Collective Agreements Databaseባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

ህብረት  ስምምነት

 ተ.ቁ

ርዕስ 

አንቀጽ

ገጽ


 የሥምምነት ዓላማ

1

1


ትርጉም

2

1


የስምምነቱ  ተፈጻሚነት  ወሰን 

3

4


የአሰሪው መብት እና ግዴታ 

4

4


የአሰሪው መብት

4

4


የአሰሪው ግዴታዎች

4

7


 የመሰረታዊ የሰራተኛ ማሕበሩ መብትና ግዴታ 

5

8


የማህበሩ  መብት 

5

9


የሠራተኛው  መብትና ግዴታ 

6

11


ሀ/ የሰራተኛው መብት 

6

12


ለ/  የሰራተኛው ግዴታ 

6

13


በድርጅቱ ውስጥ ስለሚደረግ ዝውውር 

 7

14


የደረጃ እድገት 

8

15


የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ  አክሲዮን ማህበር የደመወዝ ስኬል 

8

16


የሥራ ችሎታ

8

17


ለትምህርት ደረጃ 

8

18


ለአገልግሎት ዘመን 

8

19


አግባብ ያለው የሥራ ልምድ 

8

20


ለግል ማሕደር  ጥራት

8

21


የዕድገት  ተፈጻሚነት 

8

22


የደረጃ  ዕድገት  ለመወዳደር ስለሚቀርቡ ሰራተኞች 

8

23


የደረጃ  ዕድገት ኮሚቴ  ስለማቋቋም 

8

24


የዕድገት  ኮሚቴ  አሰራር ስነ ስርዓት 

8

25


ቅጥር 

9

27


ክፍት የሥራ መደቦች ማስታወቂያ ይዘት  

9

29

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር931

ህብረት  ስምምነት932

 ተ.ቁ

ርዕስ 

አንቀጽ

ገጽ


የቅጥር ኮሚቴ

9

30


የቅጥር ከሚቴ ተግባር 

9

31


 የቅጥር ኮሚቴ የውሳኔ አሰጣጥ 

10

32


ለተወሰነ  ስራ ሰራተኛ  የሚቀጠርበት ሁኔታ 

1

33


የስራ ውል አመሰራረት 

12

34


ደመወዝ 

13

35


የውሉ አበልና  የመጓጓዣ ወጭ 

14

36


 ስራን በውክልና ማሰራና ስለሚከፈለው አበል 

15

37


የሥራ አፈጻጸም  መመዘኛ ስለመሙላት 

16

38


ስለግል ማሕደር  አያያዝ

17

39


 መደበኛ የሥራ ሰዓት 

18

40


የትርፍ ሰዓ ስራ አከፋፈል 

 19

41


የሳምንት  የዕረፍት ቀን 

20

42


የሕዝብ በዓላት 

20

43


ልዩ ልዩ ፈቃድ 

20

44


የዓመት ዕረፍት  ፈቃድ 

20

45


የሕመም  ፈቃድ 

20

46


የወሊድ ፈቃድ 

20

51


የጋብቻ ፈቃድ

20

52


ለማህበር መሪዎች  የሚሰጥ  ፈቃድ

20

53


ሕጋዊ  መብትና ግዴታ  ለማስፈጸም  የሚሰጥ ፈቃድ 

20

54


ለትምህርት ወይም ለስልጠና የሚሰጥ  ፈቃድ 

20

55


ሕጋዊ  መብትና ግዴታ  ለማስፈጸም  የሚሰጥ ፈቃድ 

20

56


ደመወዝ  የማይከፈልበት  ፈቃድ

20

57


አክሲዮን ማሕበሩ ኤች አይቪ ኤድስን  በስራ ቦታ 

20

58

27459

75ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

76ህብረት  ስምምነት

 ተ.ቁ

ርዕስ 

አንቀጽ

ገጽ


የመድን ዋስትና

21

60


በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ  አዋጅ  ቁጥር 371/96

21

61


የጉዳት ካሳ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ግዴታዎች  

22

62


የሥራ ውል መቋረጥ

22

63


የሥራ ውል  መቋረጥ

22

64


ከሕግ  ውጭ የሥራ ውል  መቋረጥ 

22

68


ከሕግ  ውጭ የሥራ ውል  የሚቋረጥበት  ሰራተኛ 

23

66


 የሥራ ስንብት  ክፍያና ከሳ አፈጻጸም

23

67


የሥራ ስንበት  ክፍያ አፈጻጸም 

23

68


ያለማስጠንቀቂያ  ስራ ለሚርቅ  ሰራተባ ስለሚሰጥ  

24

69


የጡረታ  መብት ስለመጠበቅ

25

70


ለገንዘብ ከፋዮ የሚሰጥ  ማካካሻ  ክፍያ 

26

71


ሕገ ወጥ ድርጊት 

 26

72


የሚከተሉትን  መፈጸም ለማንኛውም  አሠሪ ሕገ ወጥ  

26

73


የሚከተሉትን  መፈጸም  ለማንኛውም ሰራተኛ ሕገ ወጥ

26

75


  የሥነ ስርዓ  እርምጃ  አወሳሰድ 

27

76


የቅጣት አወሳሰን 

27

79


የጥፋት ደረጃ እና የሚያስከትለው ቅጣት 

27

80


የሥራ ደንብ ባለማክበር  የሚያስከትሉ ቅጣቶች 

27

81


የጠፈጸመው ጥፋ ትክክለኛነት ስለማጣራት 

27

82


ከስራ የሚሳግዱ ጥፋቶች

27

83


ያለ ማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያስወጡ ጥፋቶች 

27

84


የቅጣት  ተፈጻሚነት  የጊዜ ወሰን ገደብ 

27

85


ስለ ቅሬታ  አቀራብ ስነ ስርዓት

27

86


ስለሰራተኛው ጤንነት  ደህንነት የሥራ ልብስና አደጋ 

28

89


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

ህብረት  ስምምነት

 ተ.ቁ

ርዕስ 

አንቀጽ

ገጽ


ስለ ሰራተኛው ጤንነት  ደህንነት  ጥበቃ 

29

90


የስራ ልብስና የአደጋ መከላከያ 

29

91


 ለሰራተኛ  የሚገባው የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ 

29

92


ቱታ 

29

93


 ካፖርት

29

94


ሸሚዝና ሱሪ

29

95


የጨርቅ  ቆብ ከስፖንጅ  የተሰራ  የብናኝ መከላከያ 

29

96


የጨርቅ ቆብ 

29

97


የአፍ እ የአፍንጫ ማስክ

29

9


ወተት 

29

98


ከቆዳ  የተሰራ የእጅ  ጓንት 

29

99


ፕላስቲክ  ጎግልስ 

29

91


የፕላስቲክ  ሽርጥ

 29

92


የጆሮ  ድምጽ መከላከያ 

29

93


የብርሃ መከላከያ መነጽር 

29

94


የኬሚካል  መከላከያ  ፕላስቲክ  መነጽር 

29

95


ቦት ቆዳ  ጫማ

29

96


ጉርድ  ቆዳ ጫማ 

29

97


የኬሚካል  መከላከያ ፕላስቲክ መነጽር 

29

9


የብረት ቆብና  ሸራ ቀበቶ 

29

98


ብረት  ቆብ 

29

99


የዝብ ልብስ 

29

91


የነፋስ መከላከያ ቆብ ያለው ጃኬት 

29

92


ካፖርት

29

93


ሸሚዝ 

29

94

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

ህብረት  ስምምነት

 ተ.ቁ

ርዕስ 

አንቀጽ

ገጽ


ካልሲና ወፍራም  ቀበቶ 

29

91


ከረቫት 

29

92


ጉርድ ባለ ሸራ ጎማ ጫማ 

29

93


ፕላስቲክ  ጓንት 

29

94


የሥራ  ልብስ ካኪ  ቴትረን  በሀገር ውስጥ  የተሰራ  ከለለ

29

95


የደንብ  ልብስ  መለዩ

29

96


ሸራ ጫማ 

29

97


ሳሙና /200/ግራም

29

9


የህክምና  አገልግሎት  ስለመስጠት 

29

98


በስራ ሰዓት

29

99


በሆስፒታል  የሚሰጥ  ሕክምና 

29

91


በክሊኒኩ  ውስጥ የሚደረጉ  ሕክምናዎች 

29

92


ከስራ ጋር  የተያያዘ  አደጋ ወይም  ሕመም  የሚሰጥ 

 29

93


የሕመምተኛ ማመላለሻ  አገልግሎት

29

94


በሕመም ምክንያት ስለሚሰጥ ስራ 

230

95


ለሠራተኛው ቤተሰብ የሚሰጥ የሕክምና አገልግሎት

30

96


ልዩ ልዩ ማህበራዊ አገልግሎት

30

97


ቀብር 

30

9


የብድር አገልግሎት

30

98


የመኖሪያ ቤት 

30

99


ስፖርት 

30

91


ለሰራተኛ የሚሰጡ ዕቃዎች 

30

92


የክበብ አስተዳደር 

30

93


በአ/ማህበሩ ውስጥ የሚገኝ ሣር

31

94


የሰራተኛው የውስጥ ሻይ ቤት

31

95

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

ህብረት  ስምምነት

 ተ.ቁ

ርዕስ 

አንቀጽየትምህርት 

31

95


የጤና አጠባበቅ ትምህርት አሰጣጥ

31

96


የሙያ ስልጠና 

31

96


የደመወዝ ጭማሬ እና የማበረታቻ (ቦነስ) ክፍያ

31

96


የ2006 የበጀት አመት

31

96


ቀጣይ የትርፍ ክፍፍል አፈጻጸም ሂደቶች 

31

96


የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ስህተት ስለማረም 

31

97


ስህተት የሚታረመው በሚከተለው ሁኔታ ነው 

32

98


ሕብረት ስምምነቱ ከሌሎች ሕጎች ጋር ስላው 

32

99


ከህብረት ስምምነት ውስጥ ስላልተጠቀሱ ጉዳዮች

32

100


በተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሰራተኞች ተፈጻሚ የሚሆን 

33

111


ያለፉትን ኃ/ስምምነቶች ጠቅሶ መጠየቅ ስላለመቻሉ

33

112


የስምምነቱ አተረጓጎም 

 33

113


ህብረት ስምምነቶ ጸድቆ የሚቆይበት ጊዜ

33

114


ህብረት ስምምነቱ የተፈረመበት ቀን 

34

115ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

አንቀጽ አንድ

የስምምነት ዓላማ፡-

የዚህ የህብረት ስምምነት ዋና ዓላማ በአ/ማህበርና  በሰራተኛ መካከል የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማስፈን እንዲቻል የሥራ ሁኔታዎቻችን እና  የሥራ ግንኙነቶችን በመወሰን የአክሲዮን ማህበሩን እና የሰራተኛው መብት እንዲከበር የማድረግ ግዴታቸውን እንዲወጡ በማድረግ ነው፡፡

