Untitled Document

የህብረት ስምምነት ሞዴል
በኢትዮጵያ ኮንፌዴሬሽን ሠራተኛ ማህበራት
(ኢሠማኮ)

 

 

 

 

ህዳር 11/2009 .
አዲስ አበባ

 

ሞዴል የህብረት ድርድር
…………..ጋርመንት ኩባንያ የአሰሪዎች ሠራተኛ ማህበራት
ይህ የህብረት ስምምነት በኢትዮጵያ ህግ መሰረት በተቋቋመው የ………………ጋርመንት ኩባንያ ከዚህ በኋላ ድርጅቱ …………… ተብሎ በሚጠራ እና በተሻሻለው የአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/2003 መሰረት በተቋቋመው የሠራተኛ ማህበር መካከል በዛሬው ቀን 30/11/2008 ተፈረመ፡፡
አጭር እርእስ
የህብረት ስምምነቱ በአጭሩ ስምምነቱ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡
ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር በዚሁ ህብረት ስምምነት የሚከተሉት ቃላት እና ሀረጎች ተተርጉሟል፡፡
ሀ. አዋጅ - የአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1997 ዓ.ም፣ ቁጥር 494/1998 ዓ.ም እንዲሁም በውስጡ ያሉትን ማሻሻያዎች ማለት ነው፡፡
ለ. የውስጥ መምሪያ ወይም የድርጅቱ ኩባንያ ፖሊሲ - ድርጅቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የስራ መርሃ ግብር፣ የእረፍት ጊዜ፣ የደሞዝ ክፍያ የስራ አፈፃፀም መለኪያ ዘዴ/ስርዓት፣ የስራ ላይ ደህንነት እና የጤና ጥበቃ መለኪያ፣ የአደጋ መከላከል፣ የስነምግባር መመሪያ እና አፈፃፀማቸው እደዚሁም በዚሁ አዋጅ እና ሌሎች ተፈፃሚ በሆኑ ህጎች መሰረት የስራ ቅጥር አይነት መመሪያ እና የስራ ሁኔታ ለመወሰን ድንጋጌ እንዲያወጡ ሁለቱንም የአስተዳደራዊ እና የኦፕሬሽን ፖሊሲ የሚሰጥ የስራ መመሪያ እና ውስጣዊ ፖሊሲ ማለት ነው፡፡
ሐ. ሰራተኛ በአዋጅ ቁጥር 377/2003 አንቀጽ 4 ጎን ለጎን በስራ ቅጥር ውል መሰረት ከድርጅቱ ጋር ላልተወሰነ ጊዜ የስራ ቅጥር ግንኙነት ያለው ማንኛውም አካላዊ ግለሰብ ማለት ሲሆን በዚሁ ስምምነት አንቀጽ 2.1.1 መሰረት ከዚሁ ስምምነት ውጭ የሆኑትን የስራ አመራር አባላትን የማያካትት ነው፡፡
መ. አረጋጋጭ ሁንዴ ጋርመንት ኩባንያ ህጋዊ ባለስልጣናቱ፣ ተወካዮቹ፣ ሹሞቹ፣ ክፍሎች እና ቅርንጫፎችን ያካተተ ማለት ነው፡፡
ሠ. ህብረት/አንድነት በሁንዴ ጋርመንት ኩባንያ የንግድ ማህበር እና የህብረቱ ህጋዊ ስራ አስፈፃሚዎች/መሪዎችን ጨምሮ የተመዘገቡ እና የተረጋገጠላቸው ማለት ነው፡፡
ረ. የስራ ቅጥር ውል  በስራ ቅጥር ጊዜ በዚሁ የህብረት ስምምነት መሰረት ሽፋን ያገኘ የስራ ዝርዝር መግለጫው እና ማሻሻያው እንዲሁም ይህንን ስምምነት ያካተተ ለሰራተኛው የሚሰጥ የስራ ቅጥር ደብዳቤን ያካትታል፡፡
ሰ. ስምምነት ይህ አራተኛው የህብረት ስምምነት እንዲሁም  የተመዘገበው ማሻሻያው እና እንደሁኔታው በሁለቱም የጋራ ስምምነት በድርጅቱ እና በህብረቱ ሊሰጥ የሚችለው ደንብ የሚያካትት ነው፡፡
ሸ. እቅድ የድርጅቱ አመታዊ እቅድ እና የረጅም ጊዜ የስትራቴጂክ ፕላን እና ራእይ ማለት ነው፡፡
ቀ. የአሰሪው ቅጥር ግቢ - በስራቸው ባህሪ ምክንያት ሰራተኞች የሚገኙበት የስራ ቦታ በድርጅቱ ባለቤትነት የተያዘ ህንፃ፣ ማሽን፣ ተሸከርካሪ፣ እንዲሁም መሬት ወይም ድርጅቱ በኪራይ በያዘው ማንኛውም የስራ ቦታ የሚገኝ ስራው የሚካሄድበት ወይም በድርጅቱ በባለቤትነት ይሁን በኪራይ ወይም በሊዝ በመያዝ ለሰራተኞች የሚሰጥ ቦታ ማለት፡፡
በ. ስነ ፆታዊ ጥቃት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በስራ ባደረቦች ወይም  በአሰሪው ደንበኞች ላይ ምንም አይነት ጥቃት ለማድረስ መሞከር ወይም በሀገሪቱ ተፈፃሚ በሆነ ህግ የተከለከለውን የሰራተኛወን የስራ አቅም ላይ ጫና በሚያሳድር መልኩ አካላዊ ይሁን የቃል ወይም የምልክት ተግባር ማሳየት ወይም ፆታዊ ስሜት ለማነሳሳት የሚያስችል መልዕክት ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡
ምዕራፍ አንድ ጠቅላላ ድጋጌዎች
አንቀጽ አንድ
የህብረት ስምምነቱ አላማዎች

  • የዚሁ የህብረት ስምምነት አላማ በድርጅቱ፣ ሰራተኞች እንዲሁም በህብረት ስራ ማህበሩ መካከል በጠበቀ ረጅም እና መልካም ግንኙነት በኢንደስትሪው ሰላም የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ እንዲሁም በድርጅቱ እና በሰራተኞቹ በሁለቱም በጋራ ስምምነት ተቀባይነት ያገኘ የጠበቀ እና የበለጠ የስራ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል ነው፡፡

ህብረቱ ድርጅቱ በላቀ ኢንዳስትሪያዊ ውድድር አሁን ያለውን አቅሙን ለማጠናከር በሚያስችለው መልኩ የስራ መመሪያ እና ደንብ ማውጣት በሚያስፈልገው በከባድ ውድድር እና በላቀ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን እና ተወዳዳሪ ሆኖ እንደሚቀጥል  ይገነዘባል፡፡  

  • ከላይ በአንቀጽ 1.1 የተገለፀው አጠቃላይ ይዘት እንደተጠበቀ ሆኖ ስምምነቱ የሚከተሉት የተወሰኑ አላማዎች ይኖሩታል፡-
   • የኢንደስትሪ ሰላሙ በድርጅቱ ውስጥ የተረጋገጠ መሆኑን አመርቂ የሆነ የስራ ግንኙነት በመልካም ግንኙነት መከናወኑን ሰራተኞች ያላቸውን ትስስር በማጠናከር ግዴታቸውን መወጣት ይችሉ ዘንድ መብታቸውን እና ግዴታቸውን በመገንዘብ ጥረት ማድረግ እንዲችሉ፡፡
   • ሰራተኛው ተቀባይነት ባለው ህገ ደንብ፣ ስነ ምግባር መመሪያ በሚያሟላ መልኩ ሃላፊነቱ መወጣት እዲችል ፍላጎቱን እና ጥረቱን በስራው ላይ እንዲያውል፣ ምርታመነትን እንዲያሻሽል እና ሁለቱም ድርጅቱ እና የህብረት ማህበሩ ሰራተኛውን ማበረታታከት እና ማመስገን እንዲችሉ ማስቻል፡፡
   • የሰራተኞች ደህንነት የድርጅቱ ዋናው ፍላጎት፣ ህልውና እና ትርፋማነት በማወቅ ጤናውን መጠበቅ፣ ትምህርታዊ እውቀቱን እና አካላዊ ጤንነቱን ማሳደግ ጥሩ ንሮን የሚያረጋግጥለት ለስራው ምክንያታዊ የሆነ ደሞዝ እና ካሳ በማቅረብ ኑሮው የተጠበቀ እንዲሆን ማስቻል፡፡ መሰረታዊ ሰብአዊ መብትን እንዲያረጋግጥ ማስቻል እና በአሰሪው ስራ አመራር/ውሳኔ አሰጣጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል፡፡
   • የድርጅቱ ቀጣይነት ያለውን ህልውና ለማረጋገጥ እና እያደገ በመጣው የአየር ትራንስፖርት የገበያ ውድድር እስታንዳርዱን ለማሻሻል
   • የድርጅቱ የአየር ትራንስርት አገልግሎት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ውጤታማ፣ ምቹ እና ተወዳዳሪ እንዲሁም ከማንኛውም አደጋ ወይም ስጋት ነፃ እንዲሆን ማስቻል፡፡  
   • ድርጅቱ ለደንበኞቹ ውጤታማ፣ የተቀናጀ እና ዘመናዊ አገልግሎት እንዲሰጥ አቅሙን ማጠናከር እና ድርጅቱ የተቋቋመበትን መሰረታዊ አላማ ለማሳካት ይችል ዘንድ የተቀናጀ ስራ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ደንቦችን እዲያቋቁም ማድረግ፡፡

አንቀጽ ሁለት
ስምምነቱ ሁኔታ እና የተፈፃሚነት ወሰን

  • በዚህ ስምምነት የተሸፈኑ ሰራተኞች
   • ይህ የህብረት ስምምነት የስራ ሃላፊነታቸው በዚሁ ስምምነት እዝል 3 የተዘረዘረው እና በአዋጁ የተገለፁትን የስራ አመራር አባላትን ሳያካትት ለተወሰነ እና ላልተወሰነ ጊዜ በድርጅቱ ለተቀጠሩ ሰራተኖች በሙሉ ተፈፃሚ እና አስገዳጅ ይሆናል፡፡
   • ይህ ስምምነት ለተወሰነ እና ላልተወሰነ ጊዜ በድርጅቱ ለተቀጠሩ ከላይ በንዑስ አንቀጽ አንድ የተገለፁትን በአሰሪው እና በሰራተኞች መካከል  በተናጠል እና በጋራ የተከናወነው

አንቀጽ ሦስት
የወገኖቹ መብት እና ግዴታ

  • የአሰሪው መብት እና ግዴታ
   • የአሰሪው ግዴታዎች
 • በሀገሪቱ ተፈፃሚ በሆኑ ህጎች ከተጠበቁለት መብቶች በተጨማሪ በዚሁ ህብረት ስምምነት ውስጥ እንዲሁም በሌሎች ተፈፃሚ ህጎች እና ደንቦች በግልጽ ካልተጠቀሰ  በስተቀር ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ አስፈላጊ ሆኖ ባገኘው እና ብቃት ካላቸው ሹሞቹ ባለስልጣናት ወይም ተወካዮቹ፣ ስራ አስፈፃሚዎች፣ የሰጅራ አመራር ሰራተኞች በኩል አግባብነት እና ተፈፃሚነት ባለው ህግ መሰረት ሰራተኞቹን የመምራት፣ እቅድ እንዲኖራቸው የማድረግ፣ የመቆጣጠር፣ ስራዎቹን መምራት፣ መቅጠር፣ ማስተዳደር፣ ማሳደግ፣ ማዘዋወር፣ መቀነስ፣ ስነ ስርዓት ማስያዝ፣ የማገድ እና የማባረር መብቱ በሙሉ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ፖሊሲዎቹን እንዲሁም የውስጥ መምሪያ እና ደንብ የመወሰን፣ የመስጠት፣ የመቅረፅ፣ የማሻሻል፣ የመመደብ፣ የመቀየር፣ ወይም የመሻር መብት፤ አሰሪው የደሞዝ መጠን እና ሌላ ማንኛውም ክፍያ የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን ህብረቱ በዚሁ ስምምነት ተዘርዝሮ የተገለፀው ለውጡ ወይም ለለውጥ የቀረበው ሃሳብ የሰራተኞች መብት እና ጥቅማ ጥቅማጥም እንደሚፃረር ካመነበት ህብረቱ ጉዳዩን ከድርጅቱ ሊወያይበት ይችላል፡፡
   • የአሰሪው ሃላፊነት

በህግ ከተመለከተው ሃላፊነት በተጨማሪ ድርጅቱ የሚከተሉት ሃላፊነት ይኖሩታል፡፡

 • ለስራው በሰራተኞች የሚፈለግ መሳሪያ/ቁሳቁስ፣ አስፈላጊ ጥሬ እቃ እና የደህንነት መሳሪያዎችን ማቅረብ
 • የዚሁ ህብረት ስምምነት ድንጋጌዎችን፣ የስራ መመሪያውን እንደዚሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ በህግ መሰረት የሚሰጠውን የውስጥ ህገ ደንብ እና ፖሊሲ መገንዘብ እና ማክበር
 • ሰራተኞቹን ከስራ ላይ አደጋ ለመከላከል ይችል ዘንድ የሰጀራተኞቹን ደህንነት እና የስራ ላይ ጤንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ እርምጃዎችን በሙሉ የመውሰድ እና ከዚሁ እርምጃ ተጓዳኝ የሆነውን ስልጣን ባለው ህጋዊ ባለስልጣን የሚሰጠውን እስታንዳርድ እና መመሪያ የመከተል
 • በየጊዜው ለእያንዳንዱ የስራ ሃላፊነት  የስራ መጠሪያ ደረጃ እና የደሞዝ እርከን የመወሰን እና ለሰራተኞች ዝርዝር የስራ መግለጫ መስጠት
 • በድርጅቱ ውስጥ መመሪያ እና ፖሊሲ የሰፈሩትን ደንቦች በዚሁ የህብረት ስምምነት ወይም አዋጅ በሰራተኞች የተያዘውን መብት እና ጥቅማ ጥቅም ወይም የስራ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሌለው ማረጋገጥ እንዲሁም በዚህ ስምምነት፣ በአዋጅ እና በሌላ የአሰሪ እና ሰራተኛ ህግ እና ደንብ የተመለከቱትን መከተል እና ተግባራዊ ማድረግ
 • በሚከተሉት የማይወሰን ነገር ግን የስራውን ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት ከጊዜ ወደ ጊዜ በድርጅቱ ሊቀረጽ እና ሊሻሻል በሚችለው ደህንነት አያያዝ /አመራር ማንዋል መሰረት አግባብነት ላላቸው ወይም ለሚመለከታቸው ሰራተኞች የሚከተሉትን የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን ማቅረብ ወይም መቀየር

ሀ. ጉግል /መነፃር
ለ. የፊት ሽፋን
ሐ. የመተንፈሻ አካላት
መ. የጀሮ ማዳመጫ
ሠ. ጓንት
ረ. የእሳት ማጥፊያ
ሰ. በጀሮ የሚሰካ
ሸ. ጭምብል
ቀ. ተከላካይ አልበሳት
በ. ሄልሜት
ተ. የዝናብ ልብስ እና ኮፍያ
ቸ. መሰላል እና
ነ. አሰሪው ከስራ ተዛማጅ የሆኑ የጤና ጠንቆችን በስራ ላይ ለመከላከል በስራ ላይ አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት እርምጃዎችን በሙሉ ማሟላት አለበት፡፡
ማስታወሻ
ሀ. በስራቸው ባህሪ ምክንያት በተደጋጋሚ ለዝናብ ተጋላጭ የሆኑ ሰራተኞች የዝናብ ልብስ እና ኮፍያ የሚሰጣቸው ሲሆን አልፎ አልፎ ተጋላጭ ለሆኑ በብድር መልኩ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡
ለ. በስራው ሁኔታ ምክንያት አስገዳች በሚሆንበት ጊዜ ጓንት እና የሴፍቲ ደህንነት ጫማ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ሐ. ድርጅቱ ከስራው ጋር የተሳሰረ የጤና እንከን /ጉዳት ለመከላከል አስፈላጊ የሆነውን ነገር በሙሉ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
መ. እንደስራቸው ባህሪ ወይም እንደአስፈላጊነቱ በእንደዚህ አይነት አደጋ ለተጋለጡ የሚመለከታቸው ሰራተኞች ድርጅቱ በየአመቱ የኦዲዮ ሜትሪክ  እና ራዲየሽን /ጨረር ምርመራ የሚያካሄድ ይሆናል፡፡

 • በድርጅቱ የውስጥ ደንብ ወይም ፖሊሲ መሰረት መለዮ መልበስ ለሚያስፈልጋቸው ሰራተኞች ከክፍያ ነፃ ዩኒፎርም ወይም መለዮ መስጠት
 • በድርጅቱ የተሰጠውን ሙሉ ልብስ ወይም የወርክሾፕ ልብስ ሰራተኛ ሙሉ ልብሱን ለብሶ ስራ ላይ እስካዋለው ድረስ የማሳጠቢያ ወጭ መሸፈን
 • አዲስ እና ዘመናወሊ ቴክኖሎጂ ለማስተዋወቅ ስልጠና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ከስራው ጋር ተዛማጅ የሆነ ስልጠና መስጠት ወይም ሰራተኞች ለሌሎች ስልጠና እንዲሰጡ  ማድረግ
 •  በኩከባንያው የደህንነት ማኔጅመንት ፖሊሲ ማንዋል መሰረት በአንቀጽ 3.1.2 (6) ያልተካተቱን የደህንነት መሳሪያዎች መስጠት
 •  ለህብረቱ አባልነት የሚከፈል ከሰራተኛ ወርሃዊ ደሞዝ መቁረጥ እና በሰራተኛው በስጽሁ በሚፈቀድበት ጊዜ ይህንኑ ወደ ህብረቱ ሂሳብ ማዘዋወር፡፡ ድርጅቱ እንደዚህ አይነት ቅነሳ የሚቆም ሲሆን  በሰራተኛው ወይም በህብረቱ በኩል ብቻ ሲጠየቅ ከዚህ ቀጥሎ የሰራተኛው ደሞዝ ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል፡፡
 •  ህብረቱ ህጋዊ ማስታወቂያ፣ ቡሌቲን እና መፈክር መስቀል የሚችልበትን አግባብነት ያለው ቦታ እና የማስታወቂጀያ ሰሌዳ ማዘጋጀት
 •  ቅነሳው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም በራሱ በሰራተኛው ጥያቄ መሰረት የሚደረግ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውንም የደሞዝ ቅነሳን በተመለከተ ለሚመለከተው ሰራተኛ በቅድሚያ የ15 ቀናት መስታወቂያ መስጠት
 •  ህብረቱ ጥቅም ላይ የሚያውለው አስፈላጊ ጽ/ቤት መስጠት
 •  አሰሪው ማድረግ የሌለበት

ሀ. የሰራተኛን ህጋዊ መብቶች፣ ጥቅማጥቅሞችን በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ የሚጎዳ ወይም የሚያግድ ማንኛውም ተግባር መፍቀድ
ለ. ህጋዊ መብታቸውን፣ ጥቅማጥቅማቸውን ወይም ማንኛውንም ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ካለው ሃላፊነት ከሚወስድ ባለስልጣን ድጋፍ ከመጠየቅ የሚከለክላቸውን በሰራተኛው ወይም ተወካዮቻቸው ላይ ማንኛውንም ከልካይ ተግባራት መውሰድ
ሐ. በህብረቱ አባልነታቸው ወይንም ስለህብረቱ በህጋዊ ተግባራት ላይ በመሳተፋቸው ምክንያት በህብረቱ ሰራተኞች ወይም ሹሞች ላይ ጣልቃ ገብነት፣ አካላዊ ጥቃት ወይም ማግለል
መ. ለተመሳሳይ ጥፋት ከአንድ ጊዜ አንድን ሰራተኛ መክሰስ ወይም መቅጣት
ሠ. የአንዱን አላማ ለማሳካት ጥፋት በሰሩት ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ የዲስፕሊን እርምጃ መጣል
ረ. ቡድኑ ጥፋቱን መፈፀሙ ማረጋገጥ ካልተቻለ በስተቀር በማንኛውም ጥፋት ሰራተኞችን በቡድን መክሰስ
ሰ. በሹሞቹ በኩል ማንኛውንም አካላዊ ጥቃት እና ስድብ ማድረስ
ሸ. የወደፊት የስራ አፈፃፀሙን ለመከልከል ወይም ለማደናቀፍ በማሰብ አንድን ሰራተኛ ከክፍል ወደ ክፍል ማዘዋወር
ቀ. ከሰራተኛው መደበኛ ተግባራት ውጭ የሆኑ መመሪያ ወይም ትዕዛዝ መስጠት ወይም ማስተላለፍ ማለትም በአቅሙ ልክ ያልሆኑ ለምሳሌ እንዲህ አይነት ምርመራ ወይም ትዕዛዝ የአሰሪውን የጽሁፍ ፖሊሲ እና ደንብ በሚጥስ መልኩ ወይም የአሰሪው ወይም የሰራተኞው የራሱ ህይዎት እና አካል አደጋ ላይሊጥል የሚችል ትእዛዝ መስጠት

ድርጅቱ ሰራተኞቹ በዚሁ ስምምነት መሰረት ስለ መብታቸው እና ሃላፊነታቸው ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንዲያግዝ የዚሁ የህብረት ስምምነት በጽሁፍ ማሰራጨት አለበት፡፡

 

   • የስራ ቅጥር ውል አንድ አካል ተደርጎ ይታመናል፡፡
  1. የሰራተኞች መብት እና ግዴታ
   1. በሰራተኞች የተያዘ መብት

በህግ መሰረት የተቀመጠው የሰራተኞች መብት እንደተጠበቀ ሆኖ የድርጅቱ ሰራተኞች የሚከተሉት መብቶች ይኖሯቸዋል፡፡

 1. በብረቱ በኩል በተናጠል በግለሰብ ደጀረጀ ወይም በተናጠል ወደ ድርጅቱ አቤቱታ ወይም ቅሬታ የማቅረብ መብት
 2. የዚሁ ስምምነት ህገ ደንብ እደተጠበቀ ሆኖ ክፍት የስራ ቦታ ካለ ከዝቅተኛ  ደረጃ የስራ መደብ የእድገት ወይም ዝውውር የመጠየቅ መብት፡፡ ነገር ግን አሰሪው በጥያቄው መሰረት ለመፈፀም አይገደድም፡፡
 3. አንድ ሰራተኛ ከዝርዝር የስራ መግለጫው ውጭ ለመስራት ላይገደድ ይችላል፡፡ ከስራው ተዛማጅ የሆነ ማንኛውንም ስራ በቅርብ አለቃው በእምነት የተሰሰጠውን ሃላፊነት እና ተግባራት እንዲወጣ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከዝርዝር የስራ መግለጫው ባሻገር ወይም በተለየ ቦታ ከመመደቡ በፊት የተሻሻለው ወይም ወቅታዊ የተደረገው ዝርዝር የስራ መግለጫ የሚሰጠው ይሆናል፡፡ ይህም በግል መሀደሩ ፋይል ሆኖ ይቀመጣል፡፡
 4. በጣም ዝቅተኛ ደሞዝ እንደሚከፈለው ወይም የስራ ጫና እንዳለበት የሚሰማው ሰራተኛ አስጋቢ ከሆነ ምክንያት ዳግም እዲገመገምለት ጥያቄውን ለህብረቱ ማቅረብ ይችላል፡፡ ህብረቱ በዚሁ ስምምነት አንቀጽ 4 መሰረት ከድርጅቱ ሊወያይበት ይችላል፡፡
 5. የድርጅቱ ሰራተኛ ከድርጅቱ የስራ አፈፃፀም እቅድ እና ግምገማ ተዛማጅ በሆኑ ተግባራት ላይ የመሳተፍ እንደዚሁም በቀጥታ ይሁን በተወካየሞቻቸው በኩል ሰራተኛን በሚያሳትፍ ተግባር ላይ የመሳተፍ እና በቃል እና በጽሁፍ ሃሳቡን የመግለጽ መብት
 6. ሰራተኞች በህብረቱ የመወከል መብት ይኖራቸዋል፡፡ በህብረቱ የውስጥ ህገ ደንብ መሰረት በህብረተሉ ተግባራት የመሳተፍ ከህብረቱ ሹሞች ስለ ስራ ሁኔታን በተመለከቱ ጉዳዮች በነፃነት የመወያየት፣ ማንኛውንም ግጭት ወደ ዩኒየኑ ወይም ወደ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቲር ወይም በድርጅቱ እና በህብረቱ መካከል ስምምነት ወደተደረሰበት ስልጣን ወደአለው ሶስተኛ ወገን ወይም ወደ ፍርድ ቤት የመውሰድ መብት
   1. የሰራተኞች ግዴታ

በህግ መሰረት ሰራተኖች ያላባቸውን ግዴታ እንደተጠበቀ ሆኖ እንዳንዱ ሰራተኛ ያለበት ግዴታ

 1. የዚሁ ስምምነት ደንቦች አዋጅ እና ሌሎች አሰሪ እና ሰራተኛ ህጎች፣ የድርጅቱ ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ደንብ ፣ የስራ ቅጥር ውሉን እና ዝርዝር የስራ መግለጫ እንዲሁም ከስራው ጋር ተዛማጅ የሆኑትን በድርጅቱ የተሰጡ በስራ መመሪያ እና በእስታንዳርድ ደንብ የተመለከቱን ጉዳዮች በሙሉ ማክበር እና በዚሁ መገዛት
 2. የተሰጠውን ስራ እና መመሪያ ማከናወን እንደዚሁም የተቀጠረበትን ስራ ሙሉ በሙሉ ትጋት እና ችሎታ የታከለበት በንቃት እና በጥንቃቄ ሃላፊነትን የመፈፀም እና የአሰሪውን ውጤት እና ምርታማነትን ማሻሻል
 3. ድርጅቱ ክብር እና እውቀት ሊያገኝ በሚችልበት መልኩ እራስን መምራት እና የኩባንያውን ተግባራት እና ሃላፊነት ከሚፃረሩ ማናቸውን ተግባራት መቆጠብ  
 4. በቅርብ አለቃው ከዝርዝር የስራ መግለጫው ተዛማጅ የሆኑ ትዕዛዞች ወይም ከስራው ጋር የተገናኘ ማንኛውንም የስራ ትዕዛዝ በመደበኛው የስራ ጊዜው የሚሰጡትን ሁሉንም ስራዎች እና መምሪያዎች በችሎታው ወይም በአቅሙ መጠን በጥራት እና በጊዜው ማከናወን
 5. ለድርጅቱ ህልውና የመአዘን ድንጋይ እንደመሆኑ መሰጠን የደንበኛን አገልግሎት ሙሉ እውቅና በመያዝ መንቀሳቀስ፣ አየር መንገዱ የሚገባውን ክብር በሚያስጠብቅ መልኩ ደንበኞቹን መንከባከብ እና ማክበር እዲሁም ከእለት ተዕለት ተጋባሩ ተዛማጅ የሆኑትን ለደንበኞች እንከን አልባ አገልግሎት መስጠት
 6. በስራ ባልደረቦቹ ወይም በአሰሪው ደንበኞች ላይ ማንኛውንም አይነት ፆታዊ ትንኮሳ ተግባራትን ከማድረግ ወይም ከመፈፀም ወይም ለመፈፀም ከመሞከር መቆጠብ
 7. በድርጅቱ ወጭ በአሰሪው የሚፈለገውን በየጊዜው የህክምና ምርመራ ማካሄድ እና ተከላካይ የህክምና እና የደህንነት እርምጃዎችን መፈፀም
 8. የራሱን ህይዎት ወይም ደህንነት ወይም የተከታዮቹ ሰራተኞች ወይም ሌሎች ሰራተኞች ስጋት ላይ ሊጥል ከሚችል አደጋ ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት ከማድረግ መቆጠብ
 9. በድርጅቱ ስልጣን ባለው የሰራተኞች ወይም ባለስልጣናት መምሪያ መሰረት በድርጅቱ ማሽነሪ፣ መሳሪያ፣ ፕላንት ወይም ሌላ ጥቅሙን ሊጎዳ የሚችል ወይም በግለሰቦች ወይም በስራ ባደረቦቹ፣ በበረራ ላይ ባሉ ተሳፋሪዎች ወይም በማንኛውም አውሮፕላን አደጋ ሲከሰት ወይም እንደሚከሰት ሲታሰብ በራሱ ላይ፣ በቤተሰቡ ወይም በንብረት ላይ አደጋ ወይም ጥፋት እንደማያስከትል እና ይህንን ለማድረግ አቅም ያለው ከሆነ በተጠየቀ ጊዜ ድጋፍ የመስጠት  
 10.  የድርጅቱን ፈንድ ወይም ንብረት ሲሰርቅ፣ አለአግባብ ሲጠቀምበት ወይም አላግባብ ሲያባክን ሲመለከቱ ወይም እጅ ከፈንጅ በሚይዙበት ጊዜ ጭብጡን አግባብነት ወዳለው የድርጅቱ ባለስልጣን ወይም የጥበቃ ጽ/ቤት ወዲያውኑ ሪፖርት የማድረግ፡፡ ነገር ግን እንደዚህ አይነት ድርጊት ወደ ድርጅቱ ባለስልጣን ሪፖርት ማድግ በማይቻልበት ጊዜ እና የጉዳዩ ባህሪ አፋጣኝ ትኩረት በሚያስፈልግበት ጊዜ በአካባቢው ወደሚገኝ ተገቢ የሆነ መንግስታዊ ወይም ስልጣን ወደአለው መንግስታዊ ባልስልጣን ሪፖርት መደረግ አለበት፡፡
 11.  ማንኛው ሰራተኛ በአዋጁ፣ በዚህ ስምምነት ወይም በድርጅቱ የውስጥ ፖሊሲ እና ደንብ መሰረት የተከለከሉትን ድርጊቶች ከማግድረግ እራሱን መቆተብ አለበት፡፡ በተለይ ማንኛውም ሰራተኛ ማድረግ የሌለበት

ሀ. ከድርጅቱ ስልጣን ካላቸው አካላት ቅድሚያ ፈቃድ ሳያገኝ የድርጅቱ ይዞታ የሆነ ወይም በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የሚገኝ ማንኛውም ንብረት ወይም ቁሳቁስ ከአሰሪው ቅጥር ግቢ ማውጣት ወይም ለራስ ወይም ለ3ኛ ወገን ጥቅም ላይ እንዲውል ማድግ
ለ. ጉዳትን ወይም ውድመትን ማንኛውም በራስ ተነሳሽነት አሉታዊ ሁኔታን ሊያስከትል በሚችል መልኩ ሌሎች በስራ ላይ ያሉትን ሰራተኖች ሊያውክ ወይም ደግሞ ሰላማቸውን ሊነሳ በሚችል መልኩ ወደ ስራ መቅረብ
ሐ. በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝን ማንማውም ግለሰብ ላይ መዛት መሳደበቭ አካላዊ ጥቃት ወይም መቀለድ
መ. የድርጅቱን ፖሊሲ፣ መምሪያ፣ ህግ እና ደንብ ወይም በዚህ ስምምነት የተመለከቱትን ግዴታዎች መጣስ ወይም አሳንሶ ማየት

ሠ. ሃላፊነቱን በሚወጣበት ጊዜ ለማወቅ ወይም ተደራሽ ለመሆን እድሉን አግኝቶ የነበረውን የበረራ ኦፕሬሽን እና የአውሮፕላን ጥገና ወይም የቴክኒክ ደንብ ማንዋል የተመለከቱትን አስመልክቶ ወይንም ከአየር መንገዱ የስራ ተግባራት የተሳሰሩ የኩባንያው ሚስጢር ወይም የኩባንያው ማንዋል አየር መንገዱን ሊስጠይቅ በሚችል መልኩ ለራስ መጠቀም ወይም በህግ መሰረት ብቃት ባላቸው ባለስልጣናት ካልተጠየቀ በስተቀር ከአየር መንገዱ ወይም ከደንበኞች ተዛማጅ የሆነውን የኩባያውን ማንኛውንም ዳታ ወይም ሚስጢር አሳልፎ አለመስጠት፡፡
  1. የህብረቱ እንዲሁም የአሰሪው ስራ አመራር መብት እና ሃላፊነት
   1. በህብረቱ የተያዘ መብት
 1. ህብረቱ በህግ፣ በመመሪያ እና በዚህ ስምምነት በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳዮችን በተመለከተ ከአሰሪው የመወያየት ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው
 2. ህብረቱ በዚህ ስምምነት በተገለፀ መልኩ በአሰሪው ስራ አመራር መሳተፍ ይችላል
 3. በህብረቱ ውስጣዊ ደንብ መሰረት ይህንን ለማድረግ የተፈቀደላቸው የህብረቱ አመራር ብቻ ከአሰሪው ወገን በዚህ የህብረት ስምምነት ሂደት በህብረት መሳተፍ ይችላሉ
 4. ከህብረቱ የስራ አስፈፃሚ ሹሞች፣ የምክር ቤቱ አባላት የመደብር አስተናጋጆች እና ከኦዲት ኮሚቴ አባላት ሰብተቀር በዚሁ ስምምነት አዋጅ መሰረት ለህብረቱ በተሰጠው እንዲህ አይነት ተግባር ወይም መብት መፈፀም የሚችል ሌላ ሰራተኛ አይኖርም፡፡
   1. የህብረቱ ግዴታ/ተግባር

ህብረቱ

 1. የድርጅቱን የውስጥ ፖሊሲ እና አዋጅ፣ በአሰሪ እና ሰራተኛ አስተዳደር ሌሎች መምሪያዎች እና ደንቦች  እንዲሁም የዚህ ስምምነት ህጎችን የማወቅ
 2. ከድርጅቱ በመመካከር በአዋጁ ወይም በነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት የተከለከሉ ከአላማዎቹ ተቃራኒ የሆኑ ተግባራትን በሙሉ መከላከል እና እንደዚህ አይነት ድርጊት ከመከሰት ለመከላከል አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል
 3. አባላቱ የአዋጁ መሰረታዊ መርህ የአሰሪ እና ሰራተኛ ህግ እና ደንብ እንደዚሁም የስምምነቱ እስታንዳር እና ድጋጌ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ወይም ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ያደርጋል፡፡
 4. ድርጅቱን እና ሰራተኛውን በተመለከተ መመሪያ እና ፖሊሲ ለማመንጨት ተነሳሽነቱን መውሰድ እና የሚሻሻለውን ሃሳብ ማቅረብ
 5. የድርጅቱን እድገት እና ትርፋማነት ለማሻሻል ድጋፍ ማድረግ በሚችል አካባቢ ሁሉ በህጉ መሰረት ከድርጅቱ ጋር መተባበር እና አጋርነትን ማሳየት እንደዚሁም ስለ የስራ ጤንነት እና የስራ አካባቢ ሁኔታ በድርጅቱ እና በሰራተኞቹ መካከል አስተማማኝ የስራ ግንኙነት ለመፍጠር በሚረዱ ነጥቦች ዙሪያ ከድርጅቱ ጋር ሃሳብ መለዋወጥ
 6. የህብረቱ ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ምክር ቤት፣ የመደብር አስተናጋጆች አባላት ዝርዝር በሙሉ በጽሁፍ ለድርጅቱ ማስተላለፍ
   1. የህብረቱ የተሳትፎ ነጥብ

ሀ. ህብረቱ በዚህ ስምምነት የተመለከቱን በሚከተሉት ስራ አመራር ተግባራት የሚሳተፍ ይሆናል፡፡

 1. ድርጅቱ ክፍት እንዲሆኑ ባደረጋቸው የውስጥ የስራ መክፈቻ እና ለሰራተኞቹ ጨረታ በመክፈት
 2. በሰራተኞች የዲሲፕሊን ኮሚቴ

ለ. ህብረቱ ከድርጅቱ የስራ አመራር ተዛማጅ ባልሆኑት አካባቢዎች/ነጥቦች በጉዳዩ አስፈላጊነት የሚወሰን ከአሰሪው ጋርበሚደረሰው ስምምነት መሰረት ማህበራዊ ተግባራት  በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡

አንቀጽ አራት
የጋራ ምክክር እና የሁለትዮሽ ግንኙነት

  1. የምክክር ስብሰባ /ማህበራዊ ውይይት
   1. የጋራ ምክክር አላማው የሰራተኞች እና የአየር መንገዱ ምርታማነት እንዲጨምር ከማሰብ በድርጅቱ እና በህብረቱ መካከል ያለውን የኢንደስትሪን መልካም ግንኙነት እና ሰላም እንዲጨምር ለማድረግ ነው፡፡
   2. መደበኛ ስብሰባ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ድርጅቱ እና ህብረቱ በአንዱ ወገን ጥያቄ የዚህን ስምምነት፣ የድርጅቱን ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ደንብ ትርጓሜ ወይም የተለመዱ ተግባራት ወይም  በርካታ ሰራተኞችን በጋራ ሊጎዱ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ለመመካከር በእያንዳንዱ ወር የመጨረሻው ሀሙስ ቀን ሊገናኙ ይችላሉ፡፡ የመጨረሻው ሀሙስ በሳምንቱ መጨረሻ ወይም በአላት ላይ ከዋለ ስብሰባው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ማንኛውም ወገን ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲተላለፍ መጠየቅ አይችልም፡፡ (በህብረቱ በእንደዚህ አይነት ስብሰባ ግለሰባዊ ቅሬታ ውውይይት ካልተደረገ በስተቀር)
  1. አስቸኳይ /ልዩ ስብሰባ
   1. የሚቀጥለውን ወርሃዊ ስብሰባ ከመካሄዱ አስቀድሞ የጋራ ትኩረት በሚያስፈልጉ አስቸኳይ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት በእያንዳንዱ አመት ማንኛውም ወገን 5 ጊዜ አስቸኳይ/ልዩ ስብሰባ መጥራት ይችላል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ተቸማሪ አስቸኳ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡
   2. የስብሰባው ቀን በሁለቱም ወገኖች የጋራ ስምምነት የሚወሰን ይሆናል፡፡
   3. እንዲህ አይነት ያለ ስብሰባ በሙሉ በአንዱ ወገን በቀረበው የአጀንዳ ጉዳይ አስቸኳይ እና ውጤታማ ውሳኔ መውሰድ የሚችሉ በሀላፊነት ያሉ ሹሞች የሚሳተፉበት ይሆናል፡፡
   4. በእንደዚህ አይነት ስብሰባ ከአሰሪው ከ3 በላይ ተወካዮች እና ከህብረቱ 3 ሹሞች በላይ መሳተፍ የለሌባቸው ሲሆን ነገቸር ግን የስብሰባውን አስፈላጊነት እና አጀንዳው ክብደት ግምት ውስጥ በማስገባት ከህብረቱ እስከ 10 ሹሞች በስፍሰባው ሊሳተፉ ይችላሉ፡፡
   5. የአጀንዳው ጉዳይ ቢያንስ በቅድሚያ ከአንድ ሳምንት በፊት ሊተላለፍ ይችላል፡፡ በዚሁ አጀንዳ ጉዳይ ያልተሸፈነው ጉዳይ በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ካልሆነ በስተቀር በእንደዚህ አይነት ስብሰባ ወይይይት አይደረግበትም፡፡
   6. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማንኛውም ወገን ከህጋዊ አማካሪ መምጣት ወይም ምስክሮችን መጥራት ወይም ማረጋገጫ ማቅረብ ይችላል፡፡
   7. አጀንዳውን ከሚሸፍኑ ጉዳዮች በፊት የተካሄደው ስብሰባ በሚቀጥለው ቀን የሚቀጥል ይሆናል
   8. የውይይቱ ቃለ ጉጀባኤ፣ ተቀባይነት ያገኘ የመፍትሔ ሃሳብ፣ ውሳኔ እና /ወይም ስምምነት እንደአግባብነቱ በአሰሪው ወይም በህብረቱ የሚመዘገብ ሲሆን በሁለቱም ወገኖች ለጅምሩ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡
   9. በእንደዚህ አይነት ስብሰባ የተደረሰው ስምምነት በሁለቱም ወገኖች ፊርማ ተፈፃሚ ይሆናል ነገር ግን ስምምነቱ ከተደገመ፣ ከተሻሻለ ወይም አዲስ የስራ ቅጥር የሚፈጥር ከሆነ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቲር ከተመዘገበ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን የዚሁ ስምምነት አንዱ ተጨማሪ አካል ይሆናል፡፡
   10. የመደበኛ ስብሰባ የስብሰባው ቅደም ተከተል ከላይ በአንቀጽ 4.2.1 እስከ 4.2.9 በተጠቀሰው መሰረት ተመሳሳይ ይሆናል፡፡
  2. የሁለትዮሽ ግንኙነት

ህብረቱ በሁሉም ተግባቦቶች በአሰሪው በኮርፖሬት የሰው ሃብት ስራ አመራር ክፍል በኩል የሚገናኝ ይሆናል፡፡ እንደዚሁም አሰሪው በኮርፖሬት የሰው ሃብት ስራ አመራር ክፍል በኩል ከህብረቱ የሚገናኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ህብረቱ የከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ ሹሞች ትኩረት የሚያስፈልገው ማንኛውም ጉዳይ በሚገጥምበት ጊዜ ህብረቱ ከከፍተኛ ስራ አስፈፃሚዎች በተግባቦት በኩል በቀጥታ ሊጀገናኝ ይችላል፡፡

ምዕራፍ ሁለት የስራ ሁኔታ
አንቀጽ አምስት
የሙከራ ጊዜ

  1. ከመጀመሪያ የቅጥር ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን የአንድ ሰራተኛ የመጀመሪያዎቹ 45 የስራ ቅጥር ቀናት የሙከራ ጊዜ የሚሆን ሲሆን ይህም በስራ ቅጥር ውሉ በግልጽ የተቀመጠ ነው፡፡ በዚሁ የሙከራ ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ ቅድመ ማስታወቂያ፣ ቅድመ ክፍያ እና ካሳ  ለሰራተኛው መስጠት ሳያስፈልግ የስራ ቅጥሩን ማቋረጥ ይችላል፡፡
  2. አንድ ሰራተኛ ለድርጅቱ ቅድመ ማስታወቂያ መስጠት ሳያስፈልገው በሙከራ ጊዜ በማንኛውም ሰአት መልቀቅ ይችላል፡፡
  3. በዚሁ ስምምነት የተመለከቱት አከላለፆች ካልሆነ በስተቀር የድርጅቱ ህግ እና ፖሊሲ የዚሁ ህብረት ስምምነት ደንቦች ከሙከራ ጊዜ ባለ ማንኛውም ሰራተኛ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡

አንቀጽ ስድስት
የስራ ሰአታት

  1. መደበኛ የስራ ሰአት
 1. “መደበኛ የስራ ሰአታት” በህግ፣ በህብረት ስምምነቱ ወይም በድርጅቱ ስራ መምሪያ መሰረት አንድ ሰራተኛ ሃላፊነቱን የሚወጣባቸው የስራ ሰዓታት ወይም እራሱን ፣በስራ ዝግጁ የሚያደርግበት ማለት ነው፡፡
 2. በዚሁ ስምምነት ካልተገለፀ በስተቀር የድርጅቱ አንድ ሰራተኛ መደበኛ የስራ ሰዓታት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ8 ሰዓታት ያልበለጠ እና በሳምንት ከ40 ሰዓታት ያልበለጠ ነው፡፡ ነገር ግን በዚሁ የድርጅቱ ክፍሎች ስራዎቹ በፈረቃ በሚከናወኑበት ጊዜ መደበኛ የስራ ሰዓት መርሃ ግብሩ ሊቀያየር ይችላል፡፡
 3. የመደበኛ እና ፈረቃ የስራ ሰዓታት ጊዜ መጀመሪያ እና መጨረሻ በድርጅቱ ውስጣዊ መመሪያ በተገለፀው/በተወሰደው መሰረት ይሆናል፡፡
 4. የድርጅቱ የስራ ሰዓታት በሳምንት ውስጥ ለእያንዳንዱ የስራ ቀን በእኩል የሚሰራጭ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በተሰጠው ስራ ባህሪ ምክንያት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማንኛውም የሳምንቱ የስራ ቀናት የስራ ሰዓታት ብዛት ማከፋፈል ወይም መቀነስ እንደዚሁም ልዩነቱን ለሳምንቱ ቀሪ ቀኖች ማሰራጨት ይቻላል፡፡ ነገር ግን በማንኛውም የስራ ቀን የሚኖረው መደበኛ 8 የስራ ሰዓታት ከ2 ሰዓት በላይ ማራዘም ወይም መጨመር አይቻልም፡፡
  1. ከስራ ማረፍ - እረፍት

ሀ. በመደበኛ የቀኑ የስራ ሰዓታት የሚሰሩ ሰራተኞች የስራው ሁኔታ ወይም ባህሪ ካላስገደደ በስተቀር ከእኩለ ቀን በፊት የ15 ደቂቃ ከስራ ላይ እረፍት እና አንዱ ሙሉ ሰዓት የምሳ እና ከሰዓት በኋላ 15 ደቂቃ እረፍት የማግኘት መብተ አላቸው፡፡
ለ. የሚሰጠው የማንኛውም የፈረቃ ስራ፣ እረፍት በጠቅላላ ለሁለት እረፍቶች ሲካፈል ከ30 ደቂቃ በላይ መሆን የለበትም፡፡
ሐ. ከስራ ላይ እረፍት ማለትም የምሳ ወይም የእራት እረፍት በድርጅቱ ለእያንዳንዱ ክፍል በሚሰጠው መርሃ ግብር መሰረት ለሰራተኞች የሚሰጥ ይሆናል፡፡
መ. ድርጅቱ አንድ ሰራተኛ በምሳ ወይም በእራት እረፍት ላይ ሳለ እንዲሰራ ከፈለገ እና ሳራተኛውም በዚሁ የእረፍት ጊዜው ያንን ሰአት እየሰራ ካሳለፈ ድርጅቱ ሌሎች ሰራተኞች የተጠቀሙበትን ያህል እኩል የሆነ ተዛማጅ የምሳ ወይም የዕራት እረፍት የሚሰጥ እና /ወይም ምግብ /አገልግሎት የሚያዘጋጅለት ይሆናል፡፡

ከመደበኛው እለታዊ የስራ ሰዓታት ወይም ከአንቀጽ 6.1/4/ ጎን ለጎን ሳምንታዊ የተከፋፈለ ሳምንተዊ የስራ ሰዓታት በላይ እንዲሰራ የተፈለገ ወይም የተመደበ ማንኛውም ሰራተኛ የስራ ላይ እረፍት 15 ደቂቃ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ ሰባት
የፈረቃ ስራ

  1. በድርጅቱ የስራ መርሃ ግብር እንዲሁም በዚህ ስምምነት አንቀጽ 6 በተመለከተው መሰረት ማንኛውም ሰራተኛ በድርጅቱ የቀን፣ ምሽት ወይም የሌሊት ፈረቃ በሁሉም መደበኛ ፈረቃዎች እንዲሰራ ያስፈልጋል፡፡
  2. በድርጅቱ ስራ ባህሪይ ምክንያት በተለየ ካላስፈለገ በስተቀር ማንኛውም ሰራተኛ በማንኛውም ቀን፣ ምሽት ወይም የሌሊት ፈረቃ ከአንድ ወር በላይ እዲሰራ አይመደብም፡፡ ነገር ግን  ድንገተኛ ክስተት ወይም አስገዳጅ ሁኔታ በሚኖርበት ጊዜ በሌሊት ፈረቃ እየሰራ ያለ ማንኛውም ሰራተኛ ከአንድ ተጨማሪ መርሃ ግብር በላይ እዲሰራ አይጠየቅም፡፡ የፈረቃ መርሃ ግብር ለውጥ በሚደረግበት ጊዜ የፈረቃ /ፈረቆች/ቀን፣ ምሽት፣ ሌሊት/ የሚታዩ ወይም የሚጠበቁ ይሆናል፡፡
  3. በፈረቃ የሚሰሩ ሰራተኞች የመደበኛ የስራ ሰዓታት መጀመሪያ በተወሰነው ፈረቃ ስራቸውን የጀመሩበት ሰዓት ይሆናል፡፡ ተፈፃሚ የሚሆን የፈረቃ ፕሪሚየም/አረቦን አንድ ሰራተኛ በሚመለከተው ፈረቃ ስራውን በጀመረበት ሰአት መሰረት የሚሰላ ይሆናል፡፡
  4. የፈረቃ ፕሪሚየም/አረቦን ክፍያ ለማስላት ያለመ የፈረቃ ስራ መርሃ ግብር መጀመሪያ ሰዓት ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ግምት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡

የቀን ፈረቃ ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ
የምሽት ፈረቃ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ
የሌሊት ፈረቃ ከሌሊቱ 6፡00 ጀምሮ ይሆናል፡፡

  1. በሽፍት ስራ የተመደበ ሰራተኛ ፈረቃው በሚቀየርበት ወይም የእለት እረፍት በሚወስድበት ጊዜ የሰራተኛው ቀሪ ሰዓት በእለቱ እንዲሰራ ተመድቦበት የነበረ መደበኛ የስራ ሰዓት ከተጠናቀቀው የስራ ሰዓት በኋላ ከ16 ሰዓት ጀምሮ የሚሰላ ይሆናል፡፡
  2. በመደበኛ የኦፊስ ሰዓታት ብቻ ለሚሰሩ ሰራተኞች የሳምንቱ የእረፍት ቀናቸው በአዋጁ መሰረት የሚሰላ ወይም የሚጀምር ይሆናል፡፡
  3. የፈረቃ መርሃ ግብሩ ወደ 2 ካልተከፋፈለ ወይም ካልተሰራጨ በስተቀር በመደበኛ የኦፊስ ሰዓታት ወይም በመደበኛ የፈረቃ ስራ ከሁለቱም በአንዱ የመደበኛ ስራውን እንዲያከናውን የተመደበ ሠራተኛ ድርጅቱ 8 ወይም ከዚያ በታች ሰዓታት እንዲሰራ እንደያዘው 8 ሰዓታት እንደሰራ ተደርጎ ይያዝለታል፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ 8 የስራ ሰዓታት መርሃ ግብር ወደ 2 በሚከፈልበት ጊዜ በፈረቃ ላይ ላሉት ሰራተኞች ከስራ ቦታ እና ወደ ቤታቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡
  4. የድርጅቱ የስራ ተግባራት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እስካላደረሰ ወይም ድርጅቱ ማንኛውም ተጨማሪ ወጭ አንዲያወጣ ምክንያት እስካልሆነ ድረስ በስራ ደረጃ እኩል ሃላፊነት ያላቸው የፈረቃ ሰራተኞች በቅድሚ የቅርብ ተቆጣጣሪቸው ፈቃድ በማግኘት እና በማሳወቅ እርስ በእርሳቸው የፈረቃ መርሃ ግብራቸውን መቀያየር ይችላሉ፡፡
  5. በምሽት ፈረቃ የሚሰሩ ሰራጠኞች ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በፊት 1፡00 ሰዓት የእራት ሰዓት ይሰጣቸዋል፡፡
  6. የምሽት እና ሌሊጀት ፈረቃ አረቦን/አበል

ሀ. የፈረቃ አረቦን በምሽት ወይም ሌሊት ፈረቃ ተመድበው ለሚሰሩ ሰራተኞች ከዚህ በታች የተመለከተው ብቻ ይከፈላል፡፡

የስራ ደረጃ

የምሽት ፈረቃ

የሌሊት ፈረቃ

1 – 4

ብር 2.40 በሰዓት

ብር 2.70 በሰዓት

5 – 9 እና 30 – 33

ብር 3.20 በሰዓት

ብር 3.55 በሰዓት

10 – 17 እና ከ34 በላይ

ብር 3.80 በሰዓት

ብር 4.20 በሰዓት

ለ. አንድ ሰራተኛ በምሽት ፈረቃ ስራ ጀምሮ እስከ ሌሊት ፈረቃ መስራት በሚቀጥልበት ጊዜ የዚሁ ሰራተኛ የፈረቃ አበሉ እሱ በሰራበት ፈረቃ በተገለፀው ተመን መሰረት ይሆናል፡፡
ሐ. አንድ ሰራተኛ በምሽት ፈረቃ ስራ ጀምሮ እስከ ቀን ፈረቃ ድረስ እየሰራ በሚቀጥልበት ጊዜ የሰራተኛው የፈረቃ አበሉ የሰራበትን ጠቅላላ የሰዓታት ብዛት በሌሊት ፈረቃ ተምን የሚሰላ ይሆናል፡፡
መ. በፈረቃ የስራ ሰዓታት ውስጥ ትርፍ ሰዓት የሚሰራ ሰራተኛ የትርፍ ሰዓት በተሰራበት ፈረቃ ከትርፍ ሰዓት ክፍያ በተጨማሪ ተፈፃሚ የሚሆነው የፈረቃ አበል የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ ስምንት
የትርፍ ሰዓት ስራ
8.1. የትርፍ ሰዓት ክፍያ ወሰን እና መብት ያላቸው ሰራተኞች

 1. የትርፍ ሰዓት ስራ ማለት ከላይ በአንቀጽ 6.1 እንደተገለፀው ከመደበኛ ስራ ሰዓታት በላይ በተጨባጭ የተሰራን ስራ ወይም ለሁለት ሳምንታት ጊዜ የሚከፋፈለው አማካኝ 80 ሰዓት ነው፡፡
 2. የትርፍ ሰዓት ስራ በሚከተሉት ሁኔታዎቸም እና በድርጅቱ ስልጣን ባለው ተወካይ ግልጽ መመሪያ መሰረት መፈቀድ አለበት፡፡ የትርፍ ሰዓት ስራ ትዕዛዝ እና ማረጋገጫ ስራውን ለማድረግ ብቃት ባላቸው ሰራተኞች መካከል በእኩል ሚከፋፈል ሲሆን የዚሁ መዝገብ በአግባቡ መያዝ አለበት፡፡
 3. በዚሁ አንቀጽ መሰረት የሚከፈል የትርፍ ሰዓት ክፍያ የምግብ አብሳዮች እና የበረራ አስተናጋጆች አባላት ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከምግብ አዘጋጅ እና የበረራ አስተናጋጅ አባላት በስተቀር በአውሮፕላን ይሁን በሌና ማንኛውም የማጓጓዣ ዘዴ ለስራ በሚጓዙበት ጊዜ ማንኛውም ሰራተኛ ትርፍ ሰዓት ክፍያ መብት አይኖረውም፡፡
 4. አንድ ሰራተኛ በድርጅቱ ስራ ከ8 ሠዓታት በላይ በሚወስድ የበረራ ጊዜ ሳለ ከውጭ በእረፍት ቀኑ እንዲመለስ በሚጠየቅበት ጊዜ እና የሚቀጥለው ቀን የስራ ቀን ከሆነ የሚደርስበት ቀን እንደእረፍት ቀኑ የሚቆተር ይሆናል፡፡ በተጨማሪም አንድ ሰራተኛ ለኩባያው ስራ በእረፍት ጊዜው እንዲጓዝ በሚጠየቅበት ጊዜ ለመጀመሪያው ቀን ብቻ ማካካሻ እረፍት የሚሰጠው ይሆናል፡፡
 5. የሌሊት ፈረቃ ስራውን ካከናወነ በኋላ የሚለቅ ሰራተኛ የትርፍ ሰዓት እዲሰራ አይጠየቅም፡፡ ነገር ግን ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት እና በድርጅቱ መመሪያ መሰረት አንድ ሰራተኛ ለሁለት ተከታታይ ሽፍቶች እንዲሰራ ሲጠየቅ ለሰራው ትርፍ ሰዓታት ከሚከፈለው የትርፍ ሰዓታት ክፍያ በተጨማሪ በሚቀጥለው ቀን የማካካሻ እረፍት የሚሰጠው ይሆናል፡፡

8.2. የትርፍ ሰዓት ስራ ሁኔታ

 1. ድርጅቱ በሚከተሉት ሁኔታዎች መሰረት ማንኛውንም ሰራተኛ የትርፍ ሰዓት ስራ እንዲሰራ የመጠየቅ መብት አለው፡፡

ሀ. ድርጅቱ እዲከናወን የሚፈልገውን ማንኛውንም አስቸኳይ ስራ ወይም
ለ. ድርጅቱ ስራው እንዲሰራ አማራጭ በማያገኝበት ጊዜ ወይም
ሐ. አደጋ ወይም ስጋት ድባብ በሚከሰትበት ጊዜ ወይም
መ. ከቁጥጥር ውጭ በሆነ በማንኛውም ምክንያት ወይም ምንም አይነት ፋታ የማይሰጥ ቀጣይነት ያለው ስራ ሲኖር ወይም በተለያየ ምክንያት ከስራ ቦታ ውጭ ያሉትን ወይም በእረፍት ላይ ያሉ ሰራተኞች ለመተካት ሲፈለግ

 1. ከላይ በአንቀጽ 8.2/1/ሀ በተገለፁት ምክንያቶች የትርፍ ሰዓት ስራ የስራ ሰዓታት  በማንኛውም ወር ውስጥ ከ20 ሰዓታት በላይ ወይም በማንኛውም ነጠላ 24 ሰዓታት ከሁለት ሰዓት በላይ ወይም በማንኛውም ከአንድ መቶ ሰዓታት በላይ መሆን የለበትም፡፡

8.3. የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስሌት

 1. ከዚህ በታች በተመለከቱት ጊዚያት ውስጥ ለተከናወነ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ በተጨባጭ ደሞዝ በሰዓት ተመን መሰረት ተባዝቶ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

ሀ. በ06፡00 ሰዓት እና 22፡00 ሰዓታት መካከል ለተከናወነ ስራ የሰዓት ተመኑ ½ ጊዜ
ለ. በ22፡00 ሰዓት እና 06፡00 ሰዓታት መካከል ለተከናወነ ስራ የሰዓት ተመኑ 12/3 ጊዜ
ሐ. በሳምንቱ የእረፍት ቀናት የተከናወነ የትርፍ ሰዓት ስራ በሰዓት ተመኑ ሁለት ጊዜ
መ. በዚህ ስምምነት በተዘረዘረው ህዝባዊ በዓላት ለተከናወነ የትርፍ ሰዓት ስራ በሰዓት ተመኑ 2 ጊዜ በፖሊሲው መሰረት ኩባያው በሚያከብረው ዋዜማ እንዲሰራ የተመደበ ሰራተኛ በበአላት ተመን የትርፍ ሰዓታት ሚከፈለው ይሆናል፡፡

 1. በማንኛውም ወር በመጀመሪያዎቹ 15 ቀናት የተገኘ የትርፍ ሰአት ክፍያ ከተጠቀሰው መደበኛ እና ወርሃዊ ደሞዝ በጋራ ሚከፈለው ይሆናል፡፡
 2. ሰራተኛው ሲጠይቅ እና ድርጅቱ ሲስማማ የተሰራ የትርፍ ሰዓት በእረፍት ጊዜ ሊካካስ ይችላል፡፡ ለትርፍ ሰዓት ስራ ከቤቱ የሚጠራ አንድ ሰራተኛ ማንኛውም እረጅም ወይም ተገቢ በሚሆንበት በተጨባጭ በሰራው ሰዓት ወይንም ዝቅተኛ 5 ሰዓታት ይኖሩታል፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ
ሳምንታዊ የእረፍት ጊዜ (የእረፍት ቀን)
አንድ ሰራተኛ በ7 ቀናት ውስጥ በተከታታይ የ48 ሰዓታት እረፍት የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን የፈረቃ ስራው ባህሪ እንደዚህ አይነት እረፍት በማይፈቅድበት ወይም ሰራተኛው ይህንን ከጠየቀ በዛች ሳምንት ውስጥ ሁለት የተለያዩ የረፍት ቀናት ይሰጠዋል፡፡

አንቀጽ አስር
እረፍት
10.1. ትርጓሜ
10.1.1. እረፍት ማለት ከክፍያ ወይም ካለ ክፍያ ከስራ የሚቀሩበት የተፈቀደ እረፍት እና በዚህ ስምምነት፣ ህግ ወይም በድርጅቱ ውስጣዊ ፖሊሲ መሰረት የተሰጡን የተለያዩ እረፍቶች የሚያካትት ነው፡፡
10.1.2. አመታዊ እረፍት ለማስላት ያለመ (የሰራተኛው ሳምንታዊ እረፍት) ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም ከዚህ በታች በአንቀጽ 10.2 የተመለከቱ ህዝባዊ በአላት አይቆተሩም
10.2. ህዝባዊ በአላት
10.2.1. የድርጅቱ ሰራተኖች በሙሉ የሚከተሉትን ህዝባዊ በአላት ማወቅ አለባቸው፡፡
ሀ. የኢትዮጵያ አዲስ አመት መስከረም አንድ
ለ. መስቀል
ሐ. ኢድአልድሃ/አረፋ በዋለበት ቀን 
መ. ገና ታህሳስ 28 ወይም 29
ሠ. ጥምቀት ጥር 11
ረ. መውሊድ በዋለበት
ሰ. የአድዋ ድል የካቲት 23
ሸ. ሚያዚያ 27
ቀ. ስቅለት በዋለበት ቀን
በ. ፋሲካ በዋለበት ቀን
ተ. የላባደሮች ሚያዚያ 23
ቸ. ግንቦት 20 ደርግ የወደቀበት ቀን
ነ. ኢድ አልፈጥር በዋለበት ቀን
በፌደራል መንግስት ወይም በክልል መንግስታት ተፈፃሚነት ባው አዋጅ መመሪያ እና በህዝብ ማስታወቂያ እንዲከበሩ ታወጀላቸው ህዝባዊ በአላት ለሚመለከተው የድርጅቱ ሰራተኛ እንደበእ ሚቆጠር ይሆናል፡፡
10.2.2. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.1 ከተዘረዘሩት በስተቀር ድንገተኛ በአላት በቀን መቁጠሪያ ያልተመዘገቡ በሚሆኑበት ጊዜ እና ድርጅቱ ይህንን በአል ያላሳወቀ በሚሆንበት ጊዘጄ ሁሉም ሰራተኞች በመደበኛ የስራ ቦታቸው እንዲገኙ ያስፈልጋል፡፡
10.2.3. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.2. ደንብ መሰረት ሰራተኞች እዲሰሩ ከተመደቡ ድርጅቱ በስራ ላይ ላሉት ሰራተኞች በበአል የሰዓታት ክፍያ ተመን መሰረት ክፍያ የሚፈፅም ይሆናል፡፡ ይህም ሆኖ ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ካልተመደቡ ድርጅቱ ለቀን ፈረቃ ሰራተኖች በሚያደርገው ተመሳሳይ መንግድ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ለመመለስ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
10.3. አመታዊ እረፍት
10.3.1. አጠቃላይ

 1. አንድ ሰራተኛ በመርሃ ግብሩ በተቀመጠው  እና ለድርጅቱም ሆነ ለሰራተኛው አመች በሆነ መልኩ በሚከተለው አኳኋን ያልተቋረጠ ከክፍያ ጋር አመታዊ እረፍት የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡፡
 2. ለዚሁ የአመታዊ እረፍት ስሌት አላማ ሲባል የአመታዊ እረፍት ጊዜው ታህሳስ 23 እስከ ታህሳስ 22 የሚቆጠር ይሆናል፡፡
 3. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 የተደነገገው ድንጋጌ ተገዥ የሚሆን አመታዊ የእረፍት ጊዜው ወቅቱን ከድርጅቱ የበጀት አመት ለማቆራኘት ይቻል ዘንድ በህብረቱ እና በድርጅቱ የጋራ ስምምነት መሰረት ለወደፈቱ ሊቀየር ይችላል፡፡

10.3.2. የአመት እረፍት ቀናት አሰጣጥ /አመዳደብ

 1. ለአንድ አመት ያገለገለ ሰራተኛ 18 የስራ ቀናት አመታዊ እረፍት የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
 2. ከአንድ አመት በላይ ያገለገለ ማንኛውም ሰራተኛ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 ከተተቀሰው በተጨማሪ በእያንዳንዱ አመት አንድ የስራ ቀን ዓመታዊ እረፍት መብት ይኖረዋል፡፡
 3. ከላይ በአንቀጽ 10.3.2 /2 ከተመለከተው የአንድ የእረፍት ቀን ተጨማሪ ስሌት ሲባል ከዚሁ አመት አንፃር ከታህሳስ 22 በፊት የተቀጠረ ማንኛውም ሰራተኛ አንድ አመት እንዳገለገለ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
 4. ከአንድ ዓመት በታች ያገለገለ ወይም ከዓመት በፊት ወዲያውኑ የተቀጠረ ማንኛውም ሰራተኛ የሚከተለውን ዓመታዊ የእረፍት ቀናት የማግኘት መብት ሲኖረው እንዲሁም  በሚከተለው አኳኋን የአገልግሎት ጊዜ ስሌት አመታዊ እረፍት የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡

የሰራተኛ የአገልግሎት ጊዜ (ከጥር በፊት በወራት)

ሰራተኛው ዓመታዊ እረፍት ቀናት የማግኘት መብቱ ብዛት (በስራ ቀናት)

1

1

2

2

3

3

4

5

5

6

6

7

7

8

8

9

9

10

10

12

11

13

12

14

10.3.3. አመታዊ እረፍት የሚሰጥበት ደንብ /ቅደም ተከተል

 1. አንድ ሰራተኛ ከ12 ወራት አገልግሎት በኋላ በአመቱ የመጀመሪያ ዓመታዊ እረፍ የመውሰድ መብት ሲኖረው ከዚህ በኋላም የእረፍት መብት ይኖረዋል፡፡ በድንገተኛ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር አዲስ ሰራተኛ ለድርጅቱ በተከታታይ 3 ወራት አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ብቻ አመታዊ እረፍት የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
 2. ዓመታዊ እረፍት በድርጅቱ እቅድ መሰረት እንዲሁም የሁለቱም ሰራተኛ እና ድርጅቱ ጥቅም ውስጥ በማስገባት በዓመት ውስጥ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ነገር ግን የአንድ ሰራተኛ የአገልግሎት ጊዘው ከአንድ አመት በታች ከሆነ ከአገልግሎት ጊዜው እኩል ሆነ በአገልግሎት ዓመት መጨረሻ ላይ ዓመታዊ እረፍት የመውሰድ መብት ይኖረዋል፡፡
 3. አንድ ሰራተኛ አመታዊ እረፍት በተከማቸበት አመት በዓመቱ የተከማቸውን ዓመታዊ እረፍት ሊጠቀምበት ይችላል፡፡
 4. አንድ ሰራተኛ በዚሁ ህብረት ስምምነት ደንብ መሰረት ዓመታዊ እረፍት የማግኘት መብት ሲኖረው እንደዚህ አይነት እረፍት በድርጅቱ የተግባር እቅድ መሰረት የሚጥ ይሆናል፡፡
 5. በእያንዳንዱ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ አንድ ሰራተኛ አመታዊ እረፍት ለመውሰድ ያቀደበትን ጊዜ በተመለከተ 3 ምርጫዎቹን የሚያሳይ የጽሁፍ ፕሮፖዛል ለቅርብ ተቆጣጣሪው የማቅረብ መብት ይኖረዋል፡፡ እንደዚሁም ተቆጣጣሪው በእያንዳንዱ ጥቅት ወር ውስጥ ሰራተኛውን ጥቅም እና የድርጅቱን ስራ ሁለቱንም ግምት ውስጥ በማስገባት ከምርጫዎቹ አንዱን በማጽደቅ ተፈፃሚ ያደርጋል፡፡ የፀደቀው ዓመታዊ የእረፍት መርሃ ግብር በሰራተኛው የግል ፋይል አባሪ የሚደረግ ሲሆን በመምሪያው የሚቀመጥ ይሆናል፡፡ ፕሮግራሙም በሚጸድቅበት ጊዜ አመች በሆነ የመገናኛ /የተግባቦት ዘዴ በኩል ለሰራተኛው የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
 6.  የሰራተኛው የመጀመሪያ ምርጫ በተፈቀደው የስራ መርሃ ግብር መሰረት ሚከበር ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሰራተኛው ምርጫ በተመሳሳይ ተቆጣጣሪ ስር ካሉት የሌሎች ሰራተኞች ምርጫ የሚቃረን ከሆነ ከፍተኛ ቀደምትነት /ሲነሪቲ ያለው ሰራተኛ ቅድሚያ ሚሰጠው ይሆናል፡፡ በቀደምትነት መሰረት ውሳኔ መስጠት በማይቻልበት ጊዜ ይህንን ለመወሰን የምዝገባ ቁጥር ቅደም ተከተል ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
ድርጅቱ በተቻለ መጠን ሰራተኛው ዓመታዊ እረፍቱን እንዲወስድ ትብብር ያደርጋል ነገር ግን የሰራተኛው ዓመታዊ እረፍት በስራ ጫና ምክነያት በሚተላለፍበት ጊዜ በቀደምትነት ጫና ሳያድርበት በሚቀጥለው ዓመት በመጀመሪያው ምርጫ አመታዊ እረፍቱን የሚወሰድ ይሆናል፡፡  

10.3.5. አጠቃቀም
አመታዊ እረፍት ማከማቸት እና ማስተላለፍ

 • ድርጅቱ ሰራተኛው በተቻለ መጠን አመታዊ እረፍቱን እንዲወስድ ማድረግ አለበት፡፡
 • አመታዊ እረፍት ሰራተኛው በሰራበት ወር ውስጥ የሚከማች ሲሆን ክፍያ ተቀብሎበት ይህንን ባገኘበት በሚቀጥለው አመት ውስጥ የሚወስድ ይሆናል፡፡
 • የተመለከተው ህገ ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ሰራተኛ አመታዊ እረፍቱን በከፊል ለመውሰድ በሚጠይቅበት ጊዜ እና ድርጅቱም በሚስማማበት ወቅት እረፍቱን ለሁለት በማካፈል ሊሰጥ ይችላል፡፡
 • በሰራተኛው ጥያቄ እና ስምምነት ወይም የስራው ሂደት ይህንን ለማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ የሰራተኛው ዓመታዊ እረፍት ጊዜ ድርጅቱ ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ ነገር ግን በኦፕሬሽን /በስራው መስፈርት ወይም በስራው ጫና ምክንያት የአንድ ሰራተኛ አመታዊ እረፍት ጊዜ ማስተላለፍ በሚያስፈልግበት ጊዜ ለሚመለከተው ሰራተኛ ቢያንስ ከ15 ቀናት በፊት በግልጽ ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡
 • በማንኛውም ዓመት የተላለፈው አመታዊ እረፍት በምንም አይነት መንገድ ከተከታታይ 2 ዓመታት በላይ ሊተላፍ አይችልም፡፡

10.3.6. ከሰራተኛ ዓመታዊ እረፍት ተዛማጅ የሆነ ክፍያ

 • በዓመት እረፍት የሚወጣ ሰራተኛ ከጠየቀ የሰራበትን ቀናት ያካተተ ደሞዝ እና የእረፍት ጊዜ ደሞዝ ጭምር ይከፈለዋል፡፡
 • በዓመት እረፍት ላይ ላለ ሰራተኛ ተፈፃሚ የሚሆን የደሞዝ መጠን በስራ ላይ ሰለ ማግኘት ከነበረበት የገንዘብ መጠን እኩል መሆን አለበት፡፡
 • ስራውን ያቋረጠ ሰራተኛ ወይም በድርጅቱ ፈቃድ መሰረት የለቀቀ ሰራተኛ ወይም በጦረታ የተገለለ ሰራተኛ እስካቆረጠበት ወይም እስከለቀቀበት ቀን ድረስ የተከማቸውን እና ያልተጠቀመበትን አመታዊ እረፍት በሰራታው ወቅታዊ ደሞዝ በሚከተለው መሰረት የሚሰላ ይሆናል፡፡

የእረፍት ክፍያን በተመለከተ = ዓመታዊ የእረፍት ቀናት * ወርሃወሊ ደሞዝ 22

 • የተከማቸ አመታዊ እረፍት የመጭውን ጊዜ ከባድ የስራ ጫናን በማሰብ ሊሰጥ አይችልም፡፡
 • አንድ ሰራተኛ በቅድሚያ ከ5 ሳምንታት በፊት በማስታወቂያ ካልተነገረው ወይም ይህ እንዲሁን ካልተስማማ በስተቀር ከመርሃ ግብሩ ጊዜ በላይ አመታዊ እረፍት እንዲወስድ አይገደድም
 • በእረፍት ያለ አንድ ሰራተኛ ሆስፒታል ከገባ ወይም በሆስፒታል የአልጋ እጥረት በመኖሩ ምክንያት ቤት ውስጥ እንዲታከም ከታዘዘ ለዚሁ የሆስፒታል ቆይታ  ወይም ለህክምናው የሚያስፈልገው ጊዜ እንደህመም የሚወሰድ ሲሆን ከአመታዊ እረፍቱ አይቀነስም፡፡
 • በህመም እረፍት ተመለከተው ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰራተኛ እና በውጭ ሀገር እዲታከም በኢትዮጵያ የህክምና ቦርድ ካልተረጋገጠለት ከውጭ ሀገር የተሰጠው የህመም እረፍት እንደሌላ እረፍት ለምሳሌ እንደ ህመም እረፍት ሳሆን ካለ ክፍያ እረፍት በሚል የሚዝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰራተኛ ሆስፒታል ውስጥ ከተኛ በዚሁ ስምምነት ደንብ አንቀጽ 10.4.8 መሰረት የህመም እረፍት ሊሰጠው ይችላል፡፡
 • አንድ ሰራተኛ አመታዊ እረፍቱን መጠቀም ከመጀመሩ በፊት የህመም እረፍት ከተሰጠው የህመም እረፍቱን ሙሉ በሙሉ ከመጠቀሙ በፊት አመታዊ እረፍቱን እንዲተቀምበት መጠየቅ የለበትም፡፡ ነገር ግር የህመም እረፍቱን እንዳጠናቀቀ ወዲያውኑ ዓመታዊ እረፍቱን መጠቀም ይችላል፡፡
 • አንድ ሰራተኛ በተቆጣጣሪው ውሳኔ መሰረት ድንገተኛ ክስተት ሲያጋጥመው ከተከመቻው አመታዊ እረፍት የሚቀነስ የተጠቀሰውን ድንገተኛ ክስተት ለማሟላት አስፈላጊ የሆኑ ቀናት የሚጥ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ ድንጋጌ ለበረራ አስተናጋጅ አባላት ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
 • ሴት ሰራተኛ በአመታዊ እረፍት ጊዜ ከወለደች ከወሊድ ቀን ጀምሮ የወሊድ እረፍት የማግኘት መብት ይኖራታል፡፡ የተቋረጠውን አመታዊ እረፍቷ ከተጠቀመችበት በኋላ ስራዋን የምትቀጥል ይሆናል፡፡
 • መጠቀም የጀመረውን አመታዊ እረፍት ከመገባደዱ በፊት ተመልሶ ወደ ስራ እንዲመጣ የሚጠራ ሰራተኛ አይኖርም
 • የማይታይ ማንኛውም ክስተት በሚገጥምበት ጊዜ ድርጅቱ ሰራተኛው በአመታዊ እረፍት ላይ ሳለ ተመልሶ እንዲመጣ ለመጥራት ሲገደድ ድርጅቱ ተመልሶ እንዲመጣ የመጥራ መብቱ  የተጠበቀ ሲሆን ሰራተኛውም ወደ ስራ መመለሱን ሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
 • በሰራተኛው ጥቅ ላይ ያልዋለውን አመታዊ እረፍት ድርጅቱ መስጠት በማይችልበት ጊዜ እና ወደ ስራ መመለሱ ሪፖርት ለማድረግ የሚወስደውን የጉዞ ቀናት ሳያካትት ድርጅቱ ወደ ጥሬ ገንዘብ በመቀየር ቀሪውን አመታዊ እረፍት ሊሰጠው ይችላል፡፡
 • ሰራተኛው ወደ ስራ ስለመመለሱ ሪፖርት  እንዲያደርግ ዳግም በመጠራቱ ምክንያት ያወጣውን ጉዞ ወጭ እና አበል ድርጅቱ ለሰራተኛው የሚከፍለው ይሆናል፡፡

