የስምምነቱ ዓላማ
- ሠራተኛው የማናቸውም የሥራ ውጤት ምንጭና መሠረት በመሆኑ ለጉልበቱና ለእውቀቱ ተመጣጣኝ ክፍያ አግኝቶ የሥራ መብቱ ተከብሮ የኑሮው ደረጃ እንዲሻሻል አስፈላጊ መሆኑን በማመን፣ የገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲና የመንግሥት የልማት ዕቅዶች መሠረት አክስዮን ማህበሩ የውድድር አቅሙን በማጠናከር ትርፋማ ሆኖ ለመቆየት ሠራተኛው የመሥራት ፍላጎቱንና ችሎታውን አዳብሮ ሙሉ ጉልበቱንና እውቀቱን በመጠቀም የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት በቅን ልቦናና በቅልጥፍና እንዲያከናውን ለማድረግ፣ በአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች፣ በአክስዮን ማህበሩና በማህበሩ መካከል ያለውን ግንኙነት ጤናማ በማድረግ በጋራ በመሥራት የአክስዮን ማህበሩን ራዕይ፣ ተልዕኮና ዓላማ በማሣካትና ሕልውናውን እንዲሁም የሠራተኛውን የሥራ ዋስትና በማረጋገጥ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን የሚያስችል ለተደራዳሪ ወገኖች መብትና ግዴታ እውቅና ሰጥቶ አብሮ ለመሥራት እንዲያስችል ነው፡፡
- የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011ን መሠረታዊ ጽንሰ ሃሣብና መርህን የተከተለ ነው፡፡
- የሠራተኛውን ደህንነትና ጤንነት ሊንከባከብ፣ሰብአዊ ክብሩን ሊጠብቅ፣ ተስማሚ የሥራ ሁኔታዎችን ሊፈጥር የሚችል የጋራ መተዳደሪያ ደንብ በማስፈለጉ የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አ/ማህበር እና የኮ/ጨ/ጨ/አ/ማህበር መ/ሠራተኞች ማህበር ይህንን የሕብረት ስምምነት ለ12ኛ ጊዜ የጋራ መተዳደሪያቸው ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
አንቀጽ 1 ትርጉም
የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ፡-
1.1 “አዋጅ” ማለት የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011ማለት ነው፡፡
1.2 “ሕጎች ደንቦችና መመሪያዎች” ማለት መንግሥት ያወጣቸውንና ወደፊትም የሚያወጣቸውን መመሪያዎች ደንቦችና ሕጎች አክስዮን ማህበሩ የሚያወጣው ደንብ፣ የሥራ መመሪያና ህብረት ስምምነትን ጨምሮ ማለት ነው፡፡
1.3 “አክስዮን ማህበር” ማለት የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ማለት ነው፡፡
1.4 “አሠሪ” ማለት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 2 ተራ ቁጥር 1 የተሰጠ ትርጉም ነው፡፡
1.5 “ሠራተኛ ማህበር” በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት የተቋቋመና ከሚመለከተው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሕጋዊ እውቅና ያገኘ የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ማለት ነው፡፡
1.6 “የአክስዮን ማህበሩ ማኔጅመንት ወይም የሥራ መሪ” ማለት የአክስዮን ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መምሪያ ሥራ አስኪያጅና ተጠሪነታቸው ለዋና ሥራ አስኪያጅ ወይም ለም/ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑ የአገልግሎት ኃላፊዎችና ተጠሪነታቸው ለመምሪያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑ የዋና ክፍል ኃላፊዎች ማለት ነው፡፡
1.7 “ሠራተኛ” ማለት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 4 በተመለከተው መሠረት ከኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ጋር በቅጥር ላይ የተመሠረተ የሥራ ግንኙነት ያለው ግለሰብ ነው፡፡
1.8 “ደመወዝ” ማለት አንድ ሠራተኛ በሥራ ውሉ መሠረት ለሚያከናውነው ሥራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ነው፡፡ ስለ ሌሎች ክፍያዎች በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 53 ተራ ቁጥር 2 መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
1.9 “የወር ደመወዝ” ማለት ለወር ተከፋዬች በ26 ቀናት በሥራ ውሉ መሠረት ላከናወኑት ሥራ ተተምኖ የሚደረግ ክፍያ ነው፡፡ ቀሪዎቹ አራት ቀናት የሣምንት የእረፍት ቀናት ስለሆኑ ደመወዝ አይከፈልባቸውም፡፡
1.10 “የሕብረት ስምምነት” ማለት በኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበርና በኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አ/ማህበር ሠራተኛ ማህበር መካከል የተደረገ የሕብረት ስምምነት ማለት ነው፡፡
1.11 “የሥራ ክርክር” ማለት ሕግን፣ የህብረት ስምምነትን፣ የሥራ ደንብን፣ የሥራ ውልን ወይም ሲሠራበት የቆዬ ልምድን መሠረት በማድረግ እንዲሁም በሕብረት ስምምነት ድርድር ወቅት ወይም ከሕብረት ስምምነት ጋር የተያያዙ ጉዳዬችን በሚመለከት በሠራተኛና በአሠሪ ወይም በሠራተኞች ማህበርና በአሠሪዎች መካከል የሚነሣ ክርክር ነው፡፡
1.12 “ዋና ሥራ አስኪያጅ” ማለት የኮምቦልቻ ጨ/ጨ/ አክስዮን ማህበርን ተረክቦ እንዲመራ የተመደበ የበላይ ኃላፊ ማለት ነው፡፡
1.13 “የሠራተኛ ማህበር መሪዎች” ማለት የሠራተኛ ማህበሩን ለመምራት በጠቅላላ አባል ሠራተኞች የተመረጡ የሥራ አስፈጻሚና የኦዲት ኮሚቴ አባላት ማለት ነው፡፡
1.14 “ሆርሻ”/የምክር ቤት/ አባል ማለት በየሥራ ክፍሎቹ በሠራተኞች ተመርጠው ከመደበኛ ሥራቸው ጎን ለጎን በአሠሪና ሠራተኛ መካከል አለመግባባት በሚፈጠርበት ጊዜ የማግባባትና የማስታረቅ ሥራ የሚሠሩ ማለት ነው፡፡
1.15 “መዋቅር” ማለት በባለሙያ ተጠንቶ በሥራ ላይ የዋለ አደረጃጀት ሲሆን፣ የሰው ኃይል ዕቅድ፣ ደመወዝ፣ የሥራ መደብን፣ ደረጃንና መስፈርቶችን የያዘ ሰነድ ማለት ነው፡፡
1.16 በወንድ ጾታ የተገለፁት ሴት ሠራተኞችንም ያካትታል፡፡
አንቀጽ 2 ማህበርን ስለማሣወቅ
2.1 አሠሪው የሠራተኛ ማህበሩን ስለማናቸውም የሥራ ሁኔታዎችና የህብረት ስምምነት ክርክር የሠራተኛ ተወካይ መሆኑን አውቆ ይቀበላል፡፡
2.2 አሠሪው በሕግ ከታወቀው ሠራተኛ ማህበር ሌላ በግልም ሆነ በቡድን በሕጋዊ መንገድ የመደራጀት መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕገወጥ መንገድ የማህበሩን ሕልውና የሚቃረኑ ሠራተኞችን አይደግፍም፣ አያበረታታም፣ አያስተናግድም፣ እርምጃም ይወስዳል፡፡
አንቀጽ 3 በህብረት ስምምነት ስላልተጠቀሱ ጉዳዬች
3.1 በዚህ ስምምነት ውስጥ ያልተወሰኑ ሠራተኛ ማህበሩና ማኔጅመንቱን በጋራ የሚመለከት ነጥብ ወደፊት ሲያጋጥም የአክስዮን ማህበሩ ማኔጅመንትና የሠራተኛ ማህበሩ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ተወያይተው ሲስማሙ ተጨማሪ እያደረጉ የዚህ ህብረት ስምምነት አካል እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ ይኸውም በሥራና ሥልጠና መምሪያ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
3.2 በዚህሕብረት ስምምነት በግልጽ ያልተፈቀደው እንደተከለከለ /እንዳልተፈቀደ/ ይቆጠራል/፡፡
አንቀጽ 4 ስህተትን ስለ ማረም
የአክስዮን ማህበሩ ማኔጅመንት የህብረት ስምምነት የማይፈቅደውን ወይም በስሌት ስህተት ለሠራተኛ የሥራ ደረጃ፣ የደመወዝ እድገት፣ ጭማሪ፣ የዓመት እረፍት ቢሰጥ እንዲሁም ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ይህንንም የመሣሰሉ ሌሎች ማናቸውንም ስህተቶች ተፈጽመው ሲገኙ ስህተቱን በአንድ ዓመት ውስጥ ማረም ይችላል፡፡
ይህም፡-
ሀ/ የደመወዝ ብልጫ ጭማሪና ሌሎች ቅጥማ ጥቅሞችን የተሰጠው ሠራተኛ ደመወዙ
ከተጨመረበት ቀን አንስቶ እስከተስተካከለበት ቀን ድረስ የተሰጠው ብልጫ በየወሩ የደመወዙን ¼ኛ በማይበልጥ ሁኔታ ከደመወዙ ላይ እየተቀነሰ ገቢ ይሆናል፡፡
ለ/ ተቀንሶ የተጨመረለት ግን ይስተካከልለትና ቀደም ብሎ የቀረው ተሠልቶ በአንድ
ጊዜ ይከፈለዋል፡፡ በስህተት የሥራ ደረጃ የተሰጠው ሠራተኛ ግን ትክክለኛው ደረጃ ተስተካክሎ ይጻፍለታል፡፡ ሆኖም ሌሎች የመብትና የክፍያ ስህተቶችን በተመለከተ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011እና አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ይታያል፡፡
ሐ/ የእድገትና ደረጃ ምደባ በስህተት ለሠራተኛ ከተሰጠ በታወቀበት ጊዜ ያለአግባብ የተሰጠው ደረጃና ደመወዝ እንዲነሣ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም በስህተት ሣያገኝ የቀረው ከተመደበበት ቀን አንስቶ የሚገባውን ደረጃና ደመወዝ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ስህተቱን የፈፀመው በህብረት ስምምነቱ ወይም በሥራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ይቀጣል፡፡
አንቀጽ 5 የሠራተኛ ማህበሩ በአክስዮን ማህበሩ ማኔጅመንት ስለ ሚካፈልበት ሁኔታ
5.1 አክስዮን ማህበሩን ለማስፋፋት፣ የተሻለ አመራረትና የአስተዳደር መልክ ለመስጠት የአክስዮን ማህበሩን ተልእኮና ዓላማ ለማስፈፀም በሚደረገው ጥረት ከአሠሪው ጋር በመመካከር ሃሣብ በማቅረብና ሠራተኛውን በማሣመን የበኩሉን ድርሻ ይወጣል፡፡
5.2 አክስዮን ማህበሩ አጠቃላይ ሠራተኛውን የሚነካ የውስጥ አሠራር ከመለወጡ ወይም ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በቅድሚያ ለማህበሩ ያሣውቃል፡፡
5.3 ሠራተኛ ማህበሩ በሠራተኛ ቅጥርና ዕድገት ዝውውር በሚታይበት ኮሚቴ አንድ አባል ያሣትፋል፡፡ ይሁንና በአንድ ጊዜ ከሁለት በላይ ፈተና የሚሰጥ ከሆነ ሠራተኛ ማህበሩ ከአንድ በላይ የሥራ አስፈጻሚ ሊመድብ ይችላል፡፡ ሠራተኛ ማህበሩ የማይሣተፍበትን ምክንያት /ማስረጃ/ ካቀረበ ጉዳዩ በሰ/ኃ/ል/አ መምሪያና በመ/ሠ/ማህበር ሊቀመንበር /ወኪል/ በኩል ይታያል፡፡ሆኖም ግን ሠራተኛ ማህበሩ የማይሣተፍበትን ምክንያት/ማስረጃ/ ካላቀረበ አክስዮን ማህበሩ በቅጥር፣ በዕድገትና በዝውውር ላይ ይወስናል፡፡
5.4 የሠራተኛውን ደህንነት ለመጠበቅና ሞራሉን ለመገንባት አክስዮን ማህበሩ በሚያደርገው ጥረት ሁሉ የሠራተኛ ማህበሩ እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
5.5 ሠራተኛ ማህበሩ ስለ ሥራ ሁኔታዎች፣ የሠራተኛ ማህበሩን የሥራ እንቅስቃሴ ለመገምገም፣ ሠራተኛውን ለመሰብሰብ ቢፈልግ አሠሪው በዓመት አንድ የሥራ ቀን ከሠራተኛ ማህበሩ ጋር በመመካከር ይፈቅዳል፡፡ሆኖም አስቸኳይ ሁኔታ ሲያጋጥምናማህበሩ ሲጠይቅ እንዲሁም አክሲዮን ማህበሩ ሲያምንበት በአመት አንድ ተጨማሪ የሥራ ቀን ትብብር ያደርጋል፡፡
5.6 ሠራተኛ ማህበሩ በአክስዮን ማህበሩ ዕቅድና አፈጻጸም ግምገማ ላይ ይሣተፋል፡፡የአክስዮን ማህበሩ ዓመታዊ እንዲሁም የየሩብ ዓመቱን አጠቃላይ የሥራ ዕቅድ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ወር የሥራ አፈጻጸሙን ሪፖርት በየዓመቱ መጨረሻና በየሩብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ለሠራተኛ ማህበሩ በኮፒ ይሰጣል፡፡
5.7 አደጋ የደረሰባቸው ሠራተኞች መግለጫ በአክስዮን ማህበሩ ሪስክ ማኔጅመንትና ካሣና ጥቅማ ጥቅም የሚሞላውን ቅጽ አንድ ኮፒ ለሠራተኛ ማህበሩ ይሰጣል፡፡
5.8 ጠቅላላ ሠራተኛን የሚመለከቱ ጥናቶች እንዲሁም የሥራ ደንቦች፣ መመሪያዎች ሲወጡ አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኛ ማህበሩ አንድ ኮፒ ይሰጣል፡፡
አንቀጽ 6 የአክስዮን ማህበሩ መብት
6.1 የአክስዮን ማህበሩ ሥራ የመምራት፣ የማቀድ፣ የመቆጣጠር እንዲሁም በዚህ ህብረት ስምምነት በተጠቀሱ ጉዳዬች ላይ በመመርኮዝ ሠራተኞችን የመቅጠር፣ በየቦታው የመመደብ፣ የማሣደግና ከቦታ ቦታ ለማዛወር መብቱ የአክስዮን ማህበሩ ነው፡፡
6.2 በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ሠራተኛን በበቂ ምክንያት የመቅጣት፣ ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ የማድረግና እንዲሁም ከዲስፒሊን ጋር በተገናኘ ሁኔታ ጉዳዩ እስከሚጣራ ድረስ በሌላ ሥራ ለማሠራት ወይም ማገድ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሠራተኛው አጥፊ ሆኖ ካልተገኘ የታገደበት ደመወዙ ተከፍሎት ወደ ቀድሞ ሥራው ይመልሰዋል፡፡
6.3 አዲስ የሥራ ቦታን የመክፈት ወይም የማጠፍ አስፈላጊነቱን የመወሰን፣ በየሥራ መደቡ አስፈላጊውን የሰው ኃይል የመወሰን፣ ሠራተኛን የማሣደግና የእርከን ጭማሪ የማድረግ ለየሥራ መደቡ የሚፈለገውን የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድ የማውጣት የመወሰንና ሠራተኛን የማሣደግ፣ አዲስ ሠራተኛን በሕጉ መሠረት አወዳድሮ የመቅጠር አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሠራተኛን የመሸለም በሕጉ መሠረት የማዛወር መብት የአክስዮን ማህበሩ ነው፡፡
6.4 ስለ አክስዮን ማህበሩ የሥራ ሁኔታ ስለ አክስዮን ማህበሩ ሃብትና ንብረት አጠባበቅ ከሌላ ሦስተኛ ወገን ጋር የመነጋገር፣ ስለ ዕቃ ግዥና ሽያጭ የመዋዋል፣ ኢንሹራንስ የመግባት፣ ሌላም የአክስዩን ማህበሩ ሥራ አስፈላጊ የሆነ ውል የመግባት በአክስዮን ማህበሩ ስም የመክሰስና የመከሰስ መብት አለው፡፡
6.5 በአክስዮን ማህበሩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ሥራንና የሠራተኛ ጉዳይን በሚመለከት፣ በትምህርት ኘሮግራም፣ በትርፍና ኪሣራ ወይም በማናቸውም ጉዳይ መግለጫ የመስጠትና ማስታወቂያ የማውጣት መብት አለው፡፡
6.6 ሠራተኛው ከአክስዮን ማህበሩ የተበደራቸውን ብድሮች የመንግሥት ግብር ለመክፈል፣ በጽሁፍ የተስማማበትን ጉዳይ ወይም እንዲከፍል ከፍ/ቤት የተወሰነበትን ገንዘብ አክስዩን ማህበሩ ሠራተኛው ከሚያገኘው መደበኛ ደመወዝ ቀንሶ የመተካት ወይም ለሕጋዊ ባለመብቶች የመክፈል መብት አለው፡፡
6.7 በአጥፊዎች ላይ ሊወሰዱ የሚባቸውን የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች በሕጉ መሠረት የመወሰን፣ የማሻሻል፣ ቅጣቶችን የማንሣት ወይም ይቅርታ የማድረግ የሚመለከታቸው የማኔጅመንት አካል መብት ነው፤ ሆኖም ከሥራ የተሰናበተን ሠራተኛ ይቅርታ ማድረግ የሚችለው የአክስዮን ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይም በዋና ሥራ አስኪያጅ የተወከለ ብቻ ነው፡፡
6.8 ሕግን ደንብንና መመሪያን በመከተል የቅጥር፣ የዕድገት፣ የዝውውርና የትምህርት ሥልጠናና ሌሎች የሠራተኛውን እንቅስቃሴ የሚመለከትና የምርትና ጥገና፣ ግዥና ሽያጭ፣ የንብረት አጠባበቅና አጠቃቀም፣ የፋይናንስና ሌሎች አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው ጉዳዬች መመሪያ የማውጣት፣ የመስጠትና የማስፈፀም መብት የአክስዮን ማህበሩ ነው፡፡
6.9 ለአክስዮን ማህበሩና ለሠራተኛው ደህንነት እንዲሁም ለአክስዮን ማህበሩ ሀብትና ንብረት ጥበቃ ሲባል በመውጫና በመግቢያ በር ላይ ፍተሻ የማድረግ መብት አለው፡፡
6.10 በማንኛውም ስብሰባ ላይ የሌላውን ስብእና የሚነካ ወይም ባልተጨበጠ መረጃ ሀሰተኛ መልዕክት ያስተላለፈ ወይም ሁከት እንዲፈጠር ያደረገ ሠራተኛን አክስዮን ማህበሩ በሕግ የመጠየቅ መብት አለው፡፡
አንቀጽ 7 የአክስዮን ማህበሩ ግዴታዎች
7.1 በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚህ ሕብረት ስምምነት ወይም በሌሎች የመንግሥት ሕጎች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ የተመለከቱትን መብቶችና ግዴታዎች በትክክል በሥራ ላይ የማዋል ግዴታ አለበት፡፡
7.2 አክስዮን ማህበሩ በብሔረሰብ፣ በፆታ፣ በኃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት በሠራተኞች መካከል ልዩነት አያደርግም፡፡ ሆኖም ግን የሴት ሠራተኞችን ተሣትፎ ለማሣደግ በሚደረጉ የእድገት፣ የዝውውር፣ የሥልጠና፣ የቅጥር፣ የትምህርትና ሌሎች ውድድሮች ላይ ለሴቶች 3 ነጥብ ተጨምሮ ይሰጣል፡፡ እኩል ነጥብ ሲመጣ ለሴቶች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ መንግሥት ለፆታ የሚሰጠውም ሆነ የሰጠውን ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ ሴቶችን ያበረታታል፡፡
7.3 ሊከፍል የተስማማበትን ደመወዝና ሌሎች ተከፋዩችን በተወሰነው ጊዜ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
7.4 አክስዮን ማህበሩ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ጥሬ ዕቃዎችና መሣሪያዎችን ለሠራተኞች የማቅረብና በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 12/1 ሀ እና ለ መሠረት ግዴታ አለበት፡፡
7.5 አክስዮን ማህበሩ ማንኛውም የሠራተኛ ማህበር መሪ ወይም አባል በመሆኑና ባለመሆኑ ተጽእኖ ወይም አድልዎ አይደረግበትም፡፡ የሥራ አፈጻጸም /ግምገማ/ በተመለከተ በሠራተኛ ማህበር መሪነት ከመመረጡ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘውን ነጥብ ይያዝለታል፡፡
7.6 ሠራተኛ ሲቀጥር ሲመድብና የሥራ መደብ ለውጥ ሲያደርግ የሠራተኛው ፎቶግራፍ የተለጠፈበትና የሚሠራበትን ቦታና የሥራ መደብ የሚያመለክት ደረጃውን የጠበቀ የመታወቂያ ካርድ በነጻ አክስዮን ማህበሩ ይሰጣል፡፡ ካረጀ አሮጌውን አስረክቦ አዲስ ይለውጥለታል፡፡ መታወቂያው በአያያዝ ጉድለት ምክንያት ከ5 ዓመት በታች ላገለገለ መታወቂያ ካርድ ዋጋውን ብር 25.00 /ሃያ አምስት ብር/ ከፍሎ ይለወጥለታል፡፡ ከጠፋበት ግን ሠራተኛው መታወቂያው መጥፋቱን እንዳረጋገጠ አግባብ ካለው የህግ አካል መረጃ ሲያቀርብ እና ለአክስዮን ማህበሩ በማመልከቻ ሲጠይቅ25.00 ብር /ሃያ አምስት ብር/ ከፍሎ መታወቂያው ይሰጠዋል፡፡
7.7 የሠራተኛውን ጤንነት፣ ደህንነትና እንዲሁም የሕሊና ክብር እንዲጠበቅ ተገቢውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
7.8 የአክስዮን ማህበሩና የሠራተኛውን ጥቅም የተሣሰረ መሆኑን በመረዳት የምርት መገልገያዎችና ማንኛውም የአክስዮን ማህበሩ ሃብትና ንብረት በጥንቃቄ እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡
7.9 የማንኛውም ሠራተኛ ቅጥር፣ ዕድገት፣ ቅጣትና ስንብት ውሣኔን በሚመለከት ለሠራተኛ ማህበሩ በጽሁፍ ያሣውቃል፡፡
7.10 አዲስ የሚቀጠሩ ሠራተኞችን አክስዮን ማህበሩ በራሱ ወጪ ጤንነታቸውን ያስመረምራል፡፡ከኩባንያው የሥራ ባህሪ አንጻር የሚቀጠሩ ሠራተኞችምዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን አለበት፡፡
7.11 ሠራተኛው የተቀጠረበትን ቀን፣ የደመወዝ ልክ፣ የትምህርት ማስረጃ፣ የሥራ ልምድ፣ የሥራ አፈጻጸም /ግምገማ/፣ ዕድገት ያገኘባቸውን ማስረጃዎች ሥልጠናዎችና ትምህርቶች የወሰዳቸውን ፈቃዶች፣ የጤንነት ሁኔታዎች የመሣሰሉትን በግልጽ በሚያሣይ መዝገብ በጥንቃቄ የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡
7.12 በዚህ ህብረት ስምምነት የተደነገጉ የዲሲኘሊን እርምጃዎች አወሣሰድ፣ የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓትና የመሣሰሉት ጉዳዬች አፈጻጸም የመከታተል ግዴታ አለበት፡፡
7.13 ለእያንዳንዱ ሠራተኛ በተመደበበት ሥራ የሥራ ዝርዝር መግለጫ /ጆኘ ዲስክሪብሽን/ በተጨማሪም ሠራተኛው የሚጠቀምበትን የሥራ ውጤት /የሥራ አፈጻጸም መለኪያ ግብ/ አውቆ በሥራ ላይ እንዲውል አዘጋጅቶ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
7.14 ጤናማ የሥራ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ከአደጋ ለመከላከል የሚያገለግሉና አደጋ በደረሰበት ጊዜ ለመጀመሪያ እርዳታ የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን የመፀዳጃና የሰውነት መታጠቢያ ክፍሎችን ከነ ጽዳት ሠራተኞቻቸው አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
7.15 የሠራተኛ ማህበር እንዲጠናከር የተቻለውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ አክስዮን ማህበሩና ሠራተኛ ማህበሩ በሠራተኛ ማህበሩ ሥር ለተቋቋሙት ብድርና ቁጠባ ሕብረት ሥራ ማህበር፣ ለሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበርና ለሠራተኞች መረዳጃ ማህበር አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፣ ያበረታታል፡፡
7.16 ከሠራተኛው ማህበር ጋር በመተባበር የህብረት ስምምነቱን አንቀጾች ትርጉምና አፈጻጸም ሠራተኞች እንዲረዱት ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም አክስዮን ማህበሩ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ አንድ ቅጅ የሕብረት ስምምነት ኮፒ በፖኬት ሣይዝ አሣትሞ በነጻ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
7.17 ከመንግሥት ወይም ከበላይ አካል ሠራተኛውን በሚመለከት የሚተላለፉትን አዋጅና መመሪያዎች ለሠራተኛውና ለሠራተኛ ማህበሩ በወቅቱ የማሣወቅ ግዴታ አለበት፡፡
7.18 ሠራተኛው በየወሩ ለመክፈል የተስማማበትን የሠራተኛ ማህበር ወርሃዊ የአባልነት መዋጮ፣ ገንዘብና ብድር ቁጠባ ማህበር፣ መረዳጃ ማህበር የሠራተኛ ማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በማድረግ በጠቅላላ ጉባኤ የሚወሰኑ ክፍያዎችን አክስዮን ማህበሩ ከሠራተኛው ደመወዝ ቀንሶ በተቋሞቹ በተከፈተው የባንክ ሂሣብ ገቢ ያደርጋል፤ ሌሎች ክፍያዎችን በሚመለከት ለአፈጻጸም አመቺነቱን አክስዮን ማህበሩ አረጋግጦ አከፋፈሉን የመፈፀም ግዴታ አለበት፡፡
7.19 የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የበጀት መዝጊያ፣ የሂሣብ ሪፖርቶችን፣ የሽያጭ፣ የምርት ውጤት፣ የዓመቱን ትርፍና ኪሣራ ሪፖርት ለሠራተኛ ማህበሩ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም አክስዮን ማህበሩ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታዎች ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ ሠራተኞችን በመሰብሰብ የማሣወቅ ግዴታ አለበት፡፡
7.20 አክስዮን ማህበሩ ከሠራተኛ ማህበሩ ጋር በመተባበር የፖስታ አገልግሎት ለሠራተኛው እንዲሰጥ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
7.21 ሀ/ የሥራ ውል በሚቋረጥበት ወይም ሠራተኛው በሚጠይቅበት በማንኛውም ጊዜ ሠራተኛው ሲሰራ የነበረውን የሥራ ዓይነት፣ የአገልግሎት ዘመኑንና ሲከፈለው የነበረውን ደመወዝ የሚያሣይ የምሥክር ወረቀት በነጻ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት የደመወዝና የሥራ መደብ ለውጥ ሣይኖረው ከስድስት ወር በፊት በድጋሜ መረጃ እንዲሰጠው ከጠየቀ የአገልግሎቱን ዋጋ ብር 25.00 /ሃያ አምስት ብር/ ከፍሎ ይሰጠዋል፡፡
ለ/በአንቀጽ 7.21.ሀ የተቀመጠው ኃሳብ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ሠራተኛ ስለ ራሱ ጉዳይ በጽሁፍ መረጃ እንዲሰጠው ሲጠይቅ መረጃ በነጻ ይሰጠዋል፡፡ሆኖም ግን ከስድስት ወር በፊት በድጋሜ መረጃ እንዲሰጠው ከጠየቀ የአገልግሎቱን ዋጋ ብር 25.00 /ሃያ አምስት ብር/ ከፍሎ ይሰጠዋል፡፡
7.22 ይህን የሕብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም በአዲስ የሥራ ሁኔታዎች ላይ ሠራተኛ ማህበሩ ሲጠይቅ ቀርቦ የመወያየት ግዴታ አለበት፡፡
7.23 ለሠራተኛው የሠርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ መኪና ይመድባል፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙን አክስዮን ማህበሩና ሠራተኛ ማህበሩ በጋራ ይወስናሉ፡፡
7.24 የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር በሚባሉበት ጊዜ ለማደሪያ ገርጅ በተሠራው ማረፈያ ቤት እንዲያድሩ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን ግልጋሎት የሚሰጠው ባሉት አልጋዎች ቁጥር ልክ ይሆናል፡፡
7.25 አክስዩን ማህበሩ ለሴት ሠራተኞች የጡትና የማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰርምርመራ በነጻ ይሰጣል፡፡
7.26 አክስዮን ማህበሩ ለሴት ሠራተኞች ሕጻናት ማቆያ /ዴይ ኬር/ ያመቻቻል፡፡
7.27 አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኞች የጡረታ ቁጥራቸውን ያሣውቃል፡፡ የጡረታ ጊዜያቸውም ሲደርስ የጡረታ አበል በጊዜው እንዲያገኙ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 8 አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኛ ማህበሩ የሚሰጠው ግልጋሎት
8.1 የሠራተኛ ማህበሩን ሥራ ለማከናወን በቂ የሆነ ቢሮ ከሙሉ መገልገያ ጋር ለውስጥ አገልግሎት የሚውል ስልክ፣ ለውጭ አገልግሎት የሚሰጥ የቀጥታ መስመር ሥልክ አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኛ ማህበሩ ይሰጣል፤ የቀጥታ መስመር ሥልክ ክፍያን በተመለከተ ኪራዩን ጨምሮ ለተጠቀሙበት በየወሩ እስከ ብር 3ዐዐ.00 /ሦስት መቶ/ ድረስ አክስዩን ማህበሩ ይሸፍናል፡፡
8.2 የሠራተኛ ማህበሩ ማስታወቂያና ትምህርታዊ ጽሁፍ የሚለጠፍበት ማስታወቂያ ሠሌዳ ያዘጋጃል፣ የተላላኪ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
8.3 ሠራተኛ ማህበሩ በቅድሚያ በሚያሲዘው ኘሮግራም መሠረት ለአዲስ አበባና ሌሎች ከኮምቦልቻ 3ዐዐ ኪ/ሜትር ርቀት ላላቸው ቦታዎች አክስዮን ማህበሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን ከዚህ በላይ ከሆነ ግን እንደአስፈላጊነቱ አክስዩን ማህበሩ ሲያምንበት ሊተባበር ይችላል፡፡
አንቀጽ 9 የሠራተኛ ማህበሩ መብት
9.1 በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ ስለተመለከቱትም ሆነ ከስምምነቱ ውጭ ሊያጋጠሙ ስለሚችሉ ማንኛቸውም የሠራተኛው የሥራ ሁኔታዎች ሠራተኛውን ወክሎ ከአሠሪው ጋር የመነጋገር መብት አለው፡፡
9.2 ቅሬታ ወይም በደል ደረሰብን የሚሉ ሠራተኞችን ወክሎ ከአሠሪው ጋር የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011እና የህብረት ስምምነት በሚፈቅደው መሠረት ለመደራደር ወይም ሠራተኛን /ሠራተኞችን/ ወክሎ ለመከራከር መብት አለው፡፡
9.3 በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 82 እና በህብረት ስምምነቱ በተወሰነው መሠረት የማህበሩ መሪዎች የሥራ ክርክር ለማቅረብ፣ የህብረት ስምምነት ለመደራደር፣ በማህበር ስብሰባ ለመገኘት፣ በሴሚናሮችና በሥልጠና ለመካፈል እንዲችሉ ከአንድ የሥራ ቀን /24 ሰዓት/ በፊት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ የመጠየቅ መብት አለው፡፡
9.4 ሠራተኛ ማህበሩ ስለ ሠራተኛ ሁኔታ ከሌላ አካል ጋር ለሚቀርብለት ጥያቄ ማብራሪያ የመስጠትና የመነጋገር መብት አለው፡፡
9.5 አክስዮን ማህበሩ በሚዘረጋው አዳዲስ የአሠራር ሥርዓቶችና ማሻሻያዎች ላይ ሠራተኛ ማህበሩ የመሣተፍ መብት አለው፡፡
አንቀጽ 1ዐ የሠራተኛ ማህበሩ ግዴታዎች
