ በዓል ካለ ወይም ከተገኘ ከዓመት ዕረፍት ቀኑ አይታሰብበትም፡፡

20.1.3 በህ/ስምምነቱና በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ ያልወሰደው የዓመት ፈቃድ በአዋጁ መሠረት ታስቦ በገንዘብ ይከፈለዋል፡፡

20.1.4 የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሠራተኛ የአገልግሎት ዘመኑ ከአንድ ዓመት በታች ከሆነ በአገልግሎት ልክ ተመጣጣኝ የሆነ ዕረፍት በዚያው በአገልግሎት ዓመቱ ታስቦ ይሠጠዋል፡፡

20.1.5 አሠሪው በሚያወጣው የዓመት ፈቃድ መስጫ ኘሮግራም መሠረት በእያንዳንዱ ዓመት የሚያገኘውን የዓመት ፈቃድ ለሠራተኛው ይሠጠዋል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥመው የቅርብ አለቃውን በመጠየቅ አሣማኝ ሆኖ ሲገኝ የዓመት ፈቃድ ተሠጥቶት ይሄዳል፡፡ አንድ ሠራተኛ ሥራ ከገባ በኋላ ችግር ገጥሞት ዓመት ፈቃድ ከወጣ ወይም በመምሪያ/አገልግሎት ትዕዛዝ የሥራ ሰዓቱን እንዲያቋርጥ ቢደረግ የሠራበት ሰዓት ተይዞለት በሌላ ቀን እንዲያርፍበት ይደረጋል፡፡

20.1.6 በሠራተኛው ጠያቂነት አሠሪው ሲስማማ የዓመት ፈቃድ ሊተላለፍ ይችላል ፡፡ አ/ማህበሩ በተለያዩ ምክንያት አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጠር የፈቃዱ መስጫ ጊዜውን ሊያስተላልፈው ይችላል፡፡ የተላለፈውን የዓመት ፈቃድ አመቺ ጊዜ በመፈለግ ሠራተኛው እንዲወስድ ይደረጋል፡፡ ሆኖም በምንም ሁኔታ የዓመት ፈቃድ ከሁለት ዓመት በላይ አይተላለፍም፡፡

20.1.7 አንድ ሠራተኛ የዓመት ፈቃድ ላይ ባለበት ጊዜ ቢታመም ከሐኪም በሚሠጠው የሕመም ፈቃድ ልክ የዓመት ፈቃድ ይራዘምለታል፡፡ ይህንንም ለአክሲዮን ማህበሩ ያሳውቃል፡፡

20.1.8 በፈቃድ ላይ ያለን ሠራተኛ አ/ማህበሩ ከፈለገ በማንኛው ጊዜ ስራ እንዲገባ ሊያደርግ ይችላል።

20.1.9 ሠራተኛው አ/ማህበሩን የዓመት ፈቃዱን ከፋፍሎ እንዲሠጠው ሲጠይቅና አሠሪው ሲስማማ ይሠጠዋል፡፡

20.1.10 ሠራተኛው ከፈቃድ ሲጠራ በጉዞ ያጠፋው ጊዜ ሳይቆጠር የዓመት ፈቃድ በገንዘብ ተተምኖ ሊከፈለው ይችላል፡፡

20.1.11 ሠራተኛው ከፈቃድ በመጠራቱ ምክንያት የደረሰበትን የመጓጓዣና የውሉ አበል ወጭ አሠሪው ይሸፍናል፡፡

20.1.12 በተራ ቁጥር 20.1.6 እና 20.1.8 የተመዘገቡት ተግባራዊ የሚሆኑት የአ/ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲያፀድቀው ብቻ ነው፡፡

20.1.13 አሠሪው የፈቃድ መስጫ ኘሮግራሙን የሚያወጣው በእያንዳንዱ ሠራተኛ ፍላጐትና አሠሪው ሥራውን በተለመደው ሁኔታ እንዲሠራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በተቻለ መጠን በማገናዘብ ይሆናል፡፡

20.1.14 ሠራተኛው ከጠየቀና አ/ማህበሩ ካመነበት የዓመት ፈቃድ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ይከፈለዋል፡፡

20.1.15 አ/ማህበሩ በሊዝም ሆነ በሽያጭ የባለቤትነት ስም ለውጥ ሲያደርግ የተጠራቀመ የሠራተኛ የዓመት ፈቃድና ሌሎች ጥቅማጥቅም በገንዘብ ተተምኖ ይከፈላል፡፡

ለ/ የሕመም ፈቃድ፣

20.1.1 ማንኛውም ሠራተኛ የሕመም ፈቃድ የሚያገኘው በአ/ማህበሩ ክሊኒክ አማካኝነት ወደ ታወቀ የመንግስት ህክምና ድርጅት ተልኮ ተገቢ የሆነ የህክምና የምስክር ወረቀት ሲያቀርብ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከሥራው ወጥቶ በዕረፍት ላይ እያለ ድንገተኛ ህመምና አደጋ ገጥሞት በትራንስፖርት እጥረት በአ/ማህበሩ ክሊኒክ ሊታከም ካልቻለ ከመንግስትና ከግል ከፍተኛ ህክምና ተቋሞች ማስረጃ ሲያቀርብ እና የደረሰበትን ህመም ወይም አደጋ ከቤተሰቡ አንድ ሰው ወይም ተጠሪው ለአ/ማህበሩ ሲያሳውቅ የፈቃድና የሕክምና ወጭ ይከፈለዋል፡፡ በመሆኑም ድንገተኛ ህመም የምንላቸው ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ከፍተኛ የስኳር በሽታ፣ ድንገተኛ የልብ ድካም፣ የሚጥል በሽታ፣ ከፍተኛ ተቅማጥና ትርፍ አንጀት እንዲሁም ከፍተኛ የደም መፍሰስ ህመም ናቸው፡፡ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ለሚሄዱ ታካሚዎች የሰርቪስ አገልግሎት ይሰጣል።

20.1.2 የአ/ማህበሩ ክሊኒክ ሆስፒታል የተላኩትንና የተኙትን ሠራተኞች ዝርዝር በዕለቱ ለሰው ኃይል ል/አስ/ መምሪያ ያሳውቃል፡፡

20.1.3 የሕመም ፈቃድ የተሠጠው ሠራተኛ ፈቃዱ እንደ አለቀ ወደ ሥራው መመለስ አለበት፡፡ ሕመሙ ያልተሻለው እንደሆነ የተሰጠውን ፈቃድ ጨርሶ ወደ ሥራው እንደገና መመለስ ካልቻለ ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ክሊኒኩ በመሔድ መመርመር ይችላል፡፡

20.1.4 ሠራተኛው በህመም ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የሥራ ቦታውን ወይም አካባቢ እንዲለወጥ የሐኪም ቦርድ ካዘዘለት የትዕዛዙን በጽሑፍ ለሰው ኃይል ል/አስ/ መምሪያ ማቅረብ አለበት፡፡ የሰው ኃይል ል/አስ/ መምሪያ የሐኪሙን ትዕዛዝ መሠረት አድርጐ ሊሠራ ይችላል ብሎ በሚያምንበት ቦታ መድቦ ያሠራል፡፡

20.1.5 በዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወይም በሌላ ሕጋዊ ፈቃድ ሠራተኛው ከባሕር ዳር ውጭ ባለበት ጊዜ ታሞ ቢታከም መብቱ አይቀንስም፡፡ ይኸውም በአደጋ፣ በድንገተኛ ህመም በምንላቸው በተራ ቁጥር 20.1.16 የተካተቱት ድንገተኛ ህመምና አደጋ ከደረሰበት በመንግስትና በግል ከፍተኛ የህክምና ተቋማት ማስረጃ ሲያቀርብ አስፈላጊውን ክፍያ ይፈጽማል፡፡

20.1.6 ከሥራው ጋር ባልተያያዘ ሕመም ቋሚ ሠራተኛው ሲታመም ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ መሠረት ሕክምና እና ደመወዝ ያገኛል፡፡

የሚፈቀደው የሕክምና ጊዜ የሕክምና ዕርዳታ ከደመወዙ የሚሠጠው
4 ወር 1ዐዐ% 1ዐዐ%
4 ወር 1ዐዐ% 75%
4 ወር 1ዐዐ% 5ዐ%

የህክምና ቆይታዎች /ፈቃድ/ ህጋዊ ከሆነ የመንግስት የህክምና ተቋም ማስረጃ ማቅረበ አለበት። ሆኖም ግን ሠራተኛው ድኖ ወደ ሥራው ካልተመለሰና የተሰጠው የጊዜ ገደብ ካለቀ በኋላ ድርጅቱ ከሥራ ያሰናብተዋል፡፡ ከላይ የተመለከተውን የሕክምና ዕረፍት መብት ከዓመት ወደ ዓመት አይዘዋወርም፡፡ ይህ የሕክምና ጊዜ የሚታሰበው ሕመምተኛው የሕክምና ፈቃድ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ እንዲሁም በኤች አይቪ ኤድስ፣ በካንሰር፣ በኩላሊት ሁሙማን ለአንድ ዓመት ታምመው ቢተኙ 100% ህክምና እና 100% ደመወዝ ይከፈላቸዋል።

ሐ/ የወሊድ ፈቃድ፣

20.1.7 ነፍሰ ጡር የሆነች ሠራተኛ ከዕርግዝና ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ አሠሪው ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሠጣል፡፡ ሆኖም ሠራተኛዋ ከምርመራ በኋላ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ አለባት፡፡

20.1.8 ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከመውለዷ በፊት ሐኪም እንድታርፍ ካዘዘ ከክፍያ ጋር ዕረፍት ይሠጣታል፡፡

20.1.9 ነፍሰ ጡር የሆነች ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት መውለጃዋ ቢደርስ የ 3ዐ ቀን ተከታታይ ቀናት የወሊድ እንዲሁም ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ ቀናት የወሊድ ፈቃድ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 መሠረት የወሊድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሠጣታል፡፡ በኦፕራሲዮን የወለደች እናት የወሊድ ፈቃዷን ጨርሳ ወደ ስራ ስትመለስ ለ 6 ወር በኖርማል ፈረቃ እንድትሰራ ይደረጋል።

20.1.10 ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ3ዐ ቀን ፈቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከ ምትወልድበት ቀን ድረስ በዚህ ስምምነት ተራ ቁጥር 21.1.22 መሠረት ዕረፍት ልታገኝ ትችላለች የ 3ዐ ቀን ፈቃድ ሳያልቅ ከወለደች በዚህ ስምምነት ተራ ቁጥር 21.1.23 መሠረት የምትወስደው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ይቃጠላል፡፡ ሆኖም ግን ሀኪሙ በእርግዝና ላይ የምትገኝን ሠራተኛ ቅድመ ወሊድ ሰዓቷ ሲደርስ ተከታትሎ እረፍት እንድትወጣ ያደርጋል።

20.1.11 ሠራተኛዋ ከላይ የተመለከተው የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመም በዚህ አንቀጽ ፊደል “ ለ “ የሐኪም ፈቃድ ይሠጣታል፡፡

20.1.12 አንድ ሠራተኛ ሕጋዊ ሚስቱ በወለደችበት ዕለት ደመወዝ የሚከፈልበት የ4 ተከታታይ ቀን ፈቃድ ይሠጠዋል፡፡

20.1.13 ለነፍሰ ጡር ሴቶች የሥራ ሁኔታ በአዋጁ መሠረት ይፈፀማል፡፡

20.1.14 ሴቶች በህጋዊ ህክምና እርግዝናቸው በጤናቸው ላይ ችግር የሚፈጥር መሆኑ በሐኪም ሲረጋገጥና ውርጃ እንዲፈፀም ሲደረግ የድህረ ወሊድ ፈቃድ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ይህም ጽንሱ ከ6 ወር እና በላይ ከሆነው ብቻ ነው።

መ/ የጋብቻ ፈቃድ፣

ማንኛውም የአ/ማህበሩ ሠራተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ የህግ ሚስት ወይም ባል ሲያገባ ወይም ስታገባ ሠራተኛው ወይም ሠራተኛዋ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀን የጋብቻ ፈቃድ ከመደበኛ ደመወዝ ጋር ይሠጠዋል /ይሠጣታል/ ይህም ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ሠ/ ለማህበር መሪዎች የሚሰጥ ፈቃድ፣

20.1.29 በኀ/ስምምነት ድርድር፣ በማሕበር ስብሰባ ለመገኘት፣ በሲሜናሮችና ሥልጠና ለመካፈል እንዲቻል ለማሕበሩ አመራር አባላት ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሠጣቸዋል፡፡ ይህም ከአ/ማህበሩ ውጭ ሲሆን ነው፡፡

20.1.30 የሰራተኛ ማህበሩ ሊ/መንበር እና ፀሐፊ በሙሉ ጊዜ የመሀበሩን ስራ ይሰራሉ፡፡ የመሰራታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊ/መንበር በሚያቀርበው ጥያቄ መሰረት ለማህበር ስራ አስፈፃሚ አባላት በወር አንድ ቀን የመሰብሰቢያ ቀን ይፈቅዳል፡፡ ከአ/ማህበሩ ማኔጅመንት ጋር በወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል፡፡

20.1.31 በማዕከላዊ መንግስት፣ በክልል መስተዳደር፣ በአገር አቀፍ ሠራተኛ ማሕበር በኩል ለሚገኝ የትምህርት ዕድል የማሕበር መሪዎች በመንግስት መመሪያ መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት የትምህርት ፈቃድ ይሠጣቸዋል፡፡

20.1.32 በየክፍሉ የሚገኙ የምክር ቤት /ሆርሻ/ አባላት እንደ አስፈላጊነቱ በ3 ወር አንድ ጊዜ ከአንድ የሥራ ቀን ያልበለጠ ለስብሰባ ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሠጣቸዋል፡፡ ሆኖም ማሕበር አስቸኳይ ጉዳይ ሲገጥመው አክ/ማሕበሩን በማስፈቀድ ሊሰበሰብ ይችላል፡፡

20.1.33 አንድ ሠራተኛ ለፌደሪሽን ወይም ኮንፌዴሪሽን ተመራጭ ሲሆን አክ/ማበሩ ፈቃድ ይሠጣል፡፡

20.1.34 ማሕበሩ ለጠቅላላ ጉባዔ የሥራ ሪፖርት በሚያቀርብበት ጊዜ በዓመት አንድ ቀን ከደወዝ ጋር የሚከፈል ፈቃድ ይሠጣል፡፡

ረ/ የሀዘን ፈቃድ፣

20.1.35 የአንድ ሠራተኛ ባል ወይም ሚስት፣ አባት ወይም እናት፣ ልጅ፣ ወንድም፣ እህት፣ አያት፣ አክስት፣ አጐት፣ የወንድም ልጅ፣ የእህት ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የባል ወይም የሚስት ወንድም፣ የባል ወይም የሚስት እህት ወይም የባል ወይም የሚስት አባትና እናት፣ የእንጀራ ልጅ፣ የእንጀራ አባት፣ የእንጀራ እናት፣ የወንድም ሚስት፣ የእህት ባል ሲሞቱበት 5 ተከታታይ ቀን ከመደበኛ ደመወዝ ጋር የሀዘን ፈቃድ ይሠጠዋል፡፡

20.1.36 ለሠራተኛው ከላይ የተጠቀሰውን የሀዘን ፈቃድ የሚሠጠው ወዲያውኑ ራሱ ወይም በሌላ ሰው አማካኝነት የደረሰበትን ሀዘን ለአክሲዮን ማሕበሩ የሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ ሲያሳውቅ ነው፡፡

20.1.37 ከአ/ማህበሩ ሠራተኛ መካከል በሞት ሲለይ በቀብር ስነ ሥርዓት ላይ ከመምሪያው/አገልግሎቱ እንዲሁም ከማሕበር መሪዎች የሚገኙበት ጠቅላላ 1ዐ /አሥር/ ሠራተኞች እንዲገኙ ይፈቀዳል፡፡

20.1.38 አ/ማህበሩ ለቀብር ማስፈፀሚያ የ 2 ወር ደመወዝ ለቤተሰብ ይሠጣል፡፡ ይህም ድንጋጌ ተፈፃሚ የሚሆነው አ/ማህበሩ ላልተወሰነ ጊዜ ለቀጠራቸው ሠራተኛች በሞት ከተለዩ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

20.1.39 ይህን የቀብር ማስፈፀሚያ ገንዘብ አ/ማህበሩ ለዕዳ ማካካሻ ሊያውለው አይችልም፡፡

20.1.40 ከተራ ቁጥር 20.1.35 የተመለከቱት ተፈፃሚ የሚሆኑት በሠራተኛው የግል ማሕደር በደንቡ መሠረት አስቀድሞ ተመዘግቦ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡

ሰ/ ለትምህርት ወይም ለሥልጠና የሚሠጥ ፈቃድ፣

20.1.41 በአገር ውስጥ ለሚሰጥ ስልጠና አክሲዮን ማሕበሩ ፈቅዶ ለላከው ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሠጠዋል፡፡

20.1.42 በውጭ ሀገር የሚሠጥ የስልጠና ትምህርት ሠራተኛው ሠልጥኖ እና ትምህርቱን ጨርሶ እስኪመለስ ድረስ አ/ማሕበሩ ለሠራተኛው መደበኛ ሙሉ ደመወዙን ይከፍለዋል፡፡

20.1.43 ከስልጠና እንደተመለሰ ትምህርት የወሰደበትን ጊዜ እጥፍ ለአ/ማህበሩ ሳያገለግል በግል ፈቃዱ ሥራ ሊለቅ አይችልም ሆኖም በስልጠና ወቅት አክሲዮን ማሕበሩ ለሠራተኛው ያወጣውን ማንኛውም ወጭ ተመላሽ ካደረገ ስንብት ይፈቀድለታል፡፡

20.1.44 ከላይ በተራ ቁጥር 20.1.41 እና 20.1.43 የተዘረዘሩትን የሚሠጡት በቅድሚያ አክ/ማህበሩ ሲስማማና ሲፈቅድ ብቻ ነው፡፡

20.1.45 ሠራተኛ ማህበሩ ሠራተኛውን ለማሠልጠን ቢፈልግ ቅደሚያ ለአ/ማህበሩ አቅርቦ በማኔጅመንቱ ሲፈቀድ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

20.1.46 የበላይ አካል ለስልጠና እና ለስብሰባ ሲጠየቅ ከማህበሩ አባላት ወይም አመራር ተመልምለው ሲሄዱ አክ/ማህበሩ ከደመወዝ ክፍያ ጋር ፈቃድ ይሠጣል፡፡