10.4. የሕመም እረፍት

 • የሙከራ ቅጥር ጊዜውን ያጠናቀቀ ሰራተኛ ለማንኛውም ህመም ወይም ድንገት ከስራው ጋር ተዛማጅ ላልሆኑ በዚሁ ስምምነት መሰረት የህመም እረፍት የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
 • በህመም ምክንያት ከስራ መቅረት በድርጅቱ የተመደበ ዶ/ር ካለ ሰራተኛው ለድርጅቱ የህክምና አገልግሎት ወይም ከቁጥጥር ውጭ ካልሆነ በስተቀር በሚገኝ ማንኛውም ተግባቦት በኩል ለቅርብ አለቃው በ24 ሰዓታት ውስጥ ወይም ደግሞ የተመደበ ዶ/ር በማይኖርበት ወይም በቂ የሆነ የመገናኛ ዘዴ በሌለበት በ48 ሰዓታት ውስጥ ሪፖርት ማድግ አለበት፡፡
 • የታመመ እና የድርጅቱን የህክምና አገልግሎት ለመጎብኘት የሚጠይቅ ሰራተኛ በህክምነ አገልግሎት መምሪያ በተቀመጠው ደንብ መሰረት በማንኛውም የቀኑ /የእለቱ ሰዓት ይህንን ማድረግ አለበት፡፡ ዶ/ር እንዲመለከታቸው የሚፈልጉ ሰራተኞች ብዛት ዶ/ሩቹ ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ ትርፍ ከሆኑ ሰራተኞቹ ወደ ሆስፒታል ሚላላኩ ይሆናል፡፡
 • ሰራተኛው የድርጅቱን ዶ/ር እንዲያየው የሚወስደው ጊዜ እንደህመም እረፍት አይቆጠርም፡፡ ነገር ግን በድርጅቱ ዶ/ር ሪፈር በተባለው መሰረት ሌላን ዶ/ር ለመጎብኘት የጠፋ ጊዜ እንደተከፈለው የህመም እረፍት ሚቆጠር ይሆናል፡፡
 • የድርጅቱ ዶ/ር በማይገኝበት ወቅት በማንኛውም ሰዓት የታመመ ማንናውም ሰራተኛ ድርጅቱ የብድር ስምምነት ወደአለው ሆስፒታል ወይም ክሊኒክ ከዚሁ የድርጅቱ የህክምና አገልግሎት የብድር ደብዳቤ በመስጠት የሚላክ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ ድንገተኛ በሚሆንበት ወቅት ሰራተኛው የኩባንያውን መታወቂያ በማሳየት በድርጅቱ የተሰየሙን ክሊኒኮች ወይም ሆስፒታሎች መጎብኘት ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው ያወጣው የህክምና ወጭ ጉዳዩ ድንገተኛ እንዳነበረ ድርጅቱ ካረጋገጠ ገንዘቡን ተመላሽ አያደርግም፡፡
 • በድርጅቱ ከተሰየመ የህክምና ተቋም የህመም እረፍት የተሰጠው  ወይም ከሆስፒታል የወጣ ሰራተኛ የህመም እረፍት ምስክር ወረቀት ወይም የህክምና ሪፖርቱን በተቀበለ በ5 ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ የህክምና አገልግሎት ማቅረብ ያለበት ሲሆን ከዚሁ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ ምስክር ወረቀት ወይም ሪፖርት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 • የአካላዊ ምርመራ ሪፖርት ወይም ሰራተኛው ለስራው ብቁ መሆኑን የሚያረጋግጥ መግለጫ ሰራተኛው ለስራ ከመመለሱ አስቀድሞ ከድርጅቱ ደ/ር መቀበል አለበት፡፡ ሪፖርቱ በድርጅቱ ከተሴመው ሌላ ዶ/ር ተቀበለው ከሆነ በድርጅቱ ዶ/ር መረጋገጥ አለበት፡፡
 • በዶ/ር ሚሰጥ ህመም እረፍት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፡፡

      ሀ. የሚከፈልበት የህመም እረፍት በየወሩ በ2፡30 የሚከማች ሲሆን ከፍተኛው እስከ 60 የጊዜ መቁጠሪያ ቀናት ድረስ ሊከማች ይችላል፡፡
ለ. በሀ የተከማቸው የህመም እረፍት ጊዜ የተጠቀመ ሰራተኛ እና ሆስፒታል የሚተኛበትን ወረቀት ማግኘት ችግር በመሆኑ ምክንያት ቤት እንዲታከም የታዘዘ ወይም በሆስታል የሚገኝ ሆስፒጀታል በተኛበት ጊዜ እና በሚከተለው አኳኋን ከሙሉ ክፍያ ጋር የህመም እረፍት ሊሰጠው ይችላል፡፡

 • የሙከራ ቅጥር ጊዜን ካጠናቀቀ በኋላ እስከ 10 ዓመት 40 የጊዜ መቁጠሪያ ቀናት 10 ዓመት በላይ እና እስከ 20 ዓመት የአገልግሎት አመት 50 የጊዜ መቁጠሪያ ቀናት እንዲሁም
 • ከ20 ዓመት በላይ አገልግሎት እስከ 60 የጊዜ መቁጠሪያ ቀናት

ሐ. ከላይ በፊደል ሀ ወይም ለ የተመለከተው የህመም እረፍትን ያጠናቀቀ ሰራተኛ ግማሽ ደሞዝ እስከ 60 ቀናት የህመም እረፍት ሊሰተው ይችላል፡፡ (ሌላ የህብረት ስምምነቱ 100 ፐርሰንት ይሰጣል)፡፡ እንደዚሁም ስለከፍተኛ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ቀናት የህብረት ስምምነት 180 ይሰጣል፡፡  
መ. ከላይ በፊደል ሐ የተመለከተው የህመም እረፍቱን ያጠናቀቀ ሰራተኛ ካለ ክፍያ እስከ 60 ቀናት የህመም እረፍት ሊሰጠው ይችላል፡፡
ሠ. ከላይ በፊደል ለ፣ ሐ እና መ የተመለከተው የህመም እረፍቱን ያጠናቀቀ ማንኛውም ሰራተኛ ከላይ በፊደል ሐ እና መ የተጠቀሰውን እረፍት መውሰዱን ይቀጥላል፡፡

 • በጤና ምክንያት ወደ ሌላ ስራ እንዲዛወር በህክምና ዶክተር ሃሳብ የተሰጠውን ሰራተኛ ድርጅቱ ከሞላ ጎደል ማዘዋወር ካልቻለ ሰራተኛው ብቁ ወደሚሆንበት ክፍት ወደሆነው ዝቅተኛ ስራ ደረጃ የሚዛወር ይሆናል፡፡ ቆይቶ በሚመጣው ጉዳይ ደሞዙ ከዝቅተኛ የስራ ሃላፊነት ከፍተኛው መጠን እስካላለፈ ድረስ በተከታታይ ከ12 ወራት በኋላ ደሞዙ አይቀነስም፡፡
 •  ለሰራተኛው የተሰጠ የእረፍት ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት የስራ ቅጥር ውል ከተቋረጠ የጀመረው እረፍት ከዚሁ ጎን ለጎን የሚሰረዝ ይሆናል፡፡
 •  የደርሶ መልስ የአየር ጉዞ ትኬት በክልላዊ ጽ/ቤት እንዲሁም በአዲስ አበባ ሆስፒታል ሪቨር ለተባሉ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 •  የተወሰደው የህመም እረፍት ከተከማቸው ጠቅላላ ተቀናሽ ሆኖ ከዚህ ቀጥሎ ከላይ በአንቀጽ 10.4.8 /ሀ መሰረት መከማቸቱን ይቀጥላል፡፡

10.5. የወሊድ እረፍት
10.5.1. ቅድመ ወሊድ /የድህረ ወሊድ ፈቃድ

 1. የድርጅቱ ማንኛውም ነፍሰጡር ሴት የሚኖራት መብት

ሀ. በዶ/ር ትዕዛዝ መሰረት የእርግዝና ምርመራ እና ቸክ አፕ ተከፋይ ፈቃድ
ለ. ዶ/ሩ ከወሊድ በፊት እረፍት እንድታገኝ ምክር ከሰጣት ተከፋይ ፈቃድ

 1. የድርጅቱ ነፍሰጡር ሰራተኛ አካላዊ ምርመራ ያደረገችበትን ከወሰደችው ፈቃ/እረፍት በኋላ የህክምና ምስር ወረቀት ማቅረብ አለባት
 2. ነፍሰጡር ሰራተኛዋ ከምትጠብቀው የወሊድ ቀን በፊት የ30 የጊዜ መቁጠሪያ ቀናት የሚሰጣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በቅድመ ወሊድ ጊዜ በ30 ቀናት ውስጥ ካልወለድ ከላይ በቁጥር 1 መሰረት በህክምና ዶ/ሩ ሃሳብ ተጨማሪ እረፍት ማግኘት መብት ይኖራታል፡፡ ወሊዱ 30 ቀናት ከማለፉ በፊት ከሆነ የ60 ቀናት የድህረ ወሊድ እረፍቱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

10.5.2. ድህረ ወሊድ /የድህረ ወሊድ እረፍት

 1. የድርጅቱ ነፍሰጡር ሰራተኛ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን የሚከፈል የድህረ ወሊድ እረፍት 60 የጊዜ መቁጠሪያ ቀናት የማግኘት መብት ይኖራታል፡፡ ነገር ግን ተመልሳ ለመስራት ሪፖርት ከማድረግ የሚያግታት የተለየ እና አስጊ የጤና ሁኔታ ካለበት እና ይህም በማስረጃ ከተደገፈ በራሷ ጥያቄ ካለምንም ክፍያ ከ30 ቀናት ያልበለጠ ተጨማሪ እረፍት ሊሰጣት ይችላል፡፡
 2. ከሙሉ ክፍያ የሚሰጥ የወሊድ እረፍት ከ5ኛ የእርግዝና ወራት በኋላ ያልደረሰ ወሊድ በሚገጥምበት ጊዜ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 3. ከእርግዝና የሚመነጭ ህመም በድርጅቱ የህክምና ኢንሹራን መርሃ ግብር መሰረት የሚያዝ/የሚታይ ይሆናል፡፡

10.5.3. የአባት የወሊድ እረፍት
ባለቤቱ በሆስፒታል የተገላገለች ወንድ ሰራተኛ አስፈላጊ ማስተካከያዎችን ማከናወን እንዲችል 2 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ከክፍያ እረፍት ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ባለቤቱ በዚሁ የእረፍ ቀን ውስጥ መገላገሏን የሚያረጋግጥ ማስጃ ማቅረብ አለበት፡፡
10.6. የሐዘን ፈቃድ
10.6.1. የፈቃድ መሰረት/ምክንያት

 1. የሰራተኛው አብራክ አባት ወይም እናት፣ ባል /ሚስት፣ ልጅ፣ ጉዲፈቻ የተደረገ ልጅ ወንድም ወይም እህት በሚሞትበት ጊዜ ሞት ከገጠመበት ቀን ጀምሮ የ3 ቀናት እረፍት የሚሰጥ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱ በሚቀጥለው ቀን የሚከናወን ከሆነ የሚከፈል 4 ቀናት የሀዘን ፈቃድ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 2. የአያት፣ የሚስት/ባል አባት፣ እናት ወይም የእናት ባል ወይም የአባት ሚስት ወይም የማደጎ አሳዳጊ ቤተሰቦች፣ አጎት እና አክስት በሚሞቱበት ጊዜ 2 ቀናት ሀዘን እረፍት ሚሰጥ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱ በሚቀጥለው ቀን የሚከናወን ከሆነ ከነዚህ ቤተዘመድ ሞት ከገጠመበት ቀን ጀምሮ የሚከፈል 3 ቀናት የሀዘን እረፍ/ፈቃድ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በዚህ ደንብ መሰረት የተሰጠ የሀዘን እረፍት በዓመት ከ7 ቀናት በላይ መሆን የለበትም፡፡
 3. የአንድ ሰራተኛ የአጎትል፣ የአክስት ልጅ፣ የአባት ሚስት ወንድም /እህት/ልጅ የእናት ባል ወንድም/እህት/ልጅ ሞት በሚገጥምበት ጊዜ ከአመታዊ እረፍቱ የሚቀነስ የ2 ቀናት እረፍት ለሰራተኛው የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በክፍሉ የሚፈፀም ወይም የሚከናወን የትርፍ ሰዓት የሚኖር ከሆነ ካለምን የትርፍ ሰዓት ክፍያ የስራ ጊዜ ማካካሸ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
 4. ተፈፃሚ ከሆነው የሀዘን እረፍት የበለጠ ሞት ከተከሰተበት ቦታ ወይም ወደ ቦታው ለመጓጓዝ ለትራንስፖር በማሰብ ለሰራተኛ ከተከማቸው እረፍት ከ2 ቀናት ያላነሰ በቅርብ አለቃው የሚሰጠው ሲሆን ሁኔታው እንደዚህ አይነት የእረፍት ማካካሻ ቀናት ከላይ በንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ሊያሰተው ይችላል፡፡
 5. ሌላ ማንኛውም ዘመድ ወይም ጓደኛ በሚሞትበት ጊዜ በቀብር ስነ ስርዓት እንዲገኝ  ከተከማቸው ዓመታዊ እረፍት የሚቀነስ እስከ 8 ሰዓታት እረፍት ወይም ከላይ በንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት የማካካሻ እረፍት በቅርብ አለቃው የሚሰጠው ይሆናል፡፡

10.6.2. የቀብር ፈቃድ እና ወጭ

 1. የአንድ ሰራተኛ ሞት በሚገጥምበት ጊዜ የስራ ጫናው የሚፈቅድ እስከሆነ ድረስ በቀብር እንዲገኙ የስራ ባልደረቦቹ በተመሳሳይ ወጭ በተጓዳኝ አለቆቻቸው /ሃላፊዎቻቸው ተከፋይ እስከ 4 ሰዓት የሀዘን እረፍት ይሰጣቸዋል፡፡
 2. የሰራተኛው ሚስት ወይም የአብራክ ልጅ ወይም የጉዲፈቻ ልጅ በሚሞትበት ጊዜ ድርጅቱ አስከሬኑን ለማጓጓዝ መኪና የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ በተለያዩ ምክንያቶች ማቅረብ ካልቻለ እንደአግባብነቱ (በአዲስ አበባ ከሆነ) እስከ ብር 1000 (ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ) እስከ ብር 2000 ለሰራተኛው ወይም ለሞተው ሰራተኛ ቤተሰቦች በጥሬ ገንዘብ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰራተኛው ወይም ሚስቱ /ባልየው ከሞቱ እንደአግባብነቱ ድርጅቱ የቀብር ስነ ስርአት ማስፈፀሚያ የአበባ ጉንጉን ወይም ይህንኑ ለመግዛት ገንዘብ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 3. ሟች ሰራተኛ በመኖሪያ አድራሻው አካባቢ ቤተሰብ ከሌለው እና የቀብር ስነ ስርዓቱ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት ቦታ የሚከናወን ከሆነ ድርጅቱ የሟች ሰራተኛ አስከሬን ለማጓጓዝ የምድር ላይ ትራንስፖርት ወጭውን በቀጥታ መሸፈን ወይም ብር 2000 የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 4. የአንድ ሰራተኛ ባል/ሚስት፣ የአብራክ አባት/አባት/እናት፣ የአብራክ ልጅ ወይም የጉዲፈቻ ልጅ ሞት በሚከሰትበት ወቅት ድርጅቱ በተቻለው መጠን የስራ ባልደረቦቹ በቀብር ስነ ስርዓቱ እንዲገኙ ሁኔታዎችን የሚያመቻች ይሆናል፡፡
 5. ከላይ ለተገለፁት ቤተሰቦች የቀብር ስነ ስርዓት ከአዲስ አበባ መውጣት ያለበት ማንኛውም ሰራተኛ የደርሶ መልስ የአየር ትኬት ማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
በሰራተኛው መኖሪያ ቤት የሚኖር ማንኛውም ግለሰብ በሚሞትበት ጊዜ ከላይ በአንቀጽ 10.6.1 /3 መሰረት ከተከማቸው አመታዊ እረፍቱ የማካካሻ የስራ ቀናት እስከ 3 ቀናት ድረስ በሃላፊው ሊሰተው ይችላል፡፡

10.7. ካለ ክፍያ የመቅረት ፈቃድ
10.7.1. ለተለያዩ አላማዎች የሚሰጥ እረፍት

 1. በአዋጅ ቁጥር 377/2003 አንቀጽ 83/1እና 2 መሰረት ከተጠቀሱት ጉዳዮች ማንኛውም በሚጋረጥበት ጊዜ በተጠቀሰው የአሰሪ እና ሰራተኛ ህግ እና ደንብ በተቀመተው ስርዓት መሰረት የሚከፈለው እረፍት የሚሰጠው ይሆናል፡፡
 2. አንድ ሰራተኛ በሌላ ማንኛውም ምክንያት በማንኛውም መንግስታዊ ባለስልጣን ወይም ፖሊስ መጥሪያ ከደረሰው ወይም ከታሰረ እና በዚህ ምክንያት ከስራ ከቀረ ከተከማቸው አመታዊ እረፍት ተቀናሽ የሚሆን ተከፋይ እረፍት የሚሰጠው ይሆናል፡፡ የተከማቸ እረፍት የሌለው ከሆነ ለዚሁ አላማ የተጠቀመውን እረፍት መሰረት በማድረግ እንዲሰራ ከፍተኛው እስከ 7 ቀናት የማካካሻ ጊዜ የሚሰጠው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው በዚሁ ጉዳይ ምክንያት ታስሮ ከነበረ ወይም በዚሁ ተጠርጥሮ መጥሪያ ደርሶት ከነበረ ድርጅቱ ሰራተኛው ወደ ስራ  ቦታው እንዲመለስ እስከ 6 ወር ድረስ የሚጠብቅ ይሆናል፡፡
 3. በድርጅቱ ትምህርታዊ ድጋፍ ፖሊሲ መሰረት ትምህርት ሚከታተሉ ሰራተኞች በስራ ሰዓታት ውስጥ ለሚወስዱት ፈተና ተከፋይ እረፍት የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡
 4. በአንቀጽ 10.7.1.3 መሰረት የትምህርት እረፍት የተሰጠው ሰራተኛ አስፈላጊ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡

10.7.2. የሰርግ ፈቃድ
ሀ. ሰርግ የሚደግስ ሰራተኛ ለሰርጉ ተከፋይ 4 ተከታታይ ቀናት ፈቃድ የሚሰተው ይሆናል፡፡
ለ. ማንኛውም ሰራተኛ ሰርግ የሚካሄድበትን የአቀደው ቀን አስቀድሞ ለድርጅቱ ማሳወቅ እና ሰርጉ ለእርሱ በተሰጠው የእረፍት ቀናት ውስጥ መካወኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
10.7.3. የህብረቱ ስራ ፈቃድ
በሰራተኛ እና አሰሪ ህግ መሰረት እውቅና ከተሰጠው የንግድ ህብረት ተጠሪዎች/ተወካዮች እረፍት በተጨማሪ የህብረቱን ስራ ለማስፈፀም ለህበረቱ መሪዎች የሚከተሉትን እረፍቶች የሚሰጡ ይሆናል፡፡
ሀ. አመታዊ ጉባኤውን /ስብሰባውን ለመሳተፍ እና /ወይም የህብረቱ ሹሞች ለመምረጥ ለሁሉም የህብረቱ አባላት በየአመቱ የ4 ሰዓት ፈቃድ የሚጣቸው ይሆናል፡፡ እረፍቱ /ፈቃዱ በድርጅት እና በህብረቱ መካከል ስምምነት በተደረሰበት ቀን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ለ. ህብረቱ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲካሄድ በሚፈልግበት ጊዜ የድርጅቱ ቅድመ ፈቃድ ካገኘ በኋላ ማከናወን ይችላል፡፡
ሐ. ለንግድ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በየሳምንቱ የ4 ሰዓት ፈቃድ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
መ. የህብረቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የድርጅቱ ቅድመ ፈቃድ ካገኙ በኋላ አስቸኳይ ስብሰባ/ጉባኤ ማካሄድ ይችላሉ፡፡
ሠ. ህብረቱ የህብረቱ የምክር ቤት አባላት እና የመደብር ሰራተኞች/አስተናጋጆች በየ3 ወሩ አንድ ጊዜ ስብሰባ መጥራት ይችላል፡፡ ድርጅቱ ለዚሁ አላማ ሲባል የ3 ሰዓታት ፈቃድ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ሰ. ለህብረቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አንድ አባል የህብረቱን የጽ/ቤት ተግባራት እንዲያከናውን በየቀኑ የግማሽ ቀን እረፍት የሚሰጠው ይሆናል፡፡
10.8. ካለ ክፍያ የመቅረት ፈቃድ
10.8.1. አጠቃላይ
ሀ. አንድ ሰራተኛ በድርጅቱ ውስጥ 6 ተከታታይ ወራት ካገለገለ በኋላ ብቻ ካለ ክፍያ ፈቃድ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ የአገልግሎት ጊዜው ከ6 ወራት በታች ከሆነ በአዋጁ መሰረት ሚታይ ይሆናል፡፡
ለ. አንድ ሰራተኛ የተከማቸው አመታዊ እረፍት ከመጠቀሙ በፊት ካለ ክፍያ እረፍት አይሰጠውም
10.8.2. ፈቃድ የመስጠት ደንብ/ሁኔታ
ሀ. በድርጅቱ ውሳኔ መሰረት በተለየ ወይም ከባድ በሆነ ሁኔታ ካለ ክፍያ እረፍት/ፈቃድ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንደዚህ አይነት እረፍት በአንድ አመት ውስጥ ከ60 ተከታታይ ቀናት መብለጥ የለበትም፡፡ በማንኛውም ካለ ክፍያ ፈቃድ ጊዜ ውስጥ የሰራተኛው ስም በፔሮል መመዝገቡን የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የሰራተኛው ቀደምትነት /ስሜሪቲ የሚተላለፍ ጥቅማ ጥቅም እና ሌላ የተከማቸ የአገልግሎት ጥቅም የሚዝ ይሆናል፡፡
ለ. ካለ ክፍያ እስከ 4 ቀናት ፈቃድ የተሰጠው ሰራተኛ በክፍሉ ውስጥ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ካለው እንደዚህ አይነት እረፍት በሁለት ወራት ውስጥ እንዲያካክስ ይፈቀድለታል፡፡

   ሐ. በማንኛውም ጉዳይ ካለ ክፍያ እረፍት ሲሰጥ የስምምነቱን አይነት እንዲፈጽም ለሰራተኛው ደብዳቤ የሚፃፍለት ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ አንድ
የህክምና ወጭ እና ኢንሹራንስ መርሀ ግብር

  1.  የህክምና ወጭ

ድርጅቱ በዚህ ስምምነት እዝል አራት በተዘረዘረው መሰረት ለህክምና ጥቅማ ጥቅም 10 ፐርሰን የህክምና ወጭ የሚሸፍን ወይም በራስ የሚሰጥ መርሃ ግብር የሚኖረው ይሆናል፡፡

  1. የህክምና፣ መድሀኒት እና የሆስፒታል ወጭ
   1. ህክምና እና ሆስፒታል

ሀ. ወደ ክሊኒክ ወይም ሆስታል ገብቶ ህክምና እንዲደረግለት የሚፈልግ ሰራተኛ ድርጅቱ የብድር ውል ካለው እውቅና ከተሰጠው ማንኛውም ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል እንዲታከም ወይም እንዲገባ የሚጠይቅ ደብዳቤ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
ለ. ድርጅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተመደቡ ሰራተኞች ከሆስፒታሎች ጋር የብድር አገልግሎት እንዲያገኝ የሚዋዋል ይሆናል፡፡ ይህ ማስተካከያ ወይም ስምምነት በማይከናወንበት ጊዜ ድርጅቱ ለዚሁ አላማ ሲባል ወጭን/ፍጆታን የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡ አገልግሎቶች በማይኖሩበት ጊዜ ሰራተኞቹ በአካባቢው ባለ ቅርብ ሆስፒታል ሚታከሙ ይሆናል፡፡

   1. ማንኛውም ሰራተኛ ከስራ ጣቢያው ውጭ ሲታመም እና በአካባቢው በሚገኝ ማንኛውም የቅርብ ሆስፒታል ህክምና ካገኘ በኋላ የህክምና ወረቀት ማቅረብ ያለበት ሲሆን ምስክር ወረቁ በህክምና ክፍሉ ተቀባይነት ካገኘ ይህ ፖሊሲ የሚፈቅደውን ከፍተኛ የኢንሹራንስ ሽፋን በመጠቀም ወጭው የሚመለስለት ይሆናል፡፡
   2. የሰራተኛው የሆስፒታል ቆይታ ክፍያው በዚህ ውስጥ በእዝል 4 ስር ከተመለከተው የህክምና አበል ወሰን በላይ ከሆነ ድርጅቱ ማንኛውም የበለጠ መጠን ለትርፍ ብሩ እስከ ብር 5 ሺህ ወይም የሰራተኛው እስከ 3 ወር ደሞዝ የሚከፍል ሲሆን ይህንኑ ከሰራተኛው ደሞዝ የተወሰነውን መጠን በየወሩ እየቀነሰ የሚሸፍነው ይሆናል፡፡
   3. ድርጅቱ አንድ ሰራተኛ ሪፈር በተባለበት ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል እና በታከመበት ወይም በድርጅቱ የህክምና አገልግሎት ዩኒት የማይገኘውን የታዘዘውን መድሃኒት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ከፋርማሲ ቤቶች የብድር አገልግሎት እንዲሰጥ የሚዋዋል ወይም የሚያመቻች ይሆናል፡፡
   4. በኩባያው ስራ በውጭ ሀገር ያለ ሰራተኛ በቦታው ለውጥ ምክንያት ከታመመ ወይም በነበረው ከባድ ህመም ምክንያት የተባባሰበት ከሆነ እና የህክምና ዶክተሩ ህመሙ አፋጣኝ ትኩረት እንደሚያሻው ጋረጋገጠ የህክምና ወጭ ክፍያ በሚከተለው ተገዥ ይሆናል፡፡

ሀ. ድርጅቱ በቦታ ለውጥ ምክንያት የሰራተኛውን ህመም አስመልክቶ የህክምና ወጭውን የሚከፍል ሲሆን በህክምና ኢንሹንስ/መድህን መርሃ ግብር መሰረት ከኢንሹንስ ኩባንያው ወይም ከራስ አገዝ ኢንሹራንስ ብሩ እንዲመለስለት ጥያቄ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
ለ. የአንድ ሰራተኛ ከባድ ህመም ስር የሰደደ ህመም እየሆነ በመምጣቱ አፋጣኝ ፣ህክምና የሚያስፈልገው ከሆነ ድርጅቱ ወጭውን በመሸፈን በኢትዮጵያ ታክሞ ቢሆን ኖሮ የተከፈለውን የገንዘብ መጠን ወይም ወጭ ከኢንሹራንስ ኩባያው ወይም ከራስ አገዝ ኢንሹራንስ መርሀ ግብር እና ከሰራተኛው እስከ ኢንሹራንስ/መድህን እቅድ ወሰን ድረስ የሚጠይቅ ይሆናል፡፡ ድርጅቱ ልዩነቱን የሚሸፍን ይሆናል፡፡
ሐ. ሰራተኛው ከላይ በአንቀጽ - ፊደል ሀ እና ለ በተቀመጠው ሁኔታ መሰረት የታከመ ከሆነ እና በዚሁ ተመሳሳይ የኢንሹራንስ አመት በሚኖርበት ቦታ ህመም ላይ ከወደቀ የመድህን መርሃ ግብር ፈንድ ሂሳቡ ወቅታዊ የህክምና ወጭውን መሸፈን የማይችል ከሆነ ድርጅቱ ከኢንሹራንስ ኩባንያ እስከጠየቀው የህክምና ወጭ መጠን ድረስ የሚከፍል ይሆናል፡፡

ድርጅቱ የህክምና ወጫቸውን እስከ ብር 12 ሺህ ለመሸፈን ለሰራተኛው ሚስት/ባል የህክምና ወጭ አረቦን 50 ከመቶ የሚዋጣ ይሆናል፡፡
  1. የኢንዳስትሪ ጉዳት እና የስራ ላይ በሽታ
   1. የኢንዳስትሪ ጉዳት እና የስራ ላይ በሽታ ትርጓሜ በአዋጁ ስር እንደተጠቀሰው ይሆናል፡፡
   2. ድርጅቱ በኢንዳስትሪ ጉዳት እና በስራ ላይ በሽታ ምክንያት ተከፋይ የሚሆን የህክምና ወጭ በሙሉ ይሸፍናል፡፡
   3. ጉዳቱ ወይም ህመሙ ይሄ የኢንዳስትሪ ጉዳት ወይም የስራ ላይ ህመም ነው የሚል ግጭት በሚነሳበት ወቅት በሰራተኛው እና በድርጅቱ በሁለቱም ወገኖች ስምምነት መሰረት በ3 የዶክተሮች ፓነል ጉዳዩ በጋራ ተመርምሮ ውሳኔአቸው የመጨረሻ ይሆናል፡፡
   4. ታማሚውን በጎበኘው ዶ/ር ባረጋገጠው ሪከመንዴሽን/ሃሳብ መሰረት ድርጅቱ የኢንዳስትሪ ጉዳት እና የስራ ላይ ህመም የህክምና ወጭ፣ የመድሃኒት፣ የሆስፒታል እንደዚሁም ሌሎች ተዛማጅ ወጭዎችን በሙሉ የሚከፍል ይሆናል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰራተኛ በድርጅቱ በህክምና ቦርድ አባላት ሪከመንዴሽ/ሃሳብ እና በጉዳዩ ተፈፃሚ በሆነው የመንግስት ህግ እና መመሪያ መሰረት በህክምና ተቋማት ተጨማሪ ህክምና እንዲያገኝ ወደ ውጭ የሚላክ ይሆናል፡፡ ድርጅቱ ሰራተኛው የሚላክበትን የህክምና ተቋም የሚመርጥ ይሆናል፡፡ በሰራተኛው ላይ ውዝግብን ለማስቀረት እና ተገቢውን ህክምና አድርጎ ደህንነቱን ጠብቆ መመለሱን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ በተቻለ መጠን ከጀተመረጠው የህክምና ተቋም በቅድሚያ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እና ዝግጅቶች የሚደረጉ ይሆናል፡፡
   5. አንድ ሰራተኛ የኢንደስትሪ ጉዳት ወይም የስራ ላይ ህመም በሚገጥመው ጊዜ የሚከተሉት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

ሀ. ሰራተኛው በኢንደስትሪ ጉዳት ወይም በስራ ላይ ህመም ምክንያት ስራውን ማቆም ከፈለገበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን ከስራ ከቀን ከቀረበት ቀን ለመጀመሪያዎቹ 12 ወራት ሙሉ በሙሉ ክፍያ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
ለ. ሰራተኛው በተጠቀሱት 12 ወራት ጊዜ መጨረሻ ላይ አሁንም ወደ ስራው መመለስ የማይችል ከሆነ ከደሞዙ 75 ከመቶ የሚከፈልበት ተጨመሪ 9 ወራት እረፍት ይሰጠዋል፡፡ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን በድርጅቱ ላጠናቀቀው ሙሉ የአገልግሎት አመት በእያንዳንዱ ሙሉ ዓመት ከወርሃዊ ደሞዙ ከፍተኛው መጠን እስከ  5 ከመቶ የሚጨምር ይሆናል፡፡
ሐ. ሰራተኛው ከላይ በአንቀጽ ሀ ወይም ለ ከተጠቀሱ ጊዚያት በኋላ ወደ ስራው መመለስ የመይችል ከሆነ ወይም ይህ በእንዲህ እንዳለ ለስራው ብቁ አለመሆኑ በህክምናው ከተገለፀ በዚሁ ስምምነት የኢንሹራንስ መርሀ ግብር እዝል 4 መሰረት የጥቅማ ጥቅም መብት ይኖረዋል፡፡
መ. ከላይ የተገለፀው ወቅታዊ ክፍያ በሰራተኛው ጥያቄ ወይም እንደዚህ አይነት ክፍያ በሚከተለው አኳኋን ካገኘ ሊቋረጥ ይችላል

 1. ለህክምና ወይም ለምርመራ ሪፖርት ማድረግ እምቢተኛ ከሆነ ወይም በቸልተኝነት ከተንቀሳቀሰ ወይም ህክምናውን ካለምንም ከባድ ምክንያት ለማደናቀፍ የሚሞክር ከሆነ
 2. የሚያገግምበትን በሚያዘገይ መልኩ የሚንቀሳቀስ ከሆነ
 3. በኢንደስትሪ ጉዳት የደረሰባቸው ሰራተኞችን አስመልክቶ አግባብነት በላቸው ሹሞች የተሰጠውን መመሪያ ከጣሰ
   1. ስለ አካል ጉድለት/ጉዳት የመቶኛ ግምት ግጭት በሚመለከተው የህክምና ቦርድ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት የሚፈታ ይሆናል፡፡
   2. እንደጉዳዩ ሁኔታ አንድ ሰራተኛ ወይም ህጋዊ ወራሽ ህጋዊ ወራሹ የአካል ጉዳት ወይም በሚሞትበት ጊዜ በድርጅቱ  የቡድን ድንገተኛ አደጋ የመድህን /ኢንሹራንስ ፖሊሲ ስር የተቀመጡትን ጥቅማጥቅሞች የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
   3. የኢንደስትሪ ጉዳት ወይም ሙያዊ ህመም የደረሰበት ሰራተኛ በድርጅቱ ዶ/ር ወደ ስራው ለመመለስ ብቁ መሆኑን የሚመሰክር የተረጋገጠ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
   4. በስራ ላይ ሳለ ጉዳት የደረሰበት ወይም የስራ ላይ ሙያዊ ህመም የገጠመው ሰራተኛ በአንቀጽ 10.4.2 በተገለፀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ይህንኑ ጉዳት ወይም ህመም ማቅረብ አለበት፡፡
   5. በዚሁ የኢንደስትሪ ላይ ጉዳት ምክንያት ወደተመደበበት የስራ ቦታ ተመልሶ መስራት የማይችል ማንኛውም ሰራተኛ እርሱ ብቁ ወደሚሆንበት ማንኛውም ስራ የሚመደብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንደዚህ አይነት ሰራተኛ ዝግተኛ የስራ ደረጃ /መደብ ባለው የስራ ሃላፊነት የተመደበ እንደሆነ የዚሁ ስምምነት አንቀጽ 10.4.9 ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  1. የስራ ላይ ያልሆነአ ደጋ እና ጉዳት
   1.  ድርጅቱ በዚሁ ስምምነት እዝል 4 በተመለከተው መሰረት ከስራ ውጭ ሳሉ የስራ ላይ ያልሆነን አደጋ ወይም ጉዳት በተመለከተ የጥቅማ ጥቅም ሙሉ አረቦን የሚከፍል ሲሆን የስራው አስተዳደራዊ ሂደት በመያዝ ለሰራተኛው ሙሉ ጥቅማ ጥቅም ይሰጣል፡፡
አ ንደዚሁም ከላይ በአንቀጽ 11.3.7፣ 11.3.9 እና 11.3.10 ስር የተመለከቱ ደንቦች ከስራ ውጭ ባሉበት ወቅት ለደረሰ የስራ ላይ ያልሆነን አደጋ እና ጉዳት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
   1. የቡድን የድንገተኛ ኢንሹራንስ እቅድ
 1. በዚሁ እዝል 4 ውስጥ የተመለከተው የቡድን የድንገተኛ ኢንሹራንስ እቅድ እና በድርጅቱ የተያዘው ከስራ ውጭ ሳሉ የሚከሰት የኢንደስትሪ ጉዳት ወይም የስራ ላይ ህመም ወይም የስራ ላይ ያልሆነ አደጋ ወይም ጉዳት በተመለከተ ለሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም እንደሚሸፍን እቅድ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
 2. ሀ. ድርጅቱ የአንድ ሴት ሰራተኛ ከእርግዝና ጊዜዋ ጀምሮ እስከ ወሊድ ድረስ ያሉትን የተወሳሰቡ የህክምና እና ምርመራ ወጭ ወይም ተዛማጅ ወጭዎችን የሚሸፍን ይሆናል፡፡ ነገር ግን አዲስ ከተወለደው ህፃን ተዛማጅ የሆኑ ወጭዎችን አያካትትም፡፡

.1. ወጭ የመጋራት መርሀ ግብር/ፖሊሲ
ድርጅቱ እና ተመላላሽ ታካሚ ሰራተኛው አንድ ሰራተኛ በህክምና አገልግሎጀት ዩኒት ውስጥ ዶ/ር ለመጎብኘት እና የላቦራቶሪ ክፍያን ለመክፈል የተመላላሽ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት በሚወጣበት ጊዜ 85 ከመቶ እና 15 ከመቶ በቅደም ተከተል የሚሸፍን ይሆናል፡፡
2. የአይን መነፀር ፍሬም ወጭ እና ወሰኑ
ሀ. ሰራተኛው እስከ ብር 1000 የሚዊጣ የአይን መነፀር አቃፊ 10 ከመቶ የሚሸፍን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው ከብር 1000 ብር በላይ የሚያጠከጣ የአይን መነፀር ፍሬም ሙሉ ወጭውን የሚሸፍን ይሆናል፡፡
ለ. ድርጅቱ የሌንስ እና ሌላ አይን ህክምና ወጭ .ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
3. የጥርስ መተካት እና የህክምና ወጭ
ሀ. ድርጅቱ ጥርስን እስከ ማስነቀል የጥር ህክምና ወጭ ሚሸፍን ይሆናል ነገር ግን የጥርስ መተኪያ እና ተዛማጅ ወጭዎች 92 ከመቶ በድርጅቱ እና ቀሪው 8 ከመቶ በሰራተኛው የሚሸፍን ይሆናል፡፡
ለ. የአንድ ሰራተኛ የጥርስ መተኪያ ጠቅላላ ወጭ ከብር 10 ሺህ መብለጥ የለበትም፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት
ደሞዝ፣ የደሞዝ ጭማሪ እና ሰራተኛ ማበረታቻ