አንቀጽ ሁለት

ትርጉም

 1. በዚህ ስምምነት ውስጥ አዋጁ፡- ማለትም የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ  አዋጅ ቁጥር 377/96 እና 494/98 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 25/84 የአክሲዮን ማህበሩ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 146/98 እና ወደ ፊት ከላይ የተጠቀሱትን ተክቶ የሚወጣ   አዋጅ  ወይም ደንብ  ማለት ነው፡፡
 2. ሕጎች ወይም መመሪያዎች  ፡- ማለት መንግስት  በአሰሪና በሰራተኛ ጉዳይ ላይ ያወጣቸውንና  ወደፊት  የሚያወጣቸውን  ሕጎችና  የማስፈጸሚያ  ደንቦ ማለት ነው፡፡ 
 3. ቦርድ ማለት  የባሕር  ዳር /ጨ/ጪ/አ/ማህበር  የዳይሬክተሮች  ቦርድ ማለት ነው፡፡ 
 4. የአሰሪና የሰራተኛ ጉዳይ  ወሳኝ ቦርድ ማለት  በክልሉ  የተቋቋመው  የአሠሪና ሠራተኛ  ጉዳዮችን የማየትና  የመወሰን  ስልጣ የተሰጠው አካል ነው፡፡
 5. አ/ማህበሩ፡- ማለት  የባሕር  ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ነው፡፡


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 


 1. የሰራተኛ  ማህበር  ማለት አሰሪና ሰራተኛ  ጉዳይ አዋጅ  ቁጥር  377/96 መሠረት  የተደራጀው  የባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን  ማህበር መሠረታዊ  የሠራተኛ ማህበር ማለት ነው፡፡


 1. ሠራተኛ፡-  ማለት በአሰሪ እና በሠራተኛ  ጉዳይ አዋጅ  ቁጥር 377/96 አንቀጽ  4 በተመለከተው መሰረት  ከአሰሪው ጋር  በቅጥር ላይ  የተመሰረተ  የሥራ ግንኙነት ያለው  ግለሰብ ነው፡፡


 1. አዲስ የሥራ መደብ ፡- ማለት ለአክሲዮን  ማህበሩ እድገት  መስፋት እንዲሁም  የሥራ መቃናት አስፈላጊ ሆኖ በጥናት የሚፈትና በዚህ ህ/ስምምነት  ውስጥ የሚመዘገብ አዲ የሥራ መደብ  ማለት ነው፡፡


 1. የእድገት  መስጫ ማወዳደሪያ  ሚዛን፡-  ማለት በአ/ማሕበሩ  ውስጥ በሚፈጠር የክፍት የሥራ  መደብ ላይ  ሠራተኞችን  በእድገት ለመመደብ  ችሎታቸው የሚመዘንበት ነው፡፡


 1. የሥራ መደብ ለውጥ፡- ማለት  አንድ ሠራተኛ  የነበረበት  የሥራ መደብ  ለጤንነቱ የማይስማማ መሆኑ  በሐኪም  ቦድ ሲረጋገጥለትና የሥራ መደብ  ለውጥ ጠየቀው ሰራተኛ ያቀረበው ሀሳብ በአክሲዮን  ማህበሩ  ተቀባይነት ካገኘ 

በዚህ ህብረት  ስምምነት መሰረት  የሚመደብበት  የሥራ መደብ ነው፡፡


 1. ዝውውር  ማለት  ለሥራው ወይም ለሠራተኛው  ደህንነት  ሲባል  ሠራተኛው ከነበረበት  የሥራ መደብ ወይም ተመሳሳይ  ደረጃ ወደ  አለው ሌላ የሥራ ክፍል የሚዛወርበት  ነው፡፡ 
 2. መነሻ ደመወዝ ፤- ማለት   የሥራ መደብ  በጸደቀው  መዋቅር መሰረት  የተወሰነ ዝቅተኛ ደመወዝ ነው፡፡


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. ቀድሞ  ያልታዩ ጉዳዮች  ማለት አስቀድሞ ተጠንቶ  በዚህ ህብረት ስምምነት  በግልጽ  ያልተብራራ  ድንገተኛ  ጉዳይ ማለት ነው፡፡


 1. የውል  የሥራ ክርክር፡- ማለት  በአዋጅ  377/96 በአንቀጽ 142 እና አዋጅ 377/96 በአንቀጽ 142 እና አዋጅ  494/98 ከሁሽ  ያጠቃለለ ነው፡፡ 


 1. የግል የሥራ  ክርክር፡- ማለት  በአዋጅ  377/96  በአንቀጽ 138  በክልል የመጀመሪያ  ደረጃ ፍ/ቤት  የሥራ ክርክር  ችሎት  የሚቀርቡትን  ከተራ  ቁጥር  1 ከ ሀ- ረ  በተጠቀሱት ምክንያቶች  የሚነሱ ክርክሮችን  ማለት ነው፡፡
 2. ቋሚ  ሠራተኛ ፡- ማለት  ላልተወሰነ ጊዜ በአ/ማህበሩ  የጠቀመጠ ሰራተኛ ማለት ነው፡፡
 3. የኮንትራት ሠራተኛ፡- ማለት የተወሰነ ስራን  በተወሰነ  ጊዜ ለማከናወን  የጠቀጠረ ሠራተኛ  ማለት ነው፡፡ ይህ ውል  ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ስራውም ካልተጠናቀቀ  በሁለቱ ተዋዋዮች  ስምምነት   ሊራዘም  የሚችል ነው፡፡
 4.  ጊዜያዊ  ሰራተኛ፡-  ማለት በአዋጅ  ቁጥር 377/96 አንቀጽ በቁጥር 2  በፊደል  “ሸ”  እና  “ቀ”  ላይ የተጠቀሱትን ስራዎች ለመሸፈን ከ45 ቀናት ላልበለጠ የተቀጠረ  ሰራኛ ማለት ነው፡፡
 5. መዋቅር፡-  ማለት በባለሙያ  ተጠኝቶ የጸደቀው  የአክሲዮን  ማህበሩ የሠው ኃይል  ብዛት  ደመወዝ የሥራ መደብ ደረጃና  የመስፈርቶችን የሥራ  መመሪያ የያዘ  ማለት ነው፡፡ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. የደመወዝ  ስኬል ማት፡- አ/ማህበሩ  ወደ ጎን  እድገት የሚሰጥበት ወይም ቦነስና  የደመወዝ ጭማሪ  የሚደረግበት  ለየሥራ መደቡ የጠፈቀደ የገንዘብ መጠን ማለት ነው፡፡

አንቀጽ ሶስት

የስምምነቱ  ተፈጻሚነት  ወሰን

ህ ስምምነት  በአ/ማህበሩ  ውስጥ ላልተወሰነ ተቀጥረው በሚሰሩት ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት  ይኖረዋል፡፡ 

ሁን እንጂ  ለማንኛውም አገልግሎት  ለተወሰነ በተቀጠረና በትርፍ ጊዜው  ወይም ለተወሰነ ቀናት ራሱን ችሎ  የተወሰነ ስራ በተለየ ስምምነት  ለመስራ በተቀጠረ ሰው  ላይ  ተፈጻሚነት የለውም፡፡ 

አንቀጽ አራት

 1. የአሰሪው  መብትና ግዴታ ፡
 1. በዚህ ሕብረት ስምምነት  ላይ ከተጠቀሱት  ጉዳዮች  በተጨማሪ   ማንኛውም የአ/ማህበሩን  ስራ የማቀድ  የመምራት  የመቆጣጠር ሰራታን በየስራ  መደቡ የመመደብና  በበቂ ምክንያት ከቦታ ወደ ቦታ  የማዘዋወር  መብቱ  የአክሲዮን ማሕበሩ ነው፡፡
 2.  በአሰሪና  ሠራተኛ  አዋጅ  ቁጥር 377/96 እና በአዋጅ ቁጥር   494/98 የተቀመጠው መሰረት እርምጃ  የመውሰድ  የአ/ማህበሩ መብት ነው፡፡ ይሁን  እንጂ አክሲዮን ማህበሩ  የወሰደው እርምጃ  ለመሰረታዊ ሠራተኞች ማህበሩ  በግልባች ያሳውቃል፡፡


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. አዲስ መደብ  የመክፈት አስፈላጊነቱ  የመወሰን  በየስራው  አስፈላጊውን  የሠራተኛ ኃይል  ብዛት  የመወሰን  በየሥራው  የሚፈለገውን  የት/ደረጃና  የሥራ ልምድ  የመወሰን  አዲስ ሠራተኛ በሕጉ  መሰረት  የመቅጠር  በዚህ  የህብረት  ስምምነት  መሠረት  ተወዳድሮ  ላለፈ  ሠራተኛ  የደረጃ  እድገት  የመስጠት  ለሚወሰዱ  የሥነ  ስርዓት እርምጃዎች  ይቅርታ  የማድግ ወይም  የማሻሻል መብቱ  የአክሲዮን ማህበሩ ነው፡፡


 1. ስለ አ/ማህበሩ  ንብረትና ሀብት እንዲሁም  ስለ አክሲዮን  ማሕበር የስራ ሁኔታዎች  ጉዳይ ከሌላ  ወገን ጋር  የመነጋገር  ስለ ዕቃ ግዥና ሽያጭ  የመዋዋል  ኢንሹራንስ  የመግባት  ሌላም  አስፈላጊ የሆነ ውል  የመግባት በአክሲዮን  ማሕበሩ  ስም የመክሰስና  የመክሰስ  መብትና ግዴታ  የአክሲዮን  ማህበሩ ነው፡፡ 1. ውክልና  የመስጠት መብት  የአክሲዮን ማህበሩ ሆኖ ከ30  ቀን የሚበልጥ ውክልና  መስጠት  የሚቻለው  ግን ዋና ሥራ አስፈፃ ሲፈቅድ ብቻ  ነው፡፡


 1. በሌላ  አኳኋን  ካልተወሰነ  በስተቀር  የአክሲዮን  ማሕበሩን  ስራና  ሠራተኛን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ሁሉ መግለጫ ማስታወቅያና የትምህርት  ፕሮግራም የሚያወጣ  አክሲዮን ማሕበሩ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም  ሠራተኛ  ማህበሩ  እና  በማሕበሩ የተቋቋሙ  ኮሚቴዎች መግለጫ ለመስጠትም ሆነ ማስታወቂያ  ለማውጣት  ጥያቄው  ለማሕበሩ  ቀርቦ  ማሕበሩም  ጥያቄውን  ለማኔጅመንት አቀርቦ  ሲፈቀድ በሕግ የተደነገገ  መግለጫና ማስታወቂያ ማውጣት ይችላሉ፡፡ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 


