Collective Agreements Database


ማውጫ


የህብረት ስምምነት አላማ 

ገጽ 


አንቀጽ

ትርጓሜ

1


አንቀጽ

የሰራተኛ ማህበሩን ስለማወቅ 

4


አንቀጽ

ስህተትን ስለማረም 

5


አንቀጽ

የዚህ ህብረት ስምምነት አተረጓጎም 

6


አንቀጽ

የአክሲዮን ማህበሩ መብት 

6


አንቀጽ

የአክሲዮን ማህበሩ ግዴታ 

7


አንቀጽ

የሠራተኛ ማህበሩ መብት 

8


አንቀጽ

የሠራተኛ ማህበሩ ግዴታ 

9


አንቀጽ

የሠራተኛው መብት 

10


አንቀጽ 10 

የሠራተኛው ግዴታ 

10


አንቀጽ 11 

የሥራ ውል አመሰራረት 

11


አንቀጽ 12

የሙከራ ጊዜ 

11


አንቀጽ 13 

የሥራ አፈጻጸም ምዘና 

12


አንቀጽ 14 

የደረጃ ዕድገት አሰጣጥ ሥርዓት 

13


አንቀጽ 15 

የዝውውር አፈጻጸም ስርአት 

17


አንቀጽ 16 

በተለያዩ ምክንያቶች በእስር ላይ ቆይተው ስለሚመለሱ ሰራተኞች 

18


አንቀጽ 17 

የሥራ ውል የሚቋረጥበት ሁኔት እና የካሳ አከፋፈል 

19


አንቀጽ 18 

ለፈጠራና ለሥራ ማሻሻያ ስለሚሰጡ የማትጊያ ሥርዓት የኮሚቴ አወቃቀር 

20


አንቀጽ 19 

መደበኛ የሥራ ሰአትና የደመወዝ ክፍያ 

21


አንቀጽ 20 

የትርፍ ሰዓት ሥራና አከፋፈል 

22


አንቀጽ 21 

የደመወዝ መክፈያ ጊዜ 

23


አንቀጽ 22 

የደመወዝ ጭማሪ 

24


አንቀጽ 23

የውሎ አበል ክፍያ 

24


አንቀጽ 24

የመብት ጥያቄ ስለሚቀርብበትና የክፍያ የይርጋ ጊዜ 

25


አንቀጽ 25

የሠራተኛ ደህንነትና ጤንነት 

25


አንቀጽ 26

የሠራተኛ ደህንነትና ጤንነት ኮሚቴ አመሰራረት 

26


አንቀጽ 27 

የአደጋ መከላከያ መሣሪያ የሥራ እና የደንብ ልብስ አሰጣጥ 

26


አንቀጽ 28

የህክምና አገልግሎት 

27


አንቀጽ 29

ከሥራ ጋር ለተያያዘ ጉዳይ የሚሰጥ የህክምና ክፍያ 

30


አንቀጽ 30

በህመም ምክንያት የሚሰጥ ሥራ 

31


አንቀጽ 31

ኢንሹራንስ /መድን

31


አንቀጽ 32

የዓመት ዕረፍት ፈቃድ 

32


አንቀጽ 33

የሕመም ፈቃድ 

33


አንቀጽ 34

የወሊድ ፈቃድ 

34


አንቀጽ 35

የጋብቻ ፈቃድ 

35


አንቀጽ 36

የሐዘን ፈቃድ 

35


አንቀጽ 37

ነፃ ፈቃድ 

36


አንቀጽ 38

ለሠራተኛ ማህበር ስራ የሚሰጥ ፈቃድ 

36


አንቀጽ 39

ልዩ ልዩ ተግባራትን ለማከናወን ለሠራተኛ ስለሚሰጥ ፈቃድ 

37


አንቀጽ 40

የሕዝብ በዓላት 

37


አንቀጽ 41

የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና 

38


አንቀጽ 42

የትምህርት ድጋፍ 

38


አንቀጽ 43

የማህበራዊ አገልግሎት 

40


አንቀጽ 44

የመዝናኛ አገልግሎት 

41


አንቀጽ 45

የበዓል መዋያ ክፍያ 

42


አንቀጽ 46

የብድር አገልግሎት 

42


አንቀጽ 47

ጡረታ 

42


አንቀጽ 48

የትራንስፖርት አገልግሎት 

43


አንቀጽ 49

የፖስታ አገልግሎት 

44


አንቀጽ 50

የካዝና መጠባበቂያ ገንዘብ 

44


አንቀጽ 51

ውክልና 

44


አንቀጽ 52

የቅድሚያ ደመወዝ ክፍያ 

44


አንቀጽ 53

የሥነመ-ሥርዓት ጉድለቶችና እርምጃዎች 

44


አንቀጽ 54

የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት 

48


አንቀጽ 55

የሕብረት ስምምነት ስለማሳተም 

48


አንቀጽ 56

የማህበር መዋጮ 

48


አንቀጽ 57

ቦነስ 

49


አንቀጽ 57

የኤች አይ   ኤድስ መከላከያ ተግባር 

49


አንቀጽ 59

ስፖርት 

49


አንቀጽ 60

ስለ ህጎች ውጤት 

50


አንቀጽ 61

ስለ ህጎች ተፈጻሚነት 

50


አንቀጽ 62

የሕብረት ስምምነት በሥራ ላይ ስለማዋል 

50


አንቀጽ 63

የሕብረት ስምምነቱ ፀንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ 

50


አንቀጽ 64

በዚህ ህብረት ስምምነት ያልተጠቀሱ ጥፋቶች 

50


አንቀጽ 65

ወደፊት ስለሚወጡ ህጎች ወይም ስምምነቶች 

51


አንቀጽ 66

የስምምነቱ ዘመንና ስምምነቱን ስለማደስ 

51


አንቀጽ 67

የሥራ የደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ ዝርዝር ሠንጠረዥ 

52


አንቀጽ 68

የሥነ-ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ ሠንጠረዥ 

66


የህብረት ስምምነት ዓላማ

ይህ ስምምነት በአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር እና በአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር የሠራተኛ ማህበር መካከል የተደረገ ሲሆን ከዚህ የሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት፡፡ እነዚህም በድርጅቱ እና በሰራተኛ ማህበሩ ስምምነት ተግባራዊ የሚሆኑ ናቸው፡፡ 

 1. በህብረት ስምምነቱ የተሰጡት እና የሚሰጡትን መብቶች እና ግዴታዎች እንደዚሁም ወደፊት በድርጅቱ እና በሠራተኛ ማህበሩ ስምምነት የሚደረግባቸውን ማንኛውም ጉዳዮች በመንግሥት በታወጁ ደንቦች እና ድንጋጌዎች መሠረት ለማረጋገጥ፣ 
 2. ድርጅቱ በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለማምረት በተቻለ መጠን ውጤታማ መሆንና ምርታማነትን ማሳደግ፣ 
 3. አስፈላጊ ወጪዎችንና የማምረቻ ወጪዎችን በመቀነስ እንደዚሁም ወጪ ቆጣቢ አሠራርን በማዳበር አክሲዮን ማህበሩን ውጤታማ ማድረግ፣ 
 4. በሠራተኞች መካከል፣ በሠራተኛውና በአክሲዮን ማህበሩ መካከል ጥሩ የሥራ ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ፣ 
 5. ሠራተኞች ተወዳዳሪ፣ ምርታማና የፈጠራ ሥራ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል በሠራተኞች መካከል የማበረታቻ ዘዴዎች በመቀየስና የሥራ አፈጻጸማቸውን በማሻሻል ምርታማነትን ማሳደግ፣ 

አንቀጽ 1

ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር በዚህ የህብረት ስምምነት ውስጥ፡

 1. አዋጅ ማለት የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና 494/98 እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ የዚሁ አዋጅ ማሻሻያ የሆኑ አዋጆች ናቸው፡፡ 
 2. አክሲዮን ማህበር (ድርጅትማለት የአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ማለት ነው፡፡ 
 3. የሠራተኛ ማህበር ማለት የአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ውስጥ የተደራጀና በአዋጅ አንቀፅ 115 በተራ ቁጥር 1 (መሠረት 50% +1 አባላትን ያቀፈ ሠራተኛ ማህበር ማለት ነው፡፡ 
 4. አሠሪ ማለት በሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ “2” ቁጥር “1” መሠረት የተገለፀው ማለት ነው፡፡ 
 5. ሠራተኛ ማለት በአዋጅ 377/96 እና 2.3 መሠረት ከአሰሪ ጋር በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ግንኙነት ያለው ማለት ነው፡፡ 
 6. ደመወዝ ማለት በወር ወይም 26 ቀናት አንድ ሠራተኛ በሥራ ውሉ መሠረት ለሚያከናውነው ሥራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ሲሆን የትርፍ ሰዓት ክፍያዎችን፣ የፈረቃ ሥራ አበሎችን፣ ጉርሻ (ቦነስ) ኮሚሽንን፣ የድርጅቱ የጡረታ መዋጮ ድርሻን የመሳሰሉትን አይጨምርም፡፡ 
 7. የግል የሥራ ክርክር፡  ማለት ጉዳዩ የሚመለከተው ሠራተኛ በሕግ፣ በህብረት ስምምነት፣ በደንብ፣ በሥራና በአስተዳደር ደንብ ወይም በሥራ ውል ውስጥ የተመለከተ ሁኔታን የሚሽር ወይም የሚቀንስ እርምጃ አክሲዮን ማህበሩ በመወሰዱ ምክንያት በሠራተኛው የሚነሳ ማናቸውም የሥራ ክርክር ነው፡፡ 
 8. የሕብረት ድርድር፡   ማለት በአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር እና በመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር መካከል ለአራተኛ ጊዜ የተደረገ የሕብረት ስምምነት ማለት ነው፡፡ 
 9. ቀላል ሥራ፡  ማለት አንድ ሠራተኛ የነበረበት ቦታ ወይም የሥራ መደብ ለጤንነቱ የማይስማማ መሆኑ በሐኪሞች ቦርድ ተመስክሮለት በዚህ የህብረት ስምምነት መሠረት ሠራተኛው የሚመደብበት ለጤንነቱ አመቺ የሆነ የሥራ ቦታ ነው፡፡ 
 10. ዝውውር፡ ማለት የሠራተኛውን ደረጃና ደመወዝ ሳይለካ የሚደረግ የሥራ ቦታ ለውጥ ማለት ነው፡፡ 
 11. ዕድገት፡- ማለት ሠራተኞች በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ ባለው ክፍት የሥራ መደብ እንዲወዳደሩ ሲደረግ በመስፈርቱ መሠረት የተወዳዳሪዎች ችሎታ ተመዝኖ ከዝቅተኛ ወደ ከፍተኛ የሥራ ደረጃና በምዘና መሠረት የሚሰጥ የሥራ መደብ ማለት ነው፡፡ 

አንቀጽ 2

የሠራተኛ ማህበሩን ስለማወቅ

በዚህ የህብረት ስምምነው ውስጥ የተጠቀሱት ጉዳዮችና ስለማንኛውም የሥራ ሁኔታዎች ሠራተኞችን የመወከል ከድርጅቱ ጋር የህብረት ስምምነት የመደራደር፣ የመፈራረምና የማሻሻል፣ የሠራተኛውን ቅሬታ በቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት መሠረት ለአክሲዮን ማህበሩ አቅርቦ መፍትሔ ማግኘት ወይም በፍትሕ አካላት በሥራ ክርክር ሠራተኛ የመወከል መብት የአባላቱን 50%+1 የያዘ የሚወክል ማህበር መሆኑን አክሲዮን ማህበሩ አውቆ ተቀብሎታል፡፡  

አንቀጽ 3

ስህተትን ስለማረም

3.1. በዚህ የህብረት ስምምነት በሌሎች ህጎችና መመሪያዎች ያልተፈቀዱ ሁኔታዎች መፈጸማቸው እንደታወቀ አሰሪውና የሠራተኛ ማህበሩ በመወያየት ተገቢው ማሻሻያና ማረሚያ ማድረግ ይችላሉ፡፡ 

3.2. በተጠቃሚው ጥፋት ወይም የተንኮል ስራ ሳይሆን በስህተት ወይም በሌላ ሦስተኛ ወገን ጥፋት ለሠራተኛው ያለ አግባብ የተከፈለ ገንዘብ ሲኖር አክሲዮን ማህበሩ ወይም አሰሪው በስህተት የተከፈለውን ገንዘብ ከሠራተኛ የማስመለስ መብት አለው፡፡ ሆኖም የአከፋፈሉን ሁኔታ የሠራተኛውን የመክፈል አቅም ከግምት በማስገባት የክፍያውን ጊዜ ሊያራዝም ይችላል፡፡ 

3.3. ስህተቱ የተፈጸመው በተንኮል ወይም ሆን ተብሎ በተደረገ ማሳሳይ ሲሆን አሠሪው በዚህ ህብረት ስምምነት ከተጠቀሱት እርምጃዎች ተመጣጣኝ እርምጃ በአጥፊው ላይ በመውሰድ ተፈላጊውን ሂሳብ ማስከፈል ይችላል፡፡ 

3.4. ሠራተኛ ያለውን ጥቅምና መብት በአዋጅ ቁጥር 377/96 ስለይርጋ የተመለከተው ጊዜ ከማለፉ በፊት መብቱን መጠየቅ አለበት፡፡ ነገር ግን በአሠሪው የተፈጠረ ችግር ከሆነ ይርጋ አያግደውም፡፡ 

አንቀጽ4

የዚህ ህበረት ስምምነት አተረጓጎም

በህብረት ስምምነት አንቀጽ ትርጉም ላይ የሚነሱ ማናቸውም ክርክር በአዋጅ ቁጥር 377/96 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል በወጡና በሚወጡ አዋጆች መሰረት ይፈጸማል፡፡ 

አንቀጽ 5

የአክሲዮን ማህበሩ መብት

 1.  ሥራውን ለመምራትና የአክሲዮን ማህበሩን የሥራ ዕቅድ አውጥቶ ሥራ ላይ የማዋል፡፡ 
 2. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና 494/98፣ በአክሲዮን ማህበሩ ደንብ እና በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ሠራተኛን ለመቅጠር፣ ለማስተዳደር፣ የደረጃ፣ የደመወዝ እድገት ለመስጠት፣ ለመቆጣጠር፣ ለመሾም፣ ለመሻር ወይም ከሥራ ለማሰናበት አዋጁንና ሕብረት ስምምነቱን ላይቃረን ይችላል፡፡  አክሲዮን ማህበሩ በብድር የሰጠውን ገንዘብ ከራሱ ከሰራተኛው ደመወዝ በአንቀጽ 46 መሰረት የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 3.  በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና በዚህ የህብረት ስምምነት መሠረት ሠራተኛን በበቂ ምክንያት ለመቅጣት ከደረጃ ዝቅ ለማድረግ፣  
 4. በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት የሠራተኛውን የሥራ ደረጃ ሳይቀንስ በቂ በሆነ ምክንያት ከቦታ ወደ ቦታ የማዛወር፣ 
 5. አዲስ የሥራ ቦታ ለመክፈት ደረጃ ለመስጠት፣ ሥልጠና ለመስጠት እንዲሁም ለነበረው የሥራ ቦታ የሠራተኛችን አስፈላጊነትና የሥራውን ደረጃ ለመለወጥ አስፈላጊውን የሠራተኛ ኃይል ለመመጠን የሚያስፈልጉትን የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ ለመወሰን ሊወሰዱ የሚገባቸውን የሥነ-ሥርዓት እርምጃዎች ለማሻሻል ወይም ይቅርታ ለማድረግ፡፡ 

አንቀጽ 6

የአክሲዮን ማህበሩ ግዴታ

6.1. በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅና በዚህ የህብረት ስምምነት ወይም በሌሎች የመንግስት ሕጎችና መመሪያዎች የተመለከቱትን ግዴታዎች በትክክል በሥራ ላይ ያውላል፡፡ 

6.2. አክሲዮን ማህበሩ በሥራ ውል ከተመለከቱ ልዩ ግዴታዎች በተጨማሪ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል፤ 

6.2.1. ሀ/ ለሠራተኛው በሥራ ውል መሰረት ሥራ የመስጠት፤ 

ለ/ በሥራ ውሉ ወይም በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር ለሥራው የሚያስፈልገውን መሣሪያና ጥሬ ዕቃ ለሠራተኛው ማቅረብ፣ 

ሐ/ አክሲዮን ማህበሩ ወይም አሠሪው ለሠራተኞቹ የሥራ ልብስ፣ የአደጋ መከላከያ ጥቅማ ጥቅም ወቅቱን ጠብቆ የማቅረብ ግዴታ አለበት፣ 

መ/ አክሲዮን ማህበሩ ወይም አሠሪው ከአገልግሎት ውጪ ተቋማት ጋር አገልግሎት ለማግኘት በገባው ውል መሠረት የመፈጸም ግዴታ አለበት፣ 

6.2.2. ለሠራተኛው ደመወዙንና ሌሎች ክፍያዎችን በአዋጁና በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት የመክፈል፣ 

6.2.3. ሠራተኛው የሚገባውን ሰብአዊ ክብር የመጠበቅ እና በአክሲዮን ማህበሩ በማንኛውም ሁኔታ በሠራተኛው መካከል በዘር፣ በጾታ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት አለማድረግ፣ 

6.2.4. ከሥራው በተያያዘ የሠራተኛውን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ ከአደጋ መከላከል የሚያስፈልጉትን እርምጃዎች ሁሉ የመውሰድና እነዚህንም እርምጃዎች በሚመለከት አግባብ ባላቸው ባለስልጣኖች የሚሰጡትን ደረጃዎችና አመራሮች የመከተል፣ 

6.2.5. የሠራተኛው ጤንነት እንዲመራመር በሕግ ወይም አግባብ ባለው ባለስልጣን ግዴታ በሚጣልበት ጊዜ ለምርመራው የሚያስፈልገውን ወጪ ያመቻቻል፣ 

6.2.6. በአዋጅ ቁጥር 377/96 እና በዚህ ሕብረት ስምምነት የተመለከቱትን አግባብ ያላቸውን የሣምንት ዕረፍት፣ የሕዝብ በዓልና ፈቃድ የሠራተኛውን የጤንነት ሁኔታ በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት እና ሌሎችም በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲያዙ የተወሰኑ መረጃዎች የሚያሳይ መዝገብ የመያዝ፣ 

6.2.7. የሥራ ውል በሚቋረጥበት ወይም ሠራተኛው በሚጠይቅበት በማንኛውም ጊዜ ሠራተኛው ሲሰራው የነበረው የሥራ ዓይነት፣ ያገልግሎት ዘመኑና ሲከፈለው የነበረው ደመወዝ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ለሠራተኛ በነፃ የመስጠት፣ የምስክር ወረቀት ለሠራተኛ በነፃ የመስጠት፣ 

6.2.8. አዋጅ ቁጥር 377/96ትን እና ይህንን ሕብረት ስምምነት የሥራ ደንብና በሕግ መሠረት የሚተላለፉ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን ማክበር፣ 

6.2.9. አክሲዮን ማህበሩ አዲስ ሠራተኛ ሲቀጠር ወይም ሲያሰናብት በግልባጭ ለመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ የማሳወቅ፣ 

6.2.10. አክሲዮን ማህበሩ በማንኛውም ሕጋዊ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ ሥራ ጣልቃ አለመግባት 

