Collective Agreements Database


የህብረት ስምምነት

ይህ የኅብረት ስምምነት ዛሬ ሰኔ 1 ፣ 2003 ዓ/ም በኢትዮጵያ ህጎች መሰረት በተቋቋመው እና ከዚህ በታች “ድርጅት” እየተባለ በሚጠራው አይካ አዲስ ቴክስታይል ኤንድ ኢንቨስት ግሩፕ ኃላ.የተ.የግል ማህበር 

እና

በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት በተቋቋመው እና ከዚህ በታች ማህበር እየተባለ በሚጠራው የአይካ አዲስ ቴክስታይል ኤንድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃላ.የተ.ማህበር መካከል ተፈርሟል፡፡ 

አንቀጽ 1

ትርጉም

በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር 

አዋጅ፡- ማለት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ማለት ነው፡፡ 

መመሪያዎች፡- ማለት መንግስት ውስጥ ወይም ድርጅቱ ያወጣቸውንና ወደ ፊት የሚያወጣቸው መመሪያዎች ማለት ነው፡፡

ፋብሪካ /ድርጅት/፡- በአይካ አዲስ ቴክስታይል ኤንድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃላ.የተ.ማህበር ነው፡፡ 

ሰራተኛ፡-  በአይካ አዲስ ቴክስታይል ኤንድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃላ.የተ.ማህበርበመሪነት በደመወዝ ላልተወሰነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ስራ (በቋሚነት) ለመስራት ከፋብሪካው ጋር በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት ያለው ሰው ሲሆን ስራ መሪዎችን አያጠቃልልም፡፡ 

ደመወዝ፡- ፋብሪካው ሰራተኛ በቅጥሩ መሰረት ለሚከናወነው ስራ በቀን ወይም ወይም በወር ታስቦ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ነው፡፡ 



አንቀጽ 2

የስምምነቱ ዓላማ 

  1. እያደገ በሚሄደው ከፍተኛ የንግድ ውድድር ውስጥ የድርጅቱን ህልውና አስጠብቆ በተሻለ ደረጃ እንዲገኝ ለማድረግ 
  2. ሰራተኛው የድርጅቱ ህልውና መሰረት መሆኑ ታውቆ ጤንነቱ የሚጠበቅበትን አእምሮው አካሉ የሚዳብርበትን ለሰራው ተመጣጣኝ ክፍያ አግኝቶ የመኖር ዋስትናው የሚረጋገጥበትና ሰብዓዊ ክብሩ የሚጠበቅበትንና በድርጅቱ አስተዳደር የሚሳተፍበትን ሁኔታ መፍጠር
  3. ሰራተኛው በመልካም ስነምግባር ታንጾ ለስራው ያለውን ፍላጎትና ፍቅር በሚጠናከር ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ድርጅቱም ሆነ ማህበሩ ሰራተኛን እንዲያነቃቁ እንዲያበረታቱ ለማድረግ 
  4. በድርጅቱ ውስጥ የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲሰፍን ቅን አመለካከት እንዲኖረና ጤናማ የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ድርጅቱና ሰራተኛው መብትና ግዴታውን አውቀውና አክብረው በአንድነት ስራቸውን እንዲያከናውኑና ግንኙነታቸውንም እንዲያጠናክሩ ለማድረግ ነው፡፡ 

አንቀጽ 3

የስምምነቱ አቋም

  1. ስምምነቱ የሚመለከታቸው ሰራተኞች 
  1. ይህ የህብረት ስምምነት (በድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች ላይ ሁሉ የጸና ይሆናል፡፡ ሆኖም በዚህ የህብረት ስምምነት አባሪ፣ ላይ በተዘረዘሩት ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ 
  2. ይህ የህብረት ስምምነት በሚመለከታቸው ቋሚ ሰራተኞች እና በድርጅቱ መካከል የተደረገ ስራ ውል ሆኖ ይቆጠራል፡፡ 
  1. ለድርጅቱ የተጠበቁ መብቶች 
  1. በዚህ የህብረት ስምምነት ለሰራተኞች የተሰጠውን መብት እና በድርጅቱ መካል የተደረገ የስራ ውል ሆኖ ይቆጠራል፡ 
  2. ሰራተኛው የደረጃ እድገት ለማግኘት ወይም በተመጣጣኝ ደረጃ ወይም በዝቅተኛ የደረጃ ዝውውር ሊጤቅ በጥያቄው መሰረት ለመፈጸም ድርጅቱ አይገደድም፡፡ 
  3. በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት ማንኛውም የፋብሪካውን ስራ ለማቀድ ለመምራት፣ ለመቆጣጠር ሰራተኛን በአስፈላጊው ቦታ ለመመደብ እድገት ለመስጠትና ለማዛወር መብት የፋብሪካው ነው፡፡ 
  4. ሰራተኛው ጥፋት ፈፅሞ ቢገኝ በሰራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት ሰራተኛን ለመቅጣት ከደረጃ ዝቅ ለማድረግና ለተወሰነ ጊዜ አግዶ ለማቆየት 
  5. አዲስ የስራ ቦታ ለመክፈት ለነበረው የስራ ቦታ የሰራተኛን አስፈላጊነት ለመወሰን፣ በየስራው መደብ አስፈላጊውን የሰራተኛ ኃይል ለመመጠን፣ ለስራው የሚያስፈልጉትን የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ለመወሰን፣ አዲስ ሰራተኛ በህጉ መሰረት ለመቅጠር ተወዳድሮ ላሸነፈ ሰራተኛ ለዚህ የህብረት ስምምነት መሰረት ደረጃ እድገት ለመስጠት፣ 
  6. በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በቀር የፋብሪካውን ስራና ሰራተኛን በሚመለከት ጉዳዮች መግለጫ ለመስጠትና ማስታወቂያ ለማውጣት ትምህርት ፕሮግራም ለመስጠት 
  1. ለሰራተኞች የተጠበቁ መብቶች 
  1. ሰራተኞች በማህበር ለመወከል መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ በማህበሩም ጉዳይ ለመሳተፍና ስለ ማናቸውም የስራ ሁኔታ በነጻ እርስ በርሳቸው ወይም ከማህበሩ ባለስልጣኖች ጋር መወያየት ወይም ክርክር ሲነሳ እንደ አገባቡ በአይካ አዲስ ቴክስታይል ኤንድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃላ.የተ.ማህበር የስራ ቅሬታ ኮሚቴ ወይም ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም ድርጅቱና ማህበሩ ወደተስማሙበት ሶስተኛ አካል ወይም ለፍ/ቤት የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ 
  2. ሰራተኛው የደረጃ እድገት ለማግነት ወይም በተመጣጣኝ ደረጃ ወይም በዝቅተኛ ደረጃ ዝውውር ክፍት የስራ ቦታ እስካለ ድረስ የመጠበቅ መብት አለው፡፡ 
  1. ለማህበሩ ተጠበቀ መብቶች 
  1. ማህበሩ አግባብ ባላቸው ህጎች፣ ደንቦችና አዋጆች በተሰጠው መብት መሰረት የሰራተኞችን ጉዳይ ጥቅሞችና ደህንነት በሚመለከት ከድርጅቱ ጋር በዚህ የህብረት ስምምነት በተደነገገው ስነ ስርዓት መሰረት የመወያየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  2. ማንኛውም ሰራተኛ ከማህበሩ በጽሁፍ ላይወከል በማህበሩ ስም ምን አይነት ክርክር ወይም ድርድር ከድርጅቱ ጋር ሊያደርግ አይችልም፡፡ 

አንቀጽ 4

የድርጅቱና የሰራተኛው ግዴታዎች

  1. የድርጅቱ ግዴታዎች 

ድርጅቱ ከዚህ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ይፈጽማል፡፡ 

  1. በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅና በዚህ ህብረት ስምምነት ወይም በሌሎች ህጎችና መመሪያዎች ተመለከትን መብቶችና ግዴታዎች በትክክል ስራ ላይ ማዋል፡፡ 
  2. ለሰራተኛው በሰራ ውሉ መሰረት ስራ የመስጠትንና በስራው ውሉ ሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር ለስራ የሚያስፈልገውን መሳሪያና ጥሬ እቃ ለሰራተኛው ማቅረብ አለበት፡፡ 
  3. ለሰራተኛው ደመወዙንና ሌሎች ከፍያዎችን በአዋጁ ወይም በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት የመከፈል 
  4. ለሰራተኛው የሚገባውን ሰብዓዊ ክብር የመጠበቅ 
  5. የሰራተኛው ጤንነት እንዲመረመር በህግ ወይም አግባብ ባለው ባለስልጣን ግዴታ በሚባልበት ጊዜ ለምርመራው የሚያስፈልገውን ወጪ የመቻል፡፡ 
  6. የስራ ውል በሚቋረጥበት ወይም ሰራተኛው በሚለቅበት ማናቸውም ጊዜ ሰራተኛው ሲሰራ የነበረውን የስራ አይነት፣ በአገልግሎ ዘመኑና ሲከፈለው የነበረውን ደመወዝ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ለሰራተኛው በነጻ መስጠት፡፡ 
  7. ፋብሪካው ለሰራተኛው ሰራተኛውን ፎቶ ግራፍ የተለጠፈበት የሚሰራበትን ቦታ የሚያመለክት የመታወቂያ ካርድ መሰጠትና ሰራተኛው የወሰደው መታወቂያ ካርድ መጥፋቱ የተረጋገጠ ግን ዋጋውን አስከፍሎ አዲስ የመስጠት እንዲሁም የስራ መደብ ለውጥ ሲኖር በነጻ መስጠት 
  8. በማህበሩና በድርጅቱ መካከል የሚፈረመውን ህብረት ስምምነት ለእያንዳንዱ ሰራተኛ ታትሞ እንዲሰጠው የማድረግ 
  9. ማህበሩ መጠቀሚያ የሚሆን የማስታወቂያ ሰሌዳ የማዘጋጀት 
  10. ለዚህ ስምምነት በሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንዲሁም በሌሎች የሰራተኛ ጉዳይ የሚገኙ ውስጥ የተመለከቱት መከተልና ማክበር፡፡ 
  11. በአንቀጽ 3.2.1. የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ፖሊሲዎችን ደንቦችንና ድንጋጌዎችን መከተልና ማክበር 
  12. የድርጅቱ ፖሊሲዎች ደንቦችና ድንጋጌዎች በዚህ ሰምምነት ወይም በሰራተኛ ጉዳይ አዋጆች ለሰራተኛው የተሰጡትን መብቶች ጥቅሞችና የስራ ሁኔታዎች አይቀንሱም፡፡ 
  13. በድርጅቱ ደንብ መሰረት ልዩ ልብስ መልበስ ላለባቸው ሰራተኞች የሚያስፈልገውን የስራ ልብስ በነጻ ይሰጣል፡፡ 
  14. የስራውን ጠባይ በመመልከት እና እንደ አስፈላጊነቱ ድርጅቱ ሴፍቲ አፈሰር በሚያዘጋጀው ማንዋል መሰረት ድርጅቱ ለሚመለከታቸው ሰራተኞች አደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን ይሰጧል፡፡ 
  15. ሰራተኛው በማህበር አባልነት የሚከፍለው መዋቾ ከወር ደመወዙ ተቆራጭ እንዲሆን በጽሁፍ ፈርሞ ሲጠይቅ ድርጅቱ ተገቢውን ክፍያ ከሰራተኛው ደሞዝ በመቁረጥ የተቆረጠውን ገንዘብ ወደ ማህበርተኛ ተቀናሽ የሚሆነውን ገንዘብ መቀነስ አተሞ ሙሉ ደመወዙን ለሰራተኛው ይከፍላል፡፡ 
  16. በፍ/ቤት ትእዛዝ ወይም ሰራተኛው በፈቃዱ አንዲቆረጥ ከጠየቀው በስተቀር ከሰራተኛው ደመወዝ የሚቆረጥ ገንዘብ ሊኖር ተቆራጭ መሆኑን ለሰተኛው ይከፍለል፡፡ 
  17. የማህበሩ አባል በሆነ ሰራተኞች ወይም በማህበሩ ስም ህጋዊ ተግባር በሚያከናውነት በማህበሩ መሪዎች ላይ የማደናቀፍ አግባብነት የሌለው የጣልቃ ገብነት የማስገደድና የእድሉ ተግባር አይፈጽምም፡፡ 
  18. ሰራተኛውን ለአንድ ጥፋት ከአንድ ጊዜ በላይ አይከሰስም ወይም አይቀጣም 
  19. አንድ ጥፋት ሰራተኞች በህብረት የፈጸሙ መሆናች ካልተረጋገጠ በስተቀር በህብረት አይቀጡም፡፡ 
  20. የስራ ውሉ ለተቋረጠ ሰራተኛውን ሙያውን የሰራበትን ዘመን ደመወዙንና ከስራ የለተቀበተን ምክንያት ገልጾ ፎቶግራፍ ያለበት የምስክር ወረቀት ሰራተኛው ክሊራንስ ከጨረሰበት ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ድርጅቱ ይሰጣል፡፡ 
  21. ድርጅቱ ለማህበሩ ጽ/ቤት ያዘጋጃል፡፡ 
  22. አንድ የድርጅቱ ሰራተኛ እድሜው ለጡረታ ከመድረሱ አንድ አመት በፊት ድርጅቱ ይህንኑ ያሳውቀዋል፡፡ 
  23. ሰራተኛውም ጡረታ ለመውጣት ስድስት ወር ሲቀረው አስፈላጊ ፎርማሊቲዎችን የማሟላት ግዴታ አለበት፡፡ 
  24. ይህ ስምምነት ተፈጻሚ በሚሆንባቸው ስራ መደቦች ላይ የሚሰራ ሰራተኛ የስራ ጊዜውን ጨርሶ በጡረታ ከተገለለና እዚህ ከፍት ቦታ ላይ ለመመደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሌላ ሰራተኛ ከሌላ ድርጅቱ በጡረታ ተገለለገውን ሰራተኛ በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ወይም ስለ ማንኛውም ሰው ሊያስራ ይችላል፡፡ 
  1. የሰራተኛው ግዴታዎች 
  1. በዚህ ስምምነት በሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ በሌሎችም የሰራተኛ ጉዳይ ህጎች በድርጅቱ ደንብ በስራው መግለጫ ተዘረዘና እንዲሁም በድርጅቱ የሚሰጠው //////
  2. ………. 
  3. የሰራተኛው የድርጅቱን ስምና …….. 
  4. የተሰጠው የስራ መመሪያ ወይም የተመደበለትን ስራ በሚገባ መፈጸም 
  5. ስራውን ለማከናወን የሚነሳ ሀሳባቸው ልቦታ ወይም  … መሳሪያ ወይም አቃ በጥሩ ሁኔታ ማፀበቅና 
  6. ድርጅቱ በሚያዘው መሰረት መስሪያት ወጪ ………… በመውለድ እንዲሁምስለ ንፀህና አጠባበቅና የአደጋ መከላከያ በዚያው ደረጃ …….. በጥንቃቄ መፈፀም 
  7. ሆን ብሎ ወይም …… በራሱ ወይም በሌሎች ሰዎች ህይወት አደጋ ወይም …… የሚያስከትል ድርጅቶች ሁሉ መቆጠብ 
  8. አደጋ የሚያደርስ ወይም ድርጅቱን ወይ የስራ ቡድን ወይም የድርጅቱ …… ለመጉዳት ወይም ለማጥፋት የሚቻል አስጊ ሁኔታ ሲፈጠር አስርዳታ መስጠት . ….. ማሳወቅ ከሰራተኛ አቅም በላይ ካልሆነ እርዳታ መስጠት እራሱን ወይም ….. ለአደጋ ካላጋለጠው ሰራተኛው እርዳታ የመጠየቅ ግዴታ አለበት፡፡ 
  9. የድርጅቱ ገንዘብ ወይም ሌላ ማንኛውንም ንብረት መሰረቱን ባማከለ …. ወይም ያለአግባብ መዋሉን ያየ ወይም ያወቀ ወይም እጅ ከፍንጅ የያዘ ሰራተኛ ሁኔውን ለሚመለከተው ድርጅት ወይ ባለስልጣን ወይም ለድርጅቱ ደንነት ጥበቃ ወዲያውኑ ማሳወቅ ወይም መጠቆም አለበት፡፡ ሆኖም ሁኔታው በድርጅቱ ተጠሪዎች ማሳወቅ ካልተቻለ የድርጅቱ አይነት ወዲያውኑ እርምጃ የሚያስፈልገው ለመሆኑ ……. አግባብ ባለው መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ አካል ማሳወቅ ወይም መጠቆም አለበት፡፡ 
  10. ማንኛውም ሰራተኛ በመደበኛ ስራው ላይ ሆኖ እንቅልፍ አለመተኛል 
  11. በሰራተኛ አእምሮ በሚያደነዝዝ እፅ እና በአልኮል መጠጥ ሀይል ተመርኩል ከስራ ገበታው ላይ ያለመገኘት 
  12. ሰራተኛው በተሰጠው የስራ ልብሶች የአደጋ መከላከያ መጠቀም 
  13. የፋብሪካው ማንኛውም ሰራተኛ ፋብሪካውን የአሰራር ሚስጥር ወይም ለሌሎች መረጃዎች ለሌሎች ሶስተኛ ወገን አሳልፎ አለመስጠት 
  14. ፋብሪካው አስተዳደሩ ሳይቅድ ልዩ ልዩ ማስታወቂያዎችን ያለመለጠፍ ሆኖም ከሰራተኛ ማህበር የሚወጡ እና የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችን አይመለከትም እንዲሁም በአሰሪና ሰራተኞች  ከሚፈቀደው ውጪ አድማ ያለማድረግ 
  15. ማንኛውም ሰራተኛ 