 1. አንድ ሠራተኛ  ከፍተኛ የዲሲፕሊን  ስህተት ከፈጠረና እስኪያ   ድረስ የግሰቡ በሥራ ላይ መቆየት  ጉዳት ያለው   አክ/ማህበሩ  ከአገኘው ለአንድ ወር  ሠራተኛውን ያለ ደመወዝ ከስራው ሊያግደው ይችላል፡፡  በመጨረሻም  በሚደረገው ማጣራት ግለሰቡ  ጥፋተኛ ሳይሆን  ወይም ጥፋቱ  ለመታገድ የማያበቃው ሆኖ ከተገኘ  የታገደበት የወር ደመወዝ ይከፈለዋ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ግን ደመወዙ አይከፈለውም ይህም እንደ ቅጣት አይቆጠርለትም፡፡ 
 2. አክሲዮን ማህበሩ ለሠራተኛው የመታወቂያ  ደብዳቤ  ለመጀመሪያ ጊዜ በነጻ  ይሠጣል፡፡ ሆኖም ጠፋብኝ ብለው በድጋሚ ለሚጠይቁ  ያሳተመበትን ሂሳብ ከሰራተኛው  ላይ የመጠየቅ መብት አለው፡፡
 3. የአ/ማህበሩን  ንብረት  ለሌላ ድርጅት  በትውስት የመስጠት  አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም  በነጻ ወይም  በሽያጭ  የመስጠት መብት አለው፡፡ 
 4. ያለ አግባብ   የደመወዝ  ብልጫ  ጭማሪ  የተሰጠው ሰራተኛ ሲያጋጥመው  ደመወዙ ከተጨመረበት እስከ ተስተካከለበት  ገቢ የማድረግ አክሲዮን  ማህበሩ  መብት  አለው፡፡
 5. አ/ማህበሩ  የመዋቅር  ለውጥ  ደረጃ  እና ደመወዝ ሲያስተላልፍ  አ/ማህበሩ  ካመነበት የመሰረታዊ ሠራተኛ  ማህበሩን ሊያላቅቅ ይችላል፡፡
 6.  በሐኪም  ቦርድ  የቦታ ለውጥ  የታዘዘለት  ሰራኛ ሊሰራ ወደሚችልበት ሌላ ቦታ ወስዶ  በዝቅተኛም ሆነ በተመሳሳይ  የሥራ መደብ  አሰመርቶ ማሰራት የአ/ማህበሩ መብት ነው፡፡ 

ለ/ የአሰሪው  ግዴታዎች 

 1. ለሰራተኛው  በስራ ውሉ መሰረት ሥራ የመስጠት 
 2. በስራ ውሉ ወይም  በሌላ አኳኋን  ካልተመለከተ  በስተቀር  ለስራ የሚያስፈልገውን  መሳሪያና ጥሬ ዕቃ ከሰራተኛው  የማቅረብ 


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. ሠራተኛውን የሚመለከቱ  የመንግስት አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም  በሕብረት  ስምምነት ውስጥ የተመለከቱትን  ሁሉ በሚገባ የማክበር 
 2. ሰራኞች በሙያም  ሆነ በእውቀት  እንዲሻሻሉ ከሚያደርጉ የመንግስትም ሆነ ከግል  ድርጅቶች ጋር የመተባበር 
 3. ለሠራተው ደመወዙንና  ሌሎች  ክፍያዎችን በአሰሪና ሠራተኛ  ጉዳይ አዋጅ  377/96 እና በህብረት  ስምምነቱ  መሰረት  የመክፈል
 4. ለሰራተኛው የሚገባውን ሰብዓዊ  ሰብዓዊ ክብር የመጠበቅ 
 5. የሠራተኛውን  ደህንነትና ጤንነት  ለመጠበቅና ከአደጋ ለመከላከል  የሚያስፈልጉት  በሕግ  አግባብነት  ካላቸወ  መ/ቤቶች  በሚመጡ  መመሪያዎች መሠረት  የማሟላት፡፡ 
 6. ሠራተኛው መብትና ግዴታውን በቅድሚያ እንዲያውቅ አክሲዮን  ማሕበሩ ከመሰረታዊ  ሰራተኛ ማህበሩ ጋር  ያደረገውን የሕብረት  ስምምነት ቅጅ አባዝቶ  የመስጠት፡፡
 7. የሰራተኛው ጤንነት  እንዲመረመር በሕግ ወይም አግባብ ባለው  ባለስልጣን ትዕዛዝ  በሚሰጥበት ጊዜ  ለምርመራ  የሚያስፈልገውን በወጪ የመሸፈን፡፡
 8. በአሰሪና  ሰራተኛ  አዋጅ 377/96  የተመለከቱትን ያላቸውን ዝርዝሮች  ያካተቱ  የሰራኛውን   የጤንነት  ሁኔታ በስራ ላይ  የሚርስ ጉዳት  እና ሌሎችም በሚኒስተሬር /በሰራኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር/ እንዲያዙ የተወሰኑ መረጃዎችን  የሚያሳዩ  መዝገብ  የመያዝ
 9. የሥራ ውል በሚቋረጥበት  ጊዜ  ሠራኛው ሲሰራ  የነበረው የሥራ ዓይነት የአገልግሎት  ዘመንና ሲከፈለው የነበረው ደመወዙን የሚያሳይ  የምስክር  ወረቀት ለሰራተኛው የመስጠት እንዲሁም  በስራ ላይ እያለ በዓመት  ለት ጊዜ  በየስድስት ወሩ የሥራ ልምድ  የመስጠት፡፡

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. አዲስ ተቀጣሪ ሠራተኛ  ሲቀጠር  እድገትና ዝውውር  ሲፈልግ ለማህበሩ የማሳወቅ
 2. በሠራተኛው ላይ የሥነ ሥርዓት እርምጃ  ሰወስድ በግል  ለማህበሩ ማሳወቅ 
 3. በየበጀት ዓመቱ መጨረሻ  የአ/ማህበሩን  ትርፍና ኪሳራ ለመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበሩ  የማሳወቅ
 4. መሰረታዊ የሰራተኛ ማሕበሩንና አባላቱን የሚመለከት የቃልም ሆነ የጽሑ መልእክቶ ሲመጡ  መልዕክቱ  እንዲደርስ  የማድረግ ፡፡
 5. አጠቃላይ  የአ/ማህበሩን  ሠራተኞ የሚመለከት  አዳዲስ  የአሰራር ሲስተሞና አደረጃጀቶች ሲኖት ለሰራተኛ ሕበሩ  ያሳውቃል፡፡ ለውጡም ከዚህ ህብረት  ስምምነት ጋር የሚቃረን  መሆን የለበትም ሆኖም የፈረቃ ሥራ ለውጥ እንደ ከባድ  የስራ ለውጥ ሆኖ አይታይም፡፡
 6. የሠራተኛ ማህበራዊ  መሪ የሥራ አስፈጻሚ  ኮሚቴ  አባል በመሆኑ ሕጋዊ  መብቱን  ሲያስከብር  በማንኛውም  አኳኋን  አይደናቀፍም ወይም ህገዊ  መብቱን በማስከበር በሰራኛው  ላይ እርምጃ አይወስድም  እዲሁም በሠራኛው ማህበር መሪ እና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  አባላት ላይ  የተሞላው የሥራ በአፈጻጸም  ነጥብ ላይ በማህበር  ውስጥ ከመመደቡ በፊት ካለው  የሥራ አፈጻጸም  ቀንሶ ቢገኝ  አክሲዮን  ማሕበሩ  ከሰራተኛ ማሕበሩ ጋር ጉዳዩን መርምሮ  መፍትሔ የመስጠት፡፡
 7. ይህን  የሕብረት  ስምምነት ለማሻሻል ወይም ስለ አዲስ የሥራ  ሁኔታዎች ወይም የሰራተኞ መብት  ለማስከበር ለውይይት  መሠረታዊ  ሠራኛ  ማሕበሩ  ሲጠይቅ  አሰሪው የመቀበል ፡፡ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. አክ/ ማህበሩ  አቅሙ በፈቀደ  መጠን ለሰራኛው የሰርቪስ  አገልግሎት  ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን  ከዚህ በፊት  አክ/ማህበሩ  የሰርቪስ አገልግሎት  ሲሰጥበት ከነበረው የፋይናንስ  ወይም  የኢኮኖሚ አቅም ዝቅ ከላላ  በስተቀር  የነበረው ሰርቪስ  አገልግሎት ሊቋረጥ አይችልም፡፡  ሆኖም ግን ፎርማሊቲዎችን በተመለከተ  እደተጨባጭ ሁኔታው  እየጠጠና በየጊዜው ለውጥ  ሊደረግ  ይችላል፡፡ የአዲስ አበባ  ቅ/ማ/ጽ/ቤት  ሰራ የሚሰሩበት ቀናት  ጠዋትና ማታ  ብቻ በአዲስ አበባ  የከተማ  አውቶቡ ታሪፍ መሰረት ይከፍላል፡፡
 2. የመሰረታዊ  የሠራተኛ ማሕበሩ  ሠራኞች የመሰረታዊ ሠራተኛ  ማሕበሩ  አባል ለመሆን  የፈቀዱበትን ቅጽና  የሠራተኛውን  ፊማ የያዘ  ሰነድ/ማስረጃ / ለአክሲዮን  ማህበሩ ሲያቀርብ  የማህበርተኝነት  መዋጮን  ከወር ደመወዙ እየጠቆረጠ  በመሰረታዊ  ሠራተኛ  ማሕበሩ ስም  በተከፈተው  የባንክ  ሒሳብ  ገቢ በማድረግ  ያሳውቃል፡፡ ከማህበሩ  አባልነት  የሚወጡ ሰራኞ ሲያጋጥም  ለመሰረታዊ ማሕበሩ ሠራተኛው  አመልክቶ  ለመፍቀዱ  መሰረታዊ  ሠራኛ ማህበሩ ለአ/ማህበሩ  ሲያሳውቅ ተቆራጭ  አይቀንስበትም፡፡
 3. የመሰረታዊ  ሰራተኛ ማሕበር አባላት ልዩ ልዩ  የህብረት ስራዎች ለማቋቋ በሚፈልጉበት  ጊዜ እያንዳዳቸው በፈቃደኝነት የፈረሙበትን ስም ዝርዝር የገንዘብ ልክ በማህበሩ  ደብዳቤ አማካኝነት  ሲደርስ አክ/ ማህበሩ የተባለውን  ገንዘብ ከደመወዛቸው ላይ  ቀንሶ በዚሁ  አንቀጽ  ተራ ቁጥር  /4.420 በተገለጸው  መሠረት  ይፈጸማል፡፡
 4. በዚህ አንቀጽ ተ.ቁ  41.20 እና 4.1.21. መሠረት  በአክ/ማህበሩ  አማካኝነት ከሠራተኞች ደመወዝ በ እየጠቀነሰ  በማሕበሩ የባንክ  ሒሳብ ቄጥር ገቢ  የሆነውን  ገንዘብ ትክክለኛነቱን ማሕበሩ እንዲቆጣጠር አክ/ማህበሩ  ይፈቅዳል፡፡


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

    

