ማህበራዊ ዋስትና

This page was last updated on: 2023-05-06

የጡረታ መብቶች

ህጉ ሙሉ እና ከፊል ጡረታን ይደነግጋል፡፡ ለሙሉ ጡረታ ሰራተኛው 60 ዓመት የሞላው /ለሴቶችም ተመሳሳይ ነው/ እና የ120 ወራት / 10 ዓመታት/ አልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡ አስቀድሞ ጡረታ መውጣትም የሚቻል ሲሆን ለዚህም ሰራተኛው 55 ዓመት የሞላውና ቢያንስ የ300 ወራት /25 ዓመታት/ (አገልግሎት ያለው እና ከ45-55 አመት እድሜ በማእረጋቸው መሰረት) በውትድርና ቢያንስ 10አመት አገልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡

የዕርጅና ጡረታ መጠን ሰራተኛው ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ያገኘው የነበረው አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ 30% ሆኖ በዚህ ላይም ዋስትና ያለው ሰራተኛ ከ10 ዓመት በላይ ለፈፀመው ለእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ 1.25% (ወታደር ያልሆነ) ወይም 1.65% (ወታደር) በመደመር ይታሰባል፡፡ አነስተኛው ወርሃዊ የጡረታ አበል መጠን ብር 744 ሲሆን ከፍተኛው ወርሃዊ የጡረታ አበል መጠን መድን የገባ ሰራተኛ ወርሃዊ መነሻ ደመወዝ 70% ነው፡፡ የመጀመሪያ ጡረታ አበል እንደ እርጅና ጡረታ አበል በተመሳሳይ ሊሰለፍ አንድ ሰራተኛ በ60 አመት እድሜው ለእርጅና ጡረታ ብቁ የሚያደርጉትን ሁኔታዎች የማያሟላ ከሆነ የሰራተኛው መነሻ ወርሃዊ ደመወዝ ጡረታ ከመውጣቱ አንድ ወር በፊት የነበረው ደመወዙ በአገልግሎት ዘመኑ እና መዋጮው ይከፈለዋል፡፡

ምንጭ፡ የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2011 አንቀጽ 18-21; ምንጭ ISSA የሀገር ፕሮፋይል 2019

የጥገኞች ተተኪዎች ጥቅም

ከላይ የተጠቀሱት ህጐች በህይወት ላሉ ጥገኞች ባል/ሚስት ህፃናት እና ወላጆች በህይወት ያለ የትዳር ጓደኛ ወይም  18 አመት በታች የሆኑ ህጻናት (አካል ጉዳተኛ ከሆነ 21 አመት) እና ወላጆች (በህይወት ያለ የትዳር ጓደኛ ከሌለ) ጥቅሞችን እንደሚያገኙ ይደነግጋሉ፡፡

ይህም የሟቹ ጡረታ 50% ሲሆን ይህም ለባል/ሚስት ይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 20% ለእያንዳንዱ ወላጅ የሞተበት ህፃን ይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 30% ለእያንዳንዱ ሁለቱም ወላጅ ለሞተበት ህፃን ይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 15% ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወላጅ ይከፈላል፡፡ አግባብነት ያላቸው በህይወት ያሉ ሰዎች ከሌሉ ጥቅሙ የሟቹ ጡረታ 20% ይሆናል፡፡ ሟች ከ10ዓመት በታች የሆነ አገልግሎት እና መዋጮ ካለው እና ለጡረታ ብቁ ካልሆነ በህይወት ላለ የትዳር ጓደኛ የሚከፈል ክፍያ ብቃት ላላቸው በህይወት ያሉ የትዳር ጓደኞች ለሌላው በህይወት ያለ የትዳር ጓደኛ ጥቅም በተመሳሳይ ምጣኔ ይሰላል፡፡

ምንጭ፡  የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2011 አንቀጽ 39-44; ምንጭ ISSA የሀገር ፕሮፋይል 2019

የመስራት አለመቻል / ጥቅሞች

ከላይ የተጠቀሱት ህጐች በዘለቄታነት መስራት የማያስችሉ ከስራ ጋር ግንኙነት የሌላቸው አደጋዎች /ጉዳዮች/ በሽታዎችን የተመለከቱ ድንጋጌዎች አሏቸው፡፡ ሰራተኛው መደበኛ ጥቅም የሚያስገኝ ስራ መስራት የማያስችል የተገመገመ ችግር ያጋጠመውና የ10 ዓመት አገልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡ መስራት ያለመቻል ጥቅሞችም  የሚሰራው ከእርጅና ጡረታ ጋር በተመሣሣይ ነው፡፡ መስራት ያለመቻል ጡረታ ሰራተኛው ከጉዳቱ በፊት ባሉት ሶስት አመታት የነበረው ወርሃዊ ገቢ 30% በዚህ ላይም ዋስትና ያለው ሰራተኛ ከ10 ዓመታት በላይ ላበረከተው አገልግሎት የአማካይ ወርሃዊ ገቢ 1.25% (ወታደር ላልሆነ) እና 1.65%(ወታደር) በመደመር ይሆናል፡፡

መድን የገባ ሰራተኛ ከፍተኛ ወርሃዊ የጡረታ አበል የወረሃዊ መነሻ ደመወዙ አማካይ ይሆናል፡፡

የአካል ጉዳተኝነት ከመቆሙ በፊት በነበረው ወር ውስጥ 1.25 (ሲቪል) ወይም 1.65 (ወታደራዊና ፖሊስ) በሚባሉት ወርሃዊ ደመወዝ በአንድ ጊዜ አጠቃላይ የሆነ የደመወዝ ክፍያ መጠን ከ 10 አመታት ድጐማ ይከፈለዋል. ይከፈላል.

ምንጭ፡  የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2011 አንቀጽ 22-26; ምንጭ ISSA የሀገር ፕሮፋይል 2019

ማህበራዊ የተመለከቱ ደንቦች

  • የማህበራዊ ጤና ዋስትና አዋጅ ቁጥ 690/2010 / Social Health Insurance Proclamation No.690/2010
loading...
Loading...