ማውጫ

ክፍል አንድ

መግቢያ

ርዕስ 

የህብረት ስምምነቱ ዓላማ 

ክፍል ሁለት

2. ጠቅላላ

2.1. ተስማሚ ክፍሎች 

2.2. የህብረት ስምምነቱ ተፈፃሚነት ወሰን 

2.3. ትርጓሜና ማብራሪያ /Definition/

ክፍል ሦስት

የኩባንያው፣ የሰራተኞችና የሰራተኛ ማህበሩ መብቶችና ግዴታዎች

3.1. የኩባንያው መብቶች 

3.2. የኩባንያው ግዴታዎች 

3.3. የሰራተኛ መብቶች 

3.4. የሰራተኛ ግዴታዎች 

3.5. የማህበሩ መብት 

3.6. የማህበሩ ግዴታ 

3.7. የጋራ ስብሰባና ውይይት 

ክፍል አራት

ክፍት የሥራ ቦታዎችና የሠራተኛ አመዳደብ

4.1. ክፍት የሥራ ቦታዎችና የሰራተኞች አመዳደብ ሂደት 

ክፍል አምስት 

የሙያ ማሻሻያ /ስልጠና/

5.1. የስልጠና ፕሮግራም 

ክፍል ስድስት

የሥራ አፈፃፀም ምዘና

6.1. የምዘና መመሪያ 

ክፍል ሰባት

እድገት ዝውውር ከደረጃ ዝቅ ማድረግ የስራ ውል ማቋረጥ በተጠባባቂነት ስለመመደብ

7.1. እድገት 

7.2. ዝውውር 

7.3. ተጠባባቂ ስለሚመደብባቸው ሁኔታዎች 

7.4. የጊዜ ወሰን 


በብክሮቤ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር



መሰረታዊ የሠራተኞች ማህበር

የአሰሪና ሠራተኛ የህብረት ስምምነት





 



በብክሮቤ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግል ማህበር እና በብክሮቤ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላ/የተ/የግ/ማህ. መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር መካከል የተደረገ የህብረት ስምምነት ነው፡፡ 


ኩባንያው የኩባንያው ሰራተኞችና የሰራተኞች ማህበር ኩባንያው ተወዳዳሪና ትርፋማ ሆኖ ሊሰራ የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት የጋራ ፍላጎታቸውና ጥቅማቸው መሆኑን በመገንዘብና ኩባንያውም ተወዳዳሪና ትርፋማ ሊሆን የሚችለው ሁሉም ወገኖች መብትና ግዴታቸውን አውቀውና አክብረው የተረጋጋ ሰላማዊ የሆነ የስራ ግንኙነት በመካከላቸው በመፍጠር የኢንዱስትሪ ሰላም በሰፈነበት ሁኔታ ሊሰሩ የሚችሉበት ሁኔታ ሲመቻች መሆኑን በመረዳት እና በኩባንያውና በሰራተኞች መካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመጋባባቶች በጋራ በጋራ በውይይት በቅን ልቦና በተፈጠነ ሁኔታ ሊወገዱ ሚችሉበት ስርዓት መኖር አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ህብረትን ለውጤት በመጠቀም ተግባራዊ ለማድረግ የተዘጋጀ ስምምነት ነው፡፡  



ይህ የህብረት ስምምነት በብክሮቤ ቢስነዝ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር እና በብክሮቤ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግ.ማህ. መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር መካከል በ______ቀን_________ዓ.ም የተደረገ የህብረት ስምምነት ተብሎ ይጠቀሳል፡፡ 

ሀ/ ይህ የህብረት ስምምነት በ377/96 አንቀጽ 9 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 





የአሰሪና ሰራተኛ ሕጎች፡ የአሰሪና ሰራተኛን ግንኙነት በተመለከተ በፌደራል መንግስት የወጡ አዋጆች ደንቦችን መመሪያዎችን እና እነዚህን በተመለከተ የፌደራል መንግስት ለድርጅቶች የሚያወጣቸውን ማሻሻያዎችን ያጠቃልላል፡፡ 

በብክሮቤ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ማለት፡- በሕግ አግባብ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ 

የህብረት ስምምነት፡- ማለት በብክሮቤ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር እና በዚሁ ኩባንያ ሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር መካከል በ______ቀን_________ዓ.ም የተደረገ የህብረት ስምምነትና ማሻሻያዎችን ያጠቃልላል፡፡ 

የስራ ብቃት /Qualifciation/- አንድ ሰራተኛ ለተመደበበት የስራ ቦታ ብቁ የሚያደርጉት ትምህርትና የስራ ልምድ ሲሟሉ ማለት ነው፡፡ የተመደበበትን ስራ በስራ ውጤት መመዘኛ መሰረት አሟልቶ ሲገኝ ነው፡፡ 

የስራ ውጤት /Performance/ የአንድ ሰራተኛ የስራው መጠንና ጥራት ማለት ነው፡፡ ድርጅቱ ለሰራተኛው ያስቀመጠው የስራ ግብ ማለት ነው፡፡ 

የአካል ጉዳት /Disability/- 

  1. ‹‹የአካል ጉዳት›› ማለት በአ/ሠ/አ/ቁ/ 377/96 አንቀጽ 95-112 የሚያጠቃልል ነው፡፡ 

መወዝ /Salary/- አንድ ሰራተኛ በስራ ውሉ መሰረት ለሚያከናውነው ስራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ነው፡፡ 

የትርፍ ሰዓት /Over Time/፡- አንድ ሰራተኛ በዚህ ህብረት ስምምነት ከተወሰነው መደበኛ የስራ ሰዓት በላይ በተጨማሪ በተፈቀደው ምክንያት በቀን በማታና በባዕላት ቀን የሚሰራው ስራ ማለት ነው፡፡ 











ሀ. ለኩባንያው በህግ በተሰጡት መብቶች መሰረት ፖሊሲዎችንና ደንቦችነን የማውጣት ስራዎችን የመወሰነን የመምራት እቅድ የማውጣት የሚሰራበትን አቋም የማሻሻል ወይም የመለወጥ ሰራተኞችን በአጠቃላይ የማተዳደርና የመቆጣጠር መብትን ያጠቃልላል፡፡ 

ለ. በዚህ የህብረቱ ስምምነትና በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አስገዳጅ በሆኑ ሕጎች መሰረት ድርጅቱ በሚያወጣው የአፈፃፀም መመሪያዎች መሰረት ሰራተኞችን የመቅጠር የመመደብ የማሰራት የማዘዋወር እድገት የመስጠት የስነስርዓት እርምጃ የመውሰድ የማገድና የማሰናበት መብት አለው፡፡  


ሀ. ኩባንያው ስለ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ በፌደራል መንግስት የወጡና የሚወጡ ህጎች ደንቦችንና መመሪያዎች የኩባንያውን ፖሊሲዎች እና ይህን የህብረት ስምምነት ያከብራል፡፡ 

ለ. የሰራተኛውን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅና ከአደጋ ለመከላከል የሚያስፈልጉትን እርምጃዎች ሁሉ ይወስዳል፡፡ 

ሐ. በኩባንያው ሰራተኞች መካከል የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከር የሰራተኛው የአእምሮና የአካል ብቃት እያደገና እያዳበረ የሚሄድበትን ሁኔታ ለማመቻቸትና በስራው ላይ የበለጠ ውጤታማ የሚሆንበትን ሁኔታ ለመፍጠር የማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲፈፀሩና እንዲዳብሩ በሚደረግ ጥረት ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን ተገቢውነን ድጋፍ ይሰጣል፡፡  

መ. ኩባንያው በሰራተኛው ማህበር ስራ ውስጥ ጣልቃ አይገባም፡፡ የድርጅቱ ሰራተኞች አባል እንዳይሆኑ ወይም ከአባልነት እንዲወጡ አይገፋፋም፡፡ የማህበሩ አባል በሆነና ባልሆኑት መካከል ልዩነት አያደርግም፡፡ 

ሠ. ኩባንያው የማህበሩን ሕጋዊ መብቶች ያከብራል፡፡ 

ረ. ኩባንያው ከሰራተኞች በየወሩ የሚቆረጠውን የማህበር መዋጮ ማህበሩ ለሚወክለው ገንዘብ ቼክ ሰርቶ ያስረክባል፡፡ 

ሰ. ለማህበሩ ስራ አገልግሎት የሚውል ጽ/ቤት ካለው በመስጠት ለማህበሩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ 


ሀ. የኩባንያው ሰራተኞች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ በዚህ የህብረት ስምምነት የተሰጡትን መብቶችና ጥቅሞች የማግኘት መብት አላቸው፡፡ 

ለ. ኩባንያው የሰራተኛውን መብትና ጥቅም የሚነካ እርምጃዎችን በሚወስድበት ጊዜ ሰራተኛው በቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓት መሰረት በግሉ ወይም በማህበር አማካይነት ለሚመለከተው ኃላፊ ቅሬታውን የማቅረብና የመከራከር መብት አለው፡፡ 

ሐ. ማንኛውም ሰራተኛ የታዘዘውን ስራ በአካል በጤና በህይወት ወይም በንብረት ላይ አደጋ የሚያስከትል ሁኔታ መኖሩን ካረጋገጠ ወዲያውኑ ለቅርብ አለቃውና ከዚህ በላይ ላሉ አለቆች የማሳወቅ መብት አለው፡፡ 


ሀ. ስለ ሰራተኛ ጉዳይ የወጡ ህጎችን ደንቦችንና መመሪያዎችን የኩባንያውን ፖሊሲዎችና ይህን የህብረት ስምምነት ያከብራል፡፡ 

ለ. ሙሉ ሀይሉንና ችሎታውን በስራ ላይ በማዋል ኩባንያውን ተወዳዳሪና ትርፋማ እንዲሆን የበኩሉን ጥረት ያደርጋል፡፡ 

ሐ. ስለ ጤና አጠባበቅና የአደጋ መከላከያ ዘዴዎች ህብረት ስምምነቱ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ በኩባንያው የወጡ ወይም የሚወጡ ፖሊሲዎችን ደንቦችንና መመሪያዎችን አክብሮ በጥንቃቄ ይሰራል፡፡ 