ሸ/ ሕጋዊ መብትና ግዴታ ለማስፈፀም የሚሠጥ ፈቃድ፣

20.1.47 አንድ ሠራተኛ ከአ/ማሕበሩ ጋር የሥራ ክርክር ሲመሠረት ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሠጣል፡፡ ሆኖም ግን ከሚመለከታቸው አካል ከስንት ሰዓት እስከ ስንት ሰዓት እንደቆዩ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ ለምስክርነት ካልተፈለጉ በስተቀር የሰራተኛ ማህበር ፅ/ቤት ተወክሎ እየተከራከረላቸው ከሆነ ፈቃድ አይሰጣቸውም፡፡ አዳርና አምሽ ፈረቃ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ቀኑን ሙሉ ፍርድ ቤት ከዋሉ ፈቃድ ይያዝላቸዋል፡፡ በጠዋት ፈረቃ ላይ ያሉ ሰራተኞች ከፍርድ ቤት ውሏቸውን እንደጨረሱ ወደ ስራ መመለስ አለባቸው፡፡

20.1.48 አንድ ሠራተኛ የሲቪል መብቱን ሲያስጠብቅ ወይም የሲቪል ግዴታውን ሲፈፀም ለዚሁ አላማ ላጠፋው ጊዜ ብቻ ከክፍያ ጋር ፈቃድ ይሠጠዋል፡፡

20.1.49 ከላይ በተራ ቁጥር 20.1.47 እና 20.1.48 የተጠቀሱት ተቀባይነት የሚኖረው ከዋለበት መ/ቤት ሕጋዊ የሆነ ማስረጃ ሠራተኛው ሲያቀርብ ነው፡፡

20.1.50 አንድ ሠራተኛ ከአ/ማህበሩ ዋስትና ደብዳቤ እንዲሰጠው ሲጠይቅ ቀደም ብሎ ዋስ የሆነባቸው ድርጅቶች ካሉ ተጠቅሶ ለ2 ጊዜ ብቻ ማስረጃው ይሠጠዋል፡፡

20.1.51 በተራ ቁጥር 20.1.48 የተመለከተው የሲቪል መብት እና የሲቪል ግዴታ የሚባሉት፡-

20.1.51.1 ሠራተኛው ለሥራ ክርክር ፍርድ ቤት ለዋለበት ሰዓት መረጃ ሲያቀርብ

20.1.51.2 በህዝባዊ ድርጅቶች፣ የበጐ ፈቃድ አገልግሎት፣ ለመሳተፍና ከሚመለከተው አካል አስቀድሞ ጥያቄ ሲያቀርብና አክ/ማህበሩ ሲፈቅድ

20.1.51.3 ለፀጥታ ጉዳይ /ሥራ/ በሚመለከተው አካል ሲታዘዝና አ/ማህበሩ ሲፈቅድ

20.1.51.4 በዐቃቢ ህግ እና በፖሊስ ጽ/ቤት ለምስክርነትና ለህጋዊ ማስረጃነት ሲጠራ

20.1.51.5 ለብሔራዊ ጥሪ ሠራተኛው በሚመለከተው አካል ሲፈለግ አክ/ማሕበሩ ሲያውቅና ሲፈቅድ

20.1.51.6 ማንኛውም ሠራተኛ አክ/ማህበሩ በሚያዘጋጀው ወይም በሚያካሂደው የስልጠና ኘሮግራም ሲሳተፍ ወይም አምኖበት በሐገር ውስጥና በውጭ ሀገር በሚሠጥ ሥልጠና ወይም ሴሚናር ሲልከው ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሠጠዋል፡፡

20.1.51.7 ማንኛውም ሠራተኛ በአክሲዮን ማህበሩ ፍቃድ ሆነ በግል ከተማረ በት/ቤቱ ፈተና ለሚወስድባቸው ሰዓቶች የቦታ ርቀት ግምት ውስጥ እየገባ ፈተና ለሚወስድባቸው ሰዓቶች፣ ለብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ከ3 ቀን በፊት ፈተና ስለመኖሩ ማስረጃ ካቀረቡ ሙሉ ቀን ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሠጠዋል፡፡

20.1.51.8 የሠራተኛ ማሕበር የሥራ አስፈፃሚ አካላት 9ኙ በየ 15 ቀኑ ሰኞ የሥራ አመራሩ 12ቱ በየወሩ ለሚያደርጉት ስብሰባ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሠጣቸው፡፡

ቀ/ ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ፣

አክ/ማህበሩ ሲያምንበት ማነኛውም ሠራተኛ በድንገት ለሚያጋጥመው ችግር ወይም ሁኔታ በ12 ወራት ውስጥ በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜያት እስከ 3ዐ ቀን ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ ያገኛል፡፡ ነፃ ፈቃድ የሚሠጠው ሠራተኛ የተጠራቀመ የዓመት ዕረፍት የሌለው መሆኑ ከተረጋገጠና የተመደበበት ሥራ እንደማይበደል በኃላፊው ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የተሰጡት የነፃ ፈቃድ ቀናቶች የስራ መልቀቂያ የማስጠንቀቂያ ጊዜ መሆን አይችልም።

በ/ አክሲዮን ማሕበሩ ኤች አይቪ ኤድስን በሥራ ቦታ ለመከላከል የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፣

አክ/ማሕበሩ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የኤች አይ ቪ ኤድስን ፖሊሲ ከመሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበሩ ጋር በመመካከር ያወጣል ፖሊሲውንም ይተገብራል፡፡

ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ሠራተኞች ፀረ ኤድስ መድኃኒት በነፃ የሚገኝበትን ሁኔታ ከማሕበሩ ጋር በመመካከር ያመቻቻል፡፡ እንዲሁም ለኤች አይቪ አድስ ህመምተኛ ሠራተኞች ድጋፍና እንክብካቤ ያደርጋል፡፡

የፀረ ኤድስ ማህበር አመራር አባላት ኤች አይ ቪ ኤድስን በተመለከተ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አ/ማህበሩ ያበረታታል፡፡ ጽ/ቤት ይሠጣል፡፡ ለትምህርታዊ ሴሚናሮች ወርክ ሾፖችና ስብሳቢዎች አግባብ ባለው አካል ሲጋበዝ እንደ አስፈላጊነቱ እያየ ይፈቅዳል፡፡

የፀረ ኤድስ ማሕበር ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሲኖር በ15 ቀን ውስጥ የግማሽ ቀን የስብሰባ ፈቃድ ይሠጣል፡፡

ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሠራተኞች በዕድገት፣ በውክልና፣ በዝውውርና በሌላም ነገር አድሎ እንዳይደረግባቸው በአሠሪውና በሠራተኛው እንዳይገለሉ በቂ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡

ኤች አይ ቪን ለመከላከል በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣው መመርያ መሰረት አ/ማህበሩ በአመታዊ በጀት ዕቅድ 2% በጀት ይይዛል። አፈፃፀሙም የፀረ ኤድስ አብይ ኮሚቴ ኤች አይ ቪን ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑትን በመለየት ፕሮግራም ቀርፆ ለዋና ስራ አስኪያጅ አቅርቦ ሲፈቀድ ተግባራዊ ይሆናል።

አ ን ቀ ጽ 21

የመድን ዋስትና፣

ሀ/ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ከአንቀጽ 92 ጀምሮ እስከ 112 ያለው ድንጋጌ መሠረት፣

21.1 አንድ ሰራተኛ በተለያዩ በሽታ ወይም በተፈጥሮ ሞት ከዚህ አለም በሞት ሲለይ ድርጅቱ ከመድን ዋስትና በተገባው ውል መሰረት ለህጋዊ ወራሾች ክፍያ እንዲፈፀም ያደርጋል፡፡

21.2 ሠራተኛው ከሥራ ሲወጣና ወደ ሥራ ሲገባ ለሚደርስበት አደጋ ሁለት ሁለት ሰዓት የመድን ዋስትና ይኖረዋል፡፡

21.3 የአክ/ማህበሩ ሠራተኛ በአ/ማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማንኛውም ቀን በሥራ ላይ ባለበት ጊዜ የኢንሹራንስ ዋስትና አለው፡፡

21.4 ሠራተኛው ከቤት ወደ ሥራው ከሥራው ወደ ቤት ሲሄድ በነዚህ ሰዓቶች አደጋ በደረሰበት ጊዜ ወድያውኑ በቅርብ ለሚገኘው ፖሊስ ወይም ቀበሌ መስተዳድር ወይም ቀበሌ ገ/ማህበራት ማሳወቅ አለበት፡፡ መረጃውንም በ24 ሰዓት ለአ/ማህበሩ ያሳውቃል፡፡ አ/ማህበሩም ለኢንሹራንስ በ24 ሰዓት ውስጥ ስለደረሰው አደጋ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

21.5 ከዚህ በላይ ከተራ ቁጥር 21.3. እስከ 21.4. ለተዘረዘሩት ሁኔታዎች ሠራተኛው የጉዳት ካሣ ለማግኘት የሚችለው የአደጋው ዝርዝር ሁኔታ ከፖሊስ ጣቢያ ወይም ከቀበሌ መስተዳድር ወይም ቀበሌ ገ/ማህበራት በጽሑፍ ሲረጋገጥ ነው፡፡

21.6 ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 21.3 በተጠቀሰው ሁኔታ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ ራሱ ወይም በመልዕክተኛው ለአ/ማሕበሩ የሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ የአደጋውን ሁኔታ በ24 ሰዓት ውስጥ ማሳወቅ አለበት፡፡ ሆኖም የአ/ማሕበሩ የሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ ቢሮ ዝግ በሚሆንበት ጊዜ አደጋው የደረሰ ከሆነ ቢሮው በሚከፈትበት ዕለት ጠዋት ማሳወቅ አለበት፡፡

21.7 ሠራተኛው ከሥራ ቦታው ወይንም ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪም ቢሆን የአሠሪውን ትዕዛዝ ሥራ ላይ ሲያውሉ በነበረበት ጊዜ የደረሰበት ጉዳት በሥራ ላይ እንደደረሰ አደጋ ይቆጠራል በተጨማሪም ለሥራ ጉዳይ ወይም በሥራ ላይ አደጋ ደርሶበት ለሕክምና ከባሕር ዳር ውጭ ለሚላክ ሠራተኛ የ 24 ሰዓት መድህን ዋስትና ሽፋን ይሠጠዋል፡፡

ለ/ የጉዳት ካሣ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፣

21.8 ሠራተኛው ሥራውን ሲሠራ የአካል ጉዳት ሲደርስበት ይህንኑ ወዲያውኑ ለቅርብ አለቃው ነግሮ ወደ አ/ማህበሩ ክሊኒክ ወይም አዲስ አበባ ማ/ጽ/ቤት ከሆነ ወደ መንግስት ሆስፒታል ወይም ጤና ጥበቃ ሄዶ መታከም አለበት፡፡

21.9 በሠራተኛው ላይ የደረሰበትን ጉዳት የክፍሉ አለቃ በ24 ስዓት ውስጥ ሪፖርት አዘጋጅቶ ምስክሮች ካሉ አስመስክሮ ከሌሉም አለመኖራቸውን ገልጾ ለድርጅቱ ሀኪም መስጠት አለበት፡፡

21.10 የድርጅቱ ሀኪም አደጋው በደረሰ በ24 ስዓት ውስጥ በጽሑፍ ለሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ መስጠት አለበት፡፡

21.11 የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ የጉዳቱ ካሣ የሚያስጠይቅ ከሆነ የሀኪም ሪፖርት በደረሰው በ24 ስዓት ለኢንሹራንስ ድርጅት በተገቢው ፎርም ላይ አደጋውን ሞልቶ መላክ አለበት፡፡

21.12 የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ጉዳዩን ተከታትሎ ለክፍያ አፈፃፀም ደረጃ ሲደርስ አስፈላጊውን ሰነድ አሟልቶ ለፋይናንስ መምሪያ ያስተላልፋል፡፡

21.13 በስራ ላይ አደጋ ደርሶባቸው ወዲያውኑ በጡሮታ ከሥራ ለሚገለል ሠራተኛ የኢንሹራንስ ክፍያ እንደተጠበቀ ሆኖ የሰራተኛውን የስራ ዋስትና ግምት ዉስጥ በማስገባት ድርጅቱ የ 2 ወር ደመወዝ ድጎማ ይሰጣል፡፡

21.14 ከስራ ጋር ባልተያያዘ አደጋ ወይም ህመም በሀኪም ቦርድ በጡሮታ ለሚገለል ሠራተኛ የሰራተኛውን የስራ ዋስትና ግምት ዉስጥ በማስገባት ድርጅቱ የ 3 ወር ደመወዝ ድጎማ ይሰጣል።

አ ን ቀ ጽ 22

22.1 የሥራ ውል መቋረጥ፣

ሀ/ የሥራ ውል መቋረጥ ፣

በዚህ ኀ/ስምምነትና በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ድንጋጌ መሠረት ይፈፀማል፡፡

ለ/ ከሕግ ውጭ የሥራ ውል መቋረጥ፣

አሠሪው ወይም ሠራተኛው የሥራ ውል በማቋረጥ ረገድ ከአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ወይም በዚህ ኀ/ስምምነት ከተወሰኑት ሁኔታዎች ውጭ የሥራ ውል ማቋረጥ ሕገ ወጥ ይሆናል፡፡

ሐ/ ከሕግ ውጭ የሥራ ውል የሚቋረጥበት ሠራተኛ፣

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 43 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አ ን ቀ ጽ 23

23.1 የሥራ ስንብት ክፍያና ካሣ አፈፃፀም፣

ሀ/ የሥራ ስንብት ክፍያ አፈፃፀም፣

ሠራተኛው በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና በዚህ ህ/ስምምነት አንቀጽ 22 በተመለከተው ምክንያት ከሥራ ሲሰናበት የሚፈለግበትን ሂሳብ ማንኛውም ተረክቦ ይሠራ የነበረበትን የሥራ መሣሪያ ያስረክባል፡፡ የመታወቂያ ወረቀትም ይመልሳል፡፡ ሆኖም የሥራ ልበሱን አይመለከትም ሠራተኛው የሚፈለግበትን ሁሉ ካጠናቀቀ በኋላ አ/ማህበሩ በሚከተለው አኳኋን ስንብት ይፈጽማል፡፡

23.1.1 ሠራተኛው ያገለገለበትን ዘመን፣ የደመወዙን መጠን የሚገልፅ፣ የሠራተኛው ፎቶ ግራፍ የያዘ የስንብት የምስክር ወረቀት ይሠጠዋል፡፡

23.1.2 የአልተጠቀመበትን የዓመት ዕረፍት ካለው በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ድንጋጌ መሠረት በገንዘብ ታስቦ ይሠጠዋል፡፡

23.1.3 የስራ ስንብት ካሣ የሚያገኙ ሠራተኞች የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ በሚፈቅደው መሠረት ይፈፀማል፡፡

23.1.4 ከሥራ ተሰናባቹ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 23-24 /4/፣ 29 /1/ እና /2/ 30-31፣ 39 መሠረት ተገቢው ክፍያ ይሠጠዋል፡፡

23.1.5 ለሠራተኛው በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ለ/ ያለማስጠንቀቂያ ሥራ ለሚለቅ ሠራተኛ ስለሚሠጥ ካሣ፣

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ጉዳይ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 32 /1/ መሠረት የሥራ ውሉን የሚያቋርጥ ሠራተኛ በዚህ ህ/ስምምነት በተራ ቁጥር 23.1.5 በተመለከተው የሥራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 41 መሠረት ይፈፀማል፡፡ ሆኖም የሥራ ውሉ እንደተቋረጠ አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የዘለቄታ ጡረታ አበል ክፍያ ለማያገኙ ሠራተኞች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

23.1.6 ሠራተኛው የ3ዐ ቀናት ማስጠንቀቂያ ሣይሰጥ ከለቀቀ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 መሠረት ይፈፀማል፡፡

23.1.7 በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 43 የተደነገገው ቢኖርም አሠሪው በዚሁ አዋጅ አንቅጽ 35 ያለማስጠንቀቂያ የተጠቀሱትን ሳያሟላ ሠራተኛውን ሲያስወጣ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 4ዐ በተመለከተው ክፍያ በተጨማሪ ሠራተኛው በማስጠንቀቂያው ጊዜ ይከፍለው ይገባ የነበረው ደመወዝ ለሠራተኛው ይከፍላል፡፡

አ ን ቀ ጽ 24

የጡረታ መብት ስለመጠበቅ

የአክሲዮን ማሕበሩ ሠራተኞች በጡረታ አበል አከፋፈል የጡረታ አዋጅ የተጠቀሰውን ሁኔታ አሟልቶ ከተገኘ የጡረታ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አ ን ቀ ጽ 25

25.1 ለገንዘብ ከፋዮች የሚሠጥ ማካካሻ ክፍያ፣

25.1.1 ለባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አ/ማህበር ዋና ገንዘብ ያዥ ለሚያቀሳቅሰው ገንዘብ ማካካሻ በየወሩ 3ዐዐ.ዐዐ /ሶስት መቶ ብር/ ይከፈለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ማ/ቅ/ጽ/ቤት ገንዘብ ያዥ ለሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ማካካሻ በየወሩ ብር 10ዐ.ዐዐ/ መቶ ብር/ ይከፈለዋል፡፡

25.1.2 ለባሕር ዳር ጨ/ጨ/አ/ማህበር ደመወዝ ከፋዮች ለብር 1ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ ሺብር/ 2 /ሁለት ብር/ እየታሰበ ይከፈላቸዋል፡፡ የደመወዝ ክፍያው በባንክ ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም።

25.1.3 ይህ ሲሆን ሠራተኛው የገንዘብ ጉድለት ካደረገ አግባብ ባለው ህግ በኃላፊነት ይጠየቃል፡፡

25.1.4 የአከፋፈል ደረጃ በፋይናንስ መምሪያ መመሪያ መሠረት ይፈፀማል።

25.1.5 አክሲዮን ማሕበሩ ለገንዘብ ያዥ እንዲከፈል የተወሰነው ወርሃዊ ክፍያ በአስራ ሁለት ወራት በሠራተኛው ስም በመጠባበቂያ ገንዘብ መልክ ያጠራቅማል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን የመጠባበቂያ ገንዘቡ ክፍያውን በየወሩ ለገንዘብ ያዥ ይከፍላል፡፡

25.1.6 ገንዘብ ያዥ በኦዲተር /ሂሳብ ኃላፊው/ የተረጋገጠ ገንዘብ ጉድለት ሲገኝበት አ/ማህበሩ በገንዘብ ያዥ ስም ካጠራቀመው መጠባበቂያ ገንዘብ ተቀናሽ በማድረግ ጉድለቱን ወዲያውኑ ያሟላል፡፡

