Collective Agreements Database


የቤኤም  ኢትዮጵያ  ልብስ ስፌት

ጨርቃ ጨርቅ  አክሲዩን ማህረ


መሰረታዊ ሠራተኞች

ማህበር








 የመሰረታዊ  ሰራተኛ   ማህበር  መተዳደሪያ ደንብ 

  1. መግቢያ 
  • የቢ ኤም  ኢትዮጵያ ልብስ  ስፌት  ጨርቃ ጨርቅ አ/ማ መሰረታዊ   ሰራተኛ ጥምረት  ማህበር በጋራ  በመደራጀት  በሕብረት  ስምምነትና  በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጃ 377/96  መሰረት መብታቸው ጥቅማቸው ለማስከበር የተቋቋመ የሰራተኛ ማህበር ነው፡፡
  1. የማህበሩ ስም 
  •  ይህ ማህበር  የቢኤም  ኢትዮጵያ  ልብስ ስፌትና  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር  ጥምረት መሰረታዊ ሠራተኛ  ማህበር ማለት ነው፡፡
  1.   ትርጓሜ  
  1.  ማህበር  ማለት የቢ ኤም  ኢትዮጵያ  ልብስ ስፌት እና ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን  ጥምረት መሰረታዊ ማህበር  ማት ነው 
  2. ድርጅት ማለት  የቢ ኤም ኢትዮጵያ  ልብስ ስፌትና  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር  ድርጅት ማለት ነው፡፡
  3. ምክር ቤት (ም/ቤት) ማለት  በድርጅት  ቅርንጫፍ ወይም ንዑስ ክፍል  ወይም የተለያዩ  የሥራ ክፍል  የሚያገኙትን  ሰራኞ በመወከል የሚቋቋም  ወይም ጠቅላላ  ሰራኞን የሚወክል አካል ነው፡፡ 
  4. ስራ አስፈጻሚ ማለት  በማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ወይም  በማህበሩ ም/ቤት  ተመርቶ የማህበሩን  የእለት ተእለት ስራ  ሚየሚያከናውን  ወይም የሚያስፈጽም  ስራ አስፈጻሚ  ማለት ነው፡፡
  5.  ኦዲት ኮሚቴ (ቁጥጥር  ኮሚቴ  ማለት በጠቅላላ  ጉባኤ  ወይም በምክር ቤት ተመርጦ የማህበሩን ስራ የሚያከናውን የማህበሩ ንብረትና ገንዘብ  የሚቆጣጠር አካል ነው፡፡
  1. የማህበሩ ዓላማ 
  1.  የማህበሩ አባላት መብትና ጥቅም ደህንነት በማክበር  ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ  ፍላጎት  እንዲሟላ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡
  2. የማምረት አቅም  የሥራ በህል  እንዲሻሻል  ጥረት  ያደርጋል፡፡
  3. በድርጅቱና  በሰራተኞቹ  መካከል  የሚፈጠሩ  ችግሮች በሰላማዊና በአዋጅና በህብረት ስምምነት እንዲፈታ ያደርጋል፡፡  
  4. መንግስታዊና  መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ገር በማነጋገር ለሰራተኛ መብትና  ጥቅም እንዲከበር  ያስፈጽማል፡
  1. ማህበሩ የተመሰረተበት ቀን  

ይህ ማህበር ከመጋቢት  30/2005 ዓ.ም ጀምሮ ተመሰረተ 

  1. የማህበሩ  ዓርማና ማህተም 
  1. የማህበሩ ዓርማ በሶስት  ማዕዘን ውስጥ አደይ አበባ ምስል  አለው፡፡
  2. የማህበሩ  ማህተም  ከዚህ በታች የሚታየው ነው፡
  1. የማህበሩ  ተግባርና ኃላፊነት 
  1. በድርጅቱ ውስጥ  ተቀጥረው ያሉትን  በማህበር እንዲደራጁ (ወይም እንዲሰበሰቡ አስፈላጊው ሁሉ ማድረግ)
  2. የአባላት  በማንኛውም  ለማህበር ስራ መወከል 
  3.  የአባላቱን  መብትና  ጥቅም እንዲከበር ማድረግ 
  4. የሥራ አካባቢን ደህንነትና ጤንነት  እንዲጠበቅ በዚህ ረገድ  የወጡ ሕጎች ደንቦች፣ መመሪያዎች በሰራተኛ ዘንድ እንዲታወቁ እንዲረዱ ማድረግ 
  5. የድርጅቱ  የእቅድና የአስተዳደር መመሪያዎች ሲነደፍ የሰራተኛ ተሳትፎ  እንዲጎለብት  ጥረት ማድረግ 
  6. በእድገት በደመወዝ ጭማሪ  በዝውውር በምደባ  በሰራኛ ቅነሳ በዲሲፕሊን በስራ ክርክር  አፈጻጸም  የሠራተኛ  ተሳትፎ ማጠናከር 
  7. በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ  አዋጅ በሌሎች  በተሰጠው መብት መሰረት  የድጅቱን ሰራተረኛ በመወከል ከድርጅቱ  ጋር  የህብረት ስምምነቶችን  መደራደር እና መፈረም፣ ማስመፈጸም 
  8. ሰራተኞ  በስራ አካባቢያቸው  ማህበራዊ አገልግሎችን እንዲሟላላቸው ሁኔታዎችን  ለማመቻቸት ጥረት  ማድረግ 
  9. የሠራተኛ የገንዘብ ቁጠባ እንዲቋቋም  ማድረግ
  10. የብድር የሕብረት ስራ አገልግሎት  ማህበራት እንዲቋቋም  ማድረግ 
  11. ለሰራኛው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት  የሚያወጡ  የልማት ስራ እንዲቋቋም  ጥረት ማድረግ
  12. የሠራተኛው ጤንነቱ የተጠበቀ፣ የአካል ብቃት  እንዲዳብር  ጤናማ አምራች  እንዲሆን በተለያዩ  የስፖት ወድድር እንዲሳተፍ 