ሀ. አግባብ ባለው ድርጅቱ ባለ ስልጣን ሳይፈቀድለት ማንኛውንም የድርጅቱን ወይም በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የሚገኘው ንብረት ወይም እቃ ለግል ወይም ከሶስተኛ ወገን ጥቅም ማዋል ማውጣት ወይም መውሰድ አይቻልም፡፡ 

ለ. ለስራ ላይ ያሉት ሰራተኞች በሚያውክና በሚረብሽ ጉዳትና ጥፋት በሚያወጣ ትክክል ባልሆነ ሁኔታ ወይ በፈጠረው መጥፎ ሁኔታ ላይ ሆኖ በስራ ላይ መገኘት አይችልም፡፡ 

ሐ. በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማናቸውም ግለሰብ ላይ መዛት ወይም ማናቸውንም ግለሰብ መሰደብ፣ መዘለና መምታት አይችልም፡፡ 

መ. የድርጅቱ ፖሊሲዎች ደንቦችና ስርዓቶች ድንጋጌዎች ወይም የዚህን ስምምነት ግዴታዎች መጣሽ ወይም….. አይችልም፡፡ 

ሠ. ለስራ ብቁ የሆነ የአዕምሮና የአካል ሁኔ ይዞ በስራ ላይ መገኘት፡፡ በድርጅቱ ውስጥ አልኮል መጠጥ ጠጥቶ አደንዛዥ እጾችን እንደ ጫት ተጠቅሞ መግባት ፈጽሞ አይችልም፡፡ 

ረ. በስራ ላይ ሰራተኛ የስራ ኃላፊው የሚሰጠውን ስራ የመስራት ግዴታ አለበት ሰራተኛው በሀላፊው ላይ ቅሬታ ቢናረው ስራወን ላያቋርጥ ቅሬታውን በአግባቡ በአስተዳደር ስራ መመሪ መሰረት ለሚመለከተው ክፍል የማቅረብ 

ሰ. በድርጅቱና በሰራተኛ ማህበር ወይም በድርጅቱና በሰራተኞች መካከል አለመግባባት የሚፈጠር ሐሰተኛ ማሰራጨት ጠብ ማንሳት ወይም ጠብ እንዲነሳ ከመገፋት በብርቱ መጠንቀቅ አለበት፡፡ 

አንቀጽ 5 

የሰራተኛ ማህበሩ ግዴታ 

ማንኛውም ሰራተኛ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ግዴታዎች መፈጸም አለበት፡፡  

  1. አባሎቹ የህብረት ስምምነት አፈጻጸም አስመልክቶ በሚሰጠው ትምህርት ተባባሪ መሆን 
  2. አባሎቹን የዘመናዊ ኢንዱስትሪ አሰራርን ባህልን እንደለበሰና ለድርጅቱ ስራ ምርታማነትን ለማሳደግ የስራ ባህላቸው ከፍ እንዲከፍል የማስተማርና የማበረታታት 
  3. ከድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በቅርብ በመነጋገር ለኢንዱስትራ ሰላም ጠንቅ የሚሀጎ የአሰራር ሂደቶችን ጥቆማ የማድረግና እርማት እንዲደረግባቸው የማሳወቅ 
  4. መልካም የሆነ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ 

አንቀጽ 6 

በህብረት ስምምነቱ ውስጥ ስላልተጠቀሱ ጉዳዮች 

በዚህ ስምምነት ውስጥ ያልተወሰነ ፋብሪካውንና ማህበሩን በጋራ የሚመለከት ነጥብ ወደፊት ቢያጋጥም የፋብሪካው አስተዳደርና የሰራተኛ ማህበሩ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በጋራ ውይይት በማድረግ የተስማሙበትን ነጥብ የዚህ ህብረት ስምምነት አካል እንዲህን ይደርጋል፡፡ ሆኖም የህብረት ስምምነቱ እካል ለመሆን ስምምነት የተደረገበት ነጥብ ሰራተኛና ማህበር ጉዳይ ጽ/ቤት መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ 




አንቀጽ 7 

ስህተት ስለማረም 

  1. ፋብሪካው በልዩ ልዩ ምክንያቶች በስህተት ለሰራተኛው የሚያስፈልገውን ደረጃ ደሞዝ እድገት ጨምሮ …………. የማመላለስ ሌሎች የተፈፀመ ………….

ሀ. የደሞዝ ብቻ ጭማሪ የተሰጠው ሰራተኛ ………… በተጨመረበት ቀን ……… አስከ ተሰጠበት ጊዜ ድረስ የተሰጠው …………

ለ. በስህተት የተቀነሰበት ግን ሊስተካከልለትና ቀደም ብሎ የቀረቡትን ክፍያ በአንድ ጊዜይከፈለዋል በስህተት ………..ደረጃ የተፃፈለት ሰራተኛ ግን ትክክለኛውን ደረጃ ተቀብሎ  …………………

አንቀጽ 8 

የቅጥር ውል አመሰራረት 

  1. በሌላ አኳሀን ያልተወሰነ ወይም በዚህ ህብረት ስምምነት ተለይቶ ካልተጠቀሰ በስተቀር ይህ ህብረት ስምምነት የእያንዳንዱ ሰራተኛ የአሰሪው ውል አካል ነው፡፡ 
  2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የእረፍት ጊዜ የስራ አይነት የደሞዝ አከፋፈልን የስራ ውጤት መለኪያ ………. የደህንነት ጥበቃና የአደጋ መከላከያ ……… ደንቦችን ለሌሎች ሰራተኛ ሁኔታዎች አፈፃፀም አሰሪው የተደነገገ የስራ ደንቦች መመሪያዎች ስራ ውል አካል ሆነው ይቀጠራሉ፡፡
  3. ለቅጥር የተመረጠ ሰው የቅጥር ውል ይሰጠዋል የቅጥር ውል ይዘት በአዋጅ ቁጥር 177…. አቀንቀጽ ….. የተጠቀሱትን መያዝ ይኖርበታል፡፡ 

አንቀጽ 9 

ማስተዋወቅ 

አዲስ የተቀጠረ ሰራተኛ ስለፋብሪካው አላማ ተግባርና ኃላፊነት አሰራር የስራ ቦታ፣ ስለ ስራ መደቦች የውስጥ መመሪየዎች ስለ ህብረት ስምምነት መብትና ግዴታዎች በፋብሪካው ክልል ውስጥ ስላለው የስራ እንቅስቃሴ ማህበራዊ ግልጋሎት አጠቃላይ በነፃ በድርጅቱ ውስጥ ኃይል በኩል ……….. ይደረግለታል፡፡ 

አንቀጽ 10

የሰራ አፈፃፀም ምዘና

  1. በአመት ሁለት ጊዜ የስራ አፈፃፀም ምዘና ሰራተኛው ያለውን አእምሯዊና አካላቂ ችሎታዎችን በመጠቀም ፋብሪካው በተወሰነ የተግባር ኃላፊነት ክልል ውስጥ የሰጠውን ተግባራት በአጥጋቢ ሁኔታ ማከናወኑን ለማወቅ በአመት ሁለት ጊዜ የሚደረግ ግምገማ ምዘና ነው፡፡ 
  2. የሰራ አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት ስርዓት ፋብሪካው ባወጣው የአስተዳደር ስራ መመሪያ መሰረት ሲሆን 

ሀ. በሰራተኛው የቅርብ አለቃ በአንድ ኮፒ ይሞላል፡፡ ለአስተዳደር ይተላለፋል፡፡ 

ለ. ቅጽን የሞላው ኃላፊ የስራ አፈጻጸም የተሞላለት ሰራተኛን አስተያየት እንዲያሰፍር በማድረግና በማስፈረም ለራሴ ኃለፊ አቅርቦ ያጸድቃል፡፡ 

ሐ. የተሞላው የስራ አፈጻጸም ቅጽ ለሚመለከተው የበላይ ኃላፊ ታይቶ ከጸደቀ በኋላ ለአስተዳደር ይተላለፋል፡፡  

መ. አስተዳደሩም ተሞልቶ የቀረበለች የስራ አፈጸጸም ቅጽ በደንቡ መሰረት በትክክል መሞላቱን ሰራተኛው የፈረመበት መሆኑንና ቅጹ ያለሰርዝ ድልዝ መሞላቱን በማረጋገጥ በሰራተኛው የግል ማህደር ኢንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡ 

ምዕራፍ አራት 

አንቀጽ 11 

ደመወዝ 

  1. ደመወዝ ማለት በተሰራበት ሰዓትና ታስቦ በወር የሚከፈል መደበኛ ክፍያ ነው፡፡ 
  2. በዚህ ህብረት ስምምነት አፈጻጸም የሚከተሉት ክፍያዎች እንደ ደመወዝ አይቆጠሩም፡፡ 