መ. ስራውን ለማከናወን አስፈላጊ ሆነው የተሰጡትን እቃዎችና መሳሪያዎች በጥንቃቄ ይይዛል ይጠብቃል፡፡ 

ሠ. ሰራተኛው ለራሱና ለኩባንያው ጥሩ ስም ዝናና ክብር የሚያስገኝ መንገድ ሁልጊዜ ራሱን ይመራል፡፡ 

ረ. በተረከበው የስራ መሳሪያ ላይ ብልሽት ቢደርስ ወይም በስራ አካባቢ ለአደጋ መንስኤ ሊሆን የሚችል ሁኔታ ሲያጋጥም በአፋጣኝ ለቅርብ አለቃው ወይም ለድርጅቱ ኃላፊዎች ያሳውቃል፡፡ በመተባበርም ችግሩ እንዲወገድ ያደርጋል፡፡ 

ሰ. ማንኛውም ሰራተኛ ድርጅቱ በሚያዘጋጀው አመታዊ የስራ እቅድ በተሰጠው የሥራ ድርሻ መሰረት ተገቢውን አፈፃፀም የማሟላት ግዴታ አለበት፡፡ 


ማህበሩ በዚህ የህብረት ስምምነትና በሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንዲሁም በኩባንያው መመሪያዎች የተመለከቱት የሥራ ሁኔታዎች በስራ ላይ መዋላቸውን የመከታተል ሠራተኛውን በመወከል ከድርጅቱ ጋር የመነጋገር የመደራደርና ስምምነት የማድረግ መብት አለው፡፡    


ሀ. ማህበሩ ኩባንያውን ተወዳዳሪና ትርፋማ በመሆን ህልውናውን ለመጠበቅ ለማድረግና ለማሻሻል ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ሙሉ ድጋፍ ይሰጣል፡፡ 

ለ. ማህበሩ ሰራተኛ የህብረት ስምምነቱን ይዘት ዓላማ ትርጉምና አፈፃፀም እንዲረዳ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ 

ሐ. ማህበሩ ሰራተኛው የህብረት ስምምነቱን ህጎችንና መመሪያዎች በመከተል የሚሰራ ጠንካራና በዲሲፒሊን የታነፀ አምራች ኃይል እንዲሆን የበኩሉን ጥረት ያደርጋል፡፡ 

መ. ማህበሩ ኩባንያው የሚያወጣቸውን የስራ እቅዶችና ፕሮግራሞችን ለማስፈፀም ሙሉ ተሳትፎና ትብብር ያደርጋል፡፡ 

ሠ. ማህበሩ ሰራተኛውን ለማሰልጠንና ለማስተማር ኩባንያው ያዘጋጀው ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ሰራተኛውን በማስተባበር ተሳትፎ ያደርጋል፡፡ 

ረ. ማህበሩ የኩባንያው የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲጠበቅ ጥረት ያደርጋል፡፡ 


ሀ. ኩባንያውና የሰራተኛ ማህበሩ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የስራ ምርታማነት እንዲዳብር ለማድረግ የዚህን ህብረት ስምምነት ዓላማ ከግብ ለማድረስ በሶስት ወር አንድ ጊዜ የጋራ ስብሰባ በማድረግ የኩባንያው እድገትና አብዛኛውን ሰራተኞች በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ፡፡

ለ. ስብሰባ ከሚደረግበት ቀን ቢያንስ አንድ ሳምንት አስቀድሞ ኩባንያውና ማህበሩ ያያዟቸውን አጀንዳዎች በፁሁፍ በመለዋወጥ መወያያ ሊሆኑ የሚችሉትን አጀንዳዎች ይቀርፃሉ፡፡ ሆኖም ኩባንያውና የሙያ ማህበሩ ሁለቱንም በሚያምኑበት ሁኔታ አስቸኳይ ጉዳይ ሲከሰት የጋራ ስብሰባ ሊጠሩ ይችላሉ፡፡ 

ሐ. በውይይቱ ቀን ከተመረጡት አጀንዳዎች ውጪ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ውይይት አይካሄድም፡፡ ሆኖም ጉዳዩ ቀደም ብሎ በአጀንዳ ሊያዝ ያልቻለበት በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ሁለቱም ወገኖች ካመኑበትና ውይይት ሊደረግበት እንደሚገባ ከተስማሙ መወያያ ሊሆን ይችላል፡፡ 

መ. የስብሰባው ቃለ ጉባኤ በሁለቱ ወገኖች ተወካዮች ተፈርሞ በሳምንት ውስጥ እንዲደርሳቸው ይደርጋል፡፡ የጋራ ስብሰባውም ዝርዝር በስነ ስርዓት በሁለቱ ወገኖች ይዘጋጃል፡፡ ለወደፊቱ ጠቀሜታዎች በውይይት ወቅት አስተያየት የተሰጠባቸው ነጥቦች ለድርጅቱ እድገትም ሆነ ለጋራ ስምምነት አካልነት ብቃት በቀጣዩ ተጨማሪ ጥናት ተደርጎባቸው እንደ ሁኔታው በስራ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ 

ሠ. ኩባንያው የሚያወጣቸውን የስራ እቅዶች ፕሮግራም በጀት ከፀደቀ በኋላ ለተግባራዊነቱ ሂደት መሳካት እንዲደረግ ማህበሩ ስለ ስራ እቅዶች በጀት ይዘትና አላማ የሚያውቅበትን መድረክ ለማዘጋጀት በኩባንያው በኩል ጥረት ይደረጋል፡፡ እንዲሁም በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ አፈፃፀም ግምገማ ስብሰባዎች ላይ እንዲሳተፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡ 

ሀ. በኩባንያው ውስጥ ክፍት የስራ መደብ ሲኖር በመጀመሪያ በኩባንያው ውስጥ ለቦታው ብቁ የሚሆነውን ሰራተኛ በማዘዋወር ለመመደብ ጥረት ይደርጋል፡፡ 

ለ. በዝውውር በክፍት የስራ ቦታ ላይ መመደብ በማይቻልበት ጊዜ የኩባንያው ሰራተኞች እንዲወዳደሩ በውስጥ ማስታወቂያ ያስታውቃል፡፡ 

ሐ. ክፍት የስራ ቦታው በኩባንያው ሰራተኞች ለማሟላት ካልተቻለ በቅድሚያ በእህት ኩባንያዎች የሚገኙ ሰራተኞች ለቦታው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ 

መ. በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ብቁ የሆነ ተወዳዳሪ ካልተገኘ ከኩባንያውና ከእህት ኩባንያዎች ውጪ የሆኑ ሰዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ 

ሠ. የክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ አወጣጥ እንዲሁም የአመራረጡ ስርአት በድርጅቱ የሰው ሀይል የስራ መመሪያና ስለዚህ ጉዳይ አፈፃፀም በተዘረዘረው እና ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ይፈፀማል፡፡ 

ሀ. ሰራተኛው የስራ ችሎታው ተሻሽሎና የእውቀት ደረጃውም እድጎ በስራው ላይ የበለጠ ውጤታማ የሆነበትን ሁኔታ ለመፍጠር ኩባንያው የሙያ ማሻሻያና ስልጠና ፕሮግራም የሚካሄድበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡ 

ለ. ኩባንያው በራሱ ተነሳሽነት ባፀደቃቸው የስልጠና ፕሮግራሞች ተካፋይ የሚሆን ሰራተኛ በስልጠናው ፕሮግራም በሚቆይበት ጊዜ ሙሉ ደመወዙና ማናቸውንም በስራ ውሉ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ያገኛል፡፡ 

ሐ. ኩባንያው በራሱ ተነሳሽነት አቅዶ ተግባራዊ ለሚያደርጋቸው ስልጠናዎች የመጓጓዣና የውሎ አበል ወጪን በሚመለከት በኩባንያው መመሪያ መሰረት ይፈፀማል፡፡    

ሀ. የስራ አፈፃፀም ምዘና በሰራተኛው የቅርብ አለቃ የሚሞላ ይሆናል፡፡ ማንኛውም ሰራተኛ የምዘናውን ውጤት እንዲያየውና ከቅርብ አለቃው ጋር እንዲወያይበት ይደረጋል፡፡ በምዘናው ያልተስማማ ሰራተኛ የስራ ምዘና ፎርም ላይ አስተያየቱን አስፍሮ ፊርማውን ያኖራል፡፡ 

ለ. የምዘናው ውጤት ሰራተኛው ተጨማሪ ስልጠና ቢሰጠው ስራውን ለማሻሻል እንደሚረዳው ሲያመላክትና ተግባራዊ ለማድረግም አመቺ ሁኔታ ሲኖር ኩባንያው የሰራተኛው ችሎታ እንዲሻሻል የስልጠና ድጋፍ ያደርግለታል፡፡ 

ሐ. የምዘናው ውጤት የሰራተኛው የስራ ችሎታ ከሚፈለገው በታች () መሆኑንና ለስራውም ብቃት የሌለው መሆኑን ሲያመላክት ድክመቶቹን በዝርዝር የሚገልፅ ችሎታውን ለማሻሻል የስድስት ወር ጊዜ የተሰጠው መሆኑን የሚያመላክትና በዚሁ ጊዜ ውስጥ ማሻሻል ካልቻለ የስራ ውሉ እንደሚቋረጥ የሚገልፅ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ 

መ. በስድስት ወራቶች ውስጥ ለሰራተኛው ተገቢውን ክትትል በማድረግ እንዲሻሻል ማበረታታት ይደረጋል፡፡ 

ሠ. የምዘና ውጤቱ ጥሩ የሆነ ሰራተኛ ከድርጅቱ የምስጋና ደብዳቤ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ 



ሀ. እድገት በኩባንያው የሰው ኃይል አገልግሎት የስራ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡ 

ለ. ሰራተኛው የእድገት አፈፃፀምን የሚመለከቱ የኩባንያውን መመሪያዎች ጠንቅቆ እንዲያውቃቸው ይደረጋል፡፡ 

ሐ. ለእድገት መሰረቱ የስራ ብቃትና ውጤት ነው፡፡ 

መ. ከአንድ በላይ የሆኑ ሰራተኞች ለአንድ የእድገት ቦታ መመዘኛዎቹን አሟልተው ሲገኙ ችሎታና የስራ ልምድ የአገልግሎት ዘመን የስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት ፈተና በመለያነት ያገለግላሉ፡፡ 