10.1 የህብረት ስምምነቱ፣ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅን ትርጉምና አፈጻጸም ከአክስዮን ማህበሩ ጋር በመተባበር ሠራተኛው እንዲረዳ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
10.2 ይህንን የህብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም በአዳዲስ የሥራ ሁኔታዎች /የአሠራር ሥርዓቶችና ማሻሻያዎች/ ላይ አክስዮን ማህበሩ ለውይይት ሲጠራ ቀርቦ የመወያየት ግዴታ አለበት፡፡
10.3 የሕብረት ስምምነቱን ህጎችና የመንግሥት መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ አሠሪው የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሥራ ዕቅዶችን ለማስፈፀም የመተባበርና የመፈፀም ግዴታ አለበት፡፡
10.4 በአክስዮን ማህበሩ የሥራ አካባቢዎች ሠራተኛው ዲስፒሊን እንዲያከብርና የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲሰፍን የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
10.5 ሠራተኛው የሥራ ሰዓት አክብሮ መላው ጉልበቱንና ችሎታውን በሥራ ላይ አውሎ ምርቱን በጥራትና በብዛት እንዲያመርትና የአክስዮን ማህበሩ ዕቅድ ግቡን እንዲመታ የማስተባበር ግዴታ አለበት፡፡
10.6 የሥራና የአደጋ መከላከያ አልባሣትን ሠራተኛው እንዲጠቀም ሠራተኛ ማህበሩ ከአክስዮን ማህበሩ ጋር በመሆን የማስፈፀምግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 11 የሠራተኛ መብቶች
11.1 ሴት ሠራተኞች ሲወጡና ሲገቡ የሚፈተሹት በሴትፈታሾችነው፡፡
11.2 በሕግ ወይም በህብረት ስምምነት፣ በሠራተኛ ማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በሥራ ደንብ በተወሰነው ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት ካልሆነ ወይም ሠራተኛው በጽሁፍ ካልተስማማ በስተቀር አክስዮን ማህበሩ ከሠራተኛው ደመወዝ ሊቀንስ ወይም በዕዳ ሊይዝ ወይም ሊያቻችል አይችልም፡፡
11.3 በመንግሥት ሕጎች፣ መመሪያዎች፣ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚህ ሕብረት ስምምነት ውስጥ ለተጠቀሱት የሥራ ሁኔታዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አለው፡፡
11.4 የሚገባውን ደመወዝና ሌላም ሕጋዊ ክፍያ ወይም ጥቅም በወቅቱ የማግኘት መብት አለው፡፡
11.5 ማንኛውም የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ በሠራተኛ ማህበሩ አማካኝነት ወይም በግሉ ቅሬታውን ወይም አቤቱታውንለግልግል ዳኞች ወይም ለሥራ ክርክር ችሎት ለማቅረብና ሕጋዊ መብቱን ለማስከበር ይችላል፡፡
11.6 ማንኛውም ሠራተኛ በግል ማህደሩ ላይ ጥርጣሬ ሲኖረው በሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያና በሠራተኛ ማህበሩ በኩል አስቀርቦ የማየት መብት አለው፡፡
11.7 የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011እንደተጠበቀ ሆኖ በሠራተኛው ጥፋት ወይም ቸልተኝነት ሣይሆን በመሣሪያ ብልሽት ወይም በጥሬ ዕቃ እጥረት ሠራተኛው ሣይሠራ ቢውል የየዕለቱን መደበኛ ደመወዝ የማግኘት መብት አለው፡፡
11.8 ሠራተኛው በማንኛውም ስብሰባ ወይም በማንኛውም ሕጋዊ መንገድ ሃሣቡንና ቅሬታውን የመግለጽና የማቅረብ መብት አለው፡፡
11.9 ማንኛውም የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ የሆነ ወይም የነበረ አስፈለጊውን የበር መግቢያና መውጫ ፎርማሊቲ አሟልቶ የመብት ጥያቄ ለማቅረብ ወደሚመለከተው ክፍል የመቅረብ መብት አለው፡፡
11.10 ማንኛውም የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደሙ መኖሩ የተረጋገጠሠራተኛ ስለተገኘበት ብቻ ከመደበኛ ሥራው ላይ ምንም አይነት አድሎና መገለል አይደረግበትም፡፡
11.11 የእድሜ ጣራው ለጡረታ የደረሰ ሠራተኛ ጡረታ ከሚወጣበት ጊዜ 6 ወር ቀድሞ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይሰጠዋል፡፡ የጡረታ ጊዜው ደርሶ የጡረታ ደብተሩ ያልደረሰውና ቀሪ ሥራ የሚቀረው ከሆነ እስከ 6 ወራት ለሚደርስ ጊዜ አክስዮን ማህበሩ በኮንትራት ቀጥሮ እያሠራው እንዲቆይ ይደረጋል፡፡ ሆኖም አክስዩን ማህበሩ ለሥራ የሚፈልገው ከሆነ ሊቀጥረው ይችላል፡፡
11.12 ደመወዝና ሌሎች ክፍያዎችን በወቅቱ ተገኝቶ ለመቀበል ካልቻለ ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚውል የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ በሚያዘጋጀው ቅጽ ላይ ማረጋገጫ በመስጠት ለወኪሉ እንዲከፈልለት ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን የተለዬ ችግር ከሆነ እንደሁኔታው በማየት የሰው ኃ/ል/አ/መምሪያ እንዲከፈል ያደርጋል፡፡
አንቀጽ 12 የሠራተኛ ግዴታዎች
12.1 ማንኛውም ሠራተኛበቅልጥፍናና በተሟላ ትጋት ሥራውን የማከናወን ግዴታ አለበት፡፡
12.2 በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011በዚህ ህብረት ስምምነትና ለሥራ ማሻሻያ ከመንግሥትና ከአክስዮን ማህበሩ የሚተላለፉትን ደንቦችና መመሪያዎች የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
12.3 ማንኛውም የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ አስቀድሞ ፈቃድ ካልተሰጠው በስተቀር በመደበኛ ሥራው ላይ የአክስዮን ማህበሩን የሥራ ሰዓት አክብሮ በሥራ ላይ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡
12.4 በአክስዮን ማህበሩ ላይ ወይም በሥራ ባልደረቦች በሚያጋጥም ጉዳት ወይም አደጋ ላይ በተፈለገው ሁኔታ ሁሉ እርዳታ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
12.5 ለሥራው አስፈላጊ ሆነው የተሰጡትን መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረቶችን በጥንቃቄ መያዝ ይኖርበታል እንዲሁም የሥራው ሰዓቱሲጠናቀቅ በሚገባ የማስቀመጥ ግዴታ አለበት፡፡
12.6 ለሥራው ወይም ለአክስዮን ማህበሩ ጥሩ ስም በሚያስገኝ መንገድ ሁልጊዜ እራስንና አካባቢን የመንከባከብና የመጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡
12.7 የሥራ አፈጻጸምምዘና ሥርዓት፣ የአካባቢና የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት፣ የካይዘን አሠራሮችንእንዲሁም ኩባንያውንና ሠራኛውን የሚጠቅሙ አዳዲስ አሠራሮችንየመቀበል ግዴታ አለበት፡፡
12.8 በአክስዮን ማህበሩ ወይም በአክስዮን ማህበሩ መሣሪያዎች ላይ የሠራተኞችን ደህንነትና ጤንነት የሚጎዳ ሁኔታ ሲያገኝ የሚደርሰውን ማንኛውንም አደጋ ወዲያውኑ ለአሠሪው የማሣወቅ ግዴታ አለበት፡፡
12.9 በሥራ ላይ መተባበርና ለአክስዮን ማህበሩ ጥቅም የለውጥ እንቅስቃሴ አሠራር ላይ አንድነት የማሣየት ግዴታ አለበት፡፡
12.10 ማንኛውም ሠራተኛ ከሚመለከተው ኃላፊ የጽሁፍ ፈቃድ ሣይቀበል የአክስዮን ማህበሩ ንብረት የሆነውን ማንኛውንም ዓይነት ምርት ወይም ጥሬ ዕቃ፣ መገልገያ ዕቃ /ቱልስ/ ከአክስዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ በማውጣት፣ ለራሱ /ለግሉ/ ሊገለገልበት ወይም ለሌላ ግለሰብ አሣልፎ ለመስጠትና ከጥቅም ውጭ ማድረግ የለበትም፡፡
12.11 በአሠሪውና በሠራተኛው ማህበር ወይም በአሠሪውና በሠራተኞች መካከል ወይምበሠራተኞች መካከል ያለመግባባት የመፍጠር፣ የሃሰት ወሬ አሉባልታ መንዛትና ጠብ ማንሣት ወይም እንዲነሣ መገፋፋት ወይም እራሱንም ሆነ የሥራ ጓደኞቹን አደጋ ላይ የሚጥል ወይም የአክስዮን ማህበሩን ጥቅም የሚነካ ሁኔታ ሲያጋጥመው ወዲያውኑ ለአሠሪው የማሣወቅ ግዴታ አለበት፡፡
12.12 ማንኛውም ሠራተኛ በአክስዮን ማህበሩ የሥራ ሰዓት በአክስዮን ማህበሩ ግቢና በማምረቻ ቦታዎች ሊያስገባ የሚችል ሁኔታዎች ሲያጋጥመው በቅድሚያ መታወቂያውን በማስያዝ የት ክፍል እንደሚሄድ ለጥበቃ ክፍል በማሣወቅ መግባት ይኖርበታል፡፡
12.13 ማንኛውም ሠራተኛ በመደበኛ የሥራ ሰዓት መተኛት የለበትም፡፡
12.14 ሠራተኛው አእምሮውን በሚያደነዝዝ፣ አነቃቂ እጽ እና በአልኮል መጠጥ ኃይል ተመርዞወይም ይዞበሥራ ገበታው ላይ መገኘት የለበትም፡፡
12.15 በአክስዮን ማህበሩ ከተቀጠረ በኋላ ከአክስዮን ማህበሩ ሣይለቅ በሌላ መ/ቤት ቋሚ ሠራተኛ ሆኖ ማገልገል አይችልም፡፡
12.16 በሥራ ሰዓትም ሆነ በሥራ ሰዓት መካከል በሚሰጥ የእረፍት ጊዜ በአክስዮን ማህበሩ ንብረት ለውጭ ሰው ወይም ለራሱ የግል ሥራ መሥራት አይችልም፡፡
12.17 አክስዮን ማህበሩና ማህበሩ ካልፈቀዱ በስተቀር በሥራ ቦታና በሥራ ጊዜ ወይም በማናቸውም ጊዜ በአክስዩን ማህበሩ ውስጥ ልዩ ልዩ እትሞች፣ ጽሁፎችና የማስፈረሚያ ሊስት የመሣሰሉትን የማደል፣ የማስፈረም፣ የመፈረም፣ የመለጠፍ ወይም ማዞር የተከለከለ ነው፡፡ ሆኖም ግን በሠራተኛ ማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የሆርሻ ተወካዬች የሠራተኛ ማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ እንዲጠራቸው የምክር ቤቱን አባላት የማስፈረምና የመፈረም መብታቸው እንደተጠበቀ ነው፡፡
12.18 አክስዮን ማህበሩ አውቆ ከፈቀደው ወይም በዚህ ህብረት ስምምነት ከተደነገገው ውጭ በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ስብሰባ ማድረግ አይፈቀድም፡፡
12.19 ከአክስዮን ማህበሩ ሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ጉቦ፣ መደለያ፣ ኮሚሽንና የመሣሰሉትን መደራደሪያዎች መቀበል የለበትም፡፡
12.20 ወደ አክስዮን ማህበሩ ድምጽ ያለውንም ሆነ ድምጽ የሌለውን ወይም ተቀጣጣይ መሣሪያ ይዞ መግባት የለበትም፡፡
12.21 ሠራተኛው የሚሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ መጠቀም ግዴታ አለበት፡፡ የሌላ ድርጅት አርማ ያለውእና የተቀደደና ደረጃውን ያልጠበቀ የሥራ ልብስ መልበስ የተከለከለ ነው፡፡
12.22 ለሥራው መቃናት ሲባል አንድ ሠራተኛ ደረጃውና ጥቅሙ ተጠብቆ ከሚሠራበት ቦታ ወይም ክፍል ወይም ፈረቃ እንዲዛወር ሲጠየቅ በቅድሚያ በፈቃደኝነት በመፈፀም፤ ቅሬታ ሲኖረው በተዛወረበት ወይም በተመደበበት የሥራ ቦታ በሥነ ሥርዓት እየሠራ የመጠየቅ ግዴታ አለበት፡፡ዝውውሩ ከዋና መ/ቤት ወደ ቅ/መ/ቤት ወይም ከቅ/መ/ቤት ወደ ዋናው መ/ቤት ከሆነ ዝውውሩ ከመፈፀሙ በፊት ለዝግጅት የሚሆን 1 ወር ጊዜ ይሰጠዋል፡፡
12.23 ማንኛውም ሠራተኛ በማንኛውም ዓይነት ፈቃድ ወይም በማንኛውም ሕጋዊ በሆነ ምክንያት ከመደበኛ ሥራው ላይ የሚቀር ከሆነ ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር በቅድሚያ ለአሠሪው አሣውቆ እንደ ሥራው ፀባይ በእጁ የሚገኘውን ዕቃና በጅምር ላይ ያለውን ሥራ ሁሉ ለቅርብ ኃላፊው የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
12.24 ማንኛውም ሠራተኛ የአክስዮን ማህበሩ የአሠራር ሚስጢር ወይም ሌሎች መረጃዎችን አሣልፎ ለግል ጥቅም ማግኛ ወይም ለሌላ ሦስተኛ ወገን ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት የአክስዮን ማህበሩ ጥቅም የሚነካ ማንኛውንም ተግባር መፈጸም የለበትም፡፡
12.25 ማንኛውም ሠራተኛ የአክስዮን ማህበሩም ሆነ የማህበሩ ንብረት ሲባክን ሲያይ ወይም ሲያውቅ ጉዳዩን ለሚመለከተው ክፍል ወዲያውኑ የማሣወቅ ግዴታ አለበት፡፡
12.26 ማንኛውም ሠራተኛ ወደ አክስዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ሲገባና ከአክስዮን ማህበሩም ሲወጣ እራሱና የያዘው ተሽከርካሪ መፈተሽ አለበት፡፡
12.27 ማንኛውም የጥበቃ ሠራተኛ ቀንም ሆነ ሌሊት በተመደበበት ቦታና ሰዓት በንቃት መገኘት አለበት፡፡
12.28 ማንኛውም ሠራተኛ የማይገባውን ጥቅም በስህተት ከተቀበለ የመመለስና የማሣወቅ ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 13 የሥራ ውል አመሠራረት ፤የሠራተኛቅጥር ፤ምደባ ፤ ሥልጠና ፤ግምገማ፤ዕድገትና ዝውውር
13.1 ጠቅላላ
13.1.1 አክስዮን ማህበሩ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011ሕግን ተከትሎ በሚወጣ የአክስዮን ማህበሩ መመሪያና በዚህ ሕብረት ስምምነት መሠረት ሠራተኛን መቅጠር፣ ማሣደግ፣ ለሥራ ብቃት ያለው ነው ብሎ ያመነበትን ሠራተኛ አወዳድሮ ለመመደብ ወይም አዛውሮ ለማሠራት ይችላል፡፡
13.1.2 በአዋጅና ሌሎች መመሪያዎች የተሰጡትን ግዴታዎችና ሕግን ተከትሎ አክስዮን ማህበሩየሚያወጣቸውን መመዘኛ /መዋቅር/ የሚያሟላና ኢትዮጵያዊ ሆኖ ከተገኘ በሃይማኖት፣ በፆታ፣ በብሔር፣ በፖለቲካ ልዩነት ሣይደረግበት በአክስዮን ማህበሩ በሚፈጠሩ ክፍት ቦታዎች ይወዳደራል፡፡
13.1.3 ለአክስዮን ማህበሩ መስፋፋት ወይም የምርት ዕድገት የተለየ ሙያን የሚጠይቅ ተጨማሪ የሰው ኃይል አስፈላጊ ሲሆን፣ አዲስ የሥራ ቦታ መፈጠሩን ወይም በተለያዩ የሥራ ቦታዎች ሠራተኛ መመደብ አስፈላጊ መሆኑን ሕግን ወይም ህብረት ስምምነትን ተከትሎ የሚወስነው አሠሪው ነው፡፡ አክስዮን ማህበሩ እንደ ሥራው ፀባይና እንደ ሥራው ብዛት ወይም አመቺነት ሠራተኛን ላልተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ሥራ ሊቀጥር ይችላል፡፡
13.1.4 በጥናት ላይ ተመስርቶ መዋቅሩንና ህብረት ሥምምነቱን በማገናዘብበተለቀቀም ሆነ አዲስ በተፈጠረ የሥራ መደብ የሚፈለገውን የትምህርት ደረጃና የሙያ ዓይነት፣ ደመወዝ፣ እንዲሁም ተፈላጊውን የሥራ ልምድ የሚወስነው አክስዮን ማህበሩ ነው፡፡
13.1.5 ለሥራው ብቁ መሆኑ ለታመነበት ሠራተኛ የቅጥር ደብዳቤው ከመሰጠቱ በፊት ተቀጣሪው ሠራተኛ አክስዮን ማህበሩ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች በቅድሚያ የማሟላት ግዴታ አለበት፡፡
13.1.6 አክስዮን ማህበሩ የመንግሥት ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ አዲስ ሠራተኛ ሲቀጥር ወይም ከውስጥ ሠራተኛ በንብረት ወይም በገንዘብ ነክ በሆነ ሥራ ላይ በዝውውር /እድገት/ ሲመድብ ዋስ እንዲያቀርብ ይደረጋል፡፡
13.1.7 አዲስ ወይም ነባር ሠራተኛ ፋብሪካው በሚያወጣው ዕቅድ መሠረት ማንኛውም የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥልጠና በአክስዮን ማህበሩ በነፃ ይሰጠዋል፡፡
13.2 የሠራተኛ አቀጣጠር ሥርዓት
ሠራተኛ ሊቀጠር የሚችለው ከዚህ በታች በተመለከቱት ምክንያቶች ነው፡፡
13.2.1 ለአክስዮን ማህበሩ መስፋፋት ወይም የምርት ዕድገት የተለዬ ሙያ የሚጠይቅ ተጨማሪ የሰው ኃይል አስፈላጊ መሆኑን አክስዮን ማህበሩ ሲወስን፣
13.2.2 አዲስ የሥራ መደብ ተፈጥሮ ወይም ነባር የሥራ ቦታ ተለቆ ወይም ተቀይሮ /ተዳልቦ/ በአክስዮን ማህበሩመዋቅር መሠረት ለቦታው የወጣውን መስፈርት የሚያሟላ ሠራተኛ ከአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች ውስጥ ሲታጣ፣
13.2.3 ለተወሰነ ሥራ ወይም ለተወሰነ ጊዜ መመሪያን በመከተል ሠራተኛ የሚቀጠርበት ሁኔታ ሲያጋጥም፣
13.2.4 በሕጉ መሠረት የውጭ ሀገር ዜጋ መቅጠር ሲያስፈልግ፣
13.3 የሥራ ውል አመሠራረት
13.3.1 ማንኛውም የሥራ ውል የሥራውን ዓይነት፣ ቦታ፣ ለሥራው የሚከፈለውን ደመወዝ መጠን፣ የስሌት ዘዴን፣ የአከፋፈሉን ሁኔታና ጊዜ፣ የሙከራ ጊዜና የሥራ አፈጻጸም መለኪያ ግብና ውሉ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ መያዝ ይኖርበታል፡፡
13.3.2 የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ፣ መንግሥት በየጊዜው የሚያወጣቸው መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ህብረት ስምምነት ከሥራ ውል እንደ አንዱ ክፍል የሚቆጠሩ ይሆናሉ፡፡
13.3.3 ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ ሠራተኛ የሚቀጠረው በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 1ዐ መሠረት ነው፡፡
13.4 የሙከራ ጊዜ ቅጥር
13.4.1 የማንኛውም የቋሚ ሥራ ተቀጣሪ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜ ከ60የሥራቀናት መብለጥ የለበትም ይህም ለሠራተኛው በጽሁፍ ይገለፃል፡፡
13.4.2 በሙከራ ጊዜ ላይ ያለ ሠራተኛ ለሥራው ብቁ ካልሆነ አክስዮን ማህበሩ ያለምንም ማስጠንቀቂያ፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣ የአገልግሎት ክፍያና ካሣ ሣይከፍል ሊያሰናብት ይችላል፡፡
13.4.3 ሠራተኛው በሙከራ ጊዜ መጨረሻ በአሠሪው አስተያየት ሥራው አጥጋቢ ከሆነ በውሉ መሠረት የተቀጠረ ለመሆኑ በጽሁፍ ይረጋገጣል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው የሙከራ ጊዜው ካለቀ በኋላ ሥራውን ከቀጠለ በውሉ መሠረት ለታቀደው ጊዜ ወይም ሥራ እንደተቀጠረ ይቆጠራል፡፡
13.4.4 በሙከራ ላይ ያለ ሠራተኛ ያለ ማስጠንቀቂያ ሥራውን ሊለቅ ይችላል
13.4.5 በሙከራ ላይ ያለ ሠራተኛ እንደ ሥራው ፀባይ የአደጋ መከላከያ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም የሙከራ ጊዜውን ከመጨረሱ በፊት ለቋሚ ሠራተኛ የሚሰጠውን ጥቅማ ጥቅም ሊያገኝ አይችልም፡፡
13.4.6 ቀድሞ የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች የነበሩ ሲሰሩበት ከነበረው የሥራ መደብ ላይ እንደገና ከተቀጠሩ የሙከራ ጊዜ አይኖራቸውም፡፡
13.4.7 የቀድሞ የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ የነበረ ሲሠራበት ከነበረው የሥራ መደብ ተመሣሣይና ተመጣጣኝ የሥራ ቦታ ላይ ወይም ደግሞ አክስዮን ማህበሩ የሠራተኛውን የቀድሞ ብቃትና በሌላ መሥሪያ ቤት ሲሰራባቸው የነበሩ የሥራ መደቦች በቂ መሆናቸውን ሲያምንበት ተመጣጣኝ የሥራ መደብ ባይሆንም እንደገና ከተቀጠረ የሙከራ ጊዜ አይኖረውም፡፡
13.5 ሥልጠና
13.5.1 አሠሪው ሠራተኛው እውቀቱን አሻሽሎ የተመደበበትን ሥራ በብቃት እንዲወጣ ከቅጥር በፊት ሥራውን ከሠራተኛ ጋር ለማስተዋወቅ የሙከራ ጊዜያቸውን የጨረሱ ሠራተኞች ያላቸውን ዕውቀት አሻሽለው የተመደቡበትን ሥራ በብቃት እንዲወጡ ወይም በዕድገትና በዝውውር ምክንያት በተጨማሪ ኃላፊነትና የሥራ ብቃት ዝግጁ እንዲሆኑ በአክስዮን ማህበሩ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አስፈላጊነቱን አክስዮን ማህበሩ ሲያምንበት አቅም በፈቀደ መጠን ሥልጠና በነፃ ይሰጣል፡፡
13.5.2 በማሠልጠኛ ኮርስ የተካፈሉ ሠራተኞች ኮርሱን ከፈፀሙ በኋላ የተከታተሉትን የትምህርት ዓይነት፣ ያገኙትን ዕውቀትና የሰለጠኑበትን ሙያ የሚያስረዳ ከአሠልጣኙ ድርጅት የተሰጣቸው ሠርቲፊኬት ወይም በድርጅቱ ለመሰልጠናቸው የሥልጠና ክፍሉ የሚሰጣቸውን መረጃ ለሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ አቅርበው በማህደራቸው እንዲያዝ ያደርጋሉ፡፡
13.5.3 በማንኛውም ሁኔታ በሥልጠና ላይ የቆየ ሠራተኛ የሥልጠና ሪፖርት እንዲሁም የሰለጠነበትን የሥልጠና ማኑዋል ኮፒዎች ለሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ መስጠትና የሰለጠነውን ሥልጠና ለሌሎች እንዲያሰለጥን ሲጠየቅ ተዘጋጅቶ ሥልጠና ይሰጣል፡፡
13.5.4 የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች ዕውቀታቸውን በትምህርት እንዲያሻሽሉ ያነቃቃል፡፡ ሆኖም የሠራተኛው የትምህርት ጊዜ ከመደበኛው የአክስዮን ማህበሩ የሥራ ሰዓት ጋር በማይጋጭ መልኩ አክስዮን ማህበሩ ተቀያይረው የሚማሩትን ሠራተኞች ያበረታታል፡፡
13.5.5 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ተጨማሪ ትምህርት ለመማር የሚፈልግ ሠራተኛ አክስዮን ማህበሩ ትምህርቱ ከሥራው ጋር ግንኙነት ያለው ሙያ መሆኑን ከሥራው ባህሪና ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ጋር የማይጋጭ እንዲሁም አክስዮን ማህበሩ እንዲማሩ በዕቅድ ከያዘው ኮታ በላይ እንዳልሆነና በሥልጠና መመሪያው መሠረት ውለታ መፈፀሙን አረጋግጦ ሠራተኛው እንዲማር የትምህርት ቤቱን ስም በቅድሚያ ጠቅሶ በጽሁፍ ሲፈቀድ ብቻ ትምህርት መማር ይችላል፡፡
በዚህ ሁኔታ እንዲማር የተፈቀደለት ሠራተኛ የትምህርት ወጭው መቶ በመቶ /1ዐዐ%/ ይከፈልለታል፡፡ በገንዘብ እጥረት ምክንያት መማር እየፈለጉ መማር የማይችሉ ሠራተኞችን ለማበረታታት እንዲማር ከተፈቀደለት/ላት/ የትምህርት ቤት ክፍያዉን አክስዮን ማህበሩ በቅድሚያ ከፍሎለት/ላት/ እንዲማር /እንድትማር/ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን በዚህ መሠረት ሲከፈልለት የነበረው ተማሪ /ሠራተኛ/ ትምህርቱን ቢያቋርጥ ወይም ቢወድቅ የተከፈለለትን ክፍያ ከደመወዙ በየወሩ 1/3ኛ እየተቆረጠ ለድርጅቱ ይከፍላል፡፡ ዲግሪና ከዲግሪ በላይ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሚማር ተማሪአክስዮን ማህበሩ የትምህርት ወጪውን 10ዐ% ይከፍልለታል፡፡
13.5.6 በአክስዮን ማህበሩ የሥልጠና መመሪያ መሠረት ማንኛውንም ሠልጣኝ ከሰለጠነ በኋላ አክስዮን ማህበሩን እንዲያገለግል ግዴታ ያስገባዋል፡፡
13.5.7 ሠልጣኙ ከተላከበት ወይም ከተፈቀደለት የሥልጠና ዓይነት ውጭ ቢሰለጥን አክስዮን ማህበሩ የሥልጠና ወጪውን አይከፈልም፤ አስቀድሞ የተከፈለለት/ላት/ ከሆነም ሠራተኛው ወጪውን እንዲከፍል ይደረጋል፡፡
13.6 የሥራ አፈጻጸም ምዘና
13.6.1 የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሠራተኛው ያለው አእምሮአዊ እና አካላዊ
ችሎታውን በመጠቀም በአክስዮን ማህበሩ ስትራቴጅክ ዕቅድ ውስጥ የተቀመጡትን ዓላማና ግቦች ለማሣካት የተሰጡትን ተግባራት ማከናወኑን በተቀናጀ ሁኔታለመመዘን የሚረዳ የምዘና ሥርዓት ነው፡፡
13.6.2 የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት በአክስዮን ማህበሩ መመሪያ መሠረት ይሞላል፡፡
13.6.3 የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት በሠራተኛው የቅርብ የሥራ ኃላፊ በሁለት ቅጅ ተሞልቶ በየደረጃው ባሉት የሥራ ኃላፊዎች ከፀደቀ በኋላ አንዱ ቅጅ ለሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ይላካል፡፡ ሁለተኛው ኮፒ ሠራተኛው በሚሠራበት መምሪያ ወይም ክፍል ፋይል ይደረጋል፡፡
13.6.4 የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት በዓመት ሁለት ጊዜ ሆኖ የመጀመሪያው
ከጥር 1 - ሰኔ 3ዐእና ሁለተኛው ከሐምሌ 1 - ታህሣስ 3ዐድረስ ይሞላል፡፡ ሆኖም ግን የምዘና ሪፖርት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለሰ/ኃ/ል/አ/መምሪያ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
13.6.5 የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት የሚሞላ ኃላፊ በተጨባጭ ሁኔታዎችለመመዘንና የእያንዳንዱን ተመዛኝ ደካማና ጠንካራ ጎኖች በየጊዜው በመመዝገብ የመያዝና የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርቱን በጥንቃቄና በትክክል የመሙላት ኃላፊነት አለበት፡፡ ገምጋሚው ሲጠየቅ ማረጋገጫ የማቅረብና የማስረዳት ኃላፊነት አለበት፡፡
13.6.6 የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት ከመሞላቱ በፊት የክፍል ኃላፊዎችሠራተኛው የሚታይበትን ድክመት እንዲያርም የማስረዳት ኃላፊነት አለባቸው፡፡
13.6.7 አንድ ሠራተኛ ያገኘውን የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት እንዲያውቀውና እንዲፈርምበት ይደረጋል፡፡ ሠራተኛው በወቅቱ ቅሬታ ካለው ቅሬታውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላል፡፡ የበላይ ኃላፊው በቀረበው የቅሬታ ጽሁፍ ላይ አስተያየቱን ሰጥቶበትና ለሠራተኛው ተገልጾለት ተገምጋሚው በተሰጠው መልስ የማይረካ ከሆነ የሥራ አፈጻጸሙን ምዘና በክፍሉ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወይም በአገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ያልረካ ከሆነ ለሰው ኃ/ል/አ/መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ያቀርባል፡፡ አሁንም በመልሱ ካልረካ ለዋና ሥራ አስኪያጅ ማቅረብ ይችላል፡፡
13.7 የደረጃ እድገት
13.7.1 ደረጃ እድገት ማለት ከዝቅተኛ የሥራ መደብ ወደ ከፍተኛ የሥራ መደብ የሚደረግ ምደባ ነው፡፡
13.7.2 የደረጃ እድገት የሚሰጠው ነባር ሠራተኛ በተለያዩ ምክንያቶች የሥራ መደቡን ሲለቅና የአክስዮን ማህበሩ ሥራ በመስፋፋቱ ምክንያት የሚፈጠሩትን ክፍት የሥራ መደቦች ለሥራ መደቡ የወጣውን መመዘኛ በሚያሟሉ ሠራተኞች እንዲሟላ አክስዮን ማህበሩ ሲፈቅድ ነው፡፡
13.7.3 የሥራ መደቡ የሚጠይቀውን የትምህርት ደረጃና መመዘኛ የሚያሟሉ ሠራተኞች ተወዳድረው የሥራ መደቦቹን እንዲሸፍኑ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ ከውጭ ሠራተኛ ከመቀጠሩ በፊት ይህንን የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ገንዘብ ያዥ፣ ሽያጭ ሠራተኛ፣ ኦዲት፣ ንብረትና ከንብረት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቁልፍ የሥራ መደቦች፣ እንዲሁም ከመረጃና ከአክስዮን ማህበሩ ገጽታ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሥራ መደቦች ዋና ሥራ አስኪያጅ በመስፈርቶች አወዳድሮ ይመድባል፡፡በቂ ዋስትና እንዲያቀርቡም ያደርጋል፡፡
13.7.4 በእድገት እንዲሟላ የተፈቀደው ክፍት የሥራ መደብ የተፈጠረበትን ምክንያት በሕብረት ስምምነቱና በመዋቅሩ መሠረት ለቦታው የሚያስፈልገውን የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድና ሌሎች ተፈላጊ ማስረጃዎች መሟላታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት የአክስዮን ማህበሩ ነው፡፡ ሆኖም ግን እድገት ኮሚቴው ፈተና ከመሰጠቱ በፊት ለመስፈርቱ የተሰጡትን ውጤቶች ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል፡፡
13.7.5 በእድገት እንዲሟላ የተጠየቀ ክፍት የሥራ መደብ የአክስዮን ማህበሩ መዋቅር እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያስፈልገውን የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ያሟሉ ሠራተኞች እንዲወዳደሩ አሠሪው ማስታወቂያ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ የአክስዮን ማህበሩመዋቅር እንደተጠበቀ ሆኖ በጥናት ላይ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟላ ሠራተኛ ሲታጣ አክስዮን ማህበሩ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርትና የአገልግሎት ማካካሻ ዝርዝር መሠረት ሠራተኞችን ያወዳድራል፡፡
የአገልግሎት የትምህርት ደረጃ ማካካሻ ዝርዝር
ተ.ቁ | የትምህርት ደረጃ | ማካካሻ | ስሌት |
1 | ከ3ኛ - 7ኛ ክፍል ድረስ | 8ኛ ክፍል ድረስ ይወዳደራል | 3ኛ-10ዓመት፣4ኛ-8 ዓመት፣5ኛ-6 ዓመት፣6ኛ-4 ዓመት፣7ኛ- 2 ዓመት የሥራ ልምድ |