6.2.11. አክሲዮን ማህበሩ ከሠራተኛ ደመወዝ የሚሰበሰበውን የሥራ ግብር እና ማህበራዊ ዋስትና ለሚመለከተው የመንግስት አካል ገቢ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም በሠራተኛ ማህበሩ ስም የሚሰበሰቡ ሂሳቦችን አክሲዮን ማህበሩ በየመክፈያ ወቅቱ ለሠራተኛ ማህበሩ ገቢ ያደርጋል፡፡ 

አንቀጽ 7

የሠራተኛ ማህበሩ መብት

7.1. አክሲዮን ማህበሩ የሠራተኛውን መብትና ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ሠራተኛውን የሚወክለውና ስምምነት የሚያደርገው ማህበሩ መሆኑን ያውቃል፣ 

7.2. አክሲዮን ማህበሩ በሠራተኛው ላይ ከህግና ከህብረት ስምምነት ውጪ በሠራተኛው ላይ እርምጃ የሚወስድበት ሁኔታ መኖሩን ሠራተኛ ማህበሩ በቅድሚያ ካወቀ ይህንኑ ለአክሲዮን ማህበሩ ማሳወቅ ይችላል፡፡

7.3. መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ የሠራተኛውን ሕጋዊ መብት የሚነኩ ሁኔታዎች ከተከሰቱ በማስረጃ አስደግፎ ለአክሲዮን ማህበሩ በማቅረብ እንዲስተካከል የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

7.4. ማንኛውም ሠራተኛ በማህበሩ ለመመረጥና በማህበሩ ሥራዎች ለመሳተፍ በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት መብቱ የተጠቀበ ነው፡፡ 

7.5. አክሲዮን ማህበሩ በማንኛውም ሠራተኛ በየትኛውም ደረጃ በሚገኘው የማህበር መሪ ወይም አመራር አባላት ላይ በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት በተፈቀደላቸው የማህበር ስረ ቀን የማህበሩን ስራ በመሥራታቸው ምክንያት ከሥራ በማዛወር የደረጃ እድገት በመከልከልም ሆነ በሌላ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጽእኖ አያደርግም፡፡ 

7.6. በየሩብ ዓመቱና ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ኮፒ ለመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር የማግኘት መብት አለው፡፡ 

አንቀጽ 8

የሠራተኛ ማህበሩ ግዴታ

8.1. ሠራተኛውን በሚመለከት ጉዳይ ላይ የአክሲዮን ማህበሩ ሊያወያየው ሲፈልግ ቀርቦ መወያየት አለበት፣ 

8.2. ከአክሲዮን ማህበሩ ጋር በመተባበር ሠራተኛው የዚህን የህብረት ስምምነት አንቀጾች ትርጉሞችንና አፈጻጸሞችን እንዲረዳ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፣ 

8.3. ሠራተኛው በአክሲዮን ማህበሩ ላይ ቅሬታ ኖሮት ይህንን ቅሬታ ለመፍታት ጥረት በሚደረግበት ወቅት በዚህ ህብረት ስምምነት የቅሬታ አቀራረብ ደንብ መሰረት ቅሬታውን እንዲያቀርብ ማስደረግ አለበት፣ 

8.4. የአክሲዮን ማህበሩ ምርት ጥራት እንዲኖረው አሰሪውንም ሆነ ሠራተኛውን የመቀስቀስና የማበረታታት ግዴታ አለበት፣ 

8.5. በዚህ ህብረት ስምምነትና በሌሎች የመንግስት ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የተመለከቱት ሁኔታዎች እንዲከበሩ የማድረግ ግዴታ አለበት፣

አንቀጽ 9

የሠራተኛ መብት

9.1. የሴት ሠራተኞች ሲወጡና ሲገቡ የሚፈተሹት በሴት ፈታሾች ይሆናል፣ 

9.2. አንድ ሠራተኛ በፍ/ቤት የተወሰነበትን ወይም ራሱ የወሰነበት ወይም በህብረት ስምምነት መሠረት የተፈፀመ ካልሆነ በስተቀር ከደመወዝ ላይ ምንም ዕዳ ያለ ራሱ ፈቃድ ተቆራጭ አይሆንም፡፡ 

9.3. በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 እና በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ በዝርዝር የተጠቀሱ መብቶችና የሥራ ሁኔታዎች ተጠቃሚ ይሆናል፣ 

9.4. ሠራተኛው የሰራበትን ደመወዝና ሌላም ሕጋዊ ክፍያ ሲኖር በወቅቱ የማግኘት መብት አለው፡፡ 

9.5. ማንኛውም የአክሲዩን ማህበሩ ሠራተኛ በማህበር ወይም በግል ቅሬታውን ወይም ክርክሩን ለአስማሚ አካል ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ላላቸው የፍትህ አካላት ለማቅረብና ሕጋዊ መብቱን ማስከበር ይችላል፡፡ 

9.6. የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እንደተጠበቀ ሆኖ በሠራተኛው ጥፋት ወይም ቸልተኝነት ሳይሆን በመሣሪያ ብልሽት፣ ጥሬ ዕቃ ዕጥረት ወይም ጥራቱ ቢጓደል እና ሠራተኛው ሳይሰራ ቢውል ሰራተኛው ደመወዙን የማግኘት መብት አለው፡፡ ሆኖም በዚህ ሁኔታ የማነቃቂያ መሰል ክፍያዎችን ሠራተኛው የመጠየቅ መብት አይኖርም፡፡ 

9.7. አንድ ሠራተኛ ሳያውቀው የወቀሳ፣ የማስጠንቀቂያ ወይም የቅጣት ደብዳቤ በግል ማህደሩ ውስጥ አይቀመጥም፣ 

9.8. ሠራተኛው የሥራ መደቡንና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ የማግኘት መብት አለው፡፡ 

አንቀጽ 10

የሠራተኛ ግዴታ

10.1 በሥራ ውል ላይ የተመለከተውን ሥራ ራሱ የመሥራት 

10.2. በተመደደበት የሥራ መደብ በሥራ ውል በዚህ ሕብረት ስምምነትና በሥራ ዝርዝር መመሪያ መሰረት በአሰሪው የሚሰጠውን ትእዛዝ የመፈጸም፡፡ 

10.3. ለሥራ የተሰጡትን መሣሪያዎችንና ዕቃዎች ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ 

10.4. ለሥራው ብቁ በሆነ የአዕምሮና የአካል ሁኔታ በሥራ ላይ መገኘት፣ 

10.5. በራሱ ሕይወትና ጤንነት ላይ አደጋ ሳያስከትል በሥራው ቦታ በሕይወት ንብረት ላይ አደጋ ሲደርስ ወይም አስጊ ሁኔታ ሲፈጠር የማሳወቅና ተገቢውን እርዳታ የመስጠት፣ 

10.6. ራሱንም ሆነ የሥራ ጓደኞቹን አደጋ ላይ የሚጥል ወይም የድርጅቱን ጥቅም የሚነካ ሁኔታ ሲያጋጥመው ወደያውኑ ለአሰሪው የማሳወቅ፣ 

10.7. በአዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎችና በዚህ ሕብረት ስምምነት በሥራ ደንብና በሕግ መሰረት የሚተላለፉ መመሪያዎችና ትዕዛዞችን የማክበር እና ተግባራዊ ማድረግ አለበት፡፡ 

አንቀጽ 11

የሥራ ውል አመሰራረት

11.1. አክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛውን በሚቀጥርበት ጊዜ የሥራ ውሉ ከዚህ በታች የተገለጹትን መያዝ አለበት፣ 

11.1.1. ሠራተኛው የተቀጠረበትን ጊዜ 

11.1.2. የሥራ ውሉ የሚጸናበት ጊዜ

11.1.3. ሠራተኛው የተቀጠረበት የሥራ መደብና ደረጃ፣ 

11.1.4. ለሠራተኛው የሚከፈለው ደመወዝ መጠንና የአከፋፈል ሁኔታ፣ 

11.2. የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና ይህ የህብረት ስምምነትና መንግስት በየጊዜው የሚያወጣቸው መመሪያዎች ሁሉ በተዋዋይ ወገኖች ተፈጻሚ ይሆናል፣ 

አንቀጽ 12

የሙከራ ጊዜ

12.1. ማንኛውም አዲስ ተቀጣሪ በሥራ ውሉ መሠረት ሊመደብበት ለተቃደው ቦታ ተስማሚ መሆኑ በመመዘን ለሙከራ ጊዜ መቅጠር ይቻላል፡፡ እንዲሁም የሙከራ ጊዜው ከ45 ተከታታይ ቀናት ሊበልጥ አይችልም፡፡ 

12.2. ሠራተኛው በሙከራ ጊዜ መጨረሻ በድርጅቱ አስተያየት ሥራው አጥጋቢ ከሆነ በቋሚነት መቀጠልና በጽሁፍ ይገለጽለታል፡፡ ነገር ግን ይህ ካልተፈጸመ የሙከራ ጊዜው ከተፈጸመበት  ቀን አንስቶ በቀጥታ በቋሚነት እንደተቀጠረ ይቆጠራል፣ 

12.3. በሙከራ ጊዜ ላይ ያለ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሠራተኛ ያለው መብትና ግዴታ ይኖረዋል፣ 

12.4 በሙከራ ላይ ያለ ሠራተኛ ለሥራው ብቁ አለመሆኑ አሠሪው በሥራ አፈጻጸም ግምገማ ስልት ሲያረጋግጥ ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ስንብት ክፍያና ካሳ መክፈል ሳይገደድ የሥራ ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ 

12.5. ሠራተኛው በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ ቀድሞ ሲሰራበት በነበረው የሥራ መደብ ላይ እንደገና ሲቀጠር ለሙከራ ጊዜ ሊቀጠር አይችልም፣ 

12.6. ለሙከራ የተቀጠረ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜውን ጨርሶ ቋሚ ከሆነ የአገልግሎት ዘመኑ ለሙከራ ከተቀጠረበት ጊዜ ጀምሮ ይቆጠራል፣ 

12.7. በሙከራ ላይ ያለ ሠራተኛ ያለ ማስጠንቀቂያ ሥራውን ሊለቅ ይችላል፣ 

አንቀጽ 13

የሥራ አፈጻጸም ምዘና

13.1. ከአክሲዮን ማህበሩ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሠራተኛው ያለውን አእምሮን አካላዊ ችሎታውን በመጠቀም ከአክሲዮን ማህበሩ በተወሰነ የሥልጠና ኃላፊነት ክልል ውስጥ የተሰጠውን ተግባር በአጥጋቢ ሁኔታ ማከናወኑን ወይም አለማከናወኑን ለማወቅ በተወሰነ ወቅት የሚደረግ ሥርዓት ያለው ግምገማ ነው፣ 

13.2. የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በሠራተኛው የቅርብ አለቃ በሁለት ኮፒ ተሞልቶ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ በሚገኝ ኃላፊ ለአስተዳደር ይላካል፣ በምርት ዘርፍ ፎርማኖች ባሉበት በፎርማኖች ተሞልቶ በሚቀጥለው ኃላፊ ጸድቆ ለአስተዳደር ይላካል ሠራተኛው የሥራ አፈጻጸሙ ከነውጤቱ ተገልጾለት በቅጹ ላይ ይፈርማል፣ የሥራ አፈጻጸም ውጤቱ ከ4.5 በላይና ከ2.5 በታች ነጥብ ሲሆን የሥራ አፈጻጸሙን የሞላው ኃላፊ ማብራሪያ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፣ 

13.3. የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በዓመት ሁለት ጊዜ ታህሳስ 30 እና ሰኔ 30 ይሞላል፣ 

13.4. በአንቀጽ 13.3 ያለው እንደተጠበቀ ሆኖ በሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ጊዜያት መካከል ኃላፊው በየጊዜው የሠራተኛ አፈጻጸም ስለሚሻሻልበት ሁኔታ ክትትል ምክርና እርዳታ ያደርጋል፣ ሆኖም በየትኛውም መልኩ ክትትል እና ምክሩ ባይደረግም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ውቴቱን ላለመቀበል ምክንያት አይሆንም፣ 

13.5. በሥራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት በአማካኝ ነጥብ 2.5 በታች ያገኘ ሠራተኛ ድክመቱን አውቆ እንዲያርም ውጤቱ ይገለጽለታል፡፡ ሠራተኛውም ይህን ስለማወቁ በፊርማው ያረጋግጣል፡፡ 

13.6. በሥራ አፈጻጸም ምዘና ከ3.45 በታች ያገኘ ሠራተኛ ዕድገት አያገኝም፣ 

13.7. ለምርታማነት የሚጠቅም የሥራ ምዘና ሥርዓት ሲዘረጋም ሆነ በሥራ ላይ በመዋሉ ሂደት የሠራተኛ ማህበሩ ሙሉ ትብብር ያደርጋል፣ አንቀጽ 14

የደረጃ እድገት አሰጣጥ ስርአት

14.1. በአንድ ክፍል ክፍት የሥራ መደብ ሲፈጠር ወይም ተለቆ ክፍት በመሆኑ ሠራተኛው በዕድገት እንዲመደብ ሲወስን የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች እንዲወዳደሩ በማስታወቂያ ይገለጻል፣ 

14.2. የሥራ መደቡ የሚጠይቀውን የትምህርትና የሥራ ልምድ የሚያሟሉ ሠራተኞች ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀናት ድረስ ይመዘገባሉ፣ በዚሁ መሰረት የተመዘገቡት ተወዳዳሪዎች የውድድሩ ሂደት ተከናውኖ በአንድ ወር ውስጥ ውጤት ይገለጻል፡፡ ሆኖም የሥራ አፈጻጸማቸው 3.45 በታች አይወዳደሩም፡፡ 

14.3. የደረጃ አድገት ኮሚቴ ስለማዋቀር፣ 

14.3.1. የአስተዳደር መመሪያ ሥራ አስኪያጅ  ሰብሳቢ 

14.3.2. በአክሲዮን ማህበሩ የሚሰየም የሥራ መሪ  አባል 

14.3.3. የፐርሶኔል ሠራተኛ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊ  አባልና ፀሐፊ 

14.3.4. ክፍት የሥራ ቦታ የሚገኝበት የመምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወይም የአገልግሎት ኃላፊ እነዚህ በሌሉበት የዋና ክፍል ኃላፊ  አባል 

14.3.5. የሠራተኛ ማህበር ተወካይ ሁለት ሰው  አባል 

14.4. የዕድገት ኮሚቴ ተግባር 

14.4.1. ለውድድር የተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች የተጠየቀውን መነሻ መስፈርት ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ 

14.4.2. የዕድት እጬውን የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድና፣ የሥራ አፈጻጸምና የማኅበር ሰራተኛ ይመረምራል፣ 

14.4.3. ኮሚቴው ማስረጃዎችን ከመረመረና ትክክለኛነቱን ካጣራ በኋላ ለሚወዳደርበት ቦታ ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የቃል፣ የጽሑፍ ወይም የተግባር ፈተና እንዲሰጥ ያደርጋል፣ ፈተናው ሲሰጥም ሆነ ሲታረም የኮሚቴ አባላት ይገኛሉ፡፡ 

14.4.4. ለውድድር ከቀረቡት መካከል በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጣው በቦታው እንዲመደብ ለአክሲዮን ማህበሩ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ለመጨረሻ ውሳኔ ያቀርባል፣ ሠራተኛው በደረጃ እድገት ተወዳድሮ ለማኅደር ማጣራት የሚያልፈው በቅድሚያ የጽሁፍ፣ የቃል ወይም በማንኛውም የተግባር ፈተና ከ50% በላይ ሲያመጣ ብቻ ነው፡፡ 

14.5. በተሰጠው ዕድገት የሚሰጠው የደመወዝ ጭማሪ የሚወሰነው በአክሲዮን ማህበሩ መዋቅር እና የደመወዝ ስኬል መሠረት ይሆናል፡፡ 

14.6. የዕድገት ኮሚቴ አክሲዮን ማህበሩ አውጥቶ በሚያቀርበው ውስጠ ደንብ መሠረት ሥራውን ያከናውናል፣ 

14.7. ለሠራተኛ ዕድገት የሥራ አፈጻጸምን በተመለከተ የሚሰጠው ነጥብ ከማስታወቂያ ቀደም ብሎ ባሉ ሁለት የሥራ አፈጻጸም አማካኝ ውጤቱ 3.45 በታች ከሆነ ለውድድር አይቀርብም፣ 

14.8. በውድድሩ ሂደት የሥራ አፈጻጸምን በተመለከተ የሚሰጠው ነጥብ ከማስታወቂያ ቀደም ብሎ ባሉ ሁለት የሥራ ጉዳይ ተብሎ በሚመለከተው ኃላፊ እንዲሞላለት ይደረጋል ይህንንም አክሲዮን ማህበሩ የማስፈጸም ኃላፊነት አለበት፡፡ 

14.9. አንድ ሠራተኛ በዕድገት ከተመደበበት የሥራ መደብ ላይ ቢያንስ 12 ወራት ሳያገለግል ለአዲስ ዕድገት ሊወዳደር አይችልም፡፡ 

14.10. ለዕድገት ቦታው ውድድር በሚደረግበት ጊዜ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ተወዳዳሪ ሠራተኞች ጠቅላላ ውጤታቸው እኩል ከሆነ ለሴት ሠራተኞች ቅድሚያ የዕድገት ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ከሆኑ ሌላ ፈተና ይሰጣል፡፡ 

14.11. ለዕድገት የሚሰጠው የደመወዝ ጭማሪ የጸና የሚሆነው የዕድገት ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ በፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ተቀባይነት ካገኘበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡ 

14.12. አንድ ሠራተኛ በዕድገት ተወዳድሮ የሚያገኘው የደመወዝ እርከን ጭማሪ በድርጅታዊው መዋቅር መሠረት አክሲዮን ማኅበሩና ሠራተኛ ማኅበሩ በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት ይሆናል፣ 

14.13 የነጥብ አሰጣጥ ሥርዓት፣ 

14.13.1. ፈተና 

ሀ/ የፈተና ውጤት ከ60% ይያዛል 

ለ/ የማህደር ውጤት ከ40% ይይዛል፣ 

14.13.2. የትምህርት ደረጃ 

 • የትምህርት ደረጃ 16 ነጥብ ይሰጣል፣ 

የትምህርት ደረጃ የነጥብ አሰጣጥ በወጣው ማስታወቂያ ከከፍተኛው መስፈርት ላይ ያቀረበ ሲኖር ከፍተኛው ነጥብ ይሰጥና ቀሪዎቹ እንደየደረጃው በማስላት ነጥብ ይሰጣል፡፡ በማስታወቂያ ከተገለጸው በላይ የትምህርት ደረጃ ያቀረበ ከሌላ ማስታወቂያ ላይ ለሰፈረው ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ከ16 ነጥብ በማሰብ ለቀሩት እንደ ደረጃቸው በስሌት ይሰጣል፡፡ 

14.13.3. የሥራ ልምድ፣ 

 • ለውስጥ ዕድገት
 • ለሥራ ልምድ 16 ነጥብ ይሰጣል፣ 

በዚሁ መሰረት 

 • ለቀጥተኛ የሥራ ልምድ ለአንድ ዓመት 1 ነጥብ፣
 • ለተዘዋዋሪ የሥራ ልምድ በአንድ ዓመት 0.75 ነጥብ፣ 
 • አግባብነት ለሌለው ልምድ በአንድ ዓመት 0.50 ነጥብ፣ 
 • ሆኖም በምንም ሁኔታ ነጥብ ከ16 መብለጥ አይችልም፣ 