አንቀጽ 7.15  ከማህበሩ  አባል በሞት ከዚህ አለም ሲለይ/ስትለይ ለቀብር ማስፈጸሚያ  ማህበሩ 250 ብር ለሟች  ቤተሰብ አስፈርሞ ይሰጣል፡፡

አንቀጽ 9-6  የማህበሩ ጽ/ቤት  የሚወከሉት የሥራ ክፍል ሆኖ ብዛት ከ35  አይበልጥም፡፡

አንቀጽ  10-2  መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር  ሊቀመንበር ምዕላተ ጉባኤው ከ2/3  በላይ ከሆነ  ጉባኤውን ይመራ ሆኖም የማህበሩ የሥልጣ ዘመን  ተጠናቆ  ለምርጫ ጉባኤ ይመራል ሆኖም የማህበሩ የሥልጣን ዘመን ተጠናቆ ለምርጫ ጉባኤ  ሲጠራ  የፌዴሬሽን  አመራር  ይሆናል፡፡

አንቀጽ  19-10  መሰረታዊ  ሰራኛ ማህበሩ  ከአባልነት መዋጮ ከሚያገኘው ገቢ ከአባሉ ብዛትና የወር ገቢ መጠን አንጻር  በየወሩ ለፌዴሬሽኑ  40 ፐርሰንት   ገቢ ያደርጋል፡፡  ሆኖም በየወሩ  ገቢ ማድግ ካልቻለ ለፌዴሬሽኑ  በማሳወቅ  በዐመቱ መጨረሻ ገቢ ያደርጋል፡፡

አንቀጽ  21-5  ከማህበሩ   ኦዲት  ኮሚቴ  ውስጥ በተለያዩ ምክንያት ቢጓደሉ  በምትካቸው  ተክቶ እንዲሰሩ ይደጋል፡፡

አንቀጽ  23-3 አንድ አባል  ከማህበሩ  መዋጮ  ሆነ ማህበሩ  በሌላ በኩል  ከሚያገኘው  ገቢ ሰራተኛው ብድር  እንዲሰጠው (እንዲሰጣት)  ቢጠይቁ  የማህበሩን ገቢ በማይጎዳ  ከአባልነት  መዋጮ ሌላ  የወሰደውን ብድር  ከወር ደመወዙ ተቆርጦ  ተመላሽ  እንዲሆን  ያደርጋል  ብድሩን ሳይመልስ ( ሳትመልስ) ስራ ቢለቁ  ለሚያገኙት  አገልግሎ ካሳ ሆነ  ከሌላ  ክፍያ በአንድ ጊዜ ተቆርጦ  ተመላሽ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ 35-7  የማህበሩ  ስራ አስፈጻሚ  ማህበሩ አባላት ውስጥ የማህበሩን ስራ ለመስራ ቢወከሉ  ከስራ  ሰዓት ውጪ  ሆነ በስራ  ላይ ሆነው ድርጅቱን አስፈቅዶ  ሲንቀሳቀሱ  ለትራንስፖርት  50 ብር ማህበሩ  ይከፍለዋል፡፡

አንቀጽ 36-1  የማህበሩ አመራር የሥራ ዘመን ሲጠናቀቅ እና በተለየ ምክንያት ከአመራሩ ቢጓደል  በምትካቸው በጉባኤ  እንዲመረቱ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ጉባኤውን  ለመጥራ ካልተቻለ በም/ቤቱ  እንዲወከሉ ተደርጎ ለጠቅላላ ጉባኤ በማስታወቂያ ያሳውቃል፡፡  ጠቅላላው ጉባኤው እና  የአባላት  ፊርማ  ተያይዞ ለአዲስ አበባ  ከተማ  አስተዳር ሰራተኛና ማህበረዊ ጉዳይ ቢሮ  ሪፖርት  ይደረጋል ሕጋዊነት እንዲያገኝም ይጠየቃል፡፡

አንቀጽ 36- 2 የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ  ምርጫ ደረግ ምዕላተ ጉባኤ መሞላቱ  ከተረጋገጠ በኋላ አስመራጭ  ኮሚቴ  እንዲወክሉ ተደርጎ ምርጫ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ  36-3  የአስመራጭ ኮሚቴ  በጠቅላላ ጉባኤ  የሚከሉ ሆኖ  የኮሚቴ  ብዛት 3/ሶስት/  ሲሆኑ የሚመረጡትም ብልጫ ይሆናል፡፡

