ስራና ህመም

This page was last updated on: 2023-05-06

የህመም ፈቃድ ከክፍያ ጋር

የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ህመም መኖሩ ብቃት ባለው ዶክተር ከተረጋገጠ የሙከራ ጊዜውን ላጠናቀቀ ሰራተኛ እስከ 6ወር ድረስ የህመም ፍቃድ ከክፍያ ጋር እንደሚሰጥ ይደነግጋል፡፡ አንድ ሰራተኛ በስራ ላይ ከሚደርስ ጉዳት ሌላ በሆነ ህመም መስራት የማይችል/የማትችል ከሆነ የህመም ፍቃድ የማግኘት መብት አለው/አላት፡፡ አንድ ሰራተኛ በህመም ምክንያት ከስራ መቅረቱን ለአሰሪ መግለጽ እና በመንግስት እውቅና ካገኘ የህክምና ድርጅት የህክምና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

አሰሪው የህመም ፍቃድ እንደሚከተለው ሊሰጥ ይችላል፡-

. በህመም ፍቃድ የመጀመሪያው ወር 100% ክፍያ 

. በሁለተኛ እና በሶስተኛ ወር የህመም ፍቃድ 50%

. ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ወር ድረስ የህመም ፍቃድ ያለክፍያ

ምንጭ፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 85-86;  ምንጭ ISSA የሀገር ፕሮፋይል 2019

የህክምና እንክብካቤ

በ2010 ዓ.ም የፀደቀው የማህበራዊ ጤና መድህን አዋጅ ለሰራተኞች ስለሚቀርቡ የህክምና እና የጤና አገልግሎቶች ይደነግጋል፡፡ ሁሉም ሰራተኞች የማህበራዊ ጤና መድህን መርሀ ግብር አባል መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አንድ ሰራተኛ በሥራ ላይ ጉዳት ሲደርስበት የጠቅላላና የልዩ ሕክምና እንዲሁም የቀዶ ሕክምና ወጪዎችን፤ የሆስፒታልና የመድሃኒት ወጪዎችን እና የማንኛውም አስፈላጊ ሰው ሰራሽ ምትክ ወይም ተጨማሪ አካሎችና የአጥንት ጥገና ወጪዎችን አሠሪው ይከፍላል፡፡

ምንጭ፡- የISSA 2019 የሀገራት መግለጫ ፤ የተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀፅ 105

የስራ ደህንነት

የታመመ አንድ ሰራተኛ የስራ ውሉ በህመም ፍቃዱ ወቅት የተጠበቀ ይሆናል፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 85-86

ስራና ህመምን የተመለከቱ ደንቦች

  • የአሰሪና ሰራተኛ ዓዋጅ ቁ. 377/2003 / Labour Proclamation No.377/2003
loading...
Loading...