2 | ከ8ኛ - 9ኛ ክፍል ድረስ | 10ኛ ክፍል ድረስ ይወዳደራል | 8ኛ-4ዓመት፣9ኛ-2 ዓመት የሥራ ልምድ፣ |
3 | ከ1ዐኛ - 11ኛ ክፍል ድረስ | 12ኛ ክፍል ድረስ ይወዳደራል | 10ኛ-4ዓመት፣11ኛ-2ዓመት የሥራ ልምድ፣ |
4 | 12ኛ ነባሩ ወይም 1ዐኛ አዲሱ | ኮምኘሬሄንሲቭ ሠርቲፊኬት /ሌብል 1/ ድረስ ይወዳደራል | 2ዓመት የሥራ ልምድ፣ |
5 | ኮምኘሬሄንሲቭ ሠርቲፊኬት /ሌብል 1/ | ኮምኘሪሄንሲቭ ዲኘሎማ ወይም ቴክኒክና ሙያ ተግባረ ዕድ /ሌብል 2/ ድረስ ይወዳደራል፡፡ | 2ዓመት የሥራ ልምድ፣ |
6 | ኮምኘሪሄንሲቭ ዲኘሎማ /ቴክኒክና ሙያ ተግባረ ዕድ/ /ሌብል 2/ | ሌብል 3 ድረስ ይወዳደራል፡፡ | 2ዓመት የሥራ ልምድ፣ |
7 | ሌብል 3 | ኮሌጅ አድቫንስ ዲፕሎማ ድረስ ይወዳደራል፡፡ | 2ዓመት የሥራ ልምድ፣ |
8 | ኮሌጅ አድቫንስ ዲፕሎማ | ዲግሪ ድረስ ይወዳደራል | 2ዓመት የሥራ ልምድ፣ |
9 | ዲግሪ | ማስተር ድረስ ይወዳደራል፡፡ | 2ዓመት የሥራ ልምድ፣ |
ሆኖም በመዋቅሩ መሠረት የሚጠየቀውን የትምህርት ደረጃ አሟልተው ከምረቃ በኋላ በቂ የሥራ ልምድ የሌላቸው ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት ውድድርን በተመለከተ አክስዮን ማህበሩ መመሪያ በማውጣት ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
ማስታወሻ
ሀ/ ከላይ ከ1 – 9 ለተጠቀሱት ማካካሻዎች አግባብነት ያለው ሁለት ዓመትየሥራ ልምድ እንደ አንድ ዓመት የትምህርት ማካካሻ ይታሰባል፡፡
ለ/ መሠረተ ትምህርት ወረቀት ኖሯቸው ማንበብና መጻፍ የሚችሉ እንደ 3ተኛ ክፍል ተቆጥረው እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ይወዳደራሉ፡፡ ሆኖም ግን 10 ዓመትና ከዚያ በላይ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
ሐ/ በዚህ ዓይነት የሚካካስላቸው ሠራተኞች ለውድድር የሚቀርቡት የሦስት ዓመት የሥራ አፈጻጸም አማካይ ነጥባቸው 80 ወይም ከዚያ በላይ ሲሆንና የክፍላቸው ድጋፍ ሲኖራቸው ነው፡፡
13.7.6 አክስዮንማህበሩ ለዕድገት የቀረበ ተወደዳሪ ወይም የቀረቡ ተወዳዳሪዎችን የትምህርት መረጃ፣ የሥራ ልምድ፣ የሥራ አፈጻጸም ምዘና፣ በሥራው ያላቸውን ፍላጎትና ዝንባሌ፣ የማሰብ የማመዛዘን ችሎታውን ለመገምገምና ለሚወዳደርበት ቦታ ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የጽሁፍ፣ የቃልና የተግባር ፈተና እንደ ሥራው ፀባይ በአንድ ወይም በሁለት ወይም በሦስቱም ፈተናዎች ሊወሰን ይችላል፡፡
13.7.7 እያንዳንዱ እጩ ተወዳዳሪ ለፈተና ለመቅረብ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተገምግሞ ውጤቱ አጥጋቢና ከዚያ በላይ ሆኖ ለመጨረሻ ውድድር ለመቅረብ ግን አገልግሎት ሰጪ ከሆነ በጽሁፍና በቃል ፈተና፣ ለቴክኒክና ጥገና በጽሁፍና በተግባር ፈተና ግማሽና ከግማሽ በላይ ውጤት ማግኘት ይኖርበታል፡፡
13.7.8 የሠራተኛ ቅጥርና ዕድገት በዚህ ሕብረት ስምምነት ውስጥ በተዋቀረው የቅጥርና ዕድገት ኮሚቴ መሠረት ይፈፀማል፡፡
13.7.9 ሠራተኛ ማህበሩ ለሠራተኛ ቅጥርና ዕድገት በኮሚቴ አባልነት በመሣተፍ የውሣኔ ሃሣብ ያቀርባል፡፡
13.7.10 የቅጥርና ዕድገት ኮሚቴው የውሣኔ ሃሣብ ተፈጻሚነት የሚኖረው በዋና ሥራ አስኪያጅ ወይም እርሱ በሚወክለው ኃላፊ ሲፀድቅ ብቻ ነው፡፡
13.7.11 የማኔጅመንት አካል ለሆኑ የሥራ መደቦች ላይ አክስዮን ማህበሩ ብቃት አለው ብሎ ያመነበትን መመደብ ይችላል፡፡
13.7.12 አክስዮን ማህበሩ የሠራተኛ ቅጥርና ዕድገት ማስታወቂያ ሲወጣ የሠራተኛ ማህበሩ በኮፒ እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
13.7.13 አንቀጽ 7.2 እንደተጠበቀ ሆኖ ለዕድገት ቦታ ውድድር በሚደረግበት ጊዜ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ተወዳዳሪዎች ውጤታቸው እኩል ከሆነ፣ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች ቅደም ተከተል ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
1.አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ፣
2. አገልግሎት ዘመን
3. የሥራ አፈጻጸም ብልጫ ያለው ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ግን በመጀመሪያው ብልጫ ያለው ተወዳዳሪ ካሸነፈ ወደሚቀጥሉት መስፈርቶች መሄድ አይጠበቅበትም፡፡
13.7.14 አንድ ሠራተኛ በዕድገት በተመደበበት የሥራ መደብ ላይ ቢያንስ 12 ወራት ሣያገለግል በሌላ አዲስ ዕድገት ሊወዳደር አይችልም፡፡ አዲስ ተቀጣሪም እንዲሁ 12 ወራት ሣያገለግል በዕድገት አይመደብም፡፡ ሆኖም ተወዳዳሪ ሣይቀርብ ወይም ተወዳዳሪዎቹ በሙሉ በተለያዬ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ከሆኑ ወይም ከወደቁ የተጠቀሰው ጊዜ ሣይጠበቅ ከክፍላቸው ድጋፍ የቀረበላቸው ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤታቸው 75% እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ለውድድር እንዲቀርቡ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ከታጣ አክስዮን ማህበሩበተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶአስፈላጊውን /ተገቢውን/ ሊፈጽም ይችላል፡፡ አዲስ ተቀጥሮ አንድ ዓመት ያልሞላው ሠራተኛ ከሆነ ለዋና ሥራ አስኪያጅ ቀርቦ መመሪያ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡
13.7.15 አክስዮን ማህበሩ ለውድድር ያወጣው የቅጥርም ሆነ የዕድገት ማስታወቂያ ስህተት መሆኑ ሲደረስበት በማናቸውም ወቅት ማስታወቂያውን የመሠረዝ መብት አለው፡፡
13.7.16 በማስታወቂያው መሠረት የተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ከ15 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለውድድር ወይም ለፈተና መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
13.7.17 ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር መመዘኛውን አሟልተው የተፈተኑ እጩ ተወዳዳሪዎች የፈተና ውጤቱን ከ15 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
የእድገትና ቅጥር ኮሚቴ አወቃቀር
13.7.18 የዕድገት ኮሚቴ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡፡
1. የሰው ኃ/ል/ አስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ /ተወካይ/ ሰብሣቢ
2. ዕድገት፣ ቅጥር የሚደረግለት መምሪያ ሥ/አስኪያጅ /ተወካይ/ አባል
3. በዋና ሥራ አስኪያጅ የሚወከል ኃላፊ /ተወካይ/ ………… ፡
4. የሠራተኛ አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ /ተወካይ/ ………… ፡
5. የሠራተኛ ማህበር ተወካይ ……………………………….. ፡
6. በአክስዮን ማህበሩ የሚመደብ /ድምጽ የማይሰጥ/ ………… ፀሐፊ
13.7.19 የደረጃ ዕድገት መወዳደሪያ ነጥቦች አሠጣጥ የሚከተለውን ይመስላል፡፡
1/ የጽሁፍ፣ የቃልና ተግባር ፈተና …………………… 35%
2/ የትምህርት ዝግጅት ……………………………….. 10%
3/ ለሥራ ልምድ ……………………………………… 15%
4/ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ……………………………. 15%
5/ ለአገልግሎት ዘመን ………………………………… 15%
6/ ለማህደር ጥራት …………………………………… 10%
ድምር 100%
ለሥራ ልምድ የተያዘው 15% በቀጥታ አግባብነት ላለው የሥራ ልምድና በተዘዋዋሪ አግባብነት ላለው የሥራ ልምድ ብቻ ሲሆን፣ ለአገልግሎት ዘመን 15% በሥራ ልምድ ከተያዙት ውጪ ያሉትን የሥራ ዘመናት ብቻ ነው፡፡
ነጥብ አሰጣጥ
ሀ/ የጽሁፍ ወይም የተግባር ፈተና
1. የጽሁፍ፣ የቃል ወይም የተግባር ፈተና እንደአሰፈላጊነቱ በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ ወይም ከአክስዮን ማህበሩ ውጭ ይሰጣል፡፡
2. ክፍት የሥራ መደቡ ጥገናና ቴክኒክ ከሆነ ለተግባር ፈተና 25% ለጽሁፍ 1ዐ% ይሰጣል፡፡
3. ክፍት የሥራ መደቡ የአገልግሎት ሰጪ ከሆነ ለጽሁፍ ፈተና 25% ሲሰጥ ለቃል ፈተናው 1ዐ% ይሰጠዋል፡፡
ሀ.1 ስለ ፈተና አሰጣጥ
1. የተግባርና የጽሁፍ ፈተና ዕድገት ኮሚቴው በሚመርጣቸው የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጥያቄ እንዲያወጡ ተደርጎ ፈተና ይሰጣል በእለቱም ታርሞ ይጠናቀቃል፡፡
2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ከሚሰጡት ፈተናዎች አንዱን ያለበቂ ምክንያት ካልወሰደ ለዚያ ፈተና ውጤት ዜሮ እንዳገኘ ይቆጠራል፡፡ሆኖም ግን ፈተናውን ያልወሰደበት
ምክንያት በቂ ሆኖ ከተገኘ በፈተና ኮሚቴው ይወሰናል፡፡
3. የተሰጠው ፈተና ውጤት የሚታረመው የዕድገት ኮሚቴ ወይም ተወካዬች ባሉበት ይሆናል፡፡
4. ፈተና በተሰጠ ከሁለት ሣምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ኮሚቴው የውሣኔ አስተያየቱን ለሰው ኃ/ል/አ/መምሪያ ወይም ለዋና ሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ይፀድቃል፡፡
ሀ.2 ከአክስዮን ማህበሩ ውጪ የሚሰጥ ፈተና
1/ ለተወሰኑ የሙያ መስኮች ለመፈተን ፈቃድ በተሰጣቸው ተቋማት ወይም ማዕከል ይሆናል፡፡
2/ የፈተናው ውጤት ከ35% ይያዛል፡፡
3/ የጽሁፍ፣ የቃልና የተግባር ፈተና ተፈትኖ ግማሽና ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጣ ወይም ያመጡ ተወደዳሪዎች ለቀጣይ ውድድር ወደ ማህደር ይገባሉ፡፡
4/ ለሹፌር የሥራ መደብ በውጭ ፈተና እንዲሰጥ አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጠር የማለፊያና የመውደቂያ ነጥብ በመንገድ ትራንስፖርት ሕግ መሠረት 75% ያመጣ ተወዳዳሪ በሕብረት ስምምነታችን መሠረት 17.5/35 እንዳመጣ ተቆጥሮ ለተጨማሪ ውድድር ወደ ማህደር እንዲገባ ይደረጋል፡፡ ከውጭ ለሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ግን 75 እና ከዚያ በላይ ከመቶው ካመጡ ብቻ ነው የሚያልፉት፡፡
ለ/ ለትምህርት ዝግጅት ማስረጃ 10%
1. ለሥራ መደቡ የተጠየቁትን የትምህርት ዝግጅትያሟላ ተወዳዳሪ 8% ተሰጥቶት ብልጫ ለሚኖራቸው ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዱ መደበኛ የሥራ ልምድ 0.5 ነጥብ ይሰጠዋል /ይሰጣቸዋል/፡፡ ሆኖም ግን ከ2 ነጥብ መብለጥ የለበትም፡፡ ከተጠየቁት መስፈርቶች በላይ የሚቀርብ የትምህርት ዝግጅት ከላይ የተጠቀሰው ተጨማሪ ነጥብ አይሰጠውም፡፡
2. የትምህርት ዘመኑን ሙሉ ጊዜ ተከታትሎ ካላለፈ የተጠቀሰውን የትምህርት ደረጃ እንዳጠናቀቀ አይቆጠርም፡፡
ሐ/ የሥራ ልምድ 15%
በመሠረተ ሃሣቡ ሠራተኛው በሚወዳደርበት ቦታ ወይም ተመሣሣይ ሥራ ለመለማመድ ከመቆየቱና ከመሥራቱ የተነሣ የሚገኘው የአሠራር ልምድና ዘዴ ለሥራው ቅልጥፍና ይረዳል የሚል ግምት ስላለና ሥራውን ተረክቦ ለመሥራት የሚያስችል ችሎታ አለው በሚል ሲሆን፣ የሥራ ልምድ ቀጥታ አግባብነት ያለውና በተዘዋዋሪ አግባብነት ያለው በሚል ይከፈላሉ፡፡
1/ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ማለት በቀጥታ ከሚመለከተው ሥራ ጋር ግንኙነት ያለው ማለት ነው፡፡
2/ በተዘዋዋሪ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ማለት ከሥራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ሣይኖረው በተዘዋዋሪ የሚመሳሰል ማለት ነው፡፡
3/ አክስዮን ማህበሩ በእያንዳንዱ የሥራ መደብ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ የሥራ ልምድን የሚገልጽ ዝርዝር ከአክስዮን ማህበሩ የሰው ኃይል መዋቅር ጋር ተያይዞ እንዲቀመጥ ይደረጋል፤ ቅጁንም ለመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ይሰጣል፡፡
4/ ከላይ ከተ/ቁ 1-3 ለተገለጹት የነጥብ አሰጣጥ ከታች በተገለፀው መልኩ
ይሆናል፡፡
4.1 ቀጥታ አግባብነት ላለው የሥራ ልምድ ለእያንዳንዱ ዓመት 1 ነጥብ ይሰጣል፡፡
4.2 ለተዘዋዋሪ አግባብነት ላለው የሥራ ልምድ ለእያንዳንዱ ዓመት 0.75 ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን አጠቃላይ ውጤቱ ከ15 አይበልጥም፡፡ በሥራ ልምድ ላይ ነጥብ ከተሰጠበት በላይ ያሉት የሥራ ዘመኖች ወደ አገልግሎት ተወስደው ነጥብ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
መ/የሥራ አፈጻፀም ምዘና15%
የሚያገኘው ነጥብ የሥራ አፈጻጸም የ3 ዓመት ምዘና አማካኝ x 15÷100= እንዲመዘገብለት ይደረጋል፡፡
ሠ/ የአገልግሎት ዘመን15%
ለአገልግሎት ዘመን የተመደበው ነጥብ የሚሰጠው ከተወዳዳሪዎች የግል ማህደር በሚገኘው ማስረጃ መሠረት ሲሆን፣ አገልግሎት በመንግሥት መ/ቤት ወይም በመንግሥት ድርጅቶችና ከ2ዐ በላይ ሠራተኞችን ቀጥረው የሚያሰሩ የግል ድርጅቶችን ያጠቃልላል፡፡ የነጥብ አሰጣጡም ከሥራ ልምድ ነጥብ ያልተሰጠባቸው የአገልግሎት የሥራ ዘመኖች ለእያንዳንዱ የአገልግሎት ዘመን በ0.5 ተባዝቶ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን አጠቃላይ ከ1ዐ ነጥብ አይበልጥም፡፡
ረ/ የግል ማህደር ጥራት 10%
ነጥብ አሰጣጥ
1/ ምንም ቅጣት የሌለበትና ማህደሩ ንፁህ የሆነ 8 ነጥብ ይሰጠዋል፡፡
2/ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በማህደሩ ያለ ከሆነ 6 ነጥብ ይሰጠዋል፡፡
3/ የጽሁፍና የገንዘብ ቅጣት ካለበት 4 ነጥብ ይሰጠዋል፡፡
4/ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ካለበት 2 ነጥብ ይሰጠዋል፡፡
5/ ከሥራ ተሰናብቶ የተመለሰ ሠራተኛ 1 ነጥብ ይሰጠዋል፡፡
በማህደሩ ላይ የተለያየ የፈጠራ ሥራዎችን ሠርቶ የተገኘ ሠራተኛ ከላይ በተዘረዘሩት መሠረት ከሚያገኘው ነጥብ ላይ 2 ነጥብ ይደመርለታል፡፡ የፈጠራ ሥራ ሠርቶ የተሸለመ ሠራተኛ የዕድገትም ሆነ የዝውውር ውድድር ተወዳድሮ አሸናፊ ሆኖ እስከሚገኝ ድረስ እንዲጠቀምበት የሚደረግ ሲሆን፣ ዕድገት ወይም ዝውውር ካገኘ በኋላ ለ2ኛ ጊዜ ግልጋሎት ሊሰጠው አይችልም፡፡
13.8 ዝውውር
13.8.1 ዝውውር ማለት አንድ ሠራተኛ ከአንድ የሥራ መደብ፣ ክፍል፣ ፈረቃ ወይም ከዋናው መ/ቤት ወደ ቅርንጫፍ /ከቅርንጫፍ ወደ ዋናው መ/ቤት/ ሠራተኛው የያዘው ደመወዝና ደረጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ሌላ ተመሣሣይ የሥራ መደብናደረጃ፣ የሥራ ቦታ በማዛወር ሥራና ሠራተኛን በማገናኘት የአክስዮን ማህበሩን የሥራ ውጤት ለማሻሻል ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ የሚፈፀም ተግባር ነው፡፡
13.8.2 አክስዮን ማህበሩ ሠራተኛውን የሥራ ደረጃን ጠብቆ የሚያገኘውን ደመወዝ እንደያዘ አዛውሮ ሊያሠራው ይችላል፡፡
13.8.3 ሠራተኛው ከሥራ ጋር ባልተገናኘ ሕመም ምክንያት ሐኪም በውሉ ከተመለከተው የተለዬ ሥራ እንዲሠራ ሲያዝ አሠሪው ደመወዙን ሣይቀንስ ወደ ሌላ አመቺ የሥራ ቦታ ሊያዛውረው ይችላል፡፡
13.8.4 ከአንድ የሥራ መደብ ወደ ሌላ የሥራ መደብ የሚዛወር ሠራተኛ ከቀድሞ የሥራ መደብ የሚያገኘው ቀርቶ ለአዲሱ የሥራ መደብ የሚሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ ያገኛል፡፡
13.8.5 የዝውውር ውሣኔ ደርሶት ቅሬታ ያለው ሠራተኛ ቅሬታውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም አክስዮን ማህበሩ የሠራተኛውን የወደፊት እድገት ለማደናቀፍ በሚችል ሁኔታ ዝውውር እንዲፈፀም አያደርግም፡፡
13.8.6 ማንኛውም ዝውውር በአክስዮን ማህበሩ የሥልጣን ውክልና መሠረት ይፈፀማል፡፡
13.8.6.1 በአንድ መምሪያ ውስጥ የሚደረግ የሥራ ዝውውር እስከ ደረጃ 11 ድረስ በመምሪያው ሥራ አስኪያጅ ይፈፀማል፡፡ ሆኖም ግን የዝውውሩ ሂደት በሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መመሪያይፈፀማል፡፡
13.8.6.2 ዝውውሩ ከአንድ መምሪያ ወይም አገልግሎት ወደ ሌላ መምሪያ ወይም አገልግሎት ሲሆን፣ የመምሪያዎች ወይም የአገልግሎቶች አስተያየት እየተጠየቀ እስከ ደረጃ 11 ድረስ በሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ይፈፀማል፡፡
13.8.6.3 የሥራ መደቡ ደረጃ 12 እና በላይ ያለው ዝውውር በአክስዮን ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ይፈፀማል፡፡
አንቀጽ 14 ተወካይ ሠራተኛ ስለመመደብ እና ተተኪንስ ለማፍራት
ሀ/ ተወካይ ሠራተኛ ስለ መመደብ
14.1 ተወካይ ሠራተኛ የሚመደበው አንድ የሥራ መደብ ክፍት ሲሆንና ቋሚ ሠራተኛ እስኪመደብ ወይም አንድ ሠራተኛ ለተወሰነ ጊዜ በሥራ ጉዳይ፣ በሕመም፣ በዓመት እረፍትና በመሣሰሉት ምክንያት ከሥራ ገበታው ሲለይ ጊዜያዊ ሠራተኛ በቦታው መመደብ በማይቻልበት ወይም አስፈላጊ በማይሆንበት ጊዜ የሥራ መደቡን ለመሸፈን ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ከፍ ወዳለ የሥራ መደብ ነው፡፡
14.2 በተወካይነት የሚመደበው ሠራተኛ ለክፍት ቦታው ተመጣጣኝ ችሎታና የሥራ ልምድ ያለው መሆኑ መረጋገጥ አለበት፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሠራተኛ የማይገኝ ከሆነ ወይም ተወካይ ሠራተኛ መመደብ አስፈላጊ ካልሆነ የሥራ መደቡ የሚገኝበት ኃላፊ ሥራውን ደርቦ እንዲሠራ ይደረጋል፡፡
14.3 ተወካይ ሠራተኛ የሚመደበው የአክስዮን ማህበሩን ዋና ሥራ አስኪያጅ በቅድሚያ በማስፈቀድ ሲሆን፣ ለተወካዩ በደብዳቤ ይገለጽለታል፡፡
14.4 በተወካይነት ለተመደበ ሠራተኛ የውክልናአበል ክፍያ የደመወዙን 25% ይሆናል፡፡ ይሁንና የውክልና አበል ክፍያው ከብር 10ዐ0.00/አንድ ሺህ ብር/አይበልጥም፡፡
14.5 በተወካይነትተመድቦ ለሠራ ሠራተኛ ክፍያ የሚፈፀመው በተከታታይ ለ26 የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ መሥራቱ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ለአንድ የሥራ መደብ አንድን ሠራተኛ ከ6 ወር በላይ በተወካይነት አበል እየተከፈለ ማሠራት አይቻልም፡፡ ሆኖም ግን እንደአስፈላጊነቱ ታይቶ ለአክስዮን ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ይወሰናል፡፡
14.6 ተወካይሠራተኛ የራሱን ሥራ እየሠራ የሚተካበትን ሥራ ደርቦ የሚሠራ ሠራተኛ ነው፡፡ የበታች ሠራተኛን ሥራ ደርቦ የሚሠራ ሠራተኛ የተወካይነትአበል አይከፈለውም፡፡
14.7 የተወካይነት አበል የሚከፈላቸው የሥራ መደቦች ላይ ተወክሎ የሚሠራ ማንኛውም ሠራተኛ የተወካይነትአበል የማግኘት መብት አለው፡፡
14.8 የተወካይነት አበል የሚከፈልባቸው የሥራ መደቦች በአባሪ 1/አንድ/ተያይዘዋል፡፡
ለ/ ተኪን ስለማፍራት
14.9 ተኪ ማለት አስቀድሞ በቁልፍ የሥራ መደብ ተይዞ ከውስጥ ሠራተኞች በመመልመል በሥራ መደቡ ላይ የተመደበው ሠራተኛ በሥራው ላይ እያለ የሚደረግ ሠራተኞችን የማብቃት ሥራ ነው፡፡ ይህም አክስዮን ማህበሩን ወደፊት የሚያጋጥመውን የሰው ኃይል ፍልሰትና እጥረት ለመቋቋም የሚያስችለው ሆኖ አንድ ሠራተኛ ሲለቅ ያለምንም ችግር ለመተካት እንዲያስችል ነው፡፡
14.10 የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች በጡረታ፣ በእድገት፣ በዝውውርና በስንብት አክስዮን ማህበሩን በመልቀቅ ወዘተ… መደበኛ ሥራቸውን ወይም አክስዮን ማህበሩን ለቀው ከመሄዳቸው በፊት ለቦታው የሚመጥንና የሚተካቸውን ሠራተኛ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
14.11 በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ ለቁልፍ የሥራ መደቡ የሚመጥን ተኪ ሠራተኛ ካልተገኘ ከውጭ በመቅጠር በተኪነት መያዝ ይቻላል፡፡
14.12 የተኪ ምደባ በተኪ መመሪያው መሠረት የሚፈጸም ሆኖ በተኪ ኮሚቴው ውስጥ ከመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር አንድ አባል ይመደባል፡፡
አንቀጽ 15 ስንብት
15.1 የሥራ ውል የሚቋረጠው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011መንግሥት ወደፊት የሚያወጣቸው አዋጆችና ህብረት ስምምነት መሠረት ይሆናል፡፡
15.2 በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ከሥራው የሚሰናበት እንዲሁም በልዩ ልዩ አገልግሎት ምክንያት ለረጂም ጊዜ ወደ ሌላ ተቋም የሚሄድማንኛውም የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛተገቢ መብቱን ሁሉ ለማግኘት ይችል ዘንድ በቅድሚያ በእጁ ያሉትን የፋብሪካውን ንብረቶች በሙሉ ለአክስዮን ማህበሩ ማስረከቡ መረጋገጥ አለበት፡፡
15.3 የሥራ ውሉ ተቋርጦ ለሚሠናበት ሠራተኛ በአንቀጽ 15.2 የተጠቀሰውን በቅድሚያ ካሟላ በኋላ ተገቢው ክፍያና የምሥክር ወረቀት ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
15.4 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟላ የምሥክር ወረቀት ሠራተኛው ሲጠይቅ በአማርኛ ወይም በእንግሊዘኛ ወይም በሁለቱም ቋንቋዎች ይሰጠዋል፡፡
ሀ/ የሠራተኛው ስም
ለ/ የሥራ ዓይነት
ሐ/ የሥራ መደብ
መ/ የአገልግሎት ዘመን
ሠ/ ይከፈለው የነበረው ደመወዝ
ረ/ ሠራተኛው በሥራ ላይ እያለ የነበረው እንቅስቃሴ መግለጫ
ሰ/ የሥራ ግብር መክፈሉን ማረጋገጫ
ሸ/ የጡረታ ቁጥር
15.5 የማንኛውም ሠራተኛ የስንብት ክፍያ የሚፈፀመው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011መሠረት ነው፡፡
15.6 አዋጅ ቁጥር 1156/2011እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ሠራተኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራው ቢለይና ወደ ሥራው ለመመለስ ቢያመለክት በምትኩ ሥራ ቦታው ላይ ሌላ ሠራተኛ ያልተመደበበት ከሆነና ሠራተኛው ለሥራው አስፈላጊ መሆኑን ሲያረጋግጥ አክስዮን ማህበሩ ወደ ሥራው ሊመልሰው ይችላል፡፡
15.7 በጡረታ ተሰናብተው እንደገና የሚቀጠሩ ሠራተኞች የሥራ ሥንብት ካሳ ክፍያን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 39 ንዑስ ቁጥር 1 መሠረት የአገልግሎት ካሳ ክፍያ አያገኙም፡፡
አንቀጽ16 የሥራ ሰዓት፣የሕዝብ በዓላት፣የትርፍ ሰዓትና የሣምንት የእረፍት ቀን
16.1 የሥራ ሰዓት
መደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን ከ8 ሰዓት ወይም በሣምንት ከ48 ሰዓት አይበልጥም፡፡
16.1.1 የሥራ ሰዓት አቆጣጠር ከዚህ በታች እንደተመለከተው ነው፡፡
16.1.1.1 ከሰኞእስከቅዳሜ
ለጧት ፈረቃ ከጧቱ 1፡00 - ቀኑ 9፡00 ሰዓት
ለአምሽ ፈረቃ ከቀኑ 9፡ዐዐ - ምሽቱ 5፡ዐዐ ሰዓት
ለአዳሪ ፈረቃ ከምሽቱ 5፡ዐዐ - ጧቱ 1፡ዐዐ ሰዓት
ለፈረቃ ሠራተኞች በየፈረቃው የ3ዐ ደቂቃ የምሣ/የራት/ጊዜ ይኖረዋል፡፡
16.1.1.2 በመደበኛ ሰዓት /ከፈረቃ ውጪ/ ለሚገቡ፡-
ከሰኞ እስከ አርብ
ከጧቱ 2፡00 ሰዓት - ቀኑ 6፡ዐዐ ሰዓት
ከቀኑ 7፡ዐዐ ሰዓት - ቀኑ 1ዐ፡ዐዐ ሰዓት
16.1.1.3 ቅዳሜ
ከጧቱ 2፡ዐዐ ሰዓት - ቀኑ 6፡ዐዐ ሰዓት
16.1.1.4 በማንኛውም የሥራ ወይም በሣምንት የእረፍት ቀን ወይም በሕዝብ በዓላት ቀን ከዚህ በታችለተመለከተው አገልግሎት ሰጪ ክፍል ሠራተኞች አሰሪው እንደ አስፈላጊነቱ በሥራ ላይ እንዲገኙ ሊያደርግ ይችላል፡
1. የሕክምና ባለሙያዎች፣ የትንሽ መኪና፣የአምቡላንስና የእሣት አደጋ ሹፊሮች
2. የጥበቃ ሠራተኞች
3. የኤሌክትሪክና የዲዝል ሞተርሠራተኞች፣
4. የውሃ አገልግሎትና የእሣት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች
5. የቴሌፎን ኦኘሬተር
6. የመዋኛ ገንዳ ሠራተኞች
16.1.1.5 ሠራተኛው በጽሁፍ ከፈረቃ ወደ ፈረቃ ወይም ከፈረቃ ወደ መደበኛ ፈረቃ ወይም ከመደበኛ ፈረቃ ወደ ፈረቃ በጊዜያዊም ሆነ በመደበኛ ዝውውር ሲመደብ የሥራ ሰዓቱ ተመድቦ በሚሠራበት የሥራ ሰዓት ይሆናል፡፡
16.2 የሕዝብ በዓላት
16.2.1 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሕዝብ በዓላት ቀን ይሆናሉ፡፡ ሆኖም አግባብባለው የመንግሥት ሕግ የሚሻሻል ከሆነ በሕግ የተሻሻለው ተግባራዊ ይሆናል፡፡
1. መስከረም 1 ቀን ዘመን መለወጫ
2. መስከረም 17 ቀን መስቀል
3. ታህሣስ 29 ቀን ልደት
4. ጥር 11 ቀን ጥምቀት
5. የካቲት 23 ቀን የአድዋ ድል መታሰቢያ
6. ሚያዚያ 23 ቀን የዓለም አቀፍ ወዛደሮች ቀን/ሜይ ደይ/
7. ሚያዚያ 27 ቀን የድል በዓል
8. ኢድ አልፈጥር /ረመዳን/
9. ስቅለት
10. ትንሣኤ
11. ኢድ አልአደሀ /አረፋ/
12. መውሊድ /የነብዩ መሐመድ ልደት/
13. ግንቦት 2ዐ እና መንግሥት የሚያወጣቸው በዓላት
ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የሕዝብ በዓላት በሣምንት እረፍት ቀናት ላይ ቢውል ለሠራተኛው ደመወዝ የሚከፈልበት ቀን ይሆናል፡፡
16.3 የትርፍ ሰዓት ሥራ
16.3.1 ስለ ትርፍ ሰዓት ሥራ፣ የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎችና ስለ አከፋፈሉም በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011ከአንቀጽ 66-68 በተዘረዘረው መሠረት ይፈፀማል፡፡
16.3.2 ትርፍ ሰዓት እንዲሠራ የታዘዘ ሠራተኛበአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 67 መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
16.3.3 ለትርፍ ሰዓት ክፍያ የሚፈፀመው ከ15 ደቂቃ በላይ ለተሠራ ሥራ ነው፡፡
16.3.4 ነፍሰጡር መሆናቸው የታወቀ፣ ወጣትና በቀላል ሥራ የተመደቡ ሠራተኞች ትርፍ ሰዓት እንዲሠሩ አይገደዱም፡፡
16.4 የሣምንት እረፍት ቀን
16.4.1 የሣምንት እረፍት ቀን እሁድ ይሆናል፡፡ ሆኖም በአንቀጽ 16.1.1.4 ለተዘረዘሩት የሥራ መደቦች አክስዮን ማህበሩ እሁድ የሥራ ቀን እንዲሆን ከፈለገ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 7ዐ ተ/ቁ 1 መሠረት ከሣምንቱ የሥራ ቀኖች አንዱን መርጦ የእረፍት ቀን እንዲሆን ያደርጋል፡፡ አፈጻጸሙን አክስዮን ማህበሩና ሠራተኛ ማህበሩ በጋራ ጥናት በማድረግ ይወሰናል፡፡
አንቀጽ 17 የደመወዝና ልዩ ልዩ ክፍያዎች፣ የደመወዝ ጭማሪና ማነቃቂያ ክፍያ
17.1 ደመወዝ
17.1.1 የወር ደመወዝ የሚከፈለው እ.ኢ.አ. ወር በገባ በ28ኛው ቀን ይሆናል፡፡
17.1.2 የወር ደመወዝ የሚከፈልበት ቀን በሣምንት እረፍት ቀን ወይም በሕዝብ በዓላት ቀን ከዋለ ከመደበኛ የክፍያ ቀን አንድ ቀን አስቀድሞ ይከፈላል፡፡
17.1.3 ደመወዝ የሚከፈለው በቀጥታ ለሠራተኛው ነው፡፡ ሆኖም በተለያዩ ሕጋዊ ምክንያቶች ሠራተኛው ቀርቦ መቀበል ካልቻለ የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ባዘጋጀው ቅጽ በጽሁፍ ለሚወክለው ተረጋግጦ ሊከፈለው ይችላል፡፡
17.1.4 በሕግ ወይም በሠራተኛው የጽሁፍ ስምምነት፣ በሥራ ደንብ ወይም በፍ/ቤት ትዕዛዝ ካልሆነ በስተቀር የማንኛውም ሠራተኛ ደመወዝ አይያዝም አይቆረጥም፡፡
17.1.5 በአንድ ጊዜ ከሠራተኛው ደመወዝ ላይ በዕዳ ሊቆረጥ የሚችለው የገንዘብ መጠን ከወር ደመወዙ 1/3ኛ አይበልጥም፡፡
17.2 የቅድሚያ ክፍያ
17.2.1 ሠራተኛው ከደመወዝ ቅድሚያ ክፍያ /አድቫንስ/ ሲፈልግ ወር በገባ በ4ኛው ቀን የደመወዙን 1/3ኛ መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህም በአክስዮን ማህበሩ መረጋገጥና መፈቀድ ይኖርበታል፡፡