ሠ. አንድ ሠራተኛ ከዝቅተኛ የስራ መደብ ወደ ከፍተኛ የስራ መደብ በእድገት ሲመደብ ለቦታው የተመደበውን ደመወዝ ያገኛል፡፡ ሆኖም እድገቱ የሰራተኛን አመታዊ ጭማሪ አያሳጣውም፡፡ 

ረ. ለደረጃ እድገት የሚወዳደር የሚሆን ሰራተኛ የስራ አፈፃፀሙ 3.00 ‹‹C›› ወይም ከዚህ በላይ መሆን አለበት፡፡  

ሀ. ኩባንያው ሰራተኛውን ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ በዝውውር ማሰራት ይችላል፡፡ ሰራተኛው ከመዘዋወሩ አስቀድሞ ያገኛቸው የነበሩ ጥቅማ ጥቅሞችና መብቶች ከነበረበት የስራ ቦታና የስራ ሁኔታ ገር የተያያዘ ካልሆነ በስተቀር ዝውውሩ ቀድሞ ሲያገኛቸው የነበሩትን መብቶችና ጥቅሞችን የሚነካ አይሆንም፡፡ 

ለ. ዝውውር ብቻውን የደመወዝ ጭማሪን አያስከትልም፡፡ 

ሐ. አንድ ሰራተኛ የዝውውር ጥያቄ ሲያቀርብ በኩባንያው የስራ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም ይሆና፡፡ 

ሀ. ሰራተኛው በፈቃድ በትምህርት በስብሰባ በመሳሰሉት ምክንያቶች ስራው ላይ በማይኖርበት ጊዜ ኃላፊነቱን በብቃት ይወጣል ተብሎ የሚገመት ሰራተኛ በጊዜያዊነት ተመድቦ እንዲሰራ ይደረጋል፡፡

ለ. በክፍት የስራ መደብ ላይ ለቦታው ብቃት አለው ተብሎ በኩባንያው የሚታመንበት ሰራተኛ በዘለቄታ እስኪመደብ በጊዜያዊነት ሰራተኛ ተመድቦ እንዲሰራ ይደረጋል፡፡ 

ሐ. በምደባው የሚሰራው ስራ ለአጭር ጊዜ ወይም ለረጅም ጊዜ ለሆን ይችላል፡፡ 

መ. በተለየ ሁኔታ በዋናው ስራ አስኪያጅ ካልተፈቀደ በስተቀር በሙከራ ጊዜ ውስጥ ያለ ሰራተኛ ተጠባባቂ ሆኖ እንዲሰራ አይመደብም፡፡ 

ሠ. ማንኛውም የተጠባባቂነት ምደባ በፁሁፍ ይሆናል፡፡ 

ሀ. በተጠባባቂነት የሚሰራ ስራ ከ 6 ወር መብለጥ የሌለበት ሲሆን በተለያዩ ሁኔታዎች የሚራዘም ሆኖ ከተገኘም በማናቸውም ሁኔታ ከ12 ወር የበለጠ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም ከላይ የተጠቀሰው የተጠባባቂነት ጊዜ ገደብ ውስጥ በኩባንያው በስራ ምዘና መመሪያ መሰረት የስራ አመራሩ ተጠባባቂውን በቋሚነት መመደብ ወይም ማዘዋወር ወይም ሌላ ተገቢ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ 

7.5. በተጠባባቂነት ስለመመደብ 

ሀ. አንድ ሰራተኛ አንድ የሥራ መደብን ለተወሰነነ ጊዜ ሸፍኖ መስራት አለበት፡፡     

ክፍል ስምንት

ልዩ ልዩ ጥቅሞች

8.1. አበል 

8.1.1. በውክልናና በተጠባባቂነት ምደባ ()

ሀ. በተከታታይ ሰራተኛው ካለበት የስራ መደብና ደረጃ ከፍ ባለ የስራ መደብና ደረጃ ተመድቦ አንድ ወር በሚያገለግሉበት ጊዜ ከሰላሳ ቀናት በላይ በሆነ ጊዜ ብቻ የራሱ ከሆነው ከደመወዝ ላይ 25% ታክሎ ይከፈለዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ተጠባባቂነትና ውክልናው በኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ወይም በተወካዩ ፊርማ የፀደቀ ሲሆን ነው፡፡ 

8.2. የተለያዩ ድጋፎች ()

8.2.1. መድን ኢንሹራንስ 

አፈፃፀሙም በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ይሆናል፡፡ 

8.3. ልዩ ልዩ ድጎማዎች 

8.3.1. ጉርሻ (ቦነስ) እና ማትጊያ (ኢንሴንቲቭ)

ሀ. የኩባንያው ትርፋማነት እና እንዲሁም ጠቅላላ ኢኮኖሚያዊና የአስተዳደር ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ኩባንያው በአመት አንድ ጊዜ ይሰጣል፡፡ 

8.3.2. ለቀብር የሚሰጥ ድጋፍ 

ሀ. የኩባንያው ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ በግል በሚመጣ በሽታ ቢሞት ለቀብር ማስፈፀሚያ ድጋፍ ለቤተሰቡ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ሰራተኛው የሞተው በስራ ምክንያት በደረሰበት ጉዳት ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110/ለ የተደነገገው በተጨማሪም ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

8.3.3. ትራንስፖርት /ሰርቪስ/

ሀ. ኩባንያው አቅም በፈቀደ መጠን የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ 

ለ. በክፍት    ሰራተኞች ኩባንያው ከመኖሪያ አካባቢያቸው ጋር በተዛመደ መልኩ የትራንስፖት አገልግሎት ያዘጋጃል፡፡ 

8.3.4. የትራፊክ ጥፋቶች እና ቅጣቶች በከፊል 

የኩባንያውን መኪና የሚያሽከረክር ሹፌር ሰራተኛ የትራፊክ ህጎችን ማክበር ለስራው እና ላገኘው የመንጃ ፍቃድ አብይ መስፈርቶች በመሆናቸው የማክበር ኃላፊነት አለበት፡፡ በመሆኑም የትራፊክ ህጎች በመጣስ የሚደርሱ ቅጣቶች እና ኃላፊነቱን የሰራተኛው ይሆናሉ፡፡   

8.3.5. የድርጅቱን የካፊቴሪያ አገልግሎት የጥራት ደረጃውን እና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን የድርጅቱ ማኔጅመንት እና የሰራተኛ ማህበሩ በጋራ ይቆጣጠራሉ፡፡ 

8.3.6. ድርጅቱ ለማህበሩ ስራ ማከናወኛ የሚሆን ቢሮ ካለው እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ 

8.3.7. የውሎ አበል 

አንድ ሰራተኛ ለስራ ጉዳይ ከስራ ቦታ ወይም ከሚኖርበት ከተማ ክልል ውጭ 40 ኪ.ሜ ወደ ሌላ ቦታ ለስራ ሲላክ ከዚህ በሚከተለው ሁኔታ የውሎ አበል ይከፈለዋል፡፡ ይህም ለቁርስ ከ1 ሰዓት ጀምሮ ለምሳ ከ 6፡00ሰዓት ጀምሮ፣ ለእራት ከምሽቱ 2፡00ሰዓት፣ መኝታ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓይ ይሆናል፡፡ ይህም የጉዞ ቦታ ከአዲስ አበባ ውጭ 40ኬ/ሜ ለሆኑ ጉዞዎች ሁሉ ይሆና፡፡ 

ሀ/ ለቁርስ  10%

ለምሳ  20%

ለእራት  30%

ለአልጋ  40%

ለ/ የአበል ክፍያው በደሞዝ እርከን መሰረት ሲሆን 

ከ601 – 1400   ብር 200.00

ከ1401 – 2350 ብር 250.00

ከ2351 – 3550   ብር 300.00

ሐ/ አንድ ሰራተኛ ለስራ ጉዳይ ከ10ኪ/ሜ በላይ ከወጣ የምሳ ሰዓቱን በስራ ላይ ከአሳለፈ ብር 40.00 የምሳ አበል ይከፈለዋል፡፡ 

ክፍል ዘጠኝ 

ልዩ ልዩ ፍቃዶች 

9.1. የአመት ፈቃድ 

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

9.2. የወሊድና የእንክብካቤ ፈቃድ 

ሀ. ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ ትወልዳለች ተብሎ በሀኪም የተገመተበትን ቀን የሚያስረዳ የሀኪም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባታል፡፡ 

ለ. ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ ከታወቀ ሀኪም የህክምና ማስረጃ ስታቀርብ ከመውለዷ በፊት ከእርግዝናዋ ጋር በተያያዘ ምርመራ ለማድረግ እና እረፍት ለማግኘት ከክፍያ ጋር ፈቃድ ይሰጣታል፡፡ 

ሐ. ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ ትወልዳለች ተብሎ በሀኪም ከተገመተበት ቀን በፊት 30 ተከታታይ ቀናት እንዲሁም ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 60 ተከታታይ ቀናት የወሊድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል፡፡ 

9.3. የጋብቻ ፈቃድ 

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 81 ተ.ቁ 1 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

9.4. የሀዘን ፈቃድ 

ሀ. ሰራተኛው የትዳር ጓደኛው፣ ወላጅ፣ ተወላጅ ወይም እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ የሚቆጠር ማለትም የሰራተኛው ባል ወይም ሚስት ወንድም፣ እህት፣ የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመድ ሲሞትበት 3 የስራ ቀን ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጠዋል፡፡ የክፍል ኃላፊው ፈቃድ ከመስጠቱ በፊት ከሰው ኃይል አገልግሎት ጋር በመሆን ማጣራት ያደርጋል፡፡ ሆኖም ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልግ ከሆነ ግን ካለው የአመት ፈቃድ ላይ ሊወስድ ይችላል፡፡ 

ለ. ሠራተኛው ከሚሰራበት ቦታ ውጪ ዘመድ ሞቶበት መርዶ ሲረዳና ለቅሶ ለመድረስ ቢሄድ እንደ ቦታው እርቀት ታስቦ የአመት እረፍት ፈቃድ የሚቀነስ ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም የተጠራቀመ የአመት እረፍት ፈቃድ ከሌለው ደመወዝ የማይከፈልበት ነፃ ፈቃድ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ሆኖም እንዲህ አይነቱ ለሀዘን የሚሰጥ ፈቃድ በአመት ከ07 ቀን መብለጥ የለበትም፡፡ 