14.13.4. የሥራ አፈጻጸም 4 ነጥብ ይሰጣል 

የሥራ አፈጻጸም  ነጥብ  

5 4

4 3

6 2

2 1

በመካከል የሚኖሩ በነጥብ የሚሰጡ ውጤቶች በተመሳሳይ ሁኔታ በዴሲማል እየተሰላ ውጤቱ ይቀመጣል፡፡ 

14.13.5. የማህደር ጥራት 4 ነጥብ ይሰጣል፣ 

የዲሲፒሊን ቅጣት ነጥብ  

 1. ምንም የዲሲፒሊን እርምጃ ያልተወደበት 
 2. የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ  3
 3. የገንዘብ ቅጣት የተወሰደበት  2
 4. የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው  0 ይሆናል 

14.13.6. ለውጭ ቅጥር ብቻ 

ከውጭ በጋዜጣና በተለያዩ ማስታወቂያ ለሚቀጠሩ ከዚህ በታች ያለው መስፈርት ያገለግላል 

 • የሥራ ልምድ 16 ነጥብ ይሰጣል፣ 
 • የቁጥጥር ተግባር ያላቸው ቦታዎች ሆነው ዝቅተኛ መስፈርት ኮሌጅ ዲፕሎማና ከዚህ በላይ የሚጠይቅ የትምህርት ደረጃ ሲሆን፣ የነጥብ አሰጣጡ ከምረቃው በፊትና በኋላ ባሉ አገልግሎቶች ይወሰናል፡፡ 

በዚሁ መሰረት፡- 

 • ከምረቃ በኋላ ለቀጥተኛ የሥራ ልምድ ለአንድ አመት 1 ነጥብ 
 • ከምረቃ በኋላ ለተዘዋዋሪ የሥራ ልምድ ለአንድ ዓመት 0.50 ነጥብ 
 • ከምረቃ በፊት ለተሰጠ ተዘዋዋሪ የሥራ ልምድ ለአንድ ዓመት 0.25 ነጥብ ይሰጣል፣ 
 • ሆኖም ዝቅተኛ መስፈርት ከኮሌጅ ዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ለሚጠይቁ የሥራ መደቦች፣ 
 • በተመሳሳይ የሥራ ልምድ መነሻውን ላሟላ 8 ነጥብ ይሰጣል፣ 
 • ከዚያ በላይ ላሉ ተጨማሪ አገልግሎቶችና ለቀጥተኛ የሥራ ልምድ ለአንድ ዓመት 1 ነጥብ ተጨማሪ ይሰጣል፣ 
 • ለተዘዋዋሪ የሥራ ልምድ ለአንድ ዓመት 0.5 ነጥብ ይሰጣል፣ 

14.13.7 የሥራ አፈፃፀም 

 • ለሥራ አፈጻጸም 4 ነጥብ ይሰጣል፣ 

የሥራ አፈጻጸም  ነጥብ 

5 4

4 3

3 2

2 1

 • በመካከል የሚኖሩ  በነጥብ የሚሰጡ ውጤቶች በተመሳሳይ ሁኔታ በዴሲማል እየተሰላ ውጤቱ ይቀመጣል፣ 
 • ማህደር ጥራት 4 ነጥብ ይሰጣል፣ 
 1. የዲሲፕሊን ቅጣት 
 1. ምንም የዲሲፒሊን እርምጃ ያልተወሰደበት 
 2. የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ  3
 3. የገንዘብ ቅጣት የተወሰደበት 
 4. የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ይሆናል  0

አንቀጽ 15

የዝውውር አፈጻጸም ስርአት

15.1. አንድ ሠራተኛ ከአንድ የሥራ መደብ ወይም ክፍል ወደ ሌላ የሥራ መደብ፣ ክፍል ወይም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚዘዋወረው ለአክሲዮን ማህበሩ ምርት ጥራት ዓላማና እንዲሁም ሥራንና ሠራተኛን በማገናኘት የአክሲዮን ማህበሩን የሥራ ውጤት ለማሻሻል ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ ይሆናል፣ 

15.2. በዚህ ህብረት ስምምነትና በመንግሥት መመሪያዎች የተመለከቱት ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ለሥራው እና ለሠራተኛው ደህንነት ለአክሲዮን ማህበሩ ዕድገት የምርት ውጤት ለማሻሻልና ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ ሲባል ሠራተኞችን ከክፍል ወደ ክፍል ከፈረቃ ወደ ፈረቃ የማዛወር መብቱ የአክሲዮን ማህበሩ ነው፣ 

15.3. አክሲዮን ማህበሩ የሠራተኛውን የሥራ ደረጃ ጠብቆ ወይም ተመሳሳይ የሥራ ድርሻ ሰጥቶ ወይም አክሲዮን ማህበሩ ሲያምንበት የሚያገኘውን ደረጃና ደመወዝ ሳይቀነስ አዛውሮ ሊያሰራ ይችላል፣   

15.4. በቁጥጥር የሥራ መደብ ላይ ያሉ ሠራተኞች ዝውውርን በሚመለከት በአክሲዮን ማህበሩ የበላይ ኃላፊ ሲፈቀድ ይፈጸማል፡፡  

15.5. ዝውውሩ የሠራተኛ ማህበርን ተግባራት እንቅስቃሴ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለመጉዳት በቂም በቀል የሠራተኛውን ዕድገት ለማሰናከል ወይም ሌሎች የሠራተኛን ህጋዊ ጥቅሞች በመቃረን መንፈስ አይፈጸምም፣ 

15.6. አክሲዮን ማህበሩ በራሱ ውሳኔ ከቦታ ወደ ቦታ ለሚያዛውረው ሠራተኛ ለቤተሰብና ለጓዙ ማንሻ የሚያስፈልገውን መጓጓዣ ወይም የማጓጓዣ ወጪ በሚያቀርበው ሕጋዊ ደረሰኝ መሠረት ይከፍላል፡፡ 

15.6.1. ቤተሰብ ለሌለው አንድ ሠራተኛ እስከ አራት ኩንታል ድረስ፣ 

15.6.2. ቤተሰብ ላለው ሠራተኛ እስከ ስድስት ኩንታል ድረስ፣ 

15.6.3. ቤተሰብ ማለት ሕጋዊ ሚስት ወይም ባል እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ የሰራተኛው ልጆች ናቸው፣ 

አንቀጽ 16

በተለያዩ ምክንያቶች በእስር ላይ ቆይተው ስለሚመለሱ ሠራተኞች

16.1 አንድ ሠራተኛ ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ተፈርዶበት ወይም ሳይፈረድበት በእስር ላይ ቆይቶ ሲፈታ ወንጀሉ ሥርቆት ካልሆነ በስተቀር እና ከእስር ከተፈታ በ10 ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ እንዲመለስ ከጠየቀ ሠራተኛው ወደ ሥራው እንዲመለስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ሆኖም ለታሰረበት ወይም ላልሰራበት ጊዜያት ደመወዝ መጠየቅ አይችልም፡፡ 

16.2. በዚሁ አንቀጽ 16.1 ላይ በተጠቀሰው ሁኔታ ሠራተኛው ሲታሰር አክሲዮን ማህበሩ ለአንድ ወር በቦታው ላይ ሠራተኛ ሳይመደብ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የሥራው ባሕርይ ጊዜ የማይሰጥና አጣዳፊ ከሆነ አክሲዮን ማኅበሩ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በቦታው ላይ ባለው የአክሲዮን ማህበሩ መዋቅር መሠረት የሠው ኃይሉን ማሟላት ይችላል፡፡ 

16.3. አክሲዮን ማህበሩ አንድን ሠራተኛ ወንጀል ሰርቷልና ይጣራልኝ ብሎ በግልጽ በተጻፈ ደብዳቤ ለፖሊስ ወይም ለዓቃቤ ሕግ ወዘተ … በስም ጠቅሶ ምርመራ እንዲካሄድ ከጠየቀና በዚሁ መነሻ ሰራተኛው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በህግ ጥፋተኛነቱ ካልተረጋገጠ ወይም በነፃ በተለቀቀ በእስር ላይ ለቆየበት ጊዜ አክሲዮን ማህበሩ የሠራተኛውን ደመወዝ የመክፈልና ወደ ሥራው የመመለስ ግዴታ አለበት፣ 

16.4. አንድ ሠራተኛ ሳይፈረድበት ከአንድ ወር ለበለጠ ጊዜ ታስሮ ሲፈታ አክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛው ያለውን የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድና ለአክሲዮን ማህበሩ የሚያስገኘውን ጠቀሜታ አንጻር ክፍት የሥራ ቦታ መኖሩ ሊረጋገጥ የታሰረበትን ጊዜ ደመወዝ ሳይከፍል ወደ ሥራው ሊመልሰው ይችላል፡፡ 

አንቀጽ 17

የሥራ ውል የሚቋረጥበት ሁኔታ እና ካሳ አከፋፈል

17.1. የአንድ ሠራተኛ የሥራ ውል የሚቋረጠው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ከአንቀጽ 23 እስከ 45 እና በዚህ የህብረት ስምምነት በተመለከቱትና እንዲሁም በመንግስት መመሪያ ይሆናል፡፡ 

17.2. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና 494/98 ወይም በመንግሥት መመሪያ ወይም በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት በሠራተኛው ጥፋት እስካልሆነ ድረስ ከሥራው የሚሰናበት ማንኛውም ሠራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያ ይከፈለዋል፡፡ 

17.3. ማንኛውም ሠራተኛ በዚሁ አንቀጽ 17.2 መሠረት የሥራ ስንብት ክፍያ ማግኘት የሚችለው በቅድሚያ በእጁ የሚገኙትን የአክሲዮን ማህበሩን፣ የመሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበሩን፣ የብድርና ቁጠባ ማኅበርን፣ የሸማቾች የኅብረት ሥራ ማኅበርን ንብረቶች ማስረከቡን፣ ከካንቲን አገልግሎት ክፍያ እና ከሌሎች ዕዳዎች ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥና ክሊራንስ ሲያቀርብ ነው፡፡ 

17.4. የአክሲዮን ማህበሩ ዕዳ የሚፈለግበት ሠራተኛ ዕዳውን የሚችልለት ከሆነ ከሥራ ስንብቱ ላይ ተቀንሶ ተራፊው ብቻ ይከፈለዋል፣ 

17.5. ሠራተኛው ክሊራንሱን አስፈርሞ እንዳቀረበ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት የሚሰናበተው ሠራተኛ ተገቢውን ክፍያና የምስክር ወረቀት በ7 ቀናት ውስጥ ይሰጠዋል፣ 

17.6. የምስክር ወረቀትም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ይይዛል፣ 

ሀ/ የሠራተኛው ስም 

ለ/ የሥራው ዓይነት 

ሐ/ የሥራ መደቡ 

መ/ የአገልግሎት መደብ 

ሠ/ የመንግስት ግብርና የጡረታ መዋጮ ስለመክፈሉ የሚያጠቃልል መግለጫ መሆን አለበት፤ 

17.7. ለተሰናባች ሠራተኞች ለወደፊት ኑሮው አስፈላጊ ነው ብሎ ሲጠይቅ በግል ማህደሩ ውስጥ የሚገኙ መረጃዎች ካሉ እንደ አስፈላጊነቱ በራሱ ወጪ ኮፒ በማድረግ ሊወሰድ ይችላል፤ 

17.8. ሠራተኛው ያልተጠቀመበት የዓመት ዕረፍት ካለው በገንዘብ ተለውጦ ይከፈለዋል፣ 

አንቀጽ 18

ለፈጠራና ለሥራ ማሻሻያ ስለሚሰጡ የማትጊያ ሥርዓት ኮሚቴ አወቃቀር፤

18.1. የአክሲዮን ማህበሩ የማምረት አቅምና ሂደት ለማሻሻያ የሚረዱ የፈጠራ ሥራዎችንና ለአክሲዮን ማህበሩ ዕድገት የሚጠቅሙ አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅ በግንባር ቀደምትነት የሚተጉ ሠራተኞችን ለማበረታታት የተሻሻለ የአሠራር ዘዴ ለማስፈን ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚንቀሳቀሱ ሠራተኞችንና የሥራ ኃላፊዎችን ለማበረታታት አክሲዮን ማህበሩ የማትጊያ ክፍያ ሥርዓት በማውጣት በሥራ ላይ ያውላል በተለይም በተመደበበት ሥራ ላይ አንድ ሠራተኛ ያለማቋረጥ ለ6 ወራት ያለምንም ምክንያትና ሕጋዊ ፈቃድ ያለቀሪ በሥራ ላይ የተገኘ እና የሥራ አፈጻጸሙ አጥጋቢነት በሥራ ክፍሉ የተረጋገጠ ሲሆን፣ አክሲዮን ማህበሩ የማበረታቻ ሥርዓት በማዘጋጀት በሥራ ላይ ያውላል፡፡ 

18.2. የፈጠራና የሥራ ማሻሻያ ሃሳብ ገምጋሚ ከዚህ የሚከተሉት አባላት ያሉበት ኮሚቴ ይቋቋማል 

18.2.1. የአክሲዮን ማህበሩ ኢንጅነሪንግ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ  ሰብሳቢ 

18.2.2. በአክሲዮን ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሚመደብ ባለሙያ  አባል 

18.2.3. ሠራተኛው የሚገኝበት መምሪያ ኃላፊ  አባል 

18.2.4. ከአክሲዮን ማህበሩ አስተዳደር አንድ ተወካይ  አባል 

18.2.2.5. የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ሁለት ተወካይ  አባል

የፈጠራ የሥራ ማሻሻያ ሃሳብ ገምጋሚ ኮሚቴ ያቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ለፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ሲፈቀድ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ 

አንቀጽ 19

መደበኛ የሥራ ሰዓትና ደመወዝ ክፍያ

19.1. መደበኛ የሥራ ሰዓት፣

19.1.1. የማንኛውም ሠራተኛ በቀን መደበኛ የሥራ ሰዓት 8 (ስምንት ሰዓት) በሳምንት 48 (አርባ ስምንት ሰዓት) መብለጥ የለበትም፡፡ የሰዓቱን አቆጣጠር ሠራተኛው ሥራውን እንዲጀምር ከሚያስፈልግበት ጊዜ አንስቶ ይሆናል፣ 

19.1.2. የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች በአክሲዮን ማህበሩ የሥራ ፀባይ መሠረት በሦስት ፈረቃ ተከፍለው የሚሠሩ ሲሆን በመደበኛ የሥራ ሰዓት ጊዜያቸው ሥራቸውን ያከናውናሉ፣ 

19.1.3. የአክሲዮን ማህበሩ የሥራ ሰዓት እንደሚከተለው ነው፡- 

19.1.4. በፈረቃ የሚሰሩ ሠራተኞች፡- 

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 

 • ለጧት ገቢ ከ1፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት 
 • ለከሰአት ገቢ ከ9፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት 
 • ለአዳር ገቢ ከ5፡00 እስከ ጠዋት 1፡00 ሰዓት 

19.1.5. ማንኛውም የሥራ ሰአት ወይም ከሳምንት የእረፍት ቀናት ወይም በበዓላት ቀን ሁሉ ወይም በማንኛውም አጋጣሚ አክሲዮን ማህበሩ ሥራ ቢቆምም ቀጥሎ የተመለከቱት አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች እንደ አስፈላጊነቱ በሥራ ላይ ይገኛሉ፣ 

19.1.5.1 የሕክምና ባለሙያዎችና የአንቡላንስ ሹፌሮች 

19.1.5.2. የጥበቃ ሰራተኞች እንደተለመደው በፈረቃቸው፣ 

19.1.5.3. የኤሌክትሪክ ሠራተኞችና የዲዝል መከተር ተጠባባቂዎች፣ 

19.1.5.4. የውሃ አገልግሎት፣ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች፣ 

19.2.1. የሠራተኛው የሣምንት እረፍት ቀን እሁድ ይሆናል፡፡ ሆኖም ስለ ሕዝብ በዓላትና የዕረፍት ቀን መንግሥት ካስፈለገ ከሥራ ቀናት አንዱን ቀን የዕረፍት ቀን እንዲሆን መመደብ ይችላል፣ 

19.2.2. መደበኛ የሥራ ሰዓት የሚሰሩ ሠራተኞች፣ 

ለአርባ ምንጭ ሰራተኞች 

ከሰኞ እስከ አርብ 

 • ከጧት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት 
 • የምሳ ሰዓት ከ6፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት 
 • ከቀትር በኋላ ከ7፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ሲሆን፣ 

ዘወትር ቅዳሜ ከ2፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ይሆናል፣ 

ለአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሠራተኞች

 ከሰኞ እስከ አርብ 

 • ለጧት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት 
 • የምሳ ሠዓት ከ6፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት 
 • ከቀትር በኋላ ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ይሆናል፤ 

19.2.3. በፈረቃ የሚሰሩ ሠራተኞች በሥራ ሰዓት መካከል 30፡00 ደቂቃ የምግብ ሰዓት መመገቢያ ጊዜ 8፡00 ሰዓት ውስጥ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚሁ የመመገቢያ ጊዜ በስተቀር የምሳ ሰዓት አይኖራቸውም፤ 

19.2.4. በፈረቃ ሠራተኞች ከመደበኛ ሠራተኞች የዕረፍት ሰዓቶች 30 ደቂቃ ብቻ ስለሆነ ምክያት ይህንን ለማካካስ በፈረቃ ለሚሰሩ ሠራተኞች በሚያገኙት የዓመት ፈቃድ ላይ በዓመት ሁለት የሥራ ቀናት ተደምሮ ይሰጣቸዋል፡፡ ሆኖም ወደ መደበኛ ፈረቃ ሲቀየሩ የዓመት ፈቃዱ ይነሳል፡፡ 

19.2.5. የሠራተኛ የፈረቃ ለውጥ የሚደረገው እንደ አክሲዮን ማህበሩ ሥራ ሁኔታ በየሁለት ቀኑ ይሆናል፤ 

አንቀጽ 20

የትርፍ ሰዓት ሥራና አከፋፈል

20.1. አንድ ሠራተኛ በቀን ውስጥ መሥራት ከሚገባው መደበኛ የሥራ ሰዓት በላይ የሚሠራው ሥራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ይሆናል፡፡ የትርፍ ሰዓት የሚፈቀደውንና ክፍያ የሚፈፀመው የትርፍ ሰዓት ሥራው ከ15 ደቂቃ በላይ ሲሆን ነው፡፡ 

20.2. የትርፍ ሰዓት ስራ የሚፈቀደው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 67 መሰረት ለተጠቀሱት የሥራ ሁኔታዎች ነው፣ 

20.3. አንድ በፈረቃ የሚሠሩ ሠራተኛ ተተኪ ሳይመጣለት ከሥራው መለየት ለሥራው ችግር የሚፈጥር ከሆነ ወይም በቦታው ኃላፊ ሳይኖር ቀርቶ ሲሰራ ከቆየ ሠራተኛው ለሰራበት ትርፍ ሰዓት ሥራ በአዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 68 መሠረት ይከፈለዋል፡፡ ይህም በቅርብ ኃላፊ መረጋገጥ፣ መፈቀድና መጽደቅ አለበት፣ 