25.1.7 ገንዘብ ያዥ ከአ/ማህበሩ ሲሰናበት ወይም ከገንዘብ ያዥነት የሥራ መደብ ወደ ሌላ የሥራ መደብ ሲዛወር ምንም ዓይነት የገንዘብ ጉድለት የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ በስሙ የተጠራቀመው ገንዘብ ተመላሽ ሆኖ ቀሪ ካለው ይከፈለዋል፡፡

25.1.8 ከሠራተኛው /ከተገልጋዩ/ ማነስ የተነሳ ገንዘብ ያዥ የመጠባበቂያ ገንዘብ ክፍያ የሚያገኙ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሥራ መደቦችን ደርቦ ሲይዝ በየወሩ የሚከፈለው መጠባበቂያ ገንዘብ ለከፍተኛው የሥራ መደብ የተመደበው ክፍያ ብቻ ይሆናል፡፡

25.1.9 የሥራ ቅጥር ዋስትና የሚያስፈልጋቸው የስራ መደቦችን ማለትም ለገንዘብ ቤት/ካሸር/ ሰራተኛ፡ የአውቶብስ እና አነስተኛ ተሽከርካሪ ሹፌሮች፡ ለስቶር ባለሙያዎች፡ ለጥበቃ ሰራተኞች፡ እና ሌሎችም ከገንዘብ እና ከንብረት ጋር ንክኪ ባላቸው የስራ መደቦች ላይ የተመደቡ ለወደፊትም ለሚመደቡ ሰራተኞች በማንኛውም ጊዜ ዋስትና መስያዝ አለባቸው።። ዝርዝር አሰራሩን በተመለከተ ወደፊት በሚወጣው የዋስትና መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

አ ን ቀ ጽ 26

ሕገ ወጥ ድርጊት፣

26.1 የሚከተሉትን መፈፀም ለማንኛውም አሠሪ ሕገ ወጥ ድርጊት ነው፣

ሀ/ የዚህን ህብረት ስምምነት ድንጋጌዎች በመቃረን ተገቢ ያልሆነ አድራጐትን መፈፀም፡፡

ለ/ ሠራተኛው መብቱን በሕጋዊ መንገድ እንዲያስከብር ጥረት ሲያደርግ በማንኛውም አኳኋን ማደናቀፍ ወይም መብቱን በማስከበሩ እርምጃ መውሰድ፡፡

ሐ/ በብሔርና ብሔረሰብ፣ በጐሳ፣ በፆታ፣ በኃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከትና በሌላም ሁኔታ በሠራተኞች መካከል ልዩነት ማድረግ፡፡

መ/ ፍትሕን ማጓደል ማለትም አድሎን፣ ሙሰኝነት፣ ርካሽ ድርጊቶችን፣ መፈፀም ሕገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡

ሠ/ ባልተጨበጠ ጉዳይ ላይ አሉባልታ እየነዙ ሠራተኛውን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ መምራት፣ የጤናማ ምርት እንቅስቃሴ ማደናቀፍ የሠራተኛውን መልካም ማህበራዊ ግንኙነት ማሻከር፣ ሕገወጥ ድርጊት ነው፡፡

ረ/ አ/ማህበሩ አጠቃላይ የሠራተኛ ስብሰባ ሲጠራ ለሠራተኛው ማህበር አለማሳወቅ፡

ሰ/ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በተደነገገው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ሸ/ ማንኛውም አሠሪ የአ/ማሕበሩን ሠራተኛ የግሉን ሥራ በመደበኛ የሥራ ሰዓት ያሠራ ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡

ቀ/ በስራ ቦታ ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት ማካሄድ ወይም ሲካሄድ በአዋጁ መሰረት እርምጃ ያልወሰደ፤

26.2 የሚከተሉትን መፈፀም ለማንኛውም ሠራተኛ ሕገ ወጥ ድርጊት ነው፣

ሀ/ የሠራተኛን ሕይወትና የአ/ማህበሩን ንብረት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት ሆን ብሎ በሥራ ቦታ መፈፀም፡፡

ለ/ አሠሪው በግልጽ ሳይፈቅድ የአ/ማሕበሩን ንብረት ለግል መገልገያ መጠቀምና መውሰድ፤

ሐ/ ከሥራ ላይ አእምሮ የሚያደነዝዙ ዕፀችን ወስዶና በሥራ ላይ ሰክሮ መገኘት፤

መ/ ሕግ ሲያስገድድ ወይም አሠሪው በበቂ ምክንያት ሲጠይቅ የጤና ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን፤

ሠ/ ስለ ጤንነትና ደህንነት ጥበቃና ስለ አደጋ መከላከል የወጡ የሥራ ደንቦችን አለማክበርና አስፈላጊ የሆኑትን ያደጋ መከላከያ ጥንቃቄዎችን ለመውሰድ ፈቃደኛ አለመሆን፡፡

ረ/ ባልተጨበጠ ጉዳይ ላይ አሉባልታ እየነዙ ሠራተኛውን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ መምራት፣ ጤናማ የምርት እንቅስቃሴን ማደናቀፍ፣ የሠራተኛውን ጤናማ ማህበራዊ ግንኙነት ማሻከር፣ የሠራተኛ ማህበሩና አክሲዮን ማህበሩ ሳያውቅ ሠራተኛውን ሰስብሰባ መጥራት ሕገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡

ሰ/ ሙሰኝነት፣ ዝሙት በአክሲዮን ማሕበሩ ውስጥ መፈፀም፣ ቁማር መጫወት፣ ወይም መሰል ተግባራትን ማድረግ፡፡

ሸ/ በብሔርና ብሔረሰብ፣ በጐሳ፣ በፆታ፣ በሃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት በሌላም ሁኔታ ሠራተኛውን መከፍፈል፡፡

ቀ/ በአ/ማህበሩ ጥቅም ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ህገወጥ ተግባር መፈፀም፡፡

በ/ በስራ ቦታ ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት ማካሄድ፤

ተ/ በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወይም ለመገልገል መሞከር፤

ቸ/ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በተደነገገው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አ ን ቀ ጽ 27

27.1 የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ፣

ሀ/ የቅጣት አወሳሰን፣

27.1.1. በዚህ ኀ/ስምምነት የሚሸፈኑ ሠራተኞች ሁሉ በዚሁ ስምምነት የተመለከቱትን ሥርዓት ተላልፈው በመገኘታቸው ጥፋቱ በማስረጃ ሲረጋገጥ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ይወስድባቸዋል፡፡

27.1.2. ከሥራ የሚያሰናብቱ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ሲያጋጥምና መጣራት ያለበት ሆኖ ሲገኝ በዋና ሥራ አስኪያጅ አማካኝነት ከሰው ኃብት ል/አስ/መምሪያ እና ሠራተኛ ማሕበር በአባልነት ያለበት የዲሲፕሊን አጣሪ ኮሚቴ ያቋቁማል፡፡ በተጨማሪ የድስፒሊን ኮሚቴውም የቀረበለትን ክስ ከ30 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አጣርቶ ለዋና ስራ አስኪያጅ ማቅረብ አለበት። በ30 ቀናት ውስጥ የድስፒሊን ኮሚቴው አጣርቶ ባያቀርብ ተጠያቂ ይሆናል። ዋና ስራ አስኪያጅም የድስፒሊን ኮሚቴው ያቀረበለትን የውሳነኔ ሀሳብ የማጽደቅ፣ የማሻሻል፣ የመሻር ወይም በድስፒሊን ኮሚቴ የተሰጠው የውሳኔ ሃሳብ ጉድለት ያለበት መሆኑን ሲያረጋግጥና እንደገና እንዲጣራ የመመለስ ስልጣን አለው። ጥፋቱ በታወቀ በ30 ቀን ውስጥ ዋና ስራ አስኪያጅ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል።

27.1.3. ጥፋት ፈፀመ ተብሎ የተጠረጠረን ሰራተኛ የቅርብ ሃላፊው ጥፋቱን እንዳወቀ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ማሳወቅ አለበት። ይህንን ሃላፊነት ያልተወጣ አካል ተጠያቂ ይሆናል። የሥነ - ሥርዓት ቅጣቶች ሪፖርት የሚደረጉት ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለአገልግሎት ኃላፊዎች ሁኖ በነሱ በኩል ለአክሲዮን ማሕበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ሊያሳውቅ ይችላል፡፡

27.1.4. ለሥራ መደቡ የተሠጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያዎች በሥራ ላይ ሳይለብሱና ሣይጠቀሙ በሚገኙ ሠራተኞች ላይ በመምረያው የቅርብ ኃላፊ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጎ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በዕለቱ በቀሪ ይመዘገባል፡፡ ሆኖም የሥራ ልብስ ለብሶ ከተመለሰ ይሄን ለማሟላት ያጠፋው ጊዜ ተቀንሶ ሥራውን እንዲሠራ ይደረጋል፡፡ የተወሰደበት የሥነ ሥርዓት እርምጃ እንደተጠበቀ ይሆናል፣ የሥራ ልብስ ባለመልበሱ ምክንያት የሥራ ልብስ ለማምጣት ወደ ቤቱ ሲሄድም ሆነ ሲመለስ በኀ/ስምምነቱ አንቀጽ 21 የተደነገገው የመድህን ዋስትና ሽፋን የለውም፡፡ የሥነ ስርዓት እርምጃ አወሳሰድም በዚሁ አንቀጽ ሠንጠረዥ በተራ ቁጥር 7 ይፈፀማል፡፡ ሠራተኞች ከግቢ ውስጥ ከገቡ በኋላ ተከታትሎ ሥራ የማሠራትና ደንቡን ተከትሎ እንዲሰሩ የማድረግ ኃላፊነቶች በሙሉ ሠራተኛው በየተመደበበት የመምሪያው የሚገኙ በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች ኃላፊነት ነው፡፡

ለ/ የጥፋቱ ደረጃና የሚያስከትለው ቅጣት፣

ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት የጥፋት ደረጃ 1ኛ ጥፋት 2ኛ ጥፋት 3ኛ ጥፋት 4ኛ ጥፋት 5ኛ ጥፋት
1 ከኀ/ስምምነት ስነ ሥርዓት ድንጋጌ ውጭ ለማይመለከተው አካል ጉዳይ ለመፈፀም የሞከረ ሰራተኛ  ከባድ የጽሁፍ ማብጠንቀቂያ የ2ቀን ደመወዝ ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
2 ከደረሰበት ሕመም እንዲፈወስ ሐኪም የተሰጠውን ትዕዛዝ የማያከብር  ቀላል የጽሁፍ ማብጠንቀቂያ የ 1 ቀን ደመወዝ ቅጣት የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣት የ5 ቀን ደመወዝ ቅጣት ስንብት
3 የግል ማህደሩን ለማሟላት የሚያስችሉትን መረጃዎች በጽሑፍ በተሰጠው የጊዜ ገደብ አሟልቶ የማያቀርብ  ቀላል የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የ1 ቀን ደመወዝ ቅጣት ማስጠንቀቂያ የ 3 ቀን ደመወዝ የ5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት
4 መዝናኛ፣ ክበቦችን፣ ቤተ መጽሐፍት አካባቢ የሠራተኞችን ሠላማዊ እረፍት ፀጥታ ትምህርታዊ ክትትልና ያስተናጋጆችን የሥራ እንቅስቃሴ ያወከ ቀላል የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የ1 ቀን ደመወዝ ማስጠንቀቂያ የ2 ቀን ደመወዝ ቅጣት የ4 ቀን ደመወዝ ቅጣት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት
5 ሌላውን ሠራተኛ በሥራ ጊዜ ሥራ ለማስፈታት የሞከረ ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የ 2ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
6 በሥራ ሰዓትና ቦታ ሠክሮ መግባት፣ ማጨስ እና ጫት መቃም ከባድ የ 2ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ3 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
7 የተሰጠውን የአደጋ መከላከያና የደንብ ልብስ በሥራ ላይ ያልተጠቀመ ሠራተኛ ቀላል የፁሁፍ ማስጠንቀቂያና ያባከነው ሰዓት ይቆረጣል::  የ1ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት
8 በስራ ቦታ እና ሰዓት የሞባይል ጌም፣ ፌስቡክ እና ሌሎችንም አላስፈላጊ ተግባራትን መፈፀም ቀላል የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የ1ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ3 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት
9 በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 67 ከሀ - መ በተሰጠው መሠረት ትርፍ ሰዓት እንዲሠራ ሲታዘዝ ፈቃደኛ ያልሆነ  ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የ2ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ3 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
1ዐ በድርጅቱ ክልል ውስጥ የግሉን ሽያጭ ሲያካሂድ የተገኘ ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ3ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
11 ማንኛውም የድርጅቱ ማስታወቂያ በሠሌዳዎች ላይ ያለፈቃድ መገልገል ወይም ሕጋዊ ማስታወቂያ ያላግባብ ማበላሸት ከባድ የ3ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
12 በሌላ መ/ቤት በቋሚነት ተቀጥሮ ሲሰራ የተገኘ ከባድ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ከስራ ስንብት      
13 ጉዳዩ የሚመለከተዉ አካል ሳይፈቅድ ማንኛውንም ንብረትና የሥራ ቦታዎች ለማይመለከተው ሰው ያሳየና መግለጫ የሰጠ፤ ከማሽን ላይ ያለፈቃድ መለዋወጫ የፈታ  ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የ3 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
14 በሥራ ላይ ያለውን ሰው የዘለፈ፣ ያስፈራራ፣ የዛተ ወይም ያዋረደ  ከባድ የ3 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
15 የድርጅቱን ዕቃ መሣሪያና ተሸከርካሪ መኪና ያለፈቃድ ለግል ተግባር ያዋለ ወይም ያለአግባብ ከደንብ ውጭ የተጠቀመ /የተገለገለ ከባድ የ3 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጋር ስንብት    
16 ከሚመለከተው ኃላፊነት የሚሸሽና አድሎአዊነት የሚፈጽም  ከባድ የ3ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጋር  ስንብት    
17 ወደ ሥራ ሲገባና ሲወጣ ለፍተሻ ፈቃደኝነቱን ያላሳየ ወይም ያንገራገረ ሠራተኛ ከባድ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
18 ከሥራው ጋር በተያያዘ ምክንያት የምስክርነት ቃል እንዲሰጥ ሲጠየቅ ፈቃደኛ ያልሆነ ሠራተኛ  ከባድ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
19 የሠራተኛውን ወይም የአ/ማህበሩ ወይም የማህበሩን ስም የሚያጓድፍ የሐሰት ወሬ የሚያወራና የሚቀሰቅስ  ከባድ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ4ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ6ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
2ዐ  የደረጃ ዕድገት ስብሰባ ውይይት የስራ ዝውውርና ምደባ የባለሙያ አስተያየት የመሳሰሉትን ጉዳዮች የሚመለከተውን አካል በግልጽ ከማሳወቁ በፊት ያሰራሩን ሚስጥር ያባከነ ድርጅቱ ሳይፈቅድ በጽሑፍ ሠራተኛውን እያዞረ ያስፈረመ  ከባድ የ3 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንስት    
21 ለተወሰደበት የቅጣት ውሳኔ ሐሳብ እንዲሰጥ ሲጠየቅ ፈቃደኛ ያልሆነ ሠራተኛና የሠራተኛውን ሐሳብ ሳይጠየቅ ወይም ሠራተኛውን ሳይጠይቅ ሃሳብ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም ብሎ የቅጣት ፎርሙን ሞልቶ ያስተላለፈ፡፡  ከባድ የ1 ቀን ደመወዝ የ2ቀን ደመወዝ  የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
22 የደመወዝ ቅጣት የተወሰነበትን ሠራተኛ በወቅቱ ተቆራጭ አድርጐ ለአ/ማህበሩ ገቢ ያላደረገ የሰዓት ቁጥጥርና የሂሳብ ሠራተኛ  ከባድ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ  የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
23 ሠራተኛው የደረሰበትን ችግር በደብዳቤ ጠቅሶ ፈቃድ እንዲሰጠው ለኃላፊው ካሳወቀ በወቅቱ የሠራተኛውን ጥያቄ መቀበልና አለመቀበሉን በጠያቂው ማመልከቻ ላይ በጽሑፍ መልስ ያልሰጠ የቅርብ ተጠሪ ከባድ የ1ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ2 ቀን ደመወዝ የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ  ስንብት  
24 በተቀመጠው የመኪኖች ነዳጅ አጠቃቀም ኖርማላይዜሽን መሠረት ነዳጁን በተገቢው ያልተጠቀመ አሽከርካሪ ከባድ 3ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቅያ 5ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቅያ ስንብት    

ሐ/ የሥራ ደንብን ባለማክበር የሚያስከትሉ ቅጣቶች፣

ተቁ የጥፋት ዓይነት የጥፋት ደረጃ 1ኛ ጥፋት 2ኛ ጥፋት 3ኛ ጥፋት 4ኛ ጥፋት 5ኛ ጥፋት 6ኛ ጥፋት 
1 አንድ ሰራተኛ ማርፈድ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ የሥራ መግቢያ ሰዓት 5 ደቂያና ከዚያ በላይ አሳልሮ የገባ ወይም ያረፈደ   ቀላል የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በስድስት ወር ውስጥ 9 ጊዜ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ማርፈድ ስንብት
2 አንድ ሰራተኛ መቅረት ከጀመረበት ቀን ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ ባሉት የተለያዩ ቀናት ያለፈቃድ ለቀረና ለቀረበትም በቂ ሕጋዊ ማስረጃ ሳያቀርብ የቀረ  ቀላል የቀረበት ቀን ደመወዝ የማይከፈል ሲሆን በተጨማሪ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የቀረበት ቀን ደመወዝ የማይከፈል ሲሆን በተጨማሪ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የቀረበት ቀን ደመወዝ የማይከፈል ሲሆን በተጨማሪ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የቀረበት ቀን ደመወዝ የማይከፈል ሲሆን በተጨማሪ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የቀረበት ቀን ደመወዝ የማይከፈል ሲሆን በተጨማሪ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የቀረበት ቀን ደመወዝ የማይከፈል ሲሆን  ከ6ቀን እና በላይ ከቀረ ስንብት
3 መደበኛ ሥራውን ለጊዜው ሲያቋርጥ ተመሳሳይ ደረጃ ወይም ከደረጃው በታች ያለውን ሥራ እንዲሠራ የቅርብ አለቃው ሲያዘው ያልፈፀመ ከባድ የ 1ቀን ደመወዝ የ3 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
4 ሥራውን ትቶ በሥራ ቦታ መተኛት ከባድ የ3 ቀን ደመወዝ እና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
5 ሥራ ከገባ በኋላ ያለፈቃድ የሥራ ቦታውን ለቆ ለግል ሥራ ወደ ሌላ ክፍል በመሄድ ስራ ፈቶ ሥራ የሚያስፈታ  ከባድ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ  የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት  
6 በተመደበበት ቦታ የተሰጠውን የሥራ ተዕዛዝ ተቀብሎ ያላመረተና ፈቃደኛ ያልሆነ ሠራተኛ ከባድ የ2 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ7 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
7 በተሰጠው መደበኛ ሥራ ላይ ስህተት ወይም ጥፋት መሆኑን እያወቀ እንዲታረም ያላደረገና ለአለቃው ያላሳወቀ፤ ከባድ የ3 ቀን ደመወዝና ማስጠንቀቂያ የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስንብት    
8 በተሰጠው የምርት መለኪያ መጠንና ጥራት በራሱ ጥፋት ያልሠራና ያላመረተ ሠራተኛ  ከባድ 1ዐ% የቀነሰ የአንድ ቀን ደመወዝ 2ዐ% የቀነሰ የ3 ቀን ደመወዝ 2ዐ% በላይ የቀነሰ የ5 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ካላሻሻለ አንድ ደረጃና ደመወዝ ዝቅ ብሎ ይመደባል ካላሻሻለ ስንብት