17.3 የውሎ አበል
17.3.1 ማንኛውም ሠራተኛ ለአክስዮን ማህበሩ ሥራ ጉዳይ አክስዮን ማህበሩ ካለበት ከተማ ውጭ ሲንቀሳቀስ የውሎ አበል ይከፈለዋል፡፡ ለዚህ ተግባር አሠሪው የትራንስፖርት አገልግሎት ካላቀረበ ተጓዡ የትራንስፖርት ወጪውን በመንግሥት ታሪፍ መሠረት በሚያቀርበው ሕጋዊ ማስረጃ ይከፈለዋል፡፡ ሆኖም ሁኔታው የተለየና አሣማኝ ሆኖ ሲገኝ በመምሪያው ሥራ አስኪያጅ ተፈርሞ በዋና ሥራአሰኪያጅ ሲፈቀድ ሠራተኛው በሚያቀርበው ሕጋዊ ማስረጃ መሠረት እንዲወራረድለት ይደረጋል፡፡
17.3.2 የውሎ አበል ክፍያ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
ደረጃ | የውሎ አበል ክፍያ |
ከI- XIV | 468.00ብር |
17.3.2.1 አክስዮን ማህበሩወቅታዊ ሁኔታን በማየት አበሉን ሊያስተካክል ይችላል፡፡
17.3.2.2 የበርሃ አበል መንግሥት በርሃ ተብለው በተያዙ ቦታዎች ለሚደረግ ጉዞ በአበሉ ላይ ተጨማሪ 3ዐ% ይከፍለዋል፡፡ ሆኖም ግን ለሥራ ወደ ጅቡቲና አሰብ ለሚሄዱ ሠራተኞች የአበሉን 4ዐ% ይከፈለዋል፡፡
17.3.2.3 የውጭ አገር አበል በመንግሥት መመሪያ መሠረት ይወሰናል፡፡
17.3.2.4 ማንኛውም የውሎ አበል ከ3ዐ ቀናት በላይ መብለጥ የለበትም፡፡ ሆኖም ግን ከ3ዐ ቀናት በላይ መጨመሩ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በዋና ሥራ አስኪያጅ እንደገና ታይቶ በልዩ ሁኔታ መጽደቅ ይኖርበታል፡፡
17.3.2.5 ምግብና መኝታ በሌላ ወገን ከተሸፈነ ለልዩ ልዩ ወጭ የአበሉን 25% ብቻ ይከፈላል፡፡
17.3.3 ማንኛውም የሚያሣድርና አበል የሚከፈልበት ጉዞ ከመደረጉ በፊት በሚመለከተው ኃላፊ መፈቀድ አለበት፡፡
17.3.4 በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 17.3.2 የተገለፀው የውሎ አበል ክፍያ ተመን እንደሚከተለው ነው፡፡
ለቁርስ | 1ዐ% | ለእራት | 25% |
ለምሣ | 25% | ለአልጋ | 4ዐ% |
ሀ/ ቁርስ ከጧቱ 1፡ዐዐ ሰዓት በፊት ጉዞ የጀመረ ወይም ከአለበት ከተማ ውጪ አድሮ ከጧቱ 2፡ዐዐ ሰዓት በኋላ የገባ፣
ለ/ ምሣ ከቀኑ 6፡ዐዐ ሰዓት በፊት ካለበት ከተማ የወጣ ወይም ከ7፡ዐዐ ሰዓት በኋላ የተመለሰ፣
ሐ/ አንድ ሠራተኛ ከመደበኛ የሥራ ቦታው ከ5ዐ /ሃምሣ/ ኪ/ሜ እና ከዚያ በላይ በሆነ ርቀት የአክስዮን ማህበሩን ሥራ ለማከናወን ቢታዘዝ ከጧቱ 1፡ዐዐ በፊት ለሥራ ወጥቶ ሥራውን በማከናወን በዕለቱ በማንኛውም ሰዓት ቢመለስ የሙሉ ቀን አበል ይከፈለዋል፡፡
መ/ ከቀኑ 6፡ዐዐ ሰዓት በፊት ለሥራ ወጥቶ ሥራውን በማከናወን በዕለቱ በማንኛውም ሰዓት ቢመለስ የቁርስ አበል ብቻ ተቀንሶ ቀሪው አበል ታስቦ ይከፈለዋል፡፡
ሠ/ ከምሽቱ 2፡ዐዐ ሰዓት በፊት ለሥራ ከወጣ የቁርስና የምሣ አበል ብቻ ተቀንሶ ቀሪው የእራትና የአልጋ አበል ሥራው ከሚወስደው ጊዜ የአበል ክፍያ ጋር ታስቦ ይከፈለዋል፡፡
ረ/ የመሥክ ሥራው ከአንድ ቀን በላይ የሚፈጅ ከሆነ ከፊደል ሐ - መ ድረስ የተዘረዘሩት እንደተጠበቁ ሆነው ሥራውን አጠናቆ በሚመለስበት ቀን በማንኛውም ሰዓት ቢመለስ በሥራ ላይ ያሣለፋቸው ቀናት አበልና የተመለሰበት ዕለት የሙሉ ቀን አበል ይከፈለዋል፡፡
ሰ/ ከላይ የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ሠራተኛ ከመደበኛ የሥራ ቦታው ከ5ዐ /ሃምሣ/ ኪ/ሜ በታች በሆነ ርቀት የአክስዮን ማህበሩን ሥራ አንዲያከናውን ከታዘዘና ሠራተኛውም በሥራው ላይ ያሣለፈው ጊዜ የቁርስ ወይም የምሣ ወይም የራት ወይም የመኝታ ጊዜን የሚነካ ከሆነ የቁርስ ወይም የምሣ ወይም የራት ወይም የመኝታ አበል ወይም የድምር አበል ይከፈለዋል፡፡
ሆኖም ግን ሆን ብሎ ምክንያት በመፍጠር መግባት በሚገባው ጊዜ ወይም ሰዓት ባለመግባት የውሎ አበል ጥቅም ያለአግባብ ለማግኘት የሚያደርግ ሠራተኛ በሕብረት ስምምነቱ መሠረት ይቀጣል፡፡
17.3.5 የውሎ አበል እየተከፈለው ለሚሠራ ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት አይከፈለውም፡፡
17.4 ለገንዘብ ያዥና ለደመወዝ ክፍያ የሚሰጥ ክፍያ
17.4.1 የመጠባበቂያ ገንዘብ የሚከፈለው ለዋና ገንዘብ ያዥ ብር 870.00 /ስምንት መቶ ሰባ ብር/ ፣ ለረዳት ገንዘብ ያዥ የሚከፈለው ገንዘብ ብር 670.00 ብር /ስድስት መቶ ሰባ ብር/፣ ለአ/አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገንዘብ ያዥ 670.00 ብር /ስድስት መቶ ሰባ ብር/፣ የሱቅ ሽያጭ ሠራተኛ ብር 240.00 /ሁለት መቶ አርባ ብር/ ለመዋኛ ገንዳ ካሸሪ 240.00 /ሁለት መቶ አርባ ብር/ ይሆናል፡፡
17.4.2 በደመወዝ መክፈያ ወቅት ብቻ ተመድበው ደመወዝ እንዲከፍሉ የሚደረጉ ሠራተኞች በአሠሪው ተመርጠው እንዲከፍሉ ሲደረግ፣ የሚሰጣቸው ክፍያ ብር 4ዐዐ.00 /አራት መቶ ብር/፣ ለአድቫንስ ጊዜ ሲከፍሉ ብር 2ዐዐ.00 /ሁለት መቶ ብር/ ደመወዝም ሆነ አድቫንስ በሚከፍሉበት ጊዜ ጉድለት ቢታይባቸው ለእዳ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ የደመወዝ አከፋፈልን በተመለከተ ቀልጣፋ ለማድረግ ሥራ እንዳይበደል አክስዮን ማህበሩ መመሪያ ማውጣት ይችላል፡፡
17.5 የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት የሚደረግ ክፍያና ካሣ
17.5.1 የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት የሚከፈል የስንብት ክፍያ ካሣ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011እና አዋጅ ቁጥር 494/98 መሠረት ይፈፀማል፡፡
17.5.2 አሠሪው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 32 ተራ ቁጥር 1 መሠረት ያለ ማስጠንቀቂያ የሥራ ውሉ ለሚቋረጥ ሠራተኛ በዚህ አንቀጽ ተ.ቁ 17.5.1 ከተጠቀሰው በተጨማሪ የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዝ በ3ዐ ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡
17.5.3 ያለ ማስጠንቀቂያ የሥራ ውላቸውን የሚያቋርጡ ሠራተኞችን ሁኔታ በተመለከተ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 1156/2011አንቀጽ 45 ተራ ቁጥር 1 እና 2 መሠረት ለአክስዮን ማህበሩ የአንድ ወር ደመወዛቸውን እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡
17.5.4 አሠሪው በሥራ ላይ አደጋ ለደረሰበት ሠራተኛ መሥራት አለመቻሉ በሀኪም ሲረጋገጥ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 1ዐ4 ከተጠቀሱት ግዴታዎች በተጨማሪ በአንቀጽ 1ዐ8 ተ.ቁ 2 መሠረት ጉዳት ለደረሰበት ሠራተኛ ክፍያ ያደርጋል፡፡
17.5.5 ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የሞተ እንደሆነ አሠሪው በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 11ዐ መሠረት ይፈጽማል፡፡
17.5.6 በቅጥር ላይ በተመሠረተ ግንኙነት የመነጨ ማንኛውም የመብትና የክፍያ ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011በተገለፀው መሠረት ይፈፀማል፡፡
አንቀጽ 18 ዓመታዊ የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ
18.1 የአክስዮን ማህበሩ ዓመታዊ የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ የሚሰጠው የአክስዮን ማህበሩን ሠራተኞች ለሥራ ለማነቃቃትና አክስዮን ማህበሩን ትርፋማ ለማድረግ ታስቦ ሲሆን፣ የጭማሪና የቦነስ አሰጣጡም የአክስዮን ማህበሩ ዓመታዊ ገቢ ከዓመታዊ ወጪ ሲበልጥና ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት የተጣራ ትርፍ ሲገኝ ነው፡፡
18.1.1 የአክስዮን ማህበሩ የሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የጠቅላላየሠራተኞችን የግማሽ ወር ጥቅል ደመወዝ የሚያክል ከሆነለእያንዳንዱ ሠራተኛ የወር ደመወዙን 3ዐ% ቦነስ በአንድ ጊዜ ይሰጣል /ይከፍላል/፡፡
18.1.2 የአክስዮን ማህበሩ የሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የጠቅላላ የሠራተኛውን የ1 ወር ደመወዝ የሚበልጥ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የአንድ ወር ደመወዙን 5ዐ% ቦነስ ይከፈላል፡፡
18.1.3 የአክስዮን ማህበሩ ሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የጠቅላላ የሠራተኛውን የ2 ወር ደመወዝ የሚበልጥ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የ1 ወር ደመወዙን 6ዐ% ቦነስ ይከፈላል፡፡
18.1.4 የአክስዮን ማህበሩ ሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የጠቅላላ የሠራተኛውን የ3 ወር ደመወዝ የሚበልጥ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የ1 ወር ደመወዙን 100% ቦነስ ይከፈላል፡፡
18.1.5 የአክስዮን ማህበሩ የሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የሠራተኛውን የ4 ወር ጥቅል ደመወዝ የሚበልጥ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የአንድ ወር ደመወዙን 6ዐ%ቦነስና አንድ እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይሰጣል፡፡
18.1.6 የአክስዮን ማህበሩ የሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የሠራተኛውን የ6 ወር ጥቅል ደመወዝ የሚበልጥ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የአንድ ወር ደመወዙን 80%ቦነስና አንድ እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይሰጣል፡፡
18.1.7 የአክስዮን ማህበሩ የሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የጠቅላላ ሠራተኞችን የ9ወር ጥቅል ደመወዝ የሚበልጥ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የአንድ ወር ደመወዙን ቦነስና ሁለት እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይሰጣል፡፡
18.1.8 የአክስዮን ማህበሩ የሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የጠቅላላ ሠራተኞችን የ12 ወር ጥቅል ደመወዝ የሚበልጥ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የደመወዙን 14ዐ% ቦነስና የሁለት እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይሰጣል፡፡
18.1.9 የአክስዮን ማህበሩ ሽያጭ ገቢ ሲያድግና የአክስዮን ማህበሩ የተጣራ ትርፍ የጠቅላላ ሠራተኞችን የ15 ወር ጥቅል ደመወዝ የሚበልጥ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የደመወዙን 15ዐ% ቦነስና ሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይሰጣል፡፡
18.1.10 የደመወዝ ጭማሪና የሶነስ ክፍያ ሂሣብ በኦዲት ሲረጋገጥ የኦዲት ሪፖርቱ በቀረበ ከአንድ ወር በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
18.2 ቦነስና የደመወዝ ጭማሪ የማይመለከታቸው ሠራተኞች
ሀ/ የዓመቱ የሥራ አፈጻጸማቸው ውጤት ከአጥጋቢ በታች የሆነ፣
ለ/ ከዓመት ፈቃድ፣ ከሥራ ላይ አደጋ፣ ከወሊድ ፈቃድ፣ ካንሰር፣ ስኳርና ከፍተኛ የደም ግፊት/ስትሮክ/ እና የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸውያለና ራሣቸውን ያሣወቁ ሕሙማን በስተቀር ሦስት ወርና ከዚያ በላይ ቀሪ ያለባቸው፡
ሐ/ በዲስኘሊን ግድፈት ከሥራቸው የተሰናበቱ፣
መ/ የሙከራ ጊዜያቸውን ያልጨረሱ ሠራተኞች፣
18.3 አንድ ሠራተኛ የቦነስ ክፍያ የሚያገኘው ቦነሱ በተገኘበት የሥራ ዘመን ባደረገው አስተዋጽኦ በመሆኑ የክፍያው አፈጻጸም ለሠራባቸው ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡ በሕመም ምክንያት ከሦስት ወር በላይ በስራቸው ላይ ያልተገኙ ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤታቸውበሥራ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት አጥጋቢና ከአጥጋቢ በላይ ሆኖ ከተገኘ ለሰሩባቸው ጊዜያቶች ታስቦ ቦነስ ይሰጣቸዋል፡፡
አንቀጽ 19 የደመወዝ ክፍያ ሥርዓትና የበጀት ዓመት
19.1 አክስዮን ማህበሩ የሚቀጥረው ወይም የሚመድበውን ሠራተኛ በደመወዙ እስኬል መሠረት ይከፍለዋል፡፡
19.2 አክስዮን ማህበሩ ላሉት የሥራ መደቦች የደመወዝ ስኬል ሥርዓት ይኖረዋል፡፡
19.3 የአክስዮን ማህበሩ የበጀት ዓመት እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን ተጀምሮ ታህሣስ 31 ይጠናቀቃል፡፡
አንቀጽ 20 የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ
20.1 አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኛው የጤና አገልግሎት ይረዳ ዘንድ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መመሪያ ያሟላና የአክስዮን ማህበሩን አቅም ባገናዘበ መልኩከአስፈላጊው መሣሪያና የሰው ኃይል ጋር ክሊኒክ ያደራጃል፡፡
20.2 ሠራተኛው ከባድ አደጋና ሕመም ቢያጋጥመውና ከአክስዮን ማህበሩ ሃኪም አቅም በላይ ከሆነ ወደ ሌላየመንግስትሆስፒታል ይላካል፡፡ አደጋው አሣሣቢና ከፍተኛ መሆኑን የሕክምና ባለሙያው ሲያረጋግጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አክስዮን ማህበሩ ለሕክምና አገልግሎት አምቡላንስ ከሹፊር ጋር ይመድባል፡፡ አምቡላንስ በማይኖርበት ወቅት በሌላ ተሽከርካሪ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
20.3 ሠራተኛው በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ለሚሰጠው የሕክምናና የመድሃኒት ወጪ አክስዮን ማህበሩ ወጪውን 1ዐዐ% ይሸፍናል፡፡ የታዘዘው መድሃኒት በአክስዮን ማህበሩ መድሃኒት ቤት ከሌለ ከውጪ ተገዝቶ የመጣውን መድሃኒት ዋጋ ሠራተኛው ሕጋዊ ደረሰኝ ሲያቀርብ አክስዮን ማህበሩ የመድሃኒት ወጪውን 1ዐዐ% ይሸፍናል፡፡
20.4 የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ሠራተኞች አክስዮን ማህበሩ በመንግሥት ሆስፒታል እንዲታከሙ ውል ከሞላ 1ዐዐ%፣ በግል ሆስፒታል እንዲታከሙ ውል ከተሞላላቸው 75%አክስዮን ማህበሩ የሕክምናና የመድሃኒት ወጪ ይሸፍናል፡፡ መድሃኒቱ መገዛት ያለበት ከልዩ መድሃኒት ቤቶች፣ ከቀይ መስቀልና ከከነማ መድሃኒት ቤቶች ይሆናል፡፡
20.5 አንድ ሠራተኛ በሕጋዊ ፈቃድ ላይ እያለ ወይም ድንገተኛ ሕመም ቢያጋጥመውና በመንግሥት የሕክምና ድርጅት ቢታከም ለሕክምና ያወጣውን ወጪ አክስዮን ማህበሩ 1ዐዐ% ይሸፍናል፡፡
20.6 በሥራ ላይ ሠራተኞች ቢታመሙና የክሊኒክ አገልግሎት ቢያስፈልጋቸው ከቅርብ አለቃቸው ዘንድ የመታከሚያ ቅጽ ተቀብለው ለሕክምና ይሄደሉ፡፡ ሕክምናውን እንደጨረሱ የተመለሱበትን ሰዓት ሐኪሙን በቅጹ ላይ አስሞልተው ወደ ሥራቸው በመመለስ ለቅርብ ኃላፊያቸው ማሣወቅ አለባቸው፡፡ የሕክምና ፈቃድ የተሰጣቸው ከሆነ በዕለቱ ለሥራ ክፍላቸው ያሣውቃሉ፡፡ መረጃቸውን ለሪስክ ማኔጅመንትና ለካሣና ጥቅማ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡
20.7 በእረፍት ሰዓት ላይ እያለ የታመመ ሠራተኛ የመታከሚያ ቅጽ ከቅርብ ኃላፊው ወይም እሱ ከሌለ ከእሱ በላይ የሆነ ኃላፊ አስፈርሞ በቀጥታ ወደ ክሊኒክ ሄዶ የሕክምና አገልግሎት ያገኛል፡፡ የሕመም ፈቃድ ካገኘ ለጻፈለት ወይም በሥራ ላይ ላለው አለቃ የሐኪም እረፍት ማግኘቱን ያሣያል ወይም ያሣውቃል፡፡ ሆኖም ግን ከፍተኛ ሕመም እንዳለበት ለሕክምና ክፍሉ ሲነገረው በአክስዮን ማህበሩ ተሽከርካሪ ከኮምቦልቻ ከተማ ወደ አክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ እንዲመጣና እንዲታከም ይደረጋል፡፡
20.8 የአንድ ሠራተኛ ሕመም ከአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ አቅም በላይ ሆኖ ወደ ሌላ የመንግስትሆስፒታል ሲላክ አክስዮን ማህበሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ሆኖም በተሽከርካሪ ችግር ምክንያት ሠራተኛው በሕዝብ ማመላለሻ ከሄደ በሚያቀርበው ማስረጃ ወይም አክስዮን ማህበሩ በአዘጋጀው የማወራረጃ ቅጽመሠረት ክፍያው ይፈፀማል፡፡
20.9 የአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ 24 ሰዓት የሚያገለግል የሥራ ኘሮግራም አውጥቶ ይሠራል፡፡ ሆኖም አደጋ ለደረሰባቸውና ሕመማቸው አጣዳፊ ለሆኑ ሠራተኞች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ታመው በክሊኒክ ተኝተው ለሚታከሙ ሠራተኞች የአንሶላና የብርድ ልብስ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
20.10 አንድ ሠራተኛ አስቀድሞ በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ከታከመ በኋላ ሆስፒታል እንዲታከም አስፈላጊ ከሆነ የክሊኒኩ ሐኪም በሚሰጠው ውሣኔ መሠረት ወደሚመለከተውየመንግስትሆስፒታል ይላካል፡፡ ሕመሙ ሕመምተኛው ከተላከበት ሆስፒታል አቅም በላይ ከሆነ የሆስፒታሉ ሐኪም ባዘዘው መሠረት ወደ ሌላ የመንግሥት ሆስፒታል ተልኮ ይታከማል፤ አክስዮን ማህበሩ የሕክምና ወጪውን 1ዐዐ% ይሸፍናል፡፡ ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለው የሚታከሙ ሠራተኞች የአንድ የሪፈር የህክምና ክትትል ጊዜ ከአንድ ዓመት አይበልጥም፡፡ ሆኖም ግን ከሕመማቸው ካልዳኑ ለአክስዮን ማህበሩ ሪፖርት በማድረግ የሕመማቸው ሁኔታ ታይቶ ሪፈር የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ደረጃውን ጠብቆ በሪፈራል በድጋሚ እንዲታከሙ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን የሥራ ላይ አደጋ ደርሶባቸው የሕክምናቸው ውጤት በሕክምና ቦርድ ውሣኔ ያልተሰጣቸውን ሠራተኞች አይመለከትም፡፡
20.10.1 አንድ ሠራተኛ ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ ቢታመም ወይም አደጋ ቢደርስበት በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ መታከም ካልቻለ በመንግሥት የጤና ድርጅት ታክሞ ሕጋዊ ደረሰኝ ሲያቀርብ ወጪ ያደረገውን 1ዐዐ% አክስዮን ማህበሩ ይከፍላል፡፡
20.10.2 የሕመም ፈቃድ ክፍያ ከዚህ ቀጥሎ በተመለከተው መሠረት ይሆናል፡፡
ለመጀመሪያ ሁለት ወር | 1ዐዐ% |
ለሚቀጥለው ስምንት ወራት | 50% |
ለሚቀጥለው ሁለት ወራት | 25% |
ሆኖም የሕክምናና የመድሃኒት ወጪን በተመለከተ በዚህ ሕብረት ስምምነት ስለ ሕክምናና አገልግሎት አሰጣጥ በተጠቀሰው መሠረት የሥራ ውሉ እስከሚቋረጥ ድረስ ለማንኛ ውም ሠራተኛ የሚከፈለው የሕክምናና የመድሃኒት ወጪ ክፍያ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
20.11 ሀ/
አንድሠራተኛከሥራጋርባልተያያዙሁኔታዎችበደረሰበትሕመምወይምበቀላልየሥራመደብላይእንዲሠራበሐኪምቦርድ ከታዘዘ አክስዮን ማህበሩ በቀላል የሥራ መደብ ላይ ይመድባል፡፡ ለመመደብ ካልቻለ ግን በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 28 መሠረት ይፈፀማል፡፡ሆኖም የሠራተኛውን የሥራ ዋስትና ግምት ውስጥ በማስገባት አክስዮን ማህበሩ የ4 ወር ደመወዝ ድጎማ ይሰጣል፡፡
ለ/ ከሥራ ጋር ባልተያያዘ አደጋ ወይም ሕመም በሀኪም ቦርድ የሥራ ውሉበጡረታ ለሚቋረጥ ሠራተኛ የሠራተኛውን የሥራ ዋስትና ግምት ውስጥ በማስገባት አክስዮን ማህበሩ የ3ወር ደመወዝ ድጎማ ይሰጣል፡፡እንዲሁም የአክስዮን ማህበሩ ምርት የሆነውን አንሶላ 2.1ዐ X 2.5ዐ ብዛት አንድ፣ አንሶላ 1.90 X2.50 ብዛት አንድ፣ፎጣ 1ዐዐ X 2ዐዐ ብዛት አንድ፣ ፎጣ 7ዐ X 14ዐ ብዛት አንድ እና የምሥክር ወረቀት ጋር ይሰጠዋል፡፡
20.12 ሕመምተኛው ሕመሙ አሣሣቢ ሆኖ በአክስዮን ማህበሩ ተሽከርካሪ ወደ መንግሥት ጤና ድርጅቶች ሲላክ በጉዞ ላይ የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን ክሊኒኩ ሲያምንበት አንድ የሕክምና ባለሙያና አንድ የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ የሚከፈልበት ፈቃድ በመስጠት አብሮ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡
20.13 የሠራተኛውን ቤተሰብ ከኮሌራና ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ለመከላከል የሚያስችለውን ክትባት እንዲያገኝ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተጠሪ ጽ/ቤት በሚያመቻቸው ኘሮግራም መሠረት አክስዮን ማህበሩ ትብብር ያደርጋል፣ ለሠራተኛው ቤተሰብ ነጻ ወይም የዱቤ የሕክምና ምርመራ አገልግሎት ስለሚሰጥበት አክስዮን ማህበሩ መመሪያ ያወጣል፡፡
20.14 አንድ ሠራተኛ ወደ ከፍተኛየመንግስትሆስፒታል ሪፈር ተብሎ ለሕክምና ከሄደ ሕክምናውን እስከሚያጠናቅቅ ድረስ በቀን 250.00 ብር /ሁለት መቶ ሃምሣብር/አዲስ አበባ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይከፈለዋል፡፡ ሆኖም የተሰጠው ቀጠሮ 7 ቀንና ከዚያ በላይ ከሆነ ወደ ኮምቦልቻ ይመለሣል፡፡ ደሴና ቦሩ ሆስፒታሎች ሪፈር ተብለው ከሄዱና ሕክምናው ከ6 ሰዓት በኋላ የሚያቆይ ከሆነ ለምሣ ብር8ዐ.00 /ሰማኒያ ብር/ ይከፈላል፡፡ ሆኖም ግን ተኝተው የሚታከሙትን ክፍያው አይመለከትም፡፡
20.15 አክስዮን ማህበሩ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ሆስፒታሎች ጋር ለሠራተኛው የዱቤ ሕክምና ውል ይፈራረማል፡፡ ነገር ግን አዲስ አበባ የሄዱ ሠራተኞች በድንገት ከታመሙ በቅ/ጽ/ቤቱ በኩል ቀርበው ወዲያውኑ እንዲታከሙ ይደረጋል፡፡
አክስዮን ማህበሩ የዱቤ ሕክምና ውል የሚፈራረምባቸው ሆስፒታሎች
1/ | ደሴ ሆስፒታል | 6/ | ምኒልክ ሆስፒታል |
2/ | ቦሩ ሆስፒታል | 7/ | አማኑኤል ሆስፒታል |
3/ | ጥቁር አንበሣ ሆስፒታል | 8/ | ጵውሎስ ሆስፒታል |
4/ | የካቲት 12 ሆስፒታል | 9/ | ኮምቦልቻ ሆስፒታል |
5/ | ዘነበወርቅ ሆስፒታል |
ሆኖም በሽተኛው ከላይ በተጠቀሱት ሆስፒታሎች አክስዮን ማህበሩ የዱቤ ሕክምና ውል ወደሌላቸው የመንግሥት ሆስፒታሎች ሪፈር ሲባል የሕክምናና የመድሃኒት ወጪ በተመለከተ የቅ/ጽ/ቤቱ በሕ/ስምምነቱ መሠረት ይሸፍናል፡፡
20.16 አንድ ሠራተኛ ከሥራ ጋር ባልተያያዘ ሕመም ሃኪም ቤት ተኝቶ እንዲታከም ሃኪም ሲያዝ በ3ኛ ደረጃ ተኝቶ ሊታከም ይችላል፡፡ ሆኖም በሀኪም ትዕዛዝ ከሆነ እስከ 2ኛ ደረጃ ድረስ ተኝቶ ይታከማል፡፡ ከዚህ ደረጃ በላይተኝቶ ከታከመ ልዩነቱን ሠራተኛውእንዲከፍል /ተመላሽ እንዲያደረግ/ ይደረጋል፡፡
20.17 በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ የሚሰጥ የሠራተኞችን የሕክምና ኘሮግራም በሚመለከት አክስዮን ማህበሩና ሠራተኛ ማህበሩ በጋራ ይወስናሉ፡፡
20.18 በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ እንዲተኛ የተደረገ ሠራተኞች ከአንድ ቀን በላይ ከቆየና የፋይናንስ አቅምና ምግብ የሚያቀርብለት ከሌለው የክሊኒኩ ኃላፊ በሚሰጠው አስተያየት መሠረት ምግብ እንዲቀርብለት ሆኖ አፈጻጸሙን የሠራተኛ ማህበሩና የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መመሪያ በጋራ በመነጋገር ተግበራዊ ያደርጋሉ፡፡
20.19 ከኮምቦልቻ፣ ደሴና አዲስ አበባ ውጭ ማንኛውም ሠራተኛ በመስክ ሥራ ላይ እያለ ሕመም ሲያጋጥመው በማንኛውም የሕክምና ማዕከል ታክሞ መረጃ ሲያቀርብ የሕክምናና የመድሃኒት ወጪ 1ዐዐ% ይከፈልለታል፡፡
20.20 አንድ ሠራተኛ ድንገተኛ ሕመምና አደጋ ካጋጠመው በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ሊታከም ካልቻለ በአቅራቢያው በሚገኝ የመንግሥት ጤና ጣቢያ ወይም ሆስፒታል ይታከማል፡፡ ሆኖም አማራጭ ከታጣበግል ከፍተኛ የሕክምና ተቋም ታክሞ መታከሙን የሚገልጽ ማስረጃ አክስዮን ማህበሩ እንዲያውቀው ሲያደርግናበህክምና ኃላፊ ሲረጋገጥየሕመም ፈቃድና የሕክምና ወጪ ይከፈለዋል፡፡ሆኖም ግን በግል የህክምና ተቋም የሚመጣ ክፍያ ከ30000.00 /ሠላሳ ሺህ ብር መብለጥ የለበትም፡፡ድንገተኛ ሕመም የሚባሉትም ከፍተኛ የደም ግፊት/ስትሮክ/፣ የስኳር በሽታ፣ ድንገተኛ የልብ ድካም፣ የሚጥል በሽታ፣ ከፍተኛ ተቅማጥና ትርፍ አንጀት፣ ከፍተኛ የደም መፍሰስ፣ አስም፣ ኮቪድ 19ሕመሞች ናቸው፡፡
አንቀጽ 21 ከሥራ ጋር ለተያያዘ ጉዳት የሚሰጥ ሕክምና
21.1 ሠራተኛው በሥራ ላይ በሚደርስበት አደጋ ወይም ጉዳት ከሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ለሚደርስ ሕመም ሁሉ አክስዮን ማህበሩ ኃላፊ ነው፡፡
21.2 ሠራተኛው እንዲሠራ የሚጠበቅበትን የክፍሉን ሥራ ሲሰራ ወይም በመደበኛ ሥራው ላይ ባይሆንም እንኳ በአለቆቹ ትዕዛዝ የአክስዮን ማህበሩን ሥራ በሚያከናውንበት ጊዜ ለሚደርስበት አደጋ አክስዮን ማህበሩ ኃላፊ ነው፡፡
21.3 አንድ ሠራተኛ በሥራው ላይ እንዳለ አደጋ ከደረሰበት በሚመለከተውየመንግስትየሕክምና ተቋም ታክሞ አጠቃላይ የመጨረሻ የሕክምና መረጃ ሲያቀርብ አክስዮን ማህበሩ በገባው የኢንሹራንስ ዋስትና መሠረት በ3ዐ ቀን ውስጥ የካሣ ክፍያ ይፈፀማል፡፡
21.4 በሥራ ላይ ለደረሰ ጉዳት፣ አደጋ ወይም ሕመም የሚደረገው የካሣ ክፍያ መጠን የሕክምና ቦርድ በሚያዘው መሠረት ይሆናል፡፡
21.5 በሥራ ላይ በደረሱ ሁኔታዎች ምክንያት ሠራተኛው በሕክምና ላይ ሆኖ ሥራ ላቆመባቸው ጊዜያት አክስዮን ማህበሩ በገባው ኢንሹራንስ ውል መሠረት ለሠራተኛው ደመወዝ ይከፍላል፡፡
21.6 አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ በደረሰበት አደጋ ምክንያት ተገቢው ሕክምና ተደርጎለት እስከመጨረሻው የማይድን ወይም ለሥራው ብቁ ያለመሆኑን የሐኪሞች ቦርድ ሲያረጋግጥ ከዚህ ሕብረት ስምምነትና ከአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011መሠረት የሚገባውን ሁሉ ተከፍሎት ከሥራ ይሰናበታል፡፡ በተጨማሪም በሥራ ላይ አደጋ ደርሶባቸው በጡረታ ወይም ስንብት የሥራ ውላቸው ለሚቋረጥ ሠራተኞች የ2 ወር ደመወዝ አክስዮን ማህበሩ ድጎማ ይሰጣል፡፡ ሆኖም የአገልግሎት ዘመኑ የሚፈቀድለት ከሆነ በጡረታ እንዲገለል ይደረጋል፡፡
21.7 አንድ ሠራተኛ የሥራ ላይ አደጋ ደርሶበት ወደ ሆስፒታል እንዲሄድ በባለሙያ ሲወሰን ለትራንስፖርት፣ ለምርመራና ለመድሃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ በቅድሚያ ክፍያ መልክ ይሰጠዋል፡፡ ከተሰጠው ገንዘብ ውስጥ ሕጋዊ ደረሰኝ ካላቀረበ ከደመወዙ ይቀነሣል፡፡ የወጣውን ወጪ ከኢንሹራንስ ማስመለስ የአክስዮን ማህበሩ ኃላፊነት ነው፡፡
21.8 በሥራ ላይ የሚመጣ ጉዳት ለደረሰበት ሠራተኛ ለሚከተሉት የሕክምና አገልግሎቶች የሚያስፈልገውን ወጪ አክስዮን ማህበሩ ይከፍላል፡፡
21.8.1 የጠቅላላና የልዩ ሕክምና እንዲሁም የቀዶ ጥገና ሕክምና ወጪዎች፣
21.8.2 የሆስፒታልና የመድሃኒት ወጪዎች፣
21.8.3 የማንኛውም አስፈላጊ ሰው ሠራሽ ምትክ ወይም ተጨማሪ አካሎችና የአጥንት ጥገና ወጪዎች፣
21.9 ሠራተኛው ለደረሰበት ጉዳት የሚደረግለት የሕክምና አገልግሎት የሚቋረጠው የሕክምና ቦርድ በሚሰጠው ውሣኔ መሠረት ይሆናል፡፡