ሀ. ትርፍ ሰዓት ክፍያ 

ለ. የውሎ አበል 

ሐ. የትራንስፖርት አበል 



መ. ለተጨማሪ የስራ ውጤቶች የማትጊያ ክፍያ 

ሠ.በኤነት የሚሰጥ ልዩ ልዩ ጥቅሞች 

ረ. የስራና የአደጋ መከላከያ ልብሶችና መገልገያዎች 

አንቀጽ 12 

የደመወዝ አከፋፈል 

  1. ለማንኛውም ሰራተኛ ላልሰራበት ደመወዝ አይከፈለውም፡፡ 
  2. ደመወዝ በቀጥታ ለሰራተኛው ወይም ለወኪሉ ይከፍላል፡፡ ተወካይ የፋብሪካው ሰራተኛ መሆን ይኖርበታል፡፡ 
  3. ከፋብሪካው ሰራተኛ ውጭ በሌላ ሶስተኛ ወገን ሊከፈልለት የሚችለው ውክልናው ስልጣን ባለው መስሪያ ቤ የተረጋገጠ ሲሆን ነው፡፡ 
  4. በህግ ወይም ለሰራተኛው የጽኁፍ ስምምነት በስራ ደንብ ወይም በፍ/ቤት አዛዥ ካልሆኑ በስተቀር የማንኛውም ሰራተኛ ደመወዝ አይዝም አይቆርጥም፡፡ 
  5. ደመወዝ በወሩ መጨረሻ ይከፈላል፡፡ ሆኖም የክፍያው ቀን በዓል ወይንም እሁድ ከሆነ አስቀድሞ ባለው የስራ ቀን ይከፈላል፡፡ 

አንቀጽ 13 

ከደመወዝ ላይ መቀነስ 

ከሰራተኛው ደመወዝና ልዩ ልዩ ክፍያዎች ላይ መቀነስ የሚቻለው በሚከተሉት ምክንየት ብቻ ነው፡፡ 

  1. ከፍ/ቤት በሚሰጥ ትእዛዝ 
  2. በህግ፣ በስራ ደንብ ወይም በዚህ ስምምነት መሰረት የሚቆረጥ መዋጮ ግብር 
  3. ሰራተኛው ራሱ በጽሁፍ ተስማምቶበት የሚሰጥ ብድር ሌላ ክፍያ 
  4. ፋብሪካው በህብረት ስምምነቱ፣ በስራ ደንብ ወይ በህጉ መሰረት በገንዘብ የቅጣት እርምጃ ሲወስድ 
  5. ሰራተኛ ማህበሩ ይቆረጥልኝ ብሎ በሚያቀርበው ማረጋገጫ 
  6. በአንድ ጊዜ ከሰራተኛው ደመወዝ ላይ በእዳ ሊቆረት የሚችለው የገንዘብ መጠን በወር …. አይበልጥም 

ምዕራፍ አምስት 

አንቀጽ 14 

የሰራ ሰዓት

  1. ማንኛውም ሰራተኛ መደበኛ የስራ ሰዓት በቀን ከስምንት ወይም ከሳምንት ከአርባ ስምንት ከ48 ሰዓት አይበልጥም፡፡ የስራ ሰዓት ለሳምንት የድርጅቱ ስረቃ ቀኖች እኩል ይደለደላሉ፡፡ የስራው ጠባይ ሊያስገድድ ግን በማናቸውም ሳምንት የስራተኞች የስራ ሰዓቶችን ማሳጠር እና ልዩነቱን ለተቀሩት ቀኖች ማደላደል ይቻላል፡፡ 
  2. መደበኛ ስራ ሰዓት ማለት በህግ በህብረት ስምምነት ወይም በስራ ደንብ መሰረት ሰራተኛው ስራውን የሚያከናውንበት ወይም በስራ ላይ የሚገኝበት ጊዜ ነው፡፡ 
  3. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ፋብሪካው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የስራ ሰዓትን ለመቀነስ ለማሻሻልና ለመለወጥ ይችላል፡፡ ይህ እርምጃ ሊወሰድ የደመወዝ ለውጥ አይደረግም፡፡ 

አንቀጽ 15

መደበኛ የስራ ሰዓት

  1. ፈረቃ በሽፍት ማለት በፋብሪካው የምርት ስራ በቀጥታና በድጋፍ ሰጭነት ተሰማርተው የሚሰሩ ሰራተኞች የምርት ተግባራቸውን ለማከናወንና ደጋፊ አገልግሎት ለመስጠት በየቀኑ በስራ ላይ የሚያውሉትን የስራ ሰዓት ነው፡፡
  2. የፋብሪካው ሰራተኞችና ኃላፊዎች በስራ ጸባይ ምክንያት በሶስት ፈረቃ ተከፍለው የሚሰሩ ሲሆኑ የስራ ሰዓታቸውን በቀን 8 ሰዓት በሳምንት 48 ሰዓት ይሆናል፡፡ በየሽፍቱ 45 ደቂቃ የእረፍት ጊዜ ማሸንና ስራ ሳይቶም በወረፋ 

ከሰኞ እስከ ቀዳሜ 

  1. የቀን ክፍያ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት 
  2. የአም… ከቀኑ 9፡00 እስከ ምሽቱ 5፡00 ሰዓት
    1. የስልት አዳሪ ከምሽት 5፡00 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 1፡00 ሰዓት 

    ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 

    1. ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ለሚሰራ ሰራተኞች በሰራተኞች በስራው ሰዓት መካከል የምርት ስራን በማይጎዳ ሁኔ ሰዓት የማይበልጥ የኤጀት ጊዜ ይሰካል፡፡ 
    2. በማንኛውም የስራ ሰዓት ወይም በሳምንት የእረፍት ወይም በበዓል ቀናት ሁሉ ወይም በማንኛውም አጋጣሚ ፋብሪካው ቢቆምም ቀጥሎ የተመለከቱት አገልግሎት ሰጨቺ ሰራተኞች እንደአስፈላጊነቱ ቁጥራቸው ተወስኖ በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡ 
    1. በህክምና ባለሙያ 
    2. የጥበቃ ሰራተኞች 
    3. የእሳት አደጋ ሰራተኞች 
    4. ሹፌሮች 
    5. አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ባለሙያዎች 

    አንቀጽ 16

    የሰዓት መቆጣጠሪያ ምዝገባ

    1. ሰራተኞች ለስራ ሲገቡና ከስራ ሊወጡ  በፋብሪካው የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ ይመዘገባሉ፡፡ 
    2. የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ በእጅ ፊርማ በካርድ በጣት አሻራ በሌላ ፋብሪካ አመቺ ሆኖ በሚያገኘው ዘዴ ይሆናል፡፡ 
    3. ለፋብሪካው በተዘጋጀው የመቆጣጠሪያ ምዝገባ ላይ ያልተመዘገበ ሰራተኛ በልዩ ትዕዛዝ ምክንያት መመዝገቡን አለመቻን በተዘጋጀው ፎርም ሞልቶ በቅርብ አለቃው ከተረጋገጠ ቀሪ አይሆንም፡፡ 
    4. በሰዓት መቆጣጠሪያ ከተመዘገበ ከፈረመ በኋላ በስራ ገበታው ላይ ያልተገኘ ሰራተኛ ከስራ እንደቀረ ይቆጠራል፡፡ 
    5. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 እና 4 መሰረት ቀሪ የሆነ ሰራተኛ ከስራ መቅረት የሚያስከትለው የዲሲፒሊን እርምጃ ይወሰድበታል፡፡ 

    አንቀፅ 17 

    ትርፍ ሰዓት 

    1. በህብረት ስምምነትና ….. የቀን የመደበኛ የስራ ሰዓት በላይ የስራ የትርፍ ሰዓት ስራ እንደሰራ ይቆጠራል፡፡ 
    2. የትርፍ ሰዓት የሚሰራው በፋብሪካው ስልጣን ከተሰጠው የስራ ኃላፊ በሚሰጥ …… የደሞዝ ነው 
    3. የትርፍ ሰዓት የሚሰራው ፋብሪካው ሌላ አማራጭ ላይ ኖረው ሲተር በአዋጅ ቁ ….. አንቀጽ ….. የተደነገገው አንደተጠበቀ ሆኖ 

    ሀ. አሰደጋ ሲደርስ ወይም አደጋ የሚደርስ መሆን ሲገመት 

    ለ. ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ለድጋግም 

    ሐ. አስቸኳይ የሚሰራ ስራ ሲደጋገም 

    መ. በማያቋርጥ ተከታታይ ስራ ላይ ከስራ የቀሩ ሰራተኞች ለመለካት ነው፡፡ 

    አንቀጽ 18 

    የትርፍ ሰዓት ስራ አፈጻጸም 

    1. የትፍር ሰዓት ስራ የሚሰራ ሰራተኛ ከመደበኛ ደመወዙ በተጨማሪ ቀጥሎ በተመለከተው አኳን ይከፈለዋል፡፡ 

    ሀ. ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ለሚሰራ የትርፍ ሰዓት ስራ የሚከፈለው የሰዓት ደመወዝ በአንድ ተሩብ … ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ 

    ለ. ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ለሚሰሩ ትርፍ ሰዓት ስራ ለመደበኛ ሰሪው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ አንድ ተኩል /1.5/ ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ 

    ሐ. በሳምንት የእረፍት ቀን ለሚሰሩ የትርፍ ሰዓት ስራ ለመደበኛ ስራው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በሁለት ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ 

    መ. በህዝብ በዓላት ቀን ለሚሰራ የትርፍ ሰዓት ስራ በመደበኛ ስራው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በሁለት ተኩል 2.50 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ 

    1. የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከደመወዝ ጋር ተደምሮ ይከፈለዋለ፡፡ 
    2. የህዝብ በዓልና የሳምነት እረፍት ቀን ተደራርቦ ቢውል ትርፍ ሰዓት ስራ በተ/ቁ 2/መ መሰረት ይከፈላል፡፡ 

      አንቀጽ 19 

      የሳምንት እረፍት ጊዜ 

      1. ማንኛውም ሰራተኛ በሰባት ቀናት ውስጥ ያልተቆራረጠ ሃያ አራት ሰዓት የሳምንት እረፍት ያገኛል፡፡ 
      2. የፋብሪካው ሰራተኞች በሙሉ የሳምነት እረፍት በተቻሉ መጠን ባንድ ጊዜና ባንድ ላ ይወስዳሉ፡፡ በተቻለ መጠን የሳምንት እረፍት ቀን እሁድ ይሆናል፡፡ ድርጅቱ በሚያከናውነው የስራ ወይም በሚሰጠው አገልግሎት …. ምክንያት ሳምንት እረፍት ከሁሉም ሰራተኞች እሁድ ተን ማድረግ ካልተቻለ ልዩ የሳምንት እረፍት ቀን ….. ቀን የሳምንት እረፍት ሊያደርግ ይችላል፡፡ 

      ምዕራፍ ስድስት 

      አንቀጽ 20 

      የዓመት እረፍት ፈቃድ አሰጣጥ 

      ሰራተኛው ደመወዝ የሚከፈልበት የአመት እረፍት ፈቃድ በሚከተለው ሁኔታ ይሰጣል፡፡ 

      1. ሰራተኘው የአመት እረፍት ፈቃድ ሚወስደው የእረፍት ጊዜው ከተጠራቀመበት አመት ቀጥሎ ባለው አመት ውስጥ ነው፡፡ 
      2. ድርጅቱ በቅድሚያ በጽሁፍ ካልፈቀደ በስተቀር የአመት እረፍት ፈቃድ ወደሚከቀጥለው አመት አይተላለፍም፡፡ 
      3. የአመት እረፍት ፈቃድ ሚጠራቀመው ሰራተኛ ለሰራበትና ደመወዝ ለተከፈለበት ወር ነው፡፡ 
      4. በአስቸኳይ ጉዳይ ምክንያት ካልፀና በቀር አዲስ ሰራተኛ የአመት እረፍት ፈቃድ የሚሰጠው ለድርጅቱ ስድስት ወር ተከታታይ ካገለገለ በኋላ ነወ፡፡ 
      5. ሴት ሰራተኛ በአመት የኣመት ፈቃ ላይ ሆኖ ብትወልድ ከወለድበት ቀን አንስቶ የወሊድ ፈቃድ ይሰጣል ስራ የምትጀምረው ተቋርጦ የነበረውን የኣመት እረፍት ፈቃድ ስትጨርስ ነው፡፡ 
      6. የሰራተኞች የአመት እረፍት ቀናት ብዛት እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ 
      7. አንድ የፋብሪካ ሰራተኛ ለመጀመረ የአመት እረፍት ፈቃድ ያገኛል፡፡ 
      8. የአመት እረፍት ፈቃድ በአመቱ ውስጥ ለሰራ አመት በሆነ ጊዜ ይሰጣል፡፡ 
      9. ፈቃድ የሚሰጠው በአስተዳደር በኩል ነው፡፡ 
      10. ሰራተኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከፋብሪካ ሲለቅ የአመት እረፍት ፈቃድ በገንዘብ ተቀይሮ ይለጠዋል፡፡ የአመት እረፍት ፈቃድ ከ2 ዓመት በላይ አይተላለፍም አይጠራቀምም፡፡ 
      11. የሰራተኞች የተጠራቀው የአመት እረፍት ከ2 ዓመት በላይ እንዳይዘገይ ፋብሪካው ለሰራተኞቹ በአጠቃላይ በየአመቱ የማስታወሻ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ 

        አንቀጽ 21 

        የአመት ፈቃድ መከፋፈልና ማስተላለፍ 

        1. ሰራተኛው የአመት እረፍት ፈቃድ ተከናሉ እንዲሰጠው የ….. ፋብሪካ ስታስማማ ….. ይሰጠዋ፡፡ 
        2. የአመት እረፍት ፈቃድ ሰራተኛው ሲጠይቅና ፋብሪካውም ሲስማማ ይተላለፋል 
        3. ፋብሪካው ስራ ሁኔታ ሲያስገድደው የሰራተኛውን የፈቃድ ጊዜ ሊያስተላለፍ ይችላል፡፡ 
        4. የተላለፈ የአመት እረፍት ፈቃድ ከሚቀጥለው ሁለት አመት በላይ ሰ……..