ሐ. አንድ ሰራተኛ ከሚሰራበት ምድብ የስራ ቦታው ለኩባንያው ስራ ወደ ሌላ የስራ ቦታ ሄዶ ቢሞትና እስክሬኑ ወደ መደበኛ የስራ ቦታው እንዲመጣ የቤተሰብ ፍላጎት ቢሆን ድርጅቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አስክሬኑ እንዲረመር የሚያስፈልግ ቢሆን ለምርመራ የሚወጣውን ወጪ ኩባንያው ይሸፍናል፡፡ 

መ. አንድ ሰራተኛ በሚሰራበት አካባቢ ሲሞትና ቀብሩ የሚፈፀመው ከምድብ ስራው አካባቢ ሲሆን የሰው ኃይል አስተዳደርና የስራ ክፍሉ በመነጋገር ስራው በማይበደልበት መልኩ 10 ስራተኛ ለ 3ሰዓት ያህል ፈቃድ በመስጠት በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ይደረጋል፡፡ 

ሠ. የኩባንያውሰራተኛ በመሞቱ ምክንያት ጥገኞች ለማጓጓዝ አቅም በፈቀደ መጠን ትራንስፖርት ለማቅረብ ይሞክራል፡፡ 

ረ. በአንድ ሰራተኛ ቤተሰብ ላይ አደጋ መድረሱ በመልዕክት ለኩባንያው የደረሰ ከሆነ ኩባንያው በተቻለ መጠን ለሰራተኛው በመግለፅ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ድጋፍ ያደርግለታል፡፡ ሰራተኛው ወደ ስራ ለመመለስ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 

9.5. የህመም ፈቃድ 

በአ/ሠ/አዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

9.5.1. በተፈጥሮ ምክንያት ለታመመ (Non-Industrail Illness)


በአዋጅ 377/96 ለህመም ፈቃድ በተቀመጠው መሰረት ይፈፀማል፡፡ 

9.5.2. በስራ ምክንያት ለሚከሰት ህመም /Employement related skikness


በአዋጅ 377/96 መሰረት ይፈፀማል፡፡     


9.5.3. የህመም ፈቃድ አፈፃፀም ስርዓት 

ሀ. ከሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቀናት በህመም ምክንያት የሚቀር ሰራተኛ ከቻለ እራሱ ካልሆነም በቤተሰቡ አማካኝነት ለቅርብ አለቃው አሳውቆ ስለ ህመሙ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 

ለ. ሰራተኛው ከህመሙ ካልዳነ ወይም በህመሙ ምክንያት የስራ ችሎታውን ካጣ የስራ ውሉ ይቋረጣል የስራ ውሉ በመቋረጡ ምክንያት የሚሰጡ ክፍያዎችን በህጉ መሰረት ያገኛል፡፡ 

ሐ. የህመሙ ፈቃድ ሊጠራቀም ወይም ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ አይችልም፡፡ ሰራተኛው ያልተጠቀመበት የህመም ፈቃድ ቀን ወደ ክፍያ አይለወጥም፡፡ 

መ. በኩባንያው ሀኪም መታመሙ ተረጋግጦ በተፈቀደለት የህመም ፈቃድ ጊዜ ውስጥ ተመላልሶ የታከመ ሰራተኛ በህመም ፈቃድ ላይ እያለ የህክምና የተመለሰባቸውን ቀናት በህመም ፈቃድ ውስጥ ይደመራሉ፡፡ 

ሠ. ሰራተኛው ከስራው ጋር በተያያዘ ዓመታዊ የጤና ምርመራ እንዲያደርግ በኩባንያው ሲታዘዝ የምርመራው ጊዜ እንደ ሀኪም ፈቃድ አይቆጠርም፡፡ 

ረ. አንድ ሰራተኛ በዓመት እረፍት ላይ እያለ የሀኪም ፈቃድ ቢሰጠው የአመት ፈቃድ ይራዘምለታል፡፡ 

ሰ. አንድ ሰራተኛ ለህክምና ሲሄድ በመንገድ ያሳለፋቸው ቀናት እንደ ህመም ፈቃድ አይቆጠሩለትም፡፡ 

9.6. ያለ ክፍያ ስለሚሰጥ ፈቃድ 

ሀ. ያለክፍያ ፈቃድ ሊሰጥ የሚችለው በአ/ሠ/አ/ቁ. 377/96 መሰረት ይሆናል፡፡ 

ለ. ከአቅም በላይ ችግሮች ሲያጋጥሙ የሰው ሀይል አገልግሎ ከክፍል ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ይወሰናል፡፡ 

9.7. ለትምህርት የሚሰጥ ፈቃድ  

ከስራ ሰዓት ውጪ የማታ ትምህርት ወይም በመላላክ ትምህርት የሚከታተሉ ሰራተኞችን ያበረታታል፡፡ 

ሀ. አገር አቀፍ ፈተና እና ለተልዕኮ ትምህርት በዓመቱ አጋማሽ /ሴሚስተር/፤ በዓመቱ መጨረሻ የሚሰጠውን ፈተና ሰራተኛው ሲፈተን በሚያቀርበው የፈተና ፕሮግራም ማስረጃ መሰረት ለፈተናው ቀናት ብቻ ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡  

9.8. ልዩ ልዩ ፈቃዶች 

9.8.1. ለማህበር ስራ የሚሰጥ ፈቃድ 

ሀ. የሰራተኞች ማህበር መሪዎች የስራ ክርክር ለማቅረብ፣ የህብረት ስምምነት ለመደራደር፣ በማህበር ስብሰባ ለመገኘት፣ በሴሚናሮችና በስልጠና ለመካፈል እንዲችሉ ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣቸዋል፡፡ 

ለ. የፈቃዱ ምክንያት እና ስለመሳተፉ የሚገልፅ ማስረጃ ሰራተኛው ለሰው ሀይል አገልግሎት ማቅረብ አለበት፡፡ 

9.8.2. ልዩ ልዩ ተግባሮችን ለማከናወን የሚሰጥ ፈቃድ 

ሀ. አንድ ሰራተኛ የስራ ክርክር ለማሰማት ወይም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ህጎችን ለማስፈፀም ስልጣን ያላቸው አካሎች ዘንድ ጉዳዩን ለማሰማት ሲቀርብ ለዚህ አላማ ለጠፋ ጊዜ ብቻ ከክፍያ ጋር ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ይህም በማስረጃ መደገፍ አለበት፡፡ 

ለ. አንድ ሰራተኛ የሲቪል መብቱን ሊያስጠብቅ ወይም የሲቪል ግዴታውን ሲፈፅም ለዚህ አላማ ለጠፋው ጊዜ ብቻ ከክፍያ ጋር ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ይህም በማስረጃ መደገፍ አለበት፡፡ 

9.9. ለመመገቢያና ለሻይ ቡና የሚሰጥ እረፍት 

- እንደ ኩባንያው የስራ ሂደትና የሰው ኃይል አመዳደብ መሰረት ሰራተኛው የመመገቢያና የሻይ ሰዓት ይኖረዋል፡፡  

ክፍል አስር 

10.1. መደበኛ የስራ ሰዓት 

ሀ. መደበኛ የስራ ሰዓት በቀን 8 ሰዓት ወይም በሳምንት 48ሰዓት መብለጥ የለበትም 

ለ. በኦፕሬሽንስ በምርት ክፍሎችና በሽያጭ ክፍሎች እንዲሁም የተለያየ አገልግሎት በሚሰጡ ክፍሎች የስራ ሰዓት መሰረቱ በሳምንት 48 ሰዓት ሆኖ በመደበኛና በፈረቃ (በሽፍት) ለሚሰሩ ስራዎች ተስማሚና አመቺ በሆነ ሁኔታ በስራ ኃላፊዎቹ ይደለደላል፡፡ 

ሐ. አንድ ሰራተኛ ከቁጥጥሩ ውጪ በሆነ ምክንያት በስራው ላይ ለመገኘት በማይችልበት ጊዜ በአካል ወይም በመልእክት በተቻለ ፍጥነት ለቅርብ ኃላፊው ወይም ለሰው ኃይል አገልግሎት ማሳወቅ አለበት፡፡ 

10.2. የትርፍ ሰአት ስራ 

በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

10.3. የሳምንት የዕረፍት ቀናት

ሀ. ማንኛውም የኩባንያው ሰራተኛ ከሰባት ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ያልተቆራረጠ (በተከታታይ) 24ሰዓታት የሳምንት እረፍት ይሰጠዋል፡፡ 

ለ. የሳምንቱም የአረፍት ጊዜ የኩባንያው የስራ ሁኔታ ሲፈቅድ በተቻለ መጠን እሁድ ቀን እንዲውል ይሆናል፡፡ 

10.4. የሕዝብ በዓላት 

ሀ. በሕግ መሰረት የሚከበሩ የሕዝብ በዓላት ደመወዝ የሚከፈልባቸው ናቸው፡፡ 

ለ. ሰራተኞች በሙሉ የሕዝብ በዓላት ቀናት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ 

10.5. የፈረቃ ስራ 

ሀ. ኩባንያው እንደ ስራው ሁኔታ ሰራተኞች በፈረቃ (በሽፍት) እንዲሰሩ ማድረግ ይችላል፡፡ 

ለ. በፈረቃ የሚሰራ ሰራተኛ የተመደበለትን የስራ ሰዓት ያጠናቀቀ ቢሆንም በተተኪው ሰራተኛ በመተካቱ አስቀድሞ ስራውን መተው አይችልም፡፡ ተተኪ ሰራተኛ እስኪተካ ድረስ ስራው ላይ መቆየት አለበት፡፡ አፈፃፀሙም በአዋጁ መሰረት ይፈፀማል፡፡ በሚመለከተው የስራ ኃላፊ በቅድሚያ ካልተፈቀደ በስተቀር ሰራተኞች የተመደበላቸውን የስራ ጊዜ በእርስ በርስ ስምምነት መለዋወጥ አይችልም፡፡  

ክፍል አስራ አንድ 

ስለ ክፍያ 

11.1. ስለደመወዝ ክፍያ 

ሀ. “ደመወዝ” ማለት አንድ ሰራተኛ በስራ ውል መሰረት ለሚያከናውነው ስራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ነው፡፡ 