21.10 በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 1ዐ8 ተራ ቁጥር 1 መሠረት ጊዜያዊ የአካል ጉዳት እስከሚወገድ ጊዜ ድረስ በየጊዜው የሚደረግ ክፍያ አክስዮን ማህበሩ ከአንድ ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ይከፍላል፡፡
21.11 ማንኛውም በሥራ ላይ የሚመጣ ጉዳት የደረሰበትን ሠራተኛ የሚደረገው የክፍያ መጠን ጉዳቱ ከደረሰበት ዕለት ጀምሮ ላሉት ለመጀመሪያ ስድስት ወራት ሠራተኛው ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት ያገኝ የነበረው የዓመቱ አማካይ ደመወዝ 5ዐ% የማያንስ ይሆናል፡፡
21.12 በየጊዜው የሚደረገው ክፍያ ከሚከተሉት መካከል ቀድሞ በተፈፀመው በማናቸውም ዕለት ይቆማል፡፡
21.12.1 ሠራተኛው የደረሰበት ጊዜያዊ ጉዳት የተወገደለት መሆኑ በሃኪምሲረጋገጥ፣
21.12.2 ሠራተኛው የጉዳት ጡረታ ካሣ ወይም ዳረጎት የሚያገኝበት ቀን፣
21.12.3 ሠራተኛው ሥራ መሥራት ካቆመበት ዕለት ጀምሮ አሥራ ሁለት ወር
ሲሞላው፣
21.12.4 የሥራ አደጋ ደርሶበት ለሞተ ሠራተኛ ለማንኛውም ሠራተኛ ከሚከፈለው
የቀብር ማስፈፀሚያ በተጨማሪ የአራት ወር ደመወዝ ለሟች ሕጋዊ ወራሽ ለሆኑ ቤተሰቦች /ቤተሰብ/ ይከፈላል፡፡
21.13 ሠራተኛው በኢንዱስትሪ አደጋዎች ምክንያት በሕክምና ላይ ባለበት ጊዜ ለሥራው ብቁ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ለዕድገት መወዳደር ይችላል፡፡ ለውድድር በወጣው ማስታወቂያ ለመወዳደር የተመዘገበ ሠራተኛ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት የሥራ ላይ አደጋ ካጋጠመው ፈተናው እስከ 30ቀናቶች እንዲራዘምለት ይደረጋል፡፡
አንቀጽ 22 በሕመም ምክንያት የሚሰጥ ቀላል ሥራ
22.1 ሠራተኛው በሕመም ምክንያት ከመደበኛ ሥራው ውጭ ቀላል ሥራ እንዲሠራ የአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ በቋሚነት ሊሰጥ አይችልም፡፡ ሆኖም የሕመሙን ሁኔታ በማየት የአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ዶክተር /ኃላፊ/ ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ በቀላል ሥራ እንዲመደብ ሊያደርግ ይችላል፡፡
22.2 ሠራተኛው በሕመም ምክንያት በሥራ ውል ውስጥ ከተመለከተው ውጭ በቋሚነት ቀላል ሥራ እንዲሠራ የሚወሰነው በመንግሥት ሆስፒታሎች የሕክምና ቦርድ ነው፡፡
አንቀጽ 23 ሴፍቲ ኮሚቴ
23.1 የሴፍቲ ኮሚቴ ከሠራተኛ ማህበርና ከማኔጅመንቱ የተዋቀረ ሆኖ የሥራና ሥልጠና መምሪያ ባወጣው ደንብና መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የሴቶች ስብጥር እንዲኖር ይደረጋል፡፡
23.2 ኮሚቴው የአደጋ መንስኤዎችን እያጠና የሚወገዱበትን የመፍትሄ ሃሣቦች ለዋና ሥራ አስኪያጅ በማቅረብ የአክስዮን ማህበሩንና የሠራተኛውን ደህንነት ይጠብቃል፡፡
23.3 የእሣት አደጋ መከላከያ መሣሪያዎች እንዲሟሉና የአክስዮን ማህበሩ ንብረቶች በአግባቡ እንዲቀመጡ ሪፖርት ያቀርባል፣ ያስፈጽማል፡፡
23.4 የአክስዮን ማህበሩን ጠቅላላ ንጽሕና መጠበቁን ይቆጣጠራል፣ የመፀዳጃ ቤቶችን አያያዝ ይከታተላል፡፡
23.5 ለአዲስ ተቀጣሪ ሠራተኞች ስለ ሙያ ደህንነትና ጤንነት ተገቢውን ትምህርታዊ መግለጫ በየጊዜው እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
23.6 አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከውስጥና ከውጭ ባለሙያዎችን እየጋበዘ ስለ ሙያ ደህንነትና ጤንነት ትምህርት እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
አንቀጽ 24 ኢንሹራንስ
24.1 አንድ ሠራተኛ የሥራ ተግባሩን ፈጽሞ ከወጣ በኋላ ወደ ቤቱ ሲመለስ 2፡00 ሰዓት ወይም ተግባሩን ለመፈፀም ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት 2፡ዐዐ ሰዓት በሥራ ላይ እንዳለ ይቆጠራል፡፡ ይኸውም ለአክስዮን ማህበሩ ሥራ ጉዳይ ከቤታቸው ተጠርተው የሚመጡትን ሠራተኞች ያጠቃልላል፡፡ በማንኛውም ወቅት የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች በማንኛውም ቦታ ለሥራ ሲንቀሣቀሱ ለሚደርስባቸው ጉዳት በኢንሹራንስ ይሸፈናሉ፡፡
24.2 ለሠራተኛ ደህንነት ሲባል አክስዮን ማህበሩ ከኢንሹራንስ ድርጅት ጋር የሚያደርገው ስምምነት አንድ ኮፒ ለሠራተኛ ማህበር በወቅቱ ይሰጣል፡፡
24.3 በዚህ አንቀጽ መሠረት የኢንሹራንስ መብት ያለው ሠራተኛ ሁሉ ለደረሰበት ጉዳት በ24 ሰዓት ውስጥ ለፖሊስ ጣቢያ ወይም ለአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ማስመዝገብና በቂ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ ሪፖርት ለማድረግ ካልቻለ ቤተሰቡ ወይም የአደጋውን ሁኔታ ያዬ ማንኛውም ሰው በተወሰነ ሰዓት ውስጥ ለአክስዮን ማህበሩ ማመልከት አለበት፡፡ በተወሰነው ጊዜ ያልተመዘገበ ጉዳት ተቀባይነት የለውም፡፡ ለአክስዮን ማህበሩ ሪፖርት ማድረግ ካልተቻለ ከፖሊስ ጣቢያ ወይም ከአካባቢው ቀበሌ ማረጋገጫ ያቀርባል፡፡
24.4 በሥራ ላይ እያለ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የጉዳቱን ሁኔታ የክፍሉ ኃላፊና 3 /ሦስት/ ምሥክሮች ፈርመውበት ለክሊኒኩ ተረኛ ሃኪም ያስረክባል፡፡ ይኸውም በታካሚው ካርድ ላይ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
24.5 የሥራ ላይ አደጋ የደረሰበት ሠራተኛ የውሎ አበል አከፋፈል በዚህ ሕብረት ስምምነት መሠረት ይፈፀማል፡፡ ኢንሹራንስ ድርጅት በዚህ መሠረት ካልከፈለ ልዩነቱን አክስዮን ማህበሩ ይከፍላል፡፡
24.6 አደጋ የደረሰበት ሠራተኛ በኢንሹራንስ ክሌይም ምክንያት ሣይጉላላ በአፋጣኝ ተገቢውን ሕክምና እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡ የኢንሹራንስ ክሌይም በአክስዮን ማህበሩ አማካይነት ይላክለታል፡፡
24.7 በሥራ ላይ አደጋ የደረሰበት ሠራተኛ የካሣ ክፍያ
24.7.1 ከገቢ ግብር ነጻ ነው፡፡
24.7.2 ሊተላለፍ፣ ሊከበር ወይም በዕዳ ማቻቻያነት ሊያዝ አይችልም፡፡
አንቀጽ 25 የዓመት እረፍት ፈቃድ
25.1 ሠራተኛው የዓመት እረፍት ፈቃዱን የሚያገኘው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011መሠረት ሲሆን፣ ፈቃዱን በሚወስድበት ጊዜ የእረፍቱን ጊዜ ጨምሮ ለሠራበት የሚገባውን ደመወዝ ዕረፍት ከመውጣቱ በፊት ባሉት ሦስት የሥራ ቀናቶች ይከፈለዋል፡፡ በዓመታዊ ኘሮግራም ተይዞ የሚወጣ ሠራተኛ በተጠቀሰው ጊዜ ካልተከፈለው በቀጣይ ቀን ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጎ እረፍቱ ይራዘምለታል፡፡ ሆኖም ድንገተኛ /ከአቅም በላይ/ የሆነ ችግር አክስዮን ማህበሩ ካጋጠመውና ከኘሮግራም ውጭ የዓመት እረፍት ለሚወጡ ሠራተኞች ፈቃዱ አይራዘምም፡፡
25.2 ማንኛውም የዓመት እረፍት ሣይተላለፍ ወይም ሣይከፋፈል በአክስዮን ማህበሩ የሥራ ኘሮግራም መሠረት በዓመቱ ውስጥ ለሥራውና ለሠራተኛው ምቹ በሆነ ጊዜ ይሰጣል፡፡
25.3 ዓመታዊ እረፍት ፈቃድ ሊቋረጥ ወይም ሊተላለፍ ወይም ሊከፋፈል የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 79 መሠረት ነው፡፡ ሆኖም ግን ሠራተኛውና አክስዮን ማህበሩ ከተስማሙ ዓመት እረፍትን ከኘሮግራም ውጭ ለመውሰድ ይቻላል፡፡
25.4 ሠራተኛው ከኘሮግራም ውጭ የዓመት ፈቃድ ለመውሰድ የሚያስገድደው ችግር ሲያጋጥመው፣ በጽሁፍ ሲጠየቅና አሠሪው ሲያምንበት ይሰጠዋል፡፡
25.5 የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሠራተኛ የሥራ ውሉ በሚቋረጥበት ጊዜ በሕጋዊ መንገድ የተጠራቀመ የዓመት እረፍቱ ታስቦ በገንዘብ ይከፈለዋል፡፡
25.6 የዓመት እረፍት ፈቃድ መከፋፈልን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011በአንቀጽ 79.1 መሠረት እንደተጠበቀ ሆኖ ሠራተኛው የዓመት ዕረፍቱን የቅርብ አለቃው በቅድሚያ ሲፈቅድለት ከሁለት ጊዜ በላይ በማንኛውም ጊዜ እየከፋፈለ መውጣት ይችላል፡፡
25.7 አንድ ሠራተኛ ተገቢውን የዓመት እረፍት ፈቃድ ወስዶ በእረፍት ላይ እንዳለ ቢታመምና የሐኪም ፈቃድ ቢሰጠው ወይም ሴት ሠራተኛ በዓመት እረፍት ላይ እያለች ብትወልድ በፈቃዷ መጠን የዓመት ረፍት ፈቃዷ ይራዘማል፡፡ የሕመም ወይም የወሊድ ፈቃዱ ተቀባይነት የሚኖረው በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ወይም በመንግሥት የሕክምና ተቋሞች የተሰጠ ሲሆን፣ በተጨማሪም አንዲት ሠራተኛ እቤቷ ብትወልድ በእርግዝና ጊዜ ቆይታዋ በክሊኒኩ በየጊዜው የወሰደችው መረጃ መሠረት ይፈፀማል፡፡
25.8 አንድ ሠራተኛ በዓመት እረፍት ፈቃድ ላይ እያለ ሕጋዊ ጋብቻ ቢፈጽም፤ ሐዘን ቢያጋጥመውበሚያቀርበው ማስረጃ መሠረት የዓመት እረፍት ፈቃዱ መጠን ይራዘማል፡፡
25.9 አንድ ሠራተኛ በፈቃድ ላይ እያለ አሠሪው ለሥራከጠራው በመጠራቱ ምክንያት ለሚያወጣው የውሎ አበልና የትራንስፖርት ወጪ አክስዮን ማህበሩ ይሸፍናል፡፡
25.10 በዓመት ፈቃድ ላይ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ፈቃድ ሊራዘም አይችልም፡፡
አንቀጽ 26 የሕመም ፈቃድ
26.1 በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011እና በዚህ ሕብረት ስምምነት መሠረት የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ ማንኛውም ሠራተኛ ከሥራ ጋር ግንኙነት የሌለው ሕመም ቢደርስበት የሕመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ አፈጻጸሙን በተመለከተ በአንቀጽ 2ዐ.10.2 መሠረት ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ሪፈር ተብሎ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ሦስት ወራት ድረስ በሆስፒታል የተኛ ሠራተኛ የተኛበት ቀን ተቆጥሮ ሙሉ ደመወዙ ይከፈለዋል፡፡
26.1.1 ማንኛውም የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሠራተኛ በሥራ ላይ አደጋ ሣይሆን በሌላ ሕመም ሲታመም ሕመሙ ከጀመረበት የመጀመሪያ ቀን እስከ በጀት ዓመቱ መዝጊያ ድረስ በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜያት ቢወስድም በማንኛውም እስከ 12 ወር /አሥራ ሁለት ወር/ ድረስ የሕመም ፈቃድ ያገኛል፡፡
26.2 የሠራተኛውን ሕመም መርምሮ መግለጫና ትዕዛዝ የሚሰጠው ነርስና ከነርስ በላይ የሆነ ባለሙያ ነው፡፡
26.3 ከአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ውጭ ደንቡን ተከትሎ የሚሰጥ ማንኛውም የሕመም ፈቃድ ከመንግሥት የጤና ድርጅቶች በሚቀርበው ማስረጃ መሠረት ይፈፀማል፡፡
26.4 ከቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሠራተኛ በሕመም ምክንያት ከሥራ ሲቀር ለአክስዮን ማህበሩ ስለ ሁኔታው የማሣወቅ ግዴታ አለበት፡፡ ከሌሎች የመንግሥት የሕክምና ተቋሞች ለሚገኝ የሕመም ፈቃድ በማንኛውም ሁኔታ በዕለቱ በማሣወቅ ማስረጃውን በማግስቱ ላሠሪው ያሣውቃል፡፡
26.5 ኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ለማወቅ ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑ ሠራተኞች የምርመራና የትራንስፖርትወጭ 1ዐዐ% አክስዮን ማህበሩ ይሸፍናል፡፡ ምርመራውም መሣሪያው ባለበትና በቅርብ በሚገኘው የመንግስትጤና ተቋም ይካሄዳል፡፡ሆኖም ምርመራው በመንግስት የጤና ተቋም የማይሰጥ ከሆነ የህክምና ባለሙያው በሚያዘው የጤና ተቋም ይፈጸማል፡፡
26.6 በሕጋዊ መንገድ ተመርምረው ውጤት አሣይተው የኤች. አይ. ቪ. ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለ ሠራተኞች የፀረ ኤች. አይ. ቪ. መድሃኒት ሲታዘዝላቸው አክስዮን ማህበሩ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ለታካሚዎቹመድሃኒቱ የሚቀርብበትን መንገድ የሚያመቻች ሲሆን፣ ሕክምናን በተመለከተ ግን ሙሉ ወጪውን አክስዮን ማህበሩ ይሸፍናል፡፡
26.7 በሕጋዊ መንገድ ተመርምረው ኤች. አይ. ቪ. ቫይረስ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ያረጋገጡ ሠራተኞችና የካንሰር ሕመም ያለባቸው ሠራተኞች እንደማንኛውም ሕመም 5ዐ% እንዳይገቡ ሆኖ ሙሉ ደመወዛቸው ይከፈላቸዋል፡፡
26.8 አንድ ሠራተኛ ከሥራ ጋር ባልተያያዘ በሚያውቀው ሰው አደጋ ቢደርስበትና በቂ ማስረጃዎች ካሉት በአጥፊው ላይ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ለማስወሰድ ይቻል ዘንድ የሕክምና ወጪዎችን በተመለከተ ሠራተኛው እንዲሸፍን ተደርጎ አክስዮን ማህበሩ የወጪውን ማስረጃ ለሚመለከተው አካል ይጽፍለታል፡፡
አንቀጽ 27 የጋብቻ ፈቃድ
27.1 የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ ሕጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት አምስት የሥራ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት ለአንድ ጊዜ ብቻ ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ይህ ፈቃድ የሚሰጠው አግብቶ ለማያውቅ ብቻ ነው፡፡
27.2 ሠራተኛው የጋብቻ ፈቃድ ሲፈልግ ከ7 /ሰባት/ ቀን በፊት ለሚሠራበት መምሪያ /አገልግሎት/ በጽሁፍ ማሣወቅ አለበት፡፡
27.3 ሠራተኛው የጋብቻ ፈቃዱን ጨርሶ ሲመለስ ከሚኖርበት ቀበሌ ወይም ሕጋዊ ሥልጣን ከተሰጣቸው አካሎች ማለትም ከሃይማኖታዊ ተቋማት፣ ከሀገር ባህል ሽማግሌ እና ከመንግሥት አካላት በአንዱ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
አንቀጽ 28የወሊድፈቃድ
28.1 ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከእርግዝና ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ የአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ሲያዝ ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሰጣታል፡፡ ሆኖም ሠራተኛዋ ከምርመራው በኋላ የሀኪም ማስረጃ ማቅረብ አለባት፡፡
28.2 ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከመውለዷ በፊት ሐኪም እንድታርፍ ካዘዘ ከክፍያ ጋር ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
28.3 ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችው ቀን በፊት መውለጃዋ ሲደርስ የ3ዐ ቀን ተከታታይ የወሊድ ፈቃድ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 9ዐ ተከታታይ ቀናት የወሊድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል፡፡
28.4 ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ3ዐ ቀን ፈቃድ ቢያልቅ ካልወለደች እስከምትወልድበት ቀን ድረስ በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 28.2 መሠረት እረፍት ይሰጣታል፡፡ የ3ዐ ቀን ፈቃዷ ሣያልቅ ከወለደች በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 28.3 መሠረት የምትወስደው የወሊድ ፈቃድ ይጀምራል፡፡
28.5 አንዲት ነፍሰጡር የወሊድ ፈቃዷን ስትጀምር የእረፍት ጊዜ ደመወዝ በሙሉ ይከፈላታል፡፡ ደመወዟን ሣትወስድ ከወለደች በወኪል ትወስዳለች፡፡
28.6 ለነፍሰጡር ሠራተኛ ከምሽቱ 12፡ዐዐ ሰዓት እስከ ንጋቱ 12፡ዐዐ ሰዓት ሥራ መስጠትና ትርፍ ሰዓት ማሠራት የተከለከለ ነው፡፡
28.7 አንዲት የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ በማንኛውም ሁኔታ /ቦታ/ ከወለደች ለልጇ መታቀፊያየሚሆን የአክስዮን ማህበሩን ምርት ፎጣ 1ዐዐX2ዐዐ ይሰጣታል፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አክስዮን ማህበሩ ያመቻቻል፡፡
28.8 ነፍሰጡር የሆነች የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ በእርግዝና ምክንያት የምትሠራው ሥራ ለጊዜው እንዲቃለል ወይም እንዲለወጥ ሃኪም ሲያዝ ለጤንነቷ ተስማሚ የሆነ ሌላ ቀላል ሥራ ይሰጣታል፡፡
28.9 የፀነሰች የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ ጽንሱ ችግር ገጥሞት ያስወረዳት መሆኑ በሀኪምሲረጋገጥ እንደማንኛውም ሕመም ደመወዝ የሚከፈልበት የሕመም ፈቃድና ሕክምና ይሰጣታል፡፡
28.10 የፀነሰችየአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ ጽንሱ ከ7 ወር በላይ መሆኑ የተረጋገጠ የጽንስ ውርጃ ካጋጠማት የወሊድ ፈቃድ ሁለት ወር ይሰጣታል፡፡
28.11 የአክስዮን ማህበሩ ሴት ሠራተኛመፀነሧንእንዳወቀች ለአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ማስመዝገብ አለባት፡፡
28.12 በዚህ ሕብረት ስምምነት ውስጥ ያልተጠቀሱና ከሕክምና ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች፣የገንዘብ ክፍያዎችና ሌሎች ጥቅሞች ቢኖሩ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 1156/2011መሠረትና አግባብ ባለው ሕግ ይፈፀማል፡፡
28.13 አንድ ሠራተኛ ሕጋዊ ሚስቱ በወለደችበት ጊዜ ደመወዝ የሚከፈልበት የ5 ቀን የአባትነት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ በባለቤቱ ወሊድ ምክንያት ችግር ቢገጥመው ችግሩን ለመፍታት ካለው ዓመት ፈቃድ ወይም ነፃ ፈቃድ በመውሰድ መስተናገድ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሠራተኛው በዓመት እረፍት፣ በሣምንት እረፍት፣ በሕመም እረፍትና በሐዘን ፈቃድ ላይ ከሆነ ግን ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ሠራተኛው የአባትነት ፈቃድ የሚያገኘው ከሕክምና ተቋማት መረጃ ለአክስዮን ማህበሩ ሲያቀርብ ይሆናል፡፡
28.14 ሠራተኛዋ ከወለደችና ልጇን ክትባት የምታስከትብበት ጊዜ ማለትም 4ተኛ ወርና 9ነኛ ወር ላይ ፈቃድ አክስዮን ማህበሩ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን ፈቃዱ የሚሰጣት ከጤና ተቋም መረጃ ስታቀርብ ነው፡፡
አንቀጽ 29 የሐዘን ፈቃድ
29.1 ማንኛውም ሠራተኛ የትዳር ጓደኛ ወላጅና እስከ 2ኛ ደረጃ ድረስ የሚቆጠር የሥጋ ወይም የጋብቻ ዘመድ ቢሞትበት ከክፍያ ጋር ለ3 የሥራ ቀናት የሀዘን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
29.2 ሠራተኛ ሀዘን ሲደርስበት በራሱ ወይም በመልዕክት ለቅርብ አለቃውና ለክፍሉ ማሣወቅ አለበት፡፡ ሆኖም የሀዘን ፈቃዱ ተቀባይነት የሚያገኘው ፡-
ሀ/ ባስመዘገበው የቤተሰብ ዝርዝር መሠረት ይሆናል፡፡ በባል ወይም በሚስት /ከሁለት በአንዱ/ የግል ማህደር ላይ ከተመዘገበ የሐዘን ፈቃድ ይሰጣል፡፡
ለ/ ሠራተኛው የቤተሰብ ዝርዝር ካስመዘገበ በኋላ የተወለደ ቤተሰብ፣ የተወለደ የጋብቻ ዘመድ፣ የጋብቻ ዘመድ ከሞተበት ከሚመለከተው አካል በሚያቀርበው ማስረጃ መሠረት ይፈፀማል፡፡
ሐ/ አስከሬን ከቤቱ የወጣ ከሆነ ከሚመለከተው አካል በሚያቀርበው ማስረጃ መሠረት የሀዘን ፈቃዱ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
አንቀጽ 30 ለአጋጣሚ ችግር የሚሰጥ ፈቃድ
30.1 ማንኛውም ሠራተኛ ልዩና አሣሣቢ ችግር ሲያጋጥመው ደመወዝ የማይከፈልበት እስከ 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናቶች የሚደርስ ፈቃድ ሠራተኛው የሚሠራበት መምሪያ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ግን የችግሩ አሣሣቢነት ለሰው ኃ/ል/አ/መምሪያ ቀርቦ ሲያምንበት ተጨማሪ አንድወር ነፃ ፈቃድ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ሠራተኛው ተጨማሪ ነጻ ፈቃድ የሚያስፈልገው ከሆነ ለዋና ሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ሲያምንበት ፈቃዱ ሊሰጠው ይችላል፡፡
አንቀጽ 31 ለሠራተኛ ማህበር ሥራ የሚሰጥ ፈቃድ
31.1 የሠራተኛ ማህበር በማህበር ጉዳይ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አክስዮን ማህበሩን ከአንድ ቀን በፊት ፈቃድ ሲጠይቅ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣል፡፡
31.2 ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መደበኛ ስብሰባ በሣምንት አንድ ቀን ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣል፡፡በተጨማሪም ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የሥራ ፈቃድ ሠራተኛ ማህበሩ ሲጠይቅና ሲፈቀድ ይመቻቻል፡፡
31.3 ለሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር ደመወዝ የሚከፈልበት የዘወትር ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
31.4 በየክፍሉ ለሚገኙ የሠራተኛ ማህበር ምክር ቤት አባላት ከሠራተኛ ማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ጋር ለመወያየት፣ የሦስት ወር ሪፖርት ለማሰማት፣ እንደ አስፈላጊነቱ ከዚያም ውጭ በሆኑ አስቸኳይ ጉዳዬች ላይ ለመወያየት ሠራተኛ ማህበሩ በጽሁፍ ሲጠይቅ አክስዮን ማህበሩ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣል፡፡
31.5 ሠራተኞች ለፊደሬሽን እና ለኮንፌደሬሽን ተመራጭ ሲሆኑ አክስዮን ማህበሩ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ሆኖም ተመራጩ ከኩባንያው ሲሄድማንኛውንም ንብረት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ተመራጮቹም የሥራ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ ወደ አክስዮን ማህበሩ ለመመለስ ሲጠይቁ አክስዮን ማህበሩ ወደ ሥራ ይመልሣቸዋል፡፡
አንቀጽ 32 ልዩ ልዩ ፈቃዶች
32.1 አክስዮን ማህበሩ ለማንኛውም ሠራተኛ ከፖሊስ፣ ከፍርድ ቤት ወይም ሕጋዊ ሥልጣን ባለው አካል ለምሥክርነት ወይም ለአስረጅነት መጥሪያ ሲደርሰው በቅድሚያ ለአክስዮን ማህበሩ በማሣወቅና በዚህ ለመቅረቱ መረጃ ሲያቀርብ፣ የሲቪል መብቱን ለመጠበቅና የሲቪል ግዴታዎችን ለመፈፀም እንዲሁም ለሥራ ክርክር ጉዳይ ከሥራ ሲለይ ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
32.2 አንድ ሠራተኛ ከአክስዮን ማህበሩ ጋር የሥራ ክርክር ሲመሠርት ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማምጣት ይኖርበታል፡፡
32.3 በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ የሚገኙ ሹፊሮች የመንጃ ፈቃዳቸውን ለማሻሻል በሚሰጠው ፈተና ለመሣተፍ ፈቃድ ሲጠይቁ ከደመወዝ ጋር ይሰጣቸዋል፡፡ ፈተና የተሰጠው ለመሆኑ ማስረጃ ማምጣት ይኖርበታል፡፡
32.4 ማንኛውም ሠራተኛ አክስዮን ማህበሩ በሚያዘጋጀው ወይም በአክስዮን ማህበሩ አማካኝነት በሚካሄደው የሥልጠና ኘሮግራም ሲሣተፍ ወይም አክስዮን ማህበሩ አምኖበት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በሚሰጥ ሥልጠናና ሴሚናር ሲልከው ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
32.5 ማንኛውም ሠራተኛ በግሉ የሚማር ከሆነ በትምህርት ቤት ፈተና የቦታው ርቀት ከግምት ውስጥ እየገባ ፈተና ለሚወስድባቸው ጊዜያት የፈተና ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ግን ለብሄራዊ ፈተና ተፈታኞችና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተናለሚወስዱ ሙሉ ቀን ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
አንቀጽ 33 የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ
33.1 አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኛው እንደ ሥራው ፀባይ የሚያስፈልጉትን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ በዚህ ሕብረት ስምምነት በተያያዘው አባሪና የሥራና ሥልጠና መMሪያባለሙያ ጥናት መሠረት ይሰጣል፡፡
33.2 ለሠራተኛው የተሰጠው የደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ በሥራ ላይ እያለ ከሠራተኛው ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ምክንያቶች በአሲድና በመሣሰሉት ከጥቅም ውጭ ከሆነ ይህንኑ ሠራተኛው በጊዜው ለክፍል ኃላፊውና ለሚመለከታቸው በማሣየት አዲስ ይሰጠዋል፡፡
33.3 የአደጋ መከላከያዎቹ ከሚቀጥለው እደላ በፊት ችግር ቢያጋጥማቸውና ቢበላሹ በክፍሉ አሣሣቢነት በመምሪያው ተረጋግጦ ሲቀርብ አሮጌውን በማሣየት አዲሱ ይተካል፡፡
33.4 የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ በየስድስት ወሩ በመስከረምና በመጋቢት ወር ይሰጣል፡፡
33.5 ሠራተኛው የተሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ ከተመደበበት ሥራ በሥራ ሰዓት ሁሉ የመጠቀም ኃላፊነትና ግዴታ አለበት፡፡
33.6 የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ መሣሪያ በማይጠቀም ሠራተኛ ላይ በዚህ ሕብረት ስምምነት የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሣሰድ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ ሥራ ስንብት እርምጃ ይወሰዳል፡፡ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩም ሠራተኞች የሥራ ልብሱን እንዲለብሱና የአደጋ መከላከያ አልባሣት እንዲጠቀሙ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡
33.7 የሥራ ፀባያቸው ልዩነት ካላመጣ በስተቀር የሥራ ልብስ የሚሰጠው አክስዮን ማህበሩ ከሚያመርተው ጨርቅ ይሆናል፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በአክስዮን ማህበሩና በሠራተኛ ማህበሩ በጋራ ይወሰናል፡፡
33.8 የሥራ ፀባያቸው ሣሙና የሚያስፈልጋቸው ሠራተኞች አክስዮን ማህበሩ ከ2ዐዐ ግራም ያላነሰ ሣሙና ይሰጣል፡፡ ቀደም ሲል ለሠራተኛ ይሰጥ የነበረው ሣሙና እንደተጠበቀ ሆኖ የሥራ ፀባያቸው ሣሙና ለሚያስፈልጋቸው ሠራተኞች የሥራና ሥልጠና መመሪያባለሙያ በሚሰጠው አስተያየት መሠረት በአክስዮን ማህበሩ ና በሠራተኛ ማህበሩ በጋራ ይወሰናል፡፡
አንቀጽ 34 የቀብር ሥነሥርዓት
34.1 አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ አደጋ ወይም በሕመም ምክንያት ቢሞት ለተሽከርካሪ አመቺ በሆነ መንገድ አክስዮን ማህበሩ የአስከሬን ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ያቀርባል፡፡ ይህም ቤተዘመዱ በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት አስከሬኑ ወደሚደርስበት ቦታ ነው፡፡
34.2 ወደ ሆስፒታል ተልኮ የሞተን ሠራተኛ አስከሬኑ ወደሚያርፍበት ቦታ ለማጓጓዝ አክስዮን ማህበሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡
34.3 አንድ በሥራ ላይ ያለ ሠራተኛ እንዲሁም በጡረታ ከአክሲዮን ማህበሩ የተገለለ የቀድሞ ሠራተኛበሞት ሲለይ ለከፈን የሚሆን 7 ሜትር አቡጀዲድ ጨርቅ አክስዮን ማህበሩ ይሰጣል፡፡
34.4 ከሥራ አደጋ ውጭ ለሞተ ሠራተኛ የቀብር ማስፈፀሚያ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ አክስዮን ማህበሩ የሁለት ወር ደመወዙን ይከፍለዋል፡፡ ሆኖም ግን በምንም ሁኔታ ክፍያው ከብር 10,ዐዐዐ.00 /አስር ሽህ ብር/ አያንስም፡፡ ክፍያውንም በሠራተኛ ማህበሩ አማካኝነት ለቅርብ ቤተሰቦቹ በመረጃ አስፈርሞ ይሰጣል፡፡
34.5 የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ ሲሞት አክስዮን ማህበሩ የሬሣ ሣጥን ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን መውሰድ ለማይፈልጉ ብር 5ዐዐ.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በሠራተኛ ማህበሩ አማካኝነት ለሟች ቅርብ ቤተሰብ ይሰጣል፡፡
34.6 ሠራተኛው ሲሞት በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ላይ ለሚገኙ ሠራተኞችና አንድ የሠራተኛ ማህበር ተወካይ ጭምር በጠቅላላው ለ26 /ሃያ ስድስት/ ሠራተኞች ደመወዝ የሚከፈልበት የ1 ቀን /የአንድ ቀን/ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን በአንድ ቀን ደርሶ መልስ የማይቻልበት ርቀት ቦታ አስከሬኑ የሚጓጓዝ ከሆነ ደርሶ መልስ የሚፈጀው ጊዜ ብቻ ታስቦ ደመወዝ የሚከፈልበት ክፍያ የቀብር ፈቃድ ለሁለት ሠራተኞችና ለአንድ የሠራተኛ ማህበር መሪ ፈቃድ ይሰጣል፡፡
34.7 በዚህ ሕብረት ስምምነት የተወሰኑና የቀብር ሥነ ሥርዓት ለመፈፀም አስፈላጊ የሆኑትን ለማጓጓዝ አክስዮን ማህበሩ ትራንስፖርት ያቀርባል፡፡ ሆኖም ግን የሠራተኛው የቀብር ሥነ ሥርዓት ቀድሞ የተፈፀመ ከሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት አይሰጥም፡፡
34.8 የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ ሲሞት የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ ማንኛውንም የቀብር ሥነ ሥርዓት በኃላፊነት ያስፈጽማል፡፡
አንቀጽ 35ለሠራተኞችየሚሰጥየብድርአገልግሎት
35.1 አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኛው የሚሰጠው የብድር አገልግሎት የአክስዮን ማህበሩ የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያና ሠራተኛ ማህበሩ አጥንተው በሚያዘጋጁትና የአክስዮን ማህበሩ በሚያፀድቀው የብድር ኘሮግራም መሠረት ይሆናል፡፡
35.2 አክስዮን ማህበሩ ለልዩ ልዩ ለሠራተኛው የግል ችግር የሚውል ብር 3,5ዐዐ,ዐዐዐ.00 /ሦስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር / ያበድራል፡፡ የብድር አሰጣጡም ሠራተኛ ማህበሩና የሰው ኃይል ልማት አስተዳደር መምሪያ በሚያቋቁሙት የብድር ኮሚቴ አማካኝነት የሚከናወን ይሆናል፡፡ ኮሚቴው የማይሟላ ከሆነ የኮሚቴ ሰብሣቢ ወይም የሚወከለው ከሠራተኛ ማህበሩ ሊቀመንበርና ከአክስዮን ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር በመነጋገር ይሰጣል፡፡
35.3 ማንኛውም የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ ዕዳ የሌለበት መሆኑ ከተረጋገጠ በዓመት ውስጥ ተከፍሎ የሚያልቅ ከ2 ወር ደመወዙ የማይበልጥ ገንዘብ ለመበደር ይችላል፡፡
35.4 የብድር አገልግሎት የሚሰጠው በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ ከሁለት ዓመት በላይ አገልግሎት ላበረከቱ ቋሚ ሠራተኞችና ዋስ ለሚያቀርቡ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከ1ዐ ዓመት በላይ ግልጋሎት ያላቸው ሠራተኞች ዋስ አያቀርቡም፡፡
አንቀጽ 36 የካፊቴሪያ አገልግሎት
36.1 አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኛው አገልግሎት የሚሰጥ ካንቲን የአክስዮን ማህበሩ አቅም በፈቀደ መሠረት ያዘጋጃል፡፡
36.2 ዓመታዊ ጠቅላላ ዕድሣትና ለካንቲን አገልግሎት የሚውሉ ውሃና መብራት አክስዮን ማህበሩ ይችላል፡፡
36.3 የሠራተኛ ማህበሩ ለሠራተኛ የተዘጋጀው ካንቲን ውስጥ የሚገኙትን ንብረቶች ተረክቦ ያስተዳድራል፡፡
36.4 ካንቲኑን የሚመራ በሠራተኛ ማህበሩ ሥር ኮሚቴ የሚቋቋም ሲሆን፣ ለነዚሁ የኮሚቴ አባሎች አክስዮን ማህበሩ እንደአስፈላጊነቱ ሲጠየቅና ተገቢነቱን ሲቀበል ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፡፡ካንቲኑን የሚመራ አንድ ባለሙያ አክሲዮን ማህበሩ ደመወዙን ሸፍኖ ይመድባል፡፡
36.5
36.6 ማንኛውም ሠራተኛ የካንቲኑን ንብረት እንደ ግል ንብረቱ መንከባከብ ግዴታው ነው፡፡
36.7 የሠራተኛ ማህበር ከተረከበው የሠራተኛ ካንቲን በሚያገኘው ገቢ ከሕንጻው ጋር የተሰሩት ሲቀሩ የካንቲኑ የውስጥ ዕቃዎችና መገልገያዎች በሚያረጁበትና በሚበላሹበት ጊዜ የመተካት፣ የማሣደስና አሟልቶ የመያዝ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ግን የውስጥ መገልገያ ዕቃዎች በሚበላሹበት ጊዜ በአክስዮን ማህበሩ ባለሙያዎች ይጠገናሉ፡፡
36.8 የካንቲን አገልግሎት የምግብ ተመን የሚወሰነው በአክሲዮን ማህበሩና በሠራተኛ ማህበሩ ነው፡፡
36.9 የካንቲኑን አጠቃቀም በተመለከተ የነበረው የሠራተኛ ማህበር በሌላ ሲተካና በአገልግሎት መስጠት ሂደት ችግር ሲፈጠር፣ ሠራተኛን ሊጎዳ የሚችል ሁኔታ ሲታይ ወይም ካንቲኑ ሊንቀሣቀስ የማይችልበት አጋጣሚ ቢኖር ሁኔታው እስኪስተካከል አክስዮን ማህበሩ ሥራው እንዲቀጥል የማድረግና ንብረቱ ብክነት እንዳይደርስበት ሊቆጣጠር ይችላል፡፡
36.10 ለካንቲን ሠራተኞች፣ ለላም ጠባቂዎችና ለዳቦ ቤት ሠራተኞች የሥራ ልብስ የሚሆን አክስዮን ማህበሩ ከሚያመርታቸው ጨርቆች ኦቨር ኮት፣ ቱታ፣ የራስ ቆብ፣ እንደ ሥራው ፀባይ ጫማና ጓንት በየስድስት ወሩ አክስዮን ማህበሩ በነጻ ይሰጣል፡፡
36.11 የጤና ምርመራ ተደርጎላቸው ከተላላፊ ሕመም ነጻ ያልሆኑ ሠራተኞች በካንቲን እንዲሠሩ አይደረግም፡፡ ሠራተኞቹ ከተላላፊ ሕመም ነፃ መሆናቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊ በሆነበት ወቅት በአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ ያለምንም ክፍያ ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን የአክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ በካንቲን ቁጥር 1 እና 2 ለሚገኙ ሠራተኞች በየ3 ወሩ ወይም እንደአስፈላጊነቱ በየጊዜው የጤና ምርመራ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን መከታተል ይኖርበታል፡፡
36.12 በአክስዮን ማህበሩ ግቢ ውስጥ ያለውን ዳቦ ቤት ሠራተኛ ማህበሩ ያስተዳድረዋል፡፡
36.13 አክስዮን ማህበሩ ያሠራውን ባዩጋዝ ለካንቲን ቁጥር 2 ከኤሌክትሪክ ጋር አጋዥ በመሆን ግልጋሎት እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ጥገናው በአክስዮን ማህበሩ ባለሙያዎች ይሠራል፡፡ አፈጻጸሙን ደግሞ ሠራተኛ ማህበሩ ይከታተላል፡፡
አንቀጽ 37 ስፖርት
37.1 ሠራተኛው በስፖርት አካሉንና አእምሮውን ለማጎልበትና ጤናማ ዜጋ ለመሆን ያስችለው ዘንድ አክስዮን ማህበሩና ሠራተኛ ማህበሩ አቅሙ በፈቀደ የማቴሪያል፣ የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት ይተባበራሉ፡፡
አንቀጽ 38 ለሠራተኞች የሚሰጡ ዕቃዎች
38.1 አክስዮን ማህበሩ ከሚያመርተው የምርት ውጤት ለሠራተኛ የግል አገልግሎት በዓመት ለአንድ ሠራተኛ እስከ ብር 3,0ዐዐ.00 /ሦስት ሽህ ብር/ አክስዮን ማህበሩ በጅምላ ዋጋ በዱቤ ለሠራተኛው ይሸጣል፡፡ አፈጻጸሙንም አክስዮን ማህበሩና ሠራተኛ ማህበሩ በጋራ ይወስናሉ፡፡
ሀ/ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የግል አገልግሎት የሚውል 6ዐ /ስልሣ/ ኪሎ ግራም ፍራሽ ጥጥ ፊልተር ዌስት በዓመት አንድ ጊዜ አክስዮን ማህበሩ በሚወስነው ዋጋ ይሸጣል፡፡
ለ/አክስዮን ማህበሩ ከመጠቅለያ ዕቃዎች ማለትም የጥጥ መጠቅለያ ጨርቅ፣ ኬሻ፣ የጥጥ ቦንዳ ማሠሪያ ሽቦ ሽያጭ ዋጋ 1ዐዐ% ለሠራተኞች ይሰጣል፡፡ እንዲሁም የተጋቡ ዕቃዎች ማለትም ኬሚካልና ቀለማ ቀለም ማያዣ ጀሪካኖች፣ ዘይት የሚይዙ በርሜሎች ሽያጭ ዋጋ 75% ለሠራተኞች ይሰጣል፡፡ ከላይ በተገለፀው መሠረት አክስዮን ማህበሩ በየጊዜው ሽያጩን በማከናወን የተገኘውን የገንዘብ መጠን በዓመቱ መጨረሻ ላይ በዘመን መለወጫ ጊዜ ለሠራተኞች ይሰጣል፡፡ አፈጻጸሙንም መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ ይከታተላል፡፡
አንቀጽ 39 የሥነ ሥርዓት እርምጃ
ከቅጣት በፊት የሚወሰዱ እርምጃዎች
39.1 ማንኛውም ሠራተኛ ጥፋት መፈፀሙን የቅርብ አለቃው እንደተረዳ በአጥፊው ሠራተኛ ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥፋቱን ዘርዝሮና ፈርሞ ለዋና ክፍል ይልካል፡፡ ሆኖም ግን የጥፋቱ ዝርዝር ወደ ዋና ክፍል ከመላኩ በፊት በክፍሉ ውስጥ ያለ የሠራተኛ ማህበር ተወካይ /ሆርሻ/ ዝርዝር ጥፋቱን እንዲያውቀውና አስተያየቱን በመስጠት እንዲፈርምበት ይደረጋል፡፡
39.2 የአክስዮን ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የመምሪያ ሥራ አስኪያጆችና የአገልግሎት ኃላፊዎች ማንኛውም ሠራተኛ በአክስዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሥራ ላይ ጥፋት ሲፈጽም ከተገኘ በሕብረት ስምምነቱ መሠረት የሥነ ሥርዓት እርምጃ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን የመምሪያ ሥራ አስኪያጅና የአገልግሎት ሥራ አስኪያጆች ሠራተኛ /ሠራተኞች/ ጥፋት ሲያጠፉ በሚያዩበት ጊዜ አጥፊው ሠራተኛ ለሚሠራበት መምሪያ በቃል ወይም በጽሁፍ በማሣወቅ በሠራተኛው/ በሠራተኞች/ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋሉ፡፡
39.3 በዚህ ሕብረት ስምምነት መሠረት የሚወሰዱ የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች በፍርድ ቤትና በሌላ ተቋሞች ከሚወሰዱ እርምጃዎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም፡፡
39.4 እርምጃ የተወሰደበትን ሠራተኛ ወዲያውኑ ሠራተኛ ማህበሩ እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡ በተወሰደው እርምጃ ሠራተኛው ቅሬታ ካለው ሠራተኛ ማህበሩና የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ቅሬታውን በጋራ ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ፡፡
39.5 አንድ የተሟላ የሠራተኛ ጥፋት መግለጫና የቅጣት ውሣኔ ማሣወቂያ ቅጽ ጥፋቱ እንደተፈፀመ ወይም አጥፊው እንደታወቀ አስፈላጊው ሁሉ ተፈጽሞ የቅጣት ውሣኔው በሦስት ቀናት ውስጥ ለሠራተኛው እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ ሆኖም ለሠራተኛው ቅጣቱ ካልደረሰ ተቀባይነት የለውም፡፡
39.6 ሠራተኛው ምንም ጥፋት ሣይኖረው እርምጃ እንዲወሰድበት ያደረገ ኃላፊ ላቀረበው ክስ በሕብረት ስምምነቱ ወይም በሥራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 40 የዲስኘሊን ጥፋቶችና የቅጣት አወሣሰን
40.1 የዲስኘሊን ጥፋቶችና የቅጣት አወሣሰን ሂደት
40.1.1 በማንኛውም ሠራተኛ ላይ የዲስኘሊን እርምጃ የሚወሰደው ሠራተኛውን ከጥፋቱ ለማረም፣ ሥራ እንዳይበደል ለመቆጣጠርና ሌሎች ሠራተኞች ተመሣሣይ ጥፋት ከማድረግ እንዲቆጠቡ ነው፡፡
40.1.2 የዲሲኘሊን እርምጃ ከመወሰዱ በፊት የጥፋቱ ክብደትና ሠራተኛው በፊት የነበረው ፀባይ፣ መልካም አገልግሎትና ለጥፋቱ መንስኤ የሆኑት ሁኔታዎች በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው፡፡
40.1.3 የዲስኚሊን ቅጣት የሚወሰድባቸው የቅጣት ዓይነቶች ከዚህ ሕብረት ስምምነት ጋር በተያያዘው አባሪ 3/ሦስት/መሠረት የቅጣት ደረጃውን ጠብቀው ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
40.1.4 በአባሪ ያልተጠቀሱ ጥፋቶች ሲፈፀሙ የጥፋቱ ክብደት እየተመዘነ በአባሪው ከተዘረዘረው ውስጥ በተመሣሣይ ወይም በተቀራረበ አንቀጽ እርምጃ ይወሰዳል፡፡
40.1.5 ሠራተኛው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥበተለያዩ ጊዜያት በሚያጠፋቸው ጥፋቶች እርምጃ ይወሰዳል፡፡ ሆኖም ግንየተወሰደው የሥነ ሥርዓት እርምጃ አንድ ዓመት ከሞላው ቅጣቱ ይነሣለታል፡፡
40.1.6 በአንድ ጊዜ ሁለት ጥፋቶች የፈፀመ ሠራተኛ በሁለቱም ጥፋቶች ላደረሰው ጉድለት ተጠያቂ ሆኖ ከሁለት በአንዱ ከፍተኛ ለሠራው ጥፋት በሚያስቀጣው አንቀጽ ብቻ ይቀጣል፡፡
40.2 ከሥራና ከደመወዝ ስለ ማገድ
40.2.1 የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ ከባድ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ከሚሠራበት መምሪያ /አገልግሎት/ ሪፖርት ሲቀርብበትና ጉዳዩን መጣራት እንዳለበት በሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ሲታመንበት ከሰባት ቀን ላልበለጠ ጊዜ ታግዶ ጉዳዩ ይጣራል፡፡
40.2.2 አክስዮን ማህበሩ ተፈፀመ የተባለውን ጥፋት መርምሮ በሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ውሣኔውን ያሣውቃል፡፡
40.2.3 ሠራተኛው ጥፋት ያልፈፀመ መሆኑ ሲረጋገጥ ለታገደበት ጊዜ ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ሥራው ይመለሣል፡፡
አንቀጽ 41 ለደረሰ ጥፋት ተጠያቂ በመሆን ያለ ማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያስወጡ ጥፋቶች
41.1 የአክስዮን ማህበሩን ንብረት የሠረቀ ወይም ያጭበረበረ ወይም ለሥርቆት ሆን ብሎ የተባበረ ወይም ለመስረቅ ያደረገው ሙከራ በበቂና ተጨባጭ መረጃ ከተረጋገጠ፣
41.2 የአክስዮን ማህበሩን ሰነድ ያጠፋ፣ የደለዘ፣ ከሠራተኛ የግል ማህደር ውስጥ ማንኛውንም መረጃ ያጠፋ ወይም እነዚህን ጥፋቶች እንዲፈፀሙ ያደረገ ወይም ለሌላ አሣልፎ የሰጠ፣
41.3 የአክስዮን ማህበሩን የሰዓት መቆጣጠሪያ፣ የደመወዝ አበል፣ የክፍያ ሂሣብ ማዘጋጃ የምርት ምዘናና ምዝገባ፣ የምርት የጥራት ደረጃ መቆጣጠሪያ፣ የዕድገት መወዳደሪያ ነጥቦችን፣ የማነቃቂያ ክፍያንና ሌሎች ተመሣሣይ ሥራዎችን ከትክክለኛው መንገድ ውጭ ሆን ብሎ ሌላውን ሠራተኛ ሊጠቅም የሚችል ወይም ሊጎዳ የሚችል ሥራ የሠራ ወይም የአክስዮን ማህበሩን ሚስጢርና መረጃ ለሌላ አሣልፎ የሰጠ፣
41.4 በስካር መንፈስና በአደንዛዥ ዕፅ ተመርዞ ወደ ሥራ የገባ የሕክምና ባለሙያ፣ የአክስዮን ማህበሩን መኪና ያሽከረከረሹፌር፣ የምርት መሣሪያ ያንቀሣቀሰ፣ ጉዳት ያደረሰ ወይም አካባቢውን የበጠበጠማንኛውም ሠራተኛ
41.5 የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተቀበለ በኋላ ሌላ ጥፋት የፈፀመ፣
41.6 በተከታታይ አምስት የሥራ ቀናት ወይም በአንድ ወር ውስጥ በጠቅላላ ለአሥር ቀናት ወይም በአንድ ዓመት ውስጥ በጠቅላላ ለሰላሣ የሥራ ቀናት ያለ በቂ ምክንያት ከሥራ የቀረ፣
41.7 ሀሰት መሆኑን እያወቀ ሊያገኝ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ሌሎች እንዲያገኙ ለማድረግ የተሰጠውን ፈቃድ የደለዘ ወይም ከተፈቀደለት በላይ የጨመረ ወይም ፊርማ አስመስሎ የፈረመ እንዲሁም የደለዘ፣ የሌላውን ሰው ሰዓት መቆጣጠሪያ የሞላ፣ ያስሞላና በማንኛውም የሥራ ዘርፍ ሆን ብሎ ሀሰተኛ ሰነድና የሀሰት ሪፖርት ያቀረበ፣ የምርት ውጤት መቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን ለጥቅሙ ሲል ያበላሸ፣ የአክስዮን ማህበሩን መዛግብት እንዲቃወሱ ያደረገ፣ ትክክለኛ ያልሆነ ማስረጃ በማቅረብ ሥራ የተቀጠረ ዕድገት/ዝውውር/ ለማግኘት የሞከረ ወይም ያገኘ፣
41.8 በአክስዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ በተከለከለ ቦታ ሲጋራ ሲያጨስ ወይም እሣት ሲያቀጣጥል የተገኘና ለሲጋራ መለኮሻም ሆነ ለሌለ ከኤሌክትሪክ እሣት ያቀጣጠለ፣
41.9 በሥራ ሰዓት ሥራውን ትቶ ሕገወጥ በሆነ መንገድ በመሰብሰብ አድማ ሲያካሂድ የተገኘ፣
41.10 የተጣለበትን ኃላፊነት በመዘንጋት ጉቦ ወይም መደለያ የሰጠ ወይም የተቀበለ፣ እንዲሰጥ ወይም እንዲቀበል ያደረገ፣
41.11 በአክስዮን ማህበሩ ቅጥር ገቢ ውስጥና በአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች ሠርቪስ መኪና ላይ የተደባደበና ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ፣
41.12 የአክስዮን ማህበሩን ሠራተኛ የግል ንብረት ከሥራ ቦታ /ከግቢው/ ውስጥ የሰረቀ፣
41.13 የአክስዮን ማህበሩን ዕቃ በአጥር ያቀበለ፣ የሰጠና የተቀበለ፣
41.14 በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ ያልተፈቀደ የጦር መሣሪያ፣ ድምጽ ያለውም ሆነ የሌለው መሣሪያ፣ ተቀጣጣይ መሣሪያ ባልተፈቀደ ቦታ ይዞ የተገኘና ይዞ እንዲገባ የተባበረ፣
41.15 በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘትና በጥፋትም ምክንያት ለያዘው ሥራ ብቁ ወይም ታማኝ ሆኖ ያልተገኘ፣
41.16 በአክስዮን ማህበሩ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ጉዳት ያደረሰ፣
41.17 ሆን ብሎ በሥራ ቦታ ሕይወትንና ንብረትን አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት የፈፀመ፣
41.18 ሕግ ሲያስገድድ ወይም አሠሪው ሲጠይቅ የጤና ምርመር ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን፣
41.19 ስለ ደህንነት ጥበቃና ስለ አደጋ መከላከያ የወጡ የሥራ ደንቦችን አለማክበርና አስፈላጊ የሆኑትን የአደጋ መከላከያ ጥንቃቄ ለመውሰድ ፈቃደኛ አለመሆን፣
41.20 በተከታታይ ለሦስት ጊዜ የሥራ አፈጻጸሙ ከአጥጋቢ በታች የሆነና በዚሁ ጉዳይ ላይ በወቅቱ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ያላስተካከለ፣
41.21 ከ3ዐ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የእሥራት ፍርድ ተወስኖበት ከሥራ የቀረ፣
41.22 በአክስዮን ማህበሩ መሣሪያ የግል ሥራውን ሲሠራ የተገኘና ጥፋቱ በሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ የተረጋገጠ፣
41.23 በሠራተኛ ማህበርና በአሰሪው፣ ኃላፊዎች ወይም ሠራተኞች መካከል አለመግባባትና አምባጓሮ እንዲፈጠር አሉባልታና ውሸት ሲናገር የተገኘ፣
41.24 የአክስዮን ማህበሩ መገልገያ መሣሪያ /ቱልስ/ እና ልዩ ልዩ ቁሣቁስ ሥራው እንደተጠናቀቀ ለአክስዮን ማህበሩ ሣይመልስ ለግል ሥራው እንዲውል ያደረገ ወይም ያስቀረ ወይም የለወጠ ወይም ለሌላ አሣልፎ የሰጠ፣
41.25 በአክስዮን ማህበሩ አጥር ሾልኮ የገባ ወይም የወጣ፣
41.26 የጥበቃ ቦታውን ጥሎ ወይም ትቶ በመሄድ የግል ሥራውን ሲሠራ የተገኘ፣
41.27 ከአክስዮን ማህበሩ የሥራ ትዕዛዝ ውጭ በሥራ ሰዓትም ሆነ ውጭ በአክስዮን ማህበሩ ንብረት ለውጭ ሰው ወይም ድርጅት ሲሰራ ወይም ሠርቶ የተገኘ፣
41.28 በሥራ ሰዓት ሥራውን ትቶ ሕገወጥ በሆነ መንገድ ሕግና ደንብ የማይፈቅደውን ተግባር ሲፈጽም የተገኘ፣
አንቀጽ 42 የቅጣት ማንሻ ጊዜና የቅጣት ገንዘብ አጠቃቀም
42.1 በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት አንድ ሠራተኛ ጥፋት አጥፍቶ ከተቀጣበት ቀን ጀምሮ 12 ወራትከሞላው የተያዘበት የቅጣት ሪከርድ እንደተሠረዘ ይቆጠራል፡፡
42.2 በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ከሠራተኛው በቅጣት የሚሰበሰበው ገንዘብ በተለዬ ሂሣብ ተይዞ ሠራተኛ ማህበሩና አክስዮን ማህበሩ በሚስማሙበት ውሣኔ ለአክስዮን ማህበሩ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውል ቋሚ የልማት ሥራዎች ላይ ይውላል፡፡ በየሩብ ዓመቱ ምን ያህል ገንዘብ እንደተቆረጠ አክስዮን ማህበሩ ለሠራተኛ ማህበሩ ያሣውቃል፡፡ ሆኖም ግን ለደረሰው ጥፋት ሠራተኛው የሚከፍለውን ክፍያ አይጨምርም፡፡
አንቀጽ 43 የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት
43.1 አንድ ሠራተኛ ከሥራ ጋር በተያያዘ ጉዳይና በተወሰደበት የሥነ ሥርዓት እርምጃ ቅሬታ ሲሰማው ውሣኔ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ በ7 ቀን ውስጥ በሠራተኛ ማህበሩ ተወካይ በኩል ወይም እራሱ በቅድሚያ ለሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ቅሬታውን ማቅረብ አለበት፡፡
43.2 የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ቅሬታውን መርምሮ በ7 ቀን ውስጥ ውሣኔ ይሰጣል፡፡ በተሰጠው ውሣኔ ያልረካ ሠራተኛ ቅሬታውን ለዋና ሥራ አስኪያጅ ወይም ለተወካይ ማቅረብ አለበት፡፡ በውሣኔው ያልረካ በአክስዮን ማህበሩ ለተቋቋመው የግልግል ዳኞች ማቅረብ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በግልግል ዳኞች ውሣኔ ያልረካ ከሆነ ለሥራ ክርክር ችሎት ማቅረብ ይችላል፡፡
አንቀጽ 44የጋራግዴታናኃላፊነት
44.1 አክስዮን ማህበሩ እና የሠራተኛው ማህበር በመተባበር ይህንን የህብረት ስምምነት በሥራ ላይ እንዲውልና ተፈጻሚነት እንዲኖረው ተገቢውን ጥረት የማድረግ ኃላፊነትና ግዴታ አለባቸው፡፡
አንቀጽ 45 የሕጎች ውጤት
45.1 ይህ ህብረት ስምምነት ተመዝግቦ ወጪ ሆኖ ሥራ ላይ ቢውልም ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የመንግሥት ፖሊሲ ወይም ሕግን የሚቃረን ዓረፍተ ነገር፣ ቃል ወይም ሀረግ ወይም ሃሣብ በሚኖርበት ጊዜ ተቃራኒው ሀሣብ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
45.2 በህብረት ስምምነት ውስጥ የተጠቀሱ ወይም ያልተጠቀሱ ቢሆንም እንኳ ከዚህ ቀደም የወጡና የሚወጡ የመንግሥት ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ትዕዛዞች ሁሉ የዚህ ህብረት ስምምነት አካል ሆነው ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
አንቀጽ 46 የሕብረት ስምምነት አተረጓጎም
46.1 በህብረት ስምምነት ትርጉሞች ላይ የሚነሣ ማናቸውም ክርክር በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011ወይም ተሻሽሎ በሚወጣው መሠረት ይፈፀማል፡፡
አንቀጽ 47 የስምምነት ወሰን
47.1 ይህ ስምምነት በአክስዮን ማህበሩና በመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር እና ሠራተኞች መካከል ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡ ሆኖም የአክስዮን ማህበሩ የማኔጅመንት አባላትን አያጠቃልልም፡፡
47.2 የዚህ ህብረት ስምምነት አንቀጾች ከእያንዳንዱ ሠራተኛ የቅጥር ውል ጋር ተጨማሪ ውል ሆነው ይቆጠራሉ፡፡
አንቀጽ 48 የሥራ ማቆምና ማቀዝቀዝ
48.1 የሥራ ማቆምና ማቀዝቀዝበአዋጅ ቁጥር 1156/2011አንቀጽ 158፣ 159 እና 16ዐ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 49 የጋራ ምክክር
49.1 እንደአስፈላጊነቱ ሁለቱም ወገኖች የጋራ ምክክር ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
አንቀጽ 50 የማነቃቂያ ክፍያ ሥርዓት
50.1 አክስዮን ማህበሩ በጥናት ላይ የተመሠረተ የማነቃቂያ ክፍያ ሊኖረውና እንደአስፈላጊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠና ሊሻሻል ይችላል፡፡
አንቀጽ 51 ጡረታ ለሚወጡ ሠራተኞች
51.1 ማንኛውም የአክስዮን ማህበሩ ሠራተኛ በዕድሜ ከ55 እስከ 60 ዓመትጡረታ ከአክስዮን ማህበሩ ጋር ያለው የሥራ ውል በሚቋረጥበት ጊዜብር 7ዐዐዐ.00 /ሰባት ሽህ ብር/፣የአክስዮን ማህበሩ ምርት የሆነውን አንሶላ 2.1ዐ X 2.5ዐ ብዛት አንድ፣ አንሶላ 1.90 X2.50 ብዛት አንድ፣ፎጣ 1ዐዐ X 2ዐዐ ብዛት አንድ፣ ፎጣ 7ዐ X 14ዐ ብዛት አንድ እና የምሥክር ወረቀት ጋር ይሰጠዋል፡፡
አንቀጽ 52 የህብረት ስምምነቱ ፀንቶ ስለ ሚቆይበት
52.1 ይህ የሕብረት ስምምነት በሁለቱ ተዋዋዬች ተፈርሞና ለሥራና ሥልጠና መምሪያ ቀርቦ ከተመዘገበበት ከ ……………ቀን 2ዐ…. ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ዓመታት የፀና ይሆናል፡፡
52.2 ይህ የህብረት ስምምነት በሁለቱ ወገኖች ከተፈረመ በኋላ የስምምነቱ ቅጾች በተዋዋይ ወገኖች አማካኝነት ለሥራና ሥልጠና ቢሮ ለምዝገባ ይላካል፡፡
አባሪዎች
አባሪአንድ /አንቀጽ 14 በውክልና የሚሠሩ የሥራ መደቦች/
ተ.ቁ | መምሪያ | የሥራ መደብ | ደረጃ |
1 | ኢንጅነሪንግ መምሪያ | ፎርማንና ከፎርማን በላይ | XII እና ከዚያ በላይ |
2 | ግ/ን/ቁ/መምሪያ | ኬሚካል ስቶር ኪፐር | X |
የመለዋወጫ ስቶር ኪፐር | XII | ||
የተጠናቀቀ ምርት ስቶር ኪፐር | X | ||
የን/ምዝገባና ቁጥጥር ሱፐርቫይዘር | XIII | ||
የአገር ውስጥ ግዥ ሠራተኛ | X | ||
3 | ፋ/ኮስት ማ/መምሪያ | ዋና ገንዘብ ያዥ | XI |
4 | ሰ/ኃ/ል/አስተዳደር መምሪያ | ሪ/ማ/ሠ/ካሣና ጥቅማ ጥቅም | XIV |
ሠራተኛ አስተዳደር ኦፊሰር | XII | ||
የሥምሪት ኃላፊ | X | ||
5 | አ/አበባ ቅርንጫፍ | ስቶር ኪፐር | XI |
ገንዘብ ያዥ | VIII | ||
ግዥና ትራንዚተርት | X | ||
6 | ኘ/ማ/ኢ/ሲ/ አገልግሎት | የምርት ምዝገባና ክትትል ኦፊሰር | XII |
7 | ጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት | ፊዚካል ላቦራቶሪ ክፍል | XIV |
የማ/ኳሊቲ አሹራንስ ክፍል | XIV | ||
8 | ዋና ሥራ አስኪያጅ | የዋና ሥራ አስኪያጅ ፀሐፊ | XII |
9 | ፈትል መምሪያ | ፎርማንና ከዚያ በላይ | XII እና ከዚያ በላይ |
10 | ሽመና መምሪያ | ፎርማንና ከዚያ በላይ | XII እና ከዚያ በላይ |
11 | ኘ/ጋርመንት መምሪያ | ፎርማንና ከዚያ በላይ | XII እና ከዚያ በላይ |
12 | ሕክምና አገልግሎት | ሄድ ነርስ | XIII |
ማስታወሻ
ከዚህ በላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ በምርት ክፍል ቀደም ሲል በሪኘለስመንት ይሸፈኑ የነበሩ የሥራ መደቦች እንደነበሩ የሚቀጥል ሲሆን፣ ከዚህ ውጭ ያሉ የሥራ መደቦች ግን ተወካይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሚሠራበት መምሪያ ደብዳቤ ጽፎ ለዋና ሥራ አስኪያጅ በማቅረብ ሲፈቅድ ብቻ ተግባራዊ የሚሆን ውክልናአበል እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡
አባሪሁለት /አንቀጽ 33 የሥራ ልብስና አደጋ መከላከያ/
I/ሰ/ኃ/ልማትና አስተዳደር መምሪያ
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ | ||
1 | ኦቨር ኮት | ቴሌፎን ኦኘሬተር፣ የመዝገብ ቤት ሠራተኞች፣ ሰዓት ቁጥጥር፣የሪ/ማ/ሠ/ካ/ጥ/ጥ ሠራተኞች፣ ፐርሶኔል ክለርኮች፣ የሕግ ባለሙያ፣ ጠ/አገልግሎት ኃላፊ፣ ካንቲን ማናጀር፣ የመዋኛ ገንዳ ገንዘብ ያዥ | በ6 ወር | ||
ኦቨርኮትና ቱታ | ትራንስፖርት ግቢና ቢሮ ሱፐርቫይዘርና ለግቢና ውበት | በ6 ወር በማፈራረቅ | |||
2 | ነጭ ኦቨር ኮት | የሲ/ሰ/ኃ/ሥልጠና ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