  1. የአባላት መዋጮ  በአግባቡ መሰብሰቡን ማረጋገጥ አዳዲስ  አባላት መዋጮ እንዲከፍሉ ማድረግ 
  2. የአባላት  እስታትስቲካዊ መረጃዎ በአግባቡ መያዝ
  3. ከአባላት  በሞ ከዚህ አለም  ሲለዩ የተወሰነ  አባል በመላ የቀብር ስነስርዓት  እንዲፈጸምና  ለቀብር ስነ ስርዓት  የተወሰነ ገንዘብ መስጠት ይህም ብር 250  ይሆናል፡፡
  4.  በጨ/ጤ/ቆ/ልልበሰ/ማ  ፌዴሬሽን  የተቋቋመ  መረዳጃ  እድር አባላትን በመዋጮ በማዋጣት  ማሳፍና ያለአግባብ ከስራ ታገድ ጉዳይ በፍ/ቤቱ ውሳኔ እስከሚያገኝ  ጊዜ ድረስ  የገንዘብ  ድጋፍ ማድረግ
  5. ድርጅቱ ፋብሪካውን  በማስፋት በሚያደርገው  እንቅስቃሴ ጠቃሚ  መሆኑ ከታወቀ  ድጋፍ ማድረግ
  6. በድርጅቱና  በሰራተኛው  ከሌላ አካል  ጋር የሚያደርገው  የፍ/ቤት  ክርክር ከስራ አስፈጻሚ እና ከስራ አስፈፃሚ ውጪ ባለሙያና  ስራ አስፈጻሚ ከአመነበት  የማበሩ ውክልና ወስዶ ጉዳዩን  የሚስፈጽሙ እንዲወከል ማድረግ 
  7.  የኤች አይ ቪ  ኤድስ ህሙማን  በሰራተኛው  ማህበር አባላት እርዳት እንዲያገኙ ጥረት ማድግና ለእነሱ የገቢ ምንጭ መፈለግ 
  8. የሠራተኛ ገቢ  ለማሳደግ  ድርጅቱ በሚይዘው  ለተወሰነና ላልተወሰነ ለሚሰራው ትርፍ  ሰዓት  ስራ ሰራተኛ  እንዲሳፍ ማድረግ 
  9. በሀገራዊ  ጉዳች  በተፈለገ አቅጣጫ  መጠን  ሰራተኛውን በፍላጎት  እንደ ሁኔታው  እንዲሳተፉ ማድረግ 
  10.   ሌሎች  ተጨማሪ  ለሰራተኛው ጠቃሚ ተግባሮን ማከናወን  
  1. የመሰረታዊ  ሰራተኛ  ማህበር የአመራር አካላት 
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር በአባላት ጠቅላላ ጉባኤ(ሥብሰባ)
  2. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ምክር ቤት 
  3. የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 
  4. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ኦዲት (ቁጥጥር) ኮሚቴ 
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ  (ሥብሰባ)
  1. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ጠቅላላ ስብሰባ (ጉባኤ)  የሚሳተፍበት መሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር በላይ አካል ነው፡፡
  2. ከድርጅቱ  አደረጃጀትና የስራ ጸባይ  የተነሳ ጠቅላላ የማህበሩ  አባላተር ስብሰባ ላይ ሊገኙ የማይችሉ ከሆነ ከጠቅላላ አባላት 2/3/ ሰራተኞ ተመርጠው  የጠቅላላ  ስበሰባ  አባላት ይሆናል፡፡
  3. ስብጥሩም  በጠቅላላ ስብሰባ ይወሰናል፡፡
  4. የማህበሩ  ጠቅላላ ስብሰባ  በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ሆኖም አስቸኳይ  ስብሰባ ለማድረግ  ከተፈለገ በም/ቤት  ውሳኔ ይደረጋል፡፡
  5. የሥራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ በወር  ውስጥ ሁለት ጊዜ ሰ ስብሰባ ያደርጋል፡፡  እንደ አስፈላጊነቱ  አስቸኳይ  ጉዳይ ከገጠመው  አስቸኳይ   ስብሰባ ያደርጋል፡፡
  6. የም/ቤት ስብሰባ  በዓመት ውስጥ 4 ጊዜ ያደርጋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ  አስቸኳይ ጉዳይ  ከገጠመው ስራ አስፈጻሚው ለም/ቤቱ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
  7. የማህበሩ  የሥራ ዘመን  ሲጠናቀቅ አዲስ ኮሚሽን  (ምርጫ አስፈጻሚ  ኮሚቴ) ይሰየማል፡፡
  1. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ጠቅላላ ስብሰባ 
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር መተዳደሪያ ደንብ  ያጸድቃል፣ ያሻሽላል ፣ ይለውጣል፡፡ 
  2. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማመህበር ምክር ቤት  ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና  ኦዲት ኮሚቴ ቁጥጥር  ይወስናል ይመርጣል፣ ያሰናብታል፡፡
  3. የምክር ቤት  የሚቀርበለት  የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበሩን   ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  አባላትን ምርጫን የሥራ ክፍፍል ያጸድቃል፣ ቋሚ የሆኑትን አባትን  ቁጥር ይወስናል፡፡
  4.  የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበሩን እቅድና በጀት  ይመረምራል
  5. ከምክር ቤትና ከኦዲት  ከኮሚቴ  የሚርብለት አባላት ይመርጣል ያጸድቃል
  6. ማባሩን የሚመለከቱትና  ዋና ዋና ጉዳዮች  ላይ ውሳኔ  ይሰጣል፡፡
  7. የሠራተኛ ማህበራት ፌዴሬሽን የሚወክሉ አባለት ይመርጣል ይወስናል፡፡
  8. ማህበሩ በሚፈርስበት ጊዜ  በማህበሩ ንብረት ገንዘብ ሌሎች ላይም ይወስናል ውሳኔ የሚጸናው   ከ2/3/ በላይ ሲገኙ ብቻ ነው፡፡        
  9.  አንቀጽ  10 ተራ ቁ 8 እንደተጠበቀ  ሆኖ ወደ 2ኛ አካል ሲተላለፍ  በሙሉ አባላት  ውሳኔ ሲጸድቅ ነው ይህም የሚሆነው  ማህበሩ ከተቋቋመ በት አላማና ደንብ በሕግ  ሲደገፍና የመጨረሻ  መፍትሔ ለማስቀመጥ በጠቅላላ ጉባኤ  ሲወሰን ብቻ ነው፡፡
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ም/ቤ  ተግባር ኃላፊነት 
  1. የመሰረታዊ  ሰራኛ ማበር ም/ቤት  ወይም ሆርሻ  አስፈላጊነቱ  በጠቅላላ ጉባኤ  ሲታመንበት የሚቋቋም  ይሆናል፡፡
  2. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ም/ቤት ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ  ሆኖ  የመሰረታዊ ሰራኛ ማህበሩን የሚመራ አካል ነው፡፡