        አንቀጽ 22 

        ከፈቃድ ስለመጥራት 

        1. በፈቃድ ላይ ያለ ሰራተኛን ለመጥራት
        2. ሰራተኛው ከፈቃድ ተጠርቶ ለሰራ ስራ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ …. ፈቃድ በገንዘብ ተምኖ ይከፈለዋል፡፡ 
        3. ሰራተኛ በመጠራቱ ምክንያት ወጣውን የመጓጓዣና የውል አበል ወቺ ፋብሪካው ይችላል፡፡ 
        4. በዚህ አንቀጽንኡስ አንቀጽ መሰረት ሚከፈለው ስራተኛው … ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ 

        አንቀጽ 23 

        የጋብቻ ፈቃድ

        ሰራተኛው ህጋዊ ጋብቻ ለመፈጸም ማስረጃውን አያይዞ ሊያቀርብ ደመወዙ የሚከፈልባቸው ሶስት ስራ ቀናት እረፍት ይሰጠዋል፡፡ የሚሰጠው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው፤፤ 

        አንቀፅ 24 

        የሀዘን የቀብር ፈቃድ 

        1. ሰራተኛው አባት፣ እናት፣ ሚስት፣ ባል፣ ልጅ ጉዲፈቻ ልጅ ወይ እስከ 2ኛ ደረጃ ድረስ የሚቆጠር ወይም የጋብቻ ዘመድ ሲሞትበት ደመወዝ ሚከፈልብ ስራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ 
        2. አንድ ሰራተኛ በዚህ አንቀጽ ከተገለጹት ሲሞት በተቻለው መጠን በአስቸኳይ ለድርጅቱ ስለሚያስፈልገው የሐዘን ፈቃድ ወዲያውኑ ማስታወቅ ያስፈልጋል፡፡ 
        3. የፋብሪካው ባልደረባ ሆነ ሰራተኛ በሞት ጊዜ ስራ በማይበደልበት አኳኋን በየክፍሉ ኃላፊዎች አማካይነት ከፍሉ ለተወጣቱ በጠቅላላ ለ15 ለማይበልጡ ሰራተኞች በቀብር ስነ ስርዓት ላይ እንዲገኙ ፋብሪካው ሰዓት ፈቃድ ከሙሉ ደመወዝ ጋር ይሰጣል፡፡ 
        4. በስራ ላይ በሚደርስ ጉዳት ማለትም በስራ ላይ በሚደርስ አደጋ ወይም በስራ ምክንያት በሚመጣ በሽታ የፋብሪካው ሰራተና ሲሞቱ ለሟቹ አስክሬን እንዲሁም በቀብሩ ስነ ስርዓት ላይ እንዲገኙ በተፈቀደላቸው ሰራተኞች መሄጃና የትራንስፖት አገልግሎት ቀርበል፡፡ በወቅቱ ለዚህ አገልግሎ የሚውል ተሸከርካሪ ከሌለው ተከራይቶ ይቀርባል፡፡ 
        5. ከስራ ጋር ግንኙነት ለሌላቸው ምክንት ሰራተኞች ሲሞት ለአስክሬንና በቀብሩ ስነ ስርዓት ላይ እንዲገኙ ለተፈቀደላቸው ሰራተኞች ፋብሪካው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ በወቅቱ ለዚህ አገልግሎት የሚውል ተሸከርካሪ ተከራይቶ ይቀርባል፡፡ 
        6. በስራ ላይ በሚደርስ አደጋ ወይም በስራ ምክንያት በሚመጣ በሽታ እንዲሁም በሌላ ምክንት ሰራተኛ ሲሞት ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) የቀብር ማስፈጸሚያ ለሟች ቤተሰብ ይሰጣል፡፡ 

          አንቀጽ 25

          ያለደመወዝ የሚሰጥ ፈቃድ 

          ሰራተኛው ልዩ እና አሳሳቢ ሁኔ ሲያጋጥመው በዓመት እስከ 5 ተከታታይ ቀናት ያለ ክፍያ ፈቃድ የማግነት መብት አለው፡፡ 

          አንቀጽ 26 

          ለሰራተኛ ማህበር መሪዎች የሚሰጥ ፈቃድ

          1. የማህበሩ አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት ለማቅረብ እና አንደየሁኔታው በጎደሉ አመራር አባላት ምትክ ምርጫ ለማድረግ በአመት አንድ ጊዜ ለማህበሩ አባላት ሰራተኞች አራት ሰዓት ፈቃድ ከደሞዝ ጋር ይሰጣል፡፡ 
          2. ለማህበሩ የስራ አስፈጻሚ አባላት ስብሰባ በወር አንድ ቀን ለአራት ሰዓት ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣል፡፡ 
          3. በየክፍሉ ለሚገኙ … የማይበልጡ የማህበር ምክር ቤት አባላት የማህበሩን ስራ አስፈጻሚ ሪፖርት ለመስማት በአመት ሁለት ጊዜ በስድስት ወራት አንድ ቀን ለአራት ሰዓት ማህበሩ በጽሁፍ ሲጠይቅ ድረጅቱ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣል፡፡ 
          4. ስድስት የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ አባላት ለእያንዳነዳቸው በሳምንት አራት ሰዓት ለሰራተኛ ማህበሩ ቢሮ አገልግሎት ብቻ ሚውል እረፍት አሰሪው ከደሞዝ ጋር ይሰጣል፡፡ 



          አንቀጽ 27

          ልዩ ተግባሮችን ለማከናወን የሚሰጥ ፈቃድ

          ከፍ/ቤት፡፡ ከፖሊስ ሌሎችም ተመሳሳይ አካላት በምስክርነት ወይም በማስረጃነት ሲጠራ ለተጠራበት ጊዜ ብቻ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም በስራ ክርክር ሳይሆን በሌላ ሁኔታ በከሳሽነት ወይም በተከላሽነት ለሚጠራበት ጉዳይ የሚሰጠው ደመወዝ ማይከፈልበት ፈቃድ ነው፡፡ 

          አንቀጽ 28

          የትምህርት ፈቃድ

          1. ማንኛውም ሰራተኛ በፋብሪካው በሚዘገጅ ወይም በፋብሪካው አማካይነት በሚካሄድ የስልጠና የትምህርት ፕሮግራም ሊከፈልና መከፈልም በማስረጃ ሲረጋገጥ ሙሉ ደመወዝ ይከፈላቸዋል፡፡ 
          2. ከሰራ ሰዓት ውጭ በግሉ የከፍተኛ ትምህርት ለሚከታተል ሰራተኛ  በፈተና ወቅት ቤቱ የፈተና ፕሮግራም መሰረት እተረገ…. ለፈተናው ሰዓት ብቻ ደመወዝ ሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል 
          3. በመንግስት ት/ቤት በቴክኒክና ሙያ ት/ቤት እና ከዛ በላይ ከስራቸው ጋር በቀጥታ የተገናኘ የትምህርት አይነት በትርፍ ሰዓት ለሚማሩ ሰራተኞች በድርጅቱ ውስጥ ከሁለት አመት በላይ የገለገሉ በአመት ውስጥ ለሰላሳ ሰራተኛ ትምህርታቸውን ወደ ሚቀጥለው ክፍል ማለፋቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ለከፈሉት ክፍያ ህጋዊ ደረስና ቢያቀርቡ ፋብሪካው ሰራተኞቹ ባለመዘገበት ውቴት መሰረት ከዚህ እንደሚከተለው ወጪያቸው ይሸፍናል፡፡ 

          ሀ. በጣም ከፍተኛ ማእረግ ላስመዘገበ ተማሪ 100% የትምህርት ክፍያ 

          ለ. ከፍተና ማዕረግ ላስመዘገበ ተማሪ 25% የትምህርት ክፍያን 

          ሐ. ማዕረግ ላስመዘገበ ተማሪ 50% የትምህርት ክፍያ 

          . ከ2.75- 324ላስመዘገበ ተማሪ የትምህርት ክፍያን ወጪያቸውን ይሸፍናል፡፡ ሆኖም ግን ሰራተኛው ስለሚማረው የትምህርት አይነትና ደረጃ አስቀድሞ ለፋብሪካው ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ 

          ውጤቱ ከ 2.75 በታች በሆነ ተማሪ ፋብሪካው የትምህርት ክፍያ አይከፍሉም፡፡ 

          1. በድርጅቱ ለሰራተኛው የትምህርት ክፍያ  ለመከፈል ከተስማማ ሰራተኛው ከድርጅቱ ጋር ውል የመፈራረም ግዴታ የኖርበታል፤፤ ይህ ውል ሰራተኛው ለተጨማሪአመት በድርጅቱ እንዲሰራድርጅቱ ከከፈለው የትምህርት ክፍያ ጋር ማኔጅመንት ተመጣጣኝ የሆነውን የሚ… ይሆናል፡፡ 

          አንቀጽ 29 

          የህመም ፈቃድ 

          1. የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሰራተኛ በስራ ላይ በሚደርስ ጉዳት ሳይሆን … ህመም … ውስጥ እንደሚከተለው የህመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ 

          ሀ. ለ2 ወራት ጊዜ ሙሉ ደመወዝ የሚከፈልበት 

          ለ. ለ2 ወራት 50% ደመወዝ ሚከፈልበት 

          ሐ. ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ደመወዝ ማይከፈልበት ፈቃድ 

          1. ከዚህ በላይ የተመለከተው ፈቃድ ህመሙ ከደረሰበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ባለው  የአስ ሁለት ወር ጊዜውስጥ በተከታታይ ወይም በተሌዩ ጊዜያት ቢወስድም በማንኛውም ሁኔታ 6 ወር ከ 15 ቀን አይበልጥም 
          2. ሰራተኛው የህመም ፈቃድ ማግኘት የሚችለው ስለህክምና አገልግሎት በተደነገገው መሰረት ሆኖ ፈቃዱ ተቀባይነት ሚኖረው የድርጅቱ ክሊኒክ ወይም የድርጅቱ ክሊኒክከላካቸው የህክምና ተቋማት ብቻ ነው፡፡ 

            አንቀጽ 30 

            የወሊሶ ፈቃድ 

            1. የእርግዝና ምርመራ ፈቃድ 

            ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ ከእርግዝናዋ ጊዜ የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሰጣታል፡፡ሰራተኛዋ ከምርመራ በኋላ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 

            1. የእርግዝና እረፍት 

            ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ ከመወለድ በፊት በሀኪም አንድታርፍ ከታዘዘከደመወዝ ክፍያ ጋር እረፍት ይሰጣታል፡፡

            1. ቅድመ ወሊድ ፈቃድና የወሊድ ፈቃድ 

            ሀ. ነፍሰ ጡ የሆነች ሰራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት የ30 ተከታታይ ቀናት እንዲሁም በትውልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ለ60 ተከታታይ ቀናት ወሊድ ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣታል፡፡ 

            ለ. ሰራተኛዋ ከመውለድ በፊት ወለደችው የሰላሳ ቀን ፈቃድ እስኪያልቅ ካልወለደች እስከምትወልድ ቀን ድረስከደመወዝገር የወሊድ ፈቃደ ይሰጣታል፡፡ 

            ሐ. የሰላሳ ቀንፈቃደ ሳያልብትወልድ ከወለደችበትን ጀምሮ የምትወስደው የስድሳ ቀን የወሊድፈቃደ ይጀምራል፡፡ 

            መ. ነፍሰ ጡርየ… ሴት ሰራተኛ ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ እንዲሁም የትርፍ ሰዓት ስራማሰራት አይቻልም፡፡ 

            ምዕራፍ ሰባት 

            አንቀጽ 31 

            ዝውውር

            1. ፋብሪካው ሰራተኛውን ከአንድ የስራክፍል ወደ ሌላ የስራ ክፍል ወይም የስራ ቦታ ከአንድ ፈረቃ ወደ ሌላው ፈረቃ እንዲሁም አቻ ወደሆነ የስራ መደብ ጥቅሙን በመጠበቅ አዛውር ማሰራት ይችላል፡፡ 
            2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ላይ የተገለጸው ቢኖርም ለአጭር ጊዜ ሚቆይ ስራ ለመስራት የተከማቹ ዌም አስቸኳይ ስራ ለማጠናቀቅ ጊዜው ስራው እስኪጠየቅ ስራው የሚመለከተው ኃላፊ በጊዜያዊ ዝውውር ሰራተኛን በማንቀላቀስስራ ውጭሊያሰራ ይችላል፡፡ 