መ/ የተፈፀመው ጥፋት ትክክለኛነት ስለማጣራት፣

1. አንድ ሠራተኛ ጥፋት ፈጽሟል ተብሎ ከቅርብ ኃላፊው ወይም ከሌላ አግባብ ካለው ክፍል ሪፖርት ሲቀርብ ወይም ከሥራ ጓደኛው አቤቱታ ሲቀርብ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ጥፋት ለመፈፀሙ መምሪያው/አገልግሎቱ ወይም የሰው ኃይል ል/አስተዳደር መምሪያ ይመረምራል፡፡

2. የቀረበው የክስ ሪፖርት ሠራተኛውን ለመጉዳት ሆን ተብሎ ወይም በስህተት የቀረበ ሆኖ ከተገኘ ክሱን ባቀረበው ላይ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል፡፡

3. በጥቆማ፣ በቅሬታ፣ ወይም በክስ አቤቱታ የቀረበበት ሠራተኛ የቀረበበት ጉዳይ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደ ጥፋተኛ ተቆጥሮ ከማንኛውም መብትና ጥቅም አይገደብም፡፡

ሠ/ ከሥራ የሚያሳግዱ ጥፋቶች፣

1. በሥራ ሰዓትና ቦታ የበላይ አለቃውን፣ የሥራ ጓደኛውን፣ የበታች ሠራተኛውን ወይም ማንኛውም ሰው የተማታ፣ ሊማታ የተገለገለ፣ ለሥራው ሲባል በተመደበበት ፈረቃ አልሰራም ያለ፣ ሕጋዊ ጽሑፍ አልቀበልም ያለ፣ ጥፋቱ በተፈፀመበት ቦታ የሚገኘው መምሪያ/አገልግሎት ድርጊቱ በተፈፀመ በ24 ሰዓት ውስጥ ተዋረዱን ጠብቆ ሪፖርት ለሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ ያሳውቃል፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ያልተፈፀመለት ሠራተኛ ጉዳዩን ለሰው ሀይል ል/አስ/መምሪያ ሊያቀርብ ይችላል፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰውን ድርጊት የፈፀመ ሠራተኛ አድራጐቱ በማስረጃ እስከተረጋገጠበት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ተመዛዝኖ ከሥራ ሊታገድ ወይም ከቦታው ተነስቶ በተገኘው የሥራ መደብ ተመድቦ እንዲቆይ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ሁኔታው ሲጣራ ከአድራጐቱ ነፃ ሆኖ ከተገኘ ወደነበረበት የሥራ መደብ ይመለሳል፡፡

3. በዚህ ንዑስ አንቀጽ ቁጥር 1 እና 2 የተገለጸውን ድርጊቶች በሥራ ምክንያትም ሆነ በግል ጉዳይ አድራጎቱን በፈጸሙት ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፣ የሥራ እገዳው በቅርብ አለቃው ተፈጽሞ ሪፖርቱ ተዋረዱን ጠብቆ ለሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡

ረ/ ያለ ማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያስወጡ ጥፋቶች፣

1. ሠራተኛው ወይም አ/ማህበሩን ሊጐዳ የሚችል ሁኔታ የፈፀመ ወይም ሲፈጽም አይቶ ተገቢውን እርምጃ በጊዜያቱ ያልወሰደና ሪፖርት ያላቀረበ፡፡

2. በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው መቅረት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ ለ6 ቀናት ከስራ የቀረ፣

3. በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ማርፈድ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ ለ9 ጊዜ የስራ ሰዓት ያላከበረ(ያረፈደ)፤

4. ራሱን ወይም ሌላውን ለመጥቀም፣ ለመጉዳት ሲል የሐሰት ምስክርነት የሰጠ ወይም ሪፖርት ያቀረበ ወይም የሐሰት ማስረጃ አቅርቦ ያሳሳተ ወይም ለማሳሳት የሞከረ ወይም ሠራተኛ የቀጣ ወይም እንዲቀጣ ወይም እንዳይቀጣ ያደረገ፤

5. በተከለከለ የሥራ ቦታ ሲጋራ ያጨሰ ወይም እሳት ያነደደ፤

6. ማንኛውም የአክሲዮን ማህበህሩን ንብረት የሰረቀና ያሰረቀ ወይም ያለፈቃድ የወሰደ፣ ሊወስድ ሲል የተያዘ እንዲሁም በሌላ ሰው እንዲወሰድ ያደረገ ወይም በሌላ ሰው ያስወሰደ፣ ሊያስወስድ ሲል የተያዘ ወይም የጓደኛውን የሥራ መሣሪያ የደበቀ ወይም የሰረቀ፤

7. ሆን ብሎ ወይም በቸለልተኝነት የድርጅቱን ንብረት ወይም መሣሪያ እንዲበላሽ ወይም እንዲሰበር ያደረገ ሠራተኛ፣ አንድ መኪና ወይም መሣሪያ ተረክቦ በሚሠራበት ጊዜ በተንኰል ወይም ሆን ብሎ ሰብሮ ወይም አበላሽቶ ቢገኝ ተረካቢው የተበላሸውን አግኝቶ ካላጋለጠ በቀር ድርጅቱን ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ራሱ እንዳጠፋው ይቆጠራል፡፡

8. አክ/ማህበሩ የሚያመርታቸውን ምርቶች ገበያ እንዳያገኙ ያደረገ፤

9. በአ/ማህበሩ ውስጥ በሰዓት ቁጥጥር፣ በምርት ሚዛኖች፣ በጨርቅ መከንዳት፣ በትርፍ ሰዓት አሞላል፣ በደመወዝ፣ ኰንትራት፣ አበል፣ ሂሳብና ዕድገት አሠጣጥ ላይ ተመድቦ የሚሠራ ማንኛውም ሠራተኛ ከትክክለኛው መንገድ ውጭ ሰርቶ ሌላውን ሠራተኛ ሆን ብሎ ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት የሞከረና ይህም በማስረጃ የተረጋገጠ ሆኖ ከተገኘ፤

10. በሥራ ሰዓት በሥራ ቦታ ተኝቶ የተገኘ፣ የጥበቃ ሠራተኛና የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኛ፤

11. በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከ30 ቀናት በላይ ከተፈረደበት፤

12. በዚህ ኀ/ስምምነት ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ናቸው ተብለው የተጠቀሱትን የፈጸም፤

13. እንደጥፋቱ ክብደት በሥራ ላይ የማታለል ወይም የማጭበርበር ተግባር የፈፀመ፤

14. በአ/ማህበሩ ውስጥ ቁማር ሲጫወት የተገኘ፤

15. የአ/ማህበሩን ማንኛውም ሰነድ ያጠፋ፣ የሰረዘ፣ የደለዘ ከሠራተኛው የግል ማህደር ልዩ ልዩ ጽሑፎችንና ማስረጃዎችን ያጠፋ፤

16. በተሰጠው ኃላፊነት አድሎ የፈፀመና በማስረጃ የተረጋገጠበት፤

17. የአክስዮን ማህበሩን ጥቅም የሚያሳጡ ሠነዶችን ያለፈቃድ የወሠደ፤

18. እንደጥፋቱ ክብደት በሥራ ቦታ አምባጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት የፈፀመ፤

ማሳሰቢያ፡

ሀ/ አሠሪው ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የሥራ ውል በሚቋረጥበት ጊዜ የሥራ ውሉ የሚቋረጥበትን ምክንያትና ቀን በመጥቀስ ለሠራተኛው በጽሑፍ መግለጽ አለበት፡፡ ሠራተኛው መደበኛ ፍርድ ቤት መቅረብ የሚገባው ወንጀል በድርጅቱ ውስጥ ፈጽሟል ተብሎ ሲወነጀል የአ/ማህበሩ የሰው ኃይል ል/አስተዳደር መምሪያ መረጃውን አያይዞ ለፖሊስ ያቀርባል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው በተከሰሰበት ወንጀል ነፃ ሆኖ ከተገኘ ወደ ሥራው ይመለሣል፡፡

ለ/ በዚህ ህ/ስምምነት ውስጥ የተጠቀሱትን ጥፋቶች ፈጽሞ የተቀጣ ወይም የሥራ ውሉ የተቋረጠበት ሠራተኛ አክ/ማህበሩ ቅጣቱን አሻሽሎ ሊያይለት ይችላል፡፡

ሐ/ ከአ/ማበሩ ውጪ በሆነ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ከማግኘቱም በፊትም ሆነ ፍርድ ካገኘ በኋላ እስከ 6ወር ከታሰረ እና ማስረጃ ካቀረበ አ/ማህበሩ ሰራተኛውን በፊት ሲያገኝ የነበረውን ደመወዙን እንደያዘ በተገኘው የስራ ቦታ በመመደብ ወደ ስራ ይመልሰዋል፡፡ ሆኖም የሰራተኛው ደመወዝ መከፈል የሚጀምረው አ/ማህበሩ ወደ ስራው ከመለሰበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ሠራተኛው ጥፋተኛ ሳይሆን በፍርድ ቤት በነፃ ከተለቀቀ በማንኛው ጊዜ ወደ ስራው ይመለሳል፡፡ ሆኖም የሰራተኛው ደመወዝ መከፈል የሚጀምረው አ/ማህበሩ ወደ ስራው ከመለሰበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡

ሰ/ የቅጣት ተፈጻሚነት የጊዜ ወሰን /ገደብ/፣

1. አንድ ሠራተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ የቅጣት ደረጃ ቀላል ጥፋት ከሆነ እስከ 6 ወር ድረስ ሌላ ጥፋት ካላጠፋ ከ6 ወር በኋላ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ይሻርለታል፣ ከባድ ጥፋት ወይም በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ተመሣሣይ ድርጊት ከፈፀመ ማስጠንቀቂያው እስከ 7 ወር ይቆያል፡፡

2. የሥነ-ሥርዓት እርምጃ የተወሰደበት ሰራተኛ የሥነ-ምግባርና የአፈፃፀም ማሻሻያ ካሳየ የተወሰደው የሥነ ስርዓት እርምጃ ከ7 ወር በኋላ ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህውም የሚያገለግለው ለደረጃ ዕድገት ውድድር ብቻ ነው፡፡

3. አንድ ሠራተኛ የሥነ ሥርዓት እርምጃ በጽሑፍ ፊርማ ከአወቀበት ቀን ጀምሮ በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ካላቀረበ የተወሰደውን እርምጃ አምኖ እንደተቀበለው ይቆጠራል፣ ሠራተኛው በእክል ምክንያት በተወሰነው ቀን ሊያቀርብ ካልቻለ ግን ሥራ በገባ በሶስተኛው ቀን ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡

4. አንድ ሠራተኛ በሥነ ሥርዓት እርምጃ ከሥራ ወጥቶ ወይም ከደረጃ ዝቅ ብሎ ከቆየ በኋላ በሥራ ክርክር ሰሚ አካላት ወይም በመደበኛ ፍ/ቤት ከተወሰነለት በውሣኔው መሠረት ይፈፀማል፡፡

አ ን ቀ ጽ 28

28.1 ስለ ቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት፣

የአ/ማህበሩ ሠራተኛ መብቱን ለማስከበር የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

28.1.1. አንድ ሠራተኛ በደረጃ እድገት በዝውውር፣ በነፃ ፈቃድና በመሳሰሉት ቅሬታ ሲሰማው በመጀመሪያ ደረጃ ለፈረቃ መሪው ያቀርባል፡፡ እነዚህ ኃላፊዎች የቀረበላቸውን ጉዳይ በአንድ ቀን ውስጥ ለቅሬታው መልስ መስጠት አለባቸው፡፡

28.1.2. በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 28.1.1 ላይ በተሰጠው መልስ ያልተስማማ ሠራተኛ ጉዳዩን በጽሁፍ ዘርዝሮ ለመምሪያ/አገልግሎት ሃላፊ ያቀርባል፡፡ የመምሪያ/አገልግሎት ሃላፊው የፈረቃ መሪው ለሠራተኛው የሰጡትን መልስ በማዛመድ ካጠና በኋላ በሁለት ቀን ውስጥ እንደአቀራረቡ መልስ ይሰጣል፡፡

28.1.3. በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 28.1.2 በተሰጠው መልስ ያልተስማማ እንደሆነ ከመምሪያ ያገኘውን መልስ አያይዞ ጉዳዩን ለሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ በጽሑፍ ሲያቀርብ በግልባጭ ለሠራተኛው ማህበር ያደርጋል፡፡ የሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ ጉዳዩን እንደ አቀረበለት በሁለት ቀናት ውስጥ አጥንቶ የመጨረሻ መልስ ይሠጣል፡፡

28.1.4. ሠራተኛው ከሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ በተሰጠው መልስ ካልተስማማ ቅሬታውን በጽሁፍ ለሠራተኛ ማህበሩ ያቀርባል፡፡ የሠራተኛ ማህበሩም ቅሬታውን ከደገፈው እንደገና ከሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይነጋገርበታል፡፡ ማሕበሩ አሁንም በተሰጠው መልስ ካላመነበት ጉዳዩ አግባብ ባላቸው የሥራ ክርክር ሰሚ አካላት አቅርቦ ያስወስናል፡፡ የሠራተኛ ማሕበሩ የአ/ማህበሩ የሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ በሰጠው ያመነበት ወይም የተስማማበት እንደሆነ ግን ሠራተኛው ካልተስማማበት በግሉ ለሥራ ክርክር ሰሚ አካላት ማቅረብ ይችላል፡፡

28.1.5. ጠቅላላ የአ/ማሕበሩን ሠራተኛ የሚመለከት የወል እና የአሠራር ጉድለት ቅሬታ ከሆነ በማሕበሩ በኩል አቤቱታው በቀጥታ ለአ/ማህበሩ አቅርቦ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡

28.1.6. ተመሳሳይ አቤቱታ ያላቸው የአንድ ክፍል ሠራተኞች ቁጥራቸው ከአምስት የበለጠ እንደሆነና አቤቱታውም ጠቅላላ ክፍሉን የሚመለከት ቢሆን በመምሪያው/አገልግሎቱ የጠቅላላ ምክር ቤት ተወካዮች በኩል አቤቱታውን መስመሩን ሳይለቅ ለመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ መቅረብ ይችላል፡፡

አ ን ቀ ጽ 29

29.1 ስለሠራተኛው ጤንነት ደህንነት የሥራ ልብስና አደጋ መከላከያ፣

ሀ/ ስለ ሠራተኛ ጤንነት ደህንነት ጥበቃ፡-

29.1.1. አክ/ማህበሩ ለጤንነት ጠንቅ የሚሆኑትን ነገሮች ሁሉ ለማሻሻል እንዲሁም በሥራ አደጋ ወይም በሽታ ለማድረስ የሚችሉትን ነገሮች ሁሉ ያስወግዳል፡፡ እንደሥራው ሁኔታና የሚያስፈልገው መጠን እየታየ አክ/ማህበሩ የአደጋ መከላከያዎችን ያቀርባል ማንኛውም ሠራተኛ ለሥራ መደቡ የተፈቀደውን የደህንነት መከላከያ /ሴፊቲ/ ያገኛል፡፡

29.1.2. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታን አግባብ ያለው ባለሥልጣን ሲያስታውቅ አክ/ማህበሩ መከላከያውን ያቀርባል፡፡

29.1.3. የሙያ ደህንነትና ጤንነት እንዲሁም የሥራ ቦታ አካባቢ ንፅሕናና ጥበቃን በተመለከተ አክ/ማህበሩ በሚመለከተው ባለሙያ እንዲፈፀም ያደርጋል፡፡ እንዲሁም ንፁህ የመጠጥ ውሃ ያቀርባል፡፡

29.1.4. ከኬሚካል ጋር ግንኙነት ያላቸው ሠራተኞች ስለሚጠቀሙበት ኬሚካል የአሠራር ሂደትና ጥንቃቄ የሚገልጽ ጽሑፍ ከሚገዛበት ድርጅት በማስመጣትና በአማርኛ በማዘጋጀት ሠራተኛው እንዲጠቀምበት ማድረግ፡፡

29.2 ለ/ የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ፡-

29.2.1. በዓመትና በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ ለሠራተኞች የሚሠጠው የሥራ ልብሶችና የአደጋ መከላከያዎች የመስጫ ጊዜ በየዓመቱ ከጥር 1 እስከ መጋቢት 3ዐ እና ከሀምሌ 1 እስከ የመስከረም 3ዐ ይሆናል፡፡ ይህን በማይፈፀም ማንኛውም ወገን ላይ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ድንጋጌ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

29.2.2. አ/ማህበሩ በዚህ ህ/ስምምነት መሰረት ከሚሠጠው የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ በተጨማሪ በሚመለከተው አካል እየተጠና እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጣል፡፡

29.2.3. በተለያዩ መምሪያዎችና አገልግሎቶች ቦታዎች የተለያዩ የመከላከያ ትጥቆች በሚያስፈልጉበት ጊዜ በጥናቱ መሠረት አ/ማሕበሩ ለሠራተኞች ይሠጣል፡፡

29.2.4. የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ የሚሠጠው ለሥራ መደቡ ብቻ ነው፡፡

29.2.5. በአ/ማህበሩ ውስጥ የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ ለታዘዘላቸው የሥራ መደቦች በአቅርቦት እጥረት ምክንያት በዚህ አንቀጽ በፊደል ለ በተራ ቁጥር 29.2.1 ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ማቅረብ ካልቻለ አ/ማህበሩና የሠራተኛ ማህበህሩ በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት ይፈፀማል፡፡