  3.   የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ም/ቤት  በየ3 ወር ስብሰባ  ያደርጋል ሆኖም ማህበሩ ስራ  አስፈጻሚ  ኮሚቴ ካመነበት  ወይም ከም/ቤቱ  2/3ኛ ስብሰባውን ከተየቁ አስቸኳይ  ስብሰባ ሊሰጠራ ይችላል፡፡
  4. ከስራ አስፈጻሚና ከኦዲት  ከሚቴ ቦታ ይተከላል ይመረል 
  5. አንቅጸ 11.ቁ 4 እንደተጠበቀ ሆኖ  የተጓደለ ቦታ በመተካት  እንደ አቅማቸው እና እንቅስቃሴ  በመገምገም በሽግሽግ ለመተካት ስራ ወስናል፡፡ 
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ም/ቤት
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ስራ አስፈጻሚ
  2. የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር  ኦዲት ኮሚቴ 
  3. ሌሎች  በመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር የሚመረጡ አባላት ናቸው፡፡
  1.  የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ኦዲት ኮሚቴ 
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ጠቅላላ  ስብሰባ ውሳኔዎችና  መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ 
  2. የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር  እቅድ በጀት በቅርብ መከታተል 
  3. የመሰረታዊ ሰራኛ ማህበር ስራ አስፈታሚ ኮሚቴ  ብዛት ይወስናል ያጸድቃል 
  4. የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር  ም/ቤት  በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት  የዲሲፕሊን  ጉድለት  ከታየባቸው ይመክራ፣ ያግዳል ያባርራል ውሳኔ ያስተላልፋል
  5. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር  ም/ቤት በጎደሉ  በመተዳደሪያ ደንብ  መሰረት  እንዲሞሉ ማድረግ 
  6. ከመሰረታዊ  ሰራተኛ  ማህበር የማቅረብ  ሪፖርቶችን ይመረምራል አስፈላጊ  መመሪያና ውሳኔ ይሰጣል፡፡
  7. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር  ጠቅላላ  ስብሰባ  ያዘጋጃ ሪፖርት  ያቀርባል፡፡
  8.  ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር ሆኖ ችግሮች ለመፍታት  ጥረት ያደርጋል  ተግባራዊ እንዲሆን  ያደርጋል፡፡
  9. ከጠቅላላ  አባላት የሚቀርቡ  ጉዳዮች  ከስራ አስፈጻሚ ጋር ሆኖ እንዲፈቱ  ያደርጋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ  ከድርጅቱ ጋር በመነጋገር  መፍትሔ ይፈልጋል፡፡
  1. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር  ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 
  1. ተጠሪነቱ  ለማህበሩ ም/ቤትና ለጠቅላላ ጉባኤ ሆኖ  ማህበሩን የዕለት ተእለት ስራ ይመራል፡፡
  2. የሥራ አስፈጻሚ  ስራ ከፍፍል ያደርጋል በቋሚነት  የሚሰሩ ቁጥር ይወስናል 
  3. አንቀጽ 14 ተ.ቁ 3 እንዳለ ሆኖ በቋሚነት የሚሰሩ  በምክር ቤትና  በስራ አስፈጻሚ ውሳኔ  ለመስጠት ካልተቻለ  ለጠቅላላ ጉባኤ  ቀርቦ ይወስናል፡፡
  4. የሠራተኛ  አስፈላጊ  እረፍት ማሳለፊያ  ቦታዎችን መዝናኛዎች እንዲዘጋጁ ጥረት  ያደርጋል፡፡ 
  5. ለሰራተኛው  የትራንስፖርት  አገልግሎት  እንዲያገኙ  ከድርጅቱ ጋር  በማነጋገር  መፍትሔ ይሰጣል፡፡
  6. አንቀጽ 14 ተ.ቁ 6 እንዳለ ሆኖ  መሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበሩ  ለጠቅላላ ሰራተኛ ትራሰንፖርት  ለማቅረብ  በራሱ  ጥረት ያደርጋል ይህም ከራሱ ገቢ አንጻር በማየት  
  7. የህብረት ስምምነት  ድርድር ከድርጅቱ  ያደርጋል ከድርድሩ በፊት  ለጠቅላላ  አባላት ረቂቁን  አቅርቦ  ያወያያል ተጨማሪ  አስተያየቶችን ወስዳል፡
  8. የአባላቱ መዋጮ ይሰበሰባል
  9. የማህበሩን  ገንዘብና ንብረት  ያስተዳድራል
  10. የማህበሩ  ገንዘብና  ንብረት እና ሌሎች ዋና ዋና ሰነዶች  ከአባላት ውሳኔ  ውጪ የማስተላለፍ ስልጣን የለውም
  11. የማህበሩ ሰራተኛ  ገንዘብና  ንብረት እና ሌሎች ዋና ዋና  ሰነዶ ከአባላት ውሳኔ  ውጪ የማስተላለፍ ስልጣን የለውም፡፡
  12. የማህበሩ  ሰራተኛ  ማህበር ም/ቤት  ስብሰባዎ አጀንዳ  ያዘጋጃል፡፡
  13. የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር አባላት  የድርጅቱን መመሪያ ደንቦች በሰራተኛው ተሳትፎ  እዲወጡና በቂ የገንዘብ አቅም እንዲኖረው  ውጥረት ማድግ 
  14. የመሰረታዊ  ሰራተኛ እቅድ ለምክር ቤት ይቀርባል ያስወስናል፡፡
  15. የሥራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ  ሪፖርት  አለምክር ቤትና ለጠቅላ  ጉባኤ ያቀርባል፡፡
  16. ከምክር ቤት  የሚሰጡ  ተግባችን ያከናውናል
  17. የመሰረታዊ ሰራተኛ  መህበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  ቁጥር 7 ፣ የኦዲት ኮሚቴ 3 እንዲሆን ያደርጋል
  18. ለማህበራት  ፌዴሬሽን   ሊሰማኮ በሚጡ  ስልጠናዎች ይሳተፋል ሌሎችም እንዲሳተፉ  ያደርጋል፡፡
  19. በመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር አባል ለሆኑ  ለኤች አይ ቪ  ኤድስ ህሙማን የገንዘብና  የቁሳቁስ  እርዳታ  እንዲጊኙ ጥረት ማድግና መወሰን 
  20. ከሌሎች አቻ ማህበራት ጋር ተሞክሮ መለዋወጥ 
  1. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር  ኦዲት ኮሚቴ 
  • የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር  ኦዲት  ኮሚቴ  ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ሆኖ የሚከተሉት  ተግባሮችን ያከናውናል፡፡