ለ. የደመወዝ አወሳሰንና ጭማሪ በኩባንያው የሰው ኃይል አስተዳደር መመሪያ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡ የእያንዳንዱን ሰራተኛ አስተዋፅኦ ለማንፀባረቅ የደመወዝ ክለሳ // በፖሊሲው መሰረት ይደረጋል፡፡ እንደአስፈላጊውም ተጨማሪ ክፍያ በስራ አመራሩ ሊደረግ ይችላል፡፡ 

ሐ. ደመወዝ ለእራሱ ለሰራተኛው ወይም በኩባንያው የሰው ኃይል አገልግሎት በፀደቀ የውክል ፁሁፍ ሰራተኛው በህጋዊነት ለወከለው ሰው ይከፈላል፡፡ 

መ. ደመወዝ እ.ኢ.ት አቆጣጠር ወር በገባ በ30ኛው ቀን ሰራተኛው በሚሰራበት ቦታ ወይም በባንክ በኩል ይከፈላል፡፡ የክፍያው ቀን በእረፍት ቀን ወይም በህዝብ በዓላት በቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ አስቀድሞ ባለው የስራ ቀን ይከፈላል፡፡ 

ሠ. በህግ በህብረት ስምምነት ወይም በስራ መደብ በተወሰነው ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት ካልሆነ በስተቀር ወይም ሰራተኛው በፁሁፍ ካልተስማማ አሰሪው ከሰራተኛው ደመወዝ ለቂንስ ወይም በዕዳ ሊያዝ ወይም ሊያቻችል አይችልም፡፡ 

ረ. ሰራተኛው የሚያገኛቸው ልዩ ልዩ ጭማሪዎች እንዲሰጠው ከተፈቀደለት ቀን ጀምሮ ይከፈላሉ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ክፍያው ቢዘገይም በምንም አይነት ከተፈቀደለት ቀን ጀምሮ ከሁለት ወር በላይ ሳይከፈል መቆየት አይችልም፡፡ 

ሰ. ኩባንያው መሰረቱን ምርታማነትና ትርፋማነት ለማድረግ እያንዳንዱ ሰራተኛ ባለው የስራ አፈፃፀምና የሲኒየሪቲ ቀን ጭማሪ መሰረት በኩባንያው ከተወሰነ በኋላ ስለውሳኔው ይዞታ በሰው ኃይል አገልግሎት በኩል ማህበሩ ስለሁኔታው የሚያውቅበትን መንገድ ይመቻቻል፡፡ 

ክፍል አስራ ሁለት

የሙያ የአካባቢ ጤንነት የአደጋ መከላከያ 

የስራ ልብሰና መታወቂያ

ኩባንያው ሰራተኞች በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 92-94 የተደነገጉትን ያከብራል፡፡ በዚሁ መሰረት ኩባንያውና ማህበሩ በመመካከር ሁኔታዎች የሚስተካከሉበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡ 

12.1. የስራ አካባቢ ጤንነት ቁጥጥር 

ሀ. ኩባንያው የሰራተኞቹ ጤንነት የተሟላ የማምረት ብቃታቸው የላቀ ሰርቶ አምርቶ የማደግ ፍላጎታቸው እያደገና ውጤታማነታቸውን ለማጎልበት እንዲያግዝ በማሰብ የስራ ቦታ በቂ ብርሃን እና ንፅህና በቂ አየር እንዲኖር የስራ ቦታ ወለል ንጹህና የደረቀ እንዲሆን ኩባንያው ያልተቆጠበ ጥረትና ክትትል ያደረርጋል፡፡ 

ለ. የኩባንያው ቅጥር ግቢ በአጠቃላይ ለጤና ጠንቅ ከሆኑ ነገሮች የፀዳ እንዲሁም ሰራተኛውን በማስተማርና በተግባሩም በማሳተፍ የፅዳት ዘመቻ በተወሰኑ ጊዜያት እንደአስፈላጊነቱ ይካሄዳል፡፡ 

ሐ. ኩባንያው በሚኖሩት የጤና ባለሙያዎችና በሴፍቲ ሰራተኞች አማካኝነት በመከላከል ለሰራተኞች በአመት አንድ ጊዜ ትምህርት ይሰጣል፡፡ 

መ. ኩባንያው የሰራተኞችን የስራ ጠባይ በማገናዘብ ለሰራተኛውም የተሟላ የመመገቢያ የልብስ መለዋወጫ የመታጠቢያና የመፀዳጃ ስፍራዎችን ያዘጋጃል፡፡ 

12.2. የአደጋ መከላከያና የስራ ልብስ 

ሀ. አገራዊና አለም አቀፋዊ ድንጋጌዎችና መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ በስራ ጋር በተያያዘ ሊከሰት ከሚችል አደጋ ሰራተኛውን ለመጠበቅ የሚረዱ የአደጋ መከላከያዎችን ልብሶችን ኩባንያው ለሰራተኛ ይሰጣል ዝርዝሩም በተያያዘው ተገልፆአል፡፡     

ለ. የእሳት አደጋ መከላከያዎችን በፋብሪካ በቢሮዎች በመጋዘኖች በመመገቢያዎች ቦታዎችና ሌሎችም አስፈላጊ ናቸው፡፡ በተባሉ የኩባንያው ሰፈር ውስጥ እንዲኖሩ ያደርጋል ብቃታቸውም በየጊዜው ለዚሁ በተመደቡ ሰራተኞች ይረጋገጣል ሰራተኞችም አጠቃቀማቸውን እንዲያውቁ ይደረጋል፡፡ 

ሐ. የመጨረሻ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ 

በተፈፀመው ጥፋት ክብደት ምክንያት በየደረጃ የተሰጠ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያዎችና ቅጣቶች በቂ አይሆንም ተብሎ ሊታመንበት ወይም የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የ6 ወር ጊዜ ውስጥ ጥፋቱ የተደገመ ወይም ተመሳሳይ ጥፋት የፈፀመ ከሆነ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ለአንድ ዓመት ተፈፃሚ ሲሆን በሰራተኛው የግል ማህደር ውስጥ ነዋሪ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ ሆኖም የተሰጠው የመጨረሻ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1ዓመት በላይ ለሆነው ጊዜ ማጣቀሻ ሆኖ አያገለግልም፡፡ 

መ. ከስራ ስማሰናበት፡ አንድ ሰራተኛ የመጨረሻ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኋላ ያንኑ ጥፋት ከደገመ ወይም ተመሳሳይ ጥፋት ከፈፀመ ከስራ ይሰናበታል፡፡ 

ሠ. ያለ ክፍያ አግዶ ስለማቆየት፡- ሰራተኛው የፈጸመው ጥፋት ወዲያውኑ ከስራ የሚያስወጣው ቢሆንም ባማራጭ ያለ ክፍያ ለጊዜው ከስራ ታግዶ እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል፡፡  የእገዳው ጊዜ ከ 1 ወር ጊዜመብለጥ የለበትም፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የተለየ ውሳኔ ካልተሰጠ በስተቀር የእገዳው ጊዜ እንዳበቃ በሚቀጥለው ቀን ሰራተኛው ስራው ላይ መገኘት አለበት፡፡ እገዳውን ማህበሩ በግልባጭ እንዲያውቅ ይደረጋል፡፡

ረ. ያለማስጠንቀቂያ ስለማሰናበት፡- ሰራተኛው የፈጸመው ጥፋት ከባድ በመሆኑ ምክንያት ወዲያውኑ ከስራ ሊያስወጣው የሚችል በሚሆንበት ጊዜ ቀደምብሎ የጽሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ ያልደረሰው ቢሆንም ወዲያዉኑ ከስራ ማሰናበት ይችላል፡፡

14.3 የጥፋት አይነቶችና አመዳደባቸው

ሀ. አንድ ሰራተኛ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት የጥፋት አይነቶች አንዱን ፈጽሞ ከተገኘ ወዲያዉኑ ከስራ ሊያስወጣው የሚችል በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ሰራተኛው ጥፋቱን ለመፈጸሙ በቂ ጥርጣሬ ሲኖርና ስረጃዎቹ ለጊዜው ተሟልተው ካልተገኙ ምርመራው እስከ ሚጠናቀቅ እሰከ 30 ቀናት ሰራተኛውን አግዶ ማቆየት ይቻላል፡፡

ለ.  ያለማስጠንቀቂያ  ከስራ የሚያሰናብቱትና  እግዳን የሚያስከትሉት ጥፋቶች፡-

  1. በኩባንያዉ የስራ ቦታ ባልደረባ፣ጊዜያዊ ተቀጣሪ፣ ጊዜያዊ አማካሪ ወዘተ… ላይ የሃይል ማጥቃት መፈፀም
  2. የኩባንያው ወይም ኩባንያው የሚያስተዳድራቸውን ንብረቶች መስረቅ፣
  3. የኩባንያውን ገንዘብ በማጭበርበር መውሰድ
  4. የኩባንያውን ሰነዶችን ለማሳየት ሲባል መሰረዝ፣መደለዝ መሰወርና ማጥፋት ሌሎች ለእሳት አደጋ መካከል ሊረዱ የሚችሉ ቁሳቁሶች (እንደ አሽዋ የመሳሰሉት) አማካኝ ቦታ እንዲኖሩ ኩባንያዉ ያመቻቻል፡፡

12.3 የደንብ ልብስ የስራ ትጥቅ

ሀ. በኩባንያው ውስጥ በፕሮቴክሽን (ጥበቃ) በአገልግሎትና ሌሎችም ኩባንያው        አስፈላጊነታቸውን ሲያምንበት የደንብ ልብስ (ዩኚፎርም) ሊሰጣቸው ይችላ፡፡

ለ. የፕሮቴክሽን (ጥበቃ) ሰራተኞች፣ መካኒኮች፣ የጥገና ሰራተኞችና የመሳሰሉት ሰራተኞች እንደአስፈላጊነቱ ኩባንያው የሚሰጣቸውን የስራ መሳሪያ ተጠንቅቆ የመያዝና ለድርጅቱ ስም ብቻ የመጠቀም ኃላፊነት አለባቸው፡፡ 

ሐ. ሰራተኛው ለስራ መገልገያ የተሰጡትን የስራ ልብስ በስራ ቦታዎች ላይ መጠቀም አለበት፡፡ 

መ. ሰራተኛው የተሰጠውን የደንብ ልብስና የስራ ትጥቅ በማንኛውም ሁኔታ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችልም፡፡ 