29.2.6. አ/ማህበሩ የደንብ ልብስና ሴፍቴ ማቴሪያሎችን በወቅቱ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

29.2.7. ለሥራው ደህንነት ሲባል የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ ለሚያስፈልገው የሥራ ቦታዎች የሴፍቲ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡

29.2.8. ማንኛውም ሠራተኛ የሚሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ በሥራ ቦታ ለብሶ መገኘት አለበት፡፡

29.2.9. አ/ማህበሩ ከዚህ ሠንጠረዥ ውስጥ ላሉት ወተት ለተፈቀደላቸው የሥራ ቦታዎች ወተት ያቀርባል፡፡ ሆኖም ወተት በአካባቢው ወይም በወረዳው ለማግኘት ካልቻለ ለማቅረብ አይገደድም፡፡ በተጨማሪ የወተት አሠጣጥ በተመለከተ ለወደፊቱ የሠራተኛ ማሕበሩ ከአ/ማህበሩ ጋር በመመካከር አስፈላጊውን ይፈፀማሉ፡፡

29.2.10. የሙያ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃን የአደጋ መከላከያና የሥራ ልብስን በተመለከተ አግባብ ያለው ባለሥልጣን የሚያስተላልፈውን መመሪያ አ/ማህበሩ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት ይፈፀማል፡፡

ሐ/ ለሠራተኛ የሚገባው የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ አሠጣጥ

በአ/ማህበሩ ውስጥ በተለያዩ የሥራ ክፍሎች ውስጥ ለሚሰሩ ሠራተኞች የሥራ ልብስ አሰጣጥ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደማሰጠው
1 ለምርት ክፍል መካኒኮች ቱታ በአመት 2 ጊዜ
2 ዘይትና ቅባት አጠጪዎች  በአመት 2 ጊዜ
3 መኪና ጠራጊዎች  በአመት 2 ጊዜ
4 ሳይዘር ሚክሰር ቱታ በአመት 2 ጊዜ
5 የውሃ ቧንቧ ሠራተኞች ቱታ በአመት 2 ጊዜ
6 የሴንትራል ወርክ ሾኘና ኤሌክትሪክ ሾኘ ሠራተኞች በአመት 2 ጊዜ
7 ለጋራዥ ሠራተኛ ቱታ በአመት 2 ጊዜ
8 ለትራንስፖርትና አቴንዳንት ሠራተኛ ቱታ በአመት 2 ጊዜ
9 ቤሊንግ ኦኘሬተርና ትራንስፖርት በአመት 2 ጊዜ
10 ለቦይለር ሠራተኛ በአመት 2 ጊዜ
11 ለአትክልትና የግቢ ውበት ቱታ በዓመት 2 ጊዜ
12 ለፎርክ ሊፍት ሹፌሮች በዓመት 2 ጊዜ
13 ለድሮ ኢን ሠራተኞች በዓመት 2 ጊዜ
14 ለችንጋ ቀጣይና አኮቴክስ ግራይንደር ቱታ በዓመት 2 ጊዜ
15 ለእሳት አደጋ ተከላካይ ቀይ ቴትሮን ቱታ በዓመት 2 ጊዜ
16 ለዩቲሊቲ መካኒክና መ/መካኒክ ቱታ በዓመት 2 ጊዜ
17 ለፊልተር ኘሪስ ማሽን አቴንዳንት በዓመት 2 ጊዜ
18 ኬሚካል ቀላቃይ  ቱታ በዓመት 2 ጊዜ
19 ለአውቶቡስ፣ ለአነስተኛ መኪና ሾፌሮችና እረዳቶች  ቱታ በዓመት 1 ጊዜ

መ/ ጋውን፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደማሰጠው
1 ሱፐርቫይዘሮች ጋውን በዓመት 2 ጊዜ
2 ለፈረቃ መሪዎች በዓመት 2 ጊዜ
3 ለላቦራቶሪ ኤክስፐርት በዓመት 2 ጊዜ
4 መለስተኛ ላቦራቶሪ ኤክስፐርት በዓመት 2 ጊዜ
5 ዲዛይነርና ረ/ዲዛይነር በዓመት 2 ጊዜ
6 ከፍተኛ ምርት ጥራት ኤክስፖርት በዓመት 2 ጊዜ
7 ለምርት ምዝገባና ክትትል ሠራተኛ በዓመት 2 ጊዜ
8 ለግዥና አቅርቦት ሠራተኞች በዓመት 1 ጊዜ
9 ለፈትል ዕቃ ግምጃ ቤት ሠራተኛ በዓመት 1 ጊዜ
10 ለሁሉም ፀሀፊዎችና ዳታ ኢንኮደሮች በዓመት 1 ጊዜ
11 ለገበያና ሽያጭ ሠራተኞች በዓመት 1 ጊዜ
12 የመስመር ላይ ጥራት ሠራተኛ በዓመት 2 ጊዜ
13 ለሰዓት ቁጥጥር በዓመት 1 ጊዜ
14 ለዕቅድ አፈፃፀምና የሰው ኃይል መረጃ ኦፊሰር በዓመት 1 ጊዜ
15 የሰው ኃይል አስተ/ኦፍሰሮችና መዝገብ ቤት ሠራተኛኞች በዓመት 1 ጊዜ
16 ለፋይናንስ ሠራተኞች በዓመት 1 ጊዜ
17 ለመረጃ ዴስክ ባለሙያ በዓመት 1 ጊዜ
18 ለዋና ኦዲተርና ረዳት ኦዲተር በዓመት 1 ጊዜ
19 ለኮርፖሬት፣ ለሲስተም እና ለፕላኒንግ አገልግሎት ሠራተኞች በዓመት 1 ጊዜ
20 ለነገረ ፈጅ በዓመት 1 ጊዜ
21 ለስርዓተ ፆታ ኦፊሰር በዓመት 1 ጊዜ
22 ለሥራ አስኪያጆች፣ ለመምሪያ፣ ለአገልግሎት ኃላፊዎች በዓመት 1 ጊዜ
23 ዌስት ዋተር መ/ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን በዓመት 2 ጊዜ
24 የጥሬ ጨርቅ ሜነደርና የአለቀለት ጨርቅ ጥራት ተቆጣጣሪዎች በዓመት 2 ጊዜ
25 የካንቲን ሰራተኞችና አስተባባሪ ፤ወተት አዳይ በዓመት 2 ጊዜ
26 የህፃናት ተንከባካቢ ሰራተኞች በዓመት 2 ጊዜ

ሠ/ ሸሚዝና ሱሪ፤ቱታ (አክሲዮን ማህበሩ የሚያመርተውን) ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለየርና ከተር፣ ረ/ለየርና ከተር ኦኘሬተር ቱታ በዓመት 2 ጊዜ
2 ልብስ ሰፊ፣ ፖኪንግ ኦኘሬተርና ቀዳጅ ሠራተኛ ሸሚዝ(ካኪ)ና ሱሪ” በዓመት 2 ጊዜ
3 ለፈትል፣ ሽመና እና ማ/ጋርመንት ኦፕሬተሮች ሸሚዝ(ካኪ)ና ሱሪ” በዓመት 2 ጊዜ
4 ሮውና ዌስት ወተር አቴንዳንት ቱታ በዓመት 2 ጊዜ
5 ኮምኘረሰር አቴንዳንት ቱታ በዓመት 2 ጊዜ
6 ወጥ ሰሪ እና እንጀራ ጋጋሪ እንዲሁም ዳቦ ጋጋሪ ሸሚዝ(ካኪ)ና ሱሪ” በዓመት 2 ጊዜ

ረ/ የጨርቅ ቆብ ፣ ከካኪ ጨርቅ የተሠራ የብናኝ መከላከያ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለፈትል፣ ለሽመና ማ/ማጠናቀቂያ የጽዳትና ሲልንደር ዳክት ጠራጊ ከጨርቅ የተሠራ ቆብ   በዓመት 2 ጊዜ
2 የጥጥ ቦንዳ ኦኘሬተር በዓመት 2 ጊዜ
3 ሳይዘር ሚክሰር በዓመት 2 ጊዜ
4 ለፈትል መ/ላቦራቶሪ ኤክስፐርት በዓመት 2 ጊዜ
5 ለሶሜትና ኤር ጀት ኦኘሬተር በዓመት 2 ጊዜ
6 ለሲኒየር ኦኘሬር በዓመት 2 ጊዜ
7 ዌስት ሩም ቦንዳ አሻጊ በዓመት 2 ጊዜ
8 አኮቴክስ ግራይንደር በዓመት 2 ጊዜ

ሰ/ የጨርቅ ቆብ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 የብሎዊንግ ማ/ኦኘሬተር የጨርቅ ቆብ በዓመት 2 ጊዜ
2 የካርዲንግ   “ በዓመት 2 ጊዜ
3 ለችንጋ ቀጣይና አኮቴክስ ግራይንደር በዓመት 2 ጊዜ
4 ለፈትልና ሽመና አየር መቆጣጠሪያ በዓመት 2 ጊዜ
5 ለቀ/ፈታይ ኦኘሬተር በዓመት 2 ጊዜ

ሸ/ የአፍና የአፍንጫ ማስክ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 የጥጥ ቦንዳ ኦኘሬተር የአፍና የአፍንጫ ማክስ በዓመት 2 ጊዜ
2 ለብሎዊንግ በዓመት 2 ጊዜ
3 ፋብሪክ ዶፈርና ትራንስፖርተር በዓመት 2 ጊዜ
4 ጽዳት ሠራተኛ በዓመት 2 ጊዜ
5 የውሃ ማከሚያ አቴንዳንት በዓመት 2 ጊዜ
6 ዲዛይነርና ረ/ዲዛይነር በዓመት 2 ጊዜ
7 የግቢና ውበት ሰራተኞች በዓመት 2 ጊዜ
8 የጋርመንት ቦንዳ አሻጊ በዓመት 2 ጊዜ
9 ዌስት ሩም ቦንዳ አሻጊ በዓመት 2 ጊዜ
10 አኮቴክስ ግራይነደር በዓመት 2 ጊዜ
11 ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ  በዓመት 2 ጊዜ

ቀ/ ወተት፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 የጥጥ ቦንዳ ኦኀሬተር ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
2 ካርዲንግ ኦኘሬተር ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
3 ችንጋ ቀጣይና አኮቴክስ ግራይደር ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
4 የፈትልና ሽመና አየር መቆጣጠሪያ፣ ኮምኘሪሰር አቴንዳንትና ሲሊንደር ዳክት ጠራጊዎች ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
5 ሳይዘር ሚክሰር ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
6 ዋርኘር ኦኘሬተር ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
7 ለሶሜትና ኤር ጀት ማሽን ጠራጊና ጽዳት ሠራተኛ ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
8 ለጅገር ፣ ለኘሪንቲንግ ኦኘሬተርና ኬሚካል ቀላቃይ፣ ዲሳይዚንግ፣ ወሽንግ እና ድራየር ኦፕሬተር፤ለዋና ኪሚስት  ለረዳት ኪሚስት  ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
9 ቢሊችንግና ስቴንተር ኦኘሬተር ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
10 ለብየዳ ሠራተኞች ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
11 ለፋውንደሪ ሠራተኞች ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
12 ማ/ማጠናቀቂያ ፅዳት ሠራተኛ ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
13 ከሮል ወደ ቢግ ባች አቴንዳንትና ትራንስፖርተር ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
14 ዩቲሊቲ ሠራተኞች ሆኖ ሮው እና ዌስት ወተር ተከታታይ አቴ. ፤መካኒክ እና መ/መካኒክ  ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
15 ለፎርክ ሊፍት ኦኘሬተር ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
16 ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ በማህበሩ ለተመዘገቡ ሠራተኞች ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
17 ለብሎዊንግና ካርዲንግ መካኒኮች ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
18 የፈትል ፅዳት ሰራተኛና ዘይትና ቅባት አጠጭ፤አስፓልት ጠራጊዎች፤ ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ
19 የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሩብ ሊትር በቀን አንድ ጊዜ

በ/ ከቆዳ የተሠራ የእጅ ጓንት፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለጥጥ ቦንዳ ኦኘሬተር ከቆዳ የተሠራ የእጅ ጓንት በዓመት 1 ጊዜ
2 ለብሎዊንግና ካርዲንግ መካኒኮች በዓመት 2 ጊዜ
3 ችንጋ ቀጣይና አኮቴክስ ግራይደር በዓመት 1 ጊዜ
4 ለብየዳ ሠራተኞች በ2 ዓመት 1 ጊዜ
5 ለማሽኒስትና መ/ማሽኒስት በ2 ዓመት 1 ጊዜ
6 ለማ/ማጠናቀቂያ መካኒክ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
7 ለኤሌክትሪክ ወ/ሾኘ ሠራተኞች በ2 ዓመት 1 ጊዜ
8 የኬሚካል ስቶር ኦፊሠርና ረዳት ኦፊሰር በዓመት 1 ጊዜ
9 ለጋርመንት ሽቦ ቆራጭ በዓመት 1 ጊዜ
10 ለጋርመንት ሽቦ ቦንዳ አሳሪ በዓመት 1 ጊዜ
11 ለአናፂና ግንበኛ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
12 ለፋውንደሪ ሠራተኞች በ2 ዓመት 1 ጊዜ
13 የዌስት ሩም ቦንዳ አሳሪ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
14 የካላንደር ማሽን ኦፕሬተር በ2 ዓመት 1 ጊዜ
15 የግቢና ውበት ሰራተኞች ከፕላስቲክ የተሰራ በ2 ዓመት 1 ጊዜ

ተ/ ኘላስቲክ ጐግልስ (የዐይን መከላከያ)፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ብሎዎንግ ኦኘሬተር ኘላስቲክ   ጐግልስ  በ2 ዓመት 1 ጊዜ
2 ካርዲንግ ና ፓዲንግ ኦፕሬተር በ2 ዓመት 1 ጊዜ
3 ችንጋ ቀጣይና አኮቴክስ ግራይደር በ2 ዓመት 1 ጊዜ
4 ለፈትል፤ሶሜትና ኤርጀት ጽዳት ሠራተኛ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
5 ለጅገር እና ብሊችንግ ኦኘሬተር እና ኬሚካል ቀላቃይ፤ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
6 አናፂና ግንበኛ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
7 ፋውንደሪ ሠራተኛ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
8 አውቶ ኤሌክትሪሽያን በ2 ዓመት 1 ጊዜ
9 ሴንተራል ወ/ሾኘ ለሚገኙ ጠ/መካኒክና መ/መካኒክ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
10 የአየር መቆጣጠሪያ ሠራተኛ በዓመት  1 ጊዜ
11 ግቢና ውበት ሠራተኞች በዓመት 1 ጊዜ

ቸ/ የኘላስቲክ ሽርጥ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ሳይዘር ሚክሰር ኘላስቲክ   ሽርጥ በዓመት1 ጊዜ
2 ለኬሚካል ቀላቃይ በዓመት1 ጊዜ
3 ለህክምና ጽዳትና ተላላኪ በዓመት1 ጊዜ
4 አውቶ ኤሌክትሪሽያን በዓመት1 ጊዜ
5 ፊልተር ኘሪስ አቴንዳንት በዓመት1 ጊዜ
6 ዌስት ወተር አቴንዳንት በዓመት1 ጊዜ
7 ዌስት ወተር መ/ላቦራቶሪ ቴክኒሻን በዓመት1 ጊዜ
8 ለሽንትና ሻወር ጽዳት ሠራተኛ በዓመት 1 ጊዜ
9 ለጅገርና ብሊችንግ ኦፕሬተሮች በዓመት 1 ጊዜ

ኀ/ የጆሮ ድምጽ መከላከያ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለቲዊስቲንግና ደብለር ኦኘሬተር የጀሮ ድምጽ መከላከያ በዓመት 1 ጊዜ
2 ለፋውንደሪ ሠራተኞች
3 ለፈትል መምሪያ ለኦኘን ኢንድ እና ካርዲንግ ሠራተኞች 
4 ከዋርፒንግና ሳይዚንግ በስተቀር ለሽመና መምሪያ ሠራተኞች፣ 

ነ/ የብርሃን መከላከያ መነፅር፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 የጥሬ ጨርቅ እና ያለቀለት ኢንስፔክሽን ኦኘሬተሮች የብርሃን መከላከያ መነፃር  በ2 ዓመት 1 ጊዜ

ኘ/ የቆዳ ሽርጥ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለብየዳ ሠራተኞች የቆዳ    ሽርጥ በ2 ዓመት 1 ጊዜ
2 ለአናፂ
3 ለፋውንደሪ ሠራተኞች

አ/ የብየዳ መነፀር፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለብየዳ ሠራተኞች የብየዳ መነፅር  በ2 ዓመት 1 ጊዜ

ከ/ በግራና ቀኝ ወንፊት ያለው መነፅር፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለማሽኒስትና መ/ማሽኒስት በግራና ቀኝ ወንፊት ያለው መነፅር  በ2 ዓመት 1 ጊዜ

ኸ/ የኬሚካል መከላከያ ኘላስቲክ መነፅር፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለዩቲሊቲ ሠራተኞች  የኬሚካል መከላከያ ኘላስቲክ መነፅር በ2 ዓመት 1 ጊዜ
2 ለማ/ጋርመንት ኬሚካል ቀላቃዮች፤

ወ/ ሴፍቲ ጫማ

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለከ/መካኒክና መካኒክ ፤መ/መካኒክ፤የጋራዥ መካኒክ፤ መ/ኤሌክትሪሺያን፤ ኤሌክትሪሺያን እንዲሁም ዘይት አጠጪና ቅባት ቀቢ፤ብየዳ ሰራተኛ፤ማሽኒስት፤የወርክሾፕመካኒክ ፤የወርክሾፕ የእንጨት ሰራተኞች፤መካኒካልና ኤሌክትሪካል ሱፐርቫይዘር፤ፋውንደሪ፤አናፂ፤ግንበኛ፤ የቧንቧ ሰራተኞች ሞተር ዋይንደር እና ኤሌክትሪካል ሰራተኞች ባለብረት ሁኖ ከቆዳ የተሰራ ማሰሪያ ያለውና ከቁርጭምጭሜት ከፍ ያለ በዓመት 1   ጊዜ
2 የእሳት አደጋ ተከላካይ ፤ባይለር ሠራተኛ፤ለፈትል ጥጥ ቦንዳ ኦኘሬተር፤ለጋርመንት ቦንዳ አሻጊ ሠራተኞች፤ለሰይዚንግ ማሽን ኦፕሬተሮች፤ሙቅ መጣኝ ሠራተኛ፤ትዊስተርና ኦኘሬተር፤ስቴንተር ኦኘሬተር፤ለፎርክሊፍት ኦኘሬተር፤ቢም ጫኝ እና ጣቃ ቆራጭ፤ለዋርፒንግ ማሽን ኦፕሬተሮች፤ፕሪንቲንግ ኦፕሬተር፤ያለቀለት ስቶር ትራንስፖርት ሰራተኞች፤የጥሬ ጨርቅ ታራንስፖርት ሰረራተኞች