  1. የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ  የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ በመከተል  ሰራተኞቻቸውን መከታተል
  2. የማሕበሩ  መዋጮ  በወቅቱ መሰብሰቡን ከተገቢ ቦታ መቀመጡን መከታተልና  መቆጣጠር
  3. የአባላት ንብረትና  ገንዘብ በአግባቡ መመዝቡን መቆጣጠር 
  4. በማህበሩ ስር ያሌት ተቋማት  ስራ በትክክል መካሄዱን መቆጣጠር ንብረቱም  በመተዳደሪያ ደንቡ  መሰረት መቀመጡን መከታተልና መቆጣጠር 
  5. የማህበሩ  የዕቃ ግዢ፣ ሽያጭ  በመተዳሪያ ደንቡ  መሰረት  መከናወኑን መከታል 
  6. የገንዘብ  መተዳሪያ ደንብ በማዘጋጀት በጠቅላላ ጉባኤ ጸድቆ  ተግባር መሆኑን  መከታተል
  7. አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ለጠቅላላ ጉባኤ  ማቅረብ ሌሎች  ተግባር በጠቅላላ ጉባኤ  ውሳኔ መሰረት  መፈጸምና መከታተል
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ሊቀ መንበር  ተግባርና ኃላፊነት 
  1. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር  የማህበሩን  መተዳደሪያ ደንብ በመከተል  የጠቅላላ ስብሰባ ፣ የምክር ቤት  የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  ስብሰባ ይጠራል፡፡
  2. የሥራ አስፈጻሚ  ኮሜቴ የተሰጣቸው የሥራ ድርሻ መወጣታቸውን ይከታተላል ያስተባብራል፡፡
  3. ማህበሩን  በማንኛውም  ጉዳይ ይወክላል 
  4. በማህበሩ  መተዳሪያ ደንብ  መሰረት ከገንዘብ ያዥ ፣ ከሂሳብ ሹም ገር በሰነድ ላይ ይፈርማ ያጸድቃል፡፡
  5. መሰረታዊ  የሰራተኛው  ማህበር ወክሎ በደረጃ እድገት  በዝውውር በሰራኛው ጉዳዮች  ዙሪያ ከሚመከለታቸው  ጋር በመነጋገር የመፍትሄ  አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡
  6. በድርጅት  በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶ በሚዲርጉት ስብሰባ በሌሎች  ጉዳዮች ከተጋበዙ ወይም  ከተጠሩ  ማህበሩን ወክለው  ይገኛሉ፡፡
  1. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ም/ሊቀመንበር 
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ሊቀመንበር  በሌሉበት ጊዜ  ተክቶ የማህበሩን ስራ  ያከናውናል
  2. ሊቀመንበሩን  በስራ ያግዛል  ይረዳል
  3. ከሊቀመንበሩ የሚጠውን ተግባሮችን ያከናውናል 
  4. ከሌሎች  ኮሚቴዎች ጋር በመሆን አበላትን ችግሮችን እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ዋና ጸሐፊ
  1.  የማህበሩን ስብሰባዎች ቃለ ጉባኤዎችን ይይዛል 
  2. የማህበሩን የጽሕፈት  ስራዎችን ይሰራል
  3. የማህበሩን የሥራ ዘገባ ያዘጋጃል  ያቀርባል
  4. የመሰረታዊ ሰራተኛ  ማህበር ሰነድ በአግባቡ  ይይዛል ደራጃል  በጥንቃቄ ይዘግባል፡፡
  5. የማህበሩ  ተቀጣሪ ሰራተኞች ያስተዳድራል
  6. የአዳዲስ አባላት ዲክመንት  ያዘጋጃል  በጥንቃቄ እንዲይዙ  ያደርጋል፡፡
  7. ሊቀመንበሩን  ም/ሊቀመንበሩን በሌሉበት ጊዜ  የማበሩን ስራ ያከናውናል፡፡
  1. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበር ሂሳብ ሹም 