 1. እያንዳንዱ ሠራተኛ  ስተመደበበት የሥራ መደብ  የሥራ ዝርዝር  /ጆብ ዲስክሪፕሽን/ በጽሑፍ  አክሲዮን ማሕበሩ አዘጋጅቶ ይሰጣል፡፡
 2. አክሲዮን  ማሕበሩ  ለሰራተኞች የጡረታ  ቁጥራቸውን ያሳውቃል፡፡ የጡረታ  ጊዜያቸው  ሲደርስ የጡረታ  አበል በጊዜው እንዲያገኙ  የማድረግ  ግዴታ አለበት፡፡ 
 3. የሰራተኛው የሥራ አፈጻጸም  በየአመቱ  በታህሳስ  መጨረሻና  ሰኔ መጨረሻ  ላይ ሁለት  ጊዜ  ይሞላል፡፡  በወቅቱም ሠራኛው በክፍሉ ውጤቱን እዲያወቅ ያደርጋል፡፡ ቅሬታ  ካለ በሥራ ሂደት ኃላፊው   ታይቶ  የሚጸድቅ  ወይም የሚሻሻል  ሆኖ ወደፊት  ዝርዝር አፈጻጸምና  መለኪያዎች የሥራ ደንብ  ያዘጋጃል፡፡
 4. አክሲዮን ማሕበሩ  በሕግ  ከታወቀው ሰራተኛ  ማህበር  ሌላ በውስጥም ሆነ በውጭ የማህበሩን  ሕልውና የሚቃረኑ ግለሰቦችን ወይም ሰዎን አይደግፍም ወይም አይነቅፍም፡፡
 5. አክሲዮን ማሕበሩን  የሚጎዳ  ነገር መከሰቱን በሠራተኛው ወይም በሌላ አካ ሲጠቆም አክሲዪን ማሕበሩ  አጣርቶ አስቸኳይ እርምጃ  ይወስዳል፡፡ 
 6. አክ/ ማህበሩ   ከሰራኛ ማሕበር አባላት የመሰርታዊ ሰራተኛ  ማሕበሩን በሚመለከት  የሚቀርብለትን ጥያቄ  አያስተናግድም፡፡
 7. አክ/ማህበሩ  ከሠራተኛው ደመወዝ ላይ ያለ  አግባብ ቀንሶበት ቢገኝ የተቀነሰበትን ገንዘብ በአንዴ ይከፍላል፡፡
 8. አሠሪው  ሠራተኞችን የመሰረታዊ  ሠራተኛ ማህበር አባል  እንዲሆኑ አይቀሰቅስም ጣልቃ በመግባትም ሆነ በማባባል ከመሠረታዊ ሠራተኛ  ማህበር  እንዲወጡ  አያደርግም፡፡

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. አክሲዮን ማህበሩ  የመሠረታዊ  ሠራኛ ማህበር  አባል  በሞንና ባለመሆን  በሠራተኛው  ላይ ልዩነት አይፈጥርም በመሠረታዊ  ሰራተኛ ማህበሩም ሕጋዊ  እንቅስቃሴ በማድረጉ  ምክንያት ጉዳት  አያደርስበትም፡፡  
 2. አክሲዮን ማህበሩ የመሰረታዊ  ሠራተኛ ማህበር አባል  በመሆንና ባለመሆን በሠራተኛ ማሕበሩም  ሕጋዊ እንቅስቃሴ  በማድረጉ ምክንያት ጉዳት  አያደርስበትም፡፡
 3. አ/ማህበሩ  የሥርዓተ ጾታን ጉዳይ በአመታዊ ዕቅዱ  ይዞ ይሰራል፡፡

አንቀጽ አምስት

 1. የመሠረታዊ የሰራተኛ ማህበሩ  መብትና ግዴታ ፡- 

ሀ/ የማህበሩ መብት 

1 በዚህ ስምምነት ውስጥ ስለተካተቱት  እና ሌሎች  ጉዳዮች  ሠራኛውን  ወክሎ  ከአሠሪው ጋር ሊነጋገር የሚችለው  የመሰረታዉ የሰራኛ ማህበር ብቻ ነው፡፡

 1. አ/ማህበሩ  የመዋቅር  ለውጥ ሲያደርግ በዝግጅትም  ሆነ በአፈጻጸም  ላይ የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበሩን  እንዲተባበር  ሱጠየቅ ሙሉ ተሳትፎ ማሕበሩ ያደርጋል፡፡
 2. በየንዑስ  ክፍሉ ሠራኞችን  የሚያስተባብሩ  የሚመሩ አንድ አንድ የሆርሻ ተጠሪዎች ተመርጠው ይሰራሉ፡፡
 3.  ሠራተኛውንም በምርት ስራ ተግተው  እንዲሰሩ  ይቀሰቅሳ የሰራኛውን ቅሬታ  እዚያው  ሥራ ቦታ  መፍትሔ  እንዳያገኙ ያደርጋሉ፡፡
 4. በአ/ማህብሩ  ውስጥ ያለው ሕጋዊ የመሰረታዊ  የሠራተኛ  ማሕበር  ጽ/ቤት  ሠራተኛውን  በሚመለከት  ጉዳይ ላይ ሕጋዊ  መግለጫ የመስጠት መብት አለው፡፡


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

ለ/  የማሕበሩ  ግዴታ፡

 1. ሠራተኛው  የሕብረት  ስምምነቱ  አንቀጾች ትርጉምና  አፈጻጸም  በሚገባ  እንዲረዳ  የበኩሉን ሁሉ  ያደርጋል፡፡
 2. ይህን ሕብረት  ስምምነት  ለማሻሻል ወይም ስለ አዲሱ የስራ  ሁኔታዎች ለውይይት  አሠሪው  ሲጠይቅ  ይቀበላል፡፡
 3. የሕብረት  ስምምነት ሕጎችና  መንግስታዊ መመሪያዎችን  መሠረት  በማድረግ  አሠሪው  የሚያወጣውን  አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችን እና  ዕቅዶችን  ለማስፈጸም  ማኔጅመንት  በሚያደርገው ጥረት ሁሉ ማሕበሩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
 4. በአክሲዮን  ማሕበሩና በሠራተኛው  መካከል አንዳድ ቅሬታዎች ሲፈጠሩ ጉዳዩን በውይይት ለመፍታና በመግባባት ለመፈጸም ማሕበሩ ሙሉ  ትብብር ያደርጋል፡፡
 5. የአ/ማህበሩ ምርት የበለጠ እድገት እንዲኖውና ትርፋማ እንዲሆን ሠራተኛውን  ማበረታታትና መቀስቀስ አለበት፡፡
 6. ለሰራተኛው የሚሰጡትን  የሚከፋፈሉ ምርቶች አክሲዮን ማህበሩ  በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት  በቅደም ተከተል እንዲፈጸም ክትትል ያደርጋል፡፡
 7. ሠራኛው በአ/ማህበሩ ላይ ቅሬታ  ኖሮት ይህንንም ለመውጣ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ  በዚህ ሕብረት  ስምምነት ላይ የመለከቱትን  የቅሬታ  አቀራረብ ስርዓቶች እንዲከተል ያደርጋል፡፡
 8. ማህበሩ ማንኛውም ሠራኛውን የሚመለከት ሕብረት ስምምነት  የጠጠቀሱትን ጉዳዮች በግሉ  ለማሻሻል  ለመሠረዝ  ወይል ለመለወጥ አይችልም፡፡ 

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. ማሕበሩ በአዋጅና  በህ/ስምምነት  የተደነገገውን የሠራኛ መብቶችና ግዴታዎች በአክሲዮን  ማሕበሩ ሰራኞች ዘንድ እንዲከበሩ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ወይም ወቅት  ስለ አ/ማህበሩ  እድገት እንዲሁም  ስለሚያጋጥሙ ችግሮች  የአሰራር ለውጥ ወይም ከነበረው  አደረጃጀት የተለየ ሌላ  አደረጃጀት ሲደረግ ሠራተኛ  ማሕበሩ ጉዳዩን  በጥልቀት  አውቆና ተረድቶ  ለአሰሪው ድጋፍ  ያደርጋል፡፡ 

አንቀጽ ስድስት

 1. የሰራተኛው መብትና ግዴታ 

ሀ/  የሠራተኛው መብት 

 1. ለሰራበት የሚከፈለው ደመወዝ ወይም አበል በወቅቱ  የማግኘት  መብት አለው፡፡ 
 2. ደመወዝ  የሚከፈለው ለሰራበት ወይም በሕግ  እንዲሠራ የተቀጠረበትን  ስራና ጊዜ ቢሆንም የድሮውን ፖስታ የማደል ሥራ አይከናወንም ሆኖም  ግን ጊዜን ማቴሪያልን  በማይባክን ሁኔታ ተቀናናሽ  ሂሳቦችን በግልጽ  በሚያሳይ  በተዘጋከ የመክፈያ  ሰነድ  አማካኝት  ሲጠይቅ  የማግኘት  መብት አለው፡፡
 3. ሠራተኛው ሳያውቅ  ወቀሳ ማስጠንቀቂያ  ቅጣት በግል  ማሕደሩ  ውስጥ አይቀመጥም  እንዲሁም  ሠራኛው በግል ማሕደሩ  ላይ ጥርጣሬ ሲኖረው እና ሲጠይቅ  መሰረታዊ  የሠራተኛ  ማሕበሩ  የአ/ማህበሩን አሰራር ጠብቆ የሠራተኛውን የግል ማሕደር  ማየት  ይችላል፡፡ 
 4. ማንኛውም ሠራተኛ  ጡረታ  የሚሞላበትን የሕይወት ታሪክ  ቅጽ  የትምህርት መረጃ  ወይም ሌላ  መረጃ  በጽሑፍ  ሲተይቅ ከማሕደሩ ከሚገኘው ቀሪ በራሱ ወጭ ፎቶ ኮፒ  አድርጎ የመውሰድ መብት አለው፡፡ 


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 157 ንዑስ አንቀጽ  1 እና በሀገሪቱ ሕጎች  መሰረት የሠራኛው ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች  የጠበቁ ናቸው፡፡ 
 2. በዲሲፕሊን  ችግር  ምክንያት ካልተወሰነበት በስተቀር  ሠራኛውን በስራ  ውሉ መሰረት  ከሚሰራበት ሥራ  ውሉ  ደረጃና  ደመወዝ  ዝቅ አድርጎ  ማሰራ የተከለከለ ነወ፡፡  ይሁን እንጂ  በጤና ምክንያት  መስራ ያልቻሉ ሰራተኞች  ዝቅ ባለ መደብ  ደመወዛቸውን ሳይነካ  የታዘዙትን እየሰሩ  እንዲያገግሙ ይደረጋል፡፡ ይሁን እንጂ ነገሩ  ዘላቂ ሆኖ ለአክሲዮን  ማሕበሩ  ጉዳት ካመጣ ግን በሐኪሞች  ቦርድ ውሳኔ መሰረት  ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ 
 3. አ/ማህበሩ አዲስ አደረጃጀት  በሚፈጥርበት ጊዜ አ/ማህበሩ   ለሰራኞ ተፈላጊውን  የትምህርት እና  የሥራ ልምድ መስፈርት ማደግ ምክንያት ሳያሟላ ቢገኝ  አክ/ማህበሩ  ሠራተኛውን ዝቅ ወዳለ  መደብ ባሟላበት  ደረጃ ሊመድበው ይችላል ሆኖም  ቀድሞ የያዘውን ደመወዝ አይቀነስበትም፡፡
 4. ሴቶች  የቅድ ካንሰር ምርመራ በአ/ማህበሩ ወጪ ምርመራ  ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ 
 5. ሴቶች በሕጋዊ  ሕክምና  እርግዝናቸው በጤናቸው ላይ ችግር  የሚፈጥር መሆኑ  በሐኪም  ሲረጋገጥ ውርጃ  እንዲፈጸም  ሲደረግ  ሴቷ የድህረ ወሊድ ፈቃድ  ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ/  የሰራተኛው ግዴታ 

 1.   ስለ አሠሪና ሰራተኛ ጉዳይ  የወጣ አዋጅ ተጓዳኝ  ደንቦች  ይህን የሕብረት ስምምነት   መሰረት   ወደ ፊት  የሚወጡትን  ማሻሻያዎችና  መመሪያዎች ተቀብሎ በስራ ላይ የማዋል፡፡
 2. ሠራተኛው ለተቀጠረበት ሥራ መላ ጉልበቱንና  ችሎታውን በማዋል የአክ/ማህበሩን  የሥራ ውጤት  እንዲዳብር በትጋትና  በጥንቃቄ የመስራት፡፡