20.4. የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሰራ የታዘዘ ሠራተኛ ለመስራት ሕጎችን መከተል የማይችልበት በቂ ምክንያት ካለው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 67 መሠረት አይገደድም፣ 

20.5. የትርፍ ሰዓት ሥራ ነፍሰጡሮችን አይመለከትም፣ 

20.6. የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሳይዘገይ በተሠራበት ወር ከደመወዝ ጋር ይከፈለዋል፣ 

20.7. በሠራተኛ የዕረፍት ቀን ላይ የሕዝብ በዓላት ተደርቦ የሚውል ከሆነና ሠራተኛው በዚህ ዕለት ሥራ እንዲገባ ከታዘዘ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 68 ተራ ቁጥር 1 ፊደል “መ” እና በአንቀጽ 75 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ክፍያው የሚፈጸም ይሆናል፡፡ 

20.8. ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ ለሚሠሩ ሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚከፈለው ክፍያ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 68 መሠረት ይሆናል፣ አንቀጽ 21

የደመወዝ መክፈያ ጊዜ፣

21.1. የወር ደመወዝተኛ ተከፋይ ክፍያ የሚፈጸመው እ.ኤ.አ ወር በገባ ከ27-29 ባሉት ቀናት ውስጥ ይሆናል፣ 

21.2. ክፍያዎቹ የሚደረጉበት ቀን በሳምንት ዕረፍት ወይም በሕዝብ በዓላት ቀን ላይ ከዋለ ከመደበኛ የክፍያ ቀን አስቀድሞ ባለው ሁለት ቀን ለሠራተኛው እንዲከፈል ይደረጋል፣ 

21.3. የአንድ ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈለው በቀጥታ ለሠራተኛው ሲሆን በልዩ ልዩ ሕጋዊ ምክንያቶች ሠራተኛው ቀርቦ ለመቀበል ካልቻለ ግን አስተዳደር ባዘጋጀው ቅጽ ጓደኞቹን ወክሎ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ ለወኪሉ ሊከፈለው ይችላል፡፡ ሠራተኛው የአክሲዮን ማህበሩ ባልደረባ ያልሆነ ሰው ለመወከል ከፈለገ ውክልናው በፍርድ ቤት ሕጋዊነቱ በማህተም መረጋገጥ ይኖርበታል፣ 

21.4. አክሲዮን ማህበሩ ለሠራተኛው ከደመወዝ መክፈያ ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ የደመወዝ ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል 

አንቀጽ 22

የደመወዝ ጭማሪ

የደመወዝ ጭማሪ የሚደረገው አክሲዮን ማኅበሩ ትርፋማነቱ በኦዲተሮች ከተረጋገጠ በኋላ ከትርፍ ላይ ከታክስ በኋላ የሚታሰብ ሆኖ በሚከተለው መጠን ይሆናል፡፡ 

 • ከ2,000.000-3,000.000 ከሆነ ከ4.5% 
 • ከ3,000.000-5,000.000 ከሆነ 5%
 • ከ5,000.000 በላይ ከሆነ 6%

  አንቀጽ 23

  የውሎ አበል ክፍያ፣

  23.1. ማንኛውም ሠራተኛ ለሥራ ጉዳይ ከአክሲዮን ማኅበሩ ወይም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሚገኝበት ከክ/ከተማ ክልል 20 ኪ.ሜ ርቆ ሲጓዝ አክሲዮን ማህበሩ የውሎ አበል ይከፍላል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ ለዚህ ተግባር የትራንስፖርት አገልግሎት ካላቀረበ ሠራተኛው በሚያቀርበው ማስረጃ መሠረት የትራንስፖርት ወጪውን ይከፍላል፤ 

  2.3.2. የውሎ አበል ክፍያ እንደሚከተለው ይሆናል 

  የወር ደመወዝ (በብር)  የውሎ አበል (በብር) 

  እስከ  - 499 የወር ደመወዝ  100 ብር 

  ከ500  - 999  110 ብር 

  ከ1000  - 1499  120 ብር 

  ከ1500  - 1999  130 ብር 

  ከ2000 በላይ  140 ብር ይሆናል፡፡

  23.3. ማንኛውም የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ ውሎ አበል ተከፍሎት ከተጓዘ እና ከተፈቀደለት ቀን አስቀድሞ ከተመለሰ እላፊውን የቀን ውሎ አበል ተመላሽ ያደርጋል፤ ከተፈቀደለት ቀን በላይ የሚያስቆይ ሁኔታ መኖሩን ለአክሲዮን ማህበሩ አስቀድሞ ካላሳወቀ ከተፈቀደለት ቀን በላይ የቆየበት አይከፈለውም፡፡ 

  23.4. የበረሃ አበል እንዲከፈልባቸው መንግስት የወሰነባቸው አካባቢዎች ሲሄድ እንደ ሙቀቱ መጠን መንግሥት ባወጣው የበረሃ አበል ስሌትን መሠረት በማድረግ በአበል ላይ በመቶኛ እየተጨመረ ይከፈላል፡፡ 

  23.5. ወደ አጎራባች አገር ወደቦች ለሚደረገው ጉዞ ውሎ አበል የጊዜውን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በአክሲዮን ማህበሩ ይወሰናል፡፡ 

  23.6. ሠራተኛ ለሥራ ጉዳይ እንዲሄድ ከተፈቀደለት በፊት ከተመለሰ ከተመለሰበት ቀን በኋላ ያለው ሂሳብ ተመላሽ ያደርጋል፡፡ 

  አንቀጽ 24

  የመብት ጥያቄ ስለሚቀርብበት የክፍያ የይርጋ ጊዜ፣

  24.1. የመብትም ሆነ የክፍያ ጥያቄ በይርጋ ሊቀር የሚችለው በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 ከአንቀጽ 162-166 በተመለከተው መሠረት ይሆናል፡፡ ሆኖም በአሰሪው የተፈጠረ ችግር ከሆነ ይርጋ አያግደውም፡፡ 

  አንቀጽ 25

  የሠራተኛ ደህንነትና ጤንነት፣

  25.1. የሠራተኛ ደህንነትና ጤንነት በሚመለከት አሠሪውም ሆነ ሠራተኛው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 92 እና 93 የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የሠራተኛ ማህበሩም በዚህ አዋጅና ሕብረት ስምምነት መሠረት በሠራተኛው ዘንድ ተፈፃሚነት እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ 

  25.2. የሠራተኛው ደህንነትና ጤንነት እንዲሁም የሥራ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አገልግሎት በሚመለከት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 177-182 በተመለከተ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

  አንቀጽ 26

  የሠራተኛ ደህንነትና ጤንነት ኮሚቴ አመሠራረት

  26.1. የኮሚቴ አወቃቀር 

  26.1.1. የሕክምና እና የሴፍቲ አገልግሎት ኃላፊ  ሰብሳቢ 

  26.1.2. በአስተዳደር መምሪያ የሚወከል ሶስት  አባል 

  26.1.3. በአስተዳደር መምሪያ የሚወከል አንድ  አባልና ፀሐፊ 

  26.1.4. የሠራተኛ ማህበር ተወካይ አምስት  አባል 

  26.2 የኮሚቴ ተግባር፤ 

  26.2.1. ኮሚቴው የአደጋው መንስኤዎችን እያጠና የሚወገዱበትን የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል፣ 

  26.2.2. የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እንዲሟሉና ጥገናና ሌሎች ንብረቶች በአግባቡ እንዲቀመጡ ይጠቁማል ያስፈጽማል፣ 

  26.2.3. የአክሲዮን ማህበሩ የማምረቻ መሣሪያዎች እና የማምረቻ አካባቢ ንጽህና እንዲጠብቅ ይከታተላል፡፡ 

  26.2.4. የመጸዳጃ ቤቶች፣ የመጠጥ ውሃዎችን እና የካንቲን አካባቢ ንጽህና ይቆጣጠራል፣ 

  26.2.5. ለሠራተኞች ስለ ደህንነት አጠባበቅ ትምህርት ከውስጥና ከውጭ በሚጋበዙ ባለሙያዎች እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ 

  26.2.6. የአደጋ ማስጠንቀቂያ አመላካች ፅሁፎችን በየቦታው ይለጥፋል፡፡ 

  26.2.7. ሌሎች አደጋ ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን ይፈጽማል፡፡ 

  አንቀጽ 27

  የአደጋ መከላከያ መሣሪያ፣ የሥራና የደንብ ልብስ አሰጣጥ፣

  27.1. የአደጋ፣ የሥራ የደንብ ልብስ በሚሰጥበት ጊዜ፣ 

  27.1.1. የአደጋ መከላከያ መሳሪያ፣ የሥራ እና የደንብ ልብስን በተመለከተ ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ በሚመደቡ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ሁለቱ ወገኖች ተደራድረው የሚፈጸም ሲሆን እስከዚያው ድረስ ግን በቀደመው ህብረት ስምምነት ላይ በተቀመጠው መሠረት እንዲፈጸም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ 

  አንቀጽ 28

  የሕክምና አገልግሎት፣

  28.1. የአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ የሚሰጠው አገልግሎት 24 ሰዓት ሆኖ የላብራቶሪ አገልግሎት ግን በመደበኛ ፈረቃ /በቀን/ ብቻ ይሆናል፡፡ 

  28.2. ሠራተኛው ከባድ አደጋና ሕመም ቢያጋጥመውና ከአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ አቅም በላይ ከሆነ ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል ይላካል፡፡ አደጋው አሳሳቢና ከፍተኛ መሆኑን የሕክምና ባለሙያ ሲያረጋግጥ የአንቡላንስ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ የራሱ የሆነ አምቡላንስ ከነሾፌሩ ይኖረዋል፡፡ በአምቡላንስ መልክ የተሠራ መኪና ባይኖረውም ካሉት መኪናዎች ለዚህ አገልግሎት ሊውል የሚችለውን መድቦ ሊያሰራ ይችላል፡፡ 

  • ማንኛውም የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ በክሊኒኩ አቅም የሚሰጠው ህክምና በነፃ ይሆናል፡፡ ሆኖም በክሊኒኩ የሚሰጠው የመድኃኒት ወጪውን 80% ብቻ በአክሲዮን ማህበሩ ይሸፈናል፡፡ 

  28.3. በሥራ ገበታው ላይ እያለ ሠራተኛው ሲታመምና የክሊኒክ አገልግሎት ቢያስፈልገው ከቅርብ አለቃው ዘንድ የመታከሚያ ቅጽ ተቀብሎ ወደ ሕክምና ይሄዳል፡፡ ሕክምናውን እንደፈጸመ የተመለሰ በትን ሰዓት ሀኪሙን በቅጹ ላይ ምልክት አስደርጎ ወደ ሥራው በመመለስ ለቅርብ አለቃው ያስውቃል፣ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሆስፒታል የሚላክ ከሆነ ወይም በክሊኒኩ የሕመም ፈቃድ ከሰተጠው ሠራተኛው የሕክምና መጠየቂያ ቅጹን ሊከፍሉ የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ 

  28.4. በዕረፍት ላይ ላሉ ወይም ከመደበኛ የሥራ ሰዓታቸው ውጭ ያለ ሠራተኞች በክሊኒኩ ፕሮግራም መሠረት ተራ በመያዝና ካርዳቸውን በማሳወጣት በሥነ-ሥርዓት ወደ ሐኪም ይቀርባሉ፣ አደጋ ለደረሰባቸውና ሕመማቸው አጣዳፊ ለሆኑ ሠራተኞች የጤና ባለሙያው ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፣ 

  28.5. ከሥራ ላይም ሆነ ከሥራ ሰዓት ውጭ ለሕክምና ወደ ክሊኒኩ ሄዶ የሕክምና ፈቃድ የተሰጠው ሠራተኛ ወዲያውኑ ለፐርሶኔል ሠራተኛ ግንኙነት ዋና ክፍል እና ሠራተኛው ለሚገኝበት ክፍል የማሳወቅ ግዴታ አለበት ሆኖም ታማሚው ሠራተኛ ይህንን ማድረግ ከማይችልበት ደረጃ የደረሰ ከሆነ የማሳወቅ ተግባሩ በክሊኒኩ አማካኝነት ወይም በወኪሉ አማካኝነት ወይም በክፍሉ ኃላፊ ይሆናል፡፡ 

  28.6. አንድ ሠራተኛ አስቀድሞ በአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ ከታከመ በኋላ ሕመምተኛው በሌላ ሆስፒታል እንዲታከም ወይም እንዲመረመር አስፈላጊ ለመሆኑ የአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ ኃላፊ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ከአክሲዮን ማህበሩ ጋር የሕክምና ስምምነት ወደ ተደራደረው መንግስታዊ የሕክምና ተቋም ይልካል፣ ሕመሙ ከአርባ ምንጭ ሆስፒታል አቅም በላይ ከሆነ የሆስፒታሉ ሐኪም ባዘዘው መሠረት ወደ ሌላ የመንግስት ሆስፒታል ተልኮ ይታከማል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ የሕክምና ወጪውን 80% ይከፍላል፡፡ በተጨማሪም የትራንስፖርት ወጪውን 100% ይከፍላል፡፡ ሆኖም በአንድ ሠራተኛ የሕጋዊ ፈቃድ ላይ እያለ ቢታመም ወይም አደጋ ቢደርስበትና የመኖሪያ አድራሻ ከአርባ ምንጭ ከተማና ከአካባቢው ውጭ በመሆኑ ወደ አክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ መምጣትና ካልቻለ በመንግስት የሕክምና ተቋም ታክሞ ሕጋዊ ደረሰኝ ሲያቀርብ የቀረበውን ጠቅላላ ወጪ 80% አክሲዮን ማህበሩ ይከፍላል፣ 

  28.7. አንድ ሠራተኛ ታሞ የክሊኒኩ ኃላፊ በክሊኒኩ ውስጥ ተኝቶ እንዲታከም ሲያዝለ ተኝቶ ሊታከም ይችላል፡፡ 

  28.8. አንድ ሠራተኛ ከሥራ ጋር ባልተያያዘ ሁኔታ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 በአንቀጽ 86 በተመለከተው መሠረት የሕመም ፈቃድ ተጠቅሞ ብቁ ሆኖ በሥራ ላይ ሊገኝ ካልቻለ መ/ቤቱ የአገልግሎት ካሳውንና ሕጋዊ ጥቅሙን ጠብቆ ሊያሰናብተው ይችላል፡፡ ሆኖም የአገልግሎት ዘመኑ የሚፈቅድለት ከሆነ በጡረታ እንዲገለል ይደረጋል፣ ነገር ግን ከHIV ቫይረስ ጋር ለሚኖሩት ሠራተኞች አይመለከትም፡፡ 

  28.9. አንድ ሠራተኛ ሲታመምና ከአቅም በላይ በመሆኑ ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል ተልኮ የአርባ ምንጭ ሆስፒታል ከአቅም በላይ ሆኖበት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ እንዲታከም ከላከው ለታማሚው ሠራተኛ ከዋናው መ/ቤት ለቅርንጫፍ መ/ቤት ጉዳዩን  የሚያስረዳ ደብዳቤ ይዞ እንዲሄድ እና ጨርሶ ሲመጣም በተመሳሳይ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህክምናውን ስለመከታተሉ የሚያስረዳ ደብዳቤ ይዞ እንዲመጣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ትብብር ያደርጋል፡፡ 

  28.10. አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ አደጋ ደርሶበት ወይም ከሥራ ጋር በተያያዘ ሕመም ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ እንዲታከም በሐኪም ሲወሰን ሆስፒታል እንዲተኛ ካልተደረገ በቀር በህብረት ስምምነት መሠረት ተመላላሽ ሕክምና ላይ ለቆየበትና በጉዞ ላይ ላሳለፈው ጊዜ አበል ይከፍለዋል፡፡ ከዚህ ውጪ ለማረጋገጥም ሕመም ግን በታሪፍ መሠረት ከትራንስፖርት ደርሶ መልስ ክፍያ በስተቀር አበል አይከፈልም፣ በሐኪም የተለየ ውሳኔ ካልተሰጠ በቀር ሠራተኛው ለሕክምና ቀርቦ ለዳግም ምርመራ ወይም ለውጤት ቀጠሮ ሲሰጠው ቀጠሮው ከስድስት ተከታታይ ቀናት በላይ ከሆነ ወደ አርባ ምንጭ ተመልሶ በቀጠሮ ቀን የመመለስ ግዴታ አለበት፣ 

  28.11. በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚገኙ ሠራተኞችን በተመለከተ አክሲዮን ማህበሩ አዲስ አበባ ካለው ሁኔታ ጋር በተዛመደ መልኩ አመቺ ሁኔታን በመፍጠር የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች በሚያገኙት የሕክምና አገልግሎት ጥቅም ልክ ሕክምና እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ 

  28.12. አክሲዮን ማህበሩ በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አማካኝነት ከመንግስት የሕክምና ተቋማት እና መንግስት እውቅና ከሠጠባቸው የግል የህክምና ተቋማት ጋር የዱቤ ሕክምና ውል ይገባል፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሚገኙት የመንግስት መድኃኒት ቤቶች አማካኝነት ሠራተኛው መድሃኒት እንዲያገኝ የዱቤ አገልግሎት ውል ይገባለታል፣ 

  28.13. ለአክሲዮን ማኅበሩ ሠራተኞች የሕክምና ውል የሚገባባቸው የሕክምና ተቋማት የሚከተሉት ናቸው 

  28.13.1. የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ 

  28.13.2. ሚኒሊክ ሆስፒታል 

  28.13.3. ራስ ደስታ ሆስፒታል 

  28.13.4. የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል 

  28.13.5. አማኑኤል ሆስፒታል 

  28.13.6. አለርት ሆስፒታል 

  28.13.7. ጳውሎስ ሆስፒታል እና ሌሎችም የመንግስት ሆስፒታሎች 

  28.14. አንድ ሠራተኛ አስታማሚ ሳይኖረው በከባድ ሕመም ላይ መሆኑ በባለሙያ ሲያረጋገጥ ከሕክምና ክፍል አንዱ ወይም የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ ተማሚውን ወደ አስፈላጊው ቦታ ለማድረስ የሚጠይቀውን የውሎ አበልና የትራንስፖርት ወጪ ይሸፍናል፡፡ 

  28.15. አንድ ሠራተኛ በዓይኑ ላይ የደረሰበት ጉዳት /ሕመም/ ከሥራ ጋር የተያያዘ መሆኑ በሐኪሞች ቦርድ ሲረጋገጥ አክሲዮን ማህበሩ ለሠራተኛው የታዘዘለትን መነጽር ይገዛለታል፣ 

  28.16. በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም ቢሮ ኢንስፔክሽን አገልግሎት በተወሰነ ጊዜ የጤንነት ምርመራ እንዲደረግላቸው በተወሰነባቸው የሥራ መደቦች ላይ የሚገኙ ሠራተኞች ሲኖሩ በአክሲዮን ማህበሩ ወጪ የጤና ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡ 

  28.17. ለከፍተኛ ሕክምና ከአርባ ምንጭ ሆስፒታል ውጭ በአንቀጽ ከ28.13.1. እስከ 28.13.7 በተጠቀሱት የህክምና ተቋማት ተልኮ ሆስፒታሉ ከአቅም በላይ ብሎ ወደ ግል የህክምና ተቋማት የምልካቸው ሠራተኞች ሲኖሩ ከመንግስት ሆስፒታል ወደ ግል የተላኩበትን ማዘዣ ኮፒ ለአክሲዮን ማህበሩ በማስረጃነት ያቀርባሉ በመንግስት ሆስፒታል ወደ ግል የተላኩበትን ማዘዣ ኮፒ ለአክሲዮን ማህበሩ በማስረጃነት ያቀርባሉ በመንግስት ሆስፒታል እንደታከሙም ተቆጥሮ ደረሰኙ ይወራረድላቸዋል፡፡  