የማህበሩ  ሂሳብ ሹም  የማባሩ መተዳደሪያ ደንብ በመከተል 

  1. የማህበሩን ገቢ ንብረት  በሂሳብ አያያዝ  መመዝገብ
  2. የማህበሩን ገቢና ወጪ ሰነዶች በአግባቡ እንዲጠብቅ ማድረግ
  3. የማህበሩን  ወጪን  ትክክለኛነት አረጋግጦ ማቅረብ 
  4. ከሊቀመንበሩና  ገንዘብ ያዥ ጋር  ቼክ መፈረም
  5. የማህበሩ ወጪዎች  ገቢዎች ቁጥጥር  አመች በሆነ መልኩ  ሰነዶችን ማዘጋጀትና  ማቅረብ 
  6. በስራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ የ6 ወር  የዓመት ሪፖርት  በዝርዝር ማቅረብ 
  7. እንደ አስፈላጊነቱ  የሂሳብ  ነክ ስራዎችን መከታተልና ማከናወን 
  8. ባላት መዋጮ በትክክል መሰብሰቡን መከታተል፡፡
  9. የወጪና  ገቢ  ሰነድ በፋይል  ማደራጀት 
  10. በፌዴሬሽን 40 በመቶ  በወቅቱ  ገቢ መሆኑን መከታተል
  11. ከተለያዩ  ተቋም  የሚገኙ  ገቢዎች  በአግባቡ በመከታተል  ለማህበሩ ገቢ እንዲሆን  ማድረግ
  1. የመ/ሠ/ማ ገንዘብ ያዥ ተግባርና ኃላፊነት 
  1. የማህበሩን ገቢና ወጪ  በተዘጋጀው  ደረሰኝና ፎርም መሰረት ይሰበሰባል፡፡ 
  2. የመ/ሠ/ማህበር ገንዘብ ይይዛል፡
  3.   ከሊቀመንበሩና ከሂሳብ ሹም ጋር ቼክ  ይፈርማል፡፡
  4.  ሊቀመንበሩ ሲያዝና  ሲያጸድቅ  ሂሳብ ሹም  ካረጋገጠ በኃላ ክፍያ ይፈጽማል፡፡
  5. የሂሳብ ሰነዶች  በኦዲትና  በሂሳብ ሹም ያስመረምራል 
  6. ስለማህበሩ  ገንዘብ በተመለከተ ሪፖርት  ያዘጋጃል፡፡
  7. ከስራ አስፈጻሚ  ጋር ውሳኔዎች እቅዶች በጀትን ያጸድቃል፡፡
  1. ሌሎች የማህበሩ  የሥራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ አባል 
  1. የሥራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ ስብሰባ  ወጪ በመገኘት ስለማህበሩ  ስራ ይመክራል ሀሳብ  ያቀርባል ድምጽ ይሰጣል፡፡
  2. የሥራ አስፈጻሚ  ወይም በሊቀመንበሩ የሚሰጣቸው ስራ  ያከናውናል
  3. ለማህበሩ የሥራ  ማሻሻያ ገንቢ  ሀሳቦ ለስራ አስፋጻሚ ያቀርባል ያጸድቃል፡፡
  4. ከአጠቃላይ  ጉበኤና  ከም/ቤት የሚሰጡ  ሀሳች ተግባራዊ  እደሆን ያደርጋል፡፡ 
  5. ከስራ አስፈጻሚና ከኦዲት  ኮሚቴ  የተጓደላ ኮሚቴ  ምትክ የመተካት ስራ ይሰራል፡፡
  1. የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር  የገቢ ምንጮች 
  1. ከአባላት መመዝገቢያ 
  2. አባላት በሚሰበሰበው ወርሃዊ መዋጮ
  3. በማህበሩ  ከሚያቋቁማ መዝናኛ ክበብ 
  4. ማኅበሩ  ከሚያቋቁመው  የተለያዩ ተቋማት 
  5. ለመንግስታዊና  መንግስታዊ ካልሆነ  ድርጅት  ከሚገኘው እርዳታና ድጋፍ  
  6. ከተለያዩ  ግለሰቦች ከሚገኘው እርዳታና ድጋፍ 
  1. መ/ሠ/ማህበር  አባላት መዋጮ 
  1. ማንኛውም  አባል በአዲስ ከተመዘገበ ወይም አዲስ  ገቢ የመመዝገቢያ መደበኛውን  ብር ይከፍላል፡፡
  2. የማህበሩ  አባል የሆነ  የአባልነት  አንድ ፐርሰንት(1) መዋጮ  ይከፍላል 
  3. በተለያየ  ምክንያት  ከማህበሩና  በማህበሩ  ኃላፊነት  የተወሰነ የገንዘብ  ብድር  ከደመወዝ  ተመላሽ ያደርጋል፡፡
  1. የመሰረታዊ ሰራኛ ማህበር  አባ ስመሆን 
  1. በመ/ሠ/ማ አባል ለመሆን በፈቃኝነት  ላይ የተመሰረት ይሆናል፡፡
  2. በአሰሪና  ሰራተኛ  ጉዳይ ህግ  የሚሸፍን  የድርጅቱ  ሰራተኛ  ይህንን መተዳደሪያ  ደንብ የሚቀበል ከሆነ አባል ሊሆን ይችላል፡፡
  3. በመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር አባል ለመሆን ከተፈከፈለ ማመልከቻውም  በጽሑፍ  ያቀርባል፡፡
  4. የሥራ አስፈጻሚው የአባል  ማመልከቻ ተቀብሎ አስፈላጊውን  ክፍያ በማስከፈለር  በአባልነት ይመዘገባል፡፡
  5. ከማህበሩ  አባልነት  ለመልቀቅ በሚፈል ማመልከቻ እዲያቀርቡ በማድረግ ያሰናታል፡፡
  1. የማህበሩ  አባላት መብት 
  1. የመምረጥና የመመረጥ  መብት አለው
  2. በህግ በህብረት  ስምምነት በስራ መመሪያና ደንብ ሊገኝ የሚገባቸውን መብቶች  ጥበቃ ማግኘት እንዳለበት ማድረግ 
  3. በስራ ክርክር  ወቅት ለስራ  አስፈጻሚው ድጋፍ ማድግ 