            አንቀጽ 32 

            የደረጃ እድገት

            1. የደረጃ እድገትአንድ ፋብሪካ ሰራተኛ ብዙ ሆኖ ሊገኝ ከያዘው የስራ ደረጃ ወደ ከፍተና የስራ ደረጃ 
            2. የደረጃ እድገት ሲኖር ለቦታው የሚጠየቀውን የችሎ መመዘኛ የማያሟሉ የፋብሪካ ሰራተኞች እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡


            አንቀጽ 33

            በስራ አፈጻጸም ድክመት ወይም በዲሲፒሊን ችግር ምክንያት አሰሪው ሰራተኛን ከደረጃ እና ከደመወዝ ዝቅ ማድረግ ይችላል፡፡ 

            ምዕራፍ ስምንት 

            አንቀጽ 34 

            ልዩ ልዩ አባሎችና ክፍያዎች 

            1. የውሎ አበል 

            አንድ ሰራተኛ ከአለም ገና ከተማ ክልል ውች 100 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ወዳለው ቦታ ለስራ ጉዳይ በፋብሪካው ሲላክ 250 የወሎ አበል ይከፈለዋል፡፡ 

            ሀ. የአየር ጠባይ አባል ወደሚከፈልበት የስራ ቦታ ለሚላክ ሰራተኛ ካለ ከተመለከተው በተጨማሪ ለመንግስት ሰራተኞችየውሎ አበል አከፋፈል በሚኒስትሮች ምክር ብቻ የካቲት 10ቀን19… ዓ/ም በወጣው መመሪያ መሰረት ተከትሎ ይከፈላል፡፡ 

            ለ. የውሎ አበል ተከፍሎት የሚጓዝ ሰራተኛ የትርፍ ሰዓት አይከፈለውም 

            ሐ. የውሎ አበል ተከፍሎት የሚጓዝሰራተኛ ከተወሰነውጊዜ በላይ ከቆየና የቆየበት ምክንያተቀባይነት ካላገኘ ተጨማሪ ጊዜ አበል አይታሰብለትም እንደሁኔታው የዲሲፒሊን እርምጃ ሊወሰድበትም ይችላል፡፡ 

            ምዕራፍ ዘጠኝ 

            አንቀጽ 35 

            የህክምና አገልግሎት 

            1. የፋብሪካው ሰራተኛ ጤንነት እንዲጠበቅ በክሊኒክ ነጻ ህክምና ይሰጣል፡፡ ሆኖም መድሃኒት በድርጅቱ ክሊኒክ ቢ… ብቻ የመድሃኒቱን ዋጋ በሚቀርበው ደረሰኝ መሰረት 10% ድርጅቱ ከፍሎ ቀሪው 10% በሰራተኛው መሸፈን አለበት፡፡ ነገር ግን ከ1000 ብር በላይ ላለው የህክምናና የመድሃኒት ውጪድርጅቱ 95% የሚሸፍን ላይ ቀሪው 5% በሰራተኛው ይሸፈናል፡፡ 
            2. ከስራ ጋር ላልቴያዘ ህመም ወይም አደጋ ከፋሪካው ክሊኒክ አቅም በላይ ሆኖ የፋብሪካው ከክሊኒክ ወደ… የህክምና ተቋም ወይም ከፋብሪካው ጋር የህክምና አገልግሎት ስምምነት ወዳላቸው ህክምና ተቋማት የሚላክሰራተኛ ለሚሰጠው አገልግሎ ህጋዊ ማስረጃ ሲያቀርብ ፋብሪካው ለሆስፒታል ለሆስፒታል ወጪ 90% ይከፍላል፡፡ 
            3. አሰሪው ለሰራተኛው የሚሰጠው የህክምና አገልግሎ እና የመድህኒት ወጪበአመት ውስጥ ከሶስት ሺ ብር (3000) ብር አይበልጥም፡፡ 

              አንቀጽ 36 

              የህክምና አገልግሎት ስርዓት 

              1. በስራ ሰዓት ለመታከም የሚጠይቅ ሰራተኛ ቅርብ ኃላፊውን በማሳወቅ መታከሚያ ወረቀት ሊሰጠው ለህክምና ይቀርባል፡፡ 
              2. በታካሚው የህክምና መጠየቂያ ቅጽ ወረቀቱን ቅጸ ወረቀቱን የሚሰጠው ሰራ ኃላፊ ሙሉ ስሙን በመጻፍ ይፈርሙበታል፡፡ 
              3. ለታካሚው ሰራተኛህክምና ካርድ በድርጅቱ ክሊኒክ ይወጣለታል፡፡ 
              4. ታካሚው ስራ መስራት መቻልና አለመቻሉ ወይም ሀኪም ቤት ተኝቶ የሚታከም እንደሆነ የሚወሰነው በድርጅቱ ክሊኒክ ወይም ከድርጅቱ ክሊኒክ ተልኮ በታከመበት የህክምና ተቋም ነው፡፡ 
              5. ሰራተኛው በስራ ላይ አያለ ህመም ሲያጋጥመው ከክሊኒክ አቅም በላይ ከሆነ ከፋብሪካው ጋር የህክምና ስምምነት ወዳላቸው ሆስፒታሎች በድርጅቱ ክሊኒክ ይላካል፡፡ አደጋው አሳሳቢና ከፍተኛ መሆኑን ድረጅቱ የህክምና ባለሙያ ሲያረጋግጥ የትረንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 
              6. ከስራ ላይም ሆን ከስራ ውቺ ለህክምና ወደ ክሊኒክ ሄዶ የህመም ፈቃደ ተሰጠው ሰራተኛ ወዲያውኑ ለክፍሉ ኃላፊ ወይም ለአስተዳደር በራሱ ወይም በመልእክት በ24 ሰዓት ውስጥ ማሳወቅ አለበት፡፡ ሆኖም ታማሚው ሰራተኛ የህመም ፈቃዱን ጨርሶ ወደ ስራ በተመለሰ በ8 ሰዓታት ውስጥ ህክምና ፍቃዱን የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ 

              አንቀጸ 37 

              የህክምና አገልግሎት የማይሰጡ ጉዳዮች 

              1. በአምባጓሮ ወይም ጥል በሰራተኛው ላይ የደረሰ ጉዳት፣ 
              2. በስካር፣ በእጽ ምክንያት የሚመጣ አደጋ 
              3. ለጽንስ ማስወረድ
              4. ወሊድና የእርግዝና ክትትል
              5. ረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ሚፈልጉ ከባድ በሽታዎች እንደ ካንሰር ጉበት ኩላሊት 
              6. በግል የህክምና ተቋማትና በውጭ አገር ሚደረጉ ህክምና አገልግሎት 

              አንቀጽ 38 

              ሆስፒታል ተኝቶ መታከም 

              ሆስፒታል ተኝቶ የሚታከም ሰራተኛ በተገኘው የመኝታ ክፍል ውስት የህክምናአገልግሎት ይገኛል፡፡ 

              ምዕራፍ አስር

              አንቀጽ39 

              ስልጠና

              1. ሰራተኛውን ለስልጠና መምረጥ የፋብሪካው ተግባር ነው፡፡ ለስልጠና የተመረጡ ሰራተናለስልጠናው መካፈል ግዴታ አለበት፡፡ 
              2. ከስራ ገበታ ላይ ተነስቶ ለሚሰለጥኑበት ጊዜ ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ 
              3. ሰራተኛውእናአሰሪው በሚዋዋሉት የስልጠና ውል መሰረት ሰራተኛው ስልጠናባገኘበት ሙያ አሰሪውን የማገልገል ወይም ገንዘብ መከፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡ 
              4. የፋብሪካ የስልጠና አፈጻጸም በፋብሪካው በሚወጣው አስተዳደር ስራ መመሪያ መሰረት ይሆናል፡፡ 


                ምዕራፍ አስራ አንድ 

                አንቀጽ 40

                የስንብት ማስጠንቀቂ በጽሁፍ /በእጅ/ መስጠት ማስታወቂያ ማውጣት

                1. በፋብሪካው ሆነ በሰራተኛው ስራ ውል በማቋረጥ ማስጠንቀቂያ የሚሰጠው በጽሁፍ ነው፡፡ በማስጠንቀቂያው ላይ ምክንያቱ ይዘረዘራል፡፡ ውሉ የሚቋረጥበት ቀን ይገለጻል፡፡ 
                2. ለሰራተኛው ተጻፈ ማስጠንቀቂያ ለራሱ በእጁ ይሰጣል፡፡ በአሰሪው ወይም በወኪሉ የሚሰጥ ማስጠንቀቂ ለሰራተኛው በእጅ ማስጠት አለበት፡፡ ሰራተኛውን ማግነት የማየቻል ከሆነ ወይም ማስጠንቀቂያውን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ ማስጠንቀቂያው ሰራተኛው በሚገኝበት የስራ ቦታ ግልጽ በሆነ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጠፋል፡፡ 
                3. የማስጠንቀቂያ ጊዜ 

                የሙከራ ጊዜውን ጨርሶ በቅነሳ ምክንያት ከስራ ለሚሰናበት ሰራተኛ ሁለት ወር ሲሆን፣ በቅነሳ ከሚሰናበቱ ውጭ በሌላ ምክንያት ማስጠንቀቂ ለሚሰናበቱ ሰራተኞች ደግሞ ሙከራ ጊዜውን ጨረሰና እስከ አንድ አመት ገለገለ ከሆነ አንድ ወር ከአንድ አመት በላይ እስከ 9 አመት አገልግሎት ላለው ሰራተኛው ግን ሁለተ ወር ይሆናል፡፡ ከ9 ዓመት በላይ ያገለገለ ሰራተኛ 3 ወር ማስጠንቀቂያ መስጠትአለበት፡፡ 

                አንቀጽ41

                ለጊዜው ስለማገድ 

                1. አንደ ከስራ ውል የሚ….መብትና ግዴታን በተመለከተ በአቀጹ በተደነገገ መሰረት ለጊዜው መታገድን ወይም ሰራተኛው ጥፋት አጥፍቶ ጉዳዩ አስኪጣራ ድረስ በአጥፊው ላይ ለተ… ጊዜ የሚወለድ ከስራና ከደመወዝ መታገድ ይጠቃልላል፡፡ 
                2. አንድ ሰራተኛ ጥፋት አጥፍቶ ጉዳ እስዲጣራ ከ10 ቀን ላልበለጠ ጊዜ ከስራ ከደመወዝ ሊታገድ ይችላል፡፡ 
                3. የታገደ ሰራተኛ እገዳ ሲነሳለት መነሳቱ በጽሁፍ ይገለጽለታል፡፡ 


                አንቀጽ 42 

                የእገዳ ምክንያት 

                1. ከስራ ውል ሚመነጩ መብትና ግዴታዎችን ለጊዜው ለማገድ በቂ ምክንያት የሚሆኑት የሚከተሉ ናቸው፡፡  

                ሀ. በሰራተኛው ጥያቄ … የሚሰጥ ፈቃድ 

                ለ. ለሰራተኛው በሰራተኞቹ ማህበር ወይም ህዝባዊ አገልግሎት ለመስጠት ተመርጦ ለዚሁ ተግባር ፈቃድ እንዲሰጡ ስልጣንና አግባር ባለው መስሪያ ቤት ሲጠየቅ 

                ሐ. ሰራተኛው ከ 30 ቀን ለማይበልጥ ጊዜ በተከታታይ ሲታሰርና በ10 ቀን ውስት መታሰሩ በድርጅቱ ሊታወቅ 

                መ. ብሄዊ ጥሪ 

                ሠ. ከ10 ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ ድርጅቱን ስራ በሙሉም ሆነ በከፊል የሚቋርጥ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንት 

                ረ. ከ10 ከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ ድርጅቱን ስራ የማያቋርጥ ያልተሰበ የገንዘብ ችግር 

                1. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ሠ እናረ በተመለከተው ምክንያት እገዳ ሊፈጸም ፋብሪካው ለእግዳው ምክንያት የሆነው ሁኔታ … በሶስት ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴሩ በጸሁፍ ያሳውቃል፡፡ 

                አንቀጽ 43 

                የሰራተኛ ቅነሳ 

                1. የሰራተኛ ቅነሳ በተመለከቱት ምክንያት ቁጥሩ ከፋብሪካው ጠቅላላ ሰራተኛ ቢያንስ 10% ያህሉን ሰራተና የሚመለከት ከአስር ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ ሚቆይ የሰራተኞች ቅነሳ ነው በዚህ መሰረት ፋብሪካውን ድርጅታዊ አቋም ወይም ስራ እንቅስቃሴ በሚመለከት ሚከተሉት ምክንት በማስጠንቀቂ ስራ ውል ለማቋረጥ በቂ ምክንት ይሆናሉ፡፡

                ሀ. ሰራተኞች ተሰማሩባቸውን ስራዎች በከፈልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቂታው ሚያስቆም የሰራተኞች ቅነሳ የሚያስከትለው ሁኔታ ሊከሰት 

                ለ. የፋብሪካን ምርታማነት ለማሳደግ የአሰራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ በሰራተኞች ቅነሳን የሚያስከትል ውሳኔ 

                1. የሰራተኛ ቅነሳ የሚያስከትሉ ሁኔታዎች እንዳይከሰቱ ፋብሪካውንና ሰራተኛ ማህበሩ የትራንስፖርት ሰርቪስአገልግሎት የደንብ ልብሶችና ሌሎች ወጪዎችን በተቻለ መጠኝለመቀነስ ተባብረው ይሰራሉ፡፡ 
                2. የሰራተኛ ቅነሳ ማለት ሰራተኞች ለመቀነስ ፋብሪካው እርምጃ ከወሰድበት ቀን በፊት ባለው አስራ ሁለት ወራት ውስጥ በፋብሪካው ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞችን አማካይ ቁጥር ነው፡፡ 
                3. የሰራተኛ ቅነሳ ፋብሪካው በሰራተኞች ማህበር ውስጥ ወይም ተወካይ ጋር በመመካከር የስራ ችሎታ ያላቸውንና ከፍተና የምርት ውጤት የሚያሳዩ ሰራተኞችን በሰራቸው ላይ እንዲቆዩ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ ተመሳሳይ የስራ ችሎታ ያላቸውና ተመሳሳይ የምርት ውጤት ሚያሳዩ ሰራተኞች ሲኖሩቅነሳው በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከታቸው ሰራተኞች በሚከተለው ቅደም ተከተል መሰረት ይወሰናል፡፡ 

                ሀ. ከዚህ ቀጥሎ … እስከ … የተመለከተ እንደተጠበቀ ሆኖ በፋብሪካው ለአጭር ጊዜ …. ሰራተኞች

                ለ. አነስተኛ ቁጥር ያላቸው …. 