12.4. አባሪ “አባሪ አንድ” የዚህ ክፍል አካል በመሆኑ ይህን ከግንዛቤ በማስገባት ይሠራበታል፡፡ 

ክፍል አስራ ሶስት

የስራ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ

13.1 የስራ ውል የሚቋረጠው በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ነው፡፡ 


ክፍል አስራ አራት

የዲሲፒሊን እርምጃ አወሳሰድና የቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት

14.1. የእርምጃ አወሳሰድ 

የዲሲፒሊን እርምጃ የሚወሰደው በሰው ኃይል አስተዳደር መመሪያ መሰረት ስልጣን በተሰጠው አካል ወይም ኃላፊ ይሆናል፡፡ ከመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ያሉት ለማህበሩ በቀጥታ ግልባጭ ይደረጋሉ፡፡ 

14.2. የዲሲፒሊን እርምጃዎች 

የተፈፀመው ጥፋት ክብደትና ጥፋቱ የተፈፀመበትን ሁኔታ በማመዛዘን ቀጥሎ የተዘረዘሩት የዲሲፒሊን እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላል፡፡  

ሀ. የቃል ማስጠንቀቂያ 

የሰራተኛው የእለት በእለት የስራ አፈፃፀም በቂ አለመሆኑን የቅርብ ኃላፊው ሲረዳና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ ወይም ከፍ ያለ የዲሲፒሊን እርምጃ መውሰድ እንደሌለበት ሲያምንበት የቃል ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ የቃል ማስጠንቀቂያው በሚሰጥበት ጊዜ ሰራተኛው የግል ማህደር ተመዝግቦ ለ3 ወራት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ሆኖም የተሰጠው የቃል ማስጠንቀቂያው ከ3 ወራት በላይ ለሆነ ጊዜ ማጣቀሻ ሆኖ አያገለግልም፡፡ 

ለ. የመጀመሪያ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ለሰራተኛው ከላይ የተሰጠው የቃል ማስጠንቀቂያ ውጤት (መሻሻል) ያለስገኘ ሲሆን ወይም የተፈፀመ ጥፋት ከባድ በመሆኑ ምክንያት የቃል ማስጠንቀቂያ በቂ እንደማይሆን ሲታመንበት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያው ተግባራዊነት የጊዜ ገደብ በተመለከተ የፅሁፍ ማስጠንቀቂው ከተሰበት ቀን ጀምሮ ለ6 ወራት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ማስጠንቀቂያው በሰራተኛው ግል ማህደር ውስጥ ነዋሪ ሆኖ ይቀመጣ፡፡ ሆኖም የተሰጠው የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ6 ወራት በላይ ለሆነ ጊዜ ማጣቀሻ ሆኖ አያገለግልም፡፡  

  1. የጉቦ ወይም ማናቸውም የሙስና () ተግባሮችን መፈፀም 
  2. ያለበቂ ምክንያትና ያለፈቃድ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ከስራ መቅረት ወይም በአንድ ወር ውስጥ 10 የስራ ቀናት መቅረት ወይም በዓመት ውስጥ 30 የስራ ቀናት መቅረት ወይም ያለ ክፍያ በተሰጠ ፈቃድ የፈቃዱ ቀን ካለቀ በኋላ ያለበቂና ባልተረጋገጠ ምክንያት ከ05 ቀናት በላይ በስራ ላይ አለመገኘት፡፡ 
  3. በስራ አጋጣሚ ያወቃቸው በሚስጢር መጠበቅ ያለባቸውን የድርጅቱን ሚስጢር፣ ሰነድና መረጃ የግል ጥቅም ለማግኘጥ አሳልፎ የሰጠ ወይም ያባከነ ለግል ጥቅም ያዋለ፡፡ 
  4. ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በማንኛውም የድርጅቱ ንብረት ላይ ከባድ ጉድለት ማድረስ ይኸውም አስፈላጊው መረጃ ተጣርቶ በሚመለከተው ባለሙያ ሲረጋገጥ ይሆናል፡፡ 
  5. በኩባንያው መኪና /ተሽከርካሪ/ እና ከድርጅቱ ስራ ቦታዎች ውስጥ የአልኮል መጠጥ መጠጣት ወይም በአደንዛዥ እጽ ጫት መጠቀም ወይም በስራ ሰዓትና በስራ ቦታ ሰክሮ መገኘት /ለሲጋራ ማጨሻ ከተከለከለ ስፍራ ማጨስ፡፡ 
  6. የኩባንያው ሰራተኛ የሆነና ያልሆነ ሰው የኩባንያውን መኪና እንዲያሽከረክር መፍቀድ 
  7. ያልተፈቀደላቸውን ሰዎች ወይም ጓዝ በኩባንያው መኪና መጫንና መጓጓዝ 
  8. በኩባንያው የስራ ቦታ በገንዘብ የኪሳራ ጨዋታዎች /ቁማር/ መጫወት ውጤቱ ከግምት ሳይገባ የኩባንያው የንግድ መርህ ወይም ፖሊሲ የሚፃረር ማንኛውንም ተግባር ከኩባንያው ውጪ መፈፀም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በህገ ወጥ መንገድ በድርጅቱ ንግድ ስራ ውስጥ መሳተፍ ወይም ይህን ተግባር ለሚፈፅሙ ድጋፍ መስጠት፡፡ 
  9. በኩባንያው ንብረትና በሰው ህይወት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ለመከላከል ታስበው የወጡ የደህንነት ጥበቃ ደንቦች አለማክበርና ውጤቱም በኩባንያው ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት እንዲሁም የሰው ህይወት ላይ አደጋ ሊያደርስ የሚችል ተግባር መፈፀም፡፡ 
  10. በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ መገኘትና በጥፋቱም ምክንያት ለተመደበበት ስራ ብቁ ሆኖ አለመገኘት፡፡ 
  11. የኩባንያውን ተወዳዳሪነት ሊያኮስሱ የሚችሉ የስም ማጥፋት ለተወዳዳሪ ምስጢር የማሳለፍና ደንበኛን የማራቅ ተግባሮችን መፈፀም፡፡ ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት ጥፋቶች እርምጃ ከወሰዱ በፊት ትክክለኛነቱና ህጋዊነቱ በበቂ ማስረጃ ማረጋገጥና ማጣራት አለበት፡፡ 

ሐ. ለሌሎች ተጨማሪ የጥፋት አይነቶች የሚፈፀመው የቅጣት ደረጃ ከዚህ ኃብረት ስምምነት ጋር በተያያዘው ሰንጠረዥ (አባሪ ሁለት) እንደተገለፀው ይሆናል፡፡ 

14.4. የቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት 

ሀ. ማንኛውም የዲሲፒሊን እርምጃ የተወሰደበት ሰራተኛ በሰው ኃይል የአስተዳደር መመሪያና ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ቅሬታውን በአቤቱታ ወይም በይግባኝ የማቅረብ መብት አለው፡፡ 

ለ. አቤቱታው ወይም ይግባኝ ማለት የሚችለው የዲሲፒሊን እርምጃ አወሳሰድ ስርዓቱን የጣሰ ነው ወይም ቅጣቱ በጥርጣሬና በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ነው ወይም ከጥፋቱ ጋር ያልተመዛዘነ ነው ወይም ጥፋት ያልተፈፀመ በመሆኑ ቅጣቱ አግባብነት የለውም በሚል ምክንያት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

 

14.5. የቅሬታ አቀራረብ ደረጃዎች 

ደረጃ አንድ፡- የዲሲፒሊን እርምጃ የተወሰደበት በ7 ስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን በፁሁፍ ለቅርብ ኃላፊው ማቅረብ ይችላል፡፡ በግልባጭ ለሰው ኃይል አገልግሎት እንዲደርሰው ያደርጋል፡፡ 

ደረጃ ሁለት፡- አቤቱታው በደረሰው ከ7 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የክፍሉ ኃላፊው ከሰው ኃይል አገልግሎት ጋር በመሆን አቤቱታውን ይመረምራል ሰራተኛውን ያነጋግራል፡፡ 

  • አቤቱታው ሰራተኛው ባለበት ውይይት ከተደረገበት በኋላ የዲሲፒሊን እርምጃው ስለመፅናቱ ወይም ስለመሻሩ ይነገረዋል፡፡ 
  • አቤቱታው ተቀባይነት አግኝቶ የዲሲፒሊን እርምጃው እንዲሻር በተወሰነ በሰራተኛው የግል ማህደር የተመዘገበው የስነ ስርዓርት እርምጃ እንዲሰረዝለት ይደረጋል የተወሰነበት ቅጣት ካለም ይነሳለታል፡፡ 

ደረጃ ሦስት፡- ከላይ በደረጃ ሁለት በተሰጠው ውሳኔ ሰራተኛ የማይስማማ በሚሆንበት ጊዜ የመጨረሻ አቤቱታ ለዋና አስኪያጅ ወይም ለተወካዩ ሊቀርብ ይችላል፡፡ 

  • በዚህ ደረጃ ዋና እራ አስኪያጅ ወይም ተወካዩ አቤቱታው በደረሰው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ከሰው ኃይል አስተዳደር ጋር በመሆን ሰራተኛው አቤቱታ ያቀረበበትን ምክንያት ይመረምራል፡፡ 
  • ሁለቱም ወገኖች በተገኙበት በአቤቱታው ላይ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይም ተወካዩ የመጨረሻው የአስተዳደር ውሳኔ ይሰጣል፡፡ 

ክፍል አስራ አምስት

ልዩ ልዩ

15.1. ስለ አለመግባባቶች 

የህብረት ስምምነቱን አተረጓጎም በተመለከተ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በቅድሚያ በኩባንያውና በሰራተኛው ማህበር መካከል በሚደረጉ ውይይቶች ለመፍታት ጥረቶች ያደርጋል፡፡ አለመግባባቱ በዚህ ጥረት ሊወገድ ካልቻለ በስራ ላይ ባለው አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ መሰረት ታይቶ ውሳኔ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ 