  1. ትርጓሜ
 1. በህጉ መሰረት ለዚሁ በተሰጠው ትርጓሜ ተገዥ የሚሆን “ደሞዝ” በስራ ቅጥር ውል በየወሩ ለሚከናውነው ስራ ለአንድ ሰራተኛ ተፈፃሚ የሚሆን መደበኛ ክፍያ ማለት ሲሆን ይህም በህጉ የተገለፀውን ሌላ ክፍያ ተጨማሪ ክፍያ ፣ አበል እና የወሎ አበልን አያካትትም፡፡
 2. የወሩ ደሞዝ እስከሚቀጥለው ወር 15ኛው ቀን ለተከናወነው ስራ በወሩ በ16ኛው ቀን ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  1. የክፍያ ሁኔታ እና አፈፃፀም
 3. ከበረራ አስተናጋጆች እና ከምግበ አብሳይ ሰራተኞች በስተቀር ሁሉም ሰራተኞች ደሞዛቸው በወሩ መጨረሻ ቀን በሰራተኞቹ ሂሳብ በቀጥታ በማስቀመጥ ወይም በቼክ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
 4. ቀኑ በሳምንታዊ የእረፍት ቀን ወይም በአል ላይ የሚውል ከሆነ በመጨረሻው ቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በመስከረም ወር ሰራተኖቹ በመስቀል ዋዜማ ቀን ላይ የሚከፈላቸው ይሆናል፡፡
 5. የበረራ አስተናጋጆች እና ምግብ አብሳይ ሰመራተኞች በዚሁ ስምምነት ተፈፃሚነት ባለው ደንብ መሰረት ይከፈላል፡፡
 6. የአንድን ሰራተኛ ለመክፈል ተመላሽ ገንዘብ እጥረት በሚኖርበት ጊዜ በሰራተኛው ገንዘቡ እንዲመለስ ከተጠየቀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው 6 ወራት ካለፉ በኋላ ማንኛውንም ተመላሽ ገንዘብ መጠየቅ አይችልም፡፡
  1. የፔሮል ተቀናሽ
 7. በዚሁ ህግ እና ደንብ፣ በድርጅቱ ፖሊሲ እና በዚሁ ስምምነት በተወሰነው ህግ እና መመሪያ ካልሆነ እና ይህ እንዲሆን የሰራተኛው የጽሁፍ ጥያቄ ወይም ስምምነት ካልሆነ በስተቀር የማንኛውም ሰራተኛ ደሞዝ መቀነስ አይችልም፡፡
 8. የስልጠና ወይም ሌላ ማንኛውም መሰብሰብ ያለበት እዳ ከሰራተኛው መከፈል የነበረበት እዳ ከመከፈሉ በፊት የአንድ ሰራተኛ የስራ ቅጥር ውል በሚቋረጥበት ጊዜ  ድርጅቱ ከሰራተኛው ደሞዝ ወይም ሌላ ለሰራተኛው ተከፋይ ከሚሆን ማንኛውም ክፍያ መቀነስ ወይም ከዚሁ መሰል ክፍያ ማስቀረት የሚችል ይሆናል፡፡
ሰራተኛው በጽሁፍ እና በተፈረመ የጥያቄ ቅጽ ድርጅቱ የህብረቱ መዋጮ ከደሞዙ እንዲቀንስ ከጠየቀ ብቻ ድርጅቱ ከሰራተኛው ደሞዝ አስፈላጊውን መተን እየቀነሰ ይህንኑ ወደ ህብረቱ ሂሳብ የሚያዘዋውር ይሆናል፡፡ በህብረቱ ወይም በሚመለከተው ሰራተኛ ሲጠየቅ ድርጅቱ ከሰራተኛው ወርሃዊ ደሞዝ የሚቀንሰውን የመዋጮ መጠን በማቆም የሰራተኛውን ሙሉ ደሞዝ የሚከፍል ይሆናል፡፡
  • ዓመታዊ የደሞዝ ጭማሪ
 • ድርጅቱ የሰራተኞች ምርታማነትን እንዲሁም የምርት ብዛት እና ጥራት ብሎም አመታዊ የትርፍ እድገት ግምት ውስጥ በማስገባት ለ3 ዓመታት ፅኑ የሚሆን ለሁሉም ሰራተኞች ዓመታዊ የደሞዝ ጭማሪ ያደርጋል፡፡ የደሞዝ ጭማሪው ይህ ስምምነት ከተፈረመበት የበጀት አመት ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
 • ድርጅቱ በዚሁ ስምምነት መሰረት በበጀት አመቱ መጨረሻ ከተጣራው ትርፍ ተፈፃሚ የሚሆን ግብር፣ ለመንግስት የሚከፈል እና ህጋዊ መጠባበቂያ ገንዘብ ከቀነሰ በኋላ የብር 140,000,000 (አንድ መቶ አርባ ሚሊየን ብር) ትርፍ ሲያሳካ አመታዊ የደሞዝ ጭማሪ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
 • ድርጅቱ በበጀት አመቱ በስኬት ማከናወኑን እና ከላይ የተጠቀሰው የተጣራ ትርፍ 140,000,000 (አንድ መቶ አርባ ሚሊየን ብር) መገኘቱ በሚረጋገጥበት ጊዜ ጠቅላላ የደሞዝ ጭማሪ በሚከተለው አኳኋን ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
 • እስከ ብር 2,000 ደሞዝ የሚያገኙ ሰራተኞች 8 ከመቶ ጭማሪ
 • ወርሃዊ ደሞዛቸው ከብር 2,000 በላይ እና እስከ ብር 4,000 ለሚያገኙ ሰራተኞች 7 ከመቶ ጭማሪ እና
 • ከብር 4,000 በላይ ለሚያገኙ ሰራተኞች 6 ከመቶ ጭማሪ ይሆናል፡፡
 • በደሞዝ ጭማሪ ላይ ህብረቱ ማንኛውም ጉዳይ ወይም ጥያቄ ካለው የደሞዝ ጭማሪ ተፈፃሚ ከሆነ በኋላ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በድርጅቱ የኮርፖሬት የሰው ሃብት ስራ አመራር ክፍል ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
 • የኑሮ እስታንዳርድ ወጭን ግምት ውስጥ በማስገባት እና አስፈላጊ ጥናት መሰረት ድርጅቱ ለሰራተኞቹ የሚከፍለውን የደሞዝ ክፍያ መጠን ሊያሻሽል/ሊገመግም ይችላል፡፡
 • በዚህ ወቅት ተፈፃሚ እየሆኑ ካሉት ሌሎች ድርጅቱ ተጨማሪ የደሞዝ ደረጃ ማውጣት ወይም በስራው ይዘት መሰረት በከፍተኛ ወይም በዝቅተኛ የስራ መደብ ከመመደብ ወይም አዲስ የስራ ሃላፊነት ከመክፈት ወይም ከማውጣት ወይም የስራ መጠሪያ ከመቀየር ድርጅቱን የሚያግድ በዚህ ስምምነት ውስጥ ምንም አይነት ነገር የለም፡፡
 • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 3 የተጠቀሰ የደሞዝ ጭማሪ ሰራተኛው ከፍተኛውን ጣራ እስኪደርስ ድረስ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
 • በዚሁ ስምምነት መሰረት ሰራተኛው በቋሚነት በተያዘው በጀት አመት ውስጥ ኩባያውን ለ6 ወራት ያህል ያገለገለ ከሆነ እና ስሙ በፔሮል ዝርዝሩ ካለ እና ጭማሪ ተፈፃሚ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በማንኛውም ምክንያት የስራ ቅጥሩ ውሉ ያልተቋረጠ ሰራተኛ አመታዊ የደሞዝ ጭማሪ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
 • ከላይ በንዑስ አንቀጽ 7 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የአንድ  ሰራተኛ ወቅታዊ ደሞዙ እርሱ በያዘው የስራ ሃላፊነት ተቀመጠውን ከፍተኛ የደሞዝ ጣራ የሚያልፍ ከሆነ እንደ አንድ ጊዜ ጉርሻ የአንድ ወር ደሞዙ የሚከፈለው ሲሆን አመታዊ የደሞዝ ጭማሪ የማግኘት መብት አይኖረውም፡፡
 • በዚሁ ስምምነት መሰረት በሚፈፀመው አመታዊ የደሞዝ ጭማሪ ምክንያት በያዙት ወቅታዊ የስራ ሃላፊነታቸው ከፍተኛውን ጣራ ሊያልፍ የሚችል የሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ከፍተኛውን ጣራ ያለፈው የገንዘብ መጠን ብቻ በ12 ወራት ተባዝቶ የአንድ ጊዜ ክፍያ የሚቀበል ይሆናል፡፡
  • የምርታማነት ቦነስ /ጉርሻ
 • ድርጅቱ የሰራተኛውን ምርታማነት እና የሥራ አፈፃፀም ውጤቱን በመገምገም ተፈፃሚ እየሆነ ባለው ፖሊሲ መሰረት ለተጨማሪ ትርፍ እና ምርታማነት ማነሳሳት ይችል ዘንድ  የአንድ ሰራተኛ ደሞዝ ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር በጉርሻ መልኩ የሚከፍል ይሆናል፡፡
 • የጉርሻ/ማበረታቻ እና የክፍያ ሁኔታ ብቁነት መስፈርትን በተመለከተ በህብረት ስምምነቱ ፖሊሲ እና በድርጅቱ ህገ ደንብ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በተለይ በዚሁ ስምምነት መሰረት ሰራተኛው ምርታማ ያልሆኑ ጊዚያት በአፕሬዛል ወቅት ያጠፋውን ጊዜ አጠቃላይ የህመም ፈቃድ ቀናት እንዲሁም በአመቱ የተከፈለበት እና /ወይም ያልተከፈለበት እረፍት ወይም የወሰደው እና ያልተጠቀመበትን ግምት ውስጥ የሚገባ ሲሆን ለእያንዳንዱ ሰራተኛ ተከፋይ የሚሆነው የቦነስ /ጉርሻ መጠን ለመወሰን ግምት ውስጥ የሚገባ ይሆና፡፡
  • ሽልማት
አንድ ሰራተኛ ምርጥ ውጤትን ለማሳካት (ለምሳሌ ስርቆትን መከልከል፣ ብክነትን መቀነስ እና ወጭን በመቆጠብ ምርታማነትን ለማሻሻል በስራ አፈፃፀሙ ላይ ውጤታማነት ማሳየት እና ፈጠራ ሃሳቦችን ማፍለቅ ብሎም አዲስ ተፈፃሚ የስራ ቴክኒክ እና ሃሳብ መፍጠር) የመሳሰሉትን የሚያስችሉ ከመተን በላይ ያለፈ ጥረት ማድረጉን ወይም ይህንን ስርዓት መፍጠሩ በድርጅቱ በሚረጋገጥበት ጊዜ ላቀረበው ሃሳብ እውቅና ለመስጠት ያህል ድርጅቱ የተለየ ሃሳ/ሽልማት ለሰራተኛው ሊሰጥ ይችላል፡፡ አፈፃፀም ዝርዝሩም በድርጅቱ ውስጣዊ ፖሊሲ ደንብ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ሦስት
ተወካይ ስለመሰየም
13.1. ሀ. አንድ ተቆጣጣሪ በከፍተኛ የስራ ሃላፊነት ተወክለው የሚሰሩ በዩኒቱ የድርጅቱ መዋቅር ከፍተኛውን የስራ ሃላፊነት ቀጥሎ ወይም ተቀራራቢ ሃላፊነት ከያዙት ሰራተኞች መካከል በከፍተኛ የሥራ ሃላፊነት እንዲሰሩ እንዲመደቡ መሰየም/መምረጥ ይችላል፡፡ በዚሁ መሰረት የተመረጠ ሰራተኛ በተወካይነት ስራ ሃላፊነት የማገልገል አለበት፡፡
ለ. የውክልና ስያሜ እኩል ሃላፊነት፣ ብቃት እና ስራውን ለማከናወን ጥራት ባላቸው ሰራተኞች መካከል የሚሰራጭ ይሆናል፡፡
ሐ. በተመሳሳይ ውክልና ለተሰጠው ሃላፊነት የውክልና ስያሜ አይሰጥም
13.2. ሀ. በከፍተኛ የስራ ሃላፊነት በተወካይነት የስራ ሃላፊነት የተመደበ እና የሚያገለግል የአንድ ሰራተኛ የስራ እና የክፍያ መደቡ ከዚሁ ምደባ በፊት ተይዞ በነበረው የስራ እና ደሞዝ መደብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው በከፍተኛው የስራ ሃላፊነት የመጀመሪያ ደሞዝ መሰረት ወይም በተከታታይ ከ15 ቀናት በላይ በዚሁ ከፍተኛ የስራ ሃላፊነት ለተወከለበት በራሱ ደሞዝ 12 ከመቶ ተጨምሮ የሚከፈለው ይሆናል፡፡ አንድ ሰራተኛ ለ15 ተከታታይ ቀናት ተወክሎ ከሰራ በኋላ ካቋረጠ እና መልሶ በተመሳሳይ ስራ ሃላፊነት ከተወከለ ከሁለተኛው የውክልና ስያሜ ቀን ጀምሮ ሚከፈለው ይሆናል፡፡
ለ. በውክልና የተሰየመ ሰራተኛ ከላይ እንደተጠቀሰው ለተወከለው የስራ ሃላፊነት ተከፋይ ከሚሆን ክፍያ ሌላ የሃላፊነት አበል ወይም ሌላ ክፍያ አይኖረውም፡፡
13.3. ሀ. ከላይ በአንቀጽ 13.1/ሀ የተመለከቱት ደንቦች ወይም ሁኔታዎች በማይኖርበት ጊዜ አንድ ሰራተኛ በከፍተኛው የስራ ሃላፊነት በውክልና በተከታታይ እያገለገለ እንደሆነ ከተረጋገጠ የስራው ቀደምትነት/ሲሜሪቲ በስራው እንዲወከል ተመድቦበት ከነበረው ወር ቀጥሎ ባለው ወር የመጀመሪያ ቀን ይሆናል፡፡ ነገር ግን በውክልና የስራ ሃላፊነት ላገለገለበት ጊዜ አይከፈለውም፡፡
ለ. በውክልና መሰረት የተያዘ ክፍት የሥራ ቦታ ከፍተኛው ለ90 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ በማወዳደር ለስራው ብቁ የሆኑትን ሰራተኖች መመደብ አለበት፡፡ ነገር ግን በክፍት ቦታ የስራ ሃላፊነት እንዲወከል የተመደበ ሰራተኛ በዚሁ የስራ ሃላፊነት በቋሚነት እንዲመደብ ብቁ አያደርገውም፡፡
13.4. በከፍተኛ ደረጃ ስራ ሃላፊነት የሚወከል አንድ ሰራተኛ በራሱ መደበኛ ስራ ወይም በውክልና የስራ ሃላፊነቱ የትርፍ ሰዓት እዲሰራ ከተፈለገ ለሰራበት የስራ ሃላፊነት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይከፈለዋል፡፡ ነገር ግን በውክልና የሥራ ሃላፊነት ለተሰራ የስራ ሃላፊነት የትርፍ ሰዓት ከላይ በአንቀጽ 13.2/ሀ መሰረት ሰራተኛው ለከፍተኛ የስራ ሃላፊነት እንዲወከል መብት ለተሰጠው ጊዜ ብቻ የሚከፈል ይሆናል፡፡
13.5. በከፍተኛ ደረጃ እንዲወከል የከተመደበ ሰራተኛ የራሱ ቋሚ የስራ ሃላፊነት ጎን ለጎን ማከናወን አለበት፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ተግባራት በአንድ ግለሰብ ብቻ መከናወን እንደማይችል አሳማኝ ምክንያት ካለ በሚመለከተው ክፍል የኤስቪፒ ወይም ቪፒ ወይም በዚሁ በተሰየመው ግለሰብ ፈቃድ ለሰራተኛው ቋሚ የሥራ ሃላፊነት ተወካይ ግለሰብ ሊመደብ ይችላል፡፡
13.6. በውክልና የስራ ሃላፊነት እያገለገለ ያለ ሰራተኛ በሌላ የስራ ሃላፊነት አይመደብም፡፡ እንዲህ አይነት ሁኔታ በሚከሰትበት እና ተወካይ መሰየም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ለዚሁ አላማ ሲባል ከሌላ መምሪያ ወይም ክፍል ብቁ ሰራተኛ ሊመረጥ ይችላል፡፡

13.7. የውክልና ስያሜ የተሰጠው አንድ ሰራተኛ በጽሁፍ የሚያሳውቁት ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ መምሪያ ወይም ክፍል ሁለት ሰራተኞች ተመሳሳይ የትምህር ደረጃ እና የሥራ ደረጃ ካላቸው የውክልና ስያሜው የጊዜ ቆይታው ከአንድ ወር በማይዘል በማቀያየር መሰረት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ አራት
እድገት እና ዝውውር

 1. “የስራ እድገት” በድርጅቱ መዋቅር ውስጥ አንድ ሰራተኛ ከዝቅተኛ የስራ ደረጃ/የስራ ሃላፊነት ወደ ከፍተኛ የሥራ ደረጃ/ሃላፊነት በመንቀሳቀሱ ምክንያት ሊገኝ የሚችል የስራ አፈፃፀም ውጤት ማለት ነው፡፡ አንድ ሰራተኛ ከዚህ በታች በአንቀጽ 14.1 እና 14.2 በተገለፀው ሁኔታ መሰረት ከወቅታዊ ዝቅተኛ የስራ ሃላፊነቱ ወደሚቀጥለው ከፍተኛ የስራ ሃላፊነት ከተዘዋወረ ወይም ከተመደበ የስራ እድገት አግኝቷል ተብሎ ይታመናል፡፡
 2. በድርጅቱ ክፍት የስራ ቦታ በሚኖርበት በማንኛውም ጊዜ ይህንኑ ለውጭ አመልካቾች ከመለጠፉ ወይም በማስታወቂያ ከመነገሩ በፊት በጄኦኤ ማስታወቂያ በኩል ለእድገት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያመለክቱ አስፈላውን መስፈርት ለሚያሟሉ ፍላጎት ላላቸው የድርጅቱ  ሰራተኞች በሙሉ በውስጥ ማስታወቂያ መነገር አለበት፡፡ እንደዚህ አይነት የክፍት ቦታ ስራ ማስታወቂያ ለሁሉም ሰራተኞች በግልጽ በሚታይ ቦታ መለጠፍ ያለበት ሲሆን ፍላጎት አመልልካቾች ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት የማመልከቻ ደብዳቤያቸውን ማስገባት አለባቸው፡፡
 3. አንድ ጊዜ በማስታወቂያ ተነግሮ ክፍት የስራ በታው በውስጣዊ እጭዎች ለመሙላት የማይቻል ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ድርጅቱ መስፈርቱን ማሟላት የሚችሉ የውስጥ ሰራተኞች አዲሱ ማስታወቂያ በሚወጣበት ጊዜ ከውጭ አመልካቾች እንዲሳተፉ ሊፈቀድላቸው በሚችል በውጫዊ የክፍት ስራ ቦታ ማስታወቂያ በኩል ክፍት ሆነው የስራ ሃላፊነት የመሙላት ነፃነት ወይም መብት አለው፡፡
 4. በማንኛውም ምክንያት አንድ ሰራተኛ እድገት ካገኘ ከተዘዋወረ ወይም ከስራ ሃላፊነቱ ዝቅ በሚልበት ጊዜ አዲሱ የስራ ሃላፊነት ለውጡ ደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም፣ አዲሱ የሥራ ሃላፊነት መጠሪያ እና ከአዲሱ የሥራ ሃላፊነት ዝርዝር የስራ መግለጫ ጎን ለጎን በጽፉፍ ለሰራተኛው የሚነገር ይሆናል፡፡ እንደዚህ አይነት ደብዳቤ እና ማስታወቂያ በድርጅቱ እና በሚመለከተው ሰራተኛ መካከል ያለውን የሥራ ቅጥር ውል ለማሻሻል/ለመቀየር የሚያገለግል ይሆናል፡፡
 5. ሰራተኛው በተዛወረበት አዲስ መምሪያ ወይም የሥራ ጣቢያ ለመስራት እምቢተኛ በሚሆንበት ወይም በሰራተኛው ተይዞ የነበረ የስራ ሃላፊነት ከተሰረዘ ወይም በሚያሳምን ምክንያት ተደጋጋሚ በሚሆንበት ጊዜ ወይም ወደ ሌላ የስራ ምደባ ማዘዋወር በማይቻልበት ጊዜ ድርጅቱ ለእርሱ ማስታወቂያ በመስጠት የሰራተኛውን የሥራ ቅጥር ውል ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ ይህ በሚደረግበት ጊዜ ድርጅቱ የስራ መቋረጥ ደብዳቤ ቅጅ ወደ ህብረቱ መላክ ወይም ማስታወቂያ መስጠት አለበት፡፡
 6. በስራ መደቡ ወደ ከፍተኛ የስራ ሃላፊነት የሚያድግ ሰራተኛ  አስፈላጊ የሆነ መሰረታዊ የትምህርት ብቃት፣ የስራ ልምድ፣ ችሎታ በሚጠይቀው እና ከዚህ በፊት ይዞት በነበረው የስር ሃላፊነት ባሳየው የስራ አፈፃፀም መሰረት መሆን አለበት፡፡
 7. በዚሁ የህብረት ስምምነት ካልተጠቀሰ በስተቀር የስራ እድገት ከላይ በንዑስ አንቀጽ 6 በተጠቀሰው መሰረት ሲሆን እደዚሁም በከፍተኛ የስራ መደብ በሚኖር ክፍት ስራ ቦታ/ሃላፊነት መሰረት ይሆናል፡፡
 8. በራሱ መምሪያ በተዋወቀው ክፍት የስራ ቦታ እና ከያዘው የሥራ ሃላፊነት ደረጃው ዘቅተኛ በሆነ ለመወዳደር የሚፈቀድለት ሰራተኛ አይኖርም፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ አንድ ሰራተኛ ሙያውን ለመቀየር ፍላጎት ያለውን ካለምንም አጥጋቢ ምክንያት በዚሁ ዝቅተኛ የስራ ሃላፊነት ከመወዳደር አይከለክልም፡፡
እድገት ያገኘ ሰራተኛ በወቅታዊ ደሞዙ የእድገት ጭማሪ 12 ከመቶ ወይም የአዲሱ የስራ ሃላፊነት ሰራተኛ የመጠሪያ ተመን ወይም ማንኛውም ትልቅ የሆነውን የሚሰጠው ይሆናል፡፡

የስራ አመፋፃፀም መርሀ ግብር ፈተና

 1. ማንኛውም ሰራተኛ በወቅቱ በያዘው የስራ ሃላፊነት በስራ አፈፃፀም መርሀ ግብር መሰረት ቀጥሎ ለማደግ ተፈላጊው ዝቅተኛ የአገልግሎት አመት ያጠናቀቀ ከሆነ ብቻ ለስራ አፈፃፀም/እድገት ፈተና ብቁ ይሆናል፡፡
 2. እንደዚሁም ማንኛውም ሰራተኛ ይህንኑ የእድገት መርሀ ግብር ፈተና ለመውሰድ ብቁ ለመሆን የተቀመጠውን መስፈርት በሙሉ ማሟላት አለበት፡፡
 3. ከላይ በአንቀጽ 14.2.1 የተመለከቱን ደንቦች የሚያሟላ ማንኛውም ሰራተኛ እና የእድገት ፈተናውን መውሰድ የሚፈልግ ተፈፃሚ የሚሆነው የስራ እድገት/የሥራ አፈፃፀም ፈተና ወር ላይ ከመጀመሪያው ቀን በፊት በ10 ቀናት ውስጥ ይህንን የስራ እድገት/የሥራ አፈፃፀም ፈተና የመውሰድ ሃሳን በጽሁፍ ለቅርብ አለቃው ወይም ለከፍተኛው ተቆጣጣሪ/አለቃ ማሳወቅ አለበት፡፡ የሰራተኛውን ጥያቄ የተቀበለው ተቆጣጣሪ ጥያቄውን በተቀበለ በ10 ቀናት ውስጥ የፈተናው ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ በጽሁፍ ለሰራተኛው ማሳወቅ አለበት፡፡
 4. ማንኛውም የጽሁፍ ወይም የተግባር የእድገት ፈተና በድርጅቱ ውስጣዊ ፖሊሲ እና ደንብ መሰረት የሚከናወን ይሆናል፡፡ ነገር ግን በስራ ላይ ሳለ ያካበተውን የስራ ልምድ እና የተሰጠውን ስልጠና ግምት ውስጥ የሚያስገባ መሆን አለበት፡፡
 5. በመርሃግበሩ መሰረት በወሰደው የእድገት ፈተና ውጤት ወይም ሂደት እርካታ ያልተሰማው ማንኛውም ሰራተኛ ካለ ውጤቱ ከመነገሩ በፊት ወይም ውጤቱ በተነገረ በ3 ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለህብረቱ ማቅረብ ይችላል፡፡

ከሃላፊነት ዝቅ ማድረግ

 1.  በሰራተኛው እና በድርጅቱ መካከል ለስራ መቋረጥ ምንጭ ወይም ምክንያት በሚሆንበት ጊዜ ወይም በፍ/ቤት ውሳኔ ወይም በድርጅቱ ፍላጎት ወይም ይህ ስምምነት እና አዋጁ እንደዲስፕሊን እርምጃ አካል ድርጅቱ ስራውን እንዲያቋርጥ የሚያስችለው በሚሆንበት እና ድርጅቱ ቅጣቱን በማቅለል ከውል መቋረጥ ፈንታ ከስራ ሃላፊነቱ ዝቅ ማድረግ በሚመርጥበት ጊዜ አንድ ሰራተኛ ወደ ዝቅተኛ የስራ ደረጃ ዝቅ ሊል ይችላል፡፡
 2. በራሱ ጥያቄ ወደ ዝቅተኛ ደረጃ የስራ ሃላፊነት የተዛወረ ሰራተኛ የተጠቀሰው ዝቅተኛ ደረጃ የስራ ሃላፊነት ወርሃዊ ደሞዝ እና በቀድሞው የስራ ሃላፊነቱ ዓመታ ላይ የተከማቸውን አገልግሎት ጨምሮ የሚሰጠው ይሆናል፡፡ ነገር ግብ ሰራተኛው ጠቅላላ የተሰላው ደሞዝ የዝቅተኛ ደረጃ የሥራ ሃላፊነት ከፍተኛውን ጣራ በሚያልፍበተ ጊዜ በዝቅተኛ ደረጃ የስራ ሃላፊነት ያለውን ከፍተኛው ጣራ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
 3. ወደ ዝቅተኛ የስራ ደረጃ ሃላፊነት ጊዜያዊ ዝውውር ስራውን ለማከናወን ሰራተኛው በተጨባጭ ሃላፊነቱን ከወሰደበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የዝውውር ወይም የዳግም ምደባ /ቦታ አበል

 1. አንድ ሰራተኛ ወደ ተለየ ቦታ ወይም ጣቢያ በሞዛወርበት ወቅት ድርጅቱ የሰራተኛው፣ የሚስት/ባል የልጆች እና ወደ ቦታው/ወደ ጣቢያው የውስጥ ድጋፍ ወጭዎችን በሙሉ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
 2. ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የተዘዋወረ ሰራተኛ ለእርሱም ሆነ ለቤተሰቡ አባላት ቁሳቁስ እና የግል መጠቀሚያ የማጓጓዣ /የዳግም ምደባ አበል መብት ያለው ሲሆን እንደሚከተለው ይፈፃማል፡፡

ሀ. አወንታዊ ማጓጓዣ፡ ሰራተኛው እና ባለቤቱ እያንዳንዳቸው እስከ 60 ኪ.ግ እንዲሁም እያንዳንዱ ልጅ እስከ 40 ኪ.ግ የአየር ጉዞ በአወንታዊ ማጓጓዣ መብት ይኖራቸዋል፡፡
ለ. በሚገኝ ቦታ ማጓጓዝ፡ ሰራተኛው እና ባለቤቱ እያንዳንዳቸው በተገኘ ቦታ እስከ 1 ኪ.ሎ ትርፍ ጓዝ የማጓጓዝ መብት ይኖራቸዋል
ሐ. ከዚህ በተጨማሪ በሚገኘው ቦታ መሰረት ድርጅቱ የሚያጓጉዘው

 1. ለሰራተኛው መበአየር ጭነት እስከ 1,200 ኪሎ ወይም ለምድር ላይ የማጓጓዣ ወጭ እስከ ብር 500 የሚሸፍን ይሆናል፡፡
 2. ለሰራተኛው ባለቤት በአየር ጭነት እስከ 700 ኪ.ግ
 3. ለእያንዳንዱ ልጅ የጭነት ጉዞ እስከ 100 ግራም ድርጅቱ የኢንሹራንስ አረቦን ለማቅብ የሚጓጓዘውን ከላይ የተጠቀሰው የቤተሰቡ ቁሳቁስ ለማሸግ እስከ ብር 1000 ይከፍላል፡፡
 4.  ከጣቢያ ውጭ የሚዘዋወሩ ሰራተኞች በሙሉ በድርጅቱ ውስጣዊ ፖሊሲ እና ደንብ መሰረት ይመራሉ
 5. እንደዚሁም ከላይ የተገለፀው የስራ ቅጥር ውላቸው ከተቀጠሩበት ቦታ በሌላ ቦታ ለተቋረጠባቸው ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ድርጅቱ ስራቸው የተቋረጠባቸውን ሰራተኞች ወደ ተቀጠሩበት ቦታ ወይም እነሱ መጓጓዝ ወደነበረባቸው ቦታ እርቀቱ ከዚሁ የማያልፍ ከሆነ ወደ ሌላ ቦታ የማጓጓዣ ወጭአቸውን የሚሸፍን ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት
ክፍት የስራ ቦታ እና ውስጣዊ እድገት
ሀ. የውስጥ ጨረታ/ውድድርን፣ ክፍት የሥራ ሃላፊነት/ስራ መክፈቻ በተመለከተ አንድን ሰራተኛ በጊዚያዊነት ማዘዋወር ወይም ክፍት የሥራ ሃላፊነቱን ለመሙላት ሰራተኛን ዝቅ በማድረግ መሙላት ሳይመርጥ ከቀረ በኋላ ለውድድር በድርጅቱ በማስታወቂያ የተነገረ የስራ ሃላፊነት ማለት ነው፡፡
ለ. ከላይ በአንቀጽ 19 የተመለከተው ክፍት የስራ ቦታ እጩ ሰራተኞች በማስታወቂያ የተነገረው የስራ ሃላፊነት መስፈርት ሳያሟሉ ከቀረ ወይም በተካሄደው ፈተና ወይም ቃለ መጠይቅ ከወደቁ ወይም በውስጥ ብቁ የሆነ አመልካች በማይኖርበት ጊዜ ብቻ ድርጅቱ የውጭ እጭዎች እንዲያመለክቱ የውጭ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ ግምት ውስጥ ሊያስገባ ይችላል፡፡
ሐ. የስራ መክፈቻ ማስታወቂያ በድርጅቱ የቡሌቲን ሰሌዳዎች ግልጽ በሆነ ቦታ ማስታወቂያው መለጠፍ ለበት ሲሆን ማስታወቂያ ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ ማመልከቻቸውን እዲያቀርቡ ፍላጎት ላላቸው ሰራተኞች 5 የስራ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡  
አንድ ሰራተኛ የሚከተሉትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ከሆነ ብቻ ክፍት በሆነው የስራ ቦታ ለመወዳደር ሊፈቀድለት ይችላል፡፡
ሀ. ተፈላጊ የሆነ የትምህርት የብቃት መስፈርትን እና ተገቢ የስራ ልምድን መያዝ አለበት፡፡ (ድርጅቱ በመጀመሪያው ማስታወቂያ ብቃት ያለው ሰራተኛ ባለመገኘቱ ምክንያት የስራ መክፈቻውን በሁለተኛ ጊዜ በሚያስተዋውቅበት ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ማሻሻል ወይም መቀየር ይችላል፡፡ የዚሁ ለውጥ በቅጅ ለህብረቱ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
ለ. በያዘው የሥራ ሃላፊነት ቢያንስ ለአንድ አመት ያህል ያገለገለ መሆን አለበት፡፡
ሐ. በአንቀጽ 14.1.8 መሰረት የያዘው የስራ ደረጃ ሃላፊነት ለውድድር ከተከፈተው የስራ ሃላፊነት እኩል ወይም ዝወቅተኛ መሆን አለበት፡፡
15.3. አንድ ሰራተኛ በእረፍት ላይ ሳለ በማስታወቂያ በተነገረው ማንኛውም ክፍት የስራ ቦታ ማመልከት የሚፈልግ ከሆነ የራሱ ፊርማ ያረፈበትን ማመልከቻ በማቅረብ ወይም በፋክስ መልዕክት ወይም በኢሜል መልዕክት በመላክ ማመልከት የሚችል ይሆናል፡፡
15.4. የጽሁፍ ፈተናውን ወይም ቃለ መጠይቁን ማለፍ ያልቻለ ማንኛውም ሰራተኛ በተሰጠው መስፈርት ከሌሎች እጩ ተወዳዳሪዎች በልጦ የተገኘ በመሆኑ ምክንያት ወይም አንደኛ በመውጣቱ ምክንያት ለክፍት ስራ ቦታው የወጣውን ጨረታ/ማስታወቂያ አሸናፊ እንደሆነ ተደርጎ አይወሰድም፡፡
15.5. ወደ ከፍተኛ፣ ዝቅተኛ ወይም ተመሳሳይ የስራ ሃላፊነት የተዘዋወረ ሰራተኛ ለእርሱ የተካሄደውን ፈተና ስለማለፉ በጽሁፍ ማስታወቂያ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ወይም የዝውውር እድገት ማስታወቂያ ከተገለፀለት ወይም እንደዚህ አይነት ማስታወቂያ ወይም ውጤት ካወቀበት ቀን ጀምሮ እድገቱን፣ ዝውውርን ወይም ዝቅ ማለቱን መቃወም አይችልም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰራተኛ ከቀድሞው የስራ ሃላፊነቱ ተፈፃሚ በሚሆን በሌላ የስራ መክፈቻ ማስታወቂያ በኩል በማወዳደር ብቻ ወደ ቀድሞው የስራ ሃላፊነቱ በቋሚነት ማስቀመጥ ወይም መልሶ መመደብ ይችላል፡፡
15.6. ማንኛውም እድገት ያገኘ ሰራተኛ የእድገት ቀን (የቀደምትነት/የሲኔሪቲ ሃላፊነት) ሰራተኛው ውድድሩን ማሸነፉን የሚገልጽ ለእርሱ ከተሰጠው የእድገት ደብዳቤ ቀን ጀም ወይም ዝውውሩን ካወቀበት ቀን ጀም የሚሰላ ሲሆን ነገር ግን ደሞዙ አዲሱን ስራ በተጨባጭ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ የሚሰላ ይሆናል፡፡ የሰራተኛው የቀድሞ መምሪያው ሰራተኛው ለእድገት ዝውውሩ ብቁ መሆኑ ከተገነገረበት ቀን ጀምሮ በአዲሱ መምሪያ ሪፖርት ከማድረግ ማስቀረት ወይም ከአንድ ወር በላይ ማዘግየት አይችልም፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው በጊዚያዊነት ወደተመሳሳይ የስራ ሃላፊነት ወይም ወደ ዝቅተኛ ደረጃ የስራ ሃላፊነት የተዘዋወረ ከሆነ የቀድሞው መምሪያው ከሁለት ተከታታይ ቀን በላይ ማስቀረት አይችልም፡፡
15.7. ሀ. ህብረቱ የውስት እድገት እና ዝውውር ለማከናወን በጥምር ኮሚቴ በሚቋቋመው በውስጥ የእድገት ኮሚቴ ላይ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡ የኮሚቴው ውህደት 3 የድርጅቱ ተጠሪዎች እንዲሁም 2 የህብረቱ እና 2 የድርጅቱ እንዲሁም 1 የህብረቱ ተጠሪዎች ይኖሩታል፡፡ የአባላቱ ብዛት የሚጨምር ከሆነ 1(አንድ) ከድርጅቱ እና 1 (አንድ) ከህብረቱ በ(1፡1) መሰረት ይሆና፡፡ በተጨማሪም የሰራተኞች እድገት እና ዝውውርን ጠመለከቱ ጉዳዮች በሙሉ እነዚህን ጉዳዮች በሚገዛው በድርጅቱ የውስጥ መምሪያ እና ፖሊሲ የሚመሰረት ይሆናል፡፡ ድርጅቱ ከህብረቱ ጋር በመመካከር ኮሚቴው የሚሰራበትን ህገ ደንብ እስታንዳርድ ሚሰጥ ይሆናል፡፡ ኮሚቴው ይህንን በዚህ የስራ ደንብ  መሰረት የተሰጠውን የስራ ሃላፊነት ከተወጣ በሆላ የሚፈርስ ይሆናል፡፡
ለ. ከላይ በአንቀጽ 14 ለተጠቀሰው ክፍት የስራ ቦታ ድርጅቱ የመጀመሪያ ውስጣዊ የስራ መክፈቻ ማስታወቂያ ከተካሄደ በኋላ ይህንን ተከትሎ የውስጥ እጭዎች በማስታወቂያ ለተነገረው የስራ ሃላፊነት የተቀመጠውን መስፈርት ሟሟላት ሳይችሉ ከቀረ ወይም ይህንን ተከትሎ በተካሄደው ፈተና እና ቃለ መጠይቅ ማለፍ ካልቻሉ ብቻ የውጭ እጭዎች እንዲያመለክቱ ውጫዊ ክፍት የሥራ ቦታ መስታወቂያ እንዲወጣ ምክንያት ይሆናል፡፡

ሐ. ለወጣው ክፍት የስራ ቦታ ብቁ የሆኑ አመልካቾች ምዝገባውን በሚያጠናቅቅበት ጊዜ ድርጅቱ የፈተና ቀን ሰዓት እና ቦታ የሚወስን ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት
የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና ነጥብ አሰጣጥ

  1. አላማ

ሀ. የሰራተኞቹን የስነ ምግባር ባህሪያት ለማሻሻል መልካም ጎኖቹን በማጠናከር፣ ደካማ ጎኖቹን ለማረም እና ምርታማነታቸውን በማሻሻል ለድርጅቱ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው
ለ. ሰራተኞች የራሳቸውን የክህሎት ግምገማ እንዲያደርጉ ማስቻል
ሐ. የላቀ ክህሎት ያላቸውን ሰራተኞች ለመለየት፣ እነሱን ለማበረታታት፣ ተገቢነት ያለው ስልጠና ለመስጠት እና ለከፍተኛ ስራ ሃላፊነት ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲሁም
መ. ዝቅተኛ የስራ አፈፃፀም ውጤት ላስመዘገቡ ሰራተኞች ሙያዊ እና የስራ አፈፃፀም ማሻሻያ ፕረፐግራም ለመስጠት እና ምንም አይነት መሻሻል ከሌለ ተገቢ እርምጃ ለመውሰድ ነው፡፡