                ሐ. በዚህ ንኡስ አንቀጽ ….. ያልተካተቱ ሰራተኞች 

                መ.በፋብሪካው ላይ በስራ ምክንያት  ጉዳት የደረሰባቸው ሰራተኞች 

                ሠ. የሰራተኛ ተጠሪዎች 

                ረ. ነፍሰጡር ሴቶች 

                አንቀጽ 44 

                ጡረታ 

                ፋብሪካው በግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ከወጣው አዋጅ 715/2005 መሰረት የሰራተናውን ድርሻ ከደመወዝ ላይ በመቁረጥ ድርጅቱን በመጨመር ለኤጀንሲው ጊዜ ደርጋል፡፡ 

                1. ማንኛውም ሰራተኛ ሲቀጠር የጡረታ ቅጽ ይሞላል የጡረታ መለያ ቁጥር ይገለጽለታል፡፡ 
                2. ማንናውም ሰራተኛ የመመሪያ አድማው ቢደርስ በአገልግሎት ምክንያት በጡረታ ከመገለሉ በፊት በተቻለ መጠን ከስድስት ወር አስቀድሞ የጡረታ ቅጽ ይሞላል፡፡ የተጠየቀውን ማስረጃ አሟልቶ ያቀርባል፡፡ 

                  አንቀጽ 45 

                  የስራ ውል ሲቋረጥ የሚፈጸም ክፍያ 

                  1. የስራ ውል ሲቋረጥ ደመወዝ አመት እረፍት ፈቃድ ሌሎች ክፍች በሰባት ቀናት ውስጥ ተሰርተው ለስራተኛው ይከፈለዋል፡፡ 
                  2. ሰራተኛ ከፋብሪካው ተረከበውን ወይም በልዩ ልዩ አጋጣሚ በእጁ ሊገባ የቻለውን ንብረት የተበደረውን ገንዝ ለስራ ያወጣው ያልተወራረደ ጥሬ ገንዘብ በሌላ ሰራተኛ ወይም ለሰራተኛ ወገን ዋስ ሆነለት እዳ ከተገኘ በንብረቱግምትና በእዳው ልክ ለሰራተና ከሚከፈል ማንኛውም አይነት ክፍያ ላይ ፋብሪካው በቀጥታ መቀነስና ገቢ ማድረግ ይችላል፡፡ 
                  3. የስራ ውል ሊቋረጥ የሚከፈሉ ልዩ ልዩ 1 ፍዎች የሚከናወኑት ሰራተኛው ከእዳ ነጻ መሆኑን የሚረጋገጥ ከሲንስአጠናቆ ሲቀርብ ይሆናል፡፡ 

                    አንቀጽ 46 

                    ስንብት ክፍያ 

                    ስራ ስንብት ክፍያ በአሰሪና ሰራተና ህጉ መሰረት ሊከፈለው በሚገባ ሰራተኛ የስራ ውሉ ሲቋረጥ ይከፈለዋል፡፡ 

                    አንቀጽ 47 

                    ስራ ደህንነት 

                    1. ማንኛውም ሰራተና ስውን ሊያከናውን ለሚደርስበት ስራ አደጋ ህክምና እንዲሰጠው ራሱ ስራ ባህሪ ወይም ቤተሰቦች ወዲውኑ ለፋብሪካው ማሳወቅ አለባቸው 
                    2. የቅርብ ኃላፊው የደረሰውን አደጋ በሚመላከትበ24 ኣት ውስጥ የአደጋውን መንስኤና ሁኔተ ለሚመለከተው ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡ 
                    3. ሰራተናው ደረሰበትን አደጋ ባለማሳወቅ በሚከተለው ጉዳት ፋብሪካው ተጠያቂነት የለበትም፡፡ 
                    4. ፋብሪካው ለሰራተኛ የአደጋ መከላከያ መሳሪ ልብስና ሌሎች ቁሳቁዎች ቀርባል፡፡ ስለአፈጻጸሙ …. ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የክልል ወይም የወረዳው ሚመለክታቸው የሙያ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅን አስመልክቶ በባለሙያ የሚያሰቡ አስተያየቶችንና መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋሉ፡፡ 

                    አንቀጽ 48 

                    የአደጋ መከላከያና ስራ ልብስ 

                    1. የሙያ ደህንነት ጤንነትና የስራ አካባቢን በሚመለከት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 92፣93 እና 94 ላይ የተደነገገው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 
                    2. የስራ ልብስና የአደጋ መከላከያ ጥቅም ወይም ደመወዝ ሳይሆን ሰራተኛው በስራ ላይ እያለ ከሚደርስበት አደጋ ለመከላከል በስራ ላይ እያለ ብቻ የሚጠቀምበት ነው፡፡ 
                    3. ፋብሪካው ዓርማውን በጉልህ አትሞበት ሚያቀርበውን የስራ ልብስና የአደጋ መከላከያ ሰራተኛው ላይ የሚሆንበት ወቅት መጠቀና ግዴታ አለበት፡፡ ስራ ልብስና አደጋ መከላከያን የማይጠቅም ሰራተኛ አሰሪው ይ….. የስራ ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ 
                    4. ሰራተኛው ባልታወቀ ምክንያት በአንድ ወር ውስጥ ላሉት ስራ ቀናት በስራ ገበታው ላይ የማይገኝ ከሆነ ሳሙና አይሰጠውም፡፡ 
                    5. የፋብሪካውንየፋይናንስ አቅም ግምት ውስት … ፋብሪካው አስፈላጊው በሆኑ ቦታዎች ስራ ልብስና የአደጋ መከላከያ ማስቀመጫ ፍጥነት ይሰራል፡፡ 
                    6. ጋ መከላኬና ስራ ሪ… የሚሰጡት ለሚመለከተውና ከስራው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ላለው ሰራተኛ ብቻ ነው፡፡ 
                    7. ፋብሪካው የሰራተኞች ስራ ልብስ መቀየሪ የሴቶች የወንዶች በተለያዩ ቦታዎች ማዘጋጀት አለበት፡፡ 



                      ምዕራፍ አስራ ሁለት 

                      አንቀጽ 49 

                      በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ 

                      1. ከስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ማለት ማንኛም ሰራተኛ ስራን በማከናወን ላይ ሆኖ በአካሉ ወይም በአካሉ ማንኛውም የተፈጥሮ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት ሚደርስ ጉዳት ማለት ነው፤፤ በአዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 93 መሰረት የሚከተሉት አንድስራላይ አደጋ ያ…..፡፡ 

                      ሀ. ሰራተኛው ከስራ ቦታው ወይም ከስራ ሰዓት ውች ቢሆንም የፋብሪካውን ትእዛዝ ላይ ይውል በነበረበት ጊዜ የደረሰበት ጉዳት፣ 

                      ለ. ሰራተኛው ከስራው ጋር በተያዘ ሁኔታ ከስራው በፊት ወይም በኋላ ወይም ስራው ለጊዜው ተቀርጦ በነበረበት ጊዜ በስራው ቦታ ወይም በፋብሪካው ግቢ ውስጥ ደረሰበት ማንናውም ጉዳት፡፡ 

                      ሐ. ሰራተናውወደ ስራ ቦታው ዌም ከስራው ቦታ ወደ መኖሪያ ቤቱ በተሌዩ ሁኔ ማለትም በእግር ወይም ፋብሪካ ለሰራተኞቹ አገልግሎት እንዲሰጥ በመደበው መጓጓዣ አገልግሎት ወይም ፋብሪካው …. ተግባር በተከራው በግልጸ በመደበው ተሸከርካሪ ወይም በቤት መኪና ወይም በህዝብ የ… አገልግሎት ሲጓዝ ላይ በነበረበት ጊዜ ደረሰበት ማንኛውም ጉዳት 

                      መ. ሰራተኛው ስራን በ….. ላይ ባለበት ጊዜ በፋብሪካው ወይም በሶስተና ወገን ምክንት ያደረሰበት ጉዳት 

                      አንቀጽ 50 

                      የስራ ላይ አደጋ የህክምና አገልግሎቶች አይነቶች 

                      ለሰራተኛ በስራ ላይ ጉዳት በደረሰበት ፋብሪካው የሚከተሉት ያደርጋል 

                      ሀ. የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ወዲያው መስጠት

                      ለ. ጉዳት ደረሰበት ሰራተኛ ከክሊኒክ ጤና ጣቢና በሆስፒታል ማሳከም 

                      ሐ. በሀገር ውስጥ የጠቅላላና ልዩ ህክምና እነዲሁም የቀዶ ህክምና ውጪ መከፈል 

                      መ. የሆስፒታል አገልግሎትና መድሃኒትውቺ መክፈል 

                      ሠ. የማንኛም አስፈላጊ ሰው ሰራሽና ወይም ተጨማሪ አካሎችና የአጥንት ጥገና ወጭ መክፈል ሰራተኛው ለደረሰበት ጉዳት የሚደረግነት የህክምና አገልግሎ የሚቋረጠው ከህክምናካርድ በሚሰጠው ውሳኔ ነው፡፡ 

                       አንቀጽ 51

                      የስራ ላይ አደጋ ክፈያዎች 

                      ማንኛውም በሰድራ ላይ ሚመጣ ጉዳት ማ… ሰራተኛ 

                      1. ……. 


                      አንቀጽ 52 

                      ኃላፊነት 

                      1. ሰራተኛው በስራ ላይ ……. 

                      አንቀጽ 53 

                      የአካል ጉዳት መጠን 

                      1. የአካል ጉዳት የመስራት ችሎታ መቀነስ ወይ ማጣትን በሚስከትል ሁኔታ በስራ ላይ የሚያር…. ጉዳተኛ የሚያመለከት ነው፡፡ 
                      2. ለስራ ላይ የደረሰ የአካል ጉዳት ሚከተሉትን ይዛል

                      ሀ. ጊዜያዊ አካል ጉዳት ማለት ሰራተኛ ስራውን … ጊዜ በከፊል ወይም ለሙሉ ለማከናወን አን… የሚያየዝ ጉዳት የአካል ጉዳት ነው፡፡ 

                      ለ. … የአካል ጉዳት ማለት ጉዳት የደረሰበትን ሰራተኛ የመሰራት ችታ ሚቀነስ የማይደንበስራ ላይ የሚደርስጉዳት ነው፡፡ 

                      ሐ. ከባድ አካል ወይም የመልክ መበላሸት የስከፈለ ጉዳት የመስራት ችሎታ ማጣት …… 

                      አንቀጽ 54

                      የአካል ጉዳት መጠን አወሳሰን 

                      1. የአካል ጉት መጠን የሚወሰነው ስልጣን ባለው ህክምና ቦርድ ነው ቦርዱም በተቻለ መጠን በሰራተኛው ላይ ጉዳት ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በአስ ሁለት ወራት ውስጥ የጉቱን መጠን መወሰን ይኖርበታል፡፡
                      2. ትክክል ያልሆነ ምርመራ ተደርጎለት እንደሆኑ የሰራተኛው ሁኔታ የተሳሳ ወይም የተሻሻለ እነደሆነ አግባብ … አነሳሽነት ወይም ጉዳዩ የሚመለከተው ሰራተኛ ወይም ፋብሪካው ወይም እንደሆነ በቦርዱ ያመራመራል ይታያል፡፡ 
                      3. የአካል ጉዳት መጠን ደረጃ አንድ በታበት ጊዜ የተገኘ ወጤት የሚፈቅደው ሆኖ ሊገኝ ሰራተኛው አንድ ችግት ሁኔታ ጉዳት ማግኘት መብት ሊ… …. ይችላል፡፡ 
                      4. በስራ ላይ የሚያ፣…. ጉዳት የደረሰበት ሰራተና እንደገና በስራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ደረሰበት እንደሆነ የአካል ጉዳቱ መጠነ ደረጃ ከሰራተኛው አካል ሁኔዎች አንጻር እንዲሆን ይወሰናል፡፡ 

                      አንቀጽ 55 

                      ስለጥገሞች ክፍያ 

                      ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ምክንያት በደረሰበት….. … ሰራተኛ ህጉመሰረ …… ካሳ  ያገኛል፡፡ 