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 


 1.   ሠራተኛው ሥራውን  ለማከናወን  በስራ ላይ  የሚገለገልባቸውን የአደጋ  መከላከያ ወይም  ማንኛውም መሳሪያ  ወይም ዕቃ  በጥንቃቄ ጠብቆ የመያዝ እና የማገልገል፡፡
 2. ለስራ ብቁ  በሆነ አእምሮና የአካል ሁኔታ በስራ ላይ መገኘት 
 3. በስራ ቦታ  በሕይወትና  ንብረት ላይ  አደጋ ሲደርስ  ተገቢውን  ዕርዳታ መስጠት 
 4. ራሱም ሆነ ጓደኞቹ አደጋ  ላይ የሚጥል  ወይም የአ/ማህበሩን አጠቃላይ  ጥቅም  የሚነካ ማናቸውም ሁኔታ ሲያጋጥም  በወቅቱ ለአሰሪ ማሳወቅ
 5. በአ/ማህበሩ ግቢ ውስጥ ሲጋራ ማጨስ ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ማጨስ ክልክል ነው፡፡
 6.   በአ/ማህበሩ  ስራ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሠራተኛውን  ሰብዓዊ ወይም መሰረታዊ የሥራ ሁኔታዎችን የሚለውጥ ሆኖ እስካልተገኘ ድረስ  በተመሳሳይ ስራ እንዲሰራ  የሚወጣውን መመሪያ  የመቀበል፡፡ 
 7. በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 67 ከ ሀ እስከ መ  በተጠቀሱት  መሰረት የትርፍ ሰዓት ሥራ  እንዲሠራ ሲታዘዝ የመስራት፡፡
 8. የአክሲዮን  ማሕበሩን  የኢንዱስት ሰላም የሚያውክ የሀሰት ወሬና  ውዥንብር  ከመንዛትና ጠብ አጫሪነት  ማጽዳት፡፡
 9. ሁል ጊዜ የራሱንና የአክሲዮን  ማሕበሩን ስም በመጠበቅ መልካም ጸባይ መያዝ 
 10. አክሲዮን ማሕበሩ  ካልፈቀደ  በስተቀር በስራ ቦታ በሥራ ጊዜ ልዩ ልዩ  ሕትመቶችን መጽሐፎችን ማስፈረሚያ ሊስቶችን  የመሳሰሉትን  ማል መለጠፍ  ማዞር ፈጽሞ ከለከለ ስለሆነ ይህንን አለመፈጸም፡፡


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. አክሲዮን ማሕበሩ ሳያውቅ በስራ ሰዓትም ሆነ በእረፍት  ጊዜው  በአክሲዮን  ማሕበሩ ግቢ  ውስጥ ስብሰባ ማድረግ  የተከለከለና ሕገ ወጥ ስለሆነ ይህን መፈጸም አለበት፡፡
 2. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ  መንገድ ከአክሲዮን  ማሕበሩ  ደንበኞች ወኪሎቻቸው ወይም ከማናቸውም ተገልጋይ ከሚሽን ማማለጃ ወይም ጉቦ አለመቀበል፡ 
 3. ስካር እና አእምሮን የሚያደነዝዙ ዕጾችን  ተመርዞ በስራ ቦታ መገኘት  የሚያስቀጣ መሆኑን መረዳ ማንኛውም ሠራተኛ ከአቅም በላይ  መሆኑ ሲታመንበት ካልሆነ በስተቀር አስቀድሞ ፈቃድ ሳይሰጠው ከመደበኛ ስራው ላይ መቅረት  አይገባውም፡፡
 4. በስራ ሰዓት ያለፈቃ ሥራውን ትቶ ከክፍል ወደ ክፍል  ከስራ ቦታ ውጭ አለመዘዋወር፡፡
 5. ስለ ጤና  አጠባበቅ  እና አደጋ  መከላከል በአክሲዪን ማሕበሩ የሚመጡትን  መመሪያዎች አክብሮ በጥንቃቄ ስራ ላይ ማዋል፡፡
 6. ድምጽ ያለውም ሆነ ድምጽ የሌለው የጦር መሳሪያ  ወደ አክ/ማህበሩ  ይዞ መግባት  የለበትም፡፡ ሕጋዊ ፈቃድ  ቢኖረውም  እንኳ ለጥበቃ አስረክቦ  መግዛት አለበት፡፡ 
 7. የጠቀጠረበትን ስራ በተወሰነው የሥራ ሰዓት ተገኝቶ የመስራት፡፡
 8. በስራው  ላይ የቅርብ አለቃውን  ትዕዛዝ የመፈጸም 
 9. ያለ በቂ  ምክንያት ወይም  ከአለቃው  ፈቃድ ሳይቀበል ከስራ አለመቅረት
 10. በአ/ማህበሩ  በቋሚነት  ከተቀጠረ በኋላ የሥራ ውል ሳያቋርጥ  በሌላ መ/ቤት  በቋሚነት  ተቀጥሮ አለማገልገል፡፡

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 


 1.  በስራ ሰዓት በተገቢው  ኃላፊ ሳይታዘዝ  በውጭ ሰው ወይም  ድርጅት  ስራ አለመስራት 
 2. ማህበሩ  ሳያውቀው  ሰራተኞን አቀነባብሮ በስራ ቦታና ጊዜ ማስፈረምና ተፈራርሞ ለአ/ማህበሩም ሆነ  ለማሕበሩ ማቅረብ  ሕገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡
 3. ሰራተኛው የሚሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ  መሳሪያዎችን መጠቀም  ግዴታው ነው፡፡
 4. ሰራተኛው  የሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓቶችን  የማክርና ያለፈቃድ መደበኛ ስራውን ትቶ  መቅረት  የተከለከለ ነው፡፡ 
 5. ሠራተኛው ሥራውን ትቶ  መተኛት በግቢው ውስጥና በሌሎች ቦታዎች መዘዋወር  እንዲሁም  የሚሰሩ ሰራተኞች  ስራ ማስፈታት  የተከለከለ ነው፡፡
 6. ሠራተኛው በተዋድ በአ/ማህበሩ  የሥራ ኃላፊዎች ዘንድ ዪሰጠውን መመሪያ  ተቀብሎ  የመስራት ግዴታ  አለበት፡፡
 7. በማንኛውም ሁኔተ  በአ/ማህበሩ  ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ያ ፈቃ መገልገል ወይም ሕጋዊ   ማስታወቂያ መቅድ ወይም መሰረዝ  እርምጃ ያስወስዳል፡፡
 8. ሰራተኛው  ከስራው ጋር በተያያዘ ምክንያት  አክ/ማህበሩ የምስክርነት  ቃል እንሲሰጥ ሲጠይቀው  የመተባበር ግዴታ  አለበት፡፡
 9. አክ/ማህበሩ  ወደፉት  ምርታማነትን ለማሳደግና ጥራትን  ለማሻሻል የሚቀምባቸውን አዳስ የአሰራር ስርቶች ስለሚኖ ተቀብሎ የመፈጸም  ግዴታ ይኖርበታል፡፡
 10. ማንኛውም ሠራኛ ከተፈቀድ የሻይና የምሳ ፕሮግራም ውጭ ሻይ ቤትና  ምግብ ቤት ቁጭ ብሎ መገኘት በሕግ ያስቀጣል፡፡
 11. አንድ ሰራተኛ  ቋሚ  ዝውውር  ሲፈጸምለት ከነበረበትና ከሚሄድበት  የሥራ ቦታ ላይ የሚገኙትን  የደንብ ልብስና  የደጋ መከላከያዎች ሁሉን  

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

የማግኘት  መብት የለውም  ማግኘት የሚገባው  በቋሚነት የተዘዋወረበትን የስራ መደብ  ጥቅማ ጥቅም ብቻ ነው፡፡

 1. ከዚህ በላይ  የተመለከተውን ግዴታ  የማያከብር ሰራተኛ  በሕጉ ወይም በዚህ ሕብረት  ስምምነት  የተመለከቱት የሥነ  ስርዓት  እርምጃዎች  ይወስዱበታል፡፡ 
 2. በአ/ማህበሩ በተዘጋጀው  የሥርዓተ ጾታ መመሪያ አንቀጽ  9 እና 10 የተዘረዘሩትን  የመፈጸም  ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ ሰባት

 1. በድርጅቱ  ውስጥ ስሚደረግ  ዝውውር 
 1. ሰራተኛው ለአክሲዮን ማሕበሩ ሊሰጠው የሚችለው  ጠቀሜታ  ሲታመንበትና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ  አክሲዮን ማህበሩ 
 2.   ሰራተኛው  በስራ ላይ የሚፍጽመው ጥፋት  በህ/ስምምነቱ መሰረት  ከስራ የሚያስወጣ ሆኖ ሲገኝ  አክሲዮን ማህበሩ  እንደአስፈላጊነቱ  ለማሻሻል  ከፈለገ ከፍተኛውን ቅጣትና  የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ  በመስጠት በተገኘው የስራ ቦታ  አዛውሮ ማሰራት ይችላል፡
 3. በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ በተመሳሳይ ደረጃ የሚሰሩት  ስራ ተዛማጅ ሆኖ  ሲገኝ  በሥራ መደቡ ላይ የተመደቡትን ሠራተኞች  የያዙትን የሥራ መደብ እንዲለዋወጡ ሲስማሙና አክ/ማህበሩ  ሲፈቅድ ሊዘዋወሩ ይችላሉ፡፡
 4. አክ/ማህበሩ  በአንድ የሥራ ሂደት ውስጥ ትርፍ የሰው ኃይል  ሲኖረው በዚህ  ስምምነት ተ.ቁ 1 ላይ  የተጠቀሰውን  ሳያጓድል ወደ ሌላ ቦታ  ሊያዘዋውረው ይችላል፡፡
 5. ስራው የማይበደል መሆኑ  ከታመነበትና  ቦታ ከተገኘ በሠራተኛው ጥያቄ  አክ/ማህበሩ ሲፈቅድ ሰራተኛውን  ከፈረቃ ወደ ፈረቃ   ከኬዝ 

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

ቲም ወደ ኬዝ ቲም  ከስራ ሂደት ወደ ስራ ሂደት  በዚህ ስምምነት  ተራ ቁጥር  1 ላይ  የተጠቀሱትን  ሳያጓድል ሊያዘዋውረው ይችላል፡፡

 1. ሰራተኛው ከባ/ዳር  ውጭ አዲስ አበባ  ማ/ጽ/ቤት  እና ወደፊት  አክ/ማህበሩ  በሚከፍታቸው የሽያጭ  ጣቢያዎች  ሠራኞን ማሰራ ሲፈልግ  በዚህ አንቀጽ ተ.ቁ 7.1. ላይ የተጠቀሱትን ሳያጓድል  አዛውሮ  ማሰራት ይችላል፡፡  ዝውውሩ  በአክሲዮን ማሕበሩ አነሳሽነት የተፈጸመ  ከሆነ የውሎ አበል  የትራንስፖርትና  የጓዝ  ማንሻ  ክፍያ ይፈጽማል፡፡  የጓዝ  ማንሻውም ክፍያ ከ8/ስምንት/ኩንታል  ሂሳብ ይሆናል፡፡ ይህም ተፈጻሚ የሚሆነው ሕጋዊ  ደረሰኝ ሠራተኛው ሲያቀርብ ነው፡፡
 2. በአ/ማህበሩ  ውስጥ አንድ የስራ መደብ  ሲለቀቅ  ወይም ሲከፈት  በቅድሚያ  ለዚሁ  ብቁ  ነው ተብሎ  የታመነበት ሰራተኛ ወይም በሐኪሞች  ቦርድ የስራ አካባቢ ለውጥ የታዘዘለት ሰራተኛ  ካለና  መስፈርቱን  ያሟላ ነና ከተፈቀደለት  በክፍት የስራ መደቡ ላይ ይመደባል፡፡