  አንቀጽ 29

  ከሥራ ጋር ለተያያዘ ጉዳት የሚሰጥ የሕክምና ክፍያ

  29.1. አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ ለሚደርስበት አደጋ ወይም ጉዳት ወይም ከሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔት ለሚደርስ ሕመም ሁሉ አክሲዮን ማኅበሩ ኃላፊ ነው፡፡ 

  29.2. ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጭ በሆነ ከሥራ አለቃው ባለው ሥልጣን ክልል መሠረት በሰጠው ትዕዛዝ የአክሲዮን ማህበሩን ሥራ በሚያከናውንበት ወቅት ለሚደርስበት አደጋ የተሟላ ሕክምና ያገኛል፤ በሥራ ላይ እንደደረሰ አደጋ ይቆጠራል፡፡ 

  29.3. አንድ ሠራተኛ በሥራው ላይ እንዳለ አደጋ ሲደርስበት ብቻ በሚመለከተው የሕክምና ተቋም አጠቃላይ የመጨረሻ የሕክምና መረጃ የሐኪም ቦርድ ሲያቀርብ አክሲዮን ማህበሩ በገባው የመድን ዋስትና መሠረት በአጭር ጊዜ ውስጥ የካሳ ክፍያውን እንዲፈጸምለት ያደርጋል፡፡ 

  29.4. በሥራ ላይ ለደረሰው ጉዳት ወይም አደጋ ወይም ሕመም የሚደረግ የካሳ ክፍያ መጠኝ በኢንሹራንስ ውል መሠረት ይሆናል፡፡ 

  29.5. በሥራ ላይ ለደረሱ አደጋዎች ምክንያት ሠራተኛው ሕክምና ላይ ወይ በሕመም ፈቃድ ላይ ላሳለፏቸው ጊዜያት አክሲዮን ማህበሩ በገባው የኢንሹራንስ ውል መሠረት የሠራተኛውን ደመወዝ ይከፍላል፡፡ 

  29.6. አንድሠ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ በሚያጋጥሙት አደጋዎች ምክንያት በስራ ላይ በሌለበት ጊዜ ለዕድገት የመወዳደር መብት አይነፈገውም፣ 

  29.7. አንድ ሠራተኛ በሥራ ምክንያት በደረሰበት ጉዳት ሕመም ወይም አደጋ ተገቢው ሕክምና ተደርጎለት ለሥራው ብቁ አለመሆኑ በሐኪሞች ቦርድ ሲረጋገጥ በዚህ የህብረት ሥምምነትና በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት የሚገባው ክፍያ ተከፍሎት ከሥራ ይሰናበታል፡፡ ሆኖም የአገልግሎቱ ዘመኑ የሚፈቅድለት ከሆነ በጡረታ እንዲገለል ይደረጋል፡፡ 

  አንቀጽ 30

  በሕመም ምክንያት የሚሰጥ ሥራ

  30.1. ሠራተኛው በሕመም ምክንያት በሥራ ውል ከተመለከተው ውጭ በቋሚነት ቀላል ሥራ እንዲሰራ ሊደረግ የሚችለው ከአክሲዮን ማህበሩ ጋር ግንኙነት ካለው የመንግስት ሆስፒታል የሕክምና ቦርድ ማስረጃ ሲያቀርብ ነው፡፡ 

  30.2. አንድ ሠራተኛ ቋሚ ቀላል ሥራ እንዲሰራ በሐኪሞች ቦርድ ሲወሰን አክሲዮን ማህበሩ የሠራተኛውን የሥራ ደረጃና ደመወዝ ሳይቀንስ በቀላል የሥራ ቦታ ላይ ባለው እና በተሻሻለው የጡረታ አዋጅ መሠረት የጡረታ መብቱን አግኝቶ እንዲሰናበት ይደረጋል፡፡ 

  30.3. በሐኪሞች ቦርድ ሲረጋገጥ ወደነበረበት ሥራ ሲመለስ ለጤንነቱ አስጊ አለመሆኑን ከታመነበት ሠራተኛው ቀድሞ የሥራ ቦታው እንዲመለስ ያደርጋል፡፡ 

  አንቀጽ 31

  ኢንሹራንስ /መድን/

  31.1. ሠራተኛው በሥራ ላይ ከሥራ ጋር የተያያዘ ጉዳት ወይም ሕመም ቢደረስበት የአክሲዮን ማህበሩ ከኢንሹራንስ ድርጅት ጋር በገባቸው ስምምነት መሠረት ክፍያ ይፈጽማል፡፡ 

  31.2. ለሠራተኛው ደህንነት ሲባል አክሲዮን ማህበሩ ከመድን ድርጅት ጋር የሚያደርገው የዕድሳት ስምምነት አንድ ኮፒ ለሠራተኛ ማህበር በወቅቱ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡ 

  31.3. አንድ ሠራተኛ የሥራ ተግባሩን ፈጽሞ ከወጣ በኋላ ወደ ቤቱ ሲመለስ አንድ ሠዓት ወይም የሥራ ተግባሩን ለመፈጸም ወደ ስራው ከመግባቱ በፊት አንድ ሰዓት በሥራ ላይ እንዳለ ይቆጠራል፡፡ ይህም ለአክሲዮን ማህበሩ ሥራ ጉዳይ ከቤታቸው ተጠርተው የሚመጡትን ሠራተኞችንም ያጠቃልላል፤ 

  31.4. በዚህ አንቀጽ ቁጥር 31.3 መሠረት የመድን ዋስትና የተገባለት ሠራተኛ ሁሉ ለደረሰበት ጉዳት ወዲያውኑ ለፖሊስ ጣቢያ ወይም ለአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ ማስመዝገብና በቂ ማስረጃ ማቅረብ አለበት ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ ሪፖርት ለማድረግ ካልቻለ ቤተሰቡ ወይም የአደጋውን ሁኔታ የተመለከተ ማንኛውም የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ በተወሰነው ሰዓት ውስጥ ለአክሲዮን ማህበሩ ማሳወቅ አለበት፡፡ በተወሰነ ጊዜ ያልተመዘገበ ጉዳት ተቀባይነት የለውም፡፡ 

  31.5. በሥራ ላይ ያለ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የጉዳቱን ሁኔታ ዝርዝር የክፍል ኃላፊ 3 /ሦስት/ ምስክሮችን አስመስክሮና ትክክለኛነት አረጋግጦ ሠራተኛ በኋላ ለክሊኒኩ ተረኛ የጤና ባለሙያ ያስረክበዋል፡፡ ተረኛ የህክምና ሠራተኛውም ፎርማሊቲውን አጠናቆ ለክሊኒኩ ኃላፊ ያቀርባል ይህም በካርድ መመዝገብ አለበት፡፡ 

  31.6. ማንኛውም አደጋ እጅግ ቢዘገይ አደጋው በደረሰ በ24 ሰዓት ውስጥ ለአክሲዮን ማኅበሩ ሪፖርት መደረግ አለበት፡፡ 

  አንቀጽ 32

  የዓመት ዕረፍት ፈቃድ

  32.1. በማንኛውም ሠራተኛ የዓመት ዕረፍት ፈቃዱን የሚያገኘው በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 76-80 ባለው መሠረት ሲሆን ፈቃዱን በሚወስድበት ጊዜ የሠራተበትንና የዕረፍቱን ጊዜ ጨምሮ ለሠራበት ጊዚያት የሚገባውን ደመወዝ በቅድሚያ ማግኘት አለበት፡፡ ሆኖም ከ10 ቀን በታች የዓመት ፈቃድ ለሚወስዱ ሠራተኞች በቅድሚያ ደመወዛቸውን ለመክፈል አክሲዮን ማህበሩ አይገደድም፡፡ 

  32.2. ማንኛውም ሠራተኛ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ሳይተላለፍ ወይም ሳይከፋፈል በአክሲዮን ማህበሩ የሥራ ፕሮግራም መሠረት በዓመቱ ውስጥ ሥራን በማይጎዳ ሁኔታ ታይቶ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ 

  32.3. ዓመታዊ የዕረፍት ፈቃድ ሊከፋፈል ወይም ሊተላለፍ የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 79 መሠረት ይሆናል፤ ሆኖም ካለው የዓመት ዕረፍት ፈቃድ 50% እንደ ችግሩ ሁኔታ ከአንድ ቀን ጀምሮ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ይህንንም የማስፈጸም ስራ የሥራ ክፍል ሀላፊዎች ይሆናል፡፡ 

  32.4. የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሠራተኛ የሥራ ውል በሚቋረጥበት ጊዜ ከአክሲዮን ማህበሩ በዓመት ውስጥ ለሠራበት ጊዜ ተገምቶ የሚገባውን ክፍያ ይሰጣል፤ 

  32.4.1. አንድ ሠራተኛ ተገቢውን የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወስዶ በዕረፍት ላይ እንዳለ ቢታመምና የሐኪም ፈቃድ ቢሰጠው ወይም ሴት ሠራተኛ በዓመት እረፍት ላይ ያለች ብትወልድ በፈቃድ መጠን የዓመት ዕረፍት ፈቃዱ ይራዘማል፡፡ ይህም የሕመም ወይም የወሊድ ፈቃድ ተቀባይነት የሚኖረው በአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ ወይም መንግስታዊ ሆስፒታሎች የተረጋገጠ ሲሆን ነው፡፡ በተጨማሪም አንዲት ሴት ሠራተኛ ቤትዋ ብትወልድ በእርግዝና ጊዜ ቆይታዋ በክሊኒኩ በየጊዜው በወሰደችውና በሰጠችው መረጃ መሠረት ይሆናል፤ 

  32.4.2. በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ ለጤና ጎጂ በሆነ ስራ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች ተጨማሪ የዓመት ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ እነዚህም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 77 ተራ ቁጥር 2 እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በታች ለሚዘረዘሩ የሥራ መደቦች ከአንድ ዓመት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች በየአንድ ዓመት ፈቃድ ላይ ተጨማሪ የ2 /ሁለት/ የሥራ ቀን ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣቸዋል፡፡ 

  ሀ/ ለአየር ማመቻቻ ክፍል ሠራተኞች 

  ለ/ ለብሎው ፊደር ኦፕሬተሮች 

  ሐ/ ለቤል ፕሬስ ኦፕሬተሮች 

  መ/ ለአናጺና ውድ ወርክ ሾፕ 

  ሠ/ ለብየዳ ክፍል ሠራተኞች 

  አንቀጽ 33

  የሕመም ፈቃድ

  33.1. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 85 መሠረት የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ማንኛውም ሠራተኛ ከሥራ ጋር ግንኙነት የሌለው ሕመም ከደረሰበት የሕመም ፈቃድ ይሰጠዋል፣ 

  33.2. የሕመም ፈቃድም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ወይም በተለያዩ ጊዜያት የህክምና ማስረጃ ካቀረበ ከዚህ በታች በተመለከተው አኳኋን ይፈጸማል፡፡ ሆኖም በአንድ ዓመት ውስጥ ከመብለጥ የለበትም አከፋፈሉም እንደሚከተለው ነው፡፡ 

  33.2.1. ለአንድ ወር ጊዜ ሙሉ ደመወዝ የሚከፈልበት፣ 

  33.2.2. ለሁለት ወር ጊዜ ግማሽ ደመወዝ 

  33.2.3. ለሦስት ወር ጊዜ ደመወዝ የማይከፈልበት ይሆናል፤ ሆኖም ከHIV ጋር የሚኖሩና እራሳቸውን ለአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ በማስረጃ ያሣወቁ ሠራተኞችን አይመለከትም፡፡ 

  33.3. ከላይ በአንቀጽ 33.2 የተመለከተው የሕመም ፈቃድ ከማለቁ በፊት በበጀት ዓመቱ ያለቀ የሕመም ፈቃድ አብሮ ይፈጸማል፡፡ 

  33.4. ማንኛውም የሕመም ፈቃድ በአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ ሐኪም ወይም ነርስ ይሠጣል፡፡ ከታወቀ የመንግስት ሆስፒታል ወይም ጤና ጣቢያ የሚሰጡ ፈቃዶች ከክሊኒኩ ባለሙያ ተልከው ከሆነ ተቀባይነት አለው፣ 

  33.5. አንድ ሠራተኛ በታወቀ ሆስፒታል ውስጥ ታክሞ ሳይድን ቀርቶ በተለያዩ የባህል ህክምና ለመታከም ቢፈልግ በቅድሚያ ድርጅቱን አስፈቅዶ በዓመት ፈቃድ ወይም ያለ ደመወዝ ፈቃድ ለአንድ ወር ተሰጥቶ ሊታከም ይችላል፡፡ 

  አንቀጽ 34

  የወሊድ ፈቃድ

  34.1. አንዲት ሴት ሰራተኛ ለህክምና ለክትትል እንዲረዳ ማርገዟን ጽንስ በያዘች በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ ማሳወቅና ማስመዝገብ አለባት፣ 

  34.2. ማንኛዋም ነፍሰጡር የሆነች ሴት ሠራተኛ ለምርመራ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፣ 

  34.3. ማንኛዋም ነፍሰጡር ሴት ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፣ ይኸውም የሚሰጣት የወሊድ ፈቃድ ከመውለድዋ በፊት 30 ቀናት ከወለደች በኋላ 60 ቀናት ይሰጣታል አቆጣጠሩም በተከታታይ ይሆናል፣ 

  34.4 አንዲት ነፍሰጡር ሠራተኛ የወሊድ ፈቃድዋን ስትጀምር በፈቃድ ወቅት የሚኖራት ደመወዝ በሙሉ ይከፈለታል፣ 

  34.5. ለነፍሰጡር ሠራተኛ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በኋላ ሥራ መስጠትና የትርፍ ሰዓት ሥራ ማሠራት የተከለከለ ነው፡፡ 

  34.6. በአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ ውስጥ ወልዳ ወደ ቤት ለምትሄድ ሠራተኛ አክሲዮን ማህበሩ የአምቡላንስ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አርባ ምንጭ ከተማ ላይ ቤታቸውን ላሉ ምጥ የሚይዛቸው ሴት ሠራተኞች ወደ ሆስፒታል የሚያደርሳቸው መኪና በስልክ ሲጠየቅ አክሲዮን ማህበሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ይተባበራል፣ 

  34.7. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ በእርግዝባ ምክንያት የምትሰራው ሥራ ለጊዜው እንዲቃለል ወይም እንዲለወጥ ሐኪም ሲያዝ ለጤንነቷ ተስማሚ የሆነ ሌላ ቀላል ሥራ ይሰጣታል፡፡ 

  34.8. ያረገዘች የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ ያስወረዳት እንደሆነ እንደማንኛውም ሕመም ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፣ 

  34.9. ያረገዘች የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ ከ7 ወር በላይ የሆነ ጽንስ ውርጃ ሲያጋጥማት የ45 ተከታታይ ቀናት ፈቃድ ይሰጣታል፣ ከዚህ ውጪ ሐኪም የሚሰጣት ፈቃድ ተፈፃሚ ይሆናል፣ 

  34.10. የአክሲዮን ማህበሩ ሴት ሠራተኞች ሁሉ በዚህ ሕብረት ስምምነት የተመለከቱትን መብቶች ለማግኘት የሚችሉት እንዳረገዙ ለአክሲዮን ማህበሩ ክሊኒክ ያስመዘገቡ እንደሆነ ብቻ ነው፣ 

  34.11. ሠራተኛው በእርግዝና ወቅት ከቀድሞ ወሊድ ዕረፍት ሌላ ከመውለዷ በፊት ዕረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 88 መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፣ 34.12. ከላይ የተጠቀሱት አንቀፆች እንደተጠበቁ ሆነው ነፍሰጡር ሴቶችን በሚመለከት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ 377/96 አንቀጽ 88 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

  አንቀጽ 35

  የጋብቻ ፈቃድ

  35.1. ማንኛውም የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ ሕጋዊ የጋብቻ ሥርዓት ለመፈጸም ለአንድ ጊዜ ብቻ 3 /ሦስት/ የሥራ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል፣ ፈቃዱ የሚሰጠው ሠራተኛው ለአክሲዮን ማህበሩ አገልግሎት በመስጠት ላይ ባለበት ጊዜ ለህጋዊ ጋብቻ ብቻ ይሆናል፡፡ ሠራተኛው የጋብቻ ፈቃድ ሲፈልግ ከ7 /ሰባት/ ቀናት በፊት ለፐርሶናል ሠራተኛ ግንኙነት ዋና ክፍል በፅሑፍ ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 

  አንቀጽ 36

  የሐዘን ፈቃድ

  36.1. ማንኛውም ሠራተኛ ሐዘን ሲያጋጥመው በ377/96 አዋጅ አንቀጽ 81 ንዑስ አንቀጽ 1 “ለ” መሠረት የ3 /ሦስት/ የሥራ ቀን የሀዘን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ከከተማ ክልል 100 ኪ.ሜ በላይ ርቀት ለሚሄዱት ለትራንስፖርት ጉዞ ፈቃድ 2 /ሁለት/ የሥራ ቀን ተጨማሪ ፈቃድ ይሰጣል፣ 

  36.2. በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 81 እንደተጠቀሰው ሆኖ ሠራተኛው ሐዘን ሲደርስበት በራሱ አማካኝነት ወይም በመልእክት በቅድሚያ ለአክሲዮን ማኅበሩ ማሳወቅ አለበት፡፡ እንዲሁም የሀዘን ፈቃድ ተቀባይነት የሚኖረው ሠራተኛው በአክሲዮን ማህበሩ ሲቀጠር ባስመዘገበው የቤተሰብ ዝርዝር መሠረት በየጊዜው የሚያስመዝግባቸው የቤተሰብ ለውጥ ይሆናል፡፡ በሠራተኛው ቤተሰብ ዝርዝር ባይመዘገብም ከቤቱ ሬሣ ከወጣ የ3 /ሦስት/ የሥራ ቀን የሐዘን ፈቃድ ይሰጣል፡፡ በቤተሰብ ዝርዝር ባይመዘገብም አስክሬን ሲወጣ ወደ ቀብር ቦታ ለማጓጓዝ ትራንስፖርት በመስጠት አክሲዮን ማህበሩ ይተባበራል፡፡ 

  36.3. በአርባ ምንጭ ከተማ የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ የሆነ ሰው ሲሞት የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት በዚህ ከተማ የሚፈጸም ቢሆን ከማህበሩና ከሠራተኛ የተወጣጡ 20 /ሃያ/ ሰራተኞች አመራረጡ ሥራን በማይጎዳ ሁኔታ ሆኖ በቀብሩ እንዲገኙ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣል፡፡ 

  አንቀጽ 37

  ነፃ ፈቃድ

  37.1. ማንኛውም ሠራተኛ በድንገት ለሚያጋጥመው ችግር /ሁኔታ/ ደመወዝ የማይከፈልበት 05 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ፈቃድ የማግኘት መብት አለው ሆኖም በዓመት ከሁለት ጊዜ መብለጥ የለበትም፣ 