                       አንቀጽ 56 

                      ማስረጃ 

                      5.6.1. በስራ  ምክንት የአካል ጉዳት ክፍያ የሚጠይቅ ሰራተኛ የሚከተሉን አሟልቶ ማቅረብ አለበት፣ 

                      ሀ. ስልጣን ካለው የህክምና ቦርድ የተሰጠ ሰርተፍኬት፣ 

                      ለ. ስለ አደጋው ሁኔ የሚገልጸ አግባብ ካለው መስሪያ ቤት የተሰጠ ሪፖረት 

                      ሐ. የፍ/ቤት ማስረጃ፣ ለህጋዊ ወራሾች 

                      መ. ሌሎች ተጨማሪ ተፈላጊ ማስረጃዎች፣ 

                      ተ.ቁ 

                      የጥፋቱ አይነት 

                      የቅጣቱ አይነት 


                      አስፈቅዶ ከስራ የቀረ 

                      የቀረበት ቀን የደመወዝ ቅጣት 


                      ሳያስፈቅድ 1 ቀን ከስራ የቀረ 

                      የቀረበት ቀን የደመወዝ ቅጣት እና የግማሽ ቀን የደመወዝ ቅጣት 


                      ሳያስፈቅድ 2 ቀን በተከታታይ ቀረ 

                      የቀረበት ቀን የደመወዝ ቅጣት እና የ2 ቀን የደመወዝ ቅጣት


                      ሳያስፈቅድ 3 ቀን በተከታታይ ቀረ

                      የቀረበት ቀን የደመወዝ ቅጣት እና የ3 ቀን የደመወዝ ቅጣት


                      ሳያስፈቅድ 4 ቀን በተከታታይ ቀረ

                      የቀረበት ቀን የደመወዝ ቅጣት እና የ4 ቀን የደመወዝ ቅጣት


                      ሳያስፈቅድ 5 ቀን በተከታታይ ቀረ

                      ስንብት


                      በስራ ሰዓት ስራውን ትቶ ተኝቶ የተገኘ 

                      የ1 ቀን የደመወዝ ቅጣት እና የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ 


                      በስራ ሰዓት ስራ ከመስራት ይልቅ ለሌላ ድርጅት ወይም ግለሰብ ስራ ሲሰራ የተገኘ

                      የ2 ቀን የደመወዝ ቅጣት እና የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ


                      የድርጅቱንም ሆነ የሰራተኛማህበሩን ስም የሚያጎድፍ የስም ማፋት ስራ ሲሰራ የገተኘ በመረጃ ሲረጋገጥ 

                      ስንብት


                      የድርጅቱን ንብረት የሆነውን ተሽከርካሪ ለሌላ ግለሰብ አሳልፎ የሰጠ ወይ ለግል ጥቅም እንዲውል ያደረገ 

                      ስንብት


                      የድርጅቱን ንብረት ወይም ምርት ፈቃድ በሚሰጠው አካል ወቺ ያለፈቃድ ይዞ ሲወጣ የተገኘ

                      ስንብት


                      ለተደጋጋሚ ጊዜ በመግቢያ ሰዳት ከ30 ደቂቃ በላይ ያረፈደ /ከሰርቪስ መዘግየት ምክንያት የሚፈጠር ችግርን አይመለከትም 

                      1ኛ የቃል ማስጠንቀቂያና ያረፈደበት ደቂቃ ከደሞዝ መቁረጥ 



                      በተደጋጋሚ ጊዜ በመውጫ ሰዓት ከ30 ደቂቃ ቀድሞ የወጣ 

                      1ኛ የቃል ማስጠንቀቂና ያረፈደበት ደቂቃ መቁረጥ 

                      2ኛ የጽፍ ማስጠንቀቂያና የአንድ ቀን የደሞዝ ቅጣት 

                      3ኛ ሁለተኛ የጽኁፍ ማስጠንቀቂያና የአራት ቀን የደሞዝ ቅጣት 

                      4ኛ የመጨረሻ የጽኁፍ ማስጠንቀቂያና የአራት ቀን የደሞዝ ቅጣት 

                      5ኛ ስንብት


                      በድርጅቱም ሆነ በማህበሩ በኩል የሚለጠፍ ማስታወቂያ ያለፈቃድ የገነጠለ 

                      1ኛ የመጨረሸ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

                      2ኛ ስንብት


                      አልኮል አደንዛዥ እጽ ይዞ ወደ ፋብሪካ ግቢየገባ 

                      ስንብት 


                      ድምጽ ያለው ወይ ድምጸ አልባ የጦር መሳሪያ ይዞ ወደ ፋብሪካ ግቢ የገባ 

                      ስንብት 


                      ድርጅቱ ባወጣው የግቢ ውስጥ የተሸከርካሪ የፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረክር የተገኘ /ጉዳት የደረሰበትን ሰራተኛ ነፍስ ለማዳን የሚደረግ ፍጥነትን አይመለከትም 

                      1ኛ የጸኁፍ ማስጠንቀቂያ 

                      2ኛ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂ 

                      3ኛ ስንብት 


                      ድርጅቱ ለሙያ ደህንነት safety tools /መጠቀሚያ እንዲሆን የተሰጠ እቃ/ ቁስ/ ሳይጠቀም ከስራ ላይ የተገኘ 

                      1ኛ የጸኁፍ ማስጠንቀቂያ 

                      2ኛ ላልተጠቀመበት ቀን ከስራ ማገድ ከደሞዝ ጨምሮ 

                      3ኛ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂና ላልተጠቀመበት ቀን የደሞዝ ቅጣት 

                      4ኛ ስንብት 


                      የቅርብ አለቃውን ወይም የስራ ባልደረባውን የማስፈራራት ወይም ዛቻ ያደረሰ 

                      ስንብት 


                      ከስራ ሲወጡ መብራትና ውሃን በአግባቡ አጥፍተውና ዘግተው ያልወጡ ሰራተኞች 

                      1ኛ የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ 

                      2ኛ ስንብት 


                      ሆን ብሎ የሚሰራበትን ማሽን 

                      ስንብት


                      ከህግ ውቺ አድማ ማድረግ ወይ ማነሳሳት ስራ ማቆምና ምርትን ማቀዝቀዝ የመሳሰሉት 

                      ስንብት


                      ከስራ በመቅረት የኮምፒውተር ካርድን አሳልፎ በሌላ ሰራተኛ በመስጠት ቼኪንግ checking  ማሽኑ ላይ የተነካለት ወይ ለሌላ ያስነካ 

                      ስንብት


                      መረጃ መሰረዝ መደለዝ መደበቅ እና ማበላሸት 

                      ስንብት


                      በሰራ ቦታ አምባጓሮ መፍጠር ለጠብ አጫሪነት ተጠያቂ መሆን 

                      ስንብት


                      በስራ ቦታ መደባደብ 

                      ስንብት


                      ፍተሸ ለመፈተሽ ሲጠይ ለመፈተሸ ፈቃደኛ ያልሆነ 

                      1ኛ የ1 ቀን የደሞዝ ቅጣት እና የመጀመሪ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

                      2ኛ የመጨረሻ የጽኁፍ ማስጠንቀቂያና የ1 ቀን ደሞዝ ቅጣት 

                      3ኛ ስንብት 


                      በተከለከለ ቦታ ሲጋራ ሲያጨስ የገተኘ

                      1ኛ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

                      2ኛ ስንብት 


                      በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ወሲባዊ ትንኮሳ የፈጸመ 

                      1ኛ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

                      2ኛ ስንብት


                      የህክምና ማስረጃን አጭበርብሮ ለድርጅቱ ያቀረበ

                      ስንብት


                      በሐሰት የምስክርነት ቃል የሰጠ ወይም እንዲሰጥ ያደረገ 

                      ስንብት


                      ሰራተኚችን በዘር፣ በሃይማኖት በብሔር የመከፋፈል ስራ ሲሰራ በማስረጃ የተረጋገጠ 

                      ስንብት 


                      የቅጣት እርማጃ

                      ከ12 ወር ውስጥ ከማህደር የሚሰረዝ 

                      • በድርጅቱንም ሆነ በሰራተኛ ማህበሩን በኩል የሚለጠፍ ማስታወቂያ ያለፈቃድ ይሰጣለ 
                      • የኮምፒወውተር ካርድ ያጭበረበረ 
                      • በስራ ሰዓት ስራውን ትቶ ተኝቶ የተገኘ 
                      • በስራ ሰዓት የድርጅቱን ስራ ከመስራት ይልቅ ለሌላ ድርጅት ወይ ግለሰብ ስራ ሲሰራ የተገኘ ከመግቢያ ሰዓት ያረፈደ 
                      • ከስራ መውጫ ሰዓት በፊት ቀድ የወጣ 
                      • ድርጅቱ ለሙያ ደህንነት መጠቀሚያ እንዲሆን የተሰጠውን አልባሳት ሳይጠቀም የተገኘ 
                      • ከስራ ሲወጡ መብራት ውሃን በአግባቡ አጥፍትውና ዘግተው ይለወጡ 
                      • ለመፈተሽ ያልሆነ 
                      • የተከለከለ ቦታ ሲጋራ ያጨሰ 
                      • ድርጅቱ ባውጣው የግቡ ውስጥ የተሽከርካሪ ፍጥነት በላይ ሲያሽከረክር የተገኘ 
                      • የቅርብ አለቃው ላይ ዌ የስራ ባልደረባው ላይ ባቻ ይደረስ 

                      የስነ ስርኣት እርምጃ አወሳሰድና የቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓት 

                      1. የቅጣት እርምጃዎችና የአቀጣጥ ስነ ስርዓት 

                      ሀ. አንድ ሰራተኛ ጥፋት መፈጸሙን የሰስራ ሃላፊም ሆነ ሰራተኛ ሲያመለክት ወይም ሪፖርት ሲያደርግ ፋብሪካው ትክክለኛነቱን በማስረጃ በማረጋገጥ በዚህ አንቀጽ በተ.ቁ 21 መሰረት ተፈጻሚነት ያለውን የስነ ስርዓት እርምጃ ይወስዳል፡፡ 

                      ለ. ሰራተኛ በዚህ የህብረት ስምምነት ያልተጠቀሰ ጥፋት ፈጽሞ ቢገኝ ፋብሪካው በስራ ደነብ ወይም አሰሪና ሰራተኛ ህገ መሰረት የስነ ስርዓት እርምጃ ያወሰዳል፡፡ 

                      ሐ. ሰራተኛው በስነ- ስርዓት እርምጃ አወሳሰድ ሰንጠረዥ ውስጥ ከሰፈሩት ጥፋቶች መካከል አንዱን ሲፈጽም ለዚያ ጥፋት የሚገባውን ቅጣት ከተሰጠው በኋላ ያንኑ ጠፋት ደግሞ ቢገኝ የሚቀጥለው የቅጣት እርምጃ ይወስድበታል፤፤ 

                      መ. ሰራተኛው ጥፋት ፈጽሞ ቢገኝ የስነ ስርዓት እርምጃ እንዲወስድበት ለአስተዳደር መምሪያ ተያቱ የሚቀርበው ሰራተኛው በሚገኝበት የመምሪያ ሃላፊ ወይም እርሱ በሚወከለው ሃላፊ ይሆናል፡፡ 

                      መ. ሰራተኛ ወጥፍት ፈጽሞ ቢገኝ የስነ- ስርዓት እርምጃ እንዲወለድበት ለአስተዳደር መምሪያ ተያቱ የሚቀርበው ሰራተኛው በሚገኝበት የመምሪያ ሃላፊ ወይም እርሱ ከሚወከለው ሃላፊ ይሆናል፡፡ 