  4. ማህብሩ  የሚያቋቁመው የሚያደራጀው  ኢኮኖሚያዊ አስፈላጊ እና ማህበራዊ  ጉዳዮች  የማገልገል 
  5. በጠቅላላ  ስብሰባ ላይ መገኘት 
  6. በስራ አስፈጻሚ የሚቀርብ  ሪፖርት  እቅድ ማጽደቅ መወሰን 
  7. ከስራ አስፈጻሚ  የሚጠውን አቅጣጫ በመከተል  ማከናወን  መተባበር፡፡
  8. የድርጅቱ  እድገት   የዕድገት  በመሆኑ ጠንካራ አምራች መሆንና በጋራ ጥቅም  ጋር መታገል፡፡
  9. የማህበሩን ንብረት በአግበቡ መያዝ 
  10. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ  ንብረቱን ለማህበሩ  መመለስ
  1. የአባላት  የማህበሩ አባላት ግዴታ
  1. የአባልነት  ወራዊ መዋጮ  በወቅቱ  መልፈል
  2. በጠቅላላ  ጉባኤ የጠላፈውን ውሳኔ  ተግባራዊ ማድረግ 
  3. ለማህበሩ ንብረት  ተገቢ ጥንቃቄና ጥበቃ ማድረግ 
  4. ከማህበሩ ስራ  አስፈጻሚ  የሚጠው ተግባራዊ ማድረግ 
  5. በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 በህብረት ስምምነት  መሰረት  የድርጅቱን  መመሪያና ደንብ  በመጠበቅ ግዴታን  መወጣ
  1.  የሥብሰባ ስነ ስርዓት 
  1. በየሦስት ወሩ  የም/ቤት ስብሰባ ያደርጋል
  2. በአመት መጨረሻ  በተመረጠ 1 ቀን  በጠቅላላ ጉባኤ  ይከናወናል፡፡ 
  3. የስራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ  በዚህ ውስጥ  ሁለት ቀን  በተመረጠ ቀን ስብሰባ  ያደርጋል፡፡
  4. የሥብሰባውን ምልዐተ ጉባኤ  የጠቅላላ  አባላት 2/3  መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
  5. በጠቅላላ  አባላት ውሳኔ  የሚተላለፍ ውሳኔ ከግማሽ በላይ  መሆኑን  ያረጋግጣል (መረጋገጥ አለበት)
  1. የመ//ማህበር የምርጫ ስነስርዓት 
  1. የማባሩ ስራ አስፈጻሚ  ምርጫ በየ አራ (4)ዓመት  ይከናወናል፡፡
  2. የምርጫበካር ድምጽ አሰጣጥ ወይም እጅ በማውጣት  ይሆናል፡፡
  3. በምርጫ ወቅት  ለአንድ ተወዳዳሪ  አንድ ተወዳዳሪ ወይም ለእያንዳንዱ ሁለት ተወዳዳሪ  ይቀርባል አብላጫ ድምጽ  ያገኘ ለውድድር ይቀርባል፡፡
  4. የእጩዎች  ጥቆማ  በግል እውነት በማቅረብ ወይም  በአባላት ጥቆማ  ሊሆን ይችላል፡፡
  5. ከተገኙ ጠቅላላ አባላት ውስጥ 1/3  ያልተገኘ ውድድር አይቀርብም
  6. የአዲስ  ኮሚቴ  በጠቅላላ  ጉባኤ ይመረጣል
  7. የስራ ክፍፍል  የተመረጡ  ኮሚቴዎች  የሥራ ድልድል በማድረግ  በጠቅላላ ጉባኤ ወደ  አሁኑ  ያሳውቃል፡፡
  8. ከተመረጡት ለጥቆማ ቀረበው  ተወዳሩ በተሻለ ድምጽ  ያገኙ ሶስት ተጠባበቂ  ይይዛሉ፡፡
  9. እኩል  ድምጽ ያገኘ  ከሆነ ስራ አስፈጻሚ የወሰነ ይሆናል፡፡
  10. የሚመረጡ  በአደረገው እንቅስቃሴ  አመለካከት  ተመዝኖ ይሆናል፡፡
  11. ማንኛውም  የማህበሩ ጠቅላላ  ጉበኤ የሚከናወነው ስብሰባው  በወከለው አስመራጭ ኮሚቴ  በኩል ነው፡፡
  1. የሥነ ስርዓት እርምጃ
  1. የማህበሩ  አባል ከማህበሩ  መተዳደሪያ ደንብ ወጭ ከሆነ ጥፋት ከፈጸመ  እንደጥፋቱ  አይቶ ተገምግሞ ከመጀመሪያ  ጊዜ ምክር ይሰጠዋል፡፡
  2. ለሁለተኛ  ጊዜ ጥፋት ከሰራ  የጽሑፍ  ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡
  3. በአንቀጽ 29 1 እና 2  የተጠቀሰ እንደአለ ሆኖ  አባሉ  ለመታረም ካልቻለ ለ 1 ወር ከአባልነት ይታገዳል፡፡
  4. አባሉ ታግዶ በቆየ ጊዜ  የአባልነት  መብቱ አይጠበቅለትም 
  5. በስራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ እና ኦዲት ኮሚቴ ላይ በአንቀጽ 9 ተ.ቁ 1፣2፣3፣4፣ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
  1. ከማህበሩ  ስለማስወገድ 
  1. የማህበሩ አባል ያለ በቂ  ምክንያት ከሶስት ወር በላይ የአባልነት  መዋጮ ከአቋረጠ ከአባልነት ይሰረዛል፡፡
  2. የአባልና የማህበሩ  አንድነት ሆን ብሎ  ለማናጋት ሙከታ ያደረገ በአንቀጽ 29 1 ፣ 2  እርምጃ ይወሰዳል፡፡
  3. አባሉ  ካልታረመ ከአባልነት እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ 