  አንቀጽ 38

  ለሠራተኛ ማህበር ሥራ የሚሰጥ ፈቃድ

  38.1 የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር መሪዎች ፈቃድ መስጠት ሲያስፈልግ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 82 መሰረት የስራ ክርክር ለማቅረብ፣ የሕብረት ስምምነት ለመደራደር፣ በማህበር ስብሰባ ለመገኘት፣ በሴሚናሮችና በሥልጠና ለመካፈል እንዲችሉ ለሠራተኛ ማህበር መሪዎች ከክፍያ ጋር ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ 

  38.2. የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበርና ጸሐፊ እያንዳንዳቸው በመቀያየር /በየተራ/ ጠዋትና ከሠዓት በኋላ ሳምንቱን ሙሉ በማኅበሩ ቢሮ ተገኝተው የማህበሩን ሥራ እንዲያከናውኑ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ሆኖም የሥራ ክፍላቸው ለሥራ ሲፈልጋቸው በማንኛውም ጊዜ በምድብ ሥራቸው ላይ መገኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን የማህበሩን ቢሮ የሚዘጋ ሁኔታ መፈጠር የለበትም፡፡ 

  38.3. የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ በሳምንት አንድ ቀን ማክሠኞ፣ ሒሳብ ሹምና ገንዘብ ያዥ በሳምንት ሁለት ቀን ማክሰኞ እና ቅዳሜ የማኅበሩን ሥራ እንዲያከናውኑ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ 

  38.4. የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ምክር ቤት አባላት በአራት ወር አንድ የሥራ ቀን ስብሰባ እንዲያካሂዱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ይህም ተፈጻሚ የሚሆነው ሠራተኛ ማህበሩ በጽሑፍ ሲጠይቅ ይሆናል፡፡ 

  38.5. በማህበሩ ሕገ ደንብ መሠረት የምክር ቤት ስብሰባ መደበኛ ከሆነ ከአምስት ቀን በፊት አስቸኳይ ከሆነ ከ48 ሰዓት በፊት ሠራተኛ ማህበሩ በጽሑፍ ጥያቄ ሲያቀርብ ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፡፡ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ ጠቅላላ አባላት ስብሰባ ለማድረግ ሠራተኛ ማህበሩ ሲጠይቅ በዓመት አንድ ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡ 

  38.6. የሠራተኛ ማኅበሩ ለሠራተኛው ድጋፍ ለማድረግ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ አክሲዮን ማኅበሩ ድጋፍ በማድረግ ይተባበራል፣ 

  አንቀጽ 39

  ልዩ ልዩ ተግባራትን ለማከናወን ለሠራተኛ ስለሚሰጥ ፈቃድ

  39.1. ልዩ ልዩ ተግባራትን ለማከናወን ለሠራተኛ የሚሰጥ ፈቃድን በሚመለከት በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 83 በተመለከተው መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 


  አንቀጽ 40

  የሕዝብ በዓላት

  40.1 በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 73 መሠረት እና ለሕዝብ በዓላት መንግስት ባወጣው እና በሚያወጣው ድንጋጌ መሠረት ይሆናል፤ በዚሁም መሰረት ከዚህ የሚከተሉት ደመወዝ የሚከፈልባቸው የህዝብ በዓላት ናቸው፡፡ 

  40.2. በዋና ዋና ብሔራዊ በዓላትን አስመልክቶ በመሀል ያሉ የሥራ ቀናት ተተኪ ቀናት በመስራት ለማካካስ በሚቻልበት ሁኔታ ከመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ጥያቄ ሲቀርብ አክሲዮን ማህበሩ ሊተገብር ይችላል፡፡ 

  40.2.1. መስከረም 1 ቀን የዘመን መለወጫ 

  40.2.2. መስከረም 17 ቀን መስቀል በዓል 

  40.2.3. ታህሳስ 29 ቀን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል፣ 

  40.2.4. የጥምቀት በዓል ጥር 11 ቀን፣ 

  40.2.5. የካቲት 23 ቀን የዓድዋ ድል መታሰቢያ 

  40.2.6. ዒድ አልፈጥር /ረመዳን/ 

  40.2.7. ሚያዚያ 27 ቀን የአርበኞች ድል መታሰቢያ 

  40.2.8. የስቅለት በዓል፣ 

  40.2.9. የትንሳዔ በዓል፣ 

  40.2.10. ሚያዚያ 23 ቀን ሜይዴይ የዓለም ሠራተኞች ቀን፣ 

  40.2.11. ዒድ አልአድሐ /ዓረፋ/ 

  40.2.12. ግንቦት 20 

  40.2.13. መውሊድ 


  አንቀጽ 41

  የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና፣

  41.1. አክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛው ዕውቀቱን አሻሽሎ የተመደበበት ሥራ አሟልቶ እንዲሰራ የሚያስችለውን አቅም ለመገንባት በአክሲዮን ማህበሩ ዕቅድና በሚያወጣው የውስጥ የሥልጠና አፈጻጸም መምሪያ መሠረት ሠራተኞችን ለማሰልጠን ጥረት ያደርጋል፡፡ 

  41.2. መንግስት እየተከተለ ካለው የአቅም ግንባታ ፖሊሲ አንጻር ለትምህርት ድጋፍ ይሰጣል፣ ሆኖም የሥልጠናው ሂደት አክሲዮን ማህበሩ የሠለጠነ የሠው ሀይል ፍላጎት ጋር የተጣጣመ መሆን ይኖርበታል፡፡ 

  41.3. በሥልጠናው የተካፈሉ ሠራተኞች ሥልጠና ከተከታተሉ በኋላ ያገኙትን የምስክር ወረቀት በግል ማኅደራቸው እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡ 

  አንቀጽ 42

  የትምህርት ድጋፍ

  42.1. የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች በትርፍ ጊዜያቸው ዕውቀታቸውን በትምህርት እንዲያሻሽሉ ያበረታታል፡፡ 

  42.2. ከ10ኛ ክፍል በላይ አጠናቀው ከሚሠሩት ሙያ ጋር ግንኙነት ያለው ትምህርት በትርፍ ጊዜያቸው ለሚማሩ ሠራተኞች አክሲዮን ማህበሩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ 

  42.3. በግል ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ሠራተኞች በፈተና ወቅት በትምህርት ቤት የፈተና መረሀ ግብር መሠረት የተረጋገጠ ደመወዝ የሚከፈልበት የፈተና ቀናት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች በሚያቀርቡት ማስረጃ መሰረት ደመወዝ የሚከፈልበት የፈተና ፈቃድ ይሰጣል፡፡ 

  42.4. 10ኛን ክፍል አጠናቆ ከሥራው ጋር ቀጥታ የተገናኘ ሆኖ በቴክስታይል የሙያ ዘርፍ ለሚማር ሠራተኛ አክሲዮን ማኅበሩ 75%፣ እንዲሁም ከሥራ ጋር ቀጥታ የተገናኘ ሆኖ በሌሎች የትምህርት መስኮች ለሚማሩ 50% የትምህርቱን ወጪ አክሲዮን ማህበሩ ይሸፍናል፡፡ 

  42.5. የትምህርት ድጋፍ ስለሚሰጥበት ሁኔታ 

  42.5.1. የሠራተኛው ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የሚወስደውን የትምህርት አይነት ለስራ ክፍሉ በቅድሚያ ያሳውቃል፡፡ የሥራ ክፍሉም ከሙያው ጋር ያለውን ቀጥታ ተዛማጅነት አረጋግጦ ለመምሪያው ያቀርባል፡፡ በመምሪያው አስተያየት ከተሰጠ በኋላ ለአስተዳደር ይቀርባል፡፡ አስተዳደሩ አጣርቶ ለፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ውሳኔ ሲያገኝ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 

  42.5.2. ሠራተኛው ትምህርቱን አጠናቅቆ ከትምህርት ተቋሙ መጨረሱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሲያቀርብ ገንዘቡ ይከፈለዋል፡፡ 

  42.5.3. ሠራተኛው በዚህ ሁኔታ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ በአክሲዮን ማህበሩ ለሁለት ዓመት የማገልገል ግዴታ አለበት፤ ከ5 ዓመት በታች አገልግሎ የሁለት ዓመት ግዴታውን ሳይጨርስ የስራ ውሉን የሚያቋርጥ ከሆነ ድርጅቱ ለትምህርት ወጪ ያደረገውን ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ማድረግ አለበት፡፡፡ በተጨማሪም ከ5 ዓመት በላይ አገልግሎ የሁለት ዓመት ግዴታውን ሳይወጣ የሥራ ውሉን የሚያቋርጥ በማሻሻያ አዋጅ 494/98 መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- 

  ሀ) ሙሉ ጊዜውን በትምህርትና በሥልጠና ሙሉ ወጪው ደመወዝ  ተከፍሎ የተማረ ሠራተኛ በአዋጅ ቁጥር 494/98 “ሸ” መሠረት ማገልገል አለበት፣ 

  ለ) ትምህርቱን ከሥራ ሰዓት ውጪ ከተማረና ካጠናቀቀ በኋላ ሁለት ዓመት ማገልገል ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ድርጅቱን መልቀቅ ከፈለገ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ የወጣውን ወጪ ቀሪውን የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ 

  ሐ) የትምህርት ድጋፍ ተደርጎለት ትምህርቱን በተልዕኮ ካጠናቀቀ በኋላ አንድ ዓመት አገልግሎት መስጠት አለበት፣ 

  42.5.4. ሠራተኛው የሚያቀርበው የትምህርት ማስረጃ ከግል ማህደሩ ጋር ተያይዞ ውድድር ሲኖር እንደ ማንኛውም ሠራተኛ ከመወዳደር በቀር የትምህርት ደረጃውን በማሻሻሉ ብቻ ዕድገት ወይም የደመወዝ ጭማሪ ሊጠይቅ አይችልም፣ 

  42.5.5. ሠራተኛው ትምህርት ላይ በመሆኑ ምክንያት ሥራው ላይ ችግር ቢፈጠር ትምህርት እንዲያቋርጥ ይደረጋል፣ ይህም የሚሆነው በትክክል በሥራ ላይ ችግር ስለመፈጠሩ ኃላፊው የማስረዳት ኃላፊነት አለበት፣ ሠራተኛው እንዳይማር ለማድረግ የተደረገው ሠራተኛውን ለመጉዳት ወይም በጎ ህሊና ከማጣት የመነጨ መሆን የለበትም፤ 

  42.5.6. አክሲዮን ማህበሩ ዝውውር አስፈላጊ ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይም ወደ አክሲዮን ማህበሩ በሥራ ላይ ከተፈፀመ ጥፋት ጋር ባልተያያዘ ሁኔታ ማዛወር ቢፈልግና ሠራተኛው ትምህርት በመከታተል ላይ ቢሆን የዓመቱን የትምህርት ፕሮግራም እስኪፈጽም አክሲዮን ማህበሩ ይጠበቃል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ፍቃደኛ ከሆነ ዝውውሩ ሊፈፀም ይችላል፡፡ 

  42.5.7. በአገር ውስጥ በአክሲዮን ማህበሩ በኩል የሚመጡ ትምህርቶች የሙያ ማሻሻያ ወይም ሴሚናሮች አክሲዮን ማህበሩ የውሎ አበልና ደመወዝ ይከፈላል፡፡ ሆኖም ሰልጣኙ በሚሰለጥንበት ወቅት የመኝታና የምግብ ወጪ በሌላ አካል የሚሸፈን ከሆነ በአክሲዮን ማህበሩ በኩል ለሠልጣኙ የውል አበሉን 20% ብቻ አክሲዮን ማህበሩ ይከፍላል፣ 

  42.5.8. ሠራተኛው በግሉ በከፍተኛ የትምህርት ተቋም እየተማረ የትምህርት ተቋሙ በሚያወጣው የመስክ ልምምድ ፕሮግራም ለመሄድ በምረቃው የመጨረሻ ዓመት ብቻ አምስት ቀን ፍቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡ የመስክ ልምምዱ ከ5 ቀን በላይ ሲሆን ሠራተኛው በዓመት ፈቃዱ ሊጠቀም ይችላል፡፡ 

  አንቀጽ 43

  ማህበራዊ አገልግሎት

  43.1. ሠራተኛው ከሞተ አክሲዮን ማህበሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ወጪና አገልግሎት ይሰጣል፡- 

  43.1.1. በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚደረግ የቀብር ሥነ-ሥርዓት አስክሬን ማጓጓዣ መኪና ወይም አንቡላንስ ይሰጣል፡- 

  43.1.2. ቀብሩ አርባ ምንጭ ላይ ሲሆን የጉድጓድ ማስቆፈሪያና ለቀብር ሥርዓት ማስፈፀሚያ ብር 1500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለሟች ቤተሰብ አክሲዮን ማህበሩ ይሰጣል፤ ከዚህ በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110 ሕዝባር 1 በፊደል “ለ” ላይ የተመለከተው ተፈፃሚ ይሆናል፣ 

  43.2. ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተልኮ በህክምና ላይ እያለ የሞት ሠራተኛ ካለ ሬሳውን ወደ ተፈለገው ቦታ ለመጓጓዝ አክሲዮን ማህበሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፣ 

  43.3. የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ ከሞተ እና አርባ ምንጭ የሚቀበር ሲሆን አክሲዮን ማህበሩ የሬሳ ሳጥንና 3 /ሦስት/ ሜትር የከፈን ጨርቅ ይሰጣል፣ 

  43.4. ሠራተኛው በተለያዩ አጋጣሚዎች በሌላ ቦታ እያለ ከሞተና ከተቀበረ ግን ለሣጥንና ጨርቅ መግዣ ለቀብር ማስፈጸሚያ፣ ለጉድጓድ ማስቆፈሪያ አክሲዮን ማህበሩ ብር 1100.00 /አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር/ ይሰጣል፣ ከዚህ በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110 ሕዝባር 1 ፊደል “ለ” ላይ የተመለከተው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 

  43.5. የአክሲዮን ማህበሩ ሥራ ምክንያት ወይም ለሕክምና ወደ ሌላ ክፍለ ሀገር ሄዶ ወይም እዚህ ሳለ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓመት በሞት ሲለይና ሬሳው ወሰ ቤተሰቡ መሄድ ሲያስፈልግ አክሲዮን ማህበሩ የሟቹን ሬሳ ወደሚሰራበት አካባቢ ወይም ወደሚቀበርበት ቦታ ድረስ አንድ ከአክሲዮን ማህበሩ አስተዳደር፣ አንድ ከሠራተኛ ማህበር በድምሩ ሁለት ሰራተኞች ከነሹፌሩ በመኪና አድርሰው ይመለሳሉ፡፡ ለዚህም አክሲዮን ማህበሩ ውሎ አበል ይከፍላል ተሽከርካሪ ማቅረብ ካልተቻለ ወጪው ይሸፈናል፣ 

  43.6. አንድ ሠራተኛ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ አክሲዮን ማህበሩ ባለው የትራንስፖርት መገልገያ አስክሬኑ የሚጓጓዝበት መንገድ ለመኪና አመቺ እስከሆነ ድረስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ወደሚፈጸምበት አካባቢ አስክሬኑን ለማድረስ ይተባበራል፡፡ ሠራተኛው የሟቹን አስክሬን ለመሸኘት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከ20 ያልበለጡ ከአክሲዮን ማህበሩ የተውጣጡ ሰራተኞች ሸኝተው ወደ ስራቸው ይመለሳሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ የሚመረጡ ሠራተኞች በወሳኝ ስራ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች አይሆኑም፣ 

  አንቀጽ 44

  የመዝናኛ አገልግሎት

  44.1. አክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛው አገልግሎት የሚሰጥ ካንቲን ያዘጋጃል፣ 

  44.2. አክሲዮን ማህበሩ ለካንቲኑ እድሳት ያደርጋል፡፡ ለዚሁ ካንቲን አገልግሎት ኤሌክትሪክ እና ውኃ በነፃ ይሰጣል፣ 

  44.3. የሠራተኛ ማህበሩ ለሠራተኛ አገልግሎት የተዘጋጀውን ካንቲን በውስጥ የሚገኙትን ንብረቶች ተረክቦ በሀላፊነት ያስተዳድራል፣ ይህም ሰራተኛው በካንቲን እንዲገለገል ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ለሠራተኛው ክፍት እንዲሆን ያደርጋል፤ ለዚህ አፈፃፀም ካንቲኑን በኮንትራት ከወሰደው ሰው ጋር ውል ይዋዋላል፤ የውሉን ኮፒ ለአክሲዮን ማህበሩ ይሰጣልለ ውሉን በማስፈጸም ረገድ ሠራተኛ ማህበሩ ኃላፊነት ይወስዳል፣ 

  44.4. ካንቲኑ የሚመራው በመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ ሆኖ አንድ ኮሚቴ በማህበሩ የሚቋቋም ሲሆን፣ ካንቲኑን ሠራተኛ ማህብሩ የሚሠራበት ከሆነ ብቻ ለዚሁ ስራ ለሚንቀሳቀሱ የኮሚቴ አባሎች ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ደመወዝ የሚከፈልበት ፍቃድ ይሰጣል፣ 

  44.5. የሠራተኛ ማህበሩ ከተረከበው የሠራተኛ ካንቲን በሚያገው ገቢ የካንቲኑን የውስጥ መገልገያዎች ዕቃዎች በሚሰበሩበትና አላግባብ በሚጠፉበት ጊዜ የመተካት እና አሟልቶ የመያዝ ኃላፊነት አለበት፤ 

  44.6. በካንቲኑ ውስጥ በሚሰቱ አገልግሎቶች የዋጋ ተመን ላይ አክሲዮን ማህበሩ እና የሠራተኛ ማህበሩ በጋራ ይወስናል፤ 

  44.7. በአክሲዮን ማህበሩ የጤና ክሊኒክ የንጽህናና የጤና /ሳኒቴሽን/ ቁጥጥር በጤና ባለሙያ ይደረጋል፣ 

  44.8. ያለ አግባብ ከተወሰነው የካንቲን የአገልግሎት መስጫ ሰዓት ውጭ ከስራ በመለየት በካንቲኑና በአካባቢው በሚገኙ ሰራተኞች ላይ አክሲዮን ማህበሩ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፣ 

  44.9. የካንቲን የአገልግሎት ጊዜ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ 

  44.9.1. የፈረቃ የዕረፍት ጊዜ፣ 

  44.9.2. መደበኛ በምሳ የዕረፍት ጊዜ፣ 

  44.9.3. ለጧት ፈረቃ የቁርስ ጊዜ ካንቲኑ ቁርስ በሥራ ቦታ ያቀርባል፣ ከዚህ የመስተንግዶ ሰዓት ውጪ ካንቲኑ ከጧቱ 1፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ምንም ዓይነት መስተንግዶ ማድረግ አይችልም፡፡ 

  4.10. አክሲዮን ማኅበሩ በቅጥር ግቢ ውሥጥ አቅሙ ሲፈቅድለት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያዘጋጃል፡፡ 

  አንቀጽ 45

  የበዓል መዋያ ክፍያ

  አክሲዮን ማኅበሩ ለሠራተኛው በአመት ሁለት ጊዜ ማለትም በአዲስ አመት መግቢያና በትንሳኤ በዓላት ላይ የተጣራ ብር ለቋሚ ሠራተኞች 350.00፣ ለኮንትራት ሠራተኞች 150.00 እና ለጊዜያዊ ሠራተኞች 100.00 የበዓል መዋያ ክፍያ ይሰጣል፡፡   አንቀጽ 46