3 | ቴትረን ኮት ሱሪና ሸሚዝ | ለጥበቃ ሠራተኞች፣ለሚኒሚዲያ ሠራተኛ | በ6 ወር | ||
4 | ኮት ሱሪና ሸሚዝ | የቢሮ ተላላኪዎችና ለሚኒሚዲያ ሠራተኛ | በ6 ወር | ||
5 | ቴትረን ኮት፣ሱሪ፣ ሸሚዝናቴትረን ቱታ | ለትንሽ መኪና ሹፊሮች፣ | በ6 ወር በማፈራረቅ | ||
6 | ከረባት | ለሚኒሚዲያ ሠራተኛ | በዓመት 1 ጊዜ | ||
7 | ሚኒስከርትና ሸሚዝ | ለሴት ፈታሾችና ተላላኪዎች | በ6 ወር | ||
8 | ቆዳ ጫማ | ተላላኪዎች፣ ሴት ፈታሾች፣ የሪስክ ማኔጅመንት የኢንሹራንስና የሥራ ልብስ እደላ ለሚሠራ፣ ሥልጠና ማዕከል አሠልጣኞችና ኢንስፔክተር አቴንዳንስ ክለርክ፣ ለጽዳት ሠራተኞች፣ ለግቢና ቢሮ ሱፐርቫይዘርና ለትንንሽ መኪና ሹፊሮች፣ ማባዣና ፎቶ ኮፒ ሠራተኛ፣ የማቃጠያ ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
ለላይብራሪ ሠራተኛና ለመዝገብ ቤት ሠራተኞች ፐርሶኔል ክለርክ ሠራተኞች፣ለሪ/ማ/ጥ/ጥ/ ኃላፊ፣ ለጠ/አገልግሎት ኃላፊ ለህክምና ሄድ ነርስ፣ ነርስ፣ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን፣ፋርማሲ ቴክኒሽያን፣ካርድ ክለርክ፣የክሊኒክ አስተዳደራዊ ክለርክ፣የመዋኛ ገንዳ ሠራተኞች |
በ1 ዓመት | ||||
9 | የወታደር ጫማ | ለጥበቃ ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
1ዐ | የዝናብ ልብስ | ለጥበቃ ሠራተኞች፣ እግረኞችና ፖስተኛ የመ/ቤት ሠራተኛ | በ3 ዓመት 1 ጊዜ | ||
11 | ከሹራብ የተሠራ ቱታ | ለጥበቃ ሴት ሠራተኞች | በዓመት 1 ጊዜ | ||
12 | ካልሲ | ለጥበቃ ወንድ/ሴት ሠራተኞች፣ ለትንሽ መኪና ሹፊሮች | በ6 ወር | ||
13 | የሹራብ ጓንት | ለጥበቃ ሴት ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
14 | የቆዳ ጓንት | ለጽዳትና አትክልተኛ ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
15 | ሣሙና | ለጥበቃ ሠራተኞች በሙሉ፣ ለማሠልጠኛ ማዕከል አሠልጣኞችና ኢንስፔክተር፣ ለመ/ቤት፣ ፐርስኔል፣ ካ/ጥ/ጥ ሠራተኞች፣ ግቢና ቢሮ ትራንስፖርት ሱፐርቫይዘር፣ ለጽዳትና በአትክልተኝነት ለተሠማሩ ሠራተኞች፣ ሹፊሮች፣ ተላላኪዎች፣ማባዣ ማሽን ኦኘሬተር ቤተ ንባብ ሠራተኛ፣ ለክሊኒክ ሠራተኞች፣ለሚኒ ሚዲያ ሠራተኛ፣ለመዋኛ ገንዳ ሠራተኞች፣ | በወር 1 ጊዜ | ||
ለክሊኒኩ ለአንሶላና ገዋን ማጠቢያ | በወር 1ዐ እንደአስፈላጊነቱ | ||||
16 | የገላ ሣሙና | ለሕይወት አዳኝና ረዳቱ፣ ለሕክምና ባለሙያዎች | በወር 1 ጊዜ | ||
17 | ኦሞ | ለክሊኒኩ | በወር 12 | ||
18 | ከሸራ የተሠራ ቀበቶ | ለጥበቃ ሠራተኞች ቅ/ጽ/ቤትን ጨምሮ | በዓመት 1 ጊዜ | ||
19 | የእጅ ባትሪ | ለጥበቃ ሠራተኞች ባለ ቻርጅ ባትሪ | በ1 ዓመት 1 ጊዜ | ||
2ዐ | ቱታ | ማባዣ ማሽን ኦኘሬተር፣ የቢሮና መፀዳጃ ቤት ጽዳት ሠራተኛ፣ የግቢ ጽዳትና የአትክልተኛ ኃላፊ፣ | በ6 ወር | ||
ለመዋኛ ገንዳ ሠራተኞች | በአመት አንድ ጊዜ | ||||
21 | ቦትና ቆዳ ጫማ | በአትክልተኛነት ለተሠማሩ ሠራተኞችና ለመዋኛ ጽዳት ሠራተኛ | በ6 ወር በማፈራረቅ | ||
ቦት ጫማ | ለማቃጠያ ሠራተኞች ብቻ | በአመት አንድ ጊዜ | |||
22 | ካፖርት /የብርድ መከላከያ/ | ለወንድ የጥበቃ ሠራተኞች | በ3 ዓመት 1 ጊዜ | ||
23 | ኘላስቲክ ጓንት | ለጽዳት ሠራተኞች፣ ለመዋኛ ገንዳ ሠራተኞች፣ ማባዣና ፎቶ ኮፒ ሠራተኛ | በ6 ወር | ||
24 | የጨርቅ ማክስ | ለሁሉም ሠራተኞች | በሚያልቅበት ጊዜ | ||
25 | የጨርቅ ቆብ | ለሁሉም ጽዳት ሠራተኞች፣ አትክልተኞችና እንደሥራው ባህሪ እየታዬ ለሚያስፈልጋቸው ሠራተኞች | በ6 ወር 1 ጊዜ ሆኖ እንዳስፈላጊነቱ እየታዬ የጊዜ ገደቡ ይወሰናል፡፡ | ||
26 | የዋና ፓንት | ለሕይወት አዳኝና ለረዳቱ | በ6 ወር 2 | ||
27 | ሲሊፐር ነጠላ ጫማ | ለሕይወት አዳኝና ለረዳቱ | በአመት 2 | ||
28 | ስፖርት ቱታ | ለሕይወት አዳኝና ረዳቱ | በ6 ወር | ||
29 | ዣንጥላ | ለእግረኛና ፖስተኛ የመዝገብ ቤት ሠራተኛ ተላላኪ | በአመት 1/አንድ/ ጊዜ | ||
30 | ቦርሳ | ለእግረኛና ፖስተኛ የመዝገብ ቤት ሠራተኛ ተላላኪ | በ3 ዓመት አንድ ጊዜ | ||
31 | ኬሚካል ማስክ | ለህይወት አዳኝ ሠራተኞች | በአመት አንድ ጊዜ |
II/ ሕክምና አገልግሎት
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ | ||
1 | ነጭ ኦቨር ኮት ቴትረን | ለሕክምና አገልግሎት ባለሙያዎች | በ6 ወር | ||
2 | ነጭ ኦቨር ኮት ካኪ | ላቦራቶሪ ጽዳትና ተላላኪ፣ አስተዳደራዊ ክለርክ፣ ካርድ ክለርክ፣ ምዝገባና ቁጥጥር ክለርክ | በ6 ወር | ||
3 | ቀሚስ /ናይለን/ | ለሕክምና አገልግሎት ጽዳት ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
4 | ቆዳ ጫማ | ለሕክምና አገልግሎት ጽዳት ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
5 | ኘላስቲክ ጓንት | ለሕክምና አገልግሎት ጽዳት ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
6 | ኘላስቲክ ሽርጥ | ለማዋለጃ ክፍል ብዛት 3 /ሦስት/ | በ1 ዓመት | ||
(Apron) ለጽዳት ሠራተኞች | በ6 ወር |
III/ ግዥና ንብረት ቁጥጥር መምሪያ
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ | ||
1 | ኦቨር ኮትና ቱታ | መለዋወጫ ስቶር ኪፐር፣ ስቶር ክለርክ፣ አይተም ፒከር፣ የተጠናቀቀ ምርት ስቶር ኪፐር | በ6 ወር /በማፈራረቅ/ | ||
ኦቨር ኮት | የጥጥ መጋዘን ስቶር ኃላፊ፣ | ከብርድ መከላከያ የሹራብ ቱታ ጋር በ6 ወር በማፈራረቅ | |||
2 | ኦቨር ኮት፣ ሚኒስከርትና ሸሚዝ | ጽዳትና ተላላኪዎች | በ6 ወር በማፈራረቅ | ||
ሚኒስከርትና ሸሚዝ | ለቤል ስቶር ጽዳትና ተላላኪ | ከብርድ መከላከያ የሹራብ ቱታ ጋር በ6 ወር በማፈራረቅ | |||
3 | ካኪና ቴትረን ቱታ | ቤል ስቶርና ኬሚካል ስቶር ሠራተኞች፣ዕቃ ግ/ቤት ጉልበት ሠራተኞች | በ6 ወር በማፈራረቅ | ||
4 | ካኪ ኮትና ሱሪ፣ ሸሚዝ፣ ቴትረን ቱታ | ለከባድ መኪና ሹፊሮች | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ | ||
5 | ቴትረን ቱታ | ዲዝል ፎርክሊፍት ኦኘሬተር፣ ክሬን ኦኘሬተር | ከብርድ መከላከያ የሹራብ ቱታ ጋር በ6 ወር በማፈራረቅ | ||
6 | ካልሲ | ለከባድ መኪና ሹፊር | በ6 ወር | ||
7 | ቆዳ ጫማና ሴፍቲ ሹዝ | ከባድ መኪና ሹፊሮች | በ6 ወር በማፈራረቅ | ||
8 | ቆዳ ጫማ | የቢሮ ጽዳት ሠራተኞች፣ የጥጥ መጋዘን ስቶር ኪፐር፣ ኬሚካል ስቶር ኪፐር፣ የመለዋወጫ ስቶር ኪፐር፣ ማጠናቀቂያ ስቶር ኪፐር፣ ክሬን ኦኘሬተር፣ ዲዝል ፎርክሊፍት ኦኘሬተር፣ ስቶር ክለርክና ረዳት ስቶር ኪፐር፣ ጉልበት ሠራተኛ፣ አይተም ፒከር፣ፐርቸዘር | በ6 ወር | ||
የን/አስተዳዳር ዋ/ክ ኃላፊ፣ትራንዚተር፣ ንብረት ምዝገባና ቁጥጥር ሱፐር ቫይዘር | በዓመት 1 ጊዜ | ||||
9 | ሣሙና፣ ማስክ፣ የጨርቅ ቆብ | በአመት አንድ ጊዜ ለሚከናወነው የንብረት ቆጠራ ላይ ለሚሠማሩ ሠራተኞች በሙሉ | በዓመት 1 ጊዜ | ||
10 | ካኪ ኦቨር ኮት | ለንብረት ቁጥጥር ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
11 | ሣሙና | ለሁሉም ስቶር ሠራተኞች፣ ለከባድ መኪና ሹፊሮች፣ ክሬንና ፎርክሊፍት ኦኘሬተሮች፣ ለሀገር ውስጥ ዕቃ ግዥ ሠራተኛ | በወር 1 ጊዜ | ||
12 | የጨርቅ ማስክ | ለን/ቁ/ ሠራተኞች በሙሉ | በ3 ወር ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ እየታዬ | ||
13 | የማይከ ማስክ | ለዕቃ ግ/ቤት ሠራተኞች፣ እንደ ሥራው ባህሪ | በ6 ወር | ||
14 | የጨርቅ ቆብ | ለመለዋወጫ ስቶር ሠራተኞች | በ6 ወር ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ የሚታይ | ||
15 | ኘላስቲክ ጓንት | ለሁሉም የጽዳት ሠራተኞች | በ6 ወር | ||
16 | የሹራብ ጓንት | ለመለዋወጫ ስቶር ሠራተኞች | በየ6 ወር | ||
17 | የገንዘብና ሰነድ መያዣ ቦርሣ | ለሀገር ውስጥ ግዥ ሠራተኛ | ማለቁ እየታዬ | ||
18 | የብናኝ መከላከያ መነጽር | የጥጥ መጋዘን ሠራተኞች | በ6 ወር አንድ ጊዜ | ||
19 | የብርድ መከላከያ ሹራብ | የጥጥ መጋዘን ሠራተኞች | ከኦቨር ኮት፣ ለሴቶች ሚኒስከርት ጋር በማፈራረቅ በየ6 ወሩ |
IV/ ኦዲት አገልግሎት
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ | ||
1 | ኦቨር ኮት | ለሲኒየር ኦዲተርና ኦዲተር | በ6 ወር |
V/ ፋይናንስ መምሪያ
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ | ||
1 | ሣሙናና ማስክ | ለገንዘብ ያዥና ለደመወዝ ከፋዬችና ለፋይናንስ ሠራተኞች በሙሉ | በወር 1 | ||
2 | የጨርቅ ቆብ | በቆጠራ ላይ ለሚሠማሩ ሠራተኞች | እንደአስፈላጊነቱ | ||
3 | ካኪ ኦቨር ኮት | በቆጠራ ለሚሠማሩ ሠራተኞችና ለገንዘብ ያዦች | በዓመት 1 ጊዜ |
VI ኘላንና ማኔጅመንት ኢ/ሲ/አገልግሎት
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ | ||
1 | ኦቨር ኮት | ሲስተምና ኔት ወርክ አድሚኒስትሬተር፣ ኢቫሉዌሽን ኦፊሰር፣ ደሊቨሪ ክለርክ፣ ቴክኒካል ኘላኒንግና ኮንትሮል ሄድ ቴክኒካል ኢንስፔክሽንና ስታፍ አሲስታንት | በ6 ወር | ||
2 | ሣሙናና ማስክ | ለቴክኒካል ስታፍ አሲስታንቶች፣ለኮምፒውተር ባለሙያዎች | በየወሩ 1 ጊዜ | ||
3 | ቆዳ ጫማ | ቴክኒካል ስታፍ አሲስታንቶች | በየ 6 ወሩ | ||
የተጠናቀቀ ምርት ደሊቨሪ ክለርክ ፕ/ሞ/ዋና ክፍል ኃላፊ፣ ቴ/ፕ/ኮንትሮል ሄድ፣ምርት ክ/ግ/ኦፊሰር |
በዓመት 1 ጊዜ | ||||
4 | ሴፍቲ ጫማ | የፕ/ማ/ኢ/ሲ ዋና ክፍል ኃላፊ፣ ሲስቴም ኔት ዎርክ አድንሚስትሬቶር፣ ማ/ኢ/ሲ ኤክስፐርት፣ | በዓመት 1 ጊዜ | ||
5 | የእጅ ጓንት | የፕ/ማ/ኢ/ሲ ዋና ክፍል ኃላፊ፣ ሲስቴም ኔት ዎርክ አድንሚስትሬቶር፣ ማ/ኢ/ሲ ኤክስፐርት፣ | በየ 6 ወሩ | ||
6 | የፊት መሸፈኛ ጭምብል | የፕ/ማ/ኢ/ሲ ዋና ክፍል ኃላፊ፣ ሲስቴም ኔት ዎርክ አድንሚስትሬቶር፣ ማ/ኢ/ሲ ኤክስፐርት፣ | በ2 ዓመት 1 ጊዜ |
VII/አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ |
1 | ኦቨር ኮት | ሽያጭ ሠራተኞች፣ ገንዘብ ያዥ | በ6 ወር |
2 | ኦቨር ኮት ካኪና ቴትረን ቱታ | ስቶር ኪፐር | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
3 | ቴትረንና ካኪ ቱታ | ለጫኝና አውራጅ | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
4 | ኮት ሱሪና ሸሚዝ | አ/አበባ ላሉ የጥበቃ ሠራተኞች ሾፊሮችና ተላላኪዎች /ወንድ/ | በ6 ወር |
5 | ሚኒስከርትና ሸሚዝ | ተላላኪና ጽዳት ሠራተኞች /ሴት/ | በ6 ወር |
6 | ካልሲ | ለጥበቃ ሠራተኞችና ሹፊሮች | በ6 ወር |
7 | ቆዳ ጫማ | ጽዳትና ተላላኪዎች፣ ሹፊሮች፣ ስቶር ኪፐር፣ ጫኝና አውራጆች፣ የሀገር ውስጥ ግዥ ሠራተኛ | በ6 ወር |
ትራንዚተር | በዓመት 1 ጊዜ | ||
8 | የወታደር ጫማ | አዲስ አበባ ጥበቃ ሠራተኞች | በ6 ወር |
9 | የገንዘብና ሰነድ መያዣ ቦርሣ | ለሀገር ውስጥ ግዥ ሠራተኛ | ማለቁ እየታዬ |
VIII/ ጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ |
1 | ነጭ ኦቨር ኮት | የማጠናቀቂያና ኳሊቲ አሹራንስ ክፍል ኃላፊ፣ የፊዚካል ላቦራቶሪ ክፍል ኃላፊ፣ ክሎዝ ሱፐርቫይዘር፣ ፈትል ኳሊቲ ቴስተር፣ ኘሮሰሲንግ ጋርመንት ቴስተር፣ ሽመና ኳሊቲ ቴስተር፣ ክሎዝ አናላይዘር፣ ሽመና ዝግጅት ኳሊቲ ኮንትሮል፣ አጣፊና አሻጊ፣ ሌብሊንግ ኢንስፔክተር፣ ኳሊቲ ክለርክ፣ ግሬይ ክሎዝ ኳሊቲ ኢንስፔክተር፣ ግሬይ ክሎዝ ሜንደሮች፣ ዳታ ኢንኮደር፣ የተጠናቀቀ ምርት ኳሊቲ ቸከርና ሜንደር | በ6 ወር |
2 | ቱታና ኦቨር ኮት | የተቀለመና የታተመ ኳሊቲ ቼከርና ሜንደር ደብሊንግና ፎልዲንግ ኦኘሬተሮች ከነረዳቶቻቸው፣ አጣፊና አሻጊ ምልክት አስገቢ፣ | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
3 | ቱታ | አጣፊና ለኪ ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው ክሎዝ አሬንጀር ሌብለር ስታምፐር | በ6 ወር |
4 | ኮት፣ሱሪና ሸሚዝ ሚኒስከርትና ሸሚዝ፣ ቱታ | የቢሮ ተላላኪና ጽዳት | በ6 ወር በማፈራረቅ |
5 | ኦቨር ኮት | ሾርት ፒስ ሶርተርና አሬንጀር፣ ሜንደርና ኳሊቲ ቸከር | በ6 ወር |
6 | ከጥጥና ከወፍራም ካውንት የተሠራ የእግር ሹራብና የሹራብ ቱታ | ግሬይ ክሎዝ ኢንስፔክሽን ሱፐርቫይዘር፣ ኢንስፔክሽን አጣፊና ለኪ ኦኘሬተርና ረዳት፣ ክሎዝ አሬንጀር፣ ኳሊቲ ቸከር፣ ደብሊንግና ፎልዲንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳት፣ ኘ/ጋርመንት ሾርት ፒስ ሶርተርና አሬንጀር አጣፊና አሻጊ፣ ሌብሊንግ ኢንስፔክተር፣ የታተመና የተቀለመ ኳሊቲ ቸከር፣ ግሬይ ክሎዝ ሜንደር ኳሊቲ ክለርክ ሠራተኞች | በ1 ዓመት |
7 | የሹራብ ቱታ | የታተመና የተቀለመ ኳሊቲ ቸከርና ሜንደር ሠራተኞችየተጠናቀቀ ምርት ኳሊቲ ቼክርና ሜንደር ሠራተኛ | በ1 ዓመት |
8 | ኘላስቲክ ጓንት | ኘሮሰሲንግ ጋርመንት ቴስተር ሌብልና ስታምፐር | በየ6 ወሩ |
9 | ሣሙና | ለሁሉም ለምርት ጥራት ሠራተኞች፣ ቢሮ ጽዳትና ተላላኪ፣ ፊዚካል ኳሊቲ አሹራንስ ሄድ፣ ፈትል ኳሊቲ ቴስተርና ክላሲፋየር | በወር 1 |
1ዐ | መነጽር/አይጎግል/ | ኢንስፔክሽን ሜንደር ሠራተኞች | በየ6 ወር |
መነፀር | የተጠናቀቀ ምርት ኢንስፔክሽን ኦኘሬተሮች/የብርሃን ነጸብራቅ በመኖሩ/ | በህክምና ውሳኔ | |
11 | ቆዳ ጫማ | ፈትልና ሽመና ጥራት ተቆጣጣሪ ሠራተኞች፣ የሽመና ኢንስፔክሽን የፎልዲንግ ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ጥሬ ጨርቅ ሰፊ ሠራተኞች፣ ትራንስፖርተርክሎዝ አሬንጀር ሠራተኞችና ግሬይ ክሎዝ ኢንስፔክተር፣ የታተመና የተቀለመ ኳሊቲ ቸከርና ሜንደር ኦኘሬተሮች ከነረዳቶቻቸዉ፣ የተጠናቀቀ ምርት ኳሊቲ ክለርክ፣ ቼከርና ሜንደር ሠራተኞች፣ ደብልና ፎልዲንግ ኦኘሬተሮች ከነረዳቶቻቸው፣ ግሬይ ክሎዝ ክለርክ፣ | በየ6 ወር |
አስተዳደራዊ ክለርክ | በ1 ዓመት |
IX / ኢንጅነሪንግ መምሪያ
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ |
1 | ኦቨር ኮት | የመካኒካል ወርክሾኘ ቲም ሊደር፣ የሕንጻ ኮንስትራክሽን ክፍል ኃላፊ፣ ፎርማኖችና ቲም ሊደሮች፣ ሲኒየር ኤሌክትሮኒክስና ኢንስትሩሜንቴሽን ቴክኒሽያን፣ ኤሌክትሮኒክስና ኢንስትሩሜንቴሽን ቴክኒሽያን፣ ኦፊስና አቴንዳንስ ክለርክ | በየ6 ወር |
2 | ኦቨርኮት ሸሚዝ፣ኮትና ሱሪ ሚኒስከርትና ሸሚዝ | ተላላኪዎች /ወንድና ሴት/ | በየ6 ወር በማፈራረቅ |
3 | ቱታ | ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ሞተር ዋይንደር እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር አናጺ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ኤሌክትሪሽያን እስከ ረዳቶቻቸው፣ የእንፋሎት ማመንጫና የአየር ማመቻቻ ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ማሽኒስት እስከ ጁኒየር ማሽኒስት፣ ከሲኒየር በያጅ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ኮምኘሬሰርና ዲያተርሚንግ ቦይለር፣ ኮስቲክ ሶዳ አቴንዳንት ሄልፐርና ክሊነር፣ ግንበኛና ቀለም ቀቢ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ውሃ ማጣሪያና ቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ አቴንዳንት፣ ዲዝል ጀኔሬተር ኦኘሬተር፣ ሣተላይት ስቶር ኪፐር፣ ወርክሾኘ ጽዳት ሠራተኛ | በየ6 ወር |
4 | ቴትረን ቱታ | ጋራዥ ሲኒየር መካኒክ እስከ ጁኒየር መካኒክና ረዳቶቻቸው፣ሲኒየር አውቶ ኤሌክትሪሽያን እስከ ጁኒየር አውቶ ኤሌክትሪሽያንና ረዳቶቻቸው፣ ፓወር ኘላንት አቴንዳንት ሠራተኞች | በየ6 ወር |
5 | ቆዳ ጫማና ሴፍቲ ጫማ | ቲም ሊደር፣ ፎርማኖች፣ ሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ማሽኒስት እስከ ጁኒየር ማሽኒስት፣ ከሲ/አውቶ መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ሞተር ዋይንዲንግ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ኤሌክትሪሽያን እስከ ጁኒየር ኤሌክትሪሽያንና ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር አናጽ እስከ ረዳቶቻቸው ግንበኛና ቀለም ቀቢ እስከ ረዳቶቻቸው የእሣት አደጋ ተከላካይ መኪና ሹፌር፣ ዲዝል ጀኔሬተር አቴንዳንቶች፣ ዲያተርሚክ ኮምኘሬሰርና ቦይለር ኮስቲክ ሶዳ አቴንዳንት፣ ሣተላይት ስቶር ኪፐር ሠራተኛ | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
ሴፍቲ ጫማ | ኤሌክትሪክ ዋ/ክፍል ኃላፊ፣ የድጋፍ ሰጪ ዋ/ክ/ኃላፊ፣ መካኒካል ወርክ ሾኘ ክፍል ኃላፊ፣ | በዓመት 1 ጊዜ | |
ቆዳ ጫማ | አስተዳደራዊ ክለርክ | በዓመት 1 ጊዜ | |
6 | ቆዳ ጫማ ቡትስ ባለ ዚኘ ሶሉ ከፍ ያለ | ከሲኒየር በያጅ እስከ ረዳቶቻቸው፣ የእሣት አደጋ ተከላካይ ፈረቃ ኃላፊዎችና የእሣት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞችና የእሣት አደጋ ሹፌሮች | በየ6 ወር |
7 | የፋውንደሪ ጫማ /ሴፍቲ ሹዝ/ | ለፋውንደሪ ሠራተኞችና ረዳቶቻቸው | በ1 ዓመት |
8 | ካልሲ | ለእሣት አደጋ መከላከያ መኪና ሹፌር | በየ6 ወሩ |
9 | ኮት ሱሪና ሸሚዝ | ለእሣት አደጋ ተከላካይ መኪና ሹፌር | በየ6 ወር |
10 | ብርቱካናማ ቱታ | ለእሣት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች | በየ6 ወር |
11 | የዝናብ ልብስ | ለወተር ትሪትመንት፣ ዌስት ዋተር አቴንዳንትና ፓወር አቴንዳንት፣ ዲያተርሚክ ቦይለርና ኮምኘሬሰር አቴንዳንት፣ በር ላይ ያሉየእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች | በ3 ዓመት 1 ጊዜ |
12 | የኘላስቲክ ቦት ጫማና ቆዳ ጫማ | የቧንቧና የውሃ ማጣሪያ የቆሻሻ ውሃና የእሣት አደጋ ፎርማን፣ ውሃ ማጣሪያ አቴንዳንት፣ቆሻሻ ውሃ አቴንዳንት ውሃ ማጣሪያ ቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ ቧንቧ ጥገና ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸውና የጽዳት ሠራተኞች | በየ 6 ወሩ በማፈራረቅ |
13 | የአፍና የአፍንጫ ማስክ | ለሁሉም የኢንጅነሪንግ ሠራተኞች | በ3 ወር ሆኖ /እንደአስፈላጊነቱ እየታዬ የሚሰጥ/ |
14 | ኬሚካል ማስክ | የውሃ ማጣሪያ አቴንዳንት | በየ 6 ወር |
15 | ኘላስቲክ ሽርጥ | ወተር ትርትመንትና ቀለም ቀቢና ረዳቶቻቸው | በየ6 ወር |
ለጋራዥ ሠራተኞች | በ2 ዓመት | ||
16 | ቆዳ ጓንት | እስቲም ውስጥ ለሚሠሩ ከሲኒየር መካኒክ እስከ ቴክኒካል ሄልፐር፣ የአየር ማመቻቻ ፎርማን እስከ ቴክኒካል ሄልፐር፣ የወለል ጽዳት፣ ኘላምቢንግ ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው ከሲኒየር ማሽኒስት እስከ ጁኒየር ማሽኒስት፣ ወርክሾኘ ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ዌልደር እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ኤሌክትሪሽያን እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ሞተር ዋይንዲንግ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ፓወር ኘላንት አቴንዳንት፣ ኮምኘሬሰር ዲያሜትሪክ፣ ቦይለርና ኮስቲክ ሶዳ አቴንዳንት፣ ጋራዥ ሠራተኞች ከሲኒየር እስከ ረዳቶቻቸው፣ በእንፋሎት ላይ ወይም ከእንፋሎት ጋር ግንኙነት ባለው ሥራ ላይ ለማሠሩ ሠራተኞች የአሣት አደጋ ሠራተኞች፣ | በየ 6 ወሩ |
17 | ቆዳ ጓንት እስከ ክንድ የሚደርስ | ለፋውንደሪ ሠራተኞችና ረዳቶቻቸው፣ | በየ 6 ወሩ |
18 | ኘላስቲክ ጓንት | ወተር ትርትመንት አቴንዳንት፣ የቆሻሻ ውሃ አቴንዳንት፣ ውሃ ማጣሪያና ቆሻሻ ውሃ ማጣሪያና ቧንቧ ጥገና ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር አውቶ መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር አውቶ ኤሌክትሪሽያን እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ማሽኒስት እስከ ጁኒየር ማሽኒስት፣ ቀለም ቀቢዎችና ረዳቶቻቻውና ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የሥራ መደብ ላይ የሚሠሩ የቀን ሠራተኞች የእሣት አደጋ ሠራተኛ | በየ6 ወር ለዌስት ዋተር አቴንዳንት ሆኖ ባለቀ ጊዜም ይሰጣል |
19 | ቆዳ ሽርጥ | ከሲኒየር ዌልደር እስከ ረዳቶቻቸው፣ የፋውንደሪ ሠራተኞች ረዥም ሆኖ በጀርባ የሚታሰር | በየ 6 ወር |
2ዐ | የጨርቅ ቆብ | ለሁሉም የኢንጅነሪንግ ሠራተኞች | በየ6 ወሩ ሆኖ /እንደ አስፈላጊነቱ እየታዬ/ |
21 | ሄልሜት | ለፋውንደሪ ሠራተኞች ከነረዳቶቻቸው | ሲያልቅ እየታዬ |
22 | የአይን መነጽር /አይ ጎግል/ | የቆሻሻ ውሃ አቴንዳንት፣ የውሃ ማጣሪያና የቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ አቴንዳንት፣ የአየር ማመቻቻ ፎርማን እስከ ረዳቶቻቸው፣ ኮምኘሬሰር ዲያተርሚክ ቦይለርና ኮስቲክ ሶዳ አቴንዳንት፣ ጽዳት ሠራተኞች፣ ውሃ ማጣሪያና ቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ ቧንቧ ጥገና ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ማሽኒስት እስከ ጁኒየር ማሽኒስት፣ ከሲኒየር አናጺ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር ሞተር ዋይንዲንግ እስከ ረዳቶቻቸው፣ እንፋሎት ማመንጫ ሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ጋራዥ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ኤሌክትሪሽያኖች፣ ወርክሾኘ ከሲኒር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ጽዳት ሠራተኞችና ወለል ጽዳት መካኒካል ወርክሾኘ ለሚሠሩ ሠራተኞች በሙሉ የእሣት አደጋ ሠራተኞች | በየ 6 ወር |
23 | ጎግል በራስ የሚጠለቅ | ለበያጆች | በ6 ወር |
24 | ኦሞ 2ዐዐ ግራም | ኢንጅነሪንግ አውቶ ሾኘና ማ/ወርክ ሾኘ | በወር 1 ጊዜ |
25 | ሣሙና | ኦሞ ከሚሰጣቸው ውጭ ላሉ የኢንጅነሪንግ ሠራተኞች | በወር 1 ጊዜ |
26 | የድምጽ መከላከያ | አየር ማመቻቻ፣ ቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ፣ እንፋሎት ማመንጫ፣ እንጨት ሥራና ቧንቧ ጥገና ሠራተኞች | በየ3 ወሩ |
27 | የሹራብ ቱታ | ኤሌክትሪክ ቦይለር ሠራተኞች፣ዌስት ዋተር አቴንዳንት፣ውሃ ማጣሪያ አቴንዳንት፣የተርማል ቦይለር ሠራተኞች፣ የፓወር ፕላንት አቴንዳንቶች | በዓመት 1 ጊዜ |
28 | የእጅ ባትሪ | የፓወር ፕላንት አቴንዳንቶች | በ 1 ዓመት አንድ ጊዜ |
X/ ም/አሠራር ማሻሻያ አገልግሎት
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ |
1 | ኦቨር ኮት | አ/አ/ማ/አ እና ለምርምርና ስርፀት ሠራተኞች በሙሉ | በየ6 ወር |
2 | ቆዳ ጫማ | አ/አ/ማ/አ እና ለምርምርና ስርፀት ሠራተኞች፣ ካይዘን ኦፊሰር፣ | በአመት 1 ጊዜ |
3 | ሣሙና | አ/አ/ማ/አ እና ለምርምርና ስርፀት ሠራተኞች፣ ካይዘን ኦፊሰር | በወር 1 ጊዜ |
XI/ ፈትል መምሪያ
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ |
1 | ኦቨር ኮት | የፈረቃ ምርት ኃላፊና ፎርማኖች፣ ያርን ስቶር ክለርክ፣ ዳታ ኢንኮደርና ኦፊስ ወርከር፣ ፈትል ኳሊቲ ቴስተር፣ ምርት መዝጋቢዎችና የጥገና ፎርማን፣ፈትል መምሪያ ለሚሠሩ ሴት ሠራተኞች | በ6 ወር /ለቴስተሮች ነጭ ኦቨር ኮት/ |
2 | ቱታ | የሽንት ቤት ጽዳት ሠራተኛ፣ ብሎዊንግ ማሽን ፊደር፣ ቆሻሻ ጥጥ ማጣሪያ አቴንዳንት፣ ዌስት ከተን ፓከርና ቤል አሬንጀር፣ ካርዲንግ ማሽን ኦኘሬተር፣ ድሮዊንግ ፍሬም ኦኘሬተር፣ ሮቪንግ ፍሬም ኦኘሬተር፣ ሮቪንግ ክሊነር፣ ፍሎር ክሊነር፣ ኦኘን ኢንድ ኦኘሬተር፣ ሮለር ክሊነር፣ ቀጭን ፈታይ ኦኘሬተር፣ ፈትል ወለል ጽዳት፣ ቀጭን ፈታይ ቦቢን ትራንስፖርተርና ሶርተር፣ ዋይንዲንግና አውቶ ኮነር ማሽን ኦኘሬተር፣ ዋይንዲንግ ትራንስፖርተርና ኮኘስ አሬንጀር፣ ትዊስቲንግ ማሽን ኦኘሬተር /ወንድና ሴት/፣ ትዊስቲንግ ትራንስፖርተርና ኮን አሬንጀር/ወንድና ሴት/ ሪሊንግ ማሽን ኦኘሬተር፣ ሪሊንግ ፓከርና ሪከርደርስ፣ ሪሊንግ ፓከር ሄድ፣ ሲኒየር መካኒክ እስከ ጁኒየር መካኒክ፣ ከሲ/ኤሌክትሪሽያን እብከ ጁ/ኤሌክትሪሽያን፣ ሣተላይት ስቶር ኪፐር | በየ6 ወር |
ፊልተር አቴንዳንትና ዌስት ፓከር ሠራተኞ፣ ሄድ ቤል ሰኘላይና ሪከርድስ፣ | በየ3 ወር | ||
3 | ኘላስቲክ ቦት ጫማ | ለመፀዳጃ ቤት ጽዳት ሠራተኞች | በየ6 ወር |
ለሠለጠኑ የእሣት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች | በየ2 ዓመት | ||
4 | ከጥጥ የተሠራ ካልሲ | የአራባ ማሽን ኦኘሬተሮች /አሻጊዎች/ | በየ6 ወር |
5 | ኮት፣ሱሪና ሸሚዝ ሚኒስከርትና ሸሚዝ | ተላላኪዎች /ወንድ/ሴት/ | በየ6 ወር |
6 | ቆዳ ጫማና ሴፍቲ ጫማ | ፈረቃ መሪና ምርት ፎርማኖች፣ ጥገና ፎርማን፣ ፈትል ከሲኒየር መካኒክ እስከ ጁኒየር መካኒክ፣ የምርት መዝጋቢ፣ ቆሻሻ ጥጥ ማጣሪያ አቴንዳንት፣ዌስት ከተን ቤል አሬንጀር፣ ካርዲንግ ማሽን ኦኘሬተር፣ ድሮዊንግ ፍሬም ኦኘሬተር፣ ሮቪንግ ፍሬም ኦኘሬተር፣ ሮቪንግ ክሊነር፣ ፈትል ፍሎር ክሊነር፣ ኦኘን ኢንድ ኦኘሬተር፣ ሮለር ክሊነር፣ ቀጭን ፈታይ ኦኘሬተር፣ ቀጭን ፈታይ ቦቢን ትራንስፖርተርና ሶርተር፣ ዋይንዲንግና አውቶ ኮነር ማሽን ኦኘሬተር፣ ዋይንዲንግ ትራንስፖርተርና ኮኘስ አሬንጀር፣ ትዊስቲንግ ማሽን ኦኘሬተር፣ ትዊስቲንግ ትራንስፖርተርና ኮን አሬንጀር፣ ሪሊንግ ማሽን ኦኘሬተር፣ ሪሊንግ ፓከርና ሪከርድስ፣ ሪሊንግ ፓከር፣ ሄድ ቤል ሰኘላይና ሪከርድስ ተላላኪ፣ ሣተላይት ስቶር ኪፐር፣ ፈትል ኳሊቲ ቴስተር፣ ብሎይንግ ማሽን ፊደር፣ ከኤሌክትሪክ ፎርማን እስከ ጁ/ኤሌክትሪሽያን፣ | በየ6ወሩ በማፈራረቅ |
ሴፍቲ ጫማ | የፈትል ጥገና ዋ/ክ/ኃላፊ፣ የምርት ኃላፊ፣ያርን ስቶር ክለርክ፣ | በዓመት 1 ጊዜ | |
ቆዳ ጫማ | አስተዳደራዊ ክለርክ | በዓመት 1 ጊዜ | |
7 | የቆዳ ጓንት | ዌስት ፓከር፣ ሮቪንግ ኦኘኒንግ ኦኘሬተር፣ ብሎዊንግ ማሽን ፊደር፣ ዌስት ሶርተርና ኮሌክተር ሮለር ፒከር ካርዲንግ ላይ ለሚሠሩ ከሲ/መካኒክ እስከ ጁ/መካኒክ | በየ6 ወር |
8 | የአፍና የአፍንጫ ማስክ | ለሁሉም የፈትል መምሪያ ሠራተኞች | በ1 ወር ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ |
9 | ሣሙና | ሣኒቴሪ አቴንዳንት፣ ብሎዊንግ ማሽን ፊደር፣ ካርዲንግ ማሽን ኦኘሬተር፣ የወለል ጽዳት፣ ጣራ ጽዳት፣ ፊልተር አቴንዳንት፣ብሎይንግ ማሽን ከሲ/መካኒክ እስከ ጁ/ መካኒክና ካርዲንግ ማሽን ከሲ/ መካኒክ እስከ ጁ/መካኒክ | በ2 ወር 3 |
ዌስት ከተንና ፓከር ቤል አሬንጀርና ፊልተር አቴንዳንት ሠራተኞች | በወር 2 | ||
ከላይ ሣሙና ከሚሰጣቸው ውጭ ላሉት የፈትል ሠራተኞች በሙሉ | በወር 1 ጊዜ | ||