  1. ድርጅቱ በቢኤስሲ/አይኤስሲ ውስጣዊ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት የሰራተኛው የስራ ባህሪን መሰረት በማድረግ ከሰራተኛ የሚጠበቅ ውጤት ወይም የሚወስደውን እርምጃ የማሳወቅ ተነሳሽነቱን የሚወስድ ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ሰራተኛው በዚሁ መስፈርት መሰረት እነዚህን ታረጌቶች እና ውጤቶች ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡ ህብረቱም በፖሊሲው መሰረት አፈፃፀሙን ለማረጋገጥ ክትትል ያደርጋል፡፡
  2. ሰራተኛው በስራ አፈፃፀም ግምገማው ወይም በተወሰደው እርምጃ ውሳኔ ላይ እርካታ ካላገኘ በህብረት ስምምነቱ ፖሊሲ እና በድርጅቱ ውስጣዊ መመሪያ በተመለከተው ቅሬታውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡
  3.  በተመረጡ የህብረቱ መሪዎች የሚካሄድ የስራ አፈፃፀም ግምገማ በስራ ቅጥራቸው ሁኔታ እና በመደበኛ ተግባራቸው ባሳለፉት ጊዜ በነበራቸው የስራ አፈፃፀማቸውን መሰረት በማድረግ ብቻ ፋይል የሚደረግ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ሰባት
የቅሬታ አቀራረብ ቅደም ተከተል/ደንብ
17.1. አጠቃላይ

 1. የድርጅቱን መመሪያ፣ ፖሊሲ ደንብ እና ህግ፣ የዚህ ስምምነት ወይም ህግ ትርጓሜ እና አፈፃፀሙን አስመልክቶ የሚኖር ማንኛውም ቅሬታ /አቤቱታ እንደቅሬታ ይቆጠራል፡፡
 2. ድርጅቱ፣ ህብረቱ እና የሚመለከተው እያንዳንዱ ሰራተኛ በተቻለ መጠን ለወገኖቹ የተሻለ ጥቅም ሲባል ሁሉንም ቅሬታ በስምምነት ለመፍታት በመልካም ትብብር ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. በህብረቱ በኩል ወደ ድርጅቱ ስሙ የቀረበ የህብረቱ ምክር ቤት ወይም የመደብር አስተናጋጅ አባል ከሚመለከተው ሃላፊ በመሆን ማንኛውንም ቅሬታ በመግባባት ለመፍታት ሙከራ ያደርጋል፡፡ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ጉዳዩ በዚህ ስምምነት በተመለከተው በቅሬታ አቀራረብ ደንብ መሰረት የሚታይ ይሆናል፡፡
 4. ሃላፊው በዚህ ውስጥ በተጠቀሰው የጊዜ ማእቀፍ በቅሬታው ላይ ውሳኔ የማይሰጥ ከሆነ ሰራተኛው ቅሬታውን ወደሚቀጥለው ከፍተኛ ደረጃ ሪፈር የማስደረግ መብት ይኖረዋል፡፡ ይህ ድንጋጌ በቅሬታ ደንብ መሰረት በሁሉም የቅሬታ አቀራረብ ደረጃዎች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
 5. ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰራተኛ በህመም ምክንያት በመከልከሉ ወይም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ በሌላ ምክንያት ካልቀረ በስተቀር የመጀመሪያ ደረጃ ቅሬታው ከተነሳበት ቀን ወይም ይህንኑ ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ለሚመለከተው ሃላፊ ማቅረብ አለበት፡፡
 6. ሰራተኛው ወይም ሰራተኛውን ተክቶ የሚንቀሳቀሰው ህብረት በዚሁ ውስጥ በተገፀው ጊዜ እና አኳኋን ቅሬታውን ማቅረብ ካልቻሉ ሰራተኛው ወይም ህብረቱ ይህንን የማድረግ መብታቸውን አሳልፈው እንደሰጡ የሚታመን ሲሆን ከዚህ በኋላ ጉዳዩ አይገመገምም፡፡
 7. አንድን ቅሬታ በምንይዝበት ጊዜ ሁለቱም ቅሬታ ያለው ሰራተኛ እና የሚመለከተው ሃላፊ በዚህ ስምምነት እዝል 5 የተቀመተውን የቅሬታ አቀራረብ ቅጽ መጠቀም አለባቸው፡፡ ድርጅቱ በሌላ ማንኛውም መልኩ ከረበን ቅሬታ የማስተናገድ ግዴታ ለበትም፡፡
 8. ህብረቱ የቅሬታው እና በእያንዳንዱ ደረጃ የተሰጠን ውሳኔ ቅጅ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
 9. በመጀመሪያው ደረጃ ያልተነሳ የቅሬታ ማንኛውንም ነጥብ በሁለተኛው ነጥብ እና በ3ኛው የቅሬታ ሂደት ደረጃ ላይ ማንሳት አይቻልም

17.2. ቅሬታ የማቅረብ ደንብ/ቅደም ተከተል
ሀ. ከሚሰራበት መምሪያ ግንኙነት የሌለው ቅሬታ ያለው ሰራተኛ ይህንኑ ለሚመለከተው መመሪያ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
ለ. ከላይ በአንቀጽ ፊደል ሀ ከተጠቀሱ ቅሬታዎች በስተቀር ሁሉም ቅሬታዎች በሚከተለው ደንብ መሰረት የሚታዩ ይሆናል፡፡
17.2.1. የመጀመሪያ ደረጃ ቅሬታ
ሀ. ቅሬታ ያለው ሰራተኛ ከላይ በአንቀጽ 17.1.5 በተመለከተው የጊዜ ማእቀፍ ውስጥ በእዝል 5 በተቀመጠው ተፈፃሚነት ያለው የቅሬታ አቀራረብ ቅጽ በመጠቀም የመጀመሪያ ደረጃ ቅሬታውን ለቅርብ አለቃው ማቅረብ አለመበት፡፡
ለ. አለቃው/ሃላፊው በ5 የሥራ ቀናት ውሳኔ ይሰጣል፡፡
ሐ. ቅሬታው በጽሁፍ በሰራተኛው ላይ የተጣለ የሥነምግባር እርምጃን የሚመለከት ከሆነ ሰራተኛው ቅሬታውን ወደሚቀጥለው ከፍተኛ ደረጃ ማቅረብ ይችላል፡፡
17.2.2. ሁለተኛ ደረጃ ቅሬታ
ሀ. ሰራተኛው በመጀመሪያው ደረጃ መሰረት በተሰጠው ውሳኔ እርካታ ካላገኘ ከቁጥጥሩ ውጭ በሆኑ ምክንያቶች ካልተደናቀፈ በስተቀር በአንደኛ ደረጃ ስር ውሳኔ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ወደሚቀጥለው ከፍተኛ ደረጃ ሃላፊ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
ለ. ከቁጥጥሩ ውጭ ካልሆነ በስተቀር የሚመለከተው ተቆጣጣሪ/ሃላፊ ቅሬታውን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ጉዳዩን መርምሮ በ5 ስራ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ውሳኔውን የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ስለቅሬታው ይዘት ከነሱ ጋር ለመወያየት ሁለቱንም የሚመለከተው ሰራተኛ እና የቅርብ ሃላፊውን ሊተራ ይችላል፡፡ ከተቻለ ሃላፊው/ተቆጣጣሪው ቅሬታውን በሰላም ለመፍታት ሙሉ ጥረት ያደርጋል፡፡
17.2.3. ሦስተኛ ደረጃ ቅሬታ
ሀ. በሁለተኛው ደረጃ ቅሬታ በመግባባት ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ከቁጥጥራቸው ውጭ በሆነ ምክንያት ካልተከለከሉ በስተቀር ህብረቱ ወይም ሰራተኛው ቅሬታውን ቅጹን በመሙላት በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ለሰራተኛ እና አሰሪ ግንኙነት መምሪያ የሚያርቡ ይሆናል፡፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ ግንኙነት መምሪያ ቅሬታውን ወደሚመለከተው ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ ሹም ወይም ወደ ክፍሉ ምክትል ፕሬዝዳንት የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

ለ. ከፍተኛው ሃላፊ ከሰራተኛው ወይም ከህብረቱ ተጠሪ ከተወያየ እና አስፈላጊ የሆነውን እያንዳንዱን ነገር ካደረገ በኋላ ቅሬታውን በተቀበለ በ20 የሥራ ቀናት ውስጥ ለሁለቱም ለድርጅቱ እና ለሚመለከተው ሰራተኛ ብቁ ነው ብሎ ያሰበውን ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ውሳኔው በድርጅቱ ውስጥ የመጨረሻ እና አስገዳጅ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ስምንት
የወሎ አበል
18.1. የውሎ አበል ለድርጅቱ የስራ ጉዳይ ከመኖሪያ ቤታቸው ውጭ ለሚላኩ ሰራተኞች ምግባቸውን፣ መዝናኛ፣ ትራንስር እና ሌሎች ተመሳሳይ አስፈላጊ ወጭዎች ለመሸፈን የሚሰጥ ነው፡፡
18.2. የውሎ አበሉን በቅድሚያ የሚወስድ ይሆናል በሳይት ላይ ቅድመ ክፍያ ማስተካከያ ወይም ክፍያን ማረጋገጥ የስራ ቀናቱ በሚራዘምበት ጊዜ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
18.3. ሌላ የውሎ አበል እና አበል በድርጅቱ ፖሊሲ መሰረት ብቁ ለሆኑት ሰራተኞች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
አንቀጽ አስራ ዘጠኝ
ትራንስፖርት
19.1. በድርጅቱ የትራንስፖርት አመዳደብ ኡደት ውሳኔ መሰረት ለመደበኛ የቀን ፈረቃ ሰራተኞች ድርጅቱ ከቤታቸው ወደ ስራ ቦታ እና ወደ ቤታቸው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በመደበኛ የስራ ሰዓታት ድርጅቱ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ይህንኑ ማድረግ ካልቻለ ሰራተኛው በስራ ቦጀታው ሪፖርት የማድረግ ሃላፊነት አለበት፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖር/አለመገኘት ሰራተኛ ከስራ ቦታው ከቀረ ይቅርታ አይኖረውም፡፡
19.2. ድርጅቱ የሰራተኛ መኖሪያ ለኩባያው ተሸከርካሪ አመች እስከሆነ ድረስ በሌሊት ፈረቃ እንዲሰሩ ለተመደቡ ሰራተኞች ከቤታቸው ወደ ስራ ቦታ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሃያ
ነፃ ወይም ቅናሽ የአየር ትራንስርት
20.1. በድርጅቱ እና በህብረቱ ስምምነት ተገዥ የመሆን ድርጅቱ እንደሁኔታው ከአንድ አመት አገልግሎት በላይ ላላቸው ሰራተኞች እና ብቁ የቤተሰብ አባሎቻቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሉት የበረራ መስመሮች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በውስጣዊ ፖሊስ እና ደንብ መሰረት ከሌሎች የአየር መንገዶች በፈፀመው ስምምነት መሰረት በቅናሽ ተመን ወይም በነፃ የአየር ላይ ትራንስፖርት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የሚሰጥ አመታዊ ትኬት በድርጅቱ ኤምፒ እና ፒኤም መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡ ነገር ግን በሚሰጠው የትኬት ብዛት ለውጥ እና በሰራተኞች አጠቃቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲህ አይነት ለውጥን የሚጋብዝ ፈጣን እድገት እየጨመረ እንደመምጣቱ እንዲሁም የሰራተኞች ብዛት በመጨመሩ እና ውድድሩም እየከበደ በመምጣቱ ምክንያት ድርጅቱ ለውጥን ማሳወቅ ሲፈልግ ከህብረቱ በመመካከርሊፈጽም ይችላል፡፡
20.2. በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዑደት በሚመለከተው ዘርፍ ሰራተኞች እና የቅርብ የቤተሰብ አባላት አወንታዊ የቀነሰ ተመን የአየር ትራንስፖርት እንዲኖራቸው የሚጠይቁ ተፈፃሚ የሆነ ፌር 40 ከመቶ መክፈል አለባቸው፡፡ ይህም አትራፊ ተሳፋሪ በማይኖርበት ጊዜ ብቻ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

20.3. ከ12 ወራት በታች አገልግሎት ያላቸው ሰራተኞች ድርጅቱ ግምት ውስጥ የሚያስገባው አደጋ ወይም አስቸኳይ ጉዳይ ከሌለ በስተቀር ነፃ ወይም የቀነሰ ተመን የአየር ትኬት አይሰጣቸውም፡፡

አንቀጽ ሃያ አንድ
ምርታማነት
21.1. ድርጅቱ ምርታማነታቸውን ለመጨመር የሚያስፈልጉ ስልጠናዎችን የሚሰጥ ይሆናል፡፡ እነደዚሁም የሰራተኞችን ጤና፣ ምቾት እና ክብር ለመጠበቅ አስፈላጊ እርምጃዎችን በሙሉ የሚወስድ ይሆናል፡፡
21.2. ድርጅቱ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስፈልግ የጥራት እስታንዳርድ እና ተፈላጊ ፍጥነት የሚወስን ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንደዚህ አይነት ፍጥነት እና ጥራት በቅድሚያ መመዝገብ አለበት፡፡
21.3. አንድ ሰራተኛ በሚፈለገው የጥራት እና ፍጥነት እስታንዳርድ መሰረት ስራዎቹን ማከናወን አለበት፡፡ የጥራት እና ፍጥነት እስታንዳርድ በማይወጣበት ወይም እንደዚህ አይነት እስታንዳርድ ለማውጣት በማይቻልበት ጊዜ ሰራተኛው አጥጋቢ ከሆነ የጥራት እና ፍጥነት እስታንዳርድ የተሰጠውን ስራ በትጋት እና በጥንቃቄ ማከናወን አለበት፡፡
21.4. ድርጅቱ እና ህብረቱ በመቀናጀት አካላዊ ደህንነቱን ለማሳደግ እና ባህሉን ለመደገፍ ብሎም የሰራተኞችን ምርታማነት ለማሳደግ አስፈ ላጊ የሆነ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
አንቀጽ ሃያ ሁለት
ስልጠና እና የዕድገት መርሀ ግብር
22.1. ትርጓሜ
ስልጠና - በድርጅቱ ውስጥ በስራ ላይ ሳሉ ወይም ከስራ ውጭ ሲሆኑ የሚሰጥ የማንኛውም ሙያዊ ወይም የክህሎት ልማት ስልጠና ትምህርታዊ ኮርስን ያካተተ ማለት ነው፡፡
22.2. የሥልጠና ደንብ እና መስፈርት

 1. ድርጅቱ ለስራው እና በስራ ሃላፊነት ላለው ሰራተኛ ስልጠናውን መውሰዱ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን ማንኛውን ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 2. ህብረቱ ውድድር የሚፈልግ ለስልጠና ሰራተኞችን በሚመለጡበት ጊዜ በድርጅቱ ፖሊሲ መሰረት መከተላቸውን በግልጽ የሰፈረ መስፈርት እና ደንብ መኖሩን ያረጋግጣል፡፡  
 3. በእድገት መርሃ ግብር የተጠቀሰ ስልጠና በድርጅቱ ለተመደቡ ሰራተኞች እና ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ ለድርጅቱ ለተወሰነ ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት የተለየ ስምምነት/የግዴታ ቃል ለመፈረም ፈቃደኛ ለሆኑ ብቻ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የተለየ ስምምነት ወይም የግዴታ ቃል የሚፈልግ ስልጠና ለመውሰድ አስፈላጊ የሆነ የብቁነት መስፈርት በድርጅቱ የውስጥ  ፖሊሲ እና ደንብ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡
 4. ከአንድ ወር በላይ በሚወስድ በማንኛውም ስልጠና እንዲሳተፍ የተመረተ ማንኛውም ሰራተኛ ስለስልጠናው ሂደት እና ስላገኘው ትምህርት ስልጠናው ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ አጭር ሪፖርት ለቅርብ ሃላፊው የማቅር ግዴታ አለበት፡፡

22.3. የእድገት መርሃ ግብር

ድርጅቱ የእያንዳንዱ የስራ ሃላፊነት የእድገት መርሃ ግብር የሚያዘጋጅ ሲሆን በዚሁ የእድገት መርሀ ግብር ላይ ማንኛውም ለውጥ ካለ የዚህኑ የተረጋገጠ ቅጅ በመላክ ለህብረቱ በመላክ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሃያ ሦስት
የስራ ቅጥር ውል ስለማቋረጥ
23.1. የስራ ማቋረጥ ምክንያቶች
የአንድ ሰራተኛ የሥራ ቅጥር ውል በዚሁ አዋጅ ህገ ደንብ በተመለከቱት ስርአቶች ወይም በዚሁ ስምምነት በተቀመጠው እና ወይም በድርጅቱ እና በሚመለከተው ሰራተኛ መካከል በተፈፀመው ስምምነት ከተዘረዘረው ነጥብ/ደንብ መሰረት በድርጅቱ ወይም በራተኛው ተነሳሽነት በአንዳቸው የሚቋረጥ ይሆናል፡፡
23.2. በድርጅቱ የሚቋረጥ የስራ ቅጥር ውል

 1. ድርጅቱ ተፈፃሚ በሚሆነው ህግ መሰረት ለስራ ውሉ መቋረጥ አጥጋቢ ምክንያት ነው ብሎ ባመነበት መሰረት ለሰራተኛው አስፈላጊ ማስታወቂያ በመስጠት የስራ ቅጥር ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡
 2. በዚሁ አዋጅ እና በሌሎች ተገቢ በሆኑ የአሰሪ እና ሰራተኛ ህግ በተመለከተው ደንብ ተገዥ የሚሆን ድርጅቱ በዚህ ስምምነት እዝል እንደተመለከተው የስራ ውልን የማቋረጥ ማጠንቀቂያ የሚሆን ማንኛውም አይነት ጥፋት በሚከሰትበት ጊዜ ለሰራተኛው ምንም አይነት ማስታወቂያ መስጠት ሳያስፈልግ ድርጅቱ የስራ ቅጥር ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡
 3. የኋላኛውን ጥፋት ምክንያት በማድረግ የማንኛውም ሰራተኛ የስራ ቀጥር ውል በሚቋረጥበት ጊዜ ድርጅቱ የስራ ውል መቋረጥ ተፈፃሚ የሚሆንበት ቀን እና ምክንያቱን በመጥቀስ ማንኛውም ምርመራ /ግምገማ የነበረ ከሆነ ከዚሁ ተግባር በኋላ ውሳኔ በተሰጠበት በ30 ቀናት ውስጥ ለሰራተኛው የስራ መቋረጥ ደብዳ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 4. የስራ መቋረጥ ማስታወቂያ ለሰራተኛው በአካል መሰጠት አለበት፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው ማግኘት ካልተቻለ ወይም ሰራተኛው ማስታወቂያውን ለመቀበል እምቢተኛ ከሆነ ማስታወቂያው ሰራተኛው በሚሰራበት የስራ ቦታ ለ10 የጊዜ መቁጠሪያ ቀናት በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የሚለጠፍ ይሆናል፤ እንዲሁም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በአካል ካልቀረበ ወይም ማስታወቂያውን ካልተቀበለ ማስታወቂያው እንደተቀበለ እና ይህንኑ በሰራተኛው ፋይል ተያያዥ እንደሆነ ይታመናል፡፡

በህግ ወይም በስምምነት አሰራር የስራ ቅጥር ውል ስለማቋረጥ

 1. የማንኛውም ሰራተኛ የስራ ቅጥር ውል ሰራተኛው ሲሞት ተፈፃሚ በሚሆነው ህግ ጦረታ ከወጣ ወይም ድርጅቱ በመክሰሩ ምክንያት በቋሚነት ከዘጋ ወይም በሌላ ማንኛውም ምክንያት ወይም ሰራተኛው ከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የአካል ጉድለት ያለው በመሆኑ ስራውን ማከናወን በማይችልበት ጊዜ ወዲያውኑ የሥራ ቅጥር ውሉ የሚቋረጥ ይሆናል፡፡
 2. ማንኛውም ሰራተኛ ወይም ድርጅቱ በዚህ ስምምነት መሰረት በመካከላቸው በተፈፀመው ደንብ መሰረት በተወሰነ የጽሁፍ ስምምነት ስራ ቅጥር ውሉን ማቋረጥ ይችላሉ፡፡
 3. አንድ ሰራተኛ ተፈፃሚ በሆነው ህግ እንደተመለከተው በይፋ የጡረታ እድሜው መድረሱ በሚታወቅበት ጊዜ የስራ ቅጥር ውሉ በህግ አሰራር መሰረት ወዲያውኑ የሚቋረጥ ይሆናል፡፡
 4. ከላይ እንደተመለከተው ድርጅቱ በይፋ ከሚለያዩበት ቀን ከ12 ወራት በፊት በጡረታ ለሚወጡ ሰራተኞች በጡረታ ምክንያት እንደሚሰናበቱ የሚገልጽ የጽሁፍ ማስታወቂያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ እንደዚሁም ሰራተኛው ለጡረታ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ በሚወጣበት ጊዜ አስፈላጊ ፎርማሊቲ ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
 5. ዚህ ደንብ ንዑስ አንቀጽ አንድ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ሰራተኛ ይፋዊ የጡረታ እድሜው ከመድረሱ በፊት በመንግስት ሰራተኞች ህግ መሰረት በራሱ ፍላጎት ምክንያት አስቀድሞ ከድርጅቱ በጡረታ መልኩ ለመውጣት ጥያቄ በሚያቀርብበት ጊዜ ጡረታ የመውጣት ፍላጎቱን በመግለጽ ከ30 የጊዜ መቁጠሪያ ቀናት በፊት ለድርጅቱ ማስታወቂያ መስጠት አለበት፡፡ የሰራተኛው ጥያቄ ተፈፃሚ በሚሆነው ህግ መሰረት ጎን ለጎን ተፈላጊ ከሆኑት ደንቦች በሚገመግምበት እና ጥያቄው በድርጅቱ ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ ስለሚገባው መብት ወይም ጥቅማጥቅም ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል የሚያሳውቅ ሲሆን ሰራተኛው በድርጅቱ የጡረታ ጥቅማ ጥቅም የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡

23.4. በሰራተኛ ስለሚቋረጥ የስራ ቅጥር ውል

 1. የሙከራ የሥራ ቅጥር ጊውን ያጠናቀቀ ሰራተኛ በማንኛውም ምክንያት ከስራው በራሱ ተነሳሽነት መልቀቅ በሚፈልግበት ጊዜ የሚለቅበትን ምክንያት ወይም ፍላጎት በመጥቀስ ቢያንስ ከ30 የጊዜ መቆጠሪያ ቀናት በፊት ለድርጅቱ የቅድሚ ማስታወቂያ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ የሰራተኛው መልቀቅ በተወሰነ ተፈፃሚ በሚሆን ቀን መቀበሉን በጽሁፍ በማሳወቅ የማስታወቂያ ጊዜውን ሊያሳጥረው ይችላል፡፡
 2. ከላይ በንዑስ አንቀጽ አንድ የሚፈለግ ዝቅተኛው የ30 ቀናት ቅድመ ማስታወቂያ ሳይሰጥ በራሱ ፍላጎት ከስራው የሚለቅ ማንኛውም ሰራተኛ በማስታወቂያው ምትክ እንደካሳ ለድርጅቱ የ30 ቀናት ደሞዝ የመክፈል ተጠያቂነት ይኖርበታል፡፡ ድርጅቱ ከሰራተኛው የሚጠበቅ የ30 ቀናት የማስታወቂያ እረፍት ፈር ለማስያዝ ይችል ዘንድ ለሰራተኛው ከሚከፈል የመጨረሻ ክፍያ መቀነስ ወይም መያዝ ይችላል፡፡
 3. በሰራተኛው የሚሰጥ ማንኛውም ማስታወቂያ ሰራተኛው ለቅርብ ሃላፊው ወይም ለድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት (የሰው ሃብት ስራ አመራር ክፍል) በደብዳቤ ወይም ፣በተመዘገበ መልዕክት ማቅረብ አለበት፡፡

23.5. የአገልግሎት ክፍያ እና የአገልግሎት ምስር ወረቀት

 1. በዚሁ ስምምነት ደንብ መሰረት የሥራ ቅጥር ውል በሚቋረጥበት ጊዜ ድርጅቱ ተፈፃሚ በሚሆን ህግ እና ከራሱ ፖሊሲ ጎን ለጎን የሰራተኛው ደሞዝ ተዛማጅ የሆኑ ክፍያዎች እና ሌሎች ክፍያዎች የሚከፍል ይሆናል፡፡
 2. ድርጅቱ ማንኛውም ስራውን ላቋረጠ ሰራተኛ ሙያውን፣ የአገልግሎት ወቅት፣ ደሞዝ፣ እንደዚሁም የአቋረጠበትን ምክንያት በመጥቀስ በፎቶግራፍ አያይዞ ሰራተኛው የማረጋገጫ ክሊራንሱን ካጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ የአገልግሎት ምስክር ወረቀት ሚሰጥ ይሆናል፡፡
 3. ለከፍተኛ ትምህርት ስራቸውን የለቀቁ እና ያቋረቱ ሰራተኞችን በተመለከተ በግል የሚያገኙት ፤

ሀ. አንቀጽ 23.1 እና 23.4 ድንጋጌዎች እደተጠበቁ ሆነው ድርጅቱ ሰራተኛው በውጭ ሀገር የትምህርት እድል ካገኘ መልቀቁን አይቃወምም፤

ለ. ለትምህርት ወደ ውጭ የሚሄድ ሰራተኛ የትራንስርት የሚከፍል ሌላ አካል የሌለ ከሆነ በኩባንያው ፖሊሲ መሰረት ለ90 ቀናት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ ሚገኝ የአየር ጉዞ የደርሶ መልስ ትኬት ሚሰጠው ይሆናል፡፡

ምዕራፍ ሦስት
የተወሰኑ የሰራተኞች ቡድን የስራ ሁኔታን አስመልክቶ የተለዩ ድንጋጌዎች

አንቀጽ ሃያ አራት
የትኬት ኤጀንት፣ ገንዘብ ያዥ እና የሂሳብ ባለሙያ
24.1. ድርጅቱ የኤጀንቱ፣ ገንዘብ ያዥ እና የሂሳብ ባለሙያ የሥራ አፈፃፀም ለማሻሻል/ለማሳደግ አስፈላጊ የሆኑ የስሌት ማሽን እና ማንዋል የሚሰጥ ይሆናል፡፡
24.2. ከሚመለከተው የአካውንቲግ/የሂሳብ ባለሙያዎች መምሪያ በሰራተኛው ላይ የኤጀንት አደባይስ ኖት ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ በዚሁ የኤጀንት አድባይስ ኖት የተመለከተው /የተጠቀሰው ያልተከፈለ የገንዘብ መጠን በ4 ወር ከ15 ቀናት ውስጥ መሰብሰብ በማይቻልበት ወቅት ድርጅቱ በዚሁ በተጠቀሰው ወቅት መጨረሻ ላይ ገንዘቡን ለመክፈል ከሰራተኛው ወርሃዊ ደሞዝ 15 ከመቶ የሚቀንስ ይሆናል፡፡
24.3. ሀ. በስህተት ገንዘብ ያጠፋ ገንዘብ ያዥ ይህንኑ እዳ ለመክፈል ከወርሃዊ ደሞዙ ከ15 ከመቶ በላይ ለመክፈል አይገደድም፡፡
ለ. በየቀኑ በጥሬ ገንዘብ በአማካኝ የኢትብር 10ሺህ ወይም ከዚያ በላይ የሚይዝ እያንዳንዱ ገንዘብ ያዥ ወይም እንደገንዘብ ያዥ የሚሰራ ትኬት ኤጀንት በስህተት ምክንያት ለሚተፋ ገንዘብ ከተጠያቂነት ነፃ ለማድረግ በየወሩ የተጣራ የኢት ብር 350 የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡ እንደሁኔታው በእያንዳንዱ አመት መጨረሻ ጠቅላላ የተሰጠው የገንዘብ መጠን የሂሳብ ሚዛ ወይም ሙሉ ክፍያ ለገንዘብ ያዡ ወይም ለሚመለከተው ኤጀንት የሚከፈል ይሆናል፡፡
ሐ. ነገር ግን ገንዘብ ያዥ ወይም እንደ ገንዘብ ያዥ ሆኖ የሚሰራ የትኬት ኤጀንት ስራውን ከለቀቁ እና ሌላ ገንዘብ ያዥ ወይም ኤጀንት የበጀት አመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ከተወከለ የሂሳብ ሚዛኑን ወይም ጠቅላላ ክሬዲት የተደረገው በዚሁ ሃላፊነት ባገለገለው ጊዜ መሰረት በተሰጠው ተጠያቂነት ነፃ ማድረጊያ የተጣራ ኢትብር 350 በየወሩ የሚከፍል ሲሆን ወይም በዚህ ወቅት የጠፋ ገንዘብ ከሌለ የውክልና ክፍያውን የሚከፍል ይሆናል፡፡
24.4. የትርፍ ክፍያ ወይም የትርፍ ሪፈንድ ስህተት በ4 ወራት ከ15 ቀናት ውስጥ ከታወቀ እና ሰራተኛው ያልተሰበሰበውን መመለስ ካልቻለ ድርጅቱ የሚመለከተውን የገንዘብ መጠን ለመክፈል በየወሩ ከሰራተኛው ደሞዝ 15 ከመቶ የሚቀንስ ይሆናል፡፡

24.5 የሰራተኞች ሃላፊ ስለ ተከፈሉት ክፍያዎች ወይም ተመላሽ የሆኑትን ወይም በመሰብሰብ ላይ ያሉትን እንዲከናወኑ አመራጭ ያለውን ቢሮ ሊጠቀም ይችላል፡፡

አንቀጽ ሃያ አምስት
የአየር መንገድ አስተናጋጆች
ጠቅላላ መነሻ/የሠራተኞች ግዴታ መብታቸው እና ጥቅማ ጥቅማቸው በአጠቃላይ ውል ስምምነት ስር የተጠቀሰ ነው፡፡ የሚከተለውም ተጨማሪ መብቶች፣ ጥቅሞችና ግዴታዎች ተሳፋሪዎችን የሚያግዙት ሰራተኞች የሚመለከት እና ሥራ ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
25.1 ማብራሪያ

 1. « የአገየር መንገድ አስተናጋጆች »  ማለት በሙያው የሰለጠነ እና ልምድ ያላቸው ለተሳፋሪዎች እንክብካቤ ድጋፍ የሚሰጡ ናቸው፡፡ በተሰጣቸው ሃላፊነት መሠረት ለመንገደኞች ምቾት እና ለእንክብካቤአቸው በተቀመጠው ህግ ደንብ እና ሥርዓት መሠረት አገልግሎታቸውን ይሰጣሉ፡፡
 2. « በአንድ ላይ የተደራጁ የአየር መንገድ አስተናጋጆች » ማለት ካሉት የሴት አስተናጋጆች ልምድ ካላቸው የሴት አስተናጋጆች ሙሉ በሙሉ የተውጣጡ ወይም በከፊል የተውጣጡ ማለት ነው፡፡
 3. « ጥምር አስተናጃጎች» ማለት ካሉት አየር መንገድ ላይ ላስተናጋጅነት ከሚሰሩት ሁለት ወይም ከዛ በላይ የተውጣጡ ቡድን ማለት ነው፡፡
 4. « የስራ ጊዜ» ማለት ከመነሻ በፊት 1፡30 ሰዓት አስቀድሞ እና ወይም አስተናጋጆች ለስራቸው ወደ አውሮፕላኑ ከሚመጠበት ሰዓት ጀምሮ እስከሚበሩበት፣ አስከሚሄዱበት መድረሻ ድረስ ወይም አውሮፕላኑ ከሄደበት ጉዞውን ጨርሶ ወደ ሃገር እስኪመለስበት ድረስ ያለ ነው፡፡
 5. «የሥራ ቀናቶች» በአካባቢ ሰዓት አቆጣጠር መሠረት ለተከታታይ 24፡00 ሰዓት ከሪፖርት ጀምሮ ያለ ሰዓት ነው፡፡
 6. «የበረራ ተግባራቶች» ማለት በበረራ ላይ እያለ የሚሰጥ አገልግሎት የበረራ እቅድ ማውጣት ተጨማሪ ክፍል ወይም ተሳፋሪ የማይጭኑ በረራዎች ለምሳሌ የማስታወቂያ በረራ እንደገና እቅድ የተያዘለት በረራ የጭነት በረራዎች እና የመሳሰሉት፡፡
 7. « በረራ እቅድ » ማውጣት ካሉት ተከታታይ በረራዎች ውስጥ አንዱ የበረራ ክፍል ነው፡፡
 8. « የዘገየ በረራ» ማለት በታቀደለት ሰዓት ላይ በረራ የማይጀምር የበረራ አይነት
 9. « የተሰረዘ በረራ » ማለት የተሰዘረ በረራ ወይም የተቋቋረጠ በረራ ማለት ነው፡፡
 10.  «ተጨማሪ ክፍል » ይህ ክፍል ተጨማሪ የበረራ እቅድ በታቀደላቸው የበረራ እቅድ ላይ ቦታ  በመሚላት ወይም የበረራው አቅጣጫ በመቀየሩ መሄድ ያልቻሉትን ተሳፋሪዎች የሚያጓጉዝ ማለት ነው፡፡
 11.  «የተለየ በረራ ወይም ቪአይፒ» ይህ የበረራ አይነት ያለ እቅድ ለግል ሰዎች ወይም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች ወይም በከፍተኛ ድርጅቶች ሰራተኞችን ለማጓጓዝ የታቀደ ነው፡፡
 12.  «አጋዥ በረራዎች» ማለት ተሳፋሪ ወይም እቃ የማይጭኑ ሆኖ ዋነውን በረራ ላይ ያለውን አውሮፕላን በነዳጅ እና በተለያየ ነገር የሚደግፉ የበበራ አይነት ናቸው፡፡
 13.  « እቅዶች » ማለት አውሮፕላን ውስጥ ለሚሰሩት ሠራተኞች በየእለቱ የሚሰሩትን ተግባራቶችን ተጠባባቂ የሚሰጥ ስልጠናዎች የጉዞ ሰነዶች የጤና ምርመራ የእረፍት ቀናቶችን በውስጡ የያዘ እቅድ ማለት ነው፡፡
 14.  « መነሻ እና መድረሻ »  ይህ ማለት የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ሥራቸውን የሚጀምሩበት ቦታ እና በጉዞ ላይ ያለ የበረራ ሰዓት ነው፡፡
 15.  « የበረራ ሰዓት» አውሮፕላኑ ጉዞውን ከጀመረበት ሰዓት ጀምሮ ተመልሶ እስኪያርፍ እና የአውሮፕላኑ ሞተር እስኪጠፋ ድረስ ማዕከል ያለው ጠቅላላ ሰዓት ነው፡፡
 16.  «የመነሻ የሥራ ልብስ ማለት የጉዞ ዩኒፎርም ወይም ልብስ ሲሆን ሥራቸውም ለማከናወን ከመነሻ እስከመድረሻ ድረስ የሚጠቀሙት የሥራ ዩኒፎርም ነው፡፡
 17. «  የአውሮፕላኑ መነሻ ወይም መሠረት» ይህ ማለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው ቢሮ የተመሰረተበት ከተማ አዲስ አበባ ማለት ነው፡፡
 18.  «ተጨማሪ ሥራዎችን በጋራ የሚሰሩ ሰራተኞች» ማለት የሥራ የበረራ ላይ ያለ ስራ ሆኖ በጣም ረጅም ጉዞ ሲደረግ ከሁለት ወይም ከዛ በላይ የአውሮፕላኑ ሰራተኞች የሚሰራ እና ይህ አይነት ተግባራቶች የሚደረጉት ረጅም ሰዓት በረራ በሚደረግበት ጊዜ እና ይህ ማለት አንድን ሃጉር አቋርጦ ወደ ሌላ ሃጉር በሚሄዱ የበረራ አይነት ያካትታል፡፡ ነገር ግን በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ ሁለት እና ከዛም በላይ ቡድኖች ሥራውን እንዲያከናውኑ ሊመደቡ ይችላሉ፡፡
 19.  «ወርሃዊ እቅድ» የአውሮፕላን አስተናጋጅ ሰራተኞችን ለመመደብ እንዲያመች ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ የሚወጡ እቅዶች ሲሆን ባላቸው የሥራ ሰዓት ላይ ይመሰረታል፡፡ ይህ እቅድም ለእያንዳንዱ ሰራተኞች በሳምንት አርብ እለት ወይም ሁለተኛው ወር ሳይጀምር 5 ቀን አስቀድሞ ስለወጣው የስራ እቅዳቸው ይነገራቸዋል፡፡