  1. የተመራጮች መመዘኛ 

ማህበሩ  አመራር አባል ሆኖ ለመመረጥ የሚችለው በሚከተው  መልኩ ይሆናል፡፡

  1. የማህበሩ  አባል ያለ በቂ ምክንያት  ከሶስት ወር በላይ አባልነት መወጮ  ከአቋረጠ ከአባልነት ይሰረዛል፡፡
  2. ለሰራተኛ ወገናዊነት  ያለው (ያላት)
  3. በስራው ጠንካራና የማስተባበር ችሎታ ያለው (ያላት)
  4. ለድርቱ  እድገት  በግልና በጋራ ጥረት  የሚያደርግ 
  5. የሥራ ፍላጎትና ተነሳሽነት  ያለው (ያላት) 
  6. የተሻለ የትምህርት  ዝግጅት ያለው (ያላት)
  1. ማህበሩን  ወክሎ ውል መዋዋል
  1. በማህበሩ  እድገት  ጠቃሚ  ሆኖ ሲገኝ  በጠቅላላና በም/ቤት ውሳኔ መንግስታዊ ና መንገስታዊ ያልሆነ ድርጅቶች ጋር መዋዋል 
  2. ማህበሩን  ወክለው በስራ ክርክር  በሌሎች ጉዳዮች  ከባለሙያና ማህበሩ  አምኖበት  ከወሰነ አካል ጋር መዋዋል፡፡
  3. ውል በመቀበልና በኮሚቴ  በም/ቤ በአባላት  ውሳኔ መከናወን፡፡
  4. ማህበሩን በስራ ስብሰባ በሚያደርገው  የሠራተኛ ቅጥር በአጭር ጊዜና በረጅም  በቋሚነት (ኮንትራት) ውል መዋዋል፡፡
  1. ለማህበሩ  ጽ/ቤት የሠራተኛ ቅጥር 
  1. ስራውን ለማከናወን  ተመጣጣኝ መመዘኛ በማውጣት  የሰራተኛ ቅጥር  ማከናወን 
  2. የሠራተኛ የደመወዝ መጠን የማበሩን ገቢ በአገናዘበ መፈጸም 
  3. የቅጥር ሰራተኛ  ፋይል በአግባቡ መያዝ
  4. ለቅየጥር ሰራተኛና ማህበሩ  ለሚያሰራቸው  ሰራኞ የሥራ ልምድ መስጠት፡፡፡
  5. እንደአስፈላጊነቱ  ተያዥ እንዲያቀርብ ማድረግ



  1. የማህበሩ  ዕቃዎች ጊዜ  ያፈባቸው ስለማስገድ 
  1. በማህበሩ ንብረት ተመዝግቦ የአገልግሎ ዘመናቸውን የጨረሱ እንደ አስፈላጊነቱ  በጨረታ መሸጥ 
  2. ለማህበሩ  አስፈላጊ ዕቃች እንዲገዙ እንዲታተሙ ከተፈለገ ለአንድ እቃ ከ3 በላይ ፕሮፎርማ  በመሰብሰብ የተሻለ ዝቅተኛ ዋሃ ከአቀረበ ጋር ግዥ መፈጸም፡፡
  3. ፕሮፎርማ  ከ2-3  ኮሚቴ ሆኖ መሰብሰብ፡፡ 
  4. ግዥ የሚጸመው መጀመሪያ ዓመት  አዲስ በጀት  በመክፈት ይህም የሚፈጸመው አስፈላጊነቱ  ኮሚ አምኖበት ከወሰነ ነው፡፡ 
  1. የትራንስፖርት  ውሎ አበል ክፍያ 
  1. የትራንስፖርት  የውሎ አበል የሚከፈለው ኮሚቴው  የማህበሩን ስራ ለማከናወን  ከተንቀሳቀሰ ነው፡፡
  2. የማህበሩን ስራ ለማከናወን ቀኑ  ሙሉ ከሆነ  ብር 60 ለትራንስፖርት  ይከፍላል፡፡ 
  3. የማህበሩን ስራ ለማከናወን  ቀኑ ሙሉ ከሆነ ብር 60 ለትራስፖርት ይከፍላል፡፡
  4. ከአዲስ አበባ  ውጪ ከሆነ  ውሎ አበል 100 ብር ለትራንስፖርት  ያወጣል በቀበረበ ማስረጃ  ይከፍላል፡፡
  5. ከስራ ሰዓ ውጪ የሚደረገው የኮሚቴ  ስብሰባ ሲደረግ  ለትራስፖርት  ያወጣውን በቀረበ  ማስረጃ ይከፍላል፡፡
  6. ከስራ ሰዓት  ውጪ የሚረገው የኮሚቴ ስብሰባ ሲደረግ  ለትራንስፖርት  ብር 30 ይከፍለዋል፡፡ 
  7.  በስራ ቀን  ለሚደረገው ስብሰባ  የትራንስፖርት  አይከፍልም 
  8. የትራስፖርትና  የውሎ አበል  እንደሁኔታ  ከማህበሩ  የገንዘብ  አቅም ሚዛን ጋር  በአገናዘበ ሆኖ የመጨመርና  የመቀንስ ሁኔታ  በም/ቤት ይወሰናል፡፡
  1. ማህበሩ ስሚርስበት ሁኔታ 
  1. የተቋቋመበት  ድርጅት ሲፈርስ ፣ ሲቀላቀል ሲከፋፈል 
  2. በአባላት ቁጥር  ከአሰሪና ሰራተኛ  ጉዳይ አዋጅ 377/96 ከተወሰነው በታች ሆኖ  ሲገኝ፡፡
  3. ማህበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ  ከግቡ ለማድረስ የማይቻል ከሆነ
  4. ጠቅላላ  አባላትን አንድ ለማድረግ  አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ 
  5. ማህበሩ  ሊፈርስ የሚችለው በአባለት 2/3  አምኖበት ሲወስን
  6. የማህበሩ ንብረት  ገንዘብና ሌሎች  ጠቅላላ አባላት በሚስኑት መሰረት  ተግባራዊ ይሆናል፡፡
  1. ይህ መተዳደሪያ ደንብ እንደአስፈላጊነቱ  ከጠቅላላ አባላት  ሁለት ሶስተኛ (2/3) ድምጽ ሲደግፍ  ብቻ ሊሻሻል ይችላል፡፡
  2. የመተዳሪያ ደንቡ  የሚጸናበት ጊዜ 
  3. ይህ መተዳደሪያ ደንብ  በጠቅላላ ጉባ ከጸደቀ ------------------ ጀምሮ  የጸና ይሆናል፡፡

   

BM Ethiopia Garment and Textile S.C -

Start date: → Not specified
End date: → Not specified
Name industry: → Manufacturing
Name industry: → Manufacture of textiles
Public/private sector: → In the private sector
Concluded by:
Name company: →  BM Ethiopia Garment and Textile S.C
Names trade unions: →  ቢኤም ልብስ ስፌትና ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር የሰራተኞች ማህበር
Loading...