ዘ/ ጉርድ ቆዳ ጫማ፣ ጠንካራ ሶል ያለው

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለጥበቃ ኃላፊዎችና የጥበቃ ሠራተኞች ከዋግስ ወይም ተመሳሳይ ከሆነ ቆዳ የተሰራ  በዓመት 2 ጊዜ   
2 የአነስተኛ ተሽከርካሪ ሹፌር በዓመት 1 ጊዜ   
3 ለጽዳትና ተላላኪ በዓመት 1 ጊዜ   
4 ለአውቶቡስ ሹፌርና ረዳት በዓመት 1 ጊዜ
5 ለሕክምና ጽዳትና ተላላኪ በዓመት 1 ጊዜ
6 ዲዛይነርና ረዳት ዲዛይነር በዓመት 1 ጊዜ   
7 የማቅለሚያና ጋርመንት ትራንስፖርት ሰራተኞች በዓመት 2 ጊዜ   

ዠ/ የብረት ቆብና ሸራ ቀበቶ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለእሳት አደጋ ተከላካይ የብረት ቆብና ሸራ ቀበቶ እንዳለቀ

የ/ ብረት ቆብ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለፋውንደሪ ሠራተኞች ብረት ቆብ እንዳለቀ

ደ/ የዝናብ ልብስ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለእሳት አደጋ ተከላካይ  ዝናብ መከላከል የሚችል በ 2 ዓመት1 ጊዜ
2 ለጥበቃ ሠራተኞችና ኃላፊዎች
3 ለአውቶቡስ ሾፌሮችና ረዳቶች
4 ለፊልተር ኘሪስ ማሽን አቴንዳንት
5 ለዩቲሊቲ መካኒኮችና መ/መካኒክ

ጀ/ የነፋስ መከላከያ ቆብ ያለው ጃኬት፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠው ትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለአየር መቆጣጠሪያና ኮምኘረሰር አቴንዳንት እና ለዩቲሊቲ ፈረቃ አስተባባሪ ከጥጥና ከፖሊስተር ወይም ተመሳሳይ ጥሬ እቃ የተሰራ ሁኖ ገበር ያለው በዓመት1 ጊዜ
2 ለፈትልና ሽመና ኮምፕሬሰር መካኒኮች በዓመት1 ጊዜ

ገ/ ካፖርት፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለጥበቃ ሠራተኞችና ኃላፊዎች   ከሱፍ፤ከጥጥ ወይም ከፖሊስተር የተሰራ ሙቀት የሚሰጥና ገበር ያለው በ2 ዓመት 1 ጊዜ

ጠ/ ሸሚዝ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለጥበቃ ሠራተኞችና ኃላፊዎች   በሀገር ውስጥ የተሰራ ከጥጥና ፖሊስተር የተሰራ ተመሳሳይ ከለር፤ በዓመት 2 ጊዜ
2 የአነስተኛ መኪና ሹፌሮች  በዓመት 2 ጊዜ
3 ለፎርክሊፍት ኦኘሬተር በዓመት 1 ጊዜ
4 ለአውቶቡስ ሾፌሮች በዓመት 2 ጊዜ

ጨ/ ካልሲና ቀበቶ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለጥበቃ ሠራተኞችና ኃላፊዎች   ካልስ   በ ዓመት 2 ጊዜ
ቀበቶ በ2 ዓመት 1 ጊዜ

ጰ/ ካራባት፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለጥበቃ ሠራተኞችና ኃላፊዎች   ከራባት ተመሳሳይ ከለር በዓመት 2 ጊዜ

ጸ/ ቦት ባለ ሸራ ጐማ ጫማ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለጅገር፣ ፓዲንግ፤ብሊችንግ ኦኘሬተርና ኬሚካል ቀላቃይ  ከጎማ የተሰራ የውስጥ ገበሩ ሸራ ጠርዙ ለስላሳና ሶሉ የሚተጣጠፍ በዓመት 2  ጊዜ
2 ለውሃ ማከሚያ አቴንዳንት
3 የጽዳት አትክልትና የግቢ ውበት ሠራተኛ
4 የሽንት ቤት ሻወር ጽዳት ሠራተኞች
5 ወሽንግና ድራየር፣ ዲሳይዚንግ ኦኘሬተር
6 የሮውውሃና ዌስት ዋተር አቴንዳንት
8 ፊልተር ኘሪስ አቴንዳንት
9 ለጊቢና ውበት አስተባባሪ
10 ለማ/ማጠናቀቂያ ጽዳት ሠራተኛ በዓመት 2 ጊዜ

ፀ/ ኘላስቲክ ጓንት፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለምርት ክፍል ፅዳት ሠራተኛ ኘላስቲክ  ጓንት በዓመት 2 ጊዜ
2 ለሽንት ቤት ሻወር ጽዳት ሠራተኛ ኘላስቲክ  ጓንት በዓመት 3 ጊዜ
3 ለፅዳትና ተላላኪዎች
4 ሳይዘር ሚክሰር
5 ወሽንግና ድራየር፣ ዲሳይዚንግ ኦኘሬተር፣ ጅገር ማ/ኦኘሬተር፣ ስቴንተር ማ/ኦኘሬተር
6 ለኬሚካልና ዳይ እስታፍ መጋዘን ኦፊሰር በዓመት 1 ጊዜ
7 ለኘሪንቲንግ ኦኘሬተር  በዓመት 2 ጊዜ
8 ለዲዛይነርና ረዳት ዲዛይነር
9 ለቧንቧ ሠራተኛ በዓመት 1 ጊዜ
10 ለአየር መቆጣጠሪያና ኮምኘሬሰር አቴንዳንት
11 የሕክምና ፅዳትና ተላላኪ በዓመት 2 ጊዜ
12 የውሃ ማከሚያ አቴንዳንት በዓመት 3 ጊዜ
13 ለጽዳት፣ አትክልትና የግቢ ውበት ሠራተኛ በዓመት 2 ጊዜ
14 ዩቲሊቲ መካኒክና መ/መካኒክ በዓመት 2 ጊዜ
15 ኬሚካል ቀላቃይ
16 የዌስት ወተር አቴንዳንት በዓመት 1 ጊዜ
17 የፊልተር ኘሪስ ማሽን አቴንዳንት በዓመት 2 ጊዜ
18 ለኬሚካል አውጭ ትራንስፖርት 

ፈ/ የሥራ ልብስ ካኪ ቴትረን በሀገር ውስጥ የተሠራ ከሌለ የውጭ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠው ጥቅምና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለጥበቃ ሠራተኞች እና ኃላፊዎች  ካኪ ቴትሮን ኮትና ሱሪ(ከለር በዓመት 2 ጊዜ
2 ለጤና ህክምና ሴፍቲ ሠራተኞች /ነጭ/ ጋውን ብቻ  በዓመት 2 ጊዜ

ፐ/ ሸራ ጫማ፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለፈትል፣ ለሽመና፣ ለማቅለሚያና ጋርመንት የቤሮ ፅዳት ሠራተኞች ሸራ   ጫማ በዓመት 1 ጊዜ
2 ለአየር መቆጣጠሪያና ኮምኘረሰር አቴንዳንት

ሳሙና 2ዐዐ ግራም፣

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሚሰጠውትጥቅና መከላከያ አይነት በስንት ጊዜ እንደሚሰጠው
1 ለፈትል መምሪያ ሠራተኞች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር 2 
2 ለፈትል አየር መቆጣጠርያ ሠራተኞች በወር 2 
3 ለዌስት ቦንዳ አሻጊ ዌስት ሩም
4 የጥጥ መጋዝን ሠራተኞች
5 የጥጥ ቦንዳ ኦፕሬተር
6 ለሽመና መምሪያ ሠራተኞች  
7 ለማ/ማጠናቀቂያ መምሪያ ሠራተኞች
8 ለቀለም ቀላቃይ ሠራተኞች በወር 3 
9 ለሮተሪ ፕሪንቲንግ ማሽን ኦፕሬተሮች በወር 2 
10 ለኢንጅነሪንግ መምሪያ
ሴንትራል ወርክ ሾኘ ሠራተኞች
ኤሌክትሪክ             ”
ዩቲሊቲ                ” 
ጋራዥ                 ”
እሳት አደጋ             ”
ባንቧ ሠራተኛ           ”
አናፂና ግንበኛ           ”
11 ለሰው ኃይል ል/አስ/መምሪያ    
12 ለመዝገብ ቤት ሠራተኞች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር   2
ለጥበቃ ሠራተኞችና ኃላፊዎች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር   2
ለሰው ኃይል ኦፊሰሮችና ለሚኒሚዲያ ባለሙያ በወር   1
ለፅዳትና ተላላኪ በወር   3
ለፅዳትና አትክልት የግቢ ውበት ሠራተኞች በወር   2
ለህክምናና ሴፍቲ ሠራተኞች  በወር   3
ለሰው ሀብት ልማት ዋ/ክፍል ሠራተኞች በወር   1 
13 የሰዓት ቁጥጥር ሠራተኞች  ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር   2 
14 በንብ/አስ/ጠ/አገልግሎት መምሪያ    
ኬሚካል፣ ዳይስታፍ ኦፊሰር ሳሙና/2ዐዐ/ግራም በወር 2 
ረዳት ስቶርና ሳተላይት ስቶር ኦፊሰር
ጀኔራል ሳኘላይስና የስቶር ዘጋባ ባለሙያ
የመለዋወጫ ስቶር ኦፊሰር
ለገበያና ሽያጭ ቦንዳ አመላላሽ ሠራተኞች
15 በፋይናንስ መምሪያ     
የፋይናንስ መምሪያ ስር ላሉ ሠራተኞች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር 1 
አርካይቭና መረጃ ጥንቅር ባለሙያ በወር 2 ጊዜ
የጥሬ ገንዘብ ገቢና ወጪ ባለሙያ     ”
     
16 ለፕላኒንግና ሲስተም አገልግሎት ሰራተኞች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር 1 ጊዜ
17 ለሕግ አገልግሎት ሠራተኞች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር 1 ጊዜ
18 ለሁሉም የቢሮ ፀሀፊዎች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር1 ጊዜ
19 ለሁሉም ዘይትና ቅባት አጠጭወች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር 3 ጊዜ
20 የህፃናት ማቆያ ሰራተኞች ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር 3 ጊዜ
21 በግዥ እና አቅርቦት መምሪያ፤ገበያና ፕሮሞሽንመምሪያ፤የአሰራር ሰረርዓት ማሻሻያ ጥ/ምርምር አገልግሎት፤በኦዲት እና ኢንስፔክሽን አገልግሎት ፤በስርዓተ ፆታ አገልግሎት፤በሽያጭ አገልግሎት እና ለአ/አ ማስ/ፅ/ቤት ስር ያሉ ሰራተኞች  ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር1 ጊዜ
22 ለአውቶብስ እና አነስተኛ ተሸከርካሪ ሹፌሮች፤ ሳሙና 2ዐዐ ግራም በወር1 ጊዜ

ማሳሰቢያ፡

  • የቆዳና የኘላስቲክ ጓንት፣ ጐግልስ፣ የአይን መነፀር፣ የድምፅ መከላከያ የመምሪያ/አገልግሎት ሃላፊዎች አስፈላጊነቱን ሪፖርት ሲያቀርቡ ጊዜውን ሳይጠብቅ ይሰጣል፡፡
  • በቲዊስተር ማሽን ኦኘሬተሮች ለአሁኑ ሥራ በዓመት አንድ ጥንድ ጉርድ የቆዳ ጫማ ብቻ እንዲሰጥ ሆኖ ወደፊት በቀን 8 ሰዓት በሥራ ላይ የሚውልበት ሁኔታ ሲፈጠር በዓመት ሁለት ጉርድ ቆዳ ጫማ ይሠጠዋል፡፡

አ ን ቀ ጽ 3ዐ

1. የሕክምና አገልግሎት ስለመስጠት፤

ከሥራ ሰዓት ውጭ የሆኑ ሠራተኞች መታከም ሲያስፈልጋቸው የሥራ መታወቂያ ካርዳቸውን በመያዝ በአ/ማህበሩ ክሊኒክ መታከም ይችላሉ፡፡ ሠራተኛው የሕመም ፈቃድ የተሰጠው እንደሆነ ክሊኒክ ፈቃድ የተሰጠበትን ቀን ለመምሪያው/አገልግሎቱና ለሰው ኃይል ል/አስተዳደር መምሪያ በያሉበት ያሳውቃል በምሽትና አዳር ፈረቃዎች እንዲሁም እሁድ ቀንና በብሔራዊ በዓል ቀን ሠራተኛው በድንገተኛ ሕመም ታሞ ቢመጣና ተረኛው ባለሙያ ከአቅሙ በላይ ከሆነ ሐኪሙ ተጠርቶ አስፈላጊውን ሕክምና የመስጠት ግዴታ አለበት፣ ሆኖም ግን ሐኪሙ በአካባቢው ከሌለ ሕመምተኛው ወደ ሆስፒታል መላክ አለበት፡፡

2. በሥራ ሰዓት፣

አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለና ወደ ሥራ ለመግባት የተዘጋጀ ሠራተኛ ታሞ መታከም ቢያስፈልገው ከቅርብ አለቃው የመታከሚያ ካርድ ተቀብሎ ለህክምና ይሄዳል፡፡ ሐኪሙ ፈቃድ ከሰጠው ይህን ለመምሪያው/አገልግሎቱ ያሳውቃል፡፡ ህመሙ በርትቶ ለመሄድ ያልቻለ እንደሆነ ፈቃድ መቀበሉን ክሊኒኩ ለሰው ኃይል ል/አስተዳደር መምሪያና ለሚመለከተው መምሪያ/አገልግሎት ያሳውቃል፡፡

3. በሆስፒታል የሚሰጥ ሕክምና፣

ሠራተኛው ሆስፒታል ተኝቶ እንዲታከም ሐኪም ሲፈቅድ፡-

ሀ/ ከሥራ ጋር በተያያዘ ምክንያት ለመጣ የአካል ጉዳት ወይም ሕመም ሲያጋጥም በዚህ አንቀጽ በፊደል “ሐ” በሚፈቅደው መሠረት ይፈፀማል፡፡

ለ/ ከሥራ ጋር ባልተያያዘ ምክንያት የመጣ የአካል ጉዳት ወይም ሕመም በዚህ ህብረት ስምምነት አንቀጽ 2ዐ ፊደል “ለ” ተራ ቁጥር 20.1.6 በተደነገገው መሠረት ይፈፀማል፡፡ በሶስተኛ ወገን የሚመጣ የአካል ጉዳት ካሣ አይመለከትም፡፡

ሐ/ ሠራተኛው በእረፍት ጊዜው ከባ/ዳርና ከአ/አ ውጭ ከተኛበት ሆስፒታል ወይም ከታከመበት ክሊኒክ ማስረጃ ሲያቀርብ በዚህ ህ/ስምምነት መሠረት ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡ እንዲሁም ሠራተኛው በዓመት እረፍትና አዲስ አበባ ባለበት ጊዜ ቢታመም ከአ/አበባ ማ/ቅ/ጽ/ቤት የመታከሚያ ወረቀት በመውሰድ መታከም ይችላል፡፡ የመጓጓዣውንና የሕክምና ውሎ አበል አ/ማህበሩ አይከፍልም፡፡

መ/ ሕመምተኛው በባሕር ዳር በሚገኘው ሆስፒታል በተሰጠው ሕክምና ያልተሻለው ሆኖ ወደ ሌላ ሆስፒታል እንዲላክ ሐኪሙ ሲያዘው አ/ማህበሩ ወደ ሌላ የመንግስት ሆስፒታል ልኮ የማሳከም ግዴታ አለበት፡፡ ለከፍተኛ ሕክምና አ/አበባ የሚላክ ሠራተኛ ከተላከበት ሕክምና ወደ ሌላ ሐኪም ቤት ሄደው ሊታከሙ የሚችሉት በሪፈር የተላኩበት ሆስፒታል ትዕዛዝ ሲሰጥ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ያለፈቃድ በራሳቸው ፍላጐት ከታዘዘላቸው ሆስፒታል ውጭ ሄደው ቢታከሙ አ/ማህበሩ ሂሳቡን አይከፍልም፡፡ እንዲሁም ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሌላ አካባቢ የሚላኩ ሠራተኞች ከተላኩበት ሕመም ዓይነት ውጭ የሚያመጡት ቀጠሮ በአ/ማህበሩ ሐኪም ሲረጋገጥና ባሕር ዳር ሆስፒታል መታከም የማይችሉ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡

ሠ/ ከባሕር ዳር ውጭ በአክሲደንት ለሕክምና የሚላኩ ሠራተኞች የወር ደመወዙ የሚፈቀድለትን የውሎ አበል እየተከፈለው ይታከማል፡፡ ለመጓግዣ የትራንስፖርት ደርሶ መልስ በህዝብ አውቶቡስ በየብስ በሕዝብ መመላለሻ ታሪፍ መሠረት ይከፈልለታል፡፡ ሕመምተኛው በቀጠሮ ወይም በወቅቱ ለመድረስ የማይችልበት ችግር ሲያጋጥም የአ/ማህበሩ ሐኪም በሚሰጠው ውሣኔ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ረ/ የአ/ማህበሩ ሐኪም ሲፈቅድለት አንድ ሠራተኛ አስፈላጊውን ሕክምና ወደሚያገኝበት ሌላ ክልል ወይም ከተማ ወይም ሆስፒታል አ/ማህበሩ ልኮ ያሳክማል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው በእረፍት ጊዜው ከባሕር ዳርና ከአ/አበባ ውጭ ከተኛበት ሆስፒታል ወይም ከታከመበት ክሊኒክ ማስረጃ ሲያቀርብ በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ሰ/ ከሥራ ጋር ግንኙነት ለሌለው ሕመም አ/ማህበሩ በሽተኛውን በሆስፒታል አስተኝቶ የሚያሳክመው በ3ኛ ማዕረግ ነው፡፡ 3ኛ ማዕረግ ባይገኝ በ2ኛ ማዕረግ ያሳክማል፡፡ ታካሚው ከዚህ በላይ በከፍተኛ ማዕረግ ተኝቶ ለመታከም ሲፈለግ ልዩነቱን ራሱ ከፍሎ ሊታከም ይችላል፡፡