የወርሃዊ የበረራ ሰዓቶች
25.2.1 በአንድ ወር ውስጥ ባሉት የሥራ ቀናቶች አንድ የአውሮፕላን አስተናጋጅ 80 የበረራ ሰዓቶችን እንዲሰራ ይጠበቅበታል፡፡
25.2.2 በንዑስ አንቀጽ 1 ስር የተጠቀሰው ወርሃዊ የበረራ ሰዓት የታገዱ የበረራ ሰዓቶችንም ያካትታል፡፡ በቀን ውስጥ ለ3 ሰዓት የአውሮፕላን አስተናጋጇ ስለ አካሏ ጤንነት ምርመራ መደረግ አለባት፡፡ ተደጋጋሚ ስልጠናዎችን ለዚህ አይነት የተዘጋጁ ሰነዶችን ማደስ በተጨማሪም የሥራ ዩኖፎርሞችን እና ለሚቀጥለው ሥራ ምደባ ዝግጅትነትን ያካተተ እና በአንቀጽ 25.8 በአንቀጽ 25.9 መሠረት ነው፡፡
25.3 የሥራ ጊዜ ገደብ
ሀ/ 14 ሰዓቶች ለቀን በረራ እና 13 ሰዓት ለማታ በረራ ከፍተኛው የሥራ ሰዓት ሲሆን ይህም በ24 ሰዓት ውስጥ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚያካትተው አውሮፕላኑ መብረሩን ከተዘጋበበት ሰዓት ጀምሮ አውሮፕላኑ ማረፉ እስኪታወቅበት ድረስ ነው፡፡ ለአንድ የአውሮፕላን አስተናጋጅ ሠራተኞች ቡድን 14 የሥራ ሰዓቶች የ10 ሰዓት የበረራ ሰዓት ውስጥ አውሮፕላኑ ከሁለት በላይ የሚያርፍ ከሆነ ከዚህ ሊበልጥ አይገባም፡፡
ለ/ የሚመለከተው አካል ለአውሮፕላን ውስጥ አስተናጋጅ ሠራተኞች በረጅም በረራ ጊዜ  የማረፊያ ቦታ ይዘጋጅላቸዋል፡፡
25.4 ቤት ሆኖ መዘግየት የአውሮፕላን አስተናጋጅ ሰራተኛ አባል መቆየቱን ለ1፡4 ለቆየበት ጊዜ በዚህ መልኩ ይቆጠራል፡፡
25.5 አስፈላጊ ሪፖርት የማድረጊያ ሰዓት
25.1.1 ቤት ሆኖ የሪፖርት ሰዓት
ሀ/ ለዓለም አቀፍ በረራ ሊሆን የሚገባው ከቤት ሆኖ 1፡30 በረራው ሳይጀመር ሳይጀመር አስቀድሞ ሪፖርት መደረግ አለበት፡፡ ይህ ህግ ለአሜሪካ በረራ ጊዜም ሥራ ላይ ይውላል፡፡
ለ/ ለሃገር ውስጥ በረራ በረራው ሳይጀመር 1፡00 ሰዓት አስቀድጀሞ ሪፖርት መደረግ አለበት፡፡
ሐ/ ያልታቀደ ወይም የተለየ የበረራ አይነት ቪአይፒ ለዚህ ዓይነት በረራዎች የበረራው ሰዓት ሳይደርስ 3፡00 ሰዓት አስቀድሞ ሪፖርት መደረግ አለበት፡፡
መ/ ሪፖርት የሚደረግበት ቀን በዚህ ስምምነት አንቀጽ 25.5.1 (ሀ) እና አንቀጽ 25.5.2 መሠረት ነው፡፡
ሠ/ የዚህ አንቀጽ በሪፖርት ላይ በወር ውስጥ 80 የበረራ ሰዓቶችን አያካትትም፣ ነገር ግን ለቁጥጥር እና ለሥራ ሰዓት ቁጥጥር ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ያም የሥራ ሰዓት ገደብ የሚሰላው በዚህ ውል በአንቀጽ 25.1.3 መሠረት ነው፡፡
ሀ) ለማንኛውም በረራ የሪፖርቱ ሰዓት መቁጠር የሚጀምረው ከሪፖርቱ ሰዓት ጀምሮ ወይም 1 ሰዓት ለበረራ ከታቀደበት አስቀድሞ ነው፡፡
ለ) ነገር ግን ለአማሪካ በረራ፣ ቴላቪቭ እና ለንደን የሪፖርቲንግ ሰዓት መቁጠር ሚጀመምረው የሪፖርቱ ሰዓት ወይም የበረራው መነሻ ለታቀደው የበረራ መነሻ 2 ሰዓት አስቀድሞ ነው፡፡
25.6 ከስራ የሚወጡበት ሰዓት

 1. አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ ሰራተኞቹ ከስራ የሚወጡበት ሰዓት አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ በ30 ደቂቃ ውስጥ (በረራው ሲያበቃ)
 2. ነገር ግን በቦዪንግ 777/ቢ-777 በረራዎች ላይ የሚሰሩ አስተናጋጆች ሥራ የሚለቁበት ሰዓት ቦይንጉ ካረፈ ከ45 ደቂቃ በኋላ ነው፡፡

25.7 የሥራ ጊዜ ማራዘሚያ መነሻ የሚሆነው የስራ ሰዓት ገደብ 25.7.1 የሥራ ሰዓት ማራዘሚያ በአውሮፕላን አብራሪው ትዕዛዝ መሠረት (ፒ.አይ.ሲ)

 1. የአውሮፕላኑን አብራሪ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘ የበረራው ኦፕሬሽን በአግባቡ እንዲካሄድ ብሎ ካሰበ በአንቀጽ 25.3 በአንቀጽ 251.2.2 በተገለጸው መሠረት የሥራን ጊዜ እንዲራዘም ማድረግ ይችላል፡፡
 2. የአውሮፕላን አብራሪው የሥራ ሰዓት ማራዘሚያ ገደብ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ለአስቸኳይ ጊዜ ተብሎ የታቀደ 3 ሰዓት በላይ ሊያራዝም አይችልም፡፡
እያንዳንዱ የሚራዘም ሰዓቶች ለማራዘም በታቀደ መሠረት ሳይሆን በዛን ቅጽበት አውሮፕላን አብራሪው በገጠመው ሁኔታን መሰረት በማድረግ ነው የሚራዘመው፡፡
   1. የተጨመረ የኦፕሬሽን ሰራተኞች (2 እና ብዙ ሰራተኞች)
    1. አጠቃላይ ዝግጅት
 1. በዚህ አይነት ጊዜ ሁለት ወይም ብዙ የኦፐሬሽን ሰራተኞችን መድቦ በአንቀጽ 25.3 ሥር በተገለጸው የሥራ ሰዓት በላይ እና በስራ ሰዓት ገደብ በአንቀጽ 25.7.2.2 ከዚህ በታች እንደተብራራው ሊሆን ይችላል፡፡
 2. በሥራ ላይ የተመደበው ሃላፊ በንዑስ አንቀጽ 1 በተብራራው መሠረት ለረጅም ሰዓት በረራ እና የተለየ እና ኦፕሬሽን በሚያስፈልግበት ሰዓት መሠረት ያዛል፡፡
 3. የረጅም ሰዓት በረራ የሚያመለክተው የሃጉርን የሚያቋርጥ በረራ ነው፡፡
 4. የተመደበው ኦፕሬተር ረጅም ሰዓት በረራ ከ2 ወይም ከብዙ ቁጥር ኦፕሬተሮች ሲሰማራ የአስተናጋጆች ቁጥር በበረራ ላይ ለሚሰጠው አገልግሎት ካሉት የኦፕሬሽን ሰራተኞች በላይ መሆን አለበት፡፡ እያንዳንዱ የአስተናጋጆች አባል ለተከታታይ ሶስት ሰዓቶች ከበረራ የእረፍት ጊዜ የ2 ወይም ለብዙ ቁጥር ባላቸው ኦፕሬተሮች በሚሰማሩበት

25.7.2.2 ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ኦፕሬተሮች  የሥራ ሰዓት በማንኛውም 24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ በቁጥር ብዙ ለሆኑት  ኦፕሬተሮች የሥራ ሰዓት 19 ሰዓት ሲሆን ብዙ   ቁጥር ላላቸው ኦፕሬተር ቡድኖች ደግሞ 18 ሰዓት ነው፡፡
25.7.2.3 የብዙ ቁጥር ያላቸው ኦፕሬተሮች ሥራ ላይ የሚመደቡበት ድግግሞሽ
1. በየትኛውም ወር ውስጥ ሠራተኞቹ የአትላንቲክ ውቂያኖስ ለማቋረጥ ወይም የረጅም ሰዓት በረራ ጊዜ የሚፈለጉት ሁለቴ ብቻ ነው፡፡
2. በንዑስ አንቀጽ 1 ከተገለጸው ውጪ ሥራ ላይ የተመደበው ወደ ሰሜን አሜሪካ በረራ ሲደረግ የኦፕሬሽን ችግር የመከሰት እድሉ ብዙ ስለሚሆን በወር 3 ጊዜ ሊመድብ ይችላል፡፡
3. የአትላንቲክ ውቂያኖስ ማቋረጥ በረራ ወይም የረጅም ሰዓት በረራ ሲደረግ የያንዳንዱ ሰራተኞቹን የሥራ ተግባራት እና ያላቸውን ሙያም በእርግጠኝነት ማወቅ አለበት፡፡
25.8. በአየር ማረፊያ ውስጥ ከተጠባባቂ ሠራተኛ

 1. እያንዳንዱ የአውሮፕላን ሰራተኛ አባል በተጠባባቂነት የሚቆየው ከ4 ሰዓት በላይ መሆን የለበትም፡፡
 2. በአንቀጽ 25.3 እና በአንቀጽ 27.2.2 በተገለጻው መሠረት እያንዳንዱ የአውሮፕላኑ የኦፐሬሽን ሰራተኛ በተጠባባቂነት ሲመደብ ለየትኛውም በረራ ሊሆን ይችላል፡፡
 3. አንድ የኦረፕሬሽን ሰራተኛ ለተጠባባቂነት ተመድቦ ለ4 ተከታታይ ሰዓቶች ከቆየ በኋላ እንደገና ለሚቀጥሉት 12 ሰዓታቶች በተጠባባቂነት አይመደብም፡፡
 4. በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ተጠባባቂ ሆኖ ተመድቦ አለመጠበቅ 50 በመቶ ያስቀጣል፡፡

25.9. ቤት ሆኖ በተጠባባቂነት መመደብ

 1. እያንዳንዱ የአውሮፕላን ሰራተኛ ቤት ሆኖ በተጠባባቂነት ሲጠብቅ የትኛውም በረራ ላይ ሊመደብ ይችላል፡፡ ቤት ሆኖ በተጠባባቂነት የሚመደብ ሰራተኛ ከ6 ሰዓት በላይ መጠበቅ የለበትም፡፡
 2. በተጠባባቂነት ቤት ሆኖ የሚጠብቅ ሰራተኛ ለበረራ ከተፈለገ ከሪፖርት ሰዓት 1፡30 ደቂቃ አስቀድሞ ሊያውቅ ይገባል፡፡
 3. ቤት ሆኖ በተጠባባቂነት የተመደበ ሠራተኛ ሃላፊነቱን ካልተወጣው ቅጣቱ 25 በመቶ ነው፡፡
ቤት ሆኖ በተጠባባቂነት የሚጠብቅ ሰራተኛ 6 ሰዓት ከጠበቀ በኋላ ለሚቀጥሉት 8 ሰዓታት እንደ ተጠባባቂ ሆኖ አይመደብም፡፡

የሥራ ሰዓት

 1. ሙሉ የበረራ ሰዓት ውስጥ የሥራ ሰዓት መቅረት 100 በመቶ ያስቀጣል፡፡
 2. የሥራ ሰዓት የሚያካትተው የሥራ ሰዓት ሪፖርት ጀምሮ በረራው አልቆ ወይም አውሮፕላኑ ካረፈ እስከ 30 ደቂቃ ውስጥ ያለው የሥራ ሰዓት ነው፡፡
 3. የአውሮፕላን ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በዚህ ስምምነት አንቀጽ 25.3 እና 25.7.2.2 ስር በተገለጸው መሠረት ነው፡፡
 4. በሥራ  ላይ የተመደበው ከቁጥጥሩ ወይም ከአቅሙ ውጪ የሆነ ነገር ከገጠመው ሥራ ላይ ያለውን ሠራተኛ የሥራ ሰዓቱ እስካልበለጠ ድረስ ሰራተኞቹን መድቦ እንዲሰሩ ሊያደርግ ይችላል፡፡

25.1.1 በስብሰባ እና ስልጠናዎች
1. በሥራ ላይ የተመደበው የሰራተኞች ለሁለት የማህበር ተወካዮች ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ሰራተኞች ማህበር ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ ይፈቅዳል፡፡ ፍቃድ የሚሰጣቸው ተወካዮች የሚመደቡት ሥራ ላይ የተመደበውን ሠራተኛ ተፅዕኖ በማያደርስበት መልኩ ነው መመደብ ያለባቸው፡፡
2. የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ስልጠና ላይ ሲሳተፉ በየቀኑ የ3 ሠዓት ክፍያ ስልጠናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ይከፈላቸዋል፡፡
25.1.2 የማስታወቂያ ሥራዎች በሕጉ መሰረት የአውሮፕላን ሠራተኛ አባል ከየእለት የሥራ ተግባራት ውጪ ሌላ ሥራ ላይ መመደብ የለበትም ነገር ግን በስምምነት በማስታወቂያ ሥራዎች ላይ አስፈለጊ ሆኖ ሲገኝ ሊመደብ ይችላል፡፡ በዚህ ዓይነት የተመደበው የአውሮፕላን ሠራተኛ ተግባሩን ለ100 በመቶ ቅጣት ይዳርገዋል፡፡
25.13. የአውሮፕላን ሰራተኞች የእረፍት ጊዜ
25.13.1 የአውሮፕላን ሠራተኛ ቤቱ ሆኖ የሚኖረው የእረፍት ሰዓታቶች  ከ4 ሠዓት በረራ በላይ አለማቀፍ ወይም የአገር ውስጥ በረራ ካደረገ በኋላ ለ20 ተከታታይ ሰዓት ቤቱ ሆኖ ያርፋል፡፡ ነገር ግን ከ4 ሰዓት በታች የሚወስድ በረራ ካደረገ አውሮፕላን ሰራተኛው ለ12 ሰዓት ብቻ ያርፋል፡፡ ይህ ህግ ከቤቱ ወደ ውጪ በረራ ሲያደርግ እና ከውጪ ወደ ቤቱ በረራ ካደረገ ወይም ደርሶ መልስ ጉዞ ካደረገ በኋላ ለ20 ተካታታይ እረፍት ሰዓቶች ይኖሩታል፡፡
ለማንኛውም የአውሮፕላን ሰራተኛ ተጨማሪ የበረራ ሰዓት ያለው ጉዞ አድርጎ ሲመለስ 48 የእረፍት ሰዓቶች ይኖሩታል፡፡
25.13.2 ከቤት ወይም ከኦፕሬሽን ቦታ ርቆ ያላቸው የእረፍት ጊዜ
ማለት የተከታታይ ሳይቋረጥ ከበረራው በኋላ የአውሮፕላን ሰራተኛው ሆቴል ውስጥ ሆኖ የሚያሳልፍ ጊዜ ነው፡፡ አንደዚህ አይነት የእፍት ጊዜዎች 9፡30 ወይም የበረራውን ሰዓቶች ሁለት እጥፍ በምንም በየትኛውም መልኩ ካበረረው ሰዓት ማረፍ አለበት፡፡
25.14 ሆቴል ወይም መኝታ
ከአቅም ውጪ በሆነ ምክንያት ከተከለከለ እንጂ ሥራ ላይ ተመድቦ ለእያንዳንዱ የአውሮፕላን ሰራተኛ መንታ ያዘጋጃል፣ ምክንያታዊ የሆነ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆቴል ውስጥ መኝታቸው እንዘጋጅ ያደርጋል፡፡
25.15 በወር ውስጥ የእፍት ጊዜያቶች
25.1 በወር ውስጥ የእረፍት ጊዜዎች እና እረፍቱ የሚሰጥበት መመሪያዎች
1. በእርገጣኛነው በወር ውስጥ የእፍት ጊዜያት ማለት 7 ቀናቶች ለእያንዳንዱ የአውሮፕላን ሰራተኛ የሚሰጥ እና ያም አዲስ አበባ ሆኖ የሚያሳልፉት የእረፍት ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ሥራ ላይ ተመድቦ በተለየ ምክንያት ውጪ እረፍት ላይ ያለውን ሠራተኛ ወደ ሥራ አይመድብም
2. አንድ የአውሮፕላን ሰራተኞች አባል 3 ተከታታይ የእረፍት ቀናቶች እና ተጨቸማሪ ሌላ ሁለት ተከታታይ የእፍት እና ሌላ ተጨማሪ ሁለት የእረፍት ቀናቶች በወር ውስጥ በእርግጠኝነት አሉ፡፡ ያም በ3፡2፡2
3. በንዑስ አንቀጽ 1 ውስጥ በተገለጸው መሠረት ሥራ ላይ የተመደበው እንደ አማራጭ 3 የእረፍት ቀናቶችን፣ ሁለት ተከታታይ የእረፍት ቀናቶች አንድ የእረፍት ቀን እና ሌላም አንድ ተጨማሪ የእረፍት ቀን ማለት 3፡2፡2 መሠረት በወር ውስጥ የእረፍት ቀናቶች ይኖሩታል፡፡ ነገር ግን፣ የአውሮፕላን ሰራተኛው አባል 7 የእረፍት ቀናቶች በአንዴ ከጠየቀ ሃላፊው በተቻለ መጠን ያመቻችለታል፡፡
4. ሥራው ላይ የተመደቡ ሃላፊ የአውሮፕላን ሠራተኛ አባል የእረፍት ጊዜ በሳምንታዊ በወጣው እቅድ ውስጥ ስማቸውን አይጽፍም፡፡
5. የእረፍት ቀናቶች ውስጥ የኦፕሬሽን ሰራተኞችን በረራ ተቆጣጣሪ ክፍል ደውሎ እንዲያሳውቅ አያስገድደውም የእረፍት ቀናቶች የሚቆጠሩት የቀሩት ጊዜያቶች በዚህ ስምምነት አንቀጽ 5.13 ስር የተገለጹት ቀናቶች ግምት ውስጥ በማስገባት
6. የወርሃዊ እረፍት እቅድ የሚወጣው የወሩ መጀመሪያ ላይ
1. ሃላፊው የእረፍት ቀናቶችን ለመቀጠም ከተገደደ ከኦፕሬሽን አስፈላጊነት አንጻር የእፍት ቀናቶቹ ወደሚቀጥለው ጊዜ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ የዚህ የተራዘመ የእፍት ቀን የሚሰጠው የሚቀጥለውን እቅድ በማይነካ መልኩ ነው፡፡
2. ነገር ግን የተራዘመው የእረፍት ቀን የሚቀጥለውን የሚነካ ከሆነ ሃላፊው የተጨማሪ ሰዓት ክፍያ በሚከተለው መልኩ ይከፍላል፡፡
ሀ/ ተከታታይ የእረፍት ቀናቶች ውስጥ አንዱ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ከሆነ አራት የበረራ ሰዓት ወይም ከበረሩት ሰዓት የሚበልጥ መሆን አለበት፡፡   

ለ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ወይም ደግሞ ሌሎች የእረፍት ቀናቶች ላይ ተፅዖኖ የማያሳድር ከሆነ በቀን 4 ሰዓት የእረፍት ሰዓት ይኖራቸዋል፡፡ 

ጉዞ ላይ ሽያጭ
ሀ/ ከአንድ እና ከዛ በላይ የውጭ አገር ገንዘብ የሚሰራ የአውሮፕላን ሠራተኛ በሽያጭ ወቅት ዕቃ ቢጠፋበት እስከ 10 የአሜሪካን ዶላር ግምት ያለው ከሆነ ሠራተኛው እንዲከፍል አይደረግም በተጨማሪም የሽያጩ ዋጋ እስከ 300 የአሜሪካን ዶላር በተደጋጋሚ ክስተት በኩል በተደጋጋሚ ካልተከሰተ ነገር ግን የጠፋው እቃ ትልቅ ዋጋ የሚያወጣ ከሆነ በቅርብ አለቃው ምርመራ ይደረግበታል፡፡
ለ/ አንድ የአውሮፕላን ሰራተኛ በሃላፊነት የተሰጠውን የኩባንያ ዕቃ ለመጠበቅ ሃላፊነት አለበት፡፡ እቃው ቢጠፋ  ሃላፊነቱን የወሰደ ሰራተኛ የሚከፍል ይሆናል፡፡
ሐ/ የበረራው ተቆጣጣሪ በእያንዳንዱ በረራ ወቅት ክሬዲት ካርዶችን ማስራወሻዎችን የማሽን መቆጣጠሪያ ሊስቶችን ያዘጋጃል፡፡ የአውሮፕላን በረራ ሰራተኞች በሊስት ዝርዝር ያልተካተቱ ዕቃዎች ከአገልግሎት ውጪ የሆነ ክሬዲት ካርድ በዚህ እና በማሽን መጥፋት ምክንያት ለሚከሰተው ምክንያት የአውሮፕላን ሰራተኞች ለመክፈል አይገደዱም የዶላር መመርመሪያ በሌለበት ቦታ ላይ የአውሮፕላን ሰራተኛው እቃውን ለመሸጥ አይገደድም ነገር ግን የዶላር መመርመሪያ በሌለበት ሁኔታ ላይ የአውሮፕላን ሰራተኛ እቃዎችን በዶላር ቢሸጥ ነገር ግን ዶላሩ በኋላ ላይ ፎርጅድ ሆኖ ቢገኝ ሰራተኛው የእቃውን ዋጋ ይከፍላል፡፡
መ/ ወደ ሃገር ወይም አዲስ አበባ በሚመለስ በረራ ተቆጣጣሪው ከቀረጥ ነጻ የሆኑ እቃዎችን አውሮፕላኑ ካረፈ በ30 ደቂቃ ውስጥ ይሰበስባል፡፡ የተገዛው እቃ በፕሌኑ ካልመጣ እያንዳንዱ ሠራተኛ ለበረራ አገልግሎት ክፍል ስለ በረራው ማሳወቅ አለበት፡፡
ሠ/ ለሚጠፉት እቃዎች  የአውሮፕላን ሰራተኞች የሚከፍሉት በዛን ሰዓት ባለው የውጭ ምንዛሬ መጠን ነው፡፡ ነገር ግን የአውሮፕላን ሰራተኛው በሚከተሉት ሁኔታ ተጠያቂነት አይኖርበትም፡፡

 1. እቃው የታሸገበት ላይ ያለውን ማህተም ከተሰበረ ወይም የገንዘብ መያዣው የተፈታ ወይም የጠፋ እና እቃውም የተበላሸ ምናልባት በአውሮፕላኑ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ከተሰበረ ሰራተኛው ተጠያቂነት የለበትም፡፡

25.17 የአውሮፕላን ሰራተኛው ከቤት ውጪ በሆነበት ጊዜ ቢታመም

 1. አንድ የአውሮፕላን ሰራተኛ ለበረራ ከቤት ውጪ ሆኖ ቢታመም የሚታከምበት ሆስፒታል ወይም ዶክተር ወደ ሃገር ተመልሶ መብረር ህመሙን የሚያባብስበት ሆኖ ካገኘው ሰራተኛው ወደ ሃገር እንዲመለስ አይገደድም፡፡  
 2. ለአውሮፕላን ሰራተኛው የሚወጣው የህክምና ወጪ የሚሸፈነው በገባው የጤና ኢንሹራንስ ፖሊሲ መሠረት ነው፡፡

28.18. 1. በረራ ላይ እያለ ምግብ አንድ በረራ ላይ ያለ ሰራተኛ ደረጃውን በጠበቀ ሲ-9 ምግብ ከበረራ ሰዓት ጋር አብሮ የሚሄድ ምግብ ይሰጠዋል፡፡
2. የረራው ሃላፊ በአውሮፕላኑ ውስጥ የሚዘጋጅ ምግብ ሠራተኛው የማይበላ ከሆነ ሁኔታው በዋናው አብራሪ ከተወሰነ የበረራውሃላፊ ለሰራተኛው የሚገባውን ምግብ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡ 
25.19. በረራ ላይ ንግድ

 1. ነጠላ ንግድ

ሀ/ በረራ ላይ የሚኖረው ንግድ የአውሮፕላን ሰራተኞች የሚፈቀድላቸው ንግድ የበረራ ሃላፊ ተፅዕኖ የማያሳድርበት እና በሥራ ሰዓት እና እንደ ተጨማሪ ክፍያ ተደርጎ የሚወሰድ ከሆነ ነው፡፡
ለ/ አንድ የአውሮፕላን ሰራተኛ የንግድ ሥራ በረራ ወቅት የሚኖረው ከሆነ አስቀድሞ ለበረራው ሃላፊ ማሳወቅ እና ከበረራው ሰዓት 5 ሰዓት አስቀድሞ በስራ ሳዓት ላይ ማሳወቅ ይገባዋል፡፡

 1. ወርሃዊ ንግድ አንድ የአውሮፕላን ሠራተኛ ከሃላፊ ጋር በሚመካከር ወይም ከአስተዳደሮች ጋር በመሆን የወርሃዊ የንግድ እቅዳቸውን በወሩ መጨረሻ አንድ ቀን ከ17 ሰዓት አስቀድሞ ማሳወቅ አለበት፡፡ ይህ የወሩ የመጨረሻው ቀን የበዓል ቀናቶች ወይም ቅዳሜ እና እሁን ከሆነ የቀረበው እቅድ ወይም ጥያቄ ከአንድ ቀን አስቀድሞ መግባት አለበት፡፡

25.20. የእቅድ ማማከሪያ ሰዓት የበረራው ሃላፊ የበረራውን እቅድ ለመቀየር ከፈለገ የሚመለከታቸውን የአውሮፕላን ሰራተኞችን ከ8 ሰኣት አስቀድሞ ሊያማራቸው ይገባል፡፡
25.21. በረራ ጊዜ ያለ ሥርዓት እና መመሪያ የበረራው ሃላፊ የበረራ ፖሊሰዎች መመሪያዎችን በረራ ሰራተኞች የሚተቅም አዘጋጅቶ ለእያንዳንዱ የበረራ ሰራተኞች ያከፋፍላል፡፡
25.22. ወርሃዊ ደመወዝ እና የእቃ ክፍያዎች
ሀ/ በዚህ ስምምነት አንቀጽ 12 ስር በቀረበው ተጨማሪ የሚከተለውን ሥራ ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
ለ/ የአውሮፕላን ሰራተኞች የሚከፈላቸው በወሩ 12ኛ ቀን ላይ ይሆናል፡፡ በወር  12ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀናቶች ላይ ከዋለ ከዛ በፊት ያለው ቀን ሥራ ላይ ይውላል፡፡
መ/ ከቋሚ ደመወዝ ውጪ ለሚበሩ የበረራ ሰዓቶች ተጨማሪ ክፍያዎች ይከፈለዋል፡፡ ያም ከተመደበለት በወር ከ80 ሠዓት በረራ በላይ ከሆነ በወር ለተጨማሪ የበረራ ሰዓት ባበረረው ሰዓት መጠን ክፍያው ይከፈለዋል፡፡
ለአንድ ሰዓት የሚከፈለው ክፍያ የሚሰላው 1.5 እና ባለው ሰራተኞች የሰዓት ክፍያ ተሰልቶ የሚከፈል ይሆናል፡፡
25.23. የሚፈቀዱ የሻንጣ ብዛት አንድ የአውሮፕላን ሰራተኛ አንድ ትልቅ ሻንጣ እና አንድ በእጅ የሚጎተት ሻንጣ እንዲይዝ ይፈቀድለታል፡፡

የሻንጣዎች መጥፋት
ሀ/ የአውሮፕላን ሰራተኞች ሻንጣ በበረራ ወቅት ለጊዜው ቢጠፋ የሚከተለው ክፍያ የጠፋባቸውን አልባሳት እንዲተኩ እንዲያስችላቸው በሚከተለው መልኩ ይከፈላቸዋል፡፡

 1. የበረራው ጊዜ ለ3 ቀን የሚቆይ ከሆነ 100 የአሜሪካን ዶላር ይከፈላል፡፡
 2. የበረራው ጊዜ ከ3 ቀን በላይ የሚቆይ ከሆነ  140 የአሜሪካን ዶላር ይከፈለዋል
 3. ለሻንጣቸው ከነጭራሹ ከጠፋ የበረራው ሃላፊ  ሻንጣው ለጠፋበት ሰራተኛ በአይኤቲኤ ደንብ መሠረት አስልቶ ይከፍላቸዋል፡፡

25.25 የበዓል ቀናቶች
1. በዚህ ውል ስምምነት በተቀመጠው መሠረት እያንዳንዱ የአውሮፕላን ሰራተኛ የበዓል እረፍት ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን የሥራው ሁኔታ የሚያስገድድ ከሆነ የአውሮፕላን ሰራተኛው በበዓል ቀን እንዲበር ይመደባል፡፡
2. በበዓል ቀን ሥራ ላይ የተመደቡ ሠራተኞች ተጨማሪ ክፍያ በአዋጅ መሠረት ይከፈላቸዋል፡፡
25.26. የወሊድ ጊዜ እረፍት

 1. የአውሮፕላን ሠራተኛ አባል የሆነችዋን ሴት በወሊድ ምክንያት የዓመት ሙሉ እረፍት እንድትወስድ አትገደድም፡፡ በወሊድ ምክንያት የሚሰጠው የእረፍት ጊዜ የሚወሰነው በኢትዮጵያ የሰራተኞች ህግ በሚያስገድደው መልኩ ነው፡፡
 2. እንደ ሥራው ሁኔታ ታይቶ በወሊድ ምክንያት ለተጎዳች ሰራተኛ ተጨማሪ የሶስት ወር እረፍት ያለ ክፍያ ሊፈቀድላት ይችላል፡፡ ይህም የሆነው በሰራተኛዋ ጥያቄ ከቀረበ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የአውሮፕላን ሰራተኛው ወደ ሥራ ለመመለስ ዝግጁነቱን መጨረሽ አለበት

25.27. አስገዳጅ እረፍት ጊዜዎች

የበረራው ሃላፊ የአውሮፕላን ሠራተኛው አስገዳጅ ነገር ገጥሞታል ብሎ ካረጋገጠ ተጨማሪ የአስገዳጅ ጊዜ እረፍት እንዲፈቀድላት ሊያደርግ ይችላል ይህ የአስቸኳይ ጊዜ እረፍት የበዓል ቀናቶችን እና መሰረታዊ የእረፍት ቀናቶችን አይጨምርም፡፡

አንቀጽ ሃያ ስድስት
የአቪዬሽን ባለሙያዎች
መግቢያ
ሁሉንም ሠራተኛ ከሚያጠቃልል ደንብ እና አሰራር በተጨማሪ የሚከተሉት ደንቦች በአቪዬሽን ቴክኒክ ሰራተኞች ሥራ ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
ማብራሪያ

 1. የአቪዬሽን ባለሙያ ማለት በአውሮፕላን ጥገና ሰለጠነ ማንኛውም ባለሙያ ከታወቀ የአቪዬሽን ስልጠና እና ፍቃድ ባለው አካል ለአውሮፕላን ጥገና እውቅና አግኝቶ ወይም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ወይም በተመጣጣኝ ኢንስቲቲውሽን ሰልጥኖ በአውሮፕላን ድርጅቱ የተቀጠረ ማለት ነው፡፡ 
 2. የበረራ ባለሙያ ማለት የአቪዬሽን ሙያ ኖሮት ተገቢውን የበረራ ቴክኒካዊ ሙያ ስልጠና ወሰደ እና እውቅና ካለው የትምህርት ክፍል ፍቃድ ያለው ሊጠግን የሚችለውን የአውሮፕላን ሞዴል ተለይቶ የሚታወቅ

26.1 በአስቸኳይ ጊዜ እንዲሰሩ የሚመደቡ ሰራተኞች ለሰሩት ተጨማሪ ሥራ ተጨማሪ ክፍያዎች ይከፈላቸዋል በበረራው ሃላፊ መመሪያ ስር በተደነገገው መልኩ
26.2 የበረራ ባለሙያ
26.2.1 የሥራ ጊዜ የበረራ ባለሙያ የሥራ ጊዜ የአለማቀፍ በረራ ውስጥ እንዲሰራ ከታዘዘ ጊዜው የሚወሰነው በበረራው ሃላፊ ነው፡፡
26.2.2 የዓመታዊ እረፍት አጠቃቀም
ከላይ በተጠቀሰው አንቀጽ 26.2.1 መሠረት የተመደበው የቴክኒክ ሰራተኛ ባለው የሥራ ሁኔታ እና ሥራን ሳይጀመር አስቀድሞ ወይም ስራውን ከጨረሰ በኋላ የዓመት እረፍቱን ወስዳል፡፡
26.2.3 ስልጠናዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በረራ ላይ የተመደበ የበረራ ቴክኒክ ሰራተኛ አስፈላጊውን ስልጠናዎች ባለው የውስጥ የቴክኒክ መመሪያ መሠረት ስልጠናዎች ይሰጠዋል፡፡
26.2.4 የሚቀጥለው የበረራ ምደባ እቅድ
ሀ/ የቴክኒክ ስራውን ጊዜ የጨረሰ የቴክኒክ ሰራተኛ የሚቀጥለው የሥራ እቅድ በአንቀጽ 26.2.1 በተደነገገው መሠረት ወደ ሥራው የሚመለሰው ባለው በስራ ብቃት መሠረት ነው፡፡ ያ ማለት የሰራተኛ ብቃት መመዘኛ የሚወሰነው በተለመደው የሥራ ጊዜ ላይ የሚያሳየው ብቃት እና በበረራ ወቅት በሚያሰየው የሥራ ብቃት ሁለቱንም ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡
ለ/ ሳምንታዊ የበረራ እቅዶች ለቴክኒክ ሰራተኞች የመጣው ሁለት ቀን አስቀድሞ ሲሆን ነገር ግን በየትኛውም ሰዓት የእቅድ ለውጥ ሊመጣ ይችላል፡፡ የቴክኒክ ሰራተኛ እቅድ ለሰራተኛው የሚያውቀው በውስጥ የአውሮፕላን መመሪያ መሠረት ነው፡፡
26.2.5 የሪፖርት ሰዓት ለአንድ የአውሮፕላን ትሬክት ሰራተኛ ሪፖርት የሚያደርግበት በረራ ሳይጀመር 1፡30 አስቀድሞ አዲስ አበባ ቤቱ ሆኖ ሲሆን ከቤት ውጪ ከሆነ 2 ሰዓት ከበረራው ሰዓት አስቀድሞ ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡
26.2.6 የውሎ አበል እና የትራንስፖርት ክፍያዎች
ለቴክኒክ ሰራተኛ የትራንስፖርት ክፍያ መኝታ እና አበል የሚወሰነው በአንቀጽ 25 ስር በተመለከተው መሠረት ነው፡፡
26.2.7 የቱክኒክ ሰራተኛ የሚመደብበት ሥራ የበረራው የቴክኒክ ሰራተኛ የሚመደብበት የበረራው ዓይነት የሚወሰነው ባለው የበረራ ቴክኒክ ደረጃ ፈቃድ እና ክፍያ መሠረት ነው፡፡
26.2.8 የአውሮፕላን ውስጥ የሚመደብላቸው መቀመጫ ቦታ
አንድ የመንገደኞች የሚመደብ መቀመጫ ለበረራ ቴክኒሽያን ይመደብለታል ነገር ግን አውሮፕላኑ ካልሞላ (ክፍት ቦታ ካለ) ወደ ቢዝነስ ክፍል ይቀየርለታል ባለው የበረራ ደንብ መሠረት ለቴክኒክ ሰራተኛ የሚዘጋጅለት ምግብ በተሰጠው መቀመጫ ደረጃ መሠረት ነው፡፡
26.2.9 የመሳሪያዎች ሳጥን ወይም ቱልቦክስ የበረራው ሃላፊ ለቴክኒክ ሰራተኛው አስፈላጊ መሳሪያዎች የሚቀመጡበት ሳጥን እና ከቤት ወደ ኤርፖርት ከኤርፖርት ወደ ቤት የሚያመላልስ ትራንስፖርት ያዘጋጃል፡፡
26.2.10 የሳምንታዊ የእረፍት ጊዜዎች አንድ የቴክኒክ ሰራተኛ በሳምንት ሁለት ተከታታይ የእረፍት ቀኖች አሉት፡፡ ነገር ግን የሥራ ሁኔታ እነዚህ የእረፍት ቀናቶችን ይወስናል፡፡ የቀሩት ቀናቶች ባለው በስራ ጊዜ ውስጥ በመከፋፈል ይሆናል፡፡
26.2.11 ከበረራ በኋላ የሚኖረው የእረፍት ቀናቶች የበረራ ቴክኒክ ሰራተኛ ከበረራው ተመልሶ ወደ ቤቱ ሲሄድ በሚቀጥለው በረራ ሳይመደብ ቢያንስ 10 ሰዓት በእረፍት ማሳለፍ አለበት፡፡
26.2.12 የሥራ ጊዜ ወሰን
አንድ የበረራ የቴክኒክ ሰራተኛ በቀን ውስጥ 8 የሥራ ሰዓቶች አሉት ከሪፖርት ሰዓት ጀምሮ ከ8 በላይ ሥራ ላይ ካሳለፈ ቴክኒሽያኑ ተጨማሪ ክፍያ ይከፈለዋል፡፡
26.2.13 ጉባኤ
የበረራው ሃላፊ ለሁለት የቴክኒክ ተወካዮች አለማቀፍ የቴክኒክ ማህበር ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ የእረፍት ቀናቶች ይሰጣቸዋል፡፡ የሚሰጠውም የእረፍት ቀን የሚወሰነው ስብሰባው የሚወስደው ቀናቶች እና እዛ ስብሰባ ላይ ሄዶ ለመናገር እና ለመሳተፍ የሚፈጀው ጊዜ ግምት ውስጥ ይወሰናል፡፡ የቴክኒክ ማህበር ተወካይ ቴክኒሽያኖች የሚመረጡት በዛን ጊዜ ያለውን በረራ ተፅዕኖ በማያሳድርበት መልኩ ነው፡፡
26.2.14 የተለያዩ መመሪያዎች የሚከተሉት አንቀጾች ለአውሮፕላን ሰራተኞች አባል እና እንዲሁም ለበረራ ቴክኒክ ሰራተኛ ይመለከታል፡፡ አንቀጽ 25.16፣ 25.1.14፣ 25.1.1.15፣ 25.17፣ 25.26፡፡

ምዕራፍ 4 የሚወሰዱ ስነ ስርዓታዊ እርምጃዎች እና አይነታቸው፡፡

አንቀጽ ሃያ ስምንት
የሥነ ምግባር ጥፋትና ቅጣቶች
28.1 ማብራሪያ የስነ ምግባር እርምጃዎች ማለት የሚያስተምር እርምጃ/ ቅጣት በዚህ ውል መሰረት ሥራ ላይ የሚውል ሲሆን ማንኛውም ሠራተኛ ውሉን ይህንን ውል የሚትስ ከሆነ የሥራ ህግ እና ደንብ የሚጽፍ ከሆነ በስምምነት መሠረት የበረራ ሃላፊ እና ወይም ማህበሩ የደነገገውን ህጎች የሚትሱ ሰራተኞች ላይ የሚሰድ የማስተካከያ እርምጃ ነው፡፡
28.2 የሥነ ምግባር ማስተካከያ እርምጃዎች ያስፈለገበት ምክንያቶች
ሀ/ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች የዚህን የሥነ ምግባር እርምጃ አስፈላጊነት ላይ ተስማምቷል፡፡
ለድርጅቱ ደህንነት ምርታማነት እና ለሰራተኞችም ደህንነት ሲባል እንዲሁም የተሸለ አገልግሎት ለመስጠት እነዚህ የስነ ምግባር ማስተካከያ እርምጃዎች አስፈልገዋል፡፡ ማህበረሰቡ እና የበረራ ሃላፊ ሰራተኞችን ስነ ምግባር ጥሩ ስብዕና እንዲኖራቸው እና ጥፋቶችን እንዳይፈጽሙ ለማድረግ ከፍተኛ ሰዓት እና ትረት መድቦ ሰራተኞቹ ስለሚያስፈልገው የስራ ስነ ምግባር እንዲኖራቸው እና ጥፋት ሳይሰሩ አስቀድሞ እንዲያውቁ ለማድረግ ተስማምቷል፡፡
ለ/ የበረራው ሃላፊ ጥፋት ላይ እርምጃ የሚወስደው ለሚከተለው ምክንያት ማንኛውም የበረራ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡

 1. ሰራተኛው ካጠፋው ጥፋት እንዲማር
 2. ሌሎች ሰራተኞች ተመሳሳይ አይነት ጥፋት እንዳይፈጽሙ
 3. የሥራ አካባቢ በአንድ አንድ ጥፋቶች እንዳይበላሽ ለመቆጣጠር ወይም
 4. የተሸለ የሥራ ባህል በአካባቢው እንዲለመድ ለማድረግ

ሐ/ አስፈላጊው መረጃዎች እርምጃ ሳይወሰድ በፊት መሰብሰብ እና መመርመር አለባቸው፡፡ በተጨማሪም የሚመለከተው ሃላፊ ለትፋቱ እርምጃ ለመውሰድ ውሳኔ ላይ ሳይደርስ በፊት ጥፋት ያጠፋው ሰራተኛ የቅርብ አለቃው በጥንቃቄ ስለተፈጸመው ጥፋት ምርመራ ማካሄድ አለበት፡፡ የጥፋቱን ክብደት መወሰን አለበት፡፡ ጣፉቱን ሳያጠፋ ሰራተኛው የነበረው ሥነ ምግባር መጠናት አለበት፡፡ ያንን ጥፋትም እንዲፈጽም ምክንያት የሆነ ነገር መለየት አለበት፡፡
መ/ በተሸለ ስነ ምግባር ስራዎች እንዲሰሩ ከተፈለገ የበረራው ሃላፊ የተለያዩ የስነ ምግባር እርምጃዎችን በዚህ ውል በተጠቀሰው መሠረት የቃል ማስጠንቀቂያ ወይም ምክር ወይም የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ በማዘጋጀት ከደመወዝ በመቀነስ  ለተወሰነ ጊዜ ከስራ በማገድ እና ከስራ እስከመጨረሻ በማባረር፡፡
ሠ/ የስነ ምግባር እርምጃው የተወሰደው ያለ ምክንየት ከሆነ የተቀጣው ገንዘብ ለሰራተኛው ተመላሽ ይሆናል፡፡
28.3. የሚወሰዱ የስነ ምግባር እርምጃዎች አይነት
28.3.1 የቃል ማስጠንቀቂያ
ሀ/ የቃል ማስጠንቀቂያ ማለት በቅርብ አለቃው ወይም በዋናው ሃላፊ የሚሰጥ የቃል ማስጠንቀቂያ ሲሆን ሰራተኛው ያጠፋውን ጥፋት እንዲያውቅ እና በዚህ ውል ውስጥ በተጠቀሰው መሠረት ሰራተኛው ያጠፋውን ጥፋት እንዲያውቅ እና እንዲጠነቀቅ የሚሰጥ የቃል ማስጠንቀቂያ ነው፡፡
ለ/ አነስተኛ የስነ ምግበር ጥፋት ያጠፋ ሰራተኛ በቅርብ አለቃው የቃል ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል
ሐ/ የቅርብ አለቃው የቃል ማስጠንቀቂያው የተሰጠበትን ቀን ጥፋቱ የተፈጸመበትን ቀን፣ የጥፋቱ አይነት በዚህ ውል ስምምነት አንቀጾች ውስጥ የተደነገገውን ህጎች የሚጥስ ከሆነ፡፡
28.3.2. የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ
የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ማለት በዚህ ውል አንቀ       ጽ መሠረት የተፈጸመው ጥፋት የሚጥስ መሆኑን ተጠቅሶ ጥፋቱን ላጠፋው ሰራተኛ በቅርብ አለቃው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማለት ነው፡
28.3.3. የገንዘብ ቅጣት
ሀ/ የገንዘብ ቅጣት ማለት ጥፋቱን ካጠፋ ሰራተኛ ላይ ጥፋት ስላጠፋ ከደመወዙ ላይ የሚቀነስ በዚህ ውል ስምምነት በተጠቀሰው መጠን የሚቀነስ ነው፡፡
ለ/ የመጀመሪያ 15 የወሩ ቀናቶች ውስጥ የሚቀነሰው የቅጣት ገንዘብ መዛወር ሲሆን ከወሩ 15 ቀናቶች በኋላ የሚቀነሰው የቅጣት ገንዘብ ከሚቀጥለው የወሩ ደመወዝ ላይ ነው፡፡
28.3.4 ከስራ መታገድ
ከስራ መታገድ ማለት የሥነ ምግባር  እርምጃ ሆኖ ሰራተኛው ከስራ ላይ የሚታገድ እና በዚህ ውል ስምምነት በተጠቀሰው መሠረት የደመወዝ መታገድን ይመለከታል፡፡
28.3.5 ለምርመራ ተብሎ ከስራ ላይ መታገድ ለምርመራ ከስራ መታገድ ማለት ሰራተኛው ከስራ ላይ በዚህ ውል ስምምነት መሰረት በትልቁ ለ30 የሥራ ቀናቶች ከስራ መታገድ ማለት ነው፡፡

28.3.6 የውል መቋረጥ የሥራ ውል መቋረጥ ማለት የስነ ምግባር እርምጃ ሆኖ በዚህ ውል በአዋጅ እና በዚህ ውል መሠረት ቀጣሪው ድርጀት የቀጠረው ሰራተኛ ውል ሲያቋርጥ ማለት ነው፡፡

የስነ ምግባር እርምጃ አፈጻጸም
28.4.1 የስራውን ውል ለማቋረጥ የሚዳርግ ጥፋት ውጪ የሚመለከተው አካል ሰራተኛው በተጨማሪ ማብራሪያ I ስር በተጠቀሰው መሠረት በ10 የሥራ ቀናቶች ውስጥ እርምጃውን ያስወስዳል፡፡ ነገር ግን የጥፋቱ አይነት በጊዜ ሊታወቅ የማይችል ከሆነ ወይም ተጨማሪ ምርመራ የሚያስፈልግ ከሆነ፣ የሚመለከተው አካል ጥፋቱ መፈጸሙ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ እርምጃ ይወሰዳል፡፡
28.4.2 የቅጣት አወሳሰድ
1. ሁሉም የሚወሰዱት የስነ ምግባር እርምጃዎች ከቃል ማስጠንቀቂያው ውጪ ጥፋት ላጠፋው ሠራተኛ በጽሑፍ በአለቃው ይነገረዋል፡፡ የተፈጸመውን የጥፋት እውነታዎችን የታሰውን በውል ስምምነቱ ውስጥ የጣሰውን ህጎች መመሪያዎችን ተገልጾ እና የተወሰደውን እርምጃ ይብራራለታል፡፡ የዚህ ደብዳቤ ግልባጭ በሰራተኛው ፋይል ውስጥ ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡
2. ከስራ ላይ የመነሳት ወይም የስራ ውል ማቋረጥ እርምጃ ከተወሰደ ሃላፊው የሥራ ውል መቋረጥ ደብዳቤ ለሰራተኛው ካላዘጋጀ ወይም ሰራተኛው የውል ማቋረጥ ወይም ከስራ መታገድ የሚያሳይ ደብዳቤ ላይ መፈረም ካልፈቀደ ወይም ደብዳውን ተቀብሎ ከተሰወረ ወይም ሃላፊው የውል መቋረጥን የሚያሳይ ደብዳቤ ጥፋቱን ላጠፋ ሰራተኛ በተፈጸመው ጥፋት ምክንያት መፈጸም ካልቻለ ሰራተኛው የሚሰራበት አቅራቢያ በሚታይበት ቦታ ላይ ይህ ደብዳቤ ተለጥፎ ለ10 የስራ ተናቶች ተለጥፎ ይቆያል፡፡ የዚሁ ደብዳቤ ግልባጭ ከሰራተኛው መዝገብ ወይም ፋይል ጋራ ተያይዞ ይቀመጣል፡፡
3. ሀ/ ጥፋት ያጠፋ ወይም አጥፍቷል ተብሎ የተጠረጠረ ሰራተኛ ጥፋቱ ተጨማሪ ምርመራ የሚያስፈልገው ከሆነ ሃላፊው ካመነበት ከስራ ላይ መታገዱ ለ30 ቀናቶች የሚራዘም እና ለሰራተኛው ተገቢው የሥራ ክፍያው ይደረግለታል፡፡ ይህንን ሰራተኛ ማቆየት ምርመራውን ከማካሄድ ችግር ሊፈጥር ይችላል ብሎ ሃላፊው ካመነ ወይም ተጨማሪ ችግር ሊያስከትል ይችላል ብሎ ካመነ የውሉ መቋረጫ ወይም ከስራ የመነሳት የሚገልጽ ደብዳቤ በምክትል ፕሬዝዳንት ወይም በዋናው ሥራ አስኪያጅ መረጋገጥ አለበት፡፡
ለ/ ከስራ የታገደው ሠራተኛ ጉዳይ በሰው ሃይል ጉዳይ ክፍል በኩል ለስነ ምግባር ጉዳይ ኮሚቴ እና ወደ ማህበሩ ይተላለፋል፡፡
ይህ ኮሚቴ በስራ አስኪያጁ እና  በማህበሩ ሶስት ለሁለት ሬሾ መሰረት ተወካዮቻቸውን ይወክሉ እና ሊቀመንበር በጋራ ይመረጣል፡፡
ሐ/ የስነ ምግባር ጉዳይ ኮሚቴም የተበቀለውን ጉዳይ ሲያይ ስለ ጉዳዩ የራሱን ሃሳብ ለዋና ሥራ አስኪያጅ ይሰጣል፡፡ ጉዳዩ ከተቀበለው በኋላ ኮሚቴው በ10 ቀን ውስጥ ውሳኔ መስጠት አለበት፡፡
መ/ ኮሚቴው አስተያየቱን ለምንም አይነትት ምክንያት በሰዓቱ ለዋና ሥራ አስኪያጅ ካልሰጠ ጉዳዩ ለዋና ሥራ አስኪያጅ በቀጥታ ይላክና ውሳኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡
ሠ/ ዋና ሥራ አስኪያጁ (ሲኢኦ) የኮሚቴዎችን አስተያየት ሊያሻሽል ወይም በአጠቃላይ ሊሰርዝ እና የመሰለውን የራሱን ውሳኔ የመስጠት ስልጣን አለው፡፡
ረ/ በዚህ ድንጋጌ መሠረት በጥርጣሬ ምክንያት አንድ ሰራተኛ 30 የሥራ ቀናቶች ከስራ ሊታገድ ይችላል፡፡
4. በዚህ ውል መሰረት ከስራ እየታገደ ወይም ውሉ የተቋረጠ ሰራተኛ የመ/ቤቱን የሥራ መታወቂያ የማለፊያ ካርድ ይህ ደብዳቤ ከተቀበለ ጊዜ በኋላ ይመልሳል፡፡ በተጨማሪም ሰረሰተኛው በእጁ ያለውን መ/ቤቱን ንበረት በምንም አይነት መልኩ መጠቀም አይችልም፡፡

5. የታገደ ሰራተኛ በእገዳ ጊዜ ውስጥ ሌሎች ሰራተኖች የሚያገኙትን ጥቅማጥቅሞች አያገኝም፡፡ ነገር ግን የትኬት ጥቅም ለራሱ ትኬት የማግኘት ከትኬት ጥቅም አይታገድም፡፡ ነገር ግን የጥኬት ጥቅም የቅርብ ቤተሰብ አባሉን አይታገድም፡፡

ምዕራፍ 5 የተለያዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ ሃያ ዘጠኝ
በአተረጓጎም ወይም በአሰራር ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ አለመግባባቶች

 1. በሁለቱ ተዋዋይ መካከል የሚነሱ ማንኛውም አለመግባባት አተረጓጎም ወይም የዚህ ውል ስምምነት ሥራ ላይ ማዋል ምክንያት የሚፈቱት በመመካከር ስብሰባ እና በዩኒየን እና ሰራተኞች መከካለ በሚደረገው ውይይት መሰረት ነው፡፡
መግባባት ላይ ሁለቱ ወገኖች ካልደረሱ አለመግባባቱ በአዋጅ በተደነገገው መሠረት ይፈታል፡፡

አንቀጽ ሠላሳ
ውል ስምምነቱን መቀየር ወይም በሌላ መተካት

 1. አንድ በ9ኛው አጠቃላይ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ሊጨመርበት ወይም በሌላ ሊተካ ይችላል፡፡ በዚህ ውል ስምምነት ውስጥ
 2. ይህ ብቸኛው በማህበሩ እና በሰራተኞቹ መካከል የሚደረግ የውል ስምምነት ነው ስለዚህ ከዚህ በፊት የተደረጉት የጽሑፍ ስምምነቶች ማሻሻያ 9ኛው አጠቃላይ ስምምነት ላይ ተደርጓል፡፡ በ9ኛው አጠቃላይ ውል ውስጥ የተለያዩ መመሪያዎች ደንብ ደረጃዎች እና አሰራሮች ተካቶበታል፡፡ ባለው በአጠቃላይ የውል ስምምነት መሠረት በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ጥያቄ መሠረት ውል ስምምነቱ ሊሻሻል ሊቀየር እና ሊተካ ይችላል፡፡

አንቀጽ ሰላሳ አንድ
ልዩነት ሲፈጠር በዚህ ውል ውስጥ የእንግሊዝኛ እና የአማርኛው አገላለጽ ልዩነት ቢያመጣ የአማርኛው የመጨረሻው እና ስራ ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
አንቀጽ ሰላሳ ሁለት
የውል ስምምነቱ ቆይታ ጊዜ ይህ ውል ስምምነት ለተከታታይ 3 ዓመት የሚቆይ ሲሆን እንደ ህግ ተደርጎ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ የሚውለው እኛ ተዋዋይ ወገኖች ከላይ በተመለከተው አጠቃላይ የመመካከር የሥራ ሁኔታዎች፣ አሰራር የተለያዩ ድንጋጌዎች እናም ድንጋጌዎችን ሥራ ላይ ለማዋል ይህንን ውል ስምምነት መፈጸማችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
ተፈርሟል
ተወልደ ገ/ማርያም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ግንቦት 15/2004
ማህተም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ወንደሰን ጌታነህ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዩኒየን ሊቀመንበር ግንቦት 15/2004
ማህተም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዩኒየን
ምስክሮች
ድርጅቱን በኩል

 1. ኤልሳቤት ጌታቸው - ተፈርሟል
 2. ዋሲሁን አስረስ ተፈርሟል

በማህበሩ በኩል

 1. ምሳሌ ጌታሁን - ተፈርሟል
 2. ፍቃደ አንጮ - ተፈርሟል

ማህተም
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሰራተኞች ጉዳይ ሚኒስቴር
ተጨማሪ ማብራሪያ 1 የስነ ምግባር ጥፋቶች የእርምጃዎቹ አይነት እና አተገባበራቸው
ጠቅላላ መርሆች
ድርጅቱ  የሥነ ምግባር እርምጃ እስከ ማባረር ድረስ የሚወስደው ድርጅቱ ሰራተኛው በትክክል የሥነ ምግባር ጥፋት ማጥፋቱን በጽኑ ካመነ እና ግልጽ የሆነ ጥፋት መፈጸሙን የሚያሳይ ምክንያት ድርጅቱ ካገኘ ነው፡፡
ክፍል 1 ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ከስራ ሊያስነሱ የሚችሉ የሥነ ምግባር ጥፋቶች
ንዑስ ክፍል ሀ፡ ያለምንም ቅድመ ማስታወቂያ ከስራ ላይ ሊያግዱ የሚችሉ ጥፋቶች ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተዘረዘሩት የጥፋት አይነቶች አንድ የድርጅቱ ሠራተኛ ከፈጸመ ያለ ምንም ቅድሚያማሳወቂያ ጥፋቱን ያጠፋው ሠራተኛ ከስራ ላይ ሊያባርር ይችላል፡፡

ቁ.

 የሥነ ምግባር ጥሰት ዓይነት

1.

የተሳሳተ መረጃ/ ፎርጅድ ሃሰት መረጃ በመጠቀም እና ድርጅቱን ማጭበርበር፣ መዋሸት ወይም እንደዚህ ዓይነት ተግባራት ላይ የተሰማራ የድርጅቱ ተግባሩን ከፈጸመ በኋላ ከተደረሰበት 

2.

የድርጅቱን ሠነዶች እና መረጃዎች ሆን ብሎ መቀየር ማጥፋት መሠረዝ መቅደድ ተግባር ተከፈጸመ ድርጅቱ ተግባሩ ተግባሩ ከተፈጸመ በኋላ ሰራተኛው ይህንን ድርጊት እንደፈጸመ ከደረሰበት

3

እራን ለመጥቀም ወይም ሌላ ሶስተኛ ወገን ለመጥቀም ተብሎ ሐሰተኛ ሰነዶችን፣መረጃዎችን፣ ማስረጃዎችን፣ መታወቂያ ሃሳብ ወይም ለማታለያ የተጠቀሙትን ሰርተፊኬት ወደ ድርጅቱ ወይም ከድርጅቱ ጋር አጋር ሆኖ የሚሰሩት ድርጅቶች ማስገባት   

4.

ከቤተሰብ አባል እውቅና ከተሰጣቸው ውጪ ወይም ሌላ ሰው በድርጅቱ ህግ መሰረት ያልተካተቱ ሰዎችን ማሳለፍ የቁጥጥር ቦታዎችን እንዲያርፉ ማድረግ ወይም በነጻ ማሳለፍ ወይም የማጓጓዣ ዋጋ ማስቀነስ በተለይ በኤምፒ እና በፒኤም ስር በተደነገጉት ወይም ትራንስፖርት መጠቀም ወይም ሌላውን ሰዎች እንዲዘዋወር ማድረግ ወይም እቃዎችን ማስተላለፍ ሰራተኛው ያለውን መብቶች በመጠቀም የማጓጓዣ ክፍያ ወይም ዋጋ መቀበል ወይም እንደዚህ አይነት ክፍያዎችን ለመቀበል ሙከራ ማድረግ፡፡

5.

የድርጅቱን ተሽከርካሪ ወይም የትኛውንም አይነት ሞተር ያላቸውን መሳሪያዎችን ህጋዊ የሆነ መንጃ ፈቃድ ሳይዙ ማንቀሳቀስ ወይም መንዳት 

6

 • ድርጅቱን ሣያሳውቁ ወይም እውቅና ሳያገኙ ወይም አግባብነት በሌለው ምክንያት ከስራ ላይ 7 ተከታታይ ቀናቶችን መቅረት
 • ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት በወር ውስጥ 10 የሥራ ቀናቶችን ከስራ ላይ መጥፋት ወይም ከ30 የሥራ ቀናት ውስጥ በየትኛውም ዓመት ውስጥ ባሉ ወራት ውስጥ ከስራ ላይ መጥፋት ወይም
 • ድርጅቱ ሰራተኛው መታገዱ እና የ6 ወር የእስራት ቅጣት ወይም ከዛ በላይ ወንጀለኛ ሆኖ ከታሰረ ወይም እስር ቤት ውስጥ ለ6 ወር የሚቆይ ከሆነ ወይም ከዛ በላይ ጊዜያቶች ያለ ፍርድ ቤት ውሳኔ በየትኛውም ምክንያት የሚቆይ ከሆነ ወይም
 • ሰራተኛው በድርጅቱ ቅጥር አካባቢ ከስርቆት ምክንያት የ30 ቀን እስር ከተወሰነበት 

7

የድርጅቱን ስም ወይም ገጽታ የሚያበላሽ ከፍተኛ የሆነ አሳፋሪ ተግባራትን የድርጅቱ የሚያሳፍር ተግባር ከፈጸመ እና መፈጸሙ ከተረጋገጠ

8

የድርጅቱን መረጃ/ዳታ ወይም ጥያቄዎችን ጉቦ በመቀበል እራሱን ለመጥቀም ወይም ሶስተኛ ወገን ለመጥቀም ስኬት ማስገዛት ወይም ማስያዝ ወይም ተያያዥነት ያላቸው እና መረጃ ስራዎች ከተረጋገጠ ማጭበርበር

9

ጾታዊ ትንኮሳ ወይም ከሥራ ባልደረባ ሰዎች ላይ ጾታዊ ትንኮሳ ለመፈጸም መሞከር ወይም የድርጅቱ ደንበኛ ላይ እንደዚህ ዓይነት ተግባራትን መፈጸም በድርጅቱ የሥራ ቅጥር አካባቢ ሰራተኞች ላይ አካላዊ ጉዳት እና ለህይወት የሚያሰጋ ዛቻ መሰንዘር

10

እራስን ከመከላከል ውጪ የድርጅቱን ደንበኛ ወይም መሳሪያ ለመከላከል እርምጃ አለመውሰድ ወይም ሌሎች ሰራተኞች እንዲዘህ የመከላከያ እርምጃዎችን እንዳይወስዱ ማድረግ

 

እንቅፋት መፍጠር እና አደጋ ማድረስ

11

የድርጅቱን ሰራተኛ እንዲያምጹ ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ ወይም እንደዚህ ዓይነት ተግባራት ላይ ለመሰማራት ቡድን ማቋቋም ለግል ጥቅም ወይም ለቡድን ጥቅም ተብሎ ድርጅቱ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር በድርጅቱ እንዲህ ዓይነት ተግባር ላይ መሰማራት

12

በድርጅቱ የሥራ ቦታ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር አቤቱታዎችን ማሰራጨት ወይም መቀበል ወይም የትኛውንም ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጽሑፎች የመረጃ መረብ  እና ውስጣዊ የድርጅቱ የአይቲ ስርዓት ከድርጅቱ ፍቃድ ሳያገኙ ወይም ከድርጅቱ ህጋዊ እውቅና ከሰራተኞች ማህበር ፍቃድ ሳያገኙ በዚህ ዓይነት ተግባር ላይ መሰማራት 

13

የድርጅቱ መሳሪያዎች እቃዎች ወይም በድርጅቱ ቁጥጥር ስር ያሉትን ንብረት ያለ አግባብ በመጠቀም፣ ማበላሸት ለሙስና መጠቀም ከድርጅቱ ጋር ሰራተኛው የሥራ ግንኙነት ስላለው ብቻ መስረቀት መደበቅ ለግል ጥቅም ማዋል ወይም እንዲህ አይነት ስርቆት ተግባራት ላይ ሲሰማሩ በድርጅቱ ከታወቀ ወይም እምነትን ማጉደል ወይም የድርጅቱን እቃ የሥራ አካባቢ ለማንኛውም ህገ ወጥ ተግባር መጠቀም  

14

አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ከተረጋገጠ ወይም ድርጅቱ በቂ ምክንያት ኖሮት ያንን ሰራተኛ ከተጠራጠረ ወይም ያ ሰራተኛ ያንን ሙስና ለመቀበል ወይም ለመስጠት መንገዶችን ካመቻቸ ወይም  የትኛውም ግለሰብ ከድርጅቱ ጋር ግንኙነት ያለው ወይም በዚህ ዓይነት የሙስና ተግባራት ውስጥ የተሰማራ

15

ማንኘውም አይነት አመጽ መቀስቀስ አካላዊ ጥቃት ማድረስ እራስን ከመከላከል ውጪ

16

የድርጅቱን ንበረት ወይም የሥራ ቦታ ለህገ ወጥ ተግባራት መጠቀም ወይም ሌላ ሰው እንዲጠቀም መፍቀድ

17

የድርጅቱን ንብረት አደጋ ላይ የሚጥል መሞከር ወይም ከጥንቃቄ ጉድለት በዚህ አይነት ተግባራት ላይ መሰማራት የድርጅቱን ንብረት ወይም የድርጅቱን ሰራተኛ ለማጥቃት ወይም የድርጅቱን ደንበኛ ወይም ከድርጅቱ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ለማበላሸት ሙከራ ማድረግ

18

በጽሑፍ የተቀመጡ ማስጠንቀቂያዎችን ወይም ትዕዛዞችን መጣስ ወይም የተቀመጠውን ደረጃ ተመስርቶ አለመስራት ለሰራተኞች ደህንነት ወይም ለድርጅቱ ደህንነት ተብሎ የተደነገገውን አሰራር አለመከተል ወይም ከፍተኛ የሆነ ጥፋት ድርጅቱ ላይ ማድረስ እንዲህ አይነት ስርዓት የመጣስ ተግባር መፈጸሙን በድርጅቱ ከተረጋገጠ  

19

በድርጅቱ የሥራ አካባቢ ላይ ተቀጣጣይ እና እሳት አደጋ ሊያደርሱ ይችላሉ ተብሎ የተለየ እና ክልከላ የተደረገበት አካባቢ ላይ ሲጋራ በማጨስ፣ እሳት በማቀጣጠል ተግባር ላይ መሰማራታቸውን ድርጅቱ ካረጋገጠ

20

የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ወይም አውሮፕላኖችን ወይም የአውሮፕላን መሳሪያዎችን ወይም ማሽነሪዎችን ካለ በቂ ስልጠና እና ልምድ ወይም አስቀድሞ የሚመለከተውን ባለስልጣን ሳያሳውቁ መጠቀም ወይም ሌላ ሰው እንዲጠቀም መፍቀድ

21

ያልተፈቀደ እና እውቅና ያላቸው ጥቅም ወይም የትኛውም ጥቅም እሱ በውስጡ ያለውን ነገር ሰራተኛው ሳያውቅ ሲያንቀሳቅስ መገኘት

22

ከድርጅቱ ባለስልጣን እውቅና ውጪ ህገ ወጥ የሆነ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት

23

በድርጅቱ ህግ የተከለከለ አነቃቂ እፆች እና የአእምሮን ችሎታ የሚያስተጓጉል ወይም እንዲህ አይነት እፅ ይዞ በድርጅቶ የሥራ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት 

24

በድርጅቱ የሥራ አካባቢ ላይ ሰክሮ መገኘት

25

ከድርጅቱ ስራ እና ጥቅም ውጪ ለግል ጥቅም የሌላ ሰራተኞችን ፓስፖርት ሲጠቀሙ መያዝ

26

በስራ ላይ ማጭበርበር ወይም ሲያጭበረብሩ ወይም አግባብ ያለው ምርመራ ተደርጎ የማታለል ወንጀል ላይ ተሰማርቶ መገኘት 

27

የድርጅቱን ሥራ እንዲጓተት በማድረግ ዓመታዊ ውጤቱን መቀነስ ከሰራተኞች ጉዳይ ጋር በማያያዝ ወይም አለመግባባቶች ጋር በማያያዝ የድርጅቱን ውጤት ዓመታዊ ምርት እንዲቀንስ ማድረግ

28

ነፃ ትኬት ወይም ቅናሽ ትኬት ለግል ጥቅም ወይ 3ኛ ሰው ለመጥቀም ተብሎ የድርጅቱን ዓለማወፋዊ ድንጋጌን በሚጥስ መልኩ ሐሰተኛ ሰነዶችን ወይም ማስረጃዎችን ማቅረብ

29

ቅናሽ ያለው ትኬት ወይም ነጻ ትኬትን በመጠቀም የኢትዮጵያን ህግ ወይም የሌላን ሃገር ሰራተኛን ህግ ወይም ቤተሰብ መጣስ

30

ከውል ስምምነቱ ላይ ከተቀመጡት የሥነ ምግባር ጥሰት በተጨማሪ ሌሎች ስ ምግባር ጥሰት ከስራ ሊያስባርሩ የሚችሉትን የወንጀል ድርጊት በአዋጁ እደተደነገገው መፈጸም

ንዑስ ክፍል ለ፡ ለሁለተኛ ጊዜ ከተፈጸመ ከስራ ሊያስባርር የሚችል የስነ ምግባር ጥሰት     

ቁጥር

የጥፋት አይነት

ለመጀመሪያ ቅጣት ምላሽ

1

ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ጥቅምን የሚጎዳ ወይም ተፃፃሪ የሚሆን ተግባር ወይም ከጥቅም ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ግጭቶች የሚፈጥሩ ነገር ግን ለግል ወይም ሦስተኛ ወገን ለመጥቀም የሚሰራ

ሥራን ለማቁረጥ የመጨረሻ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ

2

በሐኪም የተሰጠውን የሕክምና እረፍት ቀናትን ለራስ የግል ጉዳይ ያለአግባብ ማዋል፡፡

ለ15 ቀናት ከሥራ ስንብት

3

ያለ ተጨባጭ ምክንያት ከአንደ የሥራ ቦታ ወደ ሌላ ሥራ ቦታ መዘዋወርን እምቢ ማለት

ለ10 ቀናት ከሥራ ስንብት

4

አግባብነት የሌለውን ሰው ወይም ያልተፈቀደለትን ወደ ግቢው ወይም ሥራው ወደ ሚከናወንበት ሕንፃ ጥበቃው ወደ ተመደደበበት እንዲገባ ማድርግ (ጥፋቱ ከተረጋገጠ)

ለ10 ቀናት ከሥራ ስንብት

ንዑስ ክፍለ ሐ. ለሦስኛ ጊዜ ወደ ውል መቋረጥ የሚያደርሱ ጥፋቶች

ቁጥር

የጥፋት አይነት

1ኛ ቅጣት

2ኛ ቅጣት

1

ቁማር ወይም በኮምፒዩተር የገንዘብ ጨዋታ ወይም በሥራ ሰአት በማንኛውም መልኩ በንብረት ላይ የሚፈፀም ድርጊት

5ቀናት ያለ ክፍያ

10 ያለ ክፍያ

2

ለሠራተኛ እና በደረጃው ላሉት የጥበቃ ደህንነት መሳሪያዎች እና መመሪያዎች ተገዢ አለመሆን
ሀ. ጉዳት ሳያደርሱ
ለ. ጉዳት በማድረስ

5ቀናት ከሥራ መሰናበት  

20 ቀናት ከሥራ መሰናበት 

3

ሌሎች የራሱ፣ የቤተሰብ አባል ወይም የሌሎች ሠራተኞች መለያ ካርድ ወይም ሌሎችን የኩባንያውን አርማ እንዲጠቀም መፍቀድ
ሀ. ጉዳት ሳያደርሱ
ለ. ጉዳት በማድረስ

5ቀናት ከሥራ መሰናበት  

10 ቀናት ከሥራ መሰናበት

4

የምግብ ሠራተኞች የንፅህና መመሪያዎችን መጣስ

5 ቀናት ያለ ክፍያ

05 ቀናት ከሥራ መሰናበት

5

ሚስጥራዊ የሆኑ የስልክ ንግግሮችን ማጋለጥ ወይም ሚስጥራዊ የሆኑ ፖስታዎችን ወይም ሰነዶችን ወይም ንግግሮችን መክፈት  ወይም ተግባራትን ማጋለጥ ወይም ጉዞን ወይም ሌሎች ሚስጥራትን ለ3ኛ ወገን ወይም ስልጣን ለሌለው አካል ማሳወቅ

5 ቀናት ያለ ክፍያ

10 ቀናት ከሥራ መሰናበት፣

6

በአልኮል ተፅኖ ሥር በመሆን ሥራ ላይ መገኘት

5 ቀናት የሥራ ስንብት

15 ቀናት የሥራ ስንብት

7

የራስን ወይም የሌላ ሠራተኛን የጊዜ ካርድ ማስባጠር

15 ቀናት የሥራ ስንብት

30 ቀናት የሥራ ስንብት

8

ለሥራ አገልግሎት የተበረከተውን የደንነት መሳሪያዎችን፣ ኢኩፒመንት ወይም የኩባንያውን የደንብ ልብስ መሸጥ ወይም ለሌላ 3ኛ አካል ማስተላለፍ

10 ቀናት የሥራ ስንብት

20 ቀናት የሥራ ስንብት

9

ለተሳፋሪ ወይም ለደንበኛ ተገዢ አለመሆን አና አስፈላጊውን ክብር በማንኛውም መልኩ ያለመስጠት ወይም አግባብነት ማጣት

10 ቀናት የሥራ ስንብት

15 ቀናት የሥራ ስንብት

ንዑስ ክፍለ መ. በሦስኛ ደረጃ ላይ ወደ ውል መቋረጥ የሚያደርሱ ጥፋቶች

ቈጥር

የጥፋት አይነት

1ኛ ቅጣት

2ኛ ቅጣት

3ኛ ቅጣት

1

የጊዜ መቆጣጠሪያ ካርድ ወይም የቅፅ ወይም የቁጥጥር ቅፅ፣ ማሽን ወይም ሥራውን ለማስፈፀም የሚረዳውን ሥርአት በአግባቡ አለመጠቀም

የቃል ማስጠንቀቂያ (የቅርብ አለቃው ሠራተኛው መኖሩን ካለ አረጋገጠ)

የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ

የአንድ ቀን የክፍያ ቅጣት

2

በሠራተኛ ተግበራዊ ሊሆኑ የሚገቡትን ተጨባጭ ትእዛዞችን፣ የጽሁፍ ወይም የቃል መመሪያዎችን ወይም የተለመዱ ሥራዎችን አለመፈፀም

የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ

የ2 ቀናት የክፍያ ቅጣት

የ5 ቀናት የክፍያ ቅጣት

3

ያለ የቅርብ አለቃ ፈቃድ ሥራው መሠራት እያለበት የሥራውን ቦታ በመተው መሄድ
ሀ. ለጥበቃ ኃላፊዎች

 1. ጉዳት ሳያስከትል
 2. ጉዳት በማስከተል

ለ. ለሌሎች ሠራተኞች

10 ቀናት የክፍያ ቅጣት
የሥራ ማቁረጥ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

15 ቀናት ክፍያ
15 ቀናት ክፍያ
የ2 ቀናት ክፍያ

20 ቀናት ክፍያ
20 ቀናት ክፍያ
የ3 ቀናት ክፍያ

4

በማፈለገው ዘዴ እና ደረጃ መሠረት በሚገባና በተፈለገው ደረጃ የተሰጠውን ሥራ አለማከናወን

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

የ3 ቀናት ክፍያ

የ5 ቀናት ክፍያ

5

የሥራ ቦታን ማቆሻሽ ወይም ባልተፈቀደ ሥፍራ መብላት

የቃል ማስጠንቀቂያ

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

የ2 ቀናት ክፍያ

6

የማስጠንቀቂያ ደብዳቤን ለመቀበል ወይም በተወሰነው ውሳኔ ላይ ለመፈረም እና የመጨረሻውን የተጠናቀቀውን የአፈፃፀም ምዘና ጽሁፍ ወይም ኬኢአይ (ከመጨረሻ ውሳኔ በኃላ) አለመቀበል

የ1 ቀን ክፍያ

የ2 ቀን ክፍያ

የ3 ቀን ክፍያ

7

በሥራ ቦታ እያሉ በጥበቃ ወይም በሌሎች ሕጋዊ አካላት ለመፈተሽ ፍቃደኛ አለመሆን 

የ1 ቀን ክፍያ

የ2 ቀን ክፍያ

የ3 ቀን ክፍያ

8

ማለፍ ክልክል ነው ወይም ክልክል ወደ ሆኑ ቦታዎች መግባት

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

2 የቀናት ክፍያ

የ3 ቀናት ክፍያ

9

በቅጥር ግቢ ውስጥ ጥል ወይም ሁከትን መፍጠር እና ነገር ግን ለዚህ አይነት ድርጊት ተጠያቂ መሆን

የ2 የቀናት ክፍያ

የ3 ቀናት ክፍያ

የ5 ቀናት ክፍያ

10

በቅጥር ግቢ ውስጥ አግባብ ያለሆነ ወይም የኩባንያውን የደንነት ልብስ ለብሰው ከቅጥር ግቢ ውጭ  የሥነ ምግባር ግድፈት መፈፀም

የ2 የቀናት ክፍያ

የ3 ቀናት ክፍያ

የ4 ቀናት ክፍያ

11

ከሚፈፀመው ሥራ ውጭ በቸልተኝነት የኩባንያውን ማሽኖች፣ የሞተር መሳሪያዎች እና ሌሎች ንብረቶችን፣ ከደረጃዎች እና መመሪያዎች ውጭ መጠቀም

የ2 የቀናት ክፍያ

የ3 ቀናት ክፍያ

የ4 ቀናት ክፍያ

12

በሥራ ቦታ የሚፈፀመውን ስህተት ለቅርብ አለቃ በአስቸኳይ ሪፖርት አለማድረግ
ሀ. ጉዳትን ሳያስከተል
ለ. ጉዳት በማስከተል

የ3 የቀናት ክፍያ

የ4 ቀናት ክፍያ

የ5 ቀናት ክፍያ

13

በሠራተኛ ወይም በንብረት ላይ ያለውን ጉዳት ሪፖርት አለማድረግ
ሀ. ጉዳትን ሳያስከተል
ለ. ጉዳት በማስከተል

የ3 የቀናት ክፍያ

የ4 ቀናት ክፍያ

የ5 ቀናት ክፍያ

14

ያለ ቅድመ ፈቃድ በማስታቂያ ሰሌዳ ላይ ማስታወቂያ መለጠፍ

የ3 የቀናት ክፍያ

የ5 ቀናት ክፍያ

የ10 ቀናት ክፍያ

15

በአሰሪ ወይም በአለቃ የሚሰጠውን የተፃፈ ወይም ግልፅ ቃል መመሪያዎችን አለማክበር

የ2 የቀናት ክፍያ

የ5 ቀናት ክፍያ

የ7 ቀናት ክፍያ

16

የደንበኛውን ንብረት ያለአግባብ አለመያዝ
ሀ. ጉዳትን ሳያስከተል
ለ. ጉዳት በማስከተል

የ3 የቀናት ክፍያ
የ30 ቀናት መቋረጥ

የ10 ቀናት መቋረጠ

የ15 ቀናት መቋረጥ

17

በሥራ ሰት መተኛት
ሀ. ለደንነት ኃላፊዎች
ለ. ለሌሎች ሠራተኞች

የ5 የቀናት ክፍያ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

የ10 ቀናት መቋረጠ

የ20 ቀናት መቋረጥ

18

እውነት የሆነውን አውንታዊ መረጃን መካድ እና ወደ ስህተት አፈፃፀም የሚመራ
ሀ. ጉዳትን ሳያስከተል
ለ. ጉዳት በማስከተል

የ5 የቀናት የሥራ መቋረጥ 

የ10 ቀናት የሥራ መቋረጥ

የ20 ቀናት የሥራ መቋረጥ

19

የድርጅቱን የግል ማህደሮች፣ በኮምፒተር ላይ ያለን መረጃ ወይም በቸልተኝነት አለመመዝገብ ወይም ማስቀረት ወይም ያለውን ተጨባጭ እውነት ወይም መረጃ ክስተት ወይም ተግባራትን በሀሰት መያዝ፣ እውነት ወይም ሰነዶችን ማስወገድ፣ ማጥፋት፣ መውሰድ፣ ግልባጭ ማድረግ፣ መለወጥ፣ ይዘቱን መቀየር፣ መሰረዝ፣ ማውደም
ሀ. ጉዳትን ሳያስከተል
ለ. ጉዳት በማስከተል