                      1. የቅጣት እርምጃ ስርዓት 

                      ያለማስጠንቀቂያ ከስራ መሰናበት 

                      ሀ. የስራ መልያሉማስጠንቅ ማቋረጥ የሚቻለው በሚከተሉት ምክንያት ነው፡፡ 

                      1. ሰራተኛው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ አስየተሰጠው ከ6 ጊዜ በላይ የስራ ሰዓት አለማክበር 
                      2. በመደዳው ለአምስት የሰራ ቀናት ወይም በአንድ ወር በጠቅላላው ለአሰር ቀናት፡፡ በአንድ አመት ውስጥ በጠቅላላው ለሰላሳ ቀናት ያለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረት 
                      3. በስራው ላይ ሰነድ ወይም መረጃ መደለዝ፣ መሰረዝ፣ መቀየር፣ ማጥፋት፣ መደበቅ እና ሌሎቸቭም የሚታለ…. የማጭበርበር ተግባር መፈጸም 
                      4. ማንኛውም የፋብሪካውን ንብረት ወይም ገንዘብ አላግባብ መጠቀሙ 
                      5. ሰራተኛው ስራውን በመስራት ችሎታ እያለው የስራ ውጤቱ በህብረት ስምምነት ወይም በስራ ደንቡ ከተ… የምርት ጥራት መጠን በታች ሲሆን 
                      6. በስራው ቦታ አምባጓሮ ወይም ጠብ አጫሪ ሆኖ መገኘት 
                      7. በፋብሪካው ንብረት ወይ ከፋብሪካው ጋር ግንኙነት ባለው ማንኛውም የሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ 
                      8. በስራ ላይ ህይወትንና ንብረትን አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት መፈጸሙ በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 
                      9. ያለፋብሪካው ፈቃድ ከሰራ ቦታ ንብረት ለመውሰድ መሞከር፣ 
                      10. በስራ ላይ ሰክሮ መገኘት 
                      11. የጤና ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን 
                      12. ከሰላላ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የአስራት ፍርድ ተወስኖበት ከስራ ሲቀር 
                      13. የስራ ተቆጣጣ ሆኖ ስራውንና ሰራተኛውንና ባለመቆጣጠሩ ወይም ቸልተኝነት በማሳየቱ በፋብሪካው ስራ ላይ ጉዳት ሊደርስ፡፡ 
                      14. …… ሰው ማውጣት መስጠት ወይ ማስተላለፍ 
                      15. ከፋብሪካው ቋሚ ስራ ወይም የዘለቄታ ጥቅም ላይ ተወዳዳሪ የሆነ ወየም የሚጋጭ ስራ የሰራ 
                      16. ማንኛውም የድርጅቱን ንብረት ያብቆ ሰርቶ ለማውጣት የሞከረ 
                      17. በማስታወቂያ ሰሌዳላይ የተለጠፈን ማስታወቀዊያ ያለ ፈቃድ የገነጠለ የቀደደ፣ 
                      18. በፋብሪካው የስራ ሰዓት ውስጥ በማንኛም ጊዜ የግል ትቅም የሚያሰገኝ የግል ስራውን ሲሰራ የተገኘ፣ ወየም የፋብሪካው ያልሆነውን ማንኛውም እቃ የጠገነ ያደሰ ወይ የሰራ 
                      19. የጥበቃና የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኛ በስራው ላይ እያለ ተኝቶ የተገኘና ወይም ያለምክንያት ስራ ቦታውን ትቶ የሄደ 

                      በማስጠንቀቂያ ከስራ ማሰናበት 

                      ሀ. የስራ ውል በማስጠንቀቂያ ማቋረጥ የሚቻለው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡ 

                      ሀ. ሰራተኛው የተመደበበትን ስራ ለማከናወን ችሎታው ቀንሶ ሲገኝ የስራ ችሎታን ለማሻሻል ዌ ፋብሪካው ያዘገጀውን የትምህረት እድል ባለመቀበል ምክንያት ሲሰራ የቆየውን ስራ ችሎ የሌለው ሆኖ ሲገኝ ወየም ትምህርት ከተሰጠው በኋላ አስፈላጊውን አዲስ የስራ ችሎታ ለመቅሰም የማይችል ሲሆን 

                      ለ. ሰራተኛው ወደ ሌላ ስራ ማዘወር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ ወየም በመዋቅር ለውጥ ምክንያት ሰራተኛ መቀነስ የሚያስከትል ሁኔ ሲፈጠር 

                      ሐ. ሰራተኛ ተዛውሮ ለመስራት ፈቃደኛ ሳይን ሲቀር 

                      መ. ሰራተኛው የያዘውን የስራ መደብ ሲሰርዝና ወደ ሌላ ስራ ማዛር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ ወይ በመዋቅር ለውጥ ምክንያት የሰራተኛ መቀነስ የሚያስችል ሁኔታ ሰፈጠር 

                      ሰራተኛው የተሰማራበት ስራ በክፍልም ሆነ በሙሉ መጠናቀቁንና ለዘላቄታ የሰራተኛ ቅነሳ የሚያስከትል ሁኔ ቢፈጠር 

                      ረ. የፋብሪካው የስረ እንቅስቃሴ በመተዘቀቡ ትርፍ ሲቃነስ በሚደረግ የሰራተኛ ቅነሳ 

                      ሰ. የፋብሪካውን ምርታማነት ለማወሳደግ፣ የአሰራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይ በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሰራተኛ ቅነሳ 



                      ለ. ከስራ ማሳገድ 

                      ሀ. በፋብሪካው ላይ አደጋ በሚደርስበት ወየም በደረሰበት ጥፋት ተነሳ ወይበ እምነት ማጉደል ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ እንዲሁም ከፋብሪካው ጋር በተገናኘ ሁኔታ በወንጀል ጥፋት በህግ ተክሶ የተመሰከረበት ሰራተኛ ሁኔታ በወንጀል ጥፋት በህግ ተከሶ የተመሰከረበት ሰራተኛ ሁኔው ተጣርቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ከስራ ሊታገድ ይችላል፡፡ ጥፋተኛነቱ ከተረጋገጠ ያጠፋው ስህተት ተዘርዝሮ ውሳኔ ይሰጠዋል፡፡ 

                      ለ. የእገዳ ስነ ስርዓት በማንኛውም ጊዜ ከአንድ ወር በላይ ሊዘገይ አይችልም፡፡ 

                      ሐ. ሰራተኛው ከስራ ታግዶ አንዲቆይ ሲያስፈፈልግ ምክንያት ተዘርዝሮ ያዳፍለታል፡፡ 

                      መ. የማገጃውን ትእዛዝ ለሰራተኛው ለመስጠት የማይቻልበት ሁኔታ ካለ በፋብሪካው የማስታወቂያ ሰሌዳ ላ ለአምስት የስራ ቀናት ይለጠፋል፡፡ እገዳውም የሚጸናው የማገጃ ደብዳቤው በደረሰኝ ለሰራተኛው ከተተሰጠበት ወይም በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተለጠፈበት እለት ማግስት ጀምሮ ይሆናል፡፡ 

                      ሠ. የታገደ ሰራተኛ በእገዳው ወቅት ስራን፣ ለስራ የሚያስፈልጉ ቁሳቁኦች ሰነዶችና የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ 

                      ረ. አንድ ሰራተኛ ሲታገድ ከስራ ታግዶ ለሚቆይበት ጊዜ ደመወዙ መያዝ አለበት፡፡ 

                      የታገደ ሰራተኛ ነጻ ሆኖ ሲገኝ የታገደባቸው ቀናት ደመወዙ ታስቦ ወደ ስራው እንዲመለስ ያደርጋል፡፡ ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ ግን እንደጥፋቱ ደረጃ የአስተዳደር እርምጃ ይወስድበታል፡፡ 

                      ሸ. በተከሰሰበት ወንጀል ወየም በዲሲፒሊን ክስ በሚሰጠው ውሳኔ ሰራተኛው ጥፋተኛ ሆኖ ካልተገኘ ከስራ ታግዶ … ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ በሙሉ ያለወለድ ይከፈለዋል፡፡ 

                      2 የሰራተኛ ቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓት 

                      ሀ. በዚህ ስምምነት ቅሬታ የሚለው ቃል ከሰራተኞች የስራ ውል፣ የሰራ ሁኔዎች የሚነሳውን ከህብረት ስምምነቱ አተረጓጎም ወይም በአፈጻም ጊዜ የሚከ…. ጥያቄ ያጠቃልላል፡፡ 

                      ለ. ሰራተኛው ቅሬታ ሲኖረው አቤቱታውን ለቅርብ ሃላፊው ያቀርባል፡፡ ቅሬታ የቀረበለት ሃላፊም ጉዳዩን መርምሮ በአምስት ስራ ቀናት ውስጥ ውጤት ያለው መልስ ካልተሰጠው ሰራተኛው በሚሰራበት መምሪያ ኃላፊ የቀርባለ፡፡ 

                      ሐ. የመምሪያው ሃለፊ የሚቀርቡበትን ቅሬታ አይቶ ቅሬታውን በደረሰው አምስት ቀን ውስጥ መልስ መስጠት አለበት፡፡ 

                      መ. ሰራተኛ በመልሱ ላይ ቅሬታ ያለው ከሆነ ለአስተዳደሩ ቀርቦ በ5 ቀናት ውስጥ መልስ ማግኘት አለበት 

                      ሠ. ከላይ ከፊደል /ለ.መ/ በተጠቀሱት ቅሬታ ያለው ሰራተኛ ጉዳዩን ለዋና ስራ አስኪያጅ አቅርቦ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጠዋል፡፡ 

                      አንቀጽ 57

                      አተረጓጎም

                      በህብረት ስምምነቱ ውስጥ ባሉት ድንጋጌዎች ፋብሪካውና ማህበሩ ባይስማሙ ከሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይ ሌላ አግባብ ያል ባለስልጣን ምክርና አስተያየት በመጠየቅ ይፈልጋል፡፡ 

                      አንቀጽ 528 

                      ማሻሻያ 

                      ፋብሪካውና ማህበሩ በመስማማት ዘመኑ ሳያልቅ ህብረት ስምምነቱ እንዲሻሻል ወይ ኢንዲታይ ማድረግ ይችላሉ፡፡ እንደገና መታየትና መሻሻል አለበት የሚያሰኝ አንቀጽ ሲያጋጥም ከሁለት አንዱ እንዲሻሻልበት ቢጠይቅ ሌላኛው በቅንነት ቀርቦ መነጋገር አለበተ፡፡ 





                      ምዕራፍ አስራ አምስት 

                      አንቀጽ 59 

                      በስራ ላይ ማዋል 

                      ይህ ህብረት ስምምነት በአዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 131 መሰረት ከተመዘገቡ ቀን ጀምሮ ለሶስት አመት የጸና ይሆናል፡፡ 

                      የሰራተኛ ማህበሩ ተወካይ  የድርጅቱ ተወካይ 

                      ስም  ስም 

                      ፊርማ       ፊርማ 



                      Ayka Addis Textile and Inverstment Group P.L.C -

                      Start date: → Not specified
                      End date: → Not specified
                      Name industry: → Manufacturing
                      Name industry: → Manufacture of textiles, Manufacture of wearing apparel
                      Public/private sector: → In the private sector
                      Concluded by:
                      Name company: →  Ayka Addis Textile and Inverstment Group P.L.C
                      Names trade unions: →  የአይካ አዲስ ቴክስታይል ኤንድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃላ.የተ.ማህበር

                      TRAINING

                      Training programmes: → Yes
                      Apprenticeships: → No
                      Employer contributes to training fund for employees: → No

                      SICKNESS AND DISABILITY

                      Maximum for sickness pay (for 6 months): → Not specified %
                      Provisions regarding return to work after long-term illness, e.g. cancer treatment: → No
                      Paid menstruation leave: → No
                      Pay in case of disability due to work accident: → Yes

                      HEALTH AND SAFETY AND MEDICAL ASSISTANCE

                      Medical assistance agreed: → Yes
                      Medical assistance for relatives agreed: → No
                      Contribution to health insurance agreed: → Yes
                      Health insurance for relatives agreed: → No
                      Health and safety policy agreed: → Yes
                      Health and safety training agreed: → No
                      Protective clothing provided: → Yes
                      Regular or yearly medical checkup or visits provided by the employer: → No
                      Monitoring of musculoskeletal solicitation of workstations, professional risks and/or relationship between work and health: → 
                      Funeral assistance: → Yes
                      Minimum company contribution to funeral/burial expenses: → ETB 10000.0

                      WORK AND FAMILY ARRANGEMENTS

                      Maternity paid leave: → 13 weeks
                      Maternity paid leave restricted to 100 % of basic wage
                      Job security after maternity leave: → No
                      Prohibition of discrimination related to maternity: → No
                      Prohibition to oblige pregnant or breastfeeding workers to perform dangerous or unhealthy work: → 
                      Workplace risk assessment on the safety and health of pregnant or nursing women: → 
                      Availability of alternatives to dangerous or unhealthy work for pregnant or breastfeeding workers: → 
                      Time off for prenatal medical examinations: → 
                      Prohibition of screening for pregnancy before regularising non-standard workers: → 
                      Prohibition of screening for pregnancy before promotion: → 
                      Facilities for nursing mothers: → No
                      Employer-provided childcare facilities: → No
                      Employer-subsidized childcare facilities: → No
                      Monetary tuition/subsidy for children's education: → No
                      Leave duration in days in case of death of a relative: → Insufficient data days

                      GENDER EQUALITY ISSUES

                      Equal pay for work of equal value: → No
                      Discrimination at work clauses: → Yes
                      Equal opportunities for promotion for women: → No
                      Equal opportunities for training and retraining for women: → No
                      Gender equality trade union officer at the workplace: → No
                      Clauses on sexual harassment at work: → Yes
                      Clauses on violence at work: → Yes
                      Special leave for workers subjected to domestic or intimate partner violence: → No
                      Support for women workers with disabilities: → No
                      Gender equality monitoring: → No

                      EMPLOYMENT CONTRACTS

                      Part-time workers excluded from any provision: → No
                      Provisions about temporary workers: → No
                      Apprentices excluded from any provision: → No
                      Minijobs/student jobs excluded from any provision: → No

                      WORKING HOURS, SCHEDULES AND HOLIDAYS

                      Working hours per day: → 8.0
                      Working hours per week: → 48.0
                      Working days per week: → 6.0
                      Paid annual leave: →  days
                      Paid annual leave: →  weeks
                      Rest period of at least one day per week agreed: → Yes
                      Maximum number of Sundays / bank holidays that can be worked in a year: → 
                      Provisions on flexible work arrangements: → No

                      WAGES

                      Wages determined by means of pay scales: → No
                      Adjustment for rising costs of living: → 

                      Premium for overtime work

                      Premium for Sunday work

                      Premium for Sunday work: → 100 %

                      Allowance for commuting work

                      Meal vouchers

                      Meal allowances provided: → No
                      Free legal assistance: → No
                      Loading...