ሸ/ ሠራተኛው ታሞ በተመላላሽ እየታከመ የሕክምና ፈቃድ ሲሰጠው በህብረት ስምምነቱ መሠረት ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡

ቀ/ ሠራተኞች በልዩ ልዩ ምክንያት ከባሕር ዳር ውጭ ሄደው ከታከሙ በኋላ የሚያመጡት የምስክር ወረቀት የአ/ማህበሩ ሐኪም መርምሮ ህመሙ እዚሁ ለመታከም የሚያስችል መሆኑ ካረጋገጠ ሕክምናው ከዚሁ ይቀጥላል፡፡ ሐኪሙ እንዲሄድ ካዘዘ የሰው ኃ/ል/አስ/መምሪያ አይከለክልም፡፡

በ/ አ/ማህበሩ በጥርስና በአይን ላይ ለሚደርስ ህመም በኀ/ስምምነት መሠረት የሕክምና አገልግሎት ይሠጣል፡፡ በተለይም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 98 ንዑስ አንቀጽ 1 “ሀ“ እና “ለ“ መሠረት የመጣ በሽታ መሆኑ በሐኪሙ ከተረጋገጠ የዓይን መነፅር መግዛት አለበት፡፡ ይህም ሲሆን በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 1ዐ7 ንዑስ 1 የተዘረዘሩትን ባለሙያ አጥንቶ በሚሠጠው ውሳኔ መሠረት የኢንዱስትሪ በሽታ መሆኑ በሐኪም ሲረጋገጥ በአካል ጉዳት ካሣ ይቀመጣል፡፡

ተ/ በአ/ማህበሩ በኩል ከባህር ዳር ውጭ በግል የጤና ችግር ለሚሄዱ ሠራተኞች በቀን የውሎ አበላቸው 100% ይከፈላቸዋል፡፡ ለህክምና አዲስ አበባ የሄደ ሠራተኛ ህክምናውን ጨርሶ ሀኪም ካሰናበተ በኋላ 1ቀን የትራንስፖርት ትኬት መቁረጫ ቀን ይሰጣቸዋል።

4. በክሊኒኩ ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎች፣

በሠራተኛው ጥፋት በቸልተኝነት የሚደርሱ አደጋዎች ወይም በሽታዎች በዚሁ አንቀጽ ከተዘረዘሩት የነፃ ሕክምና ዕርዳታዎች ውጭ ሆነው በዚሁ አንቀጽ ፊደል “ሀ” ለተመለከተው የመጀመሪያ ሕክምና ዕርዳታ ብቻ ሲደረግላቸው ሌሎች አይደረግላቸውም፤

ሀ/ በአምባጓሮ የሚደርስ አደጋ

ለ/ በአባላዛር በሽታዎች

ሐ/ ከሥራ ሰዓት ውጭ በሶስተኛ ወገን የሚደርስ ድንገተኛ አደጋ /የሕክምና እረፍት/ ወረቀት የሚያመጣ ከሆነ ለሠራተኛው ደመወዙን አ/ማህበሩ ይከፍለዋል፡፡

ይህም ሲሆን አደጋ የደረሰበት ግለሰብ ሙሉ አድራሻና የአደጋው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ ሠራተኛው አለበት፡፡ በፊደል “ሐ“መሠረት ሕመም የደረሰባቸው ሠራተኞች ሕክምና እንዲደረግላቸው ሀኪሙ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በሠራተኛው ወጭ በአ/ማህበሩ ክሊኒክ መታከም ይችላል፡፡ አ/ማህበሩ በክሊኒኩ ውስጥ የሰው ኃይልና የተሟላ መሣሪያ ያደራጃል በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ውስጥ ለሚሠሩ ሠራተኞች አ/ማህበሩ ውል በሚገባበት ሆስፒታል ወይም ጤና ጣቢያ ይታከማሉ፡፡

5. ከሥራ ጋር የተያያዘ አደጋ ወይም ሕመም የሚሰጥ ሕክምና፣

5.1 ከሥራ ጋር የተያያዘ አደጋ ወይም ጉዳት ቀጥለው የተዘረዘሩትን የአደጋዎች ሕመሞችን ያጠቃልላል፡፡

ሀ/ አንድ ሠራተኛ በአ/ማሀበሩ ውስጥ በሥራ ላይ እያለ የሚደርስ ጉዳት፡

ለ/ ሠራተኛው በሥራው ወይም ከሥራው ጋር ባለው ግንኙነት ምክንያት የሚደርስ ቋሚ ወይም የሚድን የአካል ጉድለት የአእምሮ መታወክ ወይም በሥራ ምክንያት የሚከሰት በሽታ፤

ሐ/ ከስራ ጋር ባልተያያዘ ለሚደርስ የጥርስ ጉዳት ጥርስን ከመሞላትና ከመትከል ውጭ ያሉትን አገልግሎቶች አ/ማህበሩ ይሰጣል፡፡

5.2 ከዚህ በላይ በቁጥር 5.1 የተመለከቱት ጉዳዮች በሠራተኛው ላይ ቢደርሱ የሠራተኛው መብት እንደሚከተለው ይጠበቅለታል፡፡

ሀ/ የሞት ወይም የአካል ጉዳት ካሣ በዚህ የህብረት ስምምነት አ/ማህበሩ በገባው የመድህን ዋስትናና በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ከአንቀጽ 95 እስከ 112 መሠረት የኢንሹራንስ ክፍያ ይፈፀማል፡፡

ለ/ የመጨረሻ የሕክምና ቦርድ ውጤት እስከሚገኝ ድረስ ሠራተኛው ሙሉ ህክምናና ሙሉ ደመወዛቸውን ማግኘት የተፈቀደለት ስለሆነ ከላይ በፊደል “ሀ” እንደተመለከተው ኢንሹራንስ ለደመወዝና ለሕክምና የሚከፈለውን ሳይሸፍን ሲቀር አ/ማህበሩ የማስፈፀም ግዴታ አለበት፡፡

ሐ/ ለበርካታ ጊዜና ወራት ወደ ሕክምና ተቋማት የሚመላለሱ ሠራተኞች ጉዳይ አ/ማህበሩ ሆስፒተሉን በመጠየቅ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ ይኸውም የሕክምናውን ጊዜ የሚወስነው የሐኪሞች ቦርድ ብቻ ነው፡፡

መ/ ሠራተኛው አደጋ ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ድኖ ወደ ሥራው የማይመለስ መሆኑን ሐኪሙ ሲያረጋግጥ ከኢንሹራንስ የሚያገኘው ጥቅምና ጡረታ ካለው የጡረታ መብት ከሌለው የሥራ ስንብት ክፍያና ካሣ መብቱ ተጠብቆለት የሥራ ውሉ ይቋረጣል፡፡

ሠ/ ሠራተኛው የጉዳት ካሣ ተከፍሎት ሥራውን መቀጠል የሚችል ከሆነና የደረሰበት ጉዳት እንደገና የሚያገረሽበት ከሆነ በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ከሥራ ጋር ባልተያያዘ ሕክምና ብቻ ይደረግለታል፡፡

6. የሕመምተኛ ማመላለሻ አገልግሎት፣

6.1 ሠራተኛው ወደ አ/ማህበሩ ክሊኒክ፣ ወደ ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ሂዶ ለመታከም የሚያበቃ ጽኑ ሕመም ታሞ ወይም ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥመው ከማንኛውም ሥራ ቅድሚያ ተሰጥቶት ሆስፒታል የሚያደርስ ሠርቪስ አ/ማህበሩ ያቀርባል፡፡

6.2 ጽኑ ሕመም ወይም ድንገተኛ አደጋ ተብሎ የሚገመተውን የክሊኒኩ ሐኪም ቀደሞ በአንቀጽ 2ዐ ፊደል ለ ተራ ቁጥር 1 ከተዘረዘሩት ውጪ ሊያቀረብ ይችላል፡፡

7 በሕመም ምክንያት ስለሚሰጥ ሥራ፣

7.1 የቦታ ለዉጥ የሚባለው በሕመም ምክንያት በሠራተኛው ላይ ቀጥለው ከተመለከቱት አንዱ ሲደርስ ነው፡፡

7.1.1 የቦታ ለውጥ በሚመለከት የሥራ ዝዉውር የሐኪሞች ቦርድ ሲፈቅድ ደመወዝን ሳይቀንስ የቦታ ለውጥ ያደርጋል፡፡

7.1.2 የቦታ ለውጥ የሚባለው ሠራተኛው በሚሠራበት ቦታ ያለው የአየር ወይም የሥራ ፀባይ ለሠራተኛው አልስማማ ብሎ የጤና መታወክ ሲደርስበትና ሐኪሙ ለዘለቄታው በዚሁ ቦታ ለመሥራት የማይችል መሆኑን ገልፆ ሌላ አካባቢ እንዲዛወር ሲታዘዝለት ነው፡፡

7.1.3 በሐኪሞች ቦርድ ትዕዛዝ የቦታ ለውጥ ተሰጥቶት የቆየ ሠራተኛ ጤንነቱ መመለሱን የሐኪሞች ቦርድ ሲያረጋግጥለት ወደ ነበረበት ወይም በተመሳሳይ ሥራ አ/ማህበሩ ለመመደብ ይጥራል፡፡ እንደ ሁኔታው አ/ማህበሩ የሠራተኛውን ጤንነት ለማወቅ በራሱ ወጭ ያስመረምራል፡፡

7.1.4 አንድ ሠራተኛ ከ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ በቦታው ለውጥ እንዲመደብ በአንድ ሐኪም የሚሰጥ ትዕዘዝ ተቀባይነት አለው፡፡

7.1.5 ሠራተኛው በድንገተኛ ጽኑ ሕመም ታሞ ወደ ሆስፒታል ቢላክ ሕመሙን ማስረዳትና መናገር የማይችል ሆኖ ሲገኝ የክሊኒኩ ባለሙያ በአ/ማህበሩ ተሽከርካሪ በሽተኛውን ይዞ በመሄድ ያሳክማል፡፡ በተጨማሪ በሽተኛው ሆስፒታል ደርሶ በሆስፒታሉ አቅም ሊታከም የማይችል ሆኖ ከተገኘና በአስቸኳይ ከባሕር ዳር ከተማ ውጭ ተልኮ ሕክምና ካላገኘ በሕይወቱ ችግር የሚያጋጥመው መሆኑን ተገልፆ ከታዘዘ በአ/ማህበሩ ተሽከርካሪ የአ/ማህበሩ የሕክምና ባለሙያ በተፈለገው ሆስፒታል አድርሶ ይመለሳል፡፡

7.1.6 በህጉ መሰረት የአካል ጉዳት ካሳ ተከፍሎት የመስራት አቅሙ በህክምና ቦርዱ በሰጠው ማስረጃ መሰረት በፐርሰት የቀነሰበት ሰራተኛ ካሰው እስከተከፈለው ድረስ በሚመጥን ቦታ ማሰራት ይችላል። በዚህ አግባብ መፈፀም ካልተቻለ በህጉ መሰረት ድርጅቱ ሊያሰናብት ይችላል።

8 ለሠራተኛው ቤተሰብ የሚሰጥ የህክምና አገልግሎት፣

አ/ማህበሩ ለሠራተኛው /ሠራተኛዋ/ ባል ሚስትና 18 ዓመት ላልሞላው፣ ላልሞላት በራሱ /በራሷ/ ልትተዳደር ለማይችል ልጅ በማንኛውም ቀንና ሰዓት ከመደበኛው ሠራተኛ ቀጥሎ የህክምና አገልግሎት ይሠጣል፡፡

አንቀጽ 31

ልዩ ልዩ ማህበራዊ አገልግሎት

ቀብር

1. ሠራተኛው ሲሞት አ/ማህበሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቀብር ወጭ አገልግሎት ይሠጣል፡፡

ሀ/ የከፈን ጨርቅ 3.5 ሜትር አቦጀዲድ ስፋቱ 1.50 ሴ/ሜ የሆነ በገበያ ዋጋ ገዝተው በሚቀርበው ማመልከቻ መሰረት ይወራረዳል።

ለ/ ለአስከሬን ሳጥን መግዣ 100ዐ.ዐዐ /አንድ ሺህ ብር/ ይሰጣል፡፡

ሐ/ በአንቀጽ 2ዐ በፊደል “ረ“ተራ ቁጥር 6 መሠረት ለቀብር ሥርዓት ማስፈፀሚያ መኪና ከፈለገ ሠራተኞች ወደ ሥራ በማይገቡበት ወይም ከሥራ ወደ ቤት በማይሄዱበት ወቅት ብቻ ሊሰጥ ይችላል፡፡

2. የሠራተኛው ቤተሰብ ማለት ሚስት ወይም ባል በእሱ ወይም በእርሷ የምታስተዳድራቸው ወይም የሚያስተዳድራቸው ሥራ ያልያዙ ልጆች ሬሳ ከቤቱ ወይም ከቤቷ ሲወጣ ድርጅቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የቀብር አገልግሎት ይሠጣል፡፡

ሀ/ የከፈን ጨርቅ

ለ/ የአስከሬን ሳጥን እና የአበባ ጉንጉን በመያዝ አንድ ፒክ አፕ መኪና ቤተክርስትያን የሚያደርስ ተሽከርካሪ ይመደባል፡፡

3. የአ/ማህበሩ ሠራተኛ ከባ/ዳር ውጭ ለሕክምናና በሥራ ጉዳይ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ እያለ ቢሞት የሟች ቤተሰብ በባሕር ዳር እንዲቀበር ከፈለገ አስከሬኑን በአ/ማህበሩ ወጭ ወደ ባሕር ዳር አስመጥቶ ያስቀብራል፡፡ ቤተሰቦቹ በሞተበት ቦታ እንዲቀበር ከፈለጉ ግን አንቀጽ 2ዐ ፊደል ረ ተ.ራ ቁጥር 5 እና 6 እንደተጠበቀ ሆኖ ለእነሱ መጓጓዣ 10ዐዐ.ዐዐ /አንድ ሺ ብር/ ይሰጣል ቤተሰብ ወይም ወራሽ ከሌለው ገንዘቡ ለሠራተኛ ማህበሩ ተሰጥቶ ቀብሩን እንዲያስፈጽም ይደረጋል፡፡

2. የብድር አገልግሎት፣

ሀ/ ለተቋቋመው ብድርና ቁጠባ ህ/ስ/ማሕበር መዋጮና ተመላሽ ገንዘብ አ/ማህበሩ ከሠራተኛው እየሰበሰበ ለማሕበሩ ያስተላልፋል፡፡

ለ/ አንድ ሰራተኛ ከፍተኛ ችግር ሲያጋጥመውና ብድር ሲጠይቅ አ/ማህበሩ ካመነበት የአንድ ወር ደመወዝ በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚያልቅ ሊያበድረው ይችላል፤ ይህ ተፈፃሚ የሚሆነው ሰራተኛው 5ዓመት እና ከዚያ በላይ በአ/ማበሩ ውስጥ የአገልግሎት ጊዜ ሲኖረው ነው፡፡

3. ስፖርት፣

በአ/ማህበሩ ውስጥ የሚቋቋሙት የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች በአ/ማህበሩ የበላይ ጠባቂነት ይመራሉ፡፡

4. ለሠራተኛ የሚሸጡ ዕቃዎች፣

ሀ/ አ/ማህበሩ ከተዋጡ ዕቃዎች ማለትም የጥጥ መጠቅለያ ጨርቅም ሆነ ኬሻ፣ የጥጥ ቦንዳ ማሰርያ ሽቦ ሽያጭ ዋጋ 100% መ/ሠራተኛ ማህበር እየሸጠ ይጠቀማል። እንዲሁም ከተዋጡ ዕቃዎች ማለትም ኬሚካልና ቀለማ ቀለም ጀሪካኖች ዘይት የሚይዙ በርሚሎች ሽጦ 75% ይጠቀማል፤ ቀሪ 25% ለአ/ማህበሩ ገቢ ያደርጋል፡፡ በትክክል ለተባለለት አላማ መዋሉን መሠረታዊ ማህበሩ በየ6 ወሩ ለአ/ማህበሩ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

ለ/ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ በዓመት 3 ጥንድ አንሶላና ትራስ ልብስ በማምረቻ ዋጋ ይሽጥለታል፡፡ ሳይዙም 160*250 ወይም 190*250 ወይም 210*250 ወይም 240*250 የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ሐ/ በጡሮታ ለሚገለሉ የአ/ማህበሩ ሰራተኞች ባለ 190*250 ወይም ባለ 210*250 ሁለት ጥንድ አንሶላ ይሰጣቸዋል፡፡

5. የውስጥ ክበብ አስተዳደር፣

ሀ/ ከአ/ማህበሩ የውስጥ የሠራተኛ ክበብ አክሲዮን ማህበሩ ያለትርፍ ለሠራተኛው አገልግሎት ይሰጣል፡፡

6. በአ/ማህበሩ ውስጥ የሚገኝ ሣር፣

በአክሲዮን ማህበሩ ክልል ውስጥ ያለው ሣር እና ሊወገዱ የሚችሉ ዛፎችን መ/ሠራተኛ ማህበሩ እያስቆረጠ ለማጠናከሪያ ይወስዳል፡፡ በአ/ማህበሩ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ያለውን ሳር የግቢና ውበት ስራውን ከማስጠበቅ አንፃር በማንኛውም ጊዜ ሊያስወግደው ይችላል፡፡

አ ን ቀ ጽ 32

32.1 ትምህርት፣

የአ/ማህበሩ ሠራተኛ በትምህርት ሲጐለምስ የኑሮ አቋሙ ከመሻሻሉም በላይ ለአገሪቱና ለአ/ማህበሩ ምርት መዳበር ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ስለዚህ አ/ማህበሩ በሚከተለው አኳኋን የሠራተኞችን የትምህርት አቋም በብርቱ ያጠናክራል፡፡

1. ሀ/ በአ/ማህበሩ ውስጥ 5 ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገለ ሠራተኛን 9ኛ ና 1ዐኛ ክፍልን በመንግስት ት/ቤት ያስተምራል፡፡ የት/ቤት ክፍያን ወጭውንም አ/ማህበሩ ይሸፍናል፡፡