  የብድር አገልግሎት

  46.1. አክሲዮን ማህበሩ ለብድር አገልግሎት የሚውል ብር 300.000 /ሦስት መቶ ሺህ ብር/ ዓመታዊ ፈንድ ይይዛል፣ 

  46.2. በጤና ከአቅም በላይ የሆኑ እንዲሁም ሌሎች አሳማኝ ችግሮች ሲገጥሙ፣ ይኸው በብድር ኮሚቴ ሲረጋገጥና ሌላ እዳ ከሌለበት እስከ ሁለት ወር ደመወዝ ብድር በአንድ አመት ተከፍሎ የሚያልቅ ለሠራተኛው ይሰጣል፡፡ 

  46.3. ለፍትሐዊነት ሲባል የብድሩ ዝርዝር አፈጻጸም አክስዮን ማኅበሩና የሠራተኛ ማኅበሩ በጋራ በሚያወጡት መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡ 

  አንቀጽ 47

  ጡረታ፤

  47.1 በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ ያሉ ሠራተኞች አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከመደበኛ የመጦሪያ እድሜ ሲደርሱ፡፡ 

  47.2. በሕመምም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያት በጡረታ እንዲገለሉ ሲወሰን በወቅቱ በሥራ ላይ ባለው የጡረታ አዋጅ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 

  47.3. የአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች የሆነና የጡረታው ዕድሜው ድረስ በጡረታ ሲገለል አክሲዮን ማህበሩ ለዚህ ሠራተኛ 

  ሀ/ 10 ሜትር ፖሉስተር የሱሪ ጨርቅ 

  ለ/ 10 ሜትር የሸሚዝ ጨርቅ እና 

  ሐ/ 10 ሜትር የመጋረጃ ጨርቅ ስጦታ ይሰጣል፣ ምርቶቹ ከሌሉ የዋጋ ግምት ይሰጣል፡፡ 

  47.4. የሠራተኛው እና የአክሲዮን ማህበሩ የጡረታ መዋጮ ድርሻ በወቅቱ ወደ ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ገቢ ማድረግ እና ሠራተኛው የጡረታ ደብተሩን እንዲያገኝ አክሲዮን ማኅበሩ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ 

  47.5. አክሲዮን ማህበሩ ለጡረታ የደረሱ ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ ከመድረሱ ከስድስት ወር በፊት አስፈላጊ መረጃዎችን ለማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይልካል፡፡ 

  አንቀጽ 48

  የትራንስፖርት አገልግሎት፣

  48.1. አክሲዮን ማህበሩ ከአክሲዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ውጭ ለሚኖሩ ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፣ 

  48.2. ለሠራተኛው የሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት መስመር ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፣ 

  48.3. ከአክሲዮን ማህበሩ ተነሳስቶ ኳስ ሜዳ ደርሶ በቀድሞ እርዳታ ማስተባበሪያ ደርሶ ይመለሳል፣ 

  48.4. ከአክሲዮን ማህበሩ ተነስቶ በዋና መንገድ በመድሀኒዓለም ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ወደ በቀለ ሞላ ሆቴል ሄዶ በከተማ በኩል አድርጎ ወደ አክሲዮን ማህበሩ ይመለሳል፡፡ 

  48.5. ከአክሲዮን ማህበሩ ተነስቶ ወደ አርባ ምንጭ እርሻ ልማት ደርሶ ይመለሳል 

  48.6. ከኮንሶ ሰፈር ሆስፒታል ደርሶ ይመለሳል፣ 

  48.7. በትራንስፖርት አገልግሎት የሚገጥሙ ችግሮችን አክሲዮን ማህበሩና የመሰረታዊ ሠራተኛ ማኅበሩ በጋራ በመወያየት መፍትሄ ይሰጣሉ፣ 

  48.8. የከተማ መስፋፋትን ተከትሎ የአክሲዮን ማህበሩና የሠራተኛ ማህበሩ በሚያደርጉት ስምምነት የትራንስፖርት አገልግሎት ያመቻቻል፣ 

  48.9. ለአዲስ አበባ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ሠራተኞች በቀን 10.00 ብር የትራንስፖርት ክፍያ ይፈጸማል፡፡  

  አንቀጽ 49

  የፖስታ አገልግሎት

  49.1. ለአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኞች የሚመጡ የተለያዩ ደብዳቤዎችና ሌሎች እቃዎች አክሲዮን ማህበሩ አግባብ ባለው መልኩ ጥንቃቄ በማድረግ ለሠራተኛው እንዲታደል ያደርጋል፣ 

  49.2. አክሲዮን ማህበሩ ከፖስታ አገልግሎት ቢሮ ጋር በመነጋገር አንድ የፖስታ ሳጥን በአክሲዮን ማህበሩ ግቢ ውስጥ እንዲኖር ጥረት ያደርጋል፣ 

  አንቀጽ 50

  የካዝና መጠባበቂያ ገንዘብ

  50.1. የክፍያ መጠን፣ 

  50.1.1. ለዋና ገንዘብ ያዥ በየወሩ 75.00 /ሰባ አምስት ብር/ 

  50.1.2. ለገንዘብ ያዥ እና ሰብሳቢ በየወሩ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/

  50.1.3. በደመወዝ ክፍያ ወቅት ለሚሰሩ የደመወዝ ከፋዮች ደመወዝ በሚከፈሉበት ጊዜ ብር 35.00 /ሠላሳ አምስት ብር/ 

  50.2. የአከፋፈሉ ሁኔታ በ50.1.1 እና 50.1.2. ያሉት ለመጀመሪያ አንድ አመት በስማቸው በመ/ቤቱ ከተጠራቀመ በኋላ በዓመቱ መጨረሻ  ጉድለት እንደሌላቸው ሲረጋገጥ ወዲያውኑ በየወሩ መደበኛ ክፍያ ይጀምራል፡፡ ሠራተኞቹ ከሥራ ቢሰናበቱ ወይም ከገንዘብ ያዥነት ሥራ ሲነሱና ጉድለት እንደሌለባቸው ሲረጋገጥ የተጠራቀመው ሂሳባቸው ወዲያውኑ ይከፈላል፡፡ 


  አንቀጽ 51

  ውክልና

  በሠው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ይፈጸማል፡፡ 

  አንቀጽ 52

  የቅድሚያ ደመወዝ ክፍያ

  የቅድሚያ ደመወዝ ክፍያ እንደ ሠራተኛው ችግር አስገዳጅነት ሁኔታ የአክሲዮን ማኅበሩና የሠራተኛ ማኅበሩ ሲስማሙ ይፈጸማል፡፡ 

  አንቀጽ 53

  የሥነ-ሥርዓት ጉድለቶችና እርምጃዎች

  53.1. ከቅጣት በፊት የሚወሰዱ እርምጃዎች 

  53.1.1. በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት የሚወሰዱት የሥነ-ሥርዓት እርምጃዎች በፍርድ ቤትና በሌላ ከሚወስዱት እርምጃዎች ጋር ምንም ግንኙት የለውም፣ 

  53.1.2. በየሥልጣን ተዋረዱ በተወሰደ እርምጃ ቅሬታ ያለው ሠራተኛ ለአክሲዮን ማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አስተዳደር እና ለመመሪያዎችና አገልግሎቶች ወይም ተጠሪነታቸው ለፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ለሆኑ ዋና ክፍሎች ያቀርባል፡፡ ቅሬታው የቀረበለት ወገን/አክሲዮን ማኅበር/ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ቅሬታው ከቀረበለት ከ5-10 ቀን ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ 

  53.1.3. ከዚህ ህብረት ስምምነት ጋር የተያያዘ የዲሲፕሊን ቅጣት በሰንጠረዥ ላይ በተመለከተው መሰረት የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ይወስዳል እንጂ ባጠፋ ቁጥር እየተደመረበት አይደለም፣ 

  53.1.4. በአንድ ጊዜ ሁለት ጥፋቶችን የሚያጠፋ ሰራተኛ ከሁለቱ በአንዱ በከፍተኛው ጥፋት ብቻ ይቀጣል፣ 

  53.1.5 በሥነ ሥርዓት እርምጃ ሰንጠረዥ ላይ ያልተካተቱ ሌሎች ጥፋቶች ሲፈጸሙ የጥፋቱ ክብደት እየተመዘነ በሠንጠረዥ ውስጥ ከተዘረዘሩት በተመሳሳዩ ወይም በተቀራራቢው አንቀጽ እርምጃ ይወሰዳል፣ 

  53.1.6. ከሥራ የሚያሳግዱ ጥፋቶች 

  ሀ/ በአክሲዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ አምባጓሮ የፈጠረ፣  

  ለ/ ጥፋቱን ለመሸፈን ሰነዶችን /ማስረጃዎችን/ ያጠፋ ወይም አክሲዮን ማህበሩንና ሠራተኛውን ይጎዳል ወይም ጉዳት ላይ ይጥላል፤ ተብሎ የታመነበት ከሆነ ጉዳዩ እስኪጣራና ውሳኔ እስኪሰጠው ድረስ እስከ አንድ ወር ከሥራ ታግዶ ይቆያል፡፡ ሆኖም ከጥፋቱ ነፃ ሆኖ ከተገኘ የታገደበት ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ሥራው ይመለሳል፡፡ 

  ሐ/ በስካር መንፈስ ተመርዞና በአደንዛዥ ዕፅ ተመርዞ በስራ ላይ ሲገኝ፣ 

  መ/ በሥራ ዝርዝር መግለጫ የተሰጠውን ትእዛዝ ለመፈጸም ሲችል ሆን ተብሎ ትዕዛዝ ያላከበረ፣ ያልፈፀመ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አልቀበልም ያለ፣ 

  ሠ/ ያልተፈቀደለትን ድምጽ ያለው ወይም የሌለው የጦር መሳሪያ በቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ የተገኘ ሠራተኛ፣ 

  ረ/ የድርጅቱን ንብረት ያለአግባብ ለግል ጥቅሙ ያዋለ ወይም ሌሎች እንዲጠቀሙበት ሁኔታዎችን ያመቻቸ፣ 

  ሰ/ በግዴለሽነት ወይም በቸልተኝነት ወይም ሆን ብሎ በድርጅቱ ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ወይም ጉዳት እንዲደርስ የተባበረ እና ያመቻቸ፣ 

  በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 27 ላይ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት ለደረሰው ጉዳት ተጠያቂ በመሆን ያለአንዳች ማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያስወጡ ጥፋቶች ናቸው፡፡ 

  53.2. ማንኛውም አይነት የድርጅቱ ንብረት የሰረቀ ወይም ያጭበረበረ፣ 

  53.2.1. ሆን ብሎ ሰነዶችን ያጠፋ፣ የለወጠ ወይም ለሌላ ሁለተኛ ሰው ይህንን ድርጊት እንዲፈጸም ያደረገ ወይም የሌላውን ሠራተኛ ሰዓት መቆጣጠሪያ የሞላ ወይም የሠሀት ሪፖርት ያቀረበ፣ 

  53.2.2. ትክክለኛ ያልሆነ ወይም የሀሰት ማስረጃ በማቅረብ ሥራ የገባና የተቀጠረ እድገት ለማግኘት የሞከረ ወይም ያገኘ፣ የሀሰት ማስረጃ በማቅረብ የተለያዩ ጥቅሞችን ለማግኘት የሞከረ እና ያገኘ፣ 

  53.2.3. መጠጥ ጠጥቶ በስካር መንፈስ የአክሲዮን ማህበር መኪና እያሽከረከረ ጉዳት ያደረሰ፣ 

  53.2.4. የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኋላ ሌላ ጥፋት የፈጸመ፣ 

  53.2.5. ያለበቂ ምክንያት ለ6 /ስድስት/ ተከታታይ ቀናት ከሥራ የቀረ፣ 

  53.2.6. በአክሲዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ዝሙት ሲፈጽም የተገኘ፣ 

  53.2.7. ሐሰት መሆኑን እያወቀ ሊያገኝ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት የሞከረ፣ ያገኘ ወይም ሌሎች እንዲያገኙ ለማድረግ የተሰጠውን ፍቃድ የደለዘ ወይም ከተፈቀደለት በላይ የጨመረ፣ ፊርማ አስመስሎ የፈረመ፣ ወይም ሀሰተኛ ሰነድ እና ሪፖርት ያቀረበ ፕሮዳክሽን /ምርት/ አውቆ አሳስቶ የመዘገበ የምርት መጠን መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን ለጥቅሙ ሲል ሆን ብሎ ያበላሸ የአክሲዮን ማኅበሩ መዛግብት እንዲቃወስ ያደረገ ወይም ከሠራተኛው ማኅደር ውስጥ መረጃዎችን ያጠፋ፣ 

  53.2.8. በአክሲዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ሲጋራ በተከለከለበተ ቦታ ሲያጨስ እሳት ወይም ኤሌክትሪክ ሲያቀጣጥል የተገኘ፣ 

  53.2.9. ሐሰት ወሬ በመንዛት ምርት እንዲጓደል ወይም በሠራተኛ መካከል አለመግባባት የፈጠረና እንዲፈጠር ያደረገ ለዚሁም ተግባር ተባባሪ ሆኖ የተገኘና ሕገወጥ በሆነ መንገድ ሥራ ትቶ በመሰብሰብ አድማና ሥራ በማወክ ከሕገ-ወጥ ተግባር ላይ የተገኘ 

  53.2.10. በአክሲዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሕገ ወይ ጽሑፎችን የጻፈ ፖስተሮች የለጠፈ ወይም ያለ አክሲዮን ማህበሩ አስተዳደር ፍቃድ ማስታወቂያ ሠሌዳ የተጠቀመ እንዲሁም ከማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ማስታወቂያዎች ያለ ፍቃድ የቀደደና የነቀለ ሠራተኛ፣ 

  53.2.11. የተጣለበትን ኃላፊነት በመዘንጋት ጉቦ ወይም መደለያ የሠጠ ወይም የተቀበለ እንዲሰጥ ወይም እንዲቀበል ያመቻቸ ወይም ያደረገ፣ 

  53.2.12. በአክሲዮን ማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተደባደበና ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ፣ 

  53.2.13. በስካር መንፈስ ተመርዞና በአደንዛዥ እጽ ተመርዞ ሥራ ላይ ተገኝቶ ሥራንና ሠራተኛን በሚያውክ ተግባር ላይ ሲገኝ፤ ይህም በክፍል ኃላፊው ሲረጋገጥ፣ 

  53.2.14. ያልተፈቀደለትን ድምጽ ያለው ወይም የሌለው የጦር መሳሪያ በቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ የተገኘ እና እሱን በመጠቀም በሠራተኞች ወይም በድርጅቱ ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ፣ 

  53.2.15 ማንኛውም አይነት የድርጅቱን ንብረት የሰረቀ ወይም ያጭበረበረ፣ ሌሎችም እንዲሰርቁ የተባበረ፣ 

  53.2.16. በፋብሪካው አጥር ዘልሎ የገባ፣ ዘልሎ የወጣ ወይም ዕቃ ያቀበለ፣ 

  53.2.17. የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 136 ንዑስ አንቀጽ 136 ቄጥር 5 ላይ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ውጪ ግን በአፈጻጸሙ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 160 ንዑስ ቁጥር 3 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ የጣሰ የዚህ እርምጃ አፈጻጸም ከዚህ በተመለከተው መሰረት ይፈጸማል፡፡ 

  53.2.18. የሥነ ስርዓት እርምጃ አወሳሰድ በሰንጠረዥ ላይ ይገለፃል፣ 

  53.2.19. የቅጣት ማንሻ ጊዜና የቅጣት ገንዘብ አጠቃቀም በህብረት ስምምነቱ በተጠቀሰው መሰረት ይፈጸማል፣ 

  53.2.20. በዚህ የሕብረት ስምምነት መሠረት ከሠራተኛው ቅጣት የሚሰበሰበው ገንዘብ የተለየ ሂሳብ ተይዞ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ እና አክሲዮን ማህበሩ በሚስማሙበት ሁኔታ ለአክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛ አገልግሎት የሚውል ቋሚ የልማት ስራ ላይ ይውላል፣ 

  53.2.21. በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት አንድ ሠራተኛ አጥፍቶ ከተቀጣ ወይም እርምጃ ከተወሰደበት በ6 /ስድስት/ ወር ውስጥ ሌላ ጥፋት ካላጠፋ ቀደም ብሎ የተወሰደበት እርምጃ እንደተሰረዘ ይቆጠራል፡፡ ሆኖም የገንዘብ ቅጣት የተወሰደበት ሠራተኛ ገንዘቡ ተመላሽ አይደረግለትም፡፡  

  53.2.22. የአክሲዮን ማህበሩ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ወይም አስተዳደር ኃላፊ ወይም በግልጽ የተወከለው ባለስልጣን አጥጋቢና በቂ የሆነ ምክንያት መሆኑን በትክክል ከተረዳ አንድ ሠራተኛ ላይ የተወሰደውን የሥነ ሥርዓት እርምጃ ለማሻሻል ወይም ለመሰረዝ ይቻላል፣ 

  53.2.23. ሠራተኛው ጥፋት አጥፍቶ የክስ ቻርጅ በቅርብ ኃላፊው ሲሞላ ጥፋቱን እስካላመነ ድረስ ወደ አስተዳደር ከመላኩ በፊት በዋና  ክፍል ኃላፊው በሚገባ መጣራት አለበት፡፡ 

  54.1.1. አንድ ሠራተኛ ከሥራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ በተወሰደበት የሥነ ሥርዓት እርምጃ ቅሬታ ሲሰማው ውሳኔ ከተሰጠበት የሥራ ቀን አንስቶ በ2 /ሁለት/ የሥራ ቀን ውስጥ ለክፍል ኃላፊው ቅሬታውን ያቀርባል፤ ኃላፊውም በሦስት የሥራ ቀን ውስጥ ምላሽ ይሰጣል፡፡ 

  54.1.2. በዋና ክፍል ኃላፊው ምላሽ ቅሬታው ካልተፈታ ለሚሰራበት መምሪያ ኃላፊ ቅሬታው ይቀርባል፡፡ የመምሪያው ኃላፊ ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር በሁለት /2/ የስራ ቀን ውስጥ ለክፍል ኃላፊው ቅሬታውን ያቀርባል፤ ኃላፊውም በሦስት የሥራ ቀን ውስጥ ምላሽ ይሰጣል፡፡ 

  54.1.3. በመምሪያው ኃላፊ ምላሽ ቅሬታው ካልተፈታ ሠራተኛው ቅሬታውን ቀጥታ ለአስተዳደር መምሪያ ያቀርባል የአስተዳደር መምሪያ ጉዳዩን አይቶ በሦስት /3/ የሥራ ቀናት ውስጥ መልስ ይሰጣል፡፡ 

  54.1.4. በአስተዳደር መምሪያ ምላሽ ቅሬታው ካልተፈታ ሠራተኛው ቅሬታውን ለፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ቅሬታውን መርምሮ በ5 /አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ መልስ ይሰጣል፡፡ የፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ውሳኔው የድርጅቱ የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል፡፡ 

  54.1.5. ሠራተኛው የአክሲዮን ማህበሩ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ በሰጠው ውሳኔ ያልረካ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት መብቱ ለሚፈቅደው ፍ/ቤት የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው፣ 