አንቀጽ ስምነት

 1. የደረጃ ዕድገት 
 1. በአክሲዮን  ማህበሩ  ክፍት የሥራ መደብ ሲፈጠር ከውጭ  ከመቀጠሩ በፊት  ለውስጥ  ሰራተኞች የሥራ መደቡ  የሚጠይቀውን  መመዘኛዎች የሚያሟሉ መኖራቸውን  ለማጣራት  ለ 7 ቀን ያህል  የሚቆይ  ማስታወቂያ  ይወጣል፡፡ የማስታወቂያው  ግልባጭ ለሰራተኛ ማህበሩ  ይሰጣል፡፡  የመወዳደሪያ ጊዜ  ካለፈ በኋላ ሌላ  ምዝገባ አይፈቀድም፡፡ ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

/  ለአ/ማህበሩ  ስራ አክሲዮን ማህበሩ አካባቢ ውጭ የሄደ  ሠራተኛ ለክፍት  ቦታው የሚመጥን  ከሆነ አ/ማህበሩ  በውድድሩ እንዲገባ ያደርጋል፡፡ 

/በሕጋዊ ፈቃድ  በሥራ  ላይ ያልተገኘ ሠራተኛ  ከሆነ ግን  ለክፍት ቦታው የሚመጥን ሆኖ ከተገኘ በወኪሉ  /በሚመለከተው/ ሰው  አማካኝነት ሊመዘገብ ይችላል፡፡ 


 ሀ/ለክፍት  የሥራ መደቡ  ብቁ ሊሆን የሚችሉ  ሠራተኞ መኖራቸው ከተረጋገጠ  የማህበሩ ተወካይ በአባልነት  በሚገኝበት  ኮሚቴ  በማወዳደር ብልጫ ያለው  ሠራተኛ በዕድገት እንዲመደብ ይደረጋል፡፡

/ በአ/ማህበሩ  መስፈርት መሰረት  ለውስጥ ሰራተኞ ማስታወቂያ አውጥቶ  የሚያሟሉ ሲጠፋ  ለውጭ ይጋብዛ ይህ ሁሉ  ተሞክሮ ከጠፋ በሕብረት ስምምነቱ አንቀጽ 8  ስለ ዕድገት  አሰጣጥ አፈጻፀም  ከተደነገገው  በተጨማሪ ለሥራ መደቡ  መሰረት  መመደብ  አክ/ማህበሩ  የራሱን አማራጭ ይጠቀማል፡፡ የቅጥር ወይም  የዕድገት አፈጻጸም  በዋና ሥራ አስፈጻሚ  ውሳኔ ሰጭነት ይፈጸማል፡፡

/ ለአንድ ክፍት የሥራ መደብ የእድገት ማስታወቂያ ወጥቶ ምዝገባ ከተካሄደ በኋላ ዕድገት ሳይታይ 3 ወር ከሞላው ሌላ የዕድገት  ማስታወቂያ ካላወጣ  በስተቀር ለመወዳደሪያነት አያገለግልም ፡፡

/ የአ/ማህበሩ  ሠራተኞ ዕድገት  ከታየ በኃላ የተወዳዳሪዎች  ውጤት  በድርጅቱ  ማስታወቂያ  ሰሌዳ ላይ ይለጠፋል፡፡ 


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

/ አግባብ ያለው የሥራ ልምድ ማለት ክፍት  የሥራ መደብ  ማስታወቂያ  የወጣበት የስራ  መደብ ደረጃ ዝቅ ብሎ ያ መስመሩን ጠብቆ /ተከትሎ/ የሚገኝ  ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ  የዢህን አፈጻጸም  በተመለከተ አክ/ማህበሩ  ሊከተለው የሚገባ አግባብ ያው የሥራ ልምድ መመሪያ ተቀርጾ  እንዲጸድቅ ይደረጋል፡፡

ረ/ በአጠቃላይ የደረጃ ዕድገት  ውጤታቸው እኩል የሚወጡ ሠራኞችን ለመለየት ኮሚቴው ፈተና እንዲሰጥ ለማድረግ ይችላል፡፡

ሰ/  የደረጃ  ዕድገት የሚያገኙ  ሠራተኞ የደመወዝ ለውጥ የሚያገኙት  አጽዳቂው  ካጸደቀበት ቀን ጀምሮ  ይሆናል፡፡ 

ለሁሉም ደረጃ እድገቶች  ከ30  የሚታረም  የሚወዳደሩበትን  ሥራ በተመለከተ ፈተና ይወጣል፡፡ ከዚህ  ውስጥ 15 እና ከዚያ በላይ  ያመጡ ብቻ ተመርጠው  ውጤታቸው ከሌላ መስፈርት ጋር ተደምሮ በተገኘው ነጥብ አሸናፊው  ይለያል፡፡ ይሁን እንጂ  ፈተናው ከ15 በታች ያገኘ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ 

ሴት ሰራተኞች ወደ አመራር/ለኃላፊነት/ በሚወዳሩበት ጊዜ ውጤታቸው ላይ  በተጨማሪ 5  ነጥብ  ይጨመርላቸዋል፡፡

 የደረጃ እድገትና  የሚያስከትለው  የደመወዝ  ጭማሪ  በአ/ማህበሩ  ክፍት የሥራ መደብ ሲፈጠር ከውጭ ከመቀጠሩ በፊት ካሉት  ሠራተኞች መካከል  የሥራ መደቡ  የሚጠይቀውን  መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ሰራተኞች  በደረጃ ዕድገት  በማወዳደር ይመደባል፡፡ ውድድሩና አፈጻጸሙ  በህብረት ስምምነቱ  መሰመረት ሆኖ የደመወዝ አከፋፈሉ ስርዓት የሚከተለውን መምሰል ይገባዋል፡፡ 


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

ሀ/ ቀድሞ የሚገኘው  ደመወዝ ካደገበት  ቦታ መነሻ ደመወዝ እኩል ወይም በልጦ ከተገኘ የደመወዝ እስኬል  ታይቶ  የሚቀጥለውን እርከን  ያገኛል፡፡

ለ/ ቀድሞ  የሚያገኘው ደመወዝ ከደረጃው መነሻ በታች ከሆነ መነሻውን ያገኛል፡፡ 

 1.   ሠራተኛውን በእድገት ለመመደብ የሚኖሩት  የማወዳደሪያ  ሚን የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ/ ለትምህርት  30%

ለ/ አግባብ ላለው የሥራ ልምድ 30%

ሐ/ የሥራ አፈጻጸም  20%

መ/ ለአገልግሎት  15%

ሠ/ለማህደር ጥራት 

ጠቅላላ ድምር 

ቢሆንም ይህ ወደ 70%  ይለወጣል፡፡ የጽሑፍ ወይም ፈተና ከ30  ይወሰዳ አፈጻጸሙ ከላይ በተራ ቁጥር “ሸ”  መሰረት  ይፈጸማል፡፡ 

ሳሰቢያ፡- 

 1. ለትምህርት  የጠሰጠውን ነጥብ ለተጠየቀው የሥራ መስፈርቱን አሟቶ ከተገኘ መጀመሪያ  እኩል ነጥብ  ከተጠየቀው  ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ  በላይ ያለው ቢወዳደር  ለዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ  የሚያሰየጠውን ነጥብ ሳይሆን  በትምህርት ዝግጅቱ  ሊያሰጠው የሚገባውን ያገኛል፡፡ 
 2. አግባብ ያለው  የሥራ ልምድ  አያስፈልግም  ተብሎ የሥራ ደመብ በውድድሩ ወቅት ከተወዳዳሪዎች  ልምድ ቢቀርብ  የማወዳደሪያ ነጥብ አያሰጥም፡፡
 3. ሠራተኛው ላደገበት የሥራ መደብ ከዚህ በታች  የደመወዝ እስኬል ሰንጠረዥ መሰረት ይፈጸማል፡፡


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን  ማህበር  የደመወዝ እስኬል እርከን ጭማሪ 

ደረጃ

መነሻ 

1ኛ

2ኛ

3ኛ

4ኛ

5ኛ

6ኛ

7ኛ 

8ኛ

9ኛ

10ኛ

17

13118

13774

1074

14483

15186

15186

16845

16845

15845

16741

16743

16

9085

9537

13118

13774

13744

14483

14483

15166

15943

15945

15945

15

28816

9047

9083

9537

13118

13774

17774

14463

14463

5186


14

6987

7336

8616

9047

9083

9537

13118

13774

13774

14463

14463

13

6799

6089

6987

7336

8616

9047

9063

9597

13110

13774

13774

12

4838

5079

5799

6869

6987

7396

8518

9047

9083

9537

13118

11

1417

3640

4838

5079

5799

6089

6967

7336

8615

9047


10

1663

3111

3467

3840

4838

5070

5799

6089

8967

7335


9

1375

2493

1618

3111

3467

3640

4836

5079

6779

6089

6987

8

1375

1986

1438

2493

2963

3111

3467

3645

4838

50

5779

7

1891

1697

1240

1966

2375

2493

2967

3111

3464

3640


6

1616

1510

1066

1697

1891

1966

2375

2490

2963

3111


5

1438

1302

1994

1510

1616

1697

1891

1966

2375

2483


4

1240

1119

1961

1302

1438

1510

1616

1597

1991

1966


3

1066

1034


1119

1240

1302

1438

1510

1891

1897994

1974


1043

1068

1119

1240

1302

1614

1510


2

928

1926


1974

1994

1043

1956

1119

3812

1302


1

915

928

961

974

994

1043

1866

1119

1240

1302

1438


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. ስራ ችሎታ 

ሀ/ ለስራ ችሎታው የተመደበው ነጥብ የሚሰጠው በዚህ ህብረት ስምምነት  አንቀጽ 8 ተራ ቁጥር  8.14 መሰረት  ይሆናል፡፡ 

ለ/ በዚህ ህብረት ስምምነት አንቀጽ 14 ከተጠቀሰው ውጭ በዕድገት ውድድርም ከሆነ በሌላ ጊዜ ተሞልቶ  የሚቀርብ የሥራ አፈጻጸም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም፡፡

ሐ/ በአንድ ዓመት  ሁለት ጊዜ  የታህሳስ ወር መጨረሻና ሰኔ ወር መጨረሻ /የሰራተኛው የሥራ አፈጻጸም መመዘኛ በአግባቡ ተሞልቶ በአ/ማህበሩ  ውስጥ መቀመጡን የአክሲዮን ማሕበሩ  የሰው ኃይል  አስተዳደር ደጋፊ  የሥራ ሂደት  ያረጋግጣል፡፡ 