10 | የጨርቅ ቆብ | ለሁሉም የፈትል መምሪያ ሠራተኞች | በ3 ወር ሆኖ /እንደ አስፈላጊነቱ/ |
11 | የድምጽ መከላከያ | አክራሪ ማሽን፣ ኦኘን ኢንድና ድሮዊንግ አዲሱ ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች | በየ3 ወር |
12 | የአይን መነጽር /ጎግል/ | ቀጭን ፈታይ ኦኘሬተር፣ ዌስት ፓከር፣ ሮቪንግ ኦኘኒግ፣ ብሎዊንግና ካርዲንግ ኦኘሬተር፣ ማሽን ፊደር ዌስት ሶርተርና ኮሌክተር፣ ሮለር ክሊነርና ድሮዊንግ ፍሬም ኦኘሬተር | በየ6 ወር |
13 | ኘላስቲክ ጓንት | ለመፀዳጃ ቤት ጽዳት ሠራተኞች | በየ6 ወር |
14 | የጤና ምርመራ | ዌስት ፓከር ፊልተር አቴንዳንት፣ ዌስት ፓከር አሬንጀርና ለሌሎችም ሠራተኞች አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ እየተጠና ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡ | በየ3 ወር |
XII/ ሽመና መምሪያ
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ |
1 | ኦቨርኦቨር ኮት | ዳታ ኢንኮደርና ኦፊስ ወርከር፣ ኘሮዳክሽን ክለርክ፣ ዊቪንግ ኘሪፓራቶሪ ኳሊቲ ቼከር፣ ሉምሸድ ክሎዝ ኢንስፔክተር፣ ዊቪንግ ኘሪፓራቶሪ ሱፐርቫይዘርና ፎርማን፣ ዊቪንግ ሽፍት ኘሮዳክሽን ሄድና ፎርማን፣ ሽሪንግና ኢንስፔክሽን ሄድ፣ ግሬይ ክሎዝ ሜንደር፣ ኤሌክትሪክና ጥገና ፎርማን፣ ለሽመና መምሪያ ሴት ሠራተኞች | በ6 ወር ሉም ሸድ ክሎዝ ኢንስፔክተርና ኘሪፓራቶሪ ኳሊቲ ቸከር /ነጭ ኦቨር ኮት/ |
2 | ቱታ | ሪዋይንዲንግ፣ ዋርፒንግ፣ ሣይዚንግ፣ ዋርኘ ታይንግ ማሽን አኘሬተር፣ ዋርፒንግ ማሽን ሄልፐር፣ ዋርፒንግ ትራንስፖርተር፣ ሣይዚንግ፣ ዋርኘ ታይንግ ማሽን ሄልፐር፣ ሣይዚንግ ሚክሰር፣ ፎልስ ሰልቬጅ ስፑል ዋይንደር፣ ፍሎር ክሊነር፣ ቢም ሴተር፣ ዊቨር አሲስታንትና ማሽንና ፍሎር ክሊነር፣ ኮን ትራንስፖርተር፣ ሰኒተሪ አቴንዳንት፣ ሽሪንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር እስከ ጁኒየር ኤሌክትሪሽያን፣ ሉም ሸድ ከሲኒየር እስከ ጁ/መካኒክ፣ ዝግጅት ሲ/መካኒክ እስከ ቴክኒካል ሄልፐር፣ ኢንስፔክሽን መካኒክ፣ ጁ/መካኒክ፣ ቴክኒካል ሄልፐር፣ ጁ/ ዌልደር፣ ሣተላይት ስቶር ኪፐር ድሮወርና ሪደር | በየ6 ወር |
3 | ቴትረን ቱታ | ክላችና ብሬክ ሽፍት ከሲ/መካኒክ እስከ ቴክኒካል ሄልፐር፣ክላችና ብሬክ ከሲ/መካኒክ እስከ ቴ/ሄልፐር | በየ6 ወር |
4 | ቆዳ ጫማና ሴፍቲ ጫማ | ኘሮዳክሽን ክለርክ፣ ኦፊስ ቦይና ገርል፣ ዊቪንግ ኘሪፓራቶሪ ኳሊቲ ቸከር፣ ሉምሸድ ክሎዝ ኢንስፔክተር፣ ዊቪንግ ኘሪፓራቶሪ ሱፐርሻይዘርና ፎርማን፣ ሪዋይንዲንግና ዋርፒንግ ማሽን ኦኘሬተር፣ ሄልፐርና ትራንስፖርተር፣ ሣይዚንግ ማሽን ኦኘሬተርና ሄልፐር፣ ሚክሰር፣ ድሮወር ኤንድ ሪደር፣ ፎልስ ሰልቬጅ ስፑል ዋይንደር፣ ፍሎር ክሊነር፣ ሽፍት ኘሮዳክሽን ሄድና ፎርማኖች፣ ዋርኘታይንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ቢም ሴተር፣ ዊቨርና አሲስታንት፣ ማሽን ክሊነር፣ ፍሎር ክሊነር፣ ኮን ትራንስፖርተር፣ ሄድሽሪንግና ኢንስፔክሽን፣ ሽሪንግ ማሽን ኦኘሬተርና ሄልፐር፣ ኤሌክትሪክ ከፎርማን እስከ ጁኒየር ኤሌክትሪሽያን፣ ሽፍት ሲ/መካኒክ፣ ሲ/ መካኒክ እስከ ጁ/ መካኒክ፣ ፎርማን ሉምሸድ፣ ሽፍት ሲ/ መካኒክ፣ ሽፍት ሲ/ መካኒክ ክላችና ብሬክ፣ ሲ/ መካኒክ ክላችና ብሬክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ሽፍት ጁ/ መካኒክ ሴንትራል ሉብሪኬሽን ሪድ ጠጋኝ፣ ኢንስፔክሽን መካኒክ፣ ጁ/ ዌልደር፣ ጁ/ መካኒክ፣ ቴክኒካል ሄልፐር፣ ሽመና ዝግጅት ከሲ/መካኒክ እስከ ቴክኒካል ሄልፐር፣ ሣተላይት ስቶር ኪፐር፣ኢንስፔክሽን ክሎዝ ሜንደር ኦኘሬተር | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
ሴፍቲ ጫማ | የሽመና ጥገና ዋ/ክ/ኃላፊ፣ ምርት ኃላፊ፣ | በአመት 1 ጊዜ | |
ቆዳ ጫማ | አስተዳደራዊ ክለርክ | በአመት 1 ጊዜ | |
5 | ቆዳ ጓንት | ሣይዚንግ ማሽን ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው ሪድ ጠጋኝ፣ ክላችና ብሬክ ከሲ/መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ቢም ሴተር | በየ6 ወር |
6 | ኘላስቲክ ጓንት | ሣይዚንግ ማሽን ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ | በ1 ዓመት |
ሽመና ዝግጅት የመፀዳጃ ቤት ጽዳት ሠራተኞች | በየ6 ወር | ||
7 | የአፍና የአፍንጫ ማስክ | ለሁሉም የሽመና መምሪያ ሠራተኞች | በ3 ወር ሆኖ /እንደአስፈላጊነቱ/ |
8 | የጨርቅ ቆብ | ለሁሉም የሽመና መምሪያ ሠራተኞች | በ6 ወር ሆኖ /እንደአስፈላጊነቱ/ |
9 | አይ ጎግል /መነጽር/ | ለሣይዚንግ ማሽን ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ራፒየር መካኒኮች፣ ክላችና ብሬክ ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ፒካኖል፣ ዶርኒየር፣ ሱልዘር ሲ/መካኒኮችና መካኒኮች | በየ6 ወር |
1ዐ | ኘላስቲክ ቦት ጫማ | ለመፀዳጃ ቤት ሠራተኞች | በየ6 ወር |
ለሠለጠኑ የእሣት አደጋ ሠራተኞች | በ2 ዓመት | ||
11 | ሣሙና | ኦሞ ከሚሰጣቸው ውጭ ላሉ የሽመና መምሪያ ሠራተኞች | በወር 1 |
12 | ኬሚካል ማስክ | ለሣይዚንግ ሠራተኞች በሙሉ | በየ6 ወር |
13 | የጆሮ መከላከያ | ለሽመና ሠራተኞች በሙሉ | በየ3 ወር |
14 | ከጥጥና ከወፍራም ካውንት የተሠራ ቱታና የእግር ሹራብ | ሽሪንግና ክሮፒንግ ማሽን ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ግሬይ ክሎዝ ኢንስፔክሽን ሠራተኞች | በዓመት 1 ጊዜ |
15 | ኦሞ 4ዐዐ ግራም | ክላችና ብሬክ፣ሱልዘርና ሽመና ኢንስፔክሽን ጥገና ለሚሠሩ ሠራተኞች | በወር 1 |
16 | ኦቨርኮት፣ሸሚዝና ሚኒስከርት | ኦፊስ ቦይና ገርል | በየ6 ወር በማፈራረቅ |
17 | የሹራብ ቱታ | በሣይዚንግ ማሽን አካባቢ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ለዋርፒንግ ሠራተኞች | በዓመት 1 ጊዜ |
18 | መነፀር | የጥሬጨርቅኢንስፔክሽንኦኘሬተሮች¼የብርሃንነፀብራቅበመኖሩ¼ | በህክምናውሳኔ |
XIII/ ኘ/ጋርመንት መምሪያ
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ |
1 | ኦቨር ኮት ካኪ | ዳታ ኢንኮደርና ኦፊስ ወርከር፣ ኘሮዳክሽን ክለርክ፣ ቤሊንግ ሄድ፣ የምርት ፀሐፊ፣ ጋርመንት ፎርማን | በ6 ወር |
2 | ኦቨርኮት ሸሚዝና ሚኒስከርት | ኦፊስ ቦይና ገርል | በየ6 ወር በማፈራረቅ |
3 | ቴትረን ቱታና የሹራብ ቱታ | ክሊነርና ሰኒተሪ አቴንዳንት፣ ፎርክሊፍት ኦኘሬተር፣ ሲንጅንግና ዲሣይዚንግ፣ ስኮሪንግና ሃይቴኘሬቸር ዳይንግ፣ ብሊቺንግ፣ ወሽንግ፣ መርሠራይዚንግና ስሊንደር ድራየር፣ ድራይንግ፣ ሆት ፍሉ ኤንድ ፓድ ስቲም ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ኬሚካል ዋየርና ኘሪፔረር፣ ከለር ኤንድ ኬሚካል ዌየር ኘሪፔረር፣ ጅገር ዳይንግ ኦኘሬተር፣ ኮልደፓድ ባች ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ሶፍት ፍሎው ማሽን ኦኘሬተር፣ ታምብለር ድራየር ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ኘሪንቲንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ኘሪንቲንግና ስክሪን ሜከር ሄልፐር፣ ፖሊመራይዚንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ስቴንተሪንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ካላንደሪንግና ሽሪንግ ኘሩፍ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር እስከ ጁኒየር ኤሌክትሪሽያን፣ ሽፍት ሲ/መካኒክ እስከ ቴ/ሄልፐር፣ ጥገና ከሲ/መካኒክ እስከ ቴ/ሄልፐር | በየ6 ወር በማፈራረቅ |
4 | ቱታ ካኪ | ቤሊንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ፍራሽ ሰፊና ከላይ ከተገለፁት የሥራ መደቦች ውጭ የሆኑና የሥራ ልብስ ከታዘዘላቸው ውጭ ላሉት ሠራተኞች በሙሉ | በየ6 ወር |
5 | ቆዳ ጫማ | አንሶላ ቆራጭና ቤል ኘሬስ ኦኘሬተሮች፣ የጋርመንት ፎርማኖችና ተላላኪ፣ ሣተላይት ስቶር ኪፐር የሥራ ልብስ ሰፊዎች፣ሰፊዎች፣ አጣፊና አሻጊ፣ ቤል ሄድ፣ | በየ6 ወር |
5 | ሴፍቲ ጫማ | ለጥገና፣ ለኘሮሰሲንግ፣ ጋርመንት ዋና ክፍል፣ | በ1 ዓመት |
ቆዳ ጫማ | አስተዳደራዊ ክለርክ | በ1 ዓመት | |
6 | ቴትረን ኦቨር ኮት | ለመምሪያ ኃላፊ፣ ለጥገና እና ምርት ኃላፊ ኬሚስት፣ አስተዳደራዊ ከለርክ | በየ6 ወር |
7 | ሴፍቲ ጫማና ኘላስቲክ ቦት ጫማ | ለማሽን ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ትሬስ፣ ስክሪን ሜከርና ረዳቶቻቸው፣ ቀለምና ኬሚካል አዘጋጅና መዛኝ፣ ሊፍት ትራክ ኦኘሬተር፣ የወለል ጽዳት፣ ኬሚካል ዌየር አዘጋጅ፣ ኮስቲክ ሶዳ ዲዞልቨር፣ ኘሮሰሲንግ የፈረቃ ኃላፊዎችና ፎርማኖች፣ ከጥገና ፎርማን እስከ ቴክኒካል ሄልፐር፣ ዲዛይነር፣ ኬሚስት፣ ኳሊቲ ቴስተር | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
8 | የሹራብ ቱታ፣ ኦቨር ኮት ቴትረን | ሄድ ሽፍት ኘሮዳክሽን ኘሮሰሲንግ፣ ኘሪትሪትመንት ፎርማን፣ ዳይንግ ኘሪንቲንግ ኤንድ ፋይናል ፊኒሽንግ ፎርማን፣ ጥገና ፎርማን፣ ኤሌክትሪክ ፎርማን | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
9 | ቴትረን ቱታ፣ የሹራብ ቱታ | ዲዛይነር፣ ስክሪን ሜከር | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
1ዐ | ሸሚዝና ሱሪ ካኪ ባለ ማንገቻ /ለወንድ/ | ለጋርመንት ሠራተኞች፣ ልብስ ቆራጭ ሠፊና ስቲቸር ሌሎች ጋርመንት ውስጥ ላሉና ሌላ የሥራ ልብስ ለማይሰጣቸው ሠራተኞች | በየ6 ወሩ |
11 | ካኪ ሸሚዝና ሚኒስከርት/ለሴት/ | ለጋርመንት ሠራተኞች ልብስ ቆራጭ፣ ልብስ ሰፊና ስቲቸር ውስጥ ላሉና ሌላ የሥራ ልብስ ለማይሰጣቸው ሠራተኞች፣ | በየ6 ወሩ |
12 | የጨርቅ ቆብ | ለሁሉም የኘሮሰሲንግና ጋርመንት ሠራተኞች በሙሉ | በየ6 ወሩ |
13 | ኬሚካል ማስክ | ኬሚስት፣ ቀለምና ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ እስቴንተሪንግ ኦሬተርና ረዳቶቻቸው ጅገር ኦኘሬተር፣ ኮስቲክ ሶዳ ዲዞልቨር፣ ሊፍት ትራክ ኦኘሬተር፣ ሲሊንደር ድራይንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው ኬሚካል ዌር አዘጋጅ | በየ6 ወሩ |
14 | ኘላስቲክ ቦት ጫማ | ሰቴንተሪንግ ኦኘሬተሮች እና ረዳቶቻቸው፣ ብሊችንግ ኦኘሬተር እና ረዳቶቻቸው፣ መርሠራይዚንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ወሽንግ ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ሲሊንደር ድራይንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ሆት ፍሉ ኤንድ ፓድስቲም ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ጅገር ዳይንግ ኦኘሬተር፣ ኘሪንቲንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ካላንደሪንግ ሽሪክ ኘሩፍ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ፖሊመራይዚንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ሶፍት ፍሉና ቴምብለር ድራየር ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ | በየ 6 ወር |
15 | ኘላስቲክ ሽርጥ | ኬሚስት፣ ዲዛይነር፣ ትሬሰር፣ እስከሪን ሜከርና ረዳቶቻቸው፣ ስቴንተሪንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ሆትፍሉ ኤንድ ፓድስቲም ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ጅገር ኦኘሬተር፣ ኘሪንቲንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ሊፍት ትራክ ኦኘሬተር ሲሊንደር ድራየር ማሽን ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ | በዓመት 1 ጊዜ |
ቀለምና ኬሚካል አዘጋጅና መዛኝ፣ ብሊቺንግ ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ወሽንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ኘሪንቲንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ኮስቲክ ሶዳ ዲዞልቨር፣ መርሠራይዚንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ | በየ6 ወር | ||
16 | መነጽር /አይ ጎግል/ | ዲዛይነር፣ ስክሪን ሜከርና ረዳት፣ ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ፣ ኮስቲክ ሶደ ዲዞልቨር፣ መርሠራይዚንግ ዲዛይን ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ጅገር ዳይንግ ኦኘሬተርና ትሬሰር፣ ስቴንተሪንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ሲሊንደር ድራየር ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ፖሊመራይዚንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ሊፍት ትራክ ኦኘሬተር፣ ወለል ጽዳት፣ ሲንጅንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ጅገር ዳይንግ ኦኘሬተር፣ ሆት ፍሉ ፓድ ስቲም ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ስኮሪንግና ወሽንግ ማሽን ኦኘሬተሮች፣ ቀለምና ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ፣ ሶፍት ፍሉው ኦኘሬተርና ኮልድ ፓድ ባች ኦኘሬተር፣ ኘሮሰሲንግ ጥገና ላይ ያሉ ሠራተኞች በሙሉ | በየ6 ወር |
17 | ኘላስቲክ ጓንት | ዲዛይነር፣ ቀለምና ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ፣ ሲንጅንግና ዲሳይዚንግ ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ስክሪን ማሽን ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው፣ ብሊቺንግ ማሽን ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ወሽንግ ኦኘሬተር እና ረዳቶቻቸው፣ ኘሪንቲንግ ማሽን ኦኘሬተር እና ረዳቶቻቸው፣ እስቴንተሪንግ ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ሽሪንግ ኘሩፍ ኦኘሮተሮችና ረዳቶቻቸው፣ ፓኪንግ ኦኘሬተርና ትሬሰር፣ እስክሪን ሜከርና ረዳቶቻቸው፣ ሊፍት ትራክ ኦኘሬተር፣ ፖሊመራይዚንግ ኦኘሬተርና ረዳት፣ የወለል ጽዳት፣ ሆት ፍሉና ፓድ ስቲም ኦኘሬተርና ረዳት፣ ኮስቲክ ሶዳ ዲዞልቨር፣ መርሠራይዚንግ ማሽን ኦኘሬተርና ረዳት፣ ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ፣ ሶፍት ፍሎው ኦኘሬተር፣ ኮልድ ፓድ ባች ኦኘሬተር፣ | በየ 6 ወር |
ኘላስቲክና ቆዳ ጓንት | ብሊችንግና ወሽንግ ሠራተኞች | እንዳለቀ ይሰጣል | |
18 | ቆዳ ጓንት | ከሲኒየር መካኒክ እስከ ረዳቶቻቸው፣ ለስክሪን ሜከር፣ዲዛይነር | በየ6 ወር |
19 | ሣሙና | ለኘሮሰሲንግና ጋርመንት ሠራተኞች በሙሉ | በየ ወሩ እንደአስፈላጊነቱ |
2ዐ | የዝናብ ልብስ | ሶፍት ፍሎው ማሽን ኦኘሬተሮችና ረዳቶቻቸው፣ | በ3 ዓመት |
21 | የድምጽ መከላከያ | ቀለምና ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ | በየ6 ወሩ |
22 | የጤና ምርመራ የሚያስፈልጋቸው | ቀለምና ኬሚካል መዛኝና አዘጋጅ፣ ጅገር ኦኘሬተር፣ ኮስቲክ ሶዳ ዲዞልቨር፣ ሊፍት ትራክ ኦኘሬተር፣ ጅገር ዳይንግ ኦኘሬተርና ረዳቶቻቸው እና ወደፊት እንደ ሥራው ፀባይ እየተጠና የሚያስፈልጋቸው የጤና ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡ | በየ3 ወር |
23 | ቴትረን ኦቨር ኮትና የሹራብ ቱታ | ኳሊቲ ቴስተሮች | በየ6 ወሩ በማፈራረቅ |
24 | የሹራብ ቱታ | ቤሊንግ ሠራተኞች፣አስተዳደር ክለርክና ሰዓት ቁጥጥር፣ ቤሊንግ ጽዳት ሠራተኞች | በዓመት 1 ጊዜ |
25 | ሌዘር ሽርጥ | ለስክሪን ሜከር፣ዲዛይነር | በ3 ዓመት 1 ጊዜ |
26 | የብርሃን መከላከያ መነጽር | ለስክሪን ሜከር፣ዲዛይነር | በህክምና ውሳኔ |
IXማርኬቲንግ መምሪያ
ተ.ቁ | የሥራ ልብስ ዓይነት | የሥራ መደብ | የሚሰጥበት ጊዜ |
1 | ኦቨር ኮት | የሱቅ ሽያጭ ሠራተኛ | በ 6 ወር |
2 | ቆዳ ጫማ | የሱቅ ሽያጭ ሠራተኛ | በአመት አንድ ጊዜ |
3 | የጨርቅ ሳሙና | የሽያጭ ክፍል ኃላፊ፣ s!¼¥Rk@tENG x@KSpRT XÂ ¶sRcR½የሱቅ ሽያጭ ሠራተኛ | በየወሩ |
4 | የቆዳ ጫማ | የማርኬቲንግ ዋና ክፍክ ኃላፊ | በአመት አንድ ጊዜ |
5 | ስትራይቭ ኦቨር ኮት | የሽያጭ ክፍል ኃላፊ፣ s!¼¥Rk@tENG x@KSpRT XÂ ¶sRcR½ | በ 6 ወር |
ማሳሰቢያ፣
- የሴፍቲ ጫማ በሚያገኙ ክፍሎች ላሉ ሴት ሠራኞች የሚሠጣቸው የሥራ ጫማ ቆዳ ጫማ መሆኑ ይታወቅ፡፡
አባሪሦስት /አንቀጽ 40 ሌሎች ጥፋቶችና የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች/
ተ.ቁ | የጥፋት ዓይነት | 1ኛ ደረጃ ቅጣት | 2ኛ ደረጃ ቅጣት | 3ኛ ደረጃ ቅጣት | 4ኛ ደረጃ ቅጣት | 5ኛ ደረጃ ቅጣት |
1 | ያለበቂ ምክንያት እስከ 15 ደቂቃ ዘግይቶ የደረሰ ወይም ቀድሞ የወጣ | የቃል ማስጠንቀቂያ | ¼ኛ ቀን ደመወዝ | ½ኛ ቀን ደመወዝ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
2 | ያለ በቂ ምክንያት ½ ቀን የቀረ | ¼ኛ ቀን ደመወዝ | ½ኛ ቀን ደመወዝ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ1 ½ኛ ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
3 | ያለበቂ ምክንያት ያለፈቃድ 1 ቀን የቀረ | ½ ቀን ደመወዝ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
4 | ያለበቂ ምክንያት በተከታታይ 2 ቀን ያለ ፈቃድ የቀረ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
5 | ያለበቂ ምክንያት በተከታታይ 3 ቀን ያለፈቃድ የቀረ | የ1 ½ ቀን ደመወዝ | የ2 ½ ቀን ደመወዝ | የ3 ½ ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
6 | ያለበቂ ምክንያት በተከታታይ 4 ቀን ያለፈቃድ የቀረ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝ አና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||
7 | ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ ምክንያት የሥራ ቦታን ትቶ የሄደ | የ1/2 ቀን ደመወዝ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
8 | ከሥራ ሰዓት ውጭ ያለፈቃድ ያለበቂ ምክንያት ፋብሪካው ግቢ መግባት | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
9 | ሀ/ በአደንዛዥ ዕጽ በሥካር መንፈስ ተመርዞ ወደ ሥራ የመጣ |
የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||
ለ/ አደንዛዥ እጽ ወደ ሥራ ይዞ የመጣ ማንኛውም ሠራተኛ |
የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||
10 | ሀ/ በማንኛውም በአክስዮን ማህበሩ መሣሪያዎች ተሽከርካሪዎች ወይም ንብረቶች ላይ በቸልተኝነት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ጥፋቱ በሠራተኛው |
የ3 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||||
ለ/ በማንኛውም የአክስዮን ማህበሩ መሣሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎች |
የ1 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |||
11 | ሀ/ በሣምንት እረፍት ቀንና በሕዝብ በዓላትትርፍ ሰዓት እንዲሠራ ተጠይቆ ከተስማማ በኋላ መቅረት | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
ለ/ በአዋጅ ቁጥር 67በተቀመጠው መሠረት የትርፍ ሰዓት እንዲሠራ ታዞ አለመፈጸም | የ1/2 ቀን ደመወዝ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
12 | በሥራ ላይ ሆኖ ሌሎች ሠራተኞች የተሣደበ | የ1 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ | የ5ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
13 | ሀ/ የተሰጠውን የሥራ ትዕዛዝ ወይም መመሪያ |
የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
ለ/ የተሰጠውን የሥራ ትዕዛዝ ባለመፈፀሙ ለደረሰው |
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
14 | በተሰጠው ሥራ ላይ ስህተት ወይም ጥፋት ሲደርስ እያወቀ ለተቆጣጣሪው አለማሣወቅ፣ | የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
15 | በማይመለከተው ሥራ ገብቶ መኪናዎችን ወይም ሌሎች መሣሪያዎችን ወይም ዕቃዎችን ያለፈቃድ የሚነካ፣ የሚያነሣ ወይም የሚጠቀም ወይም የግል ሥራ የሠራ ወይም ሲሠራ የተገኘ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
16 | በአክስዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ማንኛውም ሠራተኛ ተገቢውን ንጽህና ሣይጠብቅ ከተፈቀደለት ቦታ በስተቀር የመፀዳዳት ተግባር የፈፀመ ወይም ተገቢውን ጽዳት የሚያበላሽ፣ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
17 | በሚያሽከረክረው መኪና ላይ የደረሰውን ግጭት የደበቀ ሾፊር ለጥፋቱ ተጠያቂ በመሆን፣ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
18 | በሥራ ላይ ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ ምክንያት ከሥራ ቦታ ተነስቶ መዘዋወር ወይም ሌላውን ሠራተኛ ሥራ ማስፈታት ከተገቢው በላይ በካንቲን መቀመጥ፣ እንዲሁም በግቢ ውስጥ መንገድ ላይ መላፋት | የቃል ማስጠንቀቂያ | የ1/2 ቀን ደመወዝ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | የ3 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
19 | በፍተሻ ጊዜ በትክክል የማይፈተሽና ተፈታሾችን ከሥነ ሥርዓት ውጭ የሚያጉላላ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
2ዐ | በኃይል ከአክስዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ለመግባት ወይም ለመውጣት የሞከረ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||
21 | የሥራ ልብስ ሣይለብስ ሥራ ላይ የተገኘ ወይም የአደጋ መከላከያ በሥራ ላይ ያልተጠቀመ፣ | የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
22 | ጥፋቱ መጣራትና መመርመር የሚያስፈልገው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ጽሁፍ ወይም ክስ ቻርጅ ላይ አልፈርምም ማለት በተከሰሰበት ጥፋት ተጨማሪ | የ1/2 ቀን ደመወዝ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
23 | በሥራ ላይ ተኝቶ የተገኘ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
24 | በሥራ ሰዓት ኃላፊነቱን ዘንግቶ የተኛ የጥበቃ ሠራተኛና የእሣት አደጋ ሠራተኛ ኤሌክትሪሽያን እና የክሊኒክ ሠራተኛ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||
25 | ተረኛ ሆኖ በምድብ ሥራው ላይ ያልተገኘ ሾፊር፣ የጥበቃ ሠራተኛና የሕክምና ባለሙያዎች | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | የ5 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||
26 | ኃላፊነቱን በመሸሽ ወይም በመዘንጋት ተግባሩን በትክክል ያልተወጣ ኃላፊና ተቆጣጣሪ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||
27 | በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ ሃሰተኛ ወሬን የሚያወራ ወይም የሃሰት ሪፖርት ያቀረበ ወይም የሃሰት ምስክርነት የሰጠ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |||
28 | የፈረቃ ሠራተኛ የሆነ ለቀያሪው ሣያስረክብ ቀድሞ የወጣ /ሣያሣውቅ የወጣ/ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ5 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
29 | የሥራ ውጤቱ ባለማቋረጥ ከተወሰነው የምርት ውጤት በታች ሲሆን፣ ከክፍሉ በሚቀርበው ሪፖርት መሠረት በሠራተኛው ጥፋት መሆኑ ተጣርቶ ሲረጋገጥ፣ | በመጀመሪያው ወር ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | በሁለተኛ ወር ላይ የ2 ቀን ደመወዝ | በሦስተኛ ወር ላይ የ3 ቀን ደመወዝ | አራተኛ ወር ላይ የ4 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
3ዐ | ከፍተኛ ሕመም ሣይዘው ወይም ሣይታመም በአንቀጽ 2ዐ.7 መሠረት በተሽከርካሪ ከኮ/ቻ ከተማ ወደ አክስዮን ማህበሩ ክሊኒክ የመጣ ሠራተኛ | የ1 ቀን ደመወዝ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | |
31 | ዝውውር ደርሶት የተመደበበት ቦታ ያልሄደ | የ2 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | የ3 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝ እና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||
32 | በኩባያው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሕገ ወጥ ጽሁፍ የፃፈ፣ ፖስተሮችን የለጠፈ ወይም ያለ አክስዮን ማህበሩ አስተዳደር ፈቃድ የማስታወቂያ ሰሌዳ የተጠቀመ ማናቸውንም ወረቀት ያስፈረመ፣ የፈረመ እና የተባበረ፣ ሣይፈቀድ ስብሰባ የተሰበሰበ ወይም የሰበሰበ | የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ | ||||
33 | የጾታ ትንኮሣ የፈፀመ /ች/ በበቂ ማስረጃ ሲረጋገጥ | የ2 ቀን ደመወዝ | የ4 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ |
ማስታወሻ
1. ሠራተኛው ለማህበራዊ ግንኙነቶች መዋጮ ለማዋጣት ወይም መሰል ሌሎች ተግባሮች የሚውሉ ወረቀቶችን መፈረምና ማስፈረም የድርጅቱን የሥራ ሰዓት እስካልተሻማ ድረስ እንደ ጥፋት አይቆጠርም፡፡
2. ሠራተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ባጠፋው ጥፋት የመጀመሪያ ቅጣት ከተቀጣ በኋላ በሌላ ጊዜ 2ተኛ ጥፋት ካጠፋ በ2ኛ ደረጃ ከዚያም የሚያጠፋ ከሆነ በ3ኛ ደረጃ ላይ በተቀመጠው የሚቀጣ ይሆናል፡፡ ይኸውም ከአንቀጽ 4ዐ ከ1 - 33 ባሉት ላይ ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