  54.1.6. ቅሬታ ያለው ሠራተኛ የቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ ከፐርሶኔል ሠራተኛ ግንኙነት ዋና ክፍል ወይም ከስራ ክፍሉ በመውሰድ በአንድ ኮፒ ሞልቶ ያቀርባል፣ 

  አንቀጽ 55

  የሕብረት ስምምነት ስለማሳተም፤

  አክሲዮን ማህበሩ ሠራተኛው ይህንን ህብረት ስምምነት በትክክል አንብቦ እንዲረዳና ግንዛቤ እንዲኖረው ለእያንዳንዱ ሠራተኛ አንዳንድ ኮፒ በማህበሩ አማካይነት ይሰጣል፤ 

  አንቀጽ 56

  የማህበሩ መዋጮ

  ማንኛውም ሠራተኛ የማህበሩ አባል ለመሆን ቢመዘገብ የአባልነት መዋጮ ከደመወዙ ተቆራጭ እንዲሆን ሠራተኛ ማህበሩ በጽሑፍ ሲጠይቅ አክሲዮን ማህበሩ በቀረበለት ጥያቄ መሠረት ገንዘቡን ከሰራተኛው ደመወዝ ላይ እንዲቆረጥ ያደርጋል፣ ሠራተኛው ከማህበር አባልነት መውጣት ቢፈልግ ጥያቄውን ለሠራተኛ ማህበሩ በማቅረብ በዚያ በኩል እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡ 

  አንቀጽ 57

  ቦነስ

  አክሲዮን ማህበሩ ከትርፍ ከታክስ በኋላ ከሚያገኘው ገቢ በሚከተለው ሁኔታ የሚከፋፈል ይሆናል፤ 

  ከ 2,000.000 – 3,000.000 ከሆነ 7%

  ከ 3,0000.001- 5,000.000 ከሆነ 9% 

  ከ 5,0000,000 በላይ ከሆነ 10% የሚከፋፈል ሲሆን የቦነሱ መጠን ግን ከሰራተኛው የሁለት ወር ደመወዝ መብለጥ አይችልም፡፡ 

  አንቀጽ 58

  HIV/ የኤች. አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ ተግባራት

  58.1. በአክሲዮን ማኅበሩና መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበሩ በጋራ በመሆን ኤች. አይ. ቪ ኤድስ ለመከላከልና ታማሚዎችን በመንከባከብ ረገድ በጋራ ይሠራሉ፡፡ 

  58.2. የመከላከልና የእንክብካቤ ተግባራት በቅርብ ሆኖ የሚሠራ የፀረ-ኤድስ ክበብ በሁለቱ አካላት ይቋቋማል፡፡ 

  58.3. ለክበቡ የሚያስፈልገውን ጽ/ቤት ሌሎች የማቴሪያል ድጋፎች በአክሲዮን ማህበሩ ይቀርባሉ፡፡ 

  58.4. ክበቡ በሚያወጣው የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ሥራውን ያከናውናል፡፡ 

  58.5. አክሲዮን ማህበሩ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩና ራሳቸውን ለአክሲዮን ማህበሩ ላሳወቁ ሠራተኞች አክሲዮን ማህበሩ ለአልሚ ምግብና ለመሳሰሉት በአጠቃላይ በየወሩ የ6000 /ስድሰት ሺህ ብር/ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ 

  አንቀጽ 59

  ስፖርት

  59.1. ሠራተኛው በስፖርት አካሉንና አእምሮውን ለማጎልበትና ጤነኛ አምራች ዜጋ ለመሆን እንዲችል የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበሩና አክሲዮን ማኅበሩ በጋራ በመሆን የስፖርት እንቅስቃሴን ያደራጃሉ፡፡ 

  59.2. የመሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበሩና የአክሲዮን ማህበሩ የስፖርት ክለብን በባለቤትነት ይመራሉ፣ ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮችን በማፈላለግ የክለቡ የገንዘብ አቅም እንዲጎለብት ያደርጋሉ፣ 

  59.3. አክሲዮን ማህበሩ ለስፖርት የሚመደበውን ወጪ በባለቤትነት ይቆጣጠራል፡፡ 

  አንቀጸ 60

  ስለ ሕጎች ውጤት

  ይህ የሕብረት ስምምነት ተመዝግቦና ወጪ ሆኖ ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የመንግስት መመሪያ ወይም ፖሊሲ የሚጥስ ወይም ሕግን የሚቃረን አንቀጽ ከተገኘ የሚቃረነው የህብረት ስምምነቱ አንቀጽ ተፈጻሚነት አይኖረውም፤ 

  አንቀጽ 61

  ስለ ሕጎች ተፈፃሚነት

  በዚህ ህብረት ስምምነት ባልተካተቱና አሠሪና ሰራተኛን በሚመለከቱ ጉዳዮችን ላይ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና የማሻሻያ አዋጅ 494/98 እና ሌሎችም መንግሥት ያወጣቸውንና የሚያወጣቸውን አዋጆች በዚህ ህብረት ስምምነትና አካል በመሆን ተፈጻሚ ይሆናል፤ 

  አንቀጽ 62

  የህብረት ስምምነት በሥራ ላይ ስለማዋል፤

  ይህ ስምምነት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 133 ቁጥር 3 መሠረት ከተፈረመበት ቀን አንስቶ እስከ ውሉ ፍጻሜ ድረስ በስምምነቱ ውስጥ የተጠቀሱትን ሁሉ አክሲዮን ማህበሩና ሠራተኛ ማህበሩ በሥራ ላይ ለማዋል ተስማምተናል፡፡ 

  አንቀጽ 63

  የህብረት ስምምነቱ ፀንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ፤

  ይህ ህብረት ስምምነት ላይ መመሪያ ከመንግስት ካልተሰጠ በስተቀር ለ3 /ሦስት/ ዓመት ፀንቶ ይቆያል ሆኖም አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 133 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፤ 

  አንቀጽ 64

  በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ ያልተጠቀሱት ጥፋቶች፤

  64.1. በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ ያልተጠቀሱ ጥፋቶች ቢከሰቱ አክሲዮን ማኅበሩ በዚህ ህብረት ስምምነት ከተዘረዘሩት ጥፋቶች ጋር በማገናዘብ ተቀራራቢ በሆነው አንቀጽ እና በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት እርምጃ ይወሰዳል፤ 

  64.2. አንድ ሠራተኛ ጥፋት አጥፍቶ እርምጃ ተወስዶበት ሳለ ሌላ ጥፋት በሌላ ሰንጠረዥ የተጠቀሰውን ቢያጠፋ እንደገና የጥፋቱ ደረጃ በአዲሱ ሠንጠረዥ አንድ ተብሎ ይጀመራል፡፡ በዚሁ አሰራር በተመሳሳይ ጥፋት ሰንጠረዥ በደረጃ ከፍታዎችም እየቀጠለ የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ይወስዳል እንጂ በተለያየ ጥፋት አንድ ተብሎ ነው የሚጀመረው፡፡ 

  አንቀጽ 65

  ወደፊት ስለሚወጡ ሕጎች ወይም ስምምነቶች

  65.1. በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ ያልተካተቱ ወይም ሊሻሻሉ የሚገባቸው አንቀጾች ቢኖሩ አክሲዮን ማህበሩና የሠራተኛ ማህበሩ በሚያደርጉት ስምምነት በህብረት ስምምነቱ እንዲካተቱ ወይም እንዲሻሻሉ ይደረጋል፡፡ ይህም በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከተመዘገበ በኋላ ተፈጻሚ ይሆናል፤ 

  65.2. በአዋጅ ቁጥር 377/96 እንደተመለከተው ወደፊት በሚወጡ ሕጎች ደንቦች እና መመሪያዎች ለሠራተኛው የተሻለ ጥቅም የሚሰጡ ሆነው ከተገኙ በስራ ላይ ለማዋል ይህ ህብረት ስምምነት አያድግም፡፡ 

  አንቀጽ 66

  የሥምምነቱ ዘመንና ስምምነቱን ስለማደስ፤

  66.1. ይህ ህብረት ስምምነት በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ኤጀንሲ/ ፀድቆ ከተመዘገበበት ወር ከመጀመሪያ ቀን ማለትም ከ     ቀን  ዓ.ም አንስቶ ለሦስት /3/ ዓመታት የፀና ይሆናል፡፡ 

  61.2. ከዚህ በላይ የተጠቀሰውና ዘመን ከማለቁ ከ3 ወር አስቀድሞ አዲስ ድርድር  ያሰበው ወገን በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ 

  61.3. ሕብረት ስምምነቱ ተጠናቆ ከተፈረመ በኋላ አክሲዮን ማህበሩ በራሱ ወጪ አሳትሞ ጉዳዩ ለሚመለከተው መ/ቤት ለሠራተኛ ማህበሩና ለእያንዳንዱ ሠራተኛ ይሰጣል፡፡ 

   የአደጋ መከላከያ መሣሪያ፣ የሥራና የደንብ ልብስ አሰጣጥ ዝርዝር ሰንጠረዥ፣ 

  ተ.ቁ

  ሥራ መደብ

  የሥራ የደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ ዝርዝር

  በስንት ጊዜ

  ፕላንና ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ

  1

  ለክፍሉ ኃላፊ

  • ነጭ ጋዋን (ኦቨርኮት)

  በ 6 ወር 1

  2

  ለመረጃ አጠናካሪና ተንታኝ

  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ነጭ ጋዋን (ኦቨርኮት)

  በ15 ቀን 1

  በ 6 ወር 1

  በ 6 ወር 1

  ፈትል መምሪያ

  1

  ለክፍሉ ፎርማን ሠራተኞች በሙሉ

  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ከካኪ የተሰራ ኦቨር ኮት

  በወር 1 

  በ 6 ወር 1 

  በ 6 ወር 1

  2

  ሲኒየር መካኒክ ጨምሮ ከሲኒየር መካኒክ በታች ላሉ ወንድ ሠራተኞች በሙሉ

  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ከካኪ የተሰራ የሥራ ልብስ ቱታ 

  በ 6 ወር 1 

  በ 6 ወር 1

  3

  ሻላፎረስት፣ ኦፕን ኢንድ፣ ሪሊንግ ወንድና ሴት ኦፕሬተር

  • ካኪ የተሰራ ቱታ ተለጣፊ ኪስ ያለው 
  • ቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሙና ባለ 250 ግራም

  በ 6 ወር 1

  በ 6 ወር 1

  በ15 ቀን

  4

  በሻላፎረስት፣ በሪሲንግ እና በኦፕን ኢንድ ላይ ከሚሰሩ ውጭ ላሉት ሴት ሰራተኖች

  • ፖፕሊን የተሰራ ቀሚስ 
  • ናይሎን የተሰራ እስከ አንገት የሚደርስ ሽርት

  በ 6 ወር 1 

  በአመት 1

  5

  ለብሎዊንግ ሠራተኞች

  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ከጨርቅ የተሰራ ቆብ 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም

  እንዳለቀ 

  በ 6 ወር 1 

  እንዳለቀ 

  በ15 ቀን 

  6

  ለቤል ስፕላይ እና አሬንጀር

  • ረጅም የቆዳ የእጅ ጓንት 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ

  እንዳለቀ 

  በወር 1 

  7

  ቤል ፕሬስ ሰራተኖችና ለቤል ፕሬስ ትራንስፖርተርስ 

  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • የአይን መከላከያ ጎግልስ 
  • ከጨርቅ የተሰራ ቆብ 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሳሙና ባ 250 ግራም

  እንዳለቀ 

  እንዳለቀ 

  እንዳለቀ 

  በበ 6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1

  8

  ለካርድ ማሽን ኦፕሬተርስ፣ ለፈትል ክፍል ቆሻሻ ጠራጊዎች ሮለር ፒከር

  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • ከጨርቅ የተሰራ ቆብ 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም

  እንዳለቀ 

  እንዳለቀ 

  በ 6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1

  ተ.ቁ

  የሥራ መደብ

  የሥራ የደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ ዝርዝር

  በስንት ጊዜ

  9

  ለሪንግ ፍራም፣ ለሪንግ ፍሬም ዶፈር ሄድ ለሮቪንግ፣ ለድሮዊንግ፣ ኮምበርና ላፕ ፎርመር ሰራተኞች

  • ከቆዳ የሰራ ጫማ 
  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም

  በ 6 ወር 1

  እንዳለቀ 

  በ15 ቀን 1

  10

  ለኦፕን ኢንድ ሠራተኞች

  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም

  እንዳለቀ 

  በ15 ቀን 1

  11

  ለፈትል ክፍል ጠቅላላ ትራንስፖርተርስ ሪሊንግፓከርን ጨምረ

  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 

  እንዳለቀ 

  በ 6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1

  12

  ለጁንየርና ለሲንየር መካኮች እስ ቴክኒካል ሄልፐርና እንዲሁም ለዘይት አጠጪዎችና ማሽን አጽጂዎች

  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም

  እንዳለቀ 

  በ15 ቀን 1

  13

  ለክፍሉ ፀሐፊዎች 

  • ከካኮ የተሰራ ኦቨር ኮት 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 

  በ6 ወር 1 

  በ6 ወር 2

  በ6 ወር 1

  14

  ሳተላይት ስቶር ኪፐርና ያርን ስቶር ኪፐር 

  • ከካኪ የተሰራ ኦቨር ኮት 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ

  በ6 ወር 1 

  በ5 ቀን 1

  በዓመት 1

  15

  የምርት ምዘገባ ክለርክ 

  • ከካኪ የተሰራ ኦቨር ኮት 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ

  በ6 ወር 1 

  በዓመት 1 

  በ15 ቀን 1

  16

  ለአየር ማመቻቻ ፎርማን 

  • ከካኪ የተሰራ ኦቨር ኮት 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ

  በ6 ወር 1 

  በ6 ወር 1 

  በ6 ወር 1 

  17

  ለአየር ማመቻቻ ሠራተኞች 

  • ከሱፍ ወይም ከጥጥ የተሰራ ቱታ 
  • የንፋስ መከላከያ የጆሮና የዓይን ጎግል 
  • ከቆዳ የተሰራ ጓንትና የጨርቅ ቆብ 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ከካኪ የተሰራ ልብስ ቱታ 
  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • የፕላስቲክ ቡትስ ጫማ
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  በዓመት 1 

  እንዳለቀ 

  እንዳለቀ 

  በ6 ወር 1 

  በ6 ወር 1 

  እንዳለቀ 

  በዓመት 

  በሣምንት 1

  18 

  ለኤሌክትሪክ ፎርማኖች 

  • ከካኪ የተሰራ ኦቨርኮት 
  • ከቆዳ የተሰራ ብረት የሌለው ጫማ 
  • የእጅ ጓንት ከፕላስቲክ የተሰራ 
  • ለፊት መከላከያ ማስክ 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 

  6 ወር 1 

  በ6 ወር 1  

  እንዳለቀ በኃ.ሲ 

  እንዳለቀ በኃ.ሲ 

  በ15 ቀን 

  19

  ሲኒየር ኤልክትሪሻን ጨምሮ 

  • ከካኪ የተሰራ የሥራ ልብስ ቱታ 
  • ከቆዳ የተሰራ ብረት የሌለው ጫማ 

  በ6 ወር 1 

  በ6 ወር 1


  ከሲኒየር በታች ላሉ 

  • የእጅ ጓንት ከፕላስቲክ የተሰራ 
  • የፊት መከላከያ ማስክ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም

  እንዳለቀ በኃ.ሲ 

  እንዳለቀ በኃ.ሲ 

  በ15 ቀን 

  20

  ለኤሌክትኖኒክስ ሰራተኞች 

  • ከካኪ የተሠራ የሥራ ልብስ /ኦቨር ኮት/  
  • ከቆዳ የተሰራ ብረት የሌለው ጫማ 
  • የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ኬሚካል መከላከያ ማስክ 
  • የዓይን መከላከያ መነጽር 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  በ6 ወር 1 

  በ6 ወር 1 

  እንዳለቀ በኃ.ሲ 


  እንዳለቀ በኃ.ሲ 

  በ15 ቀን 1

  ሽመና መምሪያ 
  1

  ለፎርማኖች 

  • ከካኪ የተሰራ ኦቨር ኮት 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም

  በ6 ወር 1

  በ6 ወር 1 

  በወር 1

  2

  ሲኒየር መካኒክን ጨምሮ እና ከሲኒየር መካኒክ በታች ላሉ የክፍሉ ሠራተኞች በሙሉ 

  • ከካኪ የተሰራ ልብስ ቱታ 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  በ6 ወር 1

  በ6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1

  3

  ለክፍሉ ሴት ሠራተኞች 

  • ከፖፕሊን የተሰራ ቀሚስ 

  በ6 ወር 1

  4

  ለሴት የሽመና እና ሪዋይንዲንግ ኦፕሬተሮች 

  • ከካኪ የተሰራ ልብስ ቱታ 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም  

  በ6 ወር 1

  በ6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1

  5

  ለዋርፒንግ ሠራተኞች 

  • የብናኝ መከላከያ ማስክ 
  • የአደጋ መከላከያ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  እንዳለቀ 

  በ6 ወር  

  በ15 ቀን 1

  6

  ለድሮዊንግ ኢንኦፕሬተሮች 

  • ከካኪ የተሰራ ቀሚስ  
  • ቆዳ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  በ6 ወር 1

  በ6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1


  7

  ለጽዳት ሴት ሰራተኞች 

  • ከካኪ የተሰራ ቀሚስ 
  • ከቆዳ የተሰራ ዓማ 
  • ሣሙና ባለ  250 ግራም  

  በ6 ወር 1 

  በ6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1

  8

  ለሳይዚንግ ሠራተኞች 

  • የእጅ ጓት 
  • የጎማ ቡትስ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 
  • ከቆዳ የተሰራ ዓማ 
  • ለብናኝ መከላከያ ማስክ 

  እንዳለቀ 

  እንዳለቀ 

  በ15 ቀን 1 

  በ6 ወር 1 

  እንዳለቀ 

  9

  ለሣይዚንግ ዋርፕድ ቢም ትራንስፖርት 

  • ከቆዳ የተሰራ ጓንት 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  እንዳለቀ 

  በ6 ወር  1 

  በ15 ቀን 1 

  10

  ለዋርፕ ታየር ሠራተኞች እና ረዳቶቻቸው

  • የድምጽ መከላከያ 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  እንዳለቀ 

  በ6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1 

  11

  ለቢም ሴተሮች ከነረዳታቸው 

  • ከቆዳ የተሰራ ጓንት 
  • የቆዳ ጫማ የአደጋ መከላከያ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  እንዳለቀ 

  በ6 ወር 1 

  በ15 ቀን 1

  12

  ለግሬይ ክሎዝ ዶፈርና ትራንስፖርተር 

  • ከቆዳ የተሰራ ጓንት 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ አደጋ መከላከያ 
  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 

  እንዳለቀ 

  በ6 ወር 1


  በ15 ቀን 1 

  13

  ለብራሺንግ ማሽን ሠራተኞች 

  • የጆሮ መከላከያ 
  • ሳሙና ባለ 250 ግራም 

  እንዳለቀ 

  በ15 ቀን 1

  14

  ለፎልዲንግ ማሽን ሠራተኞች 

  • ሣሙና ባለ 250 ግራም 
  • ከቆዳ የተሰራ ጫማ 

  በ15 ቀን 1

  በ6 ወር 1

  15

  ለፎርክሊፍት ኦፕሬተሮች