መ/ የሠራተኛው የስራ አፈጻ መመዘኛ በሰራተኛው የግል ማህደር ውስጥ ተሞልቶ  ባይገኝ በአጥፊው ላይ በዚህ ሕብረት  ስምምነት የተጠቀሰው የሥነ ስርዓ እርምጃ ይወሰዳል፡፡  የሠራተኛው ያልተሟላ  የሥራ አፈጻጸም  መመዘኛ በዚህ  ሕብረት ስምምነት አንቀጽ 142 

መሰረት  የሰራተኛ ተወካይ ባለበት  ተሞልቶ እንዲቀርብ  የአክሲዮን ማህደሩ የሰው ኃይል አስተዳደር ሰደ ደጋፊ የሥራ ሂደት ያደርጋል፡፡

 1. ለትምህርት ደረጃ  

ተመደበውን ነጥብ  የሚሰጡት የዕድገት ኮሚቴ  አባላት ናቸው፡፡  ይኸውም  ከተወዳሪዎች  የግል ማሕደር  የሚገኘውን የትምህርት  ማስረጃ መሰረት  በማድግ ሲሆን  የነጥብ አሰጣጡም ቀጥሎ በተመለከተው ሁኔ ይሆናል፡፡ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

/ አሁን  በስራ ላይ የዋለው  የBPR የተፈላጊ  ችሎታ መስፈርት  አሰራር አስቸጋሪነቱ በበቂ ጊዜ  ተፈትኖ ሲረጋገጥ አ/ማህበሩ  እያጠና ወይም እያስጠና በሚመለከተው አካ ሲጸድቅ  ስራ ለይ ይውላል፡፡  ይህም ተግባራዊ  እስከሚሆን  ድረስ በስራ ላይ ያለው ተፈላጊ ችሎታ  መስፈርት ስራ ላይ ይውላ፡፡

ለ/ ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች  መካል ለቦታው ለተጠየቀው የትምህርት  ማስረጃ ላይ  የትምህርት  ደረጃ ያለው  ተወዳዳሪ ሙሉውን  30  ነጥብ ያሰጠዋል፡፡ ለቀሩት  ተወዳዳሪዎች  ለአንድ የትምህርት  ዘመን ልዩነት  ሁለት ነጥብ  ያስቀንስባቸዋል፡፡ 

ሐ/  የክፍሉን ትምህርት  ሙሉውን  ዓት ተከታትለው  ላልጨረሱ ተወዳዳሪዎች ያላጠናቀቁበት ክፍል  6 ወር  ከቀረው ማስረጃ ከት/ቤት ካመጣ/ች  ከውድድሩ አይታገዱም፡፡  የብሔራዊ  ፈተና ተፈትነው የወደቁ ሰራኞች  እንዳጠናቀቁ ተቆጥሮ  ይያዝላቸዋል፡፡ 

ይሁን እንጂ  ለአንድ ዓይነት  የት/ዲሪጃ  ሁለት የምስክር ወረቀት የሚቂርቡ ተወዳዎች  ድርብ ነጥብ አያሰጥም  ትምህርታቸውን ሳያጠናቅቁ በተሰጠው እድል አሸናፊ  ቢሆኑም ማስረጃችውን እስኪያቀርቡ ድረስ  በተጠባባቂነት ይመደባሉ፡፡  ሆኖም  መረጃቸውን  ሲያቀርቡ ያለተጨማሪ ውድድር ለስራ  መደቡ የተፈቀደውን  የደመወዝ  ስኬል/እርከን/ ያገኛሉ፡፡ 

መ/ ሰራተኛው  በእድገት በፊት በመደበኛ  የቀንና የማታ ያገኘውን የትምህርት ማስረጃ በግል  ማሕደሩ ምዝገባው  እስከሚጠናቀቅበት ድረስ   ካላያያዘው ተቀባይነት የለውም 


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 ሠ/ ሰራተኛው  በአገር ውስጥም  ሆነ በውጭ አገር በተልዕኮ ትምህርት ተምሮ የትምህርት  ማስረጃውን አቻ ግምት በትምህር ሚኒስቴር  አረጋግጦ  በግል ማሕደሩ  ማያያዝ አለበት ይህ ን ካላደረገ ተቀባይነት የለውም፡፡

ረ/  በአጠቃላይ  የደረጃ  ዕድገት  ውጤታቸው በማንኛውም በኩል  ታይቶ  የሚበላለጡበት ሁኔታ  ከሌለ ኮሚቴው  ፈተና ሰጥቶ ሊለያቸው ይችላል፡፡

 1. በአግልግሎት ዘመን 

አገልግሎት ዘመን  ነጥብ የሚሰጡት የዕድገት  ኮሚቴ  አባላት ናቸው፡፡ ዝርዝር  አሰራሩም ከተወዳዳሪዎች  የግል ማሕደር  በሚገኘው  ማስረጃ ሲሆን  አገር ውስጥ በሚገኙ  በሌላ መንግስታዊ ያልሆኑ   መ/ቤቶች እና የግል ድርጅትም  የተሰጠ ሕጋዊና ብቁ ለሆኑ አገልግሎት  በዚሁ መሰረት ነጥብ ይሰጠዋል፡፡ ይኸውም 

ሀ/ ከቀረቡት  ተወዳዳሪዎች  መካከል ከፍተኛ አገልግሎት  ላለው ተወዳዳሪ  ሙሉውን ነጥብ ይሰጠዋ የቀሩት  ተወዳዳሪዎች ከዚሁ በመነሳት ድርሻቸው እየሰላ ይሰጣቸዋል፡፡ 

ለ/ የቀረቡት ተወዳዳሪዎች  ሁሉ ተመሳሳይ  አግልግሎት  ካላቸው  ለእያንዳንዳቸው  ሙሉው 15 ነጥብ  ይሰጣቸዋል፡፡ 

ሐ/ በመንግስት ድርጅት ተቀጥረው  የነበሩ  ተወዳዳሪዎች  የሥራ ግብር  የማይጠይቅ ሲሆን  ከግል  ድርጅቶች የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች  ብቻ የሥራ ግብር  ለመክፈላቸው ይጠየቃሉ፡፡ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. አግባብ ያለው  የሥራ ልምድ 

ሥራ ልምድ ነጥብ  የሚሰጡት  የዕድገት ኮሚቴ  አባላት ናቸው፡፡ ዝርዝር አሰራሩ ተወዳዳሪዎች  የግል ማሕደር በሚገኘው ማስረጃ  ሲሆን አገር ውስጥ በሚገኙ ከሌሎች  መ/ቤቶችና  ድርጅቶችም  ለተገኘ የሥራ ልምድ ሕጋዊ  ብቁ መሆኑ ሲረጋገጥ በዚሁ መሰረት  ይሰጠዋል፡፡ በተጨማሪም  ለተመሳሳይ ሙያ  በውጭ  አገር ለተገኘ ልምድ ሕጋዊነት  እየጠረጋገጠ ይሰጠዋል፡፡ 

ሀ/  ከቀረቡት  ተወዳዳሪዎች  መካከል በወጣው የደረጃ  ዕድገት  ማስታወቂያ  መሰረት ከፍተኛ  የሥራ ልምዱ  ላለው ተወዳሪ ሙሉው 30 ነጥብ ይሰጠዋል፡፡ የተቀሩት ተወዳዳሪዎች  ከዚህ በመነሳት  ድርሻቸው ይሰጣቸዋል፡፡ 

ለ/ የቀረቡት ተወዳዳሪዎች  ሁሉም  ተመሳሳይ  እኩል ዓመት  የሥራ ልምድ  ካላቸው ለእያንዳንዳቸው ሙሉ ነጥብ  ይሰጣቸዋል፡፡

ሐ/ በማስታወቂያ  በወጣው  ክፍት የሥራ  መደብ መስፈርት  መስመሩን የተከተለ /አግባብ  ያለው/  ከትምህርት  ዝግጅት  መሻሻል  በፊት የሚፈለገውን ዝቅተኛ  የትምህርት   ይዘት  የሰሩበት  የሥራ ልምድ  በቀጥታ  ሊያወዳራቸው  ይችላል፡፡ በደረጃ  ዕድገት   ወቅት ከአጠቃላይ ውጤት  ላይ ለሱቶች   3 ነጥብ  ተጨምሮላቸው ከወንዶ  ጋር እኩል  ከሆኑ  ቅድሚያ  ከፍተኛ የላቀ  የት/ደረጃ ላለው  ተመሳሳይ ሆነው  ከተገኙ  ከፍተኛ አገልግሎት  ላለው ይሰጣል፡፡ 

ይህ  ተከናውኖ እኩል  ሆነው  ከተገኙ የዕድገት  ኮሚቴው  ፈተና በመስጠት  ይለያቸዋል፡፡ 


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

መ/ ለአንድ የሥራ ደረጃ ለመወዳደር ብቁ  የመሆነው የሶስት ጊዜ  የሥራ አፈጻጸም  አማካኝ 3.5.  እና ከዚያ በላይ ሲሆን ነው፡፡ የሶስት  ጊዜ የሥራ  አፈጻጸም ከሌለው  ምክንያቱ  ተጣርቶ አሳማኝ   ከሆነ  የሁለቱ  አልያም የአንድ ጊዜ  የአፈጻጸም ውጤት ብቻ  ይያዝለታል፡፡  በአንድ ማስታወቂያ  በሚወጡ ውድድሮች  መመዝገብና መወዳር የሚቻለው በአንዱ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን ለእያንዳንዱ  ውድድር አግባብ ያለው  የሥራ ልምድ በስራ ደንቡ ላይ  ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡  ሠራተኛውም  ቀድሞ  እንዲያውቀው  ያደርጋል፡፡ 

 1. ለግል ማሕደር  ጥራት 

ግል ማህደር  ጥራት   የተመደበውን ነጥብ  የሚሰጡ የደረጃ  እድገት ኮሚቴው  አባላት ናቸው ይኸውም፡- 

/ ማስጠንቀቂያና ገንዘብ ቅጣት ያለበት     5 ነጥብ ያስቀንሳል 

ለ/ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው   1 ነጥበ ያስቀንሳል 

ሐ/ የገንዘብ ቅጣት የተቀጣ   2 ነጥበ ያስቀንሳል 

መ/ ማስጠንቀቂያና የገንዘብ ቅጣት የሌለበት 5ነጥብ ያሰጠዋል 

በዚህ  ላይ ጥፋት  የምንላቸው ከላይ  በፊደል ሀ  በተጠቀሰው 8 ወር  በፊደል  “ለ” እና “ሐ”  ለተሰረዘሩት  ደግሞ 6 ወር እስኪሞላው  ድረስ ተፈጻሚ  ይሆናል፡፡ ሆኖም ውድድሩ ከመካሄዱ  በፊት አልባሳት የ ያላገኙ  የዲሲፕሊን  ክስ ከውድድር አያሳግድም፡፡

 1. የዕድገት  ተፈጻሚነት 

በዕድገት  የተመደበው  ሠራተኛ በዕድገት የሚያገኘው  ደመወዝ  ማግኘት  የሚችለው ማጽደቅ  ለሚገባው ኃላፊ  ቀርቦ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ  ይሆናል፡፡ 

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

በዕድገት  የተመደበ ሠራተኛ  በሶስት ወር ጊዜ  ውስጥ በዕድገት  ላገኘው ስራው ብቁ  ሆኖ ካተገኘና በቅርብ  አለቃው ተገምግሞ ማረጋገጫ/ማስረጃ ጀቀረበ ወደ ቀድሞ  ቦታው  ወይም  በተመሳሳይ ቦታ  ቀድሞ  በነበረበት ደረጃና ደመወዝ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡ 