ለ/ ከ1ዐኛ ክፍል በላይ ለሚማር ሠራተኛ በሚሠራበት ሙያ ተመሳሳይ በሆነ ትምህርት መከታተል ሲፈልግ ጉዳዩን ለሰ/ኃ/ል/አስ/መምሪያ አቅርቦ በዋና ሥራ አስኪያጅ በኩል ሲታመንበት እንዲማር በመፍቀድ የትምህርት ክፍያውን 10ዐ% አ/ማህበሩ ይሸፍናል፡፡ ይህም የሚደረገው በአ/ማህበሩ ውስጥ 2 ዓመት ላገለገለ ሠራተኛ ሲሆን የትምህርት ክፍያው የሚፈፀመው የ1 ዓመት ትምህርት ዘመኑን ጨርሶ ማለፊያ ነጥብ ወይም አጥጋቢ ውጤት ሲያቀርብ ነው፡፡ አንድ ሠራተኛ በመማር ላይ እያለ ወይም ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ለመልቀቅ ቢፈልግ አ/ማህበሩ ለትምህርት የከፈለውን እጥፍ እንዲመልስ ይደረጋል፡፡ ወይም ከተመረቀ በሗላ 2 ዓመት ማገልገል ይኖርበታል፡፡

ሐ/ ለትምህርትና ሥልጠና ሴት ሠራተኞች ለውድድር በሚቀርቡበት ጊዜ 2ዐ% ሴቶች እርስ በርሳቸው ይወዳደራሉ፡፡ በቀሪው 8ዐ% ከወንዶች ጋር የመወዳደር መብት ይጠበቅላቸዋል፡፡ ነገር ግን የወጣውን መስፈርት ሴቶች የማያሟሉ ከሆነ ለወንዶች ይሠጣል፡፡

መ/ የአ/ማህበሩ ቋሚ ሰራተኛ ልጆች የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት አስመዝግበው ወደ ዩንቨርስቲ ሲገቡ አ/ማህበሩ ባለ 160*250 የሆነ አንድ ጥንድ አንሶላ ማበረታቻ ለተማሪዎቹ ይሰጣቸዋል፡፡

32.2 የሙያ ስልጠና፣

የአ/ማህበሩ ሠራተኞች በልዩ ልዩ ሙያዎች እንዲሠለጥኑ ማድረግ በዋነኛነት ጠቀሜታው ለአ/ማህበሩ ነው፡፡ ስለሆነም ሠራተኛው አዳዲስ ዕውቀቶችን እንዲያገኝ ክህሎቱን ከፍ በማድረግ ምርትን ማሳደግ እንዲችል ሠራተኛው በአ/ማህበሩ የሥልጠና ማዕከልና በሐገር ውስጥ ስልጠና ተቋማትና በውጭ ሀገር ልኮ ማሠልጠን ይኖርበታል፡፡

ይህም ሲሆን በስልጠና ላይ ያለው ሠራተኛ በሥራ ላይ እንዳለ ተቆጥሮ ደመወዙ ይከፈለዋል።

ሀ/ ሥልጠና የተዘጋጀው ከአ/ማህበሩ ውጭ ሆኖ በሌላ መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጥ ከሆነ ቅድሚያ አ/ማህበሩ ተጠይቆ ሲስማማበት ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ለ/ ሥልጠና ለአ/ማህበሩ የሚሰጠው ፋይዳ አነስተኛ ነው ከተባለ እንዲሰለጥን የተጠየቀለት ሰው አ/ማህበሩ ሲፈቅድለት ወይም ላይፈቅድለት ይችላል፡፡ የሚፈቅድለት ከሆነ የሰልጣኙን ደመወዝ አ/ማህበሩ እንዲከፍል ላይገደድ ይችላል፡፡

አ ን ቀ ጽ 33

የደመወዝ ጭማሪ እና የማበረታቻ /ቦነስ/ ክፍያ ዓላማው፣

ለአ/ማህበሩ ሠራተኞች ዓመታዊ የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ የሚሰጥባቸው መሠረተ ሃሳቦች ለሽያጭ ዕድገት፣ ለትርፍ ዕድገት፣ ለምርታማነት ዕድገት፣ ታሳቢ ሆኖ ነው፡፡

በዚህ አንቀፅ መሰረት የቦነስ ወይም ማበረታቻ ክፍያ ለሰራተኛው መስጠት ተነሳሽነትን የሚጨምር መሆኑ ሲረጋገጥና አ/ማህበሩ አትራፊ ሆኖ ሲገኝ በሚከተለው ሁኔታ ይፈፀማል፡-

1. ቦነስ የሚታሰበው ከተጣራ ትርፍ (Net Profit) ላይ ነው ።

2. ቦነስ የሚሰጠው ማንኛውም ሰራተኛ በደመወዙ ስኬል እና ትርፍ በተገኘበት በጀት ዓመት ባገለገለበት ጊዜ መሰረት ይሆናል።

3. ቦነስ የሚያገኝ ማንኛውም ሰራተኛ የስራ አፈፃፀሙ መታየት አለበት።

4. ትርፍ በተገኘበት በጀት ዓመት በዲሲፕሊን ጥፋት ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ የቦነስ ክፍያ አያገኝም፡፡

5. የድርጅቱ ትርፍ የሚታወቀው የድርጅቱ የበጀት አመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ በውጭ ኦዲተሮች ተመርምሮ መግለጫ ከተሰጠበት በኋላ ነው።

6. አ/ማህበሩ የመዋቅር ለውጥ ሰርቶ የደመወዝ ስኬል ለውጥ ካደረገ በትርፍ ዘመኑ በተገኘ ትርፍ መሰረት እርከን አይጨምርም።

7. በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ለሚገኝ ትርፍ የቦነስና የእርከን ክፍያን በተመለከተ፡-

7.1. ድርጅቱ የ1 ወር ጥቅል ደሞዝ ካተረፈ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የደመወዙን 40% ቦነስ ያገኛል።

7.2. ድርጅቱ የ2 ወር ጥቅል ደመወዝ ካተረፈ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የደመዙን 60% ቦነስ ያገኛል።

7.3 ድርጅቱ የ4 ወር ጥቅል ደመወዝ ካተረፈ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የደመወዙን 50% ቦነስና 1 እርከን ጭማሪ ያገኛል።

7.4 ድርጅቱ የ6 ወር ጥቅል ደመወዝ ካተረፈ ለእያንዳደንዱ ሰራተኛ የደመወዙን 75% ቦነስና 1 እርከን ጭማሪ ያገኛል።

7.5 ድርጅቱ የ 9 ወር ጥቅል ደመወዝ ካተረፈ እያንዳንዱ ሰራተኛ የ1ወር ደመወዙን ቦነስና 2 እርከን ጭማሪ ያገኛል።

7.6. ድርጅቱ የ12 ወር ጥቅል ደመወዝ ካተረፈ እያንዳንዱ ሰራተኛ የ1 ወር ተኩል ደመወዙን ቦነስና 2 እርከን ጭማሪ ያገኛል።

አ ን ቀ ጽ 34

የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር፣

1. በቅጥር ላይ በተመሠረተ ግንኙነት የመነጨ ማንኛውም ክስ የመብቱን ጥያቄ ለማቅረብ ከሚቻልበት ቀን ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡

2. ሠራተኛው የሥራ ውሌ ከሕግ ውጭ ተቋርጦብኛል በማለት ወደ ሥራው ለመመለስ የሚያቀርበው ክስ ውሉ በተቋረጠ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡

3. ሠራተኛው የሚያቀርበው የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓትና የሌሎች ክፍያዎች ጥያቄ መጠየቅ ከሚገባው ጊዜ ጀምሮ እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡

4. የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሠራተኛው ሆነ በአሠሪው የሚቀርብ ማንኛውም የክፍያ ጥያቄ የሥራ ውሉ በተቋረጠ በስድስት ወር ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡ ደመወዝም ሆነ በትርፍ ሰዓት ክፍያ በአሠሪው ስህተት ለሠራተኛው የተከፈለው ተጨማሪ ክፍያ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ካልተስተካከለ በይርጋ ይቀራል፡፡

5. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና በዚህ ኀ/ስምምነት መሠረት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀመረው በመብቱ ለመጠቀም ከቻለበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ ነው፡፡ የይርጋ ጊዜው የመጨረሻ ቀን በሥራ ቀን ያልዋለ እንደሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይውላል፡፡

አ ን ቀ ጽ 35

ስህተት ስለማረም፣

አ/ማህበሩ የሰው ኃ/ል/አስ/መምሪያ የኀ/ስምምነቱ የማይፈቅደውን ወይም ከስሌት ስህተት ለሠራተኛው የማይገባውን የሥራ ደረጃ፣ የደመወዝ ዕድገት ጭማሪ፣ የዓመት ዕረፍት፣ ሲሠጥና ይህንን የመሳሰሉትን ሌሎች ስህተቶች ተፈጽመው ሲገኙ ከአንድ ዓመት በፊት ካልታረመ በዚህ ኀ/ስምምነት አንቀጽ 34 ቁጥር 5 በይርጋ ይታገዳል፡፡ ስህተት የፈፀመው ሰራተኛም ሆነ የስራ መሪ በሰራው ስህተት ልክ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ስህተት የሚታረመው በሚከተለው ሁኔታ ነው፣

ሀ/ በስህተት ለመደቡ የሚገባውን ደመወዝ ሳያገኝ የቆየና የተስተካከለለት ሰራተኛ መደቡ ከተስተካከለበት ቀን ጀምሮ ለስራ መደቡ የተቀመጠውን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

ለ/ በስህተት የሥራ ደረጃ የተፃፈለት ሠራተኛ ግን ትክክለኛው ደረጃ ተለውጦ ይፃፍለታል፡፡

አ ን ቀ ጽ 36

ኀብረት ስምምነቱ ከሌሎች ሕጐች ጋር ስላለው ውጤት፣

ይህ ኀብረት ስምምነት ተመዝግቦ በሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የመንግስትን መመሪያ /ፖሊሲ/ የሚጥስ ወይም ሕግን የሚቃረን አረፍተ ነገር፣ ቃል፣ ሐረግ ሲገኝበት ይህው ሐረግ ወይም አረፍተ ነገር ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

አ ን ቀ ጽ 37

ከኀብረት ስምምነቱ ውስጥ ስለአልተጠቀሱት ጉዳዮች

በዚሁ ስምምነት ላይ ያልተወሰነ ነጥብ፣

ሀ/ ስለአሠሪውና ሠራተኛ ግንኙነት በተመለከተ አ/ማህበሩና ሠ/ማህበሩ እየተገናኙ መመካከር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአንደኛው ወገን ጠያቂነት አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ውይይት ማድረግ ይቻላል፡፡

ለ/ በዚህ ስምምነት ውስጥ ያልተወሰኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ሠ/ማህበሩና የሰ/ኃ/ል/አስ/መምሪያ በጋራ ከተወያዩባቸው በኋላ ለዋና ሥራ አስኪያጅ በማሣወቅ ስምምነት ላይ ሲደረስ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲመዘገብ በማድረግ የህ/ስምምነቱ አካል ይሆናል፡፡

አ ን ቀ ጽ 38

በተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሠራተኞች ተፈፃሚ የማይሆኑ እና የሚሆኑ አንቀጾችን ይመለከታል፣

ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 በዚህ ኀብረት ስምምነት የተጠቀሱ አንቀጾች ለተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሠራተኞች ተፈፃሚ የሚሆኑና የማይሆኑ አንቀጾች እንደሚከተለው ተገልፀዋል፡፡

1 አንቀጽ 7፣ 8 ፣ 3ዐ ከንዑስ አንቀጽ ቁጥር 2 በስተቀር አንቀጽ 31፣ 32 ለተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሠራተኞች ተፈፃሚ አይሆንም፡፡

2 በዚህ ኀብረት ስምምነት አንቀጽ 2ዐ ከፊደል ሀ - ቀ የተጠቀሱት ልዩ ልዩ ፈቃዶችና የሕክምና ወጭ ለተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሠራተኞች ተፈፃሚ የማይደረጉ ሲሆን ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሠራተኞች ተፈፃሚ የሚሆነው በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን የኩንትራት ሰራተኛ በስራ ላይ ለሚደርስ አደጋ /ጉዳት/ ጉዳቱ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ኩንትራቱ እስከሚጠናቀቅበት ድረስ የሀኪም ፈቃድ ካመጣ ደሞዙን እየከፈለ ያሳክማል። የኩንትራቱ ጊዜ ሲያበቃ የጉዳት መጠኑን የሚያመለክት የህክምና ማስረጃ ካመጣ የአካል ጉዳት ካሣ ከፍሎ ያሰናብተዋል።

3 ለተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሠራተኞች በኀ/ስምምነት አንቀጽ 29 “ለ “የተገለፀውን ከአደጋ መከላከያ በስተቀር በሌሎች ተጠቃሚ የሚሆነው በተከታታይ ውሉ ሳይቋረጥ ለ 6 ወር ጊዜ የሚሠራ ከሆነ ነው በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 1 ከተጠቀሱት አንቀጾች ውጭ ለተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሠራተኞች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት፡-

ሀ/ አንቀጽ 3ዐ ፊደል”ሀ” ተራ ቁጥር 1፣2 እና 3 ንዑስ ቁጥር ሀ እና ሸ የተገለፁት ሲሆኑ በፊደል “ በ “ የተጠቀሰው ተግባራዊ የሚሆነው በሥራ ምክንያት ለሚመጣ ህመም ወይም አደጋ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

ለ/ አንቀጽ 31 ተራ ቁጥር 1 እና 3 ተፈፃሚ የሚሆኑት በሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ሠራተኛው ሲሞት ብቻ ነው፡፡

አ ን ቀ ጽ 39

ያለፉትን ኀ/ስምምነቶች ጠቅሶ መጠየቅ ስለአለመቻሉ፣

ይህ ሕብረት ስምምነት በሥራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ያለፈውን ኀ/ስምምነት በመጥቀስ ጥያቄ ወይም ክርክር መመስረት አይቻልም፡፡ 18ኛው ህብረት ስምምነት በዚህ ህብረት ስምምነት ተተክቷል፡፡

አ ን ቀ ጽ 40

የስምምነቱ አተረጓጐም፣

በኀብረት ስምምነቱ አንቀጽ አተረጓጐም ምክንያት በተዋዋይ ወገኖች መካከል ክርክር የተነሳ እንደሆነ ጉዳዩ ሥልጣን ላለው የሥራ ክርክር ሰሚ አካል ይቀርባል፡፡

አ ን ቀ ጽ 41

ኀብረት ስምምነቱ ፀድቆ የሚቆይበት ጊዜ፣

ይህ ኀብረት ስምምነት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ አራት /4/ ዓመት የፀና ይሆናል፡፡ ይህም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 134 ቁጥር /3/ መሠረት ነው፡፡

አ ን ቀ ጽ 42

ኀብረት ስምምነቱ የተፈረመበት ቀን፣

ይህ ኀብረት ስምምነት ስለ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት ድርጅቱ ወይም አሠሪ እየተባለ የሚጠራው የባ/ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክ/ማህበር እና መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ተብሎ የሚጠራው የባ/ዳር ጨ/ጨ/አ/ማህበር ሠራተኞች ማህበር መካከል ዛሬ________ ቀን________ ዓ/ም ተፈርሟል፡፡

የአ/ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ

-----------------------------------

የመ/ሠራተኛ ማህበሩ ሊ/መንበር

--------------------------------------

ETH Bahir Dar Textile S.C -

Start date: → Not specified
End date: → Not specified
Name industry: → Manufacturing
Name industry: → Manufacture of textiles
Public/private sector: → In the private sector
Concluded by:
Name company: →  Bahir Dar Textile S.C
Names trade unions: →  የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር የሰራተኞች ማህበር

TRAINING

Training programmes: → Yes
Apprenticeships: → No
Employer contributes to training fund for employees: → Yes

SICKNESS AND DISABILITY

Maximum for sickness pay (for 6 months): → 100 %
Provisions regarding return to work after long-term illness, e.g. cancer treatment: → No
Paid menstruation leave: → No
Pay in case of disability due to work accident: → Yes

HEALTH AND SAFETY AND MEDICAL ASSISTANCE

Medical assistance agreed: → Yes
Medical assistance for relatives agreed: → Yes
Contribution to health insurance agreed: → No
Health insurance for relatives agreed: → No
Health and safety policy agreed: → Yes
Health and safety training agreed: → No
Protective clothing provided: → Yes
Regular or yearly medical checkup or visits provided by the employer: → No
Monitoring of musculoskeletal solicitation of workstations, professional risks and/or relationship between work and health: → No clear provision
Funeral assistance: → Yes
Minimum company contribution to funeral/burial expenses: → ETB 1000.0

WORK AND FAMILY ARRANGEMENTS

Maternity paid leave: → 17 weeks
Job security after maternity leave: → Yes
Prohibition of discrimination related to maternity: → No
Prohibition to oblige pregnant or breastfeeding workers to perform dangerous or unhealthy work: → No
Workplace risk assessment on the safety and health of pregnant or nursing women: → No
Availability of alternatives to dangerous or unhealthy work for pregnant or breastfeeding workers: → No
Time off for prenatal medical examinations: → Yes
Prohibition of screening for pregnancy before regularising non-standard workers: → No
Prohibition of screening for pregnancy before promotion: → No
Facilities for nursing mothers: → No
Employer-provided childcare facilities: → No
Employer-subsidized childcare facilities: → No
Monetary tuition/subsidy for children's education: → No
Paternity paid leave: → 4 days
Leave duration in days in case of death of a relative: → 5 days

GENDER EQUALITY ISSUES

Equal pay for work of equal value: → No
Discrimination at work clauses: → Yes
Equal opportunities for promotion for women: → No
Equal opportunities for training and retraining for women: → No
Gender equality trade union officer at the workplace: → No
Clauses on sexual harassment at work: → Yes
Clauses on violence at work: → No
Special leave for workers subjected to domestic or intimate partner violence: → No
Support for women workers with disabilities: → No
Gender equality monitoring: → No

EMPLOYMENT CONTRACTS

Trial period duration: → Not specified days
Part-time workers excluded from any provision: → No
Provisions about temporary workers: → No
Apprentices excluded from any provision: → No
Minijobs/student jobs excluded from any provision: → No

WORKING HOURS, SCHEDULES AND HOLIDAYS

Working hours per day: → 8.0
Working hours per week: → 48.0
Maximum overtime hours: → 12.0
Paid annual leave: → 16.0 days
Paid annual leave: → 3.2 weeks
Rest period of at least one day per week agreed: → Yes
Maximum number of Sundays / bank holidays that can be worked in a year: → 
Paid leave to attend court or for administrative duties: →  days
Provisions on flexible work arrangements: → No

WAGES

Wages determined by means of pay scales: → No
Adjustment for rising costs of living: → 

Premium for overtime work

Premium for Sunday work

Premium for Sunday work: → 150 %

Meal vouchers

Meal allowances provided: → No
Free legal assistance: → No
Loading...