 

የ5 ቀን የስራ ክፍያ  መቋረጥ

 

የ10 ቀን መታገድ

 

የ20 ቀናት መታገድ

20

በተመደቡበት ሃላፊነት ላይ ቸልተኝነት፣ ይህም በንብረት ወይም በህይዎት ላይ አወንታዊ ተፅኖ ማሳደር ወይም ላልተገበ ወጭ ማዳረግ
ሀ. ጉዳትን ሳያስከተል
ለ. ጉዳት በማስከተል

10 ቀን ከስራ መቋረጥ እና መታገድ

20 ቀን መታገድ

30 ቀን መታገድ

21

አግባብነት በሌለው በኮምፒውተር የታገዘ ሃብት እና በሌሎች የኤሌክትሪክ ሰማሪያዎች በመታገዝ የድርጅቱን ንብረት ለሌብነት ወይም ለማጭበርበር ተግባር፣ ይዘቱን መቀየር፣ ማውደም ወይም ማጥፋት ወይም መረጃውን ለመጠቀም መሞከር፣ የድርጅቱን የኮምፒውተር ኔትዎርክ በሚጎዳ መልኩ የኮምፒተርን መዋቅር መቀየር ወይም ሌላ እኩይ የስነምግባር  ተግባር መፈፀም
ሀ. ጉዳትን ሳያስከተል
ለ. ጉዳት በማስከተል

10 ቀን ከስራ መቋረጥ እና መታገድ

20 ቀን መታገድ

30 ቀን መታገድ

22

በስራ ላይ ትብብር እና መልካም የስራ አካባቢን የሚስተጓጉል ተግባር መፈፀም
ሀ. ጉዳትን ሳያስከተል
ለ. ጉዳት በማስከተል

3 ቀን የስራ ክፍያ መቋረጥ

የ5 ቀን ክፍያ

የ10 ቀን ክፍያ

23

በስራ ሰዓት ያለፈቃድ ከተሰተው ሃላፊነት ጋር የማይገናኝ ስራን ወይም አገልግሎትን ማከናወን

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

የ3 ቀን ክፍያ

የ5 ቀን ክፍያ

24

ስራውን ማከናወን እያለበት እንደሰራተኛ የተሰጠውን ሃላፊነት አለመወጣት

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

የ5 ቀን ክፍያ

የ10 ቀን ክፍያ

ንዑስ ክፍል ሠ፡ በጠቅላላ ስምምነት ያልተካተቱ ከባድ ጥፋቶች በመፈፀሙበት ጊዜ፣ የሚመለከተው በውይይቱ በተደረሰ ውሳኔ መሰረት ከጊዜ ወደ ጊዜ በፈፃሚው እና በሕብረቱ በሚደረገው ውይይቶች መሰረት እንደ ጉዳዩ ክብደት እርምጃ መውሰድ፡፡
ክፍል 2- ሪፖርት አለማድረግ ወይም ስህተት ተነሳ የሚወሰዱ የስነምግባር እርምጃ
ንዑስ ክፍል ሀ፡- ያለምክንያት መቅረት

 1. ሰራተኛው ያለበቂ ምክንያት በ1 ወር ውስጥ በአጠቃላይ 10 ቀን ወይም ከዚያ በላይ ለቀረ የሚከተለው የስነምግባር እርምጃ ይወሰደል፡፡

ቁጥር

ጥፋት

1ኛ ቅጣት

2ኛ ቅጣት

3ኛ ቅጣት

4ኛ ቅጣት

1

ከግማሽ እስከ 1 ቀን ከስራ መቅረት

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

1 ቀን ክፍያ

3 ቀን ክፍያ

5 ቀን ክፍያ

2

ከ2 እስከ 3 ተከታታይ የስራ ቀናት መቅረት

2 ቀን ክፍያ

3 ቀን ክፍያ

5 ቀን ክፍያ

10 ቀን ክፍያ

3

ከ4 እስከ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት መቅረት

5 ቀን ክፍያ

10 ቀን ክፍያ

15 ቀን ክፍያ

20 ቀን ክፍያ

 1. ተመሳሳይ ጥፋት ፈፅመው ከ4 ወራ በኋላ ከስራ የመቅረት ጥፋት የመጀመሪያ ጥፋት ሲባል፡፡ በንዑስ ክፍል ሀ፣ አይነት 1 እና 2 በ4 ወራት ውሰስጥ ከ4 ጊዜ በላይ ከቀረ ሰራተኛው በዓመት በጠቅላላ 30 የስራ ቀናት መቅረት ካልቀረ እንደሚከተለ፣ው ሚታይ ይሆናል፡፡

ቁጥር

ጥፋት

1ኛ ቅጣት

2ኛ ቅጣት

3ኛ ቅጣት

4ኛ ቅጣት

1

ያለበቂ ምክንያት በ4 ወራት ውስጥ ከአራት ጊዜ በላይ ከግማሽ እስከ 2 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከስራ መቅረት

በ7 ቀናት መታገድ

ለ10 ቀናት መታገድ

ለ15 ቀናት መታገድ

2 ቀናት መታገድ (ሰራተኛው 12 ወራት ውስጥ ለ30 ቀናት ከስራ ይቋረጣል)

2

ያለበቂ ምክንያት በ4 ወራት ውስጥ ከ4 ጊዜ በላይ ከግማሽ እስከ 7 ያላነሱ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከስራ መቅረት

ለ10 ቀናት መታገድ

ለ15 ቀናት መታገድ

ለ25 ቀናት መታገድ

ለ30

ንዑስ ክፍለ ለ፡ ያለበቂ ምክንያት የተካተቱ ሪፓርት ጉዳዮች
ሰራተኛው ወደ ስራ ለመድረስ በትራንስፖርት ምክንያት በማርፈድ በአስቸኳይ ሪፖርት ካላደረገ እና ይህም ከተረጋገጠ፣ ሪፖርቱን አአርፋ ሪፖርት ካደረገ ሰራተኛው በሚከተሉት የስነምግባር እርምጃ ይወስድበታል፡-

ቁጥር

ጥፋት

1ኛ ቅጣት

2ኛ ቅጣት

3ኛ ቅጣት

1

እስከ 15 ደቂቃዎች

የቃል ማስጠንቀቂያ

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

የ1 ቀን ክፍያ

2

ከ15 ደቂቃዎች በላይ ማርፈድ

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

በተቃጠሉ ሰአታት የስራ ደመወዝ ክፍያ

የ1 ቀን ክፍያ

ንዑስ ክፍል ሐ፡ በተደጋጋሚ ለያለበቂ ምክንያት በመጓተት ሪፖርት ማድረግ

ተመሳሳይ ጥፋት ፈፅመው ከ3 ወራት በኋላ ከላይ በንዑ ክፍል ለ ስር የተዘረዘሩት ጥፋት ከተፈፀሙ፣ የመጀመሪያ ጥፋት ይባላል፡፡ ነገር ግን ሰራተኛው ከ3 ጊዜ በላይ በተሰጠው በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ የሚከተሉት እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡

ቁጥር

ጥፋት

1ኛ ቅጣት

2ኛ ቅጣት

3ኛ ቅጣት

1

በ3 ወራት ውስጥ ከ3 ጊዜ በላይ መጓተት

የ2 ቀናት ክፍያ

የ3 ቀናት ክፍያ

የ5 ቀናት ክፍያ

ማስታወሻ፡
ሀ. ሰራተኛው በበቂ ምክንያት ከስራ ከቀረ፣ ደመወዙ ለቀረበት ሰዓት/ቀን ብቻ የሚቀነስ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አስፈ ላጊነቱ በአለቃው ከተረጋገጠ የተቃጠለውን በስራ እንዲያካክስ ይፈቅዳል፡፡
ለ. ሰራጠኛው የቀረበት ምክንያት ካልተረጋገጠ፣ ደመወዙን በተጨማሪ ክፍያ አይከፍል፡፡
ክፍል 3 በካቢን ክሪው አባላት እና የበረራ ቴክንሺን ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ተጨማሪ የስነምግባር እርምጃ

የሚከተሉት ድንጋጌዎች በክሪው አባላት እና የበረራ ቴክኒሺያን ላይ ብቻ ተፈፃሚ ይሆና ል፡፡ በዚህ ክፍል ያልተሸፈኑ ጥፋቶች በማጣቀሻ 1፣ ክፍል ሀ፣ ለ እና ሐ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ሚታይ ይሆናል፡፡

ቁጥር

ጥፋት

1ኛ ቅጣት

2ኛ ቅጣት

3ኛ ቅጣት

1

ከ15 እስከ 30 ደቂቃዎች በማርፈድ የበረራውን ጊዜ የማይጎዳ

የቃል ማስጠንቀቂያ

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

የ1 ቀን ክፍያ

2

ከ30 ደቂቃዎች በላይ  በማርፈድ የበረራውን ጊዜ የማይጎዳ

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

1 ቀን ክፍያ

2 ቀን ክፍያ

3

በመጓተት ከ5 እስከ 15 ደቂቃዎች በረራውን ማዘግየት

1ቀን ክፍያ

2 ቀን ክፍያ

3 ቀን ክፍያ

4

በመጓተት ከ16 እስከ 30 ደቂቃዎች በረራውን ማዘግየት

2 ቀን ክፍያ

3 ቀን ክፍያ

4 ቀን ክፍያ

5

ከ30 ደቂቃዎች በላይ በረራውን ማዘግየት

3 ቀን ክፍያ

4 ቀን ክፍያ

10 ቀን ክፍያ

6

በኩባንያው ላይ የሚጎዳ ተግባር መፈፀም ነገር ግን ከባድ ጉገዳት የማያስከትል

3 ቀን ክፍያ መቋረጥ

5 ቀን ክፍያ

10 ቀን ክፍያ

7

ጊዜውን የጠበቀ በረራ አለማድረግ

4 ቀን ክፍያ

10 ቀን ክፍያ

15 ቀን ክፍያ

8

በስራ ላይ እያሉ መተኛት

5 ቀን ክፍያ

10 ቀን ክፍያ

መቋረጥ

9

ያለበቂ ምክንያት ጊዜውን ለየጠበቀ በረራ አለማድረግ

15 ቀን መታገድ

መቋረጥ

 

10

ከበረራው በፊት ከ12 ሰዓታት በረራ አልኮል መውሰድ ከታወቀ

ለ20 ቀን መታገድ

30 ቀን መታገድ

መቋረጥ

11

በበረራው ላይ እያለ አልኮል ከወሰደ

መቋረጥ

 

 

ክፍል4- የወሰን ጊዜ እና ጥፋትን በተደጋጋሚ ማከናወን

ሰራተኛው በማጣቀሻ 1፣ ክፍፍል 1፣ ንዑስ ክፍል ለ፣ ሐ እና መ የተዘረዘሩትን ተግባራት ፈጽሞ የስነምግባር እርምጃ ተወስዶበት ከታች የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ ተመሳሳይ ተግባር ቢፈጽም የሚከተሉት እንደ የመጀመሪያ ቅጣት ይታያሉ፡፡

ቁጥር

የጥፋት ዓይነት

የወሰን ጊዜ

1

ማጣቀሻ 1፣ ክፍል 1፣ ንዑስ ክፍል (ለ) በጠቅላላ

1 ዓመት

2

ማጣቀሻ 1፣ ክፍል 1፣ ንዑስ ክፍል (ሐ) በጠቅላላ

9 ወራት

3

ማጣቀሻ 1፣ ክፍል 1፣ ንዑስ ክፍል (መ) በጠቅላላ

6 ወራት

 1. በማጣቀሻ 1፣ ክፍል 1 እና 3 ስር የተዘረዘሩት ተደጋጋሚ ጥፋቶችን መፈፀም፡፡

በማጣቀሻ 1 እና ፣ ክፍል 1 ንዑስ ክፍል (ለ) ለሁለተኛ ጊዜ ሰራተኛው ከፈፀመ ወይም በንዑ ክፍል (ሐ) ለሦስተኛ ጊዜ ወይም በንዑስ ክፍል (መ) እና ክፍል 3 ስር ከላይ የተዘረዘሩትን ጥፋቶች ለ4ኛ ጊዜ ከፈፀመ ከስራ ሚሰነበት ይሆናል፡፡  
ክፍል 5፡ የመታገድ ጊዜ ቆጠራ
ሀ. የመታገድ ጊዜ የሚቆጠረው በስራ ቀናት ነው፡፡
ለ. ማኝኛውም የታገደ ሰራተኛ የመታገድ ጊዜ ካበቃ በኋላ በቀጣዩ ቀን ለስራ የሚያመለክት ይሆናል፡፡
ክፍል 6 የስነምግባር ቅጣቶችን መፍታት

 1. በማጣቀሻ 1 ስር የተካተቱ የስነምግባር እርምጃዎች ከፍተኛ ቅጣት ነው፡፡ ነገር ግን አነስተኛ የስነምግባር እርምጃ በአለቃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡ ይህም ለመልካም እና ተጨባጭ ምክንያት ነው፡፡
 2. በዚህ የአፈፃፀም ጊዜ ውስጥ፣ ሰራተኛው ባለፉት ጊዜ ውስጥ ለፈፀመው የጥፋት ተግባር ያለውን መሻሻል የሚገልፅ ደብዳቤ ያቀርባል፡፡ መሻሻሉ የተፈፀመለት ሰራተኛ በፊት የፈፀመው ጥፋት በቀጣይ የእድገት ውድድር ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም፡፡

ማጣቀሻ 2 የክፍያ ደረጃ (የህክምና እርዳታ ዳሰሳ)
ሀ. የህክምና መድህን ከታች ከተገለፁት የማይካተቱት ጋር መከናወን የሚቀጥለው በሰንጡት የህክምና ባለሙያዎች በወቅቱ ከተገለፀ ነው፡፡
የማይካተቱ
በዚህ ክፍል ስር ጥቅም የማይካፈሉበት ሁኔታዎች፡-
ሀ. የመስማት እርዳታ ወይም የአስሞቲክ ሰርጀሪ ወይም ሰው ሰራሽ የአይን መነፀር ማግኘት፣ በውል በአንቀጽ 11.4.3 የተካተተውን ሳይጨምር
ለ. በማንኛውም አደጋ ወይም በወረራ ወይም በመከላከያ፣ የባህር ወይም የአየር ሃይል አገልግሎት ውስጥ በሚካተቱበት ጊዘጄ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የሚከሰት ጉዳይ ወይም አካላዊ ጉድለት
ሐ. አባላት ከማንኛውም አይነት መድህን ወይም ከዚህ መድህን ከሚገኘው ተቸማሪ ወጪ ለአባላት ሚከፈል ማንኛውም ወጪዎች፡፡
መ. ከህክምና ጋር ተያይዞ ጰየሚመጣ ወጪዎች ነገር ግን በመድህን ገቢው መመሪያ መሰረት ያልተከናወነ፡፡ ነገርግን ቸይህ ዓይነቱ ወጪዎች በዓመት በዓል ቀን ወይም ከቢሮ ሰዓት በኋላ ከተከሰተ ከዚህ ጋር ተያይዞ በህክምና ባለሙያ የሚከናወን ህክምና በኩባንያ ሚቀርብ ሆኖ፣ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡
ሠ. መድህን ገቢው ከኢትዮጵያ ክልል ወጪ ሆኖ ለሚከሰት የትኛውም ድንገተኛ፣ ክስተት፣ ነገር ግን ወሰኑ የሚከተለኩትን አያካትትም

 1. በበዓል ወይም በስራ ለጊዜው ውጪ ሀገር የሆነ መድህን ገቢ ሰው
 2.  በህክምና ምክንያት ውጪ ሀገር ሄደ መድህን ገቢ ሰው ይህም በህክምና ቦሀርድ ተረጋግጦ እና በጤና ሚኒስቴር ከፀደቀ ነው፡፡

ማጣቀሻ 3 ከጠቅላላው ስምምነት የማይካተቱ ገደቦች
የሃላፊነት መጠሪ

 1. ሲ.ኢ.ኦ
 2. ሲኦኦ፣ ሲኤፍኦ፣ ሲሲኦ፣ ሁሉም ኤስቪፒ እና ቪፒ፣ ጠቅላላ ምክር ረዳት ጠቅላላ ምክር፣ ሲአይኦ፣ ዋና የአይቲ ደህንነት ሃላፊ እና ሌሎች አቻ ሃላፊነቶች፡፡
 3. የስነምግባር ጉዳይ ማስፈፀሚያ ዩኒት ሃላፊ
 4. ዳይሬክተሮች ሁሉ
 5. ስራ አስኪያጆች እና ፕሮጀክት ስራ አስኪያጆች ሁሉ
 6. ስራ አስያጆች/ስቴሽን/ የሽያጭ ትራፊክ ስራ አስኪያጆች ሁሉ
 7. አለቶች/ፎርማን ሁሉ
 8. የመርከብ ካፒቴን/ዋና ፓይለት
 9. ዋና ኃላፊ
 10. የድርጅት ኃላፊ
 11. የበረራ ዋ ኢነስትራክተር
 12. ዋና የቴክኒካ ግራውንድ ኢንስትራክተር
 13. ዋና የቴክኒካል ኢንስትራክተር
 14. የላይበራሪ ሃላፊ
 15. የጋሊቢም ኢትጵያ ሃላፊ
 16. የአስተዳደር እና ፋይናንስ ሃላፊ
 17. ሜዲካል ዶክተር
 18. የኢንተርፕራይዝ ሃብት ማኔጅመንት ዋ/ፕ/ስ/አስኪያጅ
 19. ም/ፕ/ስ/አስኪያጅ
 20. አካዳሚክ ሃላፊ
 21. የአስተዳደር እና አገልግሎት ሃላፊ
 22. ሰው ሃብት ልልማት ስልጠና ሃላፊ
 23. የንግድ እና አገልግሎት ሃላፊ
 24. የአቪዴሽን ጥገና ስልጠና ሃላፊ
 25. የጥገና ዘዴዎች እና ደረጃዎች ሃላፊ

 

ማስታወሻ፡-
ድርጅቱ ከላይ በዝርዝር ያልተካተቱትን አዲስ የማኔጄሪያል ሃላፊነት በከፊል መረጃው በህብረት ሚስጥር ይሆናል፡፡
ማጣቀሻ፡ 4 የኤምኤኤስ እና ጂፒኤ ወሰን
ድርጅቱ እስከ 2004 የሚያከናውነውና ከየተረጋገጠው አዲስ የጂፒኤ እና የኤምኤኤስ እና ግል መድህን ዕቅድ የሚከተሉት ናቸው፡-

ሃላፊነት

ኤምኤኤስ

ጂፒኤ (ለህክምና አገልግሎት)

ጂፒኤ (የጉዳት እና የሞት ካሳ)

የስር ሰራተኞች የተመደቡ የውጪ ሰራተኛን ሳይጨምር

45,000 ብር

45, 000 ብር

ቢያንስ የኢትዮጵያ ብር 12.0 ወይም ሰራተኛ ከየ5 ዓመት ደመወዝ ወይም 500.000

የተሰራው የውጪ ሰራተኛ

75,000 ብር

45, 000 ብር

ቢያንስ 120,000 ወይም የሰራተኛ የ5 ዓመት ወይም 500,000

የክርው አባላት

100,000 ብር

(በውጭ መድህን የሽፋን ዕቅድ መሰረት በዚህ አልተዘረዘረም) 

(በውጭ መድህን የሽፋን ዕቅድ መሰረት በዚህ አልተዘረዘረም) 

ሰልጣን ኢትዮያንስ የውጭ ዜጎች

7,500 ብር
10,000 ብር

7,500 ብር
10,000 ብር

(በውጭ መድህን የሽፋን ዕቅድ መሰረት በዚህ አልተዘረዘረም) 

በውጪ ሀገር እንደታኪው በህክምና ቦርድ ለተረጋገጠለት ሰራተኛ፣ ድርጅቱ እስከ 10,000 የአሜሪካን ዶላር ወጪ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
ማስታወሻ፡

 1. በዚህ መሰረት ድርጅቱ የራሳቸውን የህክምና ወጪ ለሚሸፍኑት ሰራተኞች እስከ 10,000 የአሜሪካ ዶላር የሚሸፍን ይሆናል
 2. ሀ. ድርጅቱ የብድር የተመቻቸ ባለው ሀገራት ውስጥ ድርጅቱ በራሳቸው ከላይ ከየተጠቀሰውን ወጪ መሸፈን ለማይችሉት ሰራተኞች ወጪ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

ለ ድርጅቱ የብድር አገልግሎት በሌሉበት ሀገራት በተቻለው መጠን ሠራተኛው ራሱ በመረጠበት የሕክምና ተቋሚ እንዲታከም ሁኔታዎችን ያመቻቻል

 1. ድርጅቱ በራሳቸው በመሄድ እና የህክምና እርዳት በራሳቸው ወጪ ማግኘት ለማይችሉት ሠራተኞች እንዲታኩሙ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ

ማጣቀሻ 5 የሠራተኛ የቅሬታ መሙያ ቅጽ
የኢትያጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች የቅሬታ መሙያ ቅጽ
የመጀመሪያ ደረጃ ቅሬታ
ይህ ቅሬታ ቅሬታን የሚያስከተለው ጉዳይ ተከስቶ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ለአለቃ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
የሠራተኛ ስም፡
የመታወቂያ ቁጥር                                                                          
የወጪ ማእከል፡
ኃላፊነት ወይም መጠሪያ፡
ይህንን ቅሬታዬን ለቅርብ አለቃዬ ለአቶ/ወ/ሮ ------------------- አቀርባለሁ
(የቅርብ አለቃው ስም) እንደሚከተለውና የቅርብ አለቃዬ በጠቅላላ ስምምነት ቅሬታ መመሪያ መሰረት ምላሹን መስጠት ይኖርበታል፡፡

የሠራተኛ  የቅሬታው ዝርዝር፡
(እባክዎትን ቅሬታውን ምክንያት ወይም መንስሄ፣ ቀኑን፣ የተጣሰውን የጠቅላላ ስምምነቱን አንቀጽ/ፖሊሲ እንዲሁም ምን መስተካከል እንዳለበት ወይም መወሰድ ያለበትን እርምጃ ይግለጹ)
ቀን
ፊርማ
ሠራተኛ
በሁለት ግልባጭ ያዘጋጁና ሁለቱንም ግልባጭ ለአለቃዎት ይስጡ
የቅርብ አለቃዎት ይህንን የተረከበበት ቀን
የቅርብ አለቃዎት ምላሽ
የቅርብ አለቃዎች ፊርማ
የምላሹ ቀን

ማስታወሻ

 1. ቅሬታው በቅርብ አለቃው በሠራተኛው ላይ ሌላ የስነ-ምግባር እርምጃ ካስከተለበት፣ ሠራተኛው ቅሬታውን ለቀጣይ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ላለ አለቃ ቅሬታውን ያቀርባል
 2. ይህንን ቅሬታ የተረከበ አለቃ በተረከበበት በ5 ተከታታይ ሥራ ቀናት ውስጥ ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል
 3. ማንኛው አለቃ ጉዳዩን ከሠራተኛው እና ከሚመለከተው ሁሉ ጋር በመወያየት የቅሬታውን ምላሽ ከመስጠት በፊት ጉዳዩን አግባብነት ካላቸው ማስረጃዎት ጋር የሚመረምር ይሆናል
 4. ይህ የቅሬታ ምላሽ በ5 ግልባጭ ተዘጋጅቶ ዋናው ለሰራተኛው፣ አንደኛው ግልባጭ ለአለቃዎት፣ ሁለተኛው ግልባጭ ለማህበራዊ ጉዳይ ግንኙነት መምሪያ፣ ሶስተኛው ግልባጭ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ማህበር እና አራተኛው ግልባጭ ከማህደርዎት ጋር ይያያዛል

የሁለተኛ ደረጃ ቅሬታ
ከመጀመሪያው ደረጃ ቅሬታ በኋላ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀጣይ ላለው አለቃ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
የሠራተኛ ስም፡
የምዝገባ ቁጥር
የወጪ ማእከል፡
የሠራተኛው ኃላፊነት ፡
ለመጀመሪያ ደረጃ የሠራተኛ ቅሬታ ምላሹን የተረከበበት ቀን
ለ፡
(የቀጣይ ከፍተኛ አለቃ ስም)
በመጀመሪያው ደረጃ ቅሬታዬን ምላሽ ቅር በመሰኘት ይህንን ቅሬታዬን ለቀጣይ ደረጃ ይህው አድርጌአለሁ
ቀን
የሠራተኛው ስም
ሠራተኛው የዚህን ሁለት ግልባጭ የመጀመሪያውን ደረጃ ምላሽ እንዳገኘ ለቀጣይ ከፍተኛ አለቀቃ ያቀርባል
የዚህ ቅሬታ ምላሽን በቀጣይ ደረጃ/ከፍተኛ አለቃ የተወሰደበት ቀን
/ፒቲኦ
የቀጣይ/ከፍተኛ አለቃ ፊርማ
የምላሽ ቀን

ማስታወሻ

 1. ቀጣይ ከፍተኛ አለቃ ማለት የሠራተኛው ቅሬታ ገቢ ከሆነበት የቅርብ አለቃ በኃላፊነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለው ነው
 2. ውሳኔው ከቅሬታው በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚሰጥ ይሆናል
 3. ስለ ጉዳዩ ለመወያየት እና አግባብነት ያለውን ማስረጃ ለመመርመር አለቃው ሠራተኛውና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰዎች በመጥራት ይወያያል
 4. ቀጣይ አለቃውም ውሳኔውን በዚህ መሰረት ያከፋፍላል፡ ዋናው ለሰራተኛው፣ አንደኛው ግልባጭ ለአለቃዎት፣ ሁለተኛው ግልባጭ ለማህበራዊ ጉዳይ ግንኙነት መምሪያ፣ ሶስተኛው ግልባጭ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ማህበር እና አራተኛው ግልባጭ ከማህደርዎት ጋር ይያያዛል

ሶስተኛ ደረጃ ቅሬታ
ከሁለተኛ ደረጃ ቅሬታምላሽ በኋላ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታው ለማህበራዊ ግንኙነት መምሪያ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
የሠራተኛ ስም፡
የምዝገባ ቁጥር
የወጪ ማእከል፡
የሠራተኛው ኃላፊነት ፡
ለሁለተኛ ደረጃ የሠራተኛ ቅሬታ ምላሹን የተረከበበት ቀን
ለ፡ ማህበራዊ ጉዳይ ግንኙነት መምሪያ
ለሁለተኛ ደረጃ ቅሬታ የተሰጠውን ምላሽ አጥጋቢ እንዳልሆነ እናምንበታለን
የሕብረት ሰብሳቢ ፊርማ
ቀን
(የሠራተኛ ማህበር ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ቅሬታዎች ከዚህ ቅሬታ ቅጽ ላይ የውሳኔውን ግልባጭ የሚልክ ይሆናል)
በሠራተኛው ማህበር ቅጹ የተረከበበት ቀን
የሂሳብ ማስታረቅ ውጤት
/ፒቲኦ
ጉዳዩ የሚመለከተው የቪፒ/ኤስቪፒ ፊርማ
ቀን

 1. ጉዳዩ የሚመለከተው የቪፒ/ኤስቪፒ የሶስተኛው ቅሬታ ተረክቦ በ20 ቀናት ውስጥ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል
 2. ስለ ጉዳዩ ለመወያየት እና አግባብነት ያለውን ማስረጃ ለመመርመር አለቃው ሠራተኛውና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰዎች በመጥራት ይወያያል
ውሳኔው በሶስት ግልባጭ ተዘጋጅቶ አንደኛ ግልባጭ ለሰራተኛው፣ ሁለተኛው ግልባጭጉዳዩ የሚመለከተው የቪፒ/ኤስቪፒ፣ እና ሶስተኛው ግላባጭ ለማህበራዊ ጉዳይ ግንኙነት መምሪያ፣

የሌሎች የሲቢኤ ምላሽ
ለተከናወነ ሥራ ተመጣጣኝነት ክፍያ
አሰሪውና ህብረቱ ይህንን ስምምነት በሚፈጽምበት ጊዜ እንደተስማሙት ያለ ወገንተኝነት፣ ጾታዊ፣ ሀይማኖትና ቀለም አድሎ ውጭ ለተከናወነ ሥራ ተመጣጣኝነት ክፍያ የሚል መመሪያ አለው፡፡
ጾታና እኩልነት ሰቶችና ወንዶች በቀጣይነት ልማት ያላቸውን አስታዋጽኦ አስፈላጊነትን በመቀበልና ሴቶች በብዛት በሃይማኖትና በልምድና የተገለሉ መሆናቸውን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ድርጅቱና ህብረቱ የጾታና እኩልነት ፖሊሲ ለማረጋገጥ ሚዛናዊ የሆነ ድርሻ የሚያሰፍንና የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
ሁለቱም ማለትም ህብረቱና ድርጅቱ የጾታና እኩልነት የጋራ ዮሽ ንኡስ ኮሚቴ ከሁለቱም የተውጣጡ የተውጣጡና ስለ ጾታና እኩልነት ጥናት በማድረግ ለጂኤንሲ የሚስታውቁ/የሚያመለክቱ ሁለት ተወካዮችን ይሾማሉ/ያዋቅራሉ፡፡

የኤች አይቪ/ኤድስ ፖሊሲ
ባአጠቃላይ በዓለም በሰው ልጆች እና በዑጋንዳ በሰው ልጆች ላይ ኤች አይቪ/ኤድስ ያደረሰው አውንታዊ ጥቃትን በመገንዘብ ሁለቱም ማለትም ድርጅቱና ህብረቱ ይህም አስከፊነቱና ጥቃቱን ለመከላከልና የሠራተኛ መመሪያ ለመውጣት ኤች አይቪ ኤድስ ፖሊሲ የሚተገበርበትን ሥፍራ ለማዋቀር ተስማምተዋል፡፡
ሠራተኛው በኤች አይቪ ተጠቂ የሆኑትን ቤተሰቦችን ለመርዳት ለመረዳት ኤች አይቪ/ኤድስን ለመከላከል መዋጮ ያደርጋል፡፡

ያላግባብ የሆኑ ተግባራት
የሚከተሉትን ያላግባብ የሆኑትን ተግባራትን መፈጸም
ሀ. የሠራተኞችን መብት ወይም መብታቸውን የሚጋፋ ተግባር በማንኛውም መልኩ ማገድ፡፡
ለ. ከዚህ ጠቅላላ ስምምነት ወይንም አዋጅ ድንጋጌዎች የሚጻረር ድርጊት መፈጸም
ሐ. በሰራተኛው ህይወት ላይ  ጉዳት በሚያስከትል መልኩ ሃላፊነቱን እንዲወጣ የማድረግ ሁኔታ
መ. በብሔር፣ ጾታ፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ የፖለቲካ  ድርጅት እና ሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶች ከሰራተኞች መካከል ማዳላት

22. ጾታ እና እኩልነት
ሀ. ሁለቱም ማለትም ህብረቱና ድርጅቱ የጾታና እኩልነት ንኡስ ኮሚቴ ከሁለቱም የተውጣጡና በሁለቱም ወገኖች ስለ ጾታና እኩልነት ጥናት በማድረግ ለጂኤንሲ የሚስታውቁ/የሚያመለክቱ ሁለት ተወካዮችን ይሾማሉ/ያዋቅራሉ፡፡
ለ. ይህንኑ ለማከናወን ሁለቱም ወገኖች 5 ሰዎች ያቀፈ የጋርዮች ኮሚቴ እያንዳንዱ ሁለት እኩል ድርሻ ያላቸውን ተወካዮችን እና በሁለቱም ወገኖች የተስማሙበት አንድ ሰብሳቢ ይኖራቸዋል፡፡
. የኮሚቴው ተግባር

 1. የጾታ እና የእኩልነት የፖሊሲ ስራ ቦታ ወይንም በጄኤንሲ የተረጋገጠ ያዋቅራል፡፡ 
 2. የፖሊሲውን ወይንም ማንኛውም የጾታ እና የእኩልነት ደረጃ ትግበራን ይቆጣጠራል፡፡ 
 3. አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ማሻሻያ ያፈልቃል፡፡
 4. ያለ ጾታዊ፣ ዘር፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ የፖለቲካ ድርጅት አድሎ ሌሎች የጾታ እና የሰዎች በአንድ አይን የመስተናገድ የማስፈጸም ተግባር ያከናውናል፡፡

ከፍተኛ የህመምተኛ ክፍያ 100 100 ለሰራተኛው እና ለቤተሰቢ 50 በመቶ
የአካል ጉዳተኝነት መዋጮ በጀት
ማንኛውም ከስራ የተነሳ የሚያጋጥም ጉዳት በመድህን በተመቻቸ በኩባንያው የሰራተኛ እና አሰሪ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1997  አንቀጽ 109(1) መሰረት ክፍያው የሚፈጸም ይሆናል፡፡ የጉዳቱ ደረጃ በህክምና ቦርድ ታይቶ ለኩባንያው ከቀረበ ክፍያው በሰራተኛ እና አሰሪ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/2003  አንቀጽ 102(2) መሰረት ተፈጸሚ ይሆናል፡፡ ሰራተኛው ጉደዩን ለመከታተል፣ የህክምና ቦርድ ውሳኔን ለማግኘት እና ውሳኔውን ለኩባንያው ለማቅረብ የመከታተል ግዴታ አለበት፡፡ በተጨማሪም የተጎዳው ሰራተኛ ስለ ጉዳቱ ለቅርብ ሃላፊው የሚያቀርብ ሆኖ፣ ለዚህ አላማ የተዘጋጀውን ቅጽ መሙላት፣ የሃላፊውን ፊርማ ማግኘት እና ቅጹን ለድርጅቱ ጤና አገልግሎት ገቢ ማድረግ፡፡  የቅርብ  አለቃ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ፈረቃ የሌለ እንደሆነ እና የስራው ጎጂነት ከተከሰተ ተጎጂ ሰራተኛ በአስቸኳይ ቅጹን ሞልቶ በመፈረም ለጤና አገልግሎት ገቢ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን የቅርብ አለቃው  የአደጋውን ክስተት በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ እስከ 3፡00 ሰአት ማረጋገጥ አለበት፡፡ ድርጅቱ የመድህን አረቦን ሰነድ ግልባጭ ለንግድ ማህበር የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
አፓረንት ሺፕ
አሰሪው ሰራተኛው ሃላፊነቱን ለመወጣት አፈጻጸሙን እንዲያሻሽል እና በድርጅቱ ውስጥ እድገት እንዲያገኝ አስፈላጊውን የስራ ስልጠና፣ የአፓረንት ሺፕ ስልጠናን ጨምሮ በድርጅቱ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

የወሊድ ጊዜ የእረፍት ክፍያ 
የወሊድ ጊዜ የእረፍት ክፍያ፡- ከክፍያ ጋር የ6 ወራት የወሊድ የእረፍት ጊዜ ይሰጣል፡፡
እርግዝና እና ጡት ማጥባት
የጨቅላ ህጻን ተንከባበካቢ እናት  (ከአንድ አመት በታች የሆነች የህጻን እናት) መደበኛውን የሪፖርት ጊዜ ከመጀመሯ ወይንም በስራ ሰአቷ ጊዜ ህጻኑን ለመንከባከብ የአንድ ሰአት ጊዜ ያክል ሊኖራት ይገባል፡፡ ከአንድ ሰአት በላይ የሆነ ጊዜ አሰሪው ከህብረቱ ጋር ባለው ስምምነት መሰረት  የሚራዘም ይሆናል፡፡
ህጻን የምትንከባክብ እናት ህጻኑን ከመንከባከብ ጋር ተያይዞ ለሚከሰተው የስራ መዛባት ይህ ጊዜም  እንደ ስራ ሰአት ይወሰድ እና ተከፋይ ይሆናል፡፡
በራሷ ስምምነት ካልሆነ ነፍሰጡር ሴት ወይንም የጨቅላ ህጻን ተንከባበካቢ እናት  (ከአንድ አመት በታች የሆነች የህጻን እናት) የትርፍ ሰአት ስራ እንድትሰራ አትገደድም፡፡
ለነፍሰጡር ሴት የስራ ደህንነት  
አሰሪው በእርግዝና የእረፍት ቀሪ ምክንያት  ከስራዋ አያሰናብታትም

የምሽት ስራ ክፍያ፡-
በአንቀጽ 23.42 የትርፍ ሰአት ጊዜ ክፍያ የሚከፈለው ደሞዝን በ--------እና ለምሽት ስራ በ---በተመሳሳይ መልኩ ለበአል ቀናት በ---------በማባዛት ይሆናል፡፡
ወይንም ጥሩ የሚሆን አጋጣሚን አማራጭ (150% መደበኛ ደሞዝ)?

የትርፍ ሰአት ካሳ ክፍያ
ስለምግብ

 

 

 

“ናሙና የህብረት ድርድር እና ስምምነት ለኢትዮጵያ” በዌቭ ኢንዲኬተር ፋውንዴሽን - 2016 -

Start date: → Not specified
End date: → Not specified
Public/private sector: → 
Concluded by:
 
Loading...