15.2. ለፍተሻ የመተባበር ግዴታ 

ኩባንያው የስራ ቦታ ንብረትና የሰራተኛው ደህንነት በአግባቡ መጠበቅ ስላለበት በኩባንያው ስራ ቦታና ክልል አስፈላጊ ነው ተብሎ በሚታመንበት ቦታና ጊዜ ፍተሻ ይካሄዳል፡፡ የኩባንያው ሰራተኞችም የመተባበር ግዴታ ስላለባቸው አልፈተሽም ማለት አይችሉም፡፡  

15.3. የጦር መሳሪያና ስለት በተመለከተ 

በድርጅቱ ካልተፈቀደ በስተቀር በስራ ቦታ የጦር መሳሪያና ለህይወት አስጊ የሆኑ ስለቶች ሌሎችም ተመሳሳይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ መሳሪያዎችን መያዝ አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡ ይዞ መገኘትም እንደ ከባድ ጥፋት ይቆጠራል፡፡ የድርጅቱ ደህንነት የራሱ የሰራተኛው ደህንነት መሆኑን በመገንዘብ የኩባንያው ሰራተኛ በአንቀጽ 16.2 እና በዚህ አንቀጽ የተጠቀሱትን በአግባቡ እንዲያከብሩ ይተባበራል፡፡ 

15.4. የኩባንያው የስራ ቋንቋ  

የኩባንያው የስራ ቋንቋ እንግሊዘኛ ቢሆንም በተቻለ መጠን ለሰራተኛ የሚተላለፉ መልዕክቶች፣ ከማህበሩ ጋር የሚደረጉ የፅሁፍ ግንኙነት በአማርኛ ይሆናሉ፡፡ በፅሁፍ የሚደርሱ የስነ-ስርዓት እርምጃዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በተጠየቀው መሰረት ይተረጎሙታል፡፡ 

15.5. አጠቃላይ ማስታወቂያዎች 

ጠቅላላ ሰራተኛው የሚመለከት ማስታወቂያና መልዕክት ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያዎች በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፉበት ቀን ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ተለጥፈው ይቆያሉ፡፡ 

15.6. የህብረት ስምምነቱ ፀንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ 

የህብረት ስምምነቱ ፀንቶ የሚቆይበት ለሁለት ዓመት ይሆናል፡፡ 

ሀ. ይህ የህብረት ስምምነት የሰራተኛንማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ለሁለት አመታት የፀና ይሆናል፡፡ 

ለ. ኩባንያውና የሰራተኛ ማህበር የህብረት ስምምነቱን አንቀጾች በማንኛቸውም ጊዜ በስምምነት ለማሻሻል ወይም ለመለወጥ ይችላሉ፡፡ ሆኖም የተሻሻለው ወይም የተለወጠ አንቀጽ በተዋዋይ ወገኖች አማካኝነት ለአዲስ አበባ መስተዳደር የሲቪልና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ለምዝገባ ይላካል፡፡ 

15.7. አባሪዎች 

በዚህ ህብረት ስምምነት የተጠቀሱት አባሪዎች በሙሉ የህብረት ስምምነት አካል ሆነው ይቆጠራሉ፡፡ 





15.8. የተስማሚ ወገኖች ፊርማ 

ስለ ኩባንያው 


ስም ______________________

ፊርማ ______________________

ቀን    ______________________ 

ምስክሮች 

ስለ ድርጅቱ 

ስም ______________________

ፊርማ ____________________

ቀን ______________________

ስም ______________________

ፊርማ ____________________

ቀን ______________________

ስም ______________________

ፊርማ ____________________

ቀን ______________________

   ስለ ሰራተኛ ማህበር 

______________________

______________________

______________________


    ስለ ሰራተኛ ማህበሩ

______________________

______________________

______________________

______________________

______________________






       






የስራ ልብስና የንፅህና መጠበቂያ

ተ.ቁ 

የሰራ መደብ 

የሚሰጠው የእቃ አይነት 

ብዛት 

የእደላው ጊዜ 

አስተያየት 


የጥበቃ ሰራተኛ 

 
ቲትሮን ኮትና ሱሪ

1

በየአመቱ 




ሸሚዝ

1

በየአመቱ 




መለዮ

1

በየአመቱ 




ጥንድ የወታደር ቡት ጫማ

1

በየአመቱ 




የሱፍ ካፖርት

1

በየሁለት አመት 




የዝናብ ልብስ

1

በየሁለት አመት




የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



ሹፌርና ረዳት 

ቱታ

1

በአመቱ 




ሳሙና

1

እንዳለቀ 



ጽዳት ሰራተኛ 

ገዋን

1

እንዳለቀ 




ጥንድ የእጅ ጓንት

1

በየወሩ 




የአፍንጫ መሸፈኛ (ከጨርቅ የተሰራ)


በየአመቱ 




የገላ ሳሙና እና አጃክስ

1

በየወሩ 



ተላላኪ 

ገዋን

1

በየአመቱ 




የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



ሰዓት ተቆጣጣሪ 

ገዋን

1

በየአመቱ 




የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



ጠቅላላ አገልግሎት ሱፐር ቫይዘር 

ገዋን

1

በየአመቱ 




የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



የምርት አገልግሎት ሱፐር ቫይዘር 

ገዋን

1

በየአመቱ 




የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



የመጋዘን ኃላፊ 

ገዋን

1

በየአመቱ 




ቱታ ከነአላባሽ

2

በየወሩ 



የኤሌክትሪክ ሽፍት ኃላፊ 

የገላ ሳሙና

1

በየአመቱ 



ኤሌክትሪሺያን 

አጃክስ

1

በየወሩ 



ተ.ቁ

የስራ መደብ

የሚሰጠው የእቃ አይነት

ብዛት

የእደላው ጊዜ

አስተያየት


ቴክኒክ ክፍል ኃላፊ 

ቱታ ከነአላባሹ 

1

በየአመቱ 




አጃክስ 

1

በየወሩ 




የገላ ሳሙና 

1

በየወሩ 



ስትሪዮዎ ክሊቼ ቆራጭ (ዲዛይር)

ቱታ ከነአላባሽ 

2

በየአመቱ 















መካኒክ 

ቱታ ከነአላባሹ 

2

በየአመቱ 




አጃክስ ሳሙነ

1





የገላ ሳሙና 

1




ማሽኒስት 

ቱታ ከነአላባሹ 

2

በየአመቱ 



ረዳት ማሽኒስት 

የአይን መሸፈኛ ጎግል 

1

እንዳለቀ 



በያጅ 

አጃክስ 

1

በየወሩ 




የገላ ሳሙና 

1

እንዳለቀ 




የእጅ ጓንት (ጥንድ)እና ጫማ 

1

በየአመቱ 



ቴፕ ፕላንት ጥሬ ዕቃ መጋቢ 

ቱታ ከነአላባሽ  

1

በየአመቱ 



ቴፕ ፕላንት ኦፕሬተር 

ቱታ ከነአላባሽ 

1

በየአመቱ 



ዋይንደር ሰራተኛ 

ቱታ 

1

በየአመቱ 



ሪፕሮሰስ (ሪሳይክል)

ካኪ ቱታ ከነአላባሽ፣ ለሴቶች ገዋን 

2

በየአመቱ 




አጃክስ 

1

በየወሩ 




የገላ ሳሙና 

1

በየወሩ 




የጆሮ እና የአፍንጫ መሸፈኛ 

እንዳለቀ 

እንዳለቀ 



ማተሚያ ማሽን ኦፕሬተሮች እና ሰራተኞች

ቱታ ከነአላባሹ 

በየአመቱ 




የአፍንጫ መሸፈኛ ጎግል 

እንዳለቀ 

እንዳለቀ 



ማሸጊያ ማሽን ሰራተኞች 

ዋን 

በየአመቱ 



ቆራጭ 

አጃክስ 

1

በየወሩ 




ጓንት 

እንዳለቀ 

እንዳለቀ 


ተ.ቁ

የስራ መደብ

የሚሰጠው የእቃ አይነት

ብዛት

የእደላው ጊዜ

አስተያየት


የምርት ጥራትና ቁጥጥር 

 
ገዋን

1

በየአመቱ 



ሽመናና እና ማጠናቀቂያ ሱፐርቫይዘሮች 

አጃክስ

1

በየወሩ 



የሽመናና ማጠናቀቂያ ሺፍት ሊደሮች 

የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



የተጠናቀቁ ምርቶ ተረካቢና አስረካቢ 






ምርት ሰብሳቢ 






ሉም ኦፕሬተር 

የድምጽ መከላከያ

እንዳለቀ 

እንዳለቀ 



ስፌት ማሽን ኦፕሬተር 






ኮንዲዩት ሰራተኞች 

ለሴቶች ገዋን

2

በአመት 




የገላ ሳሙና እና አጃክስ

1

በየወሩ 




የአፍ እና አፍንጫ ማክስ

1

እንዳለቀ 



ለኮንድዩት ሱፐር ቫይዘር 

ቱታ ከነአላባሹ

በአመት 




አጃክስና የገላ ሳሙና

1

በአመት 




ጫማ

1

በአመት



ለብሎው ፊልም ሰራተኞች 

ካኪ ቱታ ለሴቶች ገዋን

1

በአመት




የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



የኤሌክትሪክ ገመድ ሰራተኞች 

ካኪ ቱታ፣ ለሴቶች ገዋን

1

በአመት 



የኤሌክትሪክ ገመድ ኦፕሬተሮች 

ካኪ ቱታ ከነአላባሹ

2

በአመት




አጃክስና የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



 
ምርትና ቴክኒክ ኃላፊ 

ገዋን

1

በአመት



ምርትና ቴክኒክ ፀሀፊ 

ሶፍትና የገላ ሳሙና

1

በየወሩ 



የዕቃ ግዢ 






የቢሮ ሰራተኞች 











ከክፍል አስራ አራት ጋር የተያያዘ


ተ.ቁ

የጥፋት አይነት

ለመጀመሪያ ጊዜ

ለሁለተኛ ጊዜ

ለሦስተኛ ጊዜ

ለአራተኛ ጊዜ

ለአምስተኛ ጊዜ

ለስድስተኛ ጊዜ


ያለፈቃ ወይም ያለበቂ ምክንያት ከአ 10 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት መዘግየት