 1. የሰው ኃይል  አስተዳደር ደ/የሥራ ሂደት  ባወጣው የደረጃ ዕድገት  ማስታወቂያ  መሰረት ከቀረቡት  ተወዳዳሪዎች መካል ተፈላጊውን የት/ደረጃና የሥራ ልምድ  ሌላም የሥራ መደቡ የሚጠይቀውን ልዩ ልዩ ሙያ አሟልተው የተገኙትን  ሠራተኞች  መርጦ አስፈላጊ ከሆኑ ማስረጃዎች ጋር የሰው ኃይል  አስተዳደር  ኬዝ ቲም አስተባባሪው ለዕድገት  ኮሚቴ  ያቀርባል፡፡ 
 2.  የዕድገት ኮሚቴ  ዕድገቱን  መርምሮ የውሳኔ አስተያየቱን  የመወሰን ስልጣን ላለው  አካል ከአቀረበ በኋላ ከአቅም  በላይ ካልሆነ በስተቀር በ7 ቀናት ውስጥ መልስ  መስጠት  አለበት፡፡
 1. የደረጃ ዕድገት  ለመወዳደር ስለሚቀርቡ ሠራተኞች

ሀ/ ከፍተኛ ወይም ተመሳሳይ  የሥራ ደረጃ  ያለው ሰራተኛ  በዝቅተኛ ወይም በተመሳሳይ የሥራ  ደረጃ ሊወዳደር አይችልም፡፡  ዝቅተኛ የሥራ  ደረጃ ያለው  ሰራተኛ ዕድገት የሚካሄድበት  ቦታ ከሚያስከፍለው መነሻ  ደመወዝ በላይ  ቢያገኝም መወዳደር  ይችላል፡፡ 

ለ/ ለሙከራ  ጊዜ  የተቀጠረ ሠራተኛ  የሙከራ  ጊዜወን  ካልጨረሰ ለዕድገት መወዳደር  አይችልም፡፡ 

ሐ/ ለዕድገት  የወጣውን  ክፍት የሥራ መመዘኛ  ያሚያሟላ  ማንኛ ሠራተኛ  ለውድድር መቅረብ ይችላል፡፡

መ/ አንድ  ሠራተኛ የደረጃ  ዕድገት ካገኘ  በኋላ  ቢያንስ  9 ወራት  ሳያገለግል ሌላ  አዲስ ዕድገት ሊወዳደር  አይችልም፡፡ ሆኖም  ተወዳዳሪ  ከሌለ ግን  ዕድገቱን  ካገኘ ከ 6 ወር በኋላ  ሊወዳደር ይችላል፡፡ 

   ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

የደረጃ ዕድገት  ኮሚቴ ስለማቋቋም፡-

6.1.  በሥራ  መሪነት  የታቀፉት ጊዜ ቲም  አስተባባሪዎ ፈቃድ  መሪዎች ተጠሪነታቸው ለዋና ሥራ አስፈጻሚ  የሆኑ አገልግሎቶችና የስራ ሂደት  ሥራ አስፈጻሚዎች የደረጃ  ዕድገት የሚታየው በሥራ መሪዎ ደንብ ሆኖ በዋና ሥራ አስፈጻሚ  በሚቋቋም  ኮሚቴ  የውሣኔ  ሀሣብ  የሚቀርብባቸው  ሲሆን ሌሎች  ወደቦ ግን፡-

ሀ/  የሰወ ኃይል  አስተዳደር ደ/የሥራ ሂደት  ሰብሳ 

ለ/ የሥራ አስፈጻሚ የሚወክለው ኃላፊ  አባል 

ሐ/የመሠረታዊ ሠራተኛ ማሕበር ተወካይ 

መ/ የሰው ኃይል አስ/ኩኩ ቲም አስተባባሪ  እና ኦፊሰሮች፡፡  ሆነው የውሣኔ  ሃሣብ ያቀርባሉ፡፡

የዕድገት ኮሚቴ  አሠራር ሥነ ሥርዓት፡

ሀ/ የኮሚቴው  ሰብሳቢ ዕድገት በሚካሄድት  ጊዜና ቦታ በመወሰን የዕድገት ኮሚቴ አባላት ይሰበሰባል እንደአስፈላጊነቱም አስቸኳይ  ጥሪ ያደርጋል፡፡ 

ለ/ ማስረጃዎችን  ከመረመረና ትክክለኛነታቸውን ከአጣራ በኋላ ተወዳዳሪው  ለሥራው  ያለው ፍላጎት  ዝንባሌ የማሰብና  የማመዛዘን ችሎታ ለሚወደዳደርበት ቦታ ብቁ መሆኑን ይበልጥ ለማረጋገጥ  ከሥራው ባሕሪ  የተነሳ  አንደ አስፈላጊነቱ የሚያዝ  የጽሑፍ  ወይም የተግባር ፈተና ሊሠጥ  ይችላል፡፡ 

መ/ ኮሚቴው  የቀረበለትን ማስረጃዎች መርምሮና መካከል  በአጠቃላይ  ውጤት  ብልጫ ያለውን መርምሮ  አስተያየት ማዕከል ለማጽደቅ  ኃላፊነት  ለተሰጠው ከማስረጃዎች ጋር ያቀርባል፡፡ 
ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

ሠ/ ሥራ አስፈጻሚው ወይም ውክልና  ያው በዕድገት ኮሜቴ ተመርምሮና  አስተያየጥ ታክሎነት መረጃዎች ጋር  የሚተላለፍለትን  የዕድገት ጥያቄዎች  ይወስና፡፡   

ረ/ ማንኛውም የደረጃ  ዕድገት ኮሚቴ  አባል ለአንድ ክፍል መደብ በዕጩ  ተወዳዳሪነት   ሲቀርብ ከኮሚቴ አባልነት  ዕድገቱ በቀሩት አባላት  ይታያል፡፡ የሠራተኛ ማህበሩ እራሱ ተወዳዳሪ  ሆኖ  ከቀረበ ለዚያ ጊዜ ብቻ መሰረታዊ ማሕበሩ ሌላ ሰው ይተካል፡፡ 

ሰ/  የዕድገት ኮሚቴ  ሰብሳቢና  የሠራተኛ ማሕበር ተወካይ አስፈጻሚ ተወካይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤው  ተሟላ ይባላል፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

  ቅጥር 

ሀ/  በአክሲዮን  ማህበሩ  ክፍት የሥራ መደብ  የሚፈጠር የሠራተኛ  አቆጣጠር

 1. አክ/ ማህበሩ ካሉት ሰራተኞች በደረጃ ዕድገት  ለመመደብ ሙከራ ተደርጎ  ተፈላሂን  መመዘኛ የሚያሟላ  ሊታጣ  ድርጅቱ በሚያወጣው  የራሱ የውጭ ማስታወቂያ መሠረት  ለሚቀርቡት ተወዳዳሪዎችመካከል አወዳድሮ  ይቀጥራ፡፡ 
 2. ሥራውን ለቆ የቆየ ሠራተኛ  ቀድሞ ሲሠራው በነበረው  የሥራ መደብ ላይ እንደገና በአሠሪው ሲቀጠር ለሙከራ ሱቀጠር አይችል፡፡  
 3.  በሠራተኛው  የሙከራ  ጊዜ መጨረሻ በክፍሉ  ኃላፊ አስተያየት  ሥራው አጥጋቢ  ከሆነ በውሉ መሰረት  የተቀጠረ መሆኑ በጽሑ ይረጋገጥለታል፡፡  ለሠራተኛው ይህ ማረጋገጫ ሳይሠጠው የ45 ቀን የሙከራ   ጊዜው  ሲያልፍ ለሙከራ ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ  በቋሚነት እንደተቀጠረ  ይቆጠራል፡፡ 
 4. በሙከራ ጊዜ ውስጥ  ከሁለቱም  ወገኖ አንዱ  ያለ ማስጠንቀቂያ የሥራው ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ 

ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1.   አዲስ ለሚጠር ሠራተኛ ሁሉ ለጤንነትና ለአሻራ  ምርመራ የሚላከው ሠራተኛ ሠራተኛ  ተቀጥሮ ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ሆኖ  ወጭውን አክ/ማህበሩ ይሸፈናል፡፡ 
 2. አዲስ  የጠቀጠረ ሠራተኛ የመጀመሩያው የሥራ አፈጻፀም  ከተሞላለት ለዕድገት  መወዳደር ይችላል፡፡ 

ለ/ ክፍት የሥራ መደቦች ማስታወቂያ ይዘት 

 1. የሥራ መደቡ መጠሪያ 
 2. ከሥራ መደቡ የጠወሰነ ደረጃና ደመወዝ 
 3. ከተወዳዳሪዎች  የሚፈለግ  የት/ደረጃና ሥራ ልምድ 
 4. የዕድሜ ወሰንና ፆታ 
 5. ማመልከቻ የሚቀርብበት  የተወሰነ የጊዜ ገደብ 
 6.   ተወዳዳሪዎች  ማቅረብ ያለባቸው ሌሎች  ማስረጃቾችና ሰነዶች  የወጭ ማስታወቂ የጊዜ ገደብ አ/ማህበሩ በሚወስነው ይሆናል፡፡ 
 7. ፈተና የሚሰጥበት ጊዜና ቦታ 
 8. የምዝባ ሰዓትና ቢሮ 

ሐ/ የቅጥር ኮሚቴ 

 1. በአ/ማህበሩ  ውስጥ የቅጥር ኮሚቴ  የሚመለከቱት አባላት የያዙ ይሆናል፡፡

ሀ/ የሠው ኃይ/ አስ/ደ/የሥራ ሂደት ስራ አስፈጻሚ 

ለ/ የዋና ሥራ አስፈጻሚ  ተወካይ 

ሐ/ መ/ የመሰረታዊ ሠራኛ ማህበር ተወካይ 

መ/ የሰው ኃይል  አስ/ኬዝ  ቲም አስተባባሪና ኦፊሰሮች

ሠ/ ድምጽ መስጠት የማይችል የሠራተኛ  ኦፊሰር


ባህር ዳር  ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር

Bahir Dar Textile Share company 

ህብረት  ስምምነት

Collective agreement 

 1. የቅጥር ኮሚቴ  ተወዳሪዎን በሚመረጥበት ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ  በመስኩ ሙያ  ዕውቅና ያለው ሰው አስተያየቱን  እንዲሰጥበት የቅጥር ኮሚቴው  ሊጋብዝ ይችላል፡፡ 
 2. የቅጥር ኮሚቴ  ተወዳዳሪዎችን በሚመረጥበት ጊዜ   ውሳኔውን  በድምጽ ብልጫ  ይሠጣል፡፡ የአባሎች ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ ሰብሳቢ የሚገኝበት ወገን ወሳን ይሆናል፡፡ 

መ/ የቅጥር ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት

የአ/ማህበሩ  የሰው ኃይል አስ/ ኬዝ ቲም አስታባሪ የቅጥር ማመልከቻዎች መሟላታቸውን  ከአረጋገጠ በኋላ  ለቅጥር ኮሚቴው  ሲያቀርብ ኮሚቴው 

 1. የአመልካቾችን  ማስረጃዎች በመመረምመር ፈ ተና  በመስጠት  ያወዳድራል፡፡