የቃል ማስጠንቀቂያ

የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ

የአንድ ቀን ደመወዝ ቅጣት

የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ

የሰባት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ

ከሥራ ሰንብት


እስጀ ሁለት ቀን ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረት

የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ

የአንድ ቀን ደመወዝ ቅጣት

የሰባት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

የሰባት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ

ከሥራ ስንብት



እስከ ሁለት ቀን ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረት

ያልሰራበት ቀን ደመወዝ ቅጣትና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ

ያልሰራበት ቀን ደመወዝ ቅጣትና የሶስት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

ያልሰራበት ቀን ደመወዝ ቅጣትና የሰባት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

ያልሰራበት ቀንና የአስ ቀናት ደመወዝ ቅጣት እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ

ከሥራ ስንብት



ለሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ያለፈቃድ መቅረት

ያልሰራበትን ቀን ደመወዝ ቅጣትና የአራት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

ያልሰራበትን ቀን ደመወዝ ቅጣትና የአራት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

ያልሰራበትን ቀን ደመወዝና የስምንት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

ያልሰራበት ቀንና የአስ አምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣት እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ

ከሥራ ስንብት



ተ.ቁ

የጥፋት አይነት

ለመጀመሪያ ጊዜ

ለሁለተኛ ጊዜ

ለሦስተኛ ጊዜ

ለአራተኛ ጊዜ

ለአምስተኛ ጊዜ

ለስድስተኛ ጊዜ


ለአራት ተከታታይ የስራ ቀናት ያለፈቃድ መሰረት

ያልሰራበትን ቀን ደመወዝ ቅጣትና የአራት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

ያልሰራበትን ቀን ደመወዝ ቅጣትና የስምንት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

ያልሰራበትን ቀን ደመወዝና የአስራ ቀናት ደመወዝ ቅጣት

ከሥራ ስንብት




ስራ ከገባ በኋላ ከስራ ገበታው ላይ የሚጠፋ

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ

የሶስት ቀናት ደመወዝ ቅጣት እና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ

የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማጠንቀቂያ

ከሥራ ስንብት



7

በምድብ ስራ ቦታ ላይ መተኛት

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ

የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ

የአስር ቀናት ደመወዝ ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ

ከሥራ ስንብት



8

ሁኔታዎች በተሟሉበት ጥራቱም ሆነ መጠኑ ሊለካ የሚችል ስራ ላይ ዝቅተኛ የስራ አስተዋፅኦ ማድረግ

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ

የሁለት ቀናት ደመወዝ ቅጣት

የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ

ከሥራ ስንብት



9

የብልግና ተግባር በቢሮ ወይም በመኪና ውስጥ ፈፅሞ መገኘት 

አስር ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የአስራ አምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣት እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 






10 

ምግባረ ቢስ ተግባር መፈፀም ለምሳሌ፤ ለስራ አላስፈላጊ የሆነ ቁጣ፣ ጭቅጭቅ፣ ለስራ እንቅፋት መሆንና ብልግና ስድብ ወይም ዛቻ 

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የሁለት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የሰባት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 


11 

በኩባንያው የተሰጠውን የስ ትዕዛዝ ወይም መመሪያ አለመቀበል  

ከፁሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የአስር ቀናት ደመወዝ ቅጣት እና የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ  

ከሥራ ስንብት 




12 

ብጥብጥ ለመፍጠር ወሬ መንዛት እንደ ጥፋት ክብድትና ቅለት 

የአስር ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የአስ አምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣት እና የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 




13 

ሆን ብሎ ሁለተኛ የቃል ወይም የፁሁፍ ሪፖርት ማቅረብ  

የአስራ አምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣት እና የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 





14

ሆን ብሎ የኩባንያውን ንብረት ይዘት መለወጥ ወይም መቀየር 


የአስር ቀናት ደመወዝ ቅጣት እና የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 





15 

ያለመንጃ ፈቃድና ያለፈቃድ ኩባንያው መኪና /ተሸከርካሪ/ መንዳት መሽነሪ ማንቀሳቀስ 

የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 







16

ኩባንያውለስ የሰጠውን የስራ ትጥቅና አልባሳት በቂ ባልሆነ ምክንያት ያልለበሰ (ያልተጠቀመ)   

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ   

የአስር ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 



17

ኩባንያው የሚሰጠውን ደብዳቤ አልቀበልም ማለት  

ደብዳቤውን እስኪቀበል ድረስ ከስራ ማገድ 






18

ኩባንያውን የሚጎዳ ተግባር ሲፈፀም አይቶ ለኩባንያው ሳያሳውቁ መቅረት 

የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የአስር ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 




19

ኩባንያው ለመገልገያ ለጤና መጠበቂያ ለአደጋ መከላከያ ብሎ የሰጠውን የስራ ቅጥቅና አልባሳት እንዲሁም የስራ መሳሪ መሸጥ ወይም አሳልፎ መስጠት 

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያና የንብረቱን ዋጋ እንዲከፍል 

የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ የአምስት ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የንብረቱን ዋጋ እንዲከፍል 

ከሥራ ስንብት 




20

ያልተፈቀደና የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ሕጋዊ ሚስት/ባል እና ተወላጅ ያልሆኑ ልጆች ማስመዝገብ 

የአምስት ቀናት 

ደመወዝ ቅጣት 

የአስር ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ከሥራ ስንብት 




21

በተመደበበት ስራ የበላይ ኃላፊው ሲዘው ትእዛዙን ያልተቀበለ 

የ1 ቀን ደመወዝ ቅጣት 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ሰንብት 




22

በስራ ሰዓት የግሉን ስራ የሰራ 

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ1 ቀን ደመወዝ ቅጣት 

የ3 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ4 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 


23

ያለበቂ ምክንያት የስራ ቦታውን ስቆ የሄደ ወይም በየክፍሉ እየተዘዋወረ ሌላውን ሰራተኛ ስራ ያስፈታ 

የቃል ማስጠንቀቂያ 

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ2 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 


24

የድርጅቱን ተሽከርካሪ በቸልተኝነት ወይም በጥንቃቄ ጉድለት ጉዳት ያደረሰ በባለሙያ /በመካኒክ/ ምስክርነት እንደ ጥፋቱ ክብደት የተበላሸውን ሂሳብ ከፍሎ  

የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ2 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 



25

በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁማር መጫወት እንደ ጥፋቱ ክብደት ከስራ ታግዶ 

የ2 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 




26

በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ክልክል በሆነበት ቦታ ሲጋራ ማጨስና ተቀጣጣይ ነገሮችን መጠቀም 

የቃል ማስጠንቀቂያ 

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ2 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ10 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

ስንብት 

27

በድርጅቱን ባልደረቦች መሳደብ፣ የማይገባ ፁሁፍ በሽንት ቤት ውስጥ የፃፈና መፃፉ የተረጋገጠ 

የቃል ማስጠንቀቂያ 

የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 



28

የድርጅቱን የስራ ማሽን በተንኮል ወይም ከሙያ እውቀቱ በላይ በስራ ላይ በመሳተፍ ያበላሸ ያበላሸውን መክፈሉ ተጠብቆ 

ከስራ በማገድ በዲሲፒሊን ኮሚቴ ጉዳይ ታይቶ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ 

29 

ለድርጅቱ ይጠቅማሉ ተብለው ለረጅም ጊዜ የሚቆይና ለአጭር ጊዜ የተለጠፈ ማስታወቂያ የቀደደ ወይም ድርጅቱ ሳያውቀው ሌላ ማስታወቂያ የለጠፈ 

የቃል ማስጠንቀቂያ 

የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ10 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 

30 

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የምርት ሂደት የሚቀንስ ወይም የድርጅቱንም ሆነ የሰራተኛውን ጥቀም የሚፃረር አድራጎት መፈፀም 

የቃል ማስጠንቀቂያ 

የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ10 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

መጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 

31

በድርጅቱ ውስጥ ያለድርጅቱ ፈቃድ የሀንዘብ ማሰባሰብና ልመና የስራ በእለቱ ያልሰራበት ደመወዙ ተመላሽ ሆኖ

የ01 ቀን ደመወዝ ቅጣት 

የ3 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

ስንብት 



32 

በመውጫና መግቢያ ብር ላይ ለመፈተሸ ፈቃደኛ ያልሆነ 

ወደ ውጪ መውጣትና ወደ ውስጥ እንዳይገባ በጥበቃ ሰራተኞች መከልከል 

33

የስራ ኃላፊ ሆኖ የምርት ብልሽት ወይም የመሳሪያ ብልሽት ሲደርስ እርምጃ ያልወሰደ እንደ ጥፋቱ ክብደት 

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ3 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ10 ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 


34

የስዓት ለቀረ ሰራተኛ የሰዓት ፊርማ የፈረመ 

የ10 ቀናት የደመወዝ ቅጣት 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንበት 



35 

ከስራ ለቀረ ሰራተኛ የሰዓት ፊርማ የፈረመ 

የ10 ቀናት የደመወዝ ቅጣት 

የ15 ቀናት የደመወዝ ቅጣት 

ስንብት 




36

ምትዕዛዝ መሰረት እንዲቆረጥ፣ እንዲታተ፣ እንዲሰፋና እንዲታሸግ የታዘዘውን ያበላሸ 

የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ 

የ2 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 



37

የድርጅቱን ንብረትና ገንዘብ የሰረቀና ያጎደለ ዋጋውን መክፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ እንደ ጥፋቱ ክብደት 

የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ በሚፈቅደው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡  



በሚፈቅደው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

38 

በኃላፊዎችና በሰራተኞች ላይ እንዲሁም በስራ ላይ ሁከት የፈጠረ ለጊዜው ከስራ ታግዶ 

የ1 ቀን ደመወዝ ቅጣት 

የ3 ቀናት ደመወዝ ቅጣት

የ7 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

ስንብት



39

ሀሰተኛ ማስረጃ ያቀረበ ማስረጃው የያዘው መብት ውድቅ ተደርጎ 

የ2 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ5 ቀናት ደመወዝ ቅጣት

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት



40 

ሰክሮ በስራ ቦታ መገኘት በእለቱ ከስራና ከደመወዝ ተመላሽ ሆኖ 

የ2 ቀናት ደመወዝ ቅጣት 

የ6 ቀናት ደመወዝ ቅጣት

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት 




በብክሮቤ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር መሰረታዊ የሠራተኞች ማህበር የአሰሪና ሠራተኛ የህብረት ስምምነት -

Start date: → Not specified
End date: → Not specified
Public/private sector: → 
Concluded